💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
↬ከምንም በላይ እጅግ በጣም ሙእሚኖች የሚናፍቁትና በጉጉት የሚጠብቁት ጥሪ፥

《يا أيتها النفس المطمئنة إرجعي إلى ربك راضية مرضية فادخلي في عبادي وادخلي جنتي》

↬(አንተ፥ በጌታዋ በሚገባ በማመኗ የተረጋጋች ነፍስ -መንፈስ- ባለቤት ሆይ፥ አላህ የሰጠህን ምንዳ በደስታ ተቀብለህ ከደጋግ ባሮቼ ጋር {ጀነት ግባ} የሚለው ጥሪ ነው፡፡

🤲ያረብ ይህን ጥሪ በቀጥታ ሰምተው ከሚደሰቱ ባሮችህ አድርገን
ለዚህ ትልቅ ማዕረግ የሚያበቃውን "ኢማን" ልናውቀውና ልንጠብቀው ይገባናል

✍ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ ኣደም (ሐፊዘሁላህ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
⇢አላህን ከልቡ የሚፈራ ወንድ ቢሆን እንጅ በዚህ ዘመን አያደርገውም ።

🍃አነስ ረድላሁ ዐንሁ እንድህ ሲል ያስተላልፋል፦

⇢" አንድት ሴት ባጠገብህ ካለፈች እስከምታልፍህ ድረስ አይንህን ስበር።"
( አል ወረእ ሊብኒ አቢዱንያ 72)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
በሀርቡ ሙሐደራ ላይ የተ ጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቻው
በሸይ ሀሰን አሊ
በኡስታዝ ኸድር አህመድና
በኡስታዝ ሳዳት ከማል
  â†ˇâ‡ŁđŸ”Šâ‡Łâ†ś

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➤▸የክስረት ሁሉ ክስረት ማለት:- የቂያማ እለት ራሱንም ቤተሰቡንም ያከሰረና ለጀሀነም እሳት የዳረገ ሰው ነው ።

➤▸ነገ የቂያማ እለት አንተንም ቤተሰብህንም ከክስረት ለማዳን የምትፈልግ ከሆነ ዛሬ ዱንያ ላይ ሳለህ ነፍስህንም ቤተሰብህንም ወደ መልካም ነገር ልትመራቸውና ከመጥፎ ነገሮች ልትታደጋቸው ይገባል ።

➤▸የመልካም ነገሮች ሁሉ ቁንጮ ተውሒድና ሱና ነውና ነፍስህን እንዲሁም ቤተሰብህን በተውሒድና በሱና አንፅ ።

➤▸የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋና የሚባሉት ደግሞ ሽርክና ቢድአ ናቸውና ነፍስህንም እንዲሁም ቤተሰብህን ከሽርክና ከቢድአ ልትታደግ ይገባል ።

አላህ የቂያማ እለት ከሚከስሩት አያድርገን አሚን ።
መንቁል...!!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📌♻️ ጊዜህን በቁም ነገር ላይ አውለው ♻️📌

✅ ሸህ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ።

🔺 ጊዜውን 👉አላህን በማውሳት (በዚክር)
👉ቁርአን በመቅራት
👉ከመልካም ሰዎች ጋር በመሆን
👉ከዝንጉና ከመጥፎ ጓደኞችን
በመራቅ ያሳለፈ ሰው
🔺 ቀልቡ ያማረና የለሰለሰ ይሆንለታል።

📚 مجموع فتاوى ابن باز (5/244)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ተውሒድ
#ክፍል ②

#ወሳኝና_ጠቃሚ_ነጥቦች፡-----
①–እነዚህ ሦስት የተውሂድ ክፍሎች ከፍተኛ ትስስርና ተዛምዶ ያላቸው በመሆኑ በአንዱ አምኖ በሌላው መካድ በሁሉም እንደመካድ
ይቆጠራል።
②–በአላህ መልዕእክተኛ ወቅት የነበሩት ከሃዲያን የሁሉ ነገር ፈጣሪ ፤ ሲሳይን ሰጪ ፤ ሕይወት የሚሰጠውና የሚነሳው አላህ ብቻ
መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁና ያምኑ ነበር። ይሁን እንጂ ከአላህ ውጭ የሆነን አካል ያመልኩ ስለነበር ይህ እምነታቸው ሙስሊሞች
አልቻለም።
#አላህ_እንዲህ_ይላል፡
ﻗُﻞْ ﻣَﻦ ﻳَﺮْﺯُﻗُﻜُﻢ ﻣِّﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﺃَﻣَّﻦ ﻳَﻤْﻠِﻚُ ﺍﻟﺴَّﻤْﻊَ ﻭَﺍﻟْﺄَﺑْﺼَﺎﺭَ ﻭَﻣَﻦﻳُﺨْﺮِﺝُ ﺍﻟْﺤَﻲَّ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤَﻴِّﺖِ ﻭَﻳُﺨْﺮِﺝُ ﺍﻟْﻤَﻴِّﺖَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺤَﻲِّ ﻭَﻣَﻦ ﻳُﺪَﺑِّﺮُ ﺍﻟْﺄَﻣْﺮَ ۚ
ﻓَﺴَﻴَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ۚ ﻓَﻘُﻞْ ﺃَﻓَﻠَﺎ ﺗَﺘَّﻘُﻮﻥَ
«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው።መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ
የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
(ዩኑስ 31)
③–የመልእክተኞች የመጀመሪያ ጥሪ ተውሂዱል ኡሉሂያ[አላህን ብቻ ተገዙ)
የሚለው ቁም ነገር ነው። ምክንያቱም ማንኛውም አምልኮ ተቀባይነት ይኖረው
ዘንድ ተውሂዱል ኡሉሂያ ዋና መሰረት ስለሆነና እሱ ካልተረጋገጠ ተቃራኒው ሺርክ መኖሩ አይቀሬ ስለሆነ ነው።
④–በወገኖቻቸው መካከል አለመግባባትና
ጭቅጭቅ የተፈጠረውም በዚሁ የተውሂድ ክፍል ነበር። ስለዚህ ይህን የተውሂድ ክፍል
ማወቅና በሚገባ መረዳት የማንኛውም ሰው ግዴታ ነው ። የተውሂድ ወሳኝነትና ደረጃው፡፡
①- ተውሂድ ከእስልምና መሰረቶች የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዝ ዋና መሰረት
ነው። በመሆኑም አንድ ሰው ወደ እስልምና ሃይማኖት መግባት የሚችለው፡-
#ላኢላሀ_ኢለላህ ወይም ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን
ሲመሰክርና አላህን ብቻ መገዛት እንዳለበት አምኖ ሲቀበል ነው።
የአላህ መልእክተኛ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡"ኢስላም በአምስት ነጥቦች ላይ ተመሰረተ፡-ከአላህ በስተቀር በእውነት
የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን
መመስከር፤ ሶላትን መስገድ፤ ዘካን መክፈል፤ የተከበረውን የአላህን ቤት ሓጅ
ጉብኝት ማድረግና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው ”ብለዋል።
②- ተውሂድ ከማንኛውም አምልኮ በፊት መታወቅ ያለበትና ወደ እርሱ ጥሪ
ሊደረግለት የሚገባው ወሳኝ ነጥብ ነው ።
#የአላህ_መልእክተኛ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ሙዓዝ የተባለውን
ሱሃቢ "የመን" ወደ ተባለ አገር ላስተማሪነት ሲልኩት፦“መጽሐፍ የተሰጣቸውን ሰዎች ታገኛለህ ስለዚህ ከአላህ በስተቀር በእውነት
የሚገዙት ጌታ አለመኖሩንና እኔ የአላህ መልእክተኛ መሆኔን አስተምራቸው ”አሉት።
③– አንድ አምልኮ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ተውሂድ ዋና መስፈርትና መሰረት ነው።
#ለምሳሌ፦ ሶላት ያለ ውዱእ ተቀባይነት እንደማያገኝ ሁሉ ማንኛውም አምልኮ ያለ ተውሂድ ተቀባይነት አያገኝም።
④-ተውሂድ በዚችም ሆነ በመጪዋ ዓለም የተቃና እድልና ሰላም ለማግኘት ዋና ምክንያት ነው።
#በአሏህ_ፈቃድ_ይቀጥላል…………
<~~~~~~~~~~~~~~~~>
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➦ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁሏህ ተዓላ)
እንድህ ይላሉ:_
➬ጡሩ ጓደኛ ማገኘት ከባድ ነው።
ከሱ መለየት ደሞ በጣም ቀላል ነገር ነውና! አሏህን ወደ መታዘዝ የሚመላክትህናየሚግዝህ ጓደኛ ካገኘህ በእጅህ አጥብቀህ ያዘው!!
Audio
♻️🔺ድንቅ ምክር ከሸህ ፈውዛን🔺♻️

🔺በየሚዲያ ወንድን ለሚፈትኑ
🔺የተጣበቀ ልብስ ለሚለብሱ
🔺በሰርግና በመዝናኛ ቦታ ላይ ከወንድ ጋር ለሚቀላቀሉ
🔺ፀጉራቸውና የተወሰነ የሰውነ አካላቸውን ለሚከፍቱ ሁሉ ይመለከታል

👂👂👂👂👂👂👂👂

🎙️للشيخ العلامة :صالح الفوزان - حفظه الله تعالى:
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
እህቴ ሆይ !
[ ከማህበራዊ ሚዲያ ጋር ]
~ ሚድያ ልቅ ነው። ከጀርባው ያጠፋሽውም ያለማሽውም ራይት እና ኤክስ የሚሰጥ ሰው የለውም በዚህ ምስቅልቅሉ በወጣ መድረክ ጌታውን የፈራ የጌታው መለኮታዊ ራዕይ በማሰራጨት የተጠመደ ውስኑ ቢኖርም ለተራ ጊዜው ለማቃጠል እንዲሁም ነፍስያው ወደ ምትነዳው የሚነዳ የባህር አረፋ የሆነም በርካታ ህዝብ አቅፎዋል። እንደ እኔ ባለ ሐያዐዋ ትርምሶች በበዙበት መድረክ ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም አግባብነት የለውም። በጥቅል የፌስ ቡክ ጃሒል ላደረገኝ ጌታ ምስጋና ይገባው ያሉ አሊም አውቃለሁ።
~ እኔ ሚዲያ ካልተጠቀምኩ ኢልም አላገኝም ኢልም ፍለጋ ነው ካልሽ እንፈለጉ የማይረጋገጡበት የቴሌ ግራም ቻናሎች ላይ የፈለግሽው ዑስታዝ ቻናል Join በማድረግ መከታተል ትቺያለሽ

~ አይ እኩልነትስ የሚል ነፍሲያ ከነፋፋሽ ምንም ማድረግ አልችልም ስትጠቀሚ እንደሴት ተጠቀሚ ከማለት ውጭ
__ውስጤ የሚያምንበት ነገር አለ እሱም ፌስቡክ የምትጠቀም የእውቀት ባለቤት እንደሌለች። ምክንያቱም አውቃለች የምትባለዋ ከአፍዋ የሚወጣው ስለማይ ነው። ከንግግርዋ የምረዳው እያለ አይ እስዋማ ተግባር ላይ እንዲህ ነች ብሎ የሚያታልል ልብ የለኝም። ዑለማዎች የማይደፍሩ መሣዐላ እንደ ፍትፍት ለማቅረብ ስትሞክር ሲታይ እንዴት በፌስቡክ አሊም አለ ያስብላል! ሲጀመር ለሴት የማያስፈልጋቸው ወንድ ባለበት ቦታ ሁሉ እኔም የጉዳዩ ባለቤት ነኝ ማለት በእራሱ ከዲን እውቀት የመነጨ አይደለም ምዕራባውያን ያመጡት በ- እኩልነት በሚል በርሜል ውስጥ ተነክረው የወጡት መፈክር እንጂ!። የተብዲዕና የተክፊር መሳላዐ ላይ የተጠመዱ ጥቂት ሴቶች ሳይ እንደው ኤፍ ቢ ......ብቻ ከዚህ ውጭ የሆኑ የፊዚክስ የኬምስትሪ የሌሎች የዱንያዊ ትምህርት እውቀቶች ጭንቅላታቸው የሞሉ ብዙ መኖራቸው እርግጥ ነው።በዱንያ ትምህርት ዲን ላይ ለማውራት ሞመከር ከሞኝነት ነው። እና ይሄም ምዕራባዊያን ያጠመዱት ወጥመድ ነው እራቂ ነው ምለው። እስቲ ጀምሪ ኢልም ፍለጋ አይሻ እኮ ሐዲስ በማስተላለፍ ከምርጦች ውስጥ ሆናለች ከሴቶች ምርጥ መሰለሽ?! በነቢዩ ዘመን ከነበሩ ከትላልቅ ታጋዬች ከእነ አቡ ኹረይራህ.....ከደረጃዎች ውስጥ ተመድባለች ።

ከሴቶቶችማ አሳልፈናል እኮ ! እረሳችሁት? ቁጥር አንድ እና ሁለት ጽሁፌ ላይ ልንገራችሁ እሺ "ምድር ላይ ያሉ ሴቶች የነቢዩ ሚስቶች ጨምሮ ኢልማቸው ቢሰበሰብ እና የአይሻ ኢልም ይበልጥ ነበር" ኢማም አዙሁርይ

የአንቺ ኢልም ምን ላይ ደረሰ ?!
አየሽ !አደጋ ላይ መሆንሽ
እሺ ላመላክትሽ
~ቁራዐን በመቅራት የእለተለት እንደ ቁርስ ምሳ እራትሽ የማይረሳ ይሁን። ቁራዐን እኮ የኢልም ዘርፎች ሁሉ የሚጨለፍበት ባህር ነው።ሀያዐም ያላብሳል።ከጌታችን ጋር ያለው ትስስር ያጠናክራል በተለየ የሌሊት እና ከሱብሒ በኃላ ማስተንተን ተጨምሮበትማ አይኖች እያነቡ ሆድን እያባባ ......ብቻ ከቁራን ጋ ያለው ትስስር ይጠክር።

~ትርፍ ሳት የሚሉት ነገር አያስጠላም? ሙሚን ጌታው እስኪገናኝ ዕረፍ የለውም ለዛም ነው አላህ ለነቢያችን፦

فَإِذَا فَرَغْتَ فَانصَبْ

{ በጨረስክም ጊዜ ልፋ ቀጥል }ያላቸው

ለውዱ ነቢይ ይህ ከተባሉ በውዥንብር ሜዳ ላይ የሚጠቅም የሚጎዳው ለይቶ ማወቅ ለተሳነው ለእኔ አይነት ትውልድማ ምን ሊባል ነው። ትርፍ ሳት ብሎ ያመጡትም ምዕራባዊያን ናቸው። ያልገቡበት የለም!እኛን ለማዋለል! ትርፍ ሳት የማኪያቶ ሳት የእንቅልፍ የክረምት፣ የመንፈቅ ፣ቤተሰብ ጋ፣ አጎት ጋ እረፍት.... እያለ ሳቶቹ በቂራት ያልተጠመደውማ ! ! አደጋ ነው።
ብቻ ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚ የሚል መልክት ጨምቄ ላስላተልፍ እየሞከርኩ ነው። ገብቶሻል
ከቁራን ቀጥሎ የኪታብ ቂራቶች ላይ ጠንክሪ መድረሳ ሂጄ ልቀራ ፈልጌ እንዲ ..... አይነት ዑዝር እያልሽ ብትደረድሪ አልሰማሽም። አስቀሪው ቤትሽ ድረስ መጥቶልሻል ሪከርዱ ከፍተሽ ኪታብሽ ገልጦ መቅራት አያጅብም በስልክሽ ከፍቶ መቅራት አልሐምዱሊላህ አላህ የዋለልን ጸጋ ። አጅ ነብይ አይባል በእጅሽ ይዘሽው የምትሽከረከሪ ስልክሽ ነው እና በተዘረጉልሽ አመቺ መንገዶች ሁሉ ኢልምሽ ላይ ጠንክሪ።
አላህ ያበርታችሁ ቆራጥ ታጋይ ጀግኖች አላህ ያድርጋችሁ ነገሮች አላህ ያቅልላችሁ

አብዱልከሪም መህዲ
Forwarded from á‰°á‰€áˆ­á‰°á‹‰ ያለቁ ደርሶች ማስቀመጫ ቻናል
📌✅ሶላት ከተጠናቀቀ በኋላ የሚባል ዚክር

📌✅لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرُ، اَللَّهُمَّ لاَ مَانِعَ لِمَا أَعْطَيْتَ، وَلاَ مُعْطِيَ لِمَا مَنَعْتَ، وَلاَ يَنْفَعُ ذَا الْجَدِّ مِنْكَ الْجَدُّ.

📌✅ከአላህ በስተቀር በሀቅ አሚመለክ የለም፡፡አንድ ነው፡፡ አጋርም የለውም፡፡ ስልጣን የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም የሚገባው ለርሱ ብቻ ነው፡፡ አላህ ሆይ! አንተ የሰጠኸውን ነገር የሚከለክል የለም፡፡ የከለከልከውን የሚሰጥ የለም፡፡ የክብር ባለቤትከአንተ ዘንድ ክብሩ ቅንጣት አይፈይደውም፡፡
🎻🎷🎺🎸🪕🩺🚫🚫

ሙዚቃን ማዳመጥ ወይንስ መንዙማን ማዳመጥ በጣም ከባዱ ወንጀል?

"አል አላማሀ አህመድ አነጅሚ አሏህ ይዘንለት
# ሙዚቃን ማዳማጥ ወንጀል ነው በዛ ላይ መቆየቱ ደግሞ ፊስቂነት ነው

" ነሺዳን ማዳማጥ ቢዳዓ ነው በዛ ላይ መቆየቱ ሙብተዲዕ ያስብለዋል

የፋሲቅ ሸር ከሙብተዲዕ ቀለል ያለ ነው

الفتاوى الجلية ج (١

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
በኢኽዋኖች እና በሙስጦፋ ላይ ያስጠነቀቁበት ድምፅ

(ሸይኽ ሙሐመድ አሚን/ደበቅ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
እምቢ በይ እታለም!
(ከካፊር ጋር ትዳር ለሚያስቡ እህቶች)
ለአላፊ ደስታ ስትይ ………. ለምትከስመው ጠውልጋ
ትዳር ከምትመሰርቺ ………. ኢስቲንጃ ከሌለው ጋ
ለዚች ጤዛ ዱንያ ብለሽ ………. ብልጭ ብላ ለምትጠፋ
ከለጋሱ ጌታ ዘንዳ ………. ከትንኝ ክንፍ ለማትሰፋ
እያለቀስን መጥተን ሳለ ………. እያለቀስን ለምንለቃት
አኺራችንን አስበን ………. ምናለ ብንንቃት?!!
እቱ ከጌታችን ጋራ ………. ነገ ከባድ ሂሳብ አለ
አስፈሪ ጭንቅ የሚያይበት ………. መናጢ ሁሉ ያልታደለ
ዛሬን ከመስመር ለቆ ………. ወደ ጥፋት ያጋደለ
ከእርኩሳን ጋር ተጣምሮ ………. በክህደት ላይ የዋለለ
ነገን በዛሬ የሸመተ ………. የዋህ እራሱን ያታለለ
“ያ ለይተኒ” የሚልበት ………. ነገ የቁጭት ቀን አለ፡፡
ይልቅ ስሚኝ እህት አለም፡
ትዳር የጌታ ሲሳይ ነው ………. ከባለ ዐርሹ የሚወሰን
ስለቋመጥን ሳይሆን ………. ፈቃዱ ሲኖር የሚደርሰን
“ይታደሉታል እንጂ ………. አይታገሉትም” ነው ነገሩ
ውሳኔው ከላይ እስከሚወርድ ………. ከዱዓህ ጋር ይሶብሩ፡፡
እንጂ ከእንጨት አምላኪ ጋ
እንጂ “አንድም ሶስትም” ከሚል ዜጋ
በስሜት ናላው ዞሮ ………. ሊያጠምድሽ መረብ ቢዘረጋ
ማር በሚተፋ ምላሱ ………. በስልት ወዳንቺ ቢጠጋ
ምናባዊ ሐሴት አይተሽ ………. ጉም ለመጨበጥ መንጠራራት
ለተስፋ ዳቦ እየቋመጥሽ ………. አትሁኚ የ’ሳት እራት፡፡
በምታይው ብልጭልጭ ………. እራስሽን አትደልይ
ባለ ገዳይ መርዙ እባብም ………. ለስላሳ ነው አስተውይ፡፡
ይልቁንም ረጋ ብለሽ ………. ከአፅናፍ ማዶ ተመልከቺ
ጤፍ በሚቆላ ምላሱ ………. ለተኩላ አትረቺ
ለዚች አጭር ህይወት ስትይ ………. በራስሽ ላይ አትሸፍቺ፡፡
ለዚህ ብላሽ ፈራሽ ገላ
ለዚህ ከንቱ ገልቱ አተላ
ዛሬ እጅሺን አትዘርጊ
ነገ እንዳትጠወልጊ፡፡
ሶላት ቁርኣኑ ተትቶ
ሒጃብ አደቡ ተዘንግቶ
በላኢላሀ ኢለላህ ቦታ ………. “አንድም ሶስትም” ተተክቶ
ግንባር ለመስቀል ሲዋረድ ………. የሐያሉ ሱጁድ ቀርቶ
ከቤትሽ ግድግዳ ላይ ………. የፈረንጅ ስእል ተለጥፎ
ሐያእ ግብረ-ገብነትሽ ………. ከላይሽ ላይ ተገፎ
ከግንባርሽ ላይ ነጥፎ ………. ከልብሽ ላይ ተንጠፍጥፎ
መስጂድ የለመዱ እግሮችሽ ………. ወደ ከኒሳ ሲያመሩ
ጠላ ኮረፌ እየጠመቅሽ ………. ሰካራሞች ሲያጓሩ
ይሄ እውን የሆነ እለት
ያኔ ሆነሻል የቁም ሙት!!
.
.
.
(ኢብኑ ሙነወር፣ መጋቢት 21/2008)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ለዐረብ ሀገር ወንድምና እህቶች
~~~~~~~~~~~~~
① ከሁሉም በፊት ለዲናችሁ ቅድሚያ ስጡ። ከተውሒድ ጀምራችሁ ግንዛቤያችሁን በተለያዩ መንገዶች አስፉ። ለአላህ ምስጋና ይግባውና በዚህ በኩል ብዙ ወንድሞችና እህቶች ዘንድ ተነሳሽነት ይታያል።
② ለአሰሪዎቻችሁ ታማኞች ሁኑ። የሰው ሀላፊነት እስከተቀበላችሁ ድረስ አላህን ፈርታችሁ ሀላፊነታችሁን ባግባቡ ተወጡ። በሰዐትም፣ በስራም፣ በገንዘብም፣ በክብርም፣ በልጆችም የምትታመኑ ሁኑ። አማናን መወጣት ትልቅ ሃላፊነት ነው።
③ በተቻላችሁ ከአላስፈላጊ የወንድና የሴት ቅልቅል ተጠንቀቁ። በጋራ የኪራይ ቤቶች ሊፈፀሙ ከሚችሉ አደጋዎች እራሳችሁን ጠብቁ።
④ እርስ በርስ ተዛዘኑ። ስራ ለሌለው ስራ በመፈለግ፣ ለተቸገረው በብድር ወይም እራስን በማይጎዳ መዋጮ ተጋገዙ።
⑤ ከወንጀለኞች ራቁ። አረብ ሀገር በርካታ ኢትዮጵያውያን በወንጀል ስራ ላይ መሰማራታቸው የሚታወቅ ነው። በነሱ ሳቢያ ኢትዮጵያውያን ባጠቃላይ በተደጋጋሚ ስማቸው ይጠፋል። የሚገርመው ብዙ ለነዚህ ወንጀለኞች ሽፋን የሚሰጡ ኢትዮጵያውያን መኖራቸው ነው። በነሱ ጥፋት አብራችሁ እንዳትጎዱ ተጠንቀቁ። እንዲያውም ለሌላ የሚተርፍ የተረጋገጠ ወንጀል ካያችሁ ለሚመለከተው አካል ጠቁሙ። ይሄ ለዲናችሁም ለገፅታችሁም ዋጋ አለው።
⑥ ቤተሰቦቻችሁን አትርሱ። ወላጅ ወላጅ ስለሆነ ብቻ ከባድ ሐቅ እንዳለው እሙን ነው። ከዚያም ባለፈ ስንት ፍዳቸውን አይተው አሳድገዋል። አረብ ሀገር ትሄዱ ዘንድ የተቸገሩላችሁም ብዙ ናቸው። እነዚህን ታሳቢ በማድረግ ወላጆቻችሁን አትርሱ። በዚያ ላይ አንዳንዶቻችሁ ወደ ወላጆቻችሁ ልጅ የላካችሁ ትኖራላችሁ። በዚህን ጊዜ ሐቁ ድርብርብ ነውና ኣኺራችሁን እንዳታጨልሙ ተጠንቀቁ።
⑦ እራሳችሁን አትርሱ። የወጣችሁት እንጀራ ፍለጋ ነው። ከፋም ደላ የሰው ሀገር የሰው ነው። ህልማችሁ ቋጥሮ ወደ ሀገር ለመመለስ እንጂ በልቶ ለመጥገብ፣ ደምቆ ለመልበስ አይደለም። ለዚህ ደግሞ ብልጥ መሆን ያስፈልጋል። መስራቱን ቻሉበት። መያዙንም ቻሉበት። ለቤተሰብ ስትልኩም አቅማችሁንም፣ ኖሯቸውንም፣ ሁኔታቸውንም እያገናዘባችሁ ይሁን። ለጎረምሳ ጫት መቃሚያና መንሸራሸሪያ አትላኩ። በዚህ ወንድሞቻችሁን ታበላሻላችሁ እንጂ አትጠቅሟቸውም። ገንዘባችሁንም አጥታችሁ ወንጀለኛም ትሆናላችሁ። ባጭሩ የምትሰሩትን ገንዘብ ቁም ነገር ላይ ለማዋል ተጣጣሩ። ባዶ እጃችሁን ላለመግባት በተቻላችሁ ተጠንቀቁ። ችግር መጥፎ ነው። ቤተሰብ እንኳን እንዲገፋችሁ ያደርጋል። አገራችን ለባዶ እጅ ቀርቶ ለያዘም እየከበደ ነው።
⑧ እቅድ ይኑራችሁ። ለቆይታችሁ ገደብ አስቀምጡለት። በግምት አትኑሩ። ሁለት አመት ሰራርቼ አገሬ እገባለሁ ብለው ሃያ አመት የኖሩ አሉ። ከአላማ ካልተወጣ ክፋት አልነበረውም። እየባከኑ ሲሆን ግን ያሳዝናል። "ምን ይዤ ልግባ?" እያሉ እየተብከነከኑ መኖር ይጎዳል። ስለዚህ ገደብ ያለው እቅድ ይኑራችሁ። ለእቅዳችሁም በትጋት አስቡ፣ በትጋት ስሩ። መገናኘታችሁ እቅዳችሁን የሚያሰናክል፣ ለትርጉም የለሽ ወጭ የሚዳርግ ከሆነ ተራራቁ።
⑨ ሴቶች ሆይ! መንገደኛ አታግቡ። እስኪ አሁን ሂንዲ፣ ፓኪስታኒ ማግባት ምን ይባላል? እንዲህ አይነቱ ትዳር ዘላቂ የመሆን እድሉ እጅግ የጠበበ ነው። ልጅ ከመጣም ከነ ጭራሹ አባቱ ጋር አይኖርም። ስለዚህ ለራስም ለልጅም ፈተና ነው።
(10) ለኸይር ስራ እጃችሁን ስትዘረጉ ጥንቁቅ ሁኑ። ኸይር አትስሩ አይባልም። ግን በትክክል ለታለመለት ግብ የሚደርስ መሆኑን ቢያንስ ሚዛን የሚደፋ ግምት ያዙ።
(11) ለትዳር ክብር ይኑራችሁ። ትዳርን መስፈርት በማያሟላ በተጨመላለቀ መልኩ ሳይሆን በሥርዓት ፈፅሙ። አትበዳደሉ። ኣኺራችሁን በማይጎዳ መልኩ በስርኣት ኑሩ። ለጋብቻ የተጋነነ ወጭ አታውጡ። ከሰሞንኛ ሆይሆይታ ይልቅ ለዘላቂው ትዳራችሁ ቅድሚያ ስጡ። መለያየት ግድ ካለም ባግባቡ ይሁን።

የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
ስለ ጀምዕያና ሙስጠፋ 🎙በሳዳት ከማል [ሀፊዘሁላህ]
ስለ ጀምዕያና ሙስጠፋ

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል
አቡ መርየም (ሀፊዘሁሏህ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📹مقطع مرئي📹

تلاوة بصوت الشيخ أحمد_الحذيفي حفظه الله.
ما تيسر من {سورة يوسف }.

➧"ቤት ውስጥ ስራ እየሰራች በዛውም ቁርአን የምታዳምጥ ሴት በሁለት መንገድ አጅር ታገኛለች አንደኛ የቤት ስራ በመስራቷ ሁለተኛ ቁርአን በማዳመጧ።

ሼኽ ፈውዛን
የጋብቻ ቀለበት በኢስላም እንዴት ይታያል በኡስታዝ አቡ ሙስሊም አልአሩሲ አል-አይመሮ ما حكم لبس…
በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ዑመር ሀሰን አልአሩሲ አል-አይመሮ (ሀፊዘሁሏህ)
➛ የጋብቻ ቀለበት በኢስላም እንዴት ይታያል?

◄ مَا حُكْمُ لُبْسِ خَاتَمِ الزَّوَاجِ في الْإِسْلَامِ؟

🔗 የዳውንሎድ ሊንኩን ይጫኑ Mp3  


  http://is.gd/U8gBI4

══ ≪ °📓🖇📓° ≫ ═══

🗓 የትዳር ድንጋጌዎች በቁርኣን እና በሐዲሥ (1) ከሚለው ሙሓደራ ክፍል 65 የተወሰደ ትምህርት ነው!!

═════ ≪ °📓🖇📓° ≫ ═════  
           
🎙 الأُسْتَاذُ أَبُو مُسْلِمٍ عُمَرُ بنُ حَسَنٍ الْعَرُوسَيّ


🎙
‏غـيـرة الـنـسـاء

عن عائشة - رضي الله عنها قالت

افتقدت النبي ﷺ في فِراشي ذات ليلة؛ فظننت أنه ذهب لـ بعض نسائه! فـ تحسست بيدي، فإذا هو ساجد يقول : سبحانك وبحمدك، لا إلهَ إلاّ أنت
• فقلت : بأبي أنت وأمي، إني لفي شأن وإنك لفي شأن آخر

☞የሴቶች ቅናት!

📜እናታችን ዐይሻ (አሏህ ስራዋን ይውደድና)እንዲህ ትላለች፦

➧"አንድ ለሊት የአሏህ መልእክተኛን ፍራሼ ላይ አጣኋቸው። ከኔ ፍራሽ ተነስተው አንዷ ሚስታቸው ጋር ሄደው ነው ብዬ ጠረጠርኩ።

➧በጨለማው ተነስቼ በእጄ ማሰስ ጀመርኩ ወዲያውኑ ሱጁድ ላይ ሆነው "ጌታዬ ሆይ! ከአንተ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም ከምስጋና ጋር ጥራት ይገባህ! " እያሉ አገኘዋቸው። ከዚያም እናቴና አባቴ ቤዛ ይሁኑልህ! አንተ በሌላ ጉዳይ እኔም በሌላ ጉዳይ ላይ ነበርን አልኩ።"

📚ሰሒሕ ሙስሊም

✍ዐብዱረዛቅ አል-ሐበሺይ

💎https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
‏أنتي تلبسين الحجاب ‏وتكوني جماله💎💎💎🌹🥀
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
♻️🔻ጎልተው የሚታዩ የብዙ ሰዎች ስህተት🔻♻️

#⃣🔺 ብዙ ሰዎች በተለምዶ ⤵️⤵️
♻️ ሲያስነጥሱ ➣አኡዙ ቢላህ (أععوذ بالله)
♻️ በልተው ሲያገሱ ➣አልሀምዱሊላ (الحمد لله) ይላሉ
♻️🔺ነገር ግን ሁለቱም በሸሪአ መሰረት የሌላቸው መጤ የሆኑ ተግባሮች ስለሆኑ ጥንቃቄ ልናረግ ይገባል።

🎙 قناة الشيخ محمد بن صالح العثيمين -رحمه الله-


http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru