💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
🔴 መህሯን ቁርአን ማስሀፈዝ 🔴

ፈትዋ ቁጥር : 369

📮 #ጥያቄ

📮 መህሯ ቁርአን #ሊያስሀፍዛት ተስማምተው ተጋብተው ነበር ፣ ነገር ግን ሳታሀፍዝ #በፊት ተፋቱ ፣ ታዲያ መህሯ እንዴት ነው የሚሆነው⁉️

#መልስ

በመጀመሪያ ደረጃ መህርን ቁርአን ሒፍዝ #ማድረግ ላይ በኡለሞች መካከል ልዩነት አለ። ከፊሎቹ ዑለሞች መህር #በገንዘብ መሆን ስላለበትና ቁርአን ማስሀፍዝና የመሳሰሉ #ዒባዳዎች ደግሞ ወደ አላህ #መቃረቢያ እንጅ ልውጫ ሊሆኑ አይገባም በሚል #የተከለከለ ነው ብለዋል።

ሌሎች ደግሞ ነብዩ አንዱን ሶሀብይ እሱ ዘንድ ባለው ቁርአን ሊያቀራት ዘንዳ አስማምተው አጋብተውታልና #ይቻላል ብለዋል። ምክንያቱም የታወቀ #ጥቅም ያለው ነገር ሁሉ መህር መሆን ስለሚችል ነው። #የተሻለውም አቋም የተፈቀደ መሆኑ ነው።

ታዲያ አንድ ሰው መህሯን ቁርአን ሊያስሀፍዛት ተስማምተው ከተጋቡ #በኃላ ሳያስሀፍዛት በፊት ቢፋቱ የተለያየ ፍርድ ይኖረዋል። ማለትም የተስማሙት እሱ #ራሱ ሊያስሀፍዛት ከሆነ ከዚህ በኃላ አጂነቢ በመሆናቸው ራሱ ሊያስሀፍዛት ስለማይችል #ለቢጤዎቿ የሚሰጠው መህር ተመሳሳይ ይሰጣታል።

ሆኖም የተስማሙት በሱ #ሀላፊነት ሊያስሀፍዛት ከሆነ የምታስሀፍዛት ሴት ኡስታዛ ወይም መህረም የሆነ ሰው #ቀጥሮላት እንድትሀፍዝ ማስደረግ ይኖርበታል። ሆኖም የሷ ፍላጎት ከሆነ መህሩን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል #መተው ትችላለች።

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

📚 #ምንጭ

📙 አልመውሱዓቱል ፊቅሒያህ ፣ 39 / 155 ، 156


🖋ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ወረርሽኝ በኢስላም
<===========>
የዱኒያ ሐያቱ ምንም እንኳን ቢያጥርም
ህመሙ ቢከብደው ለሞት ቢጣጣርም
ለህልፈት ቢያበቃው ድኖለት ባይሽርም
ወረርሽኝ በኢስላም አያስደነብርም

ብቻ በአላህና በነብያት መንገድ
ከቁርዓን ሐዲስ ነብሱ ሳትወገድ
አምኖ ከነበረ ቆሞ ሲንገዳገድ
በወረርሽኝ ክስተት አካሉ ቢማገድ

ምንዳው ሸሂድ ሆኖ ቀልቡ እንድትረጋ
እምነቱ ጋሻው ነው ፈፅሞ እንዳይሰጋ

አደም ነኝ የታቲ ልጅ



https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
♻️🔺 ለእናት አባት መልካም መዋል 🔺♻️

♻️🔺የሸህ መሀመድ አልይ ኣደም አላህ ይዘንላቸው ድንቅ ታሪክ

ይህ ታላቁ ኢትዮጵያዊው አሊም አላህ ቀብራቸው የጀነት ጨፌ ያድርግላቸውና ለአባታቸው ትልቅን ውለታ ውለዋል። እሱም

🔺ከተማሪያቸው መሀከል አንዱ እንደገለፀው ከሳቸው ስም በፊት አሊም ወይም ሸኽ የሚል ፅሁፍ ካዩ ያጠፋትና ከአባታቸው ስም አጠገብ ያደርጉት ነበር። ለምሳሌ (ሸህ አላማ ፈቂህ ሙሀመድ አልይ ) የሚለውን ያጠፋትና (መሀመድ ሸኽ አላማ አልይ) በማለት የክብር መጠርያውን ለአባታቸው ይሰጡ ነበር።

🖊አቡ አብደላ
قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله

إذا رأيت نفسك تنشرح لفعل السيئات وتضيق ذرعا بفعل الطاعات فاحذر وأنقذ نفسك وتب إلى الله عز وجل حتى ييسر الله لك ومهما أذنبت إذا أقبلت على الله عز وجل أقبل الله عليك.

(شرح رياض الصالحين / ج4 / ص558).

Sheikhህ ኢብኑ ዑተይሚን ራሂመሁላህ ብለዋል

መጥፎ ስራዎችን ለመስራት ሲያስረዱ እና የመታዘዝ ድርጊቶችን በመፈፀም ትዕግስት እንደሌለው ከተመለከቱ ጥንቃቄ ያድርጉ ፣ እራስዎን ያድኑ እና እአላህ ቀላል እንዲያደርጉሎት ወደ ሁሉን ቻይ ወደ አላህ ተውባ ያድርጉ ፣ እና ወደ ሁሉን ቻይ ወደ አላህ ቢመለሱ የሚሳሳቱት ነገሮች ሁሉ አሏህ
ይቀበላችሁ #ምንጭ⬇️
(شرح رياض الصالحين / ج4 / ص558).
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🔸ሸይጣን ሱረቱል በቀራህ ከሚቀራበት ቤት ይሸሻል
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
የተውሒድ ጉዳይ ጊዜ ሊሰጠው የሚችል ነገር አይደለም።
ሰው በሽርክ ሲሞት እያዩ ዝም ማለት ማዘንም አይደለም።

🎤በትላንትናው እለት እሁድ ሀርቡ ላይ የተደረገ ሙሃደራ
🎧በኡስታዝ ሳዳት ከማል አቡ መርየም።
<አድስ መሆኑን እንዳትዘነጉ>
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
ኡስታዝ ኸድር አህመድ (አል-ኬሚሴ)
ኢልም ከንግግርም ከተግባርም ይቀድማል በሚል ርዕስ ቆንጆ ሙሐደራ አድርጓል
  ↷⇣🔊⇣↶
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
● قال الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله:
.
💎المرأةُ في ميزان الإسلام، دُرَّة ثمينة، وجوهرةٌ كريمة، تُصان من كل أذىً وتحمى من كل رذيلة.

💎በኢስላም ሚዛን ሴት ልጅ፤ ውድ እንቁ እና የከበረ ፈርጥ ናት ።
ከአሰቸጋሪ እና ከመጥፎ ምግባር ሁሉ ጥበቃ ሊደረግላት ይገባል።

📓 موعظةُ النساء - 11

💎https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
አብዱላህ ኢብኑ መስኡድ (ረዲየላሁ አንሁ) እንዲህ ይላሉ

"አዋጅ!! ማንም ሰው በዲኑ ጉዳይ ሌላውን በጭፍን አይከተል። እንዲያ የሚያደርግ ከሆነ ሰውየው ሲያምን ያምናል፣ ሰውየው ሲከፍር ይከፍራል።"
ይላሉ

[አጥ-ጦበራኒ: (9/152)
Audio
የደሴ መርጥ ዑለሞች በሙስጦፋ ላይ ባደባባይ መልድ(ረድ)ጀመሩ እነሆ #ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ሐፊዞሁሏህ በኢኽዋኖችና በሙስጤ አስጠነቀቁ

አያይዘውም በድን ላይ መገለባበጥ የቢድዓ ምልክት ነው ብለው አስተነቀቁ!!

በሚቀጥለው የሸይኽ ሙሐመድ ደበቅ(አሚን)ን እንለቃለን ኢንሻአላህ

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
↬ከምንም በላይ እጅግ በጣም ሙእሚኖች የሚናፍቁትና በጉጉት የሚጠብቁት ጥሪ፥

《يا أيتها النفس المطمئنة إرجعي إلى ربك راضية مرضية فادخلي في عبادي وادخلي جنتي》

↬(አንተ፥ በጌታዋ በሚገባ በማመኗ የተረጋጋች ነፍስ -መንፈስ- ባለቤት ሆይ፥ አላህ የሰጠህን ምንዳ በደስታ ተቀብለህ ከደጋግ ባሮቼ ጋር {ጀነት ግባ} የሚለው ጥሪ ነው፡፡

🤲ያረብ ይህን ጥሪ በቀጥታ ሰምተው ከሚደሰቱ ባሮችህ አድርገን
ለዚህ ትልቅ ማዕረግ የሚያበቃውን "ኢማን" ልናውቀውና ልንጠብቀው ይገባናል

ኡስታዝ አህመድ ሸይኽ ኣደም (ሐፊዘሁላህ)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
⇢አላህን ከልቡ የሚፈራ ወንድ ቢሆን እንጅ በዚህ ዘመን አያደርገውም ።

🍃አነስ ረድላሁ ዐንሁ እንድህ ሲል ያስተላልፋል፦

⇢" አንድት ሴት ባጠገብህ ካለፈች እስከምታልፍህ ድረስ አይንህን ስበር።"
( አል ወረእ ሊብኒ አቢዱንያ 72)

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
በሀርቡ ሙሐደራ ላይ የተ ጠየቁ ጥያቄዎችና መልሶቻቻው
በሸይ ሀሰን አሊ
በኡስታዝ ኸድር አህመድና
በኡስታዝ ሳዳት ከማል
  ↷⇣🔊⇣↶

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➤▸የክስረት ሁሉ ክስረት ማለት:- የቂያማ እለት ራሱንም ቤተሰቡንም ያከሰረና ለጀሀነም እሳት የዳረገ ሰው ነው ።

➤▸ነገ የቂያማ እለት አንተንም ቤተሰብህንም ከክስረት ለማዳን የምትፈልግ ከሆነ ዛሬ ዱንያ ላይ ሳለህ ነፍስህንም ቤተሰብህንም ወደ መልካም ነገር ልትመራቸውና ከመጥፎ ነገሮች ልትታደጋቸው ይገባል ።

➤▸የመልካም ነገሮች ሁሉ ቁንጮ ተውሒድና ሱና ነውና ነፍስህን እንዲሁም ቤተሰብህን በተውሒድና በሱና አንፅ ።

➤▸የመጥፎ ነገሮች ሁሉ ዋና የሚባሉት ደግሞ ሽርክና ቢድአ ናቸውና ነፍስህንም እንዲሁም ቤተሰብህን ከሽርክና ከቢድአ ልትታደግ ይገባል ።

አላህ የቂያማ እለት ከሚከስሩት አያድርገን አሚን ።
መንቁል...!!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📌♻️ ጊዜህን በቁም ነገር ላይ አውለው ♻️📌

ሸህ ኢብኑ ባዝ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ።

🔺 ጊዜውን 👉አላህን በማውሳት (በዚክር)
👉ቁርአን በመቅራት
👉ከመልካም ሰዎች ጋር በመሆን
👉ከዝንጉና ከመጥፎ ጓደኞችን
በመራቅ ያሳለፈ ሰው
🔺 ቀልቡ ያማረና የለሰለሰ ይሆንለታል።

📚 مجموع فتاوى ابن باز (5/244)
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
#ተውሒድ
#ክፍል

#ወሳኝና_ጠቃሚ_ነጥቦች፡-----
①–እነዚህ ሦስት የተውሂድ ክፍሎች ከፍተኛ ትስስርና ተዛምዶ ያላቸው በመሆኑ በአንዱ አምኖ በሌላው መካድ በሁሉም እንደመካድ
ይቆጠራል።
②–በአላህ መልዕእክተኛ ወቅት የነበሩት ከሃዲያን የሁሉ ነገር ፈጣሪ ፤ ሲሳይን ሰጪ ፤ ሕይወት የሚሰጠውና የሚነሳው አላህ ብቻ
መሆኑን ጠንቅቀው ያውቁና ያምኑ ነበር። ይሁን እንጂ ከአላህ ውጭ የሆነን አካል ያመልኩ ስለነበር ይህ እምነታቸው ሙስሊሞች
አልቻለም።
#አላህ_እንዲህ_ይላል
ﻗُﻞْ ﻣَﻦ ﻳَﺮْﺯُﻗُﻜُﻢ ﻣِّﻦَ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﺀِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﺃَﻣَّﻦ ﻳَﻤْﻠِﻚُ ﺍﻟﺴَّﻤْﻊَ ﻭَﺍﻟْﺄَﺑْﺼَﺎﺭَ ﻭَﻣَﻦﻳُﺨْﺮِﺝُ ﺍﻟْﺤَﻲَّ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﻤَﻴِّﺖِ ﻭَﻳُﺨْﺮِﺝُ ﺍﻟْﻤَﻴِّﺖَ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺤَﻲِّ ﻭَﻣَﻦ ﻳُﺪَﺑِّﺮُ ﺍﻟْﺄَﻣْﺮَ ۚ
ﻓَﺴَﻴَﻘُﻮﻟُﻮﻥَ ﺍﻟﻠَّﻪُ ۚ ﻓَﻘُﻞْ ﺃَﻓَﻠَﺎ ﺗَﺘَّﻘُﻮﻥَ
«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው።መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ
የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ (ለምን ታጋራላችሁ) አትፈሩትምን» በላቸው፡፡
(ዩኑስ 31)
③–የመልእክተኞች የመጀመሪያ ጥሪ ተውሂዱል ኡሉሂያ[አላህን ብቻ ተገዙ)
የሚለው ቁም ነገር ነው። ምክንያቱም ማንኛውም አምልኮ ተቀባይነት ይኖረው
ዘንድ ተውሂዱል ኡሉሂያ ዋና መሰረት ስለሆነና እሱ ካልተረጋገጠ ተቃራኒው ሺርክ መኖሩ አይቀሬ ስለሆነ ነው።
④–በወገኖቻቸው መካከል አለመግባባትና
ጭቅጭቅ የተፈጠረውም በዚሁ የተውሂድ ክፍል ነበር። ስለዚህ ይህን የተውሂድ ክፍል
ማወቅና በሚገባ መረዳት የማንኛውም ሰው ግዴታ ነው ። የተውሂድ ወሳኝነትና ደረጃው፡፡
①- ተውሂድ ከእስልምና መሰረቶች የመጀመሪያውን ቦታ የሚይዝ ዋና መሰረት
ነው። በመሆኑም አንድ ሰው ወደ እስልምና ሃይማኖት መግባት የሚችለው፡-
#ላኢላሀ_ኢለላህ ወይም ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት አምላክ አለመኖሩን
ሲመሰክርና አላህን ብቻ መገዛት እንዳለበት አምኖ ሲቀበል ነው።
የአላህ መልእክተኛ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ፡"ኢስላም በአምስት ነጥቦች ላይ ተመሰረተ፡-ከአላህ በስተቀር በእውነት
የሚገዙት አምላክ አለመኖሩንና ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን
መመስከር፤ ሶላትን መስገድ፤ ዘካን መክፈል፤ የተከበረውን የአላህን ቤት ሓጅ
ጉብኝት ማድረግና የረመዷንን ወር መፆም ናቸው ”ብለዋል።
②- ተውሂድ ከማንኛውም አምልኮ በፊት መታወቅ ያለበትና ወደ እርሱ ጥሪ
ሊደረግለት የሚገባው ወሳኝ ነጥብ ነው ።
#የአላህ_መልእክተኛ ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ሙዓዝ የተባለውን
ሱሃቢ "የመን" ወደ ተባለ አገር ላስተማሪነት ሲልኩት፦“መጽሐፍ የተሰጣቸውን ሰዎች ታገኛለህ ስለዚህ ከአላህ በስተቀር በእውነት
የሚገዙት ጌታ አለመኖሩንና እኔ የአላህ መልእክተኛ መሆኔን አስተምራቸው ”አሉት።
③– አንድ አምልኮ ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ተውሂድ ዋና መስፈርትና መሰረት ነው።
#ለምሳሌ፦ ሶላት ያለ ውዱእ ተቀባይነት እንደማያገኝ ሁሉ ማንኛውም አምልኮ ያለ ተውሂድ ተቀባይነት አያገኝም።
④-ተውሂድ በዚችም ሆነ በመጪዋ ዓለም የተቃና እድልና ሰላም ለማግኘት ዋና ምክንያት ነው።
#በአሏህ_ፈቃድ_ይቀጥላል…………
<~~~~~~~~~~~~~~~~>
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➦ኢማሙ ሻፊዒይ (ረሂመሁሏህ ተዓላ)
እንድህ ይላሉ:_
➬ጡሩ ጓደኛ ማገኘት ከባድ ነው።
ከሱ መለየት ደሞ በጣም ቀላል ነገር ነውና! አሏህን ወደ መታዘዝ የሚመላክትህናየሚግዝህ ጓደኛ ካገኘህ በእጅህ አጥብቀህ ያዘው!!
Audio
♻️🔺ድንቅ ምክር ከሸህ ፈውዛን🔺♻️

🔺በየሚዲያ ወንድን ለሚፈትኑ
🔺የተጣበቀ ልብስ ለሚለብሱ
🔺በሰርግና በመዝናኛ ቦታ ላይ ከወንድ ጋር ለሚቀላቀሉ
🔺ፀጉራቸውና የተወሰነ የሰውነ አካላቸውን ለሚከፍቱ ሁሉ ይመለከታል

👂👂👂👂👂👂👂👂

🎙️للشيخ العلامة :صالح الفوزان - حفظه الله تعالى:
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru