💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Forwarded from đŸ’ŽŘŁŮŘŽŮ’تِي عَيْشِي مَعَ الكِتٰابْ وَالسُّنَّة💎
📌እህቴ አትዘኚ ፦ በእርግጥም ጌታሽ አሏህ ሀጢአትን ይምራል ፤ ተውበትንም ይቀበላል ። ቀጣዩን የቁርአን አንቀጽ ስታነቢ ልብሽ ሰላም አያገኝም? ጭንቀትሽ አይወገድም ? ደስታስ በመላው አካላትሽ አይሰራጭም?


۞ قُلْ يَا عِبَادِيَ الَّذِينَ أَسْرَفُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ لَا تَقْنَطُوا مِن رَّحْمَةِ اللَّهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ جَمِيعًا ۚ إِنَّهُ هُوَ الْغَفُورُ الرَّحِيمُ

በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ! ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና፡፡

ታዳ ለምን ታዝኛለሽ ሀዘን ሲበዛ ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ተስፋ ከቆረጥሽ ደግሞ ጌታሽን በአግባቡ መገዛት አትችይም ስለዚህ ብዙን አትዘኝ ጌታችን አሏህ ተስፋ ቆራጮችን አይወኸድም ።

https://t.me/beytbenatasselfyat
013 ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ
በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ጁወይሪያ)
♦️አዲስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

▪️كتاب منهاج الفرقة الناجية والطائفة المنصورة

➲ፊርቀቱ አናጂያህ ወጧኢፈቱል መንሱራህ

▪️ክፍል አስራ ሶስት
〰〰〰〰〰

♦️የኪታቧን PDF ለማገኘት
➴➴➘➘➷➷➴➴➘➘➷
https://t.me/https_Asselefya1/3725

🎙በኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ጁወይሪያ)
https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/https_Asselefya1
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
የመተጋገዝ ጥሪ
*****
ወንድሞችና እህቶች ሆይ! አንድ በአካል የማውቀው ወንድም የሰው መኪና ተበድሮ፣ መኪና ውስጥ ለሰው አድርስ የተባለው 40000.00 (አርባ ሺህ ብር) ውስጥ እያለ፣ በትላንትናው እለት ኢሻ ሶላት ሰግዶ ሲወጣ መኪናው ከነ ውስጡ ካለው ብር ጭምር ተሰርቋል።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በዚሁ የመኪና ዝርፍያ ከተማችን ላይ ስላለ መኪናችንን እናስጠብቅ።
ወንድምና እህቶች ሆይ! ቢያንስ የእለቱን ለሰው መስጠት የሚጠበቅበትን አርባ ሺህ ብር ተደጋግፈን የቻልነውን ወደሚከተለው የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት እንተባበረው።
መኪናዋም እንድትገኝ ዱአ እናድርግለት።
እኔ በአላህ ፈቃድ 2000 ብር አስገባለሁ።
ወንድምና እህቶች ሆይ! ዝርፊያው የደረሰበትንም ወንድም ሆነ ገንዘብ አስገቡበት ያልኳችሁን አካውንት ባለቤት ጠንቅቄ በአካል አውቃቸዋለሁ። እዚህ የፖሰትኩላችሁ የጉዳዩን እውነተኝነት ስላረጋገጥኩ ነው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000406637313
Audio
أيهما أفضل، صيام الإثنين والخميس، أم صيام الثلاثة الأيام؟

➧https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
♦️የመልካም ሚስት ስብዕና ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➲ለባሏ ደስታን የምትፈጥር ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ ➧በጣም የሚደንቀውና ትንግርት የሚፈጥረው ደግሞ ሁልጊዜም ከቤት መውጣትን ስትፈልግ ራሷን አስውባና ዘንጣ ነው መሄድ የምትፈልገው ለባሏ ግን እንኳን እንድህ ልትዋብ ይቅርና ስትወጣ የምትኳኳለውን አንድ አስረኛውን የሚያክል እንኳን አትዘገጃጅም። እስኪ ቆም እንበልና ጥያቄ እንጠይቅ ታዲያ በዚህ ሁኔታ እየቀረበችው…
➲የመልካም ሚስት ስብዕና
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

➧ለባሏ ደስታን የምትፈጥር
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲ከምዕመናን እናት አኢሻ ረድየላህ አንሃ እንደተወራው እንድህ ብላለች:-

▪️قدرَسُوْل صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم من سفرٍ وقد سترت بقرامٍ على سهوة فيها تماثيل فلما رآه رسول الله هتكه• وقال:

የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከጉዞ ተመለሱ ስዕል ባለበት ጨርቅ የቤቴን መስኮት ሸፍኜው ነበረ የአላህ መልዕክተኛ ሲያዩት ቦጭቀው (ገንጥለው) ጣሉትና እንድህ አሉ:-

▪️أشهد الناس عذابا يوم القيامة الذين يضاهون بخلق الله.

የቂያማ ዕለት ቅጣታቸው እጅግ በጣም የሚበረታው ከአላህ ፍጥረት ጋር የሚፎካከሩ ናቸው።


قالت: فجعلناه وسادة أو وسادتين
እናታችንም እንድህ አለች ወደ አንድ ወይም ሁለት ትራስነት ለወጥነው።

➲እናታችን ይህን መጋረጃ ለምንድን ነው የሰቀለችው? ምክንያቱ ምንድን ነው ስንል እናታችን አኢሻ ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወደ ቤት ሲገቡ ቤቱ ውስጥ መልካምና ውብ የሆነ ነገር እንድያገኙ ወይም ደግሞ በቤቱና በእርሷ ላይም ቆንጆ ነገር እንድመለከቱ ፈልጋ እንደሆነ እንረዳለን።

➭ከዚህ ሀድስ የምንቀስመው ትልቅ ቁም ነገር አለ እርሱም አንድት ሚስት ልክ ራሷን ሙሉ በሙሉ ማስዋብና ማቆነጃጀት እንደሚገባት ሁሉ ቤቷን ማስተካከልና ማስዋብ ባማረ መልኩ ማዘጋጀት ይገባታል። ለባሏ የምታደርገውም አቀባበል ልዩና ያሸበረቀ መሆን ይገባዋል። ይህ ሁሉ እንግድህ ከመልዕክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና የተገኘ የመልካም ሴትና ሚስት መገለጫ ባህሪ ነው።

➲ሌላው ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚጠቀሰው ኢማሙ ጠበራኒ "አልሙዕጀሚል አውሰጥ" በተሰኘው ድርሳናቸው ላይ ያሰፈሩትና ከአነስ ኢብኑ ማሊክ የተዘገበው ሐድስ ነው በዚህ ሀድስ ላይ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል

▪️ألا أُخْبِرُكُم بِنِسائكم في الجنة


"የጀነት ስለሆኑ ሴቶኛችሁ (ሚስቶቻችሁ) ልንገራችሁን? ማለትም ምስጉን በሆኑ መገለጫዎቿ እና የተከበረ በሆነ ባህሪዋ ምክንያት ከጀነት ሰዎች መካከል ለመሆን ብቁ ስለሆነችው ሚስት ማለት ነው። ከዚያም እንድህ አሉ:-

▪️كل ودودٍ وَلودٍ إذا غضبت أو أُسيء إليها أو غضب زوجها قالت هذه يدي في يدك لا أكتحل بغمض حتى ترضى

➲"አፍቃሪና ወላድ የሆነች ሁሉ ከተቆጣች ወይም በእርሷ ላይ ባሏ ከተቆጣባት እንድህ ትላለች ይህ እጀ ነው በአንተ እጅ ስር ነው ያለው አንተ እስክትወልድ ድረስ አልቀሳቀስም (አልሄድም) አይኔንም አልጨፍንም (አልተኛም)።

➧አይኔንም አልጨፍንም" ማለት ይቅር
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻
ብለህኝ በእኔ ደስተኛ እስከምትሆን ይህንንም በአይኔ አይቸ እስከማረጋግጥ ድረስ ለእንቅልፍም እራሴን አላዘጋጅም አልተኛም ለማለት ነው።
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

➧የመልካም ሚስት ስብዕና ከሚለው ከአብዱረዛቅ ቢን ዐብዱልሙሕሲን አልበድር ኪታብ የተወሰደች!

🖊ام فاروق
ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
✍️አራት ማግባት ይቻላል በሚል ሰበብ ወንጀል አይሰራ!!


☞ሱና ነው በማለት ሰበብ 4 አገባለሁ ብሎ የሚስቶችን ሀቅ ማጓደል በመብዛቱ የተነሳ የተወሰነ ለዚህ ሰው ምክር ትሆን ዘንድ ልቦጫጭር አሰብኩ!

▪በአሁን ሰዐት ላይ ወንዱ ሱናን ሰራሁ በማለት ሱናን ሲጥስ ከተመለከትንበት ጉዳይ መሀል አንደኛው አራት የማግባት ጉዳይ ነው!

▪አንደኛዋን ሚስቱን በወጉ ማስተዳደር ያቃተው በውሎ ገንዘብ የሚተዳደር ለቤት ወጪ እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ የሌለው ባል የአስቤዛ አምጣ ሲባል ከጣት እስከ ራሱ የሚርገፈገፍ ወንድ ሁለተኛ ሚስት አገባለሁ ብሎ ሚስቶቹን በረሀብ እና በስቃይ ቢቀጣ ይህ ባል እንኳን ሱናውን ሊያገኝ ቀርቶ በሰራው ተግባር ተጠያቂ የሚሆንበት አጋጣሚ እንዳይመጣበት ያስፈርለታል!

✍️ልበ_በሉ:

▪አራት ማግባት ሱና አደለም እየተባለ አደለም አራት ማግባት ሱና እንደሆነ ፈጣሪያችን አላህ ሱብሀነሁ ወታአላ ነው በቁርአኑ ያስቀመጠው!

قال تعالىٰ:" •"وَإِنْ خِفْتُمْ أَلا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَى فَانْكِحُوا مَا طَابَ لَكُمْ مِنَ النِّسَاءِ مَثْنَى وَثُلاثَ وَرُبَاعَ..... الأية"النساء(3)
✍️አላህ እንዲህ አለ:
" በየቲሞችም -ማግባት- ፍትሀዊ መሆናችሁን ብትፈሩ ከሴቶች ለናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት ሶስት ሶስት አራት አራትም አግቡ☜"


↪️አራት ለማግባት መስፈርቱ!!

① በመሀከላቸው ፍትህን ሳያጎል የሚገባቸውን ነገር በፍትህ ሰጣለሁ የሚል እምነትን መያዝ አለበት!

لقوله تعالى:" •فَإِنْ خِفْتُمْ أَلا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً )

▪አላህ እንዲህ ስላለ: " ፍትሃዊ አለመሆንን ከፈራችሁ በአንድ ተብቃቁ"

② አካላዊና ገንዘባዊ ችሎታን የቻለ መሆን አለበት!

➲ገንዘባዊ_ማለት:ለአራቱም ሚስቶቹ በእኩል አይን የሚገባቸውን ቀለብም ሆን እቃ የመስጠት አቅሙን መያዝ!
➲አካላዊ_ማለት: አካሉ የጠነከረና በጋብቻ ውስጥ ላሉ የአካል ጥንካሬን ለሚጠይቁ ጉዳዮች በሙሉ ብቁ መሆን አለበት!


③ ከጋብቻ በፊት የተደረገ ስምምነት አለመኖር ነው!

▪ከጋብቻ በፊት ባል ከሚስቱ ጋር ከአንቺ ሌላ አልጨምርም ብሎ ቃል የገባው ቃልኪዳን ካለ የማግባት እድሉን ሸሪአው ይከለክለዋል! እሷ ከእንደገና ካልፈቀደችለት በስተቀር!


▪ይሄን መስፈርት ያሟላ ወንድ ካለና ሊያገባ ቢሞክር ሚስት የመከልከል መብቱን ሸሪአ ስላልሰጣት ከዚህ ሸሪአን ከሚጥስ ተግባሯ መቆጠብ አለባት!!!!

✍️ይሄን መስፈርት ያላሟላክ ወንድ ደግሞ አራት ማግባት ይቻላል ሸሪአው ፈቅዷል፣ ሱና ነው፣ ተወዳጅ ነው የሚሉትን አርማ በማውለብለብ የተሳሳተ መንገድና እንኳን ሸሪአን ሊከተል የሸሪአ ተቃራኒ የሆነ ተግባርን ከመስራት ተቆጠብ!


✍️ كتبه: أخوكم أبو ماهر الأثري.

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1