💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
የማለዳ የቁርዐን ግብዣየ

መሳጭ ቲላዋ
ያዳምጡ ይወዱታል


እናንተ የቁርዓን ህዝቦች ሆይ ‼️
🔻ቁርዐንን ማዳመጥ
🔻 ማንበብ አትሰላቹ
ዘወትር ልባችን ከቁርዐን ጋር ይሁን ❗️
አላህ ያግራልን ⁉️

ማን ይፈልጋል ቁርዐን ማዳመጥ

እስቲ እንያቹ ቤተስብ ሁኑ ⁉️
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
https://t.me/Abu_Mahi_Ibnu_Idris
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

✅ አላህ እጅ እንዳለውና በዚህ ላይ የአህባሾች ማምታቻ

➰ክፍል ④③➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➳ክፍል ስምንት ➲አራተኛው፡ - ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው ወደአላህ የሚያቃርቡ ተግባራቶች የትንሳኤ ቀን ባሪያው በአላህ ውዴታ የሚጎናጸፍበት በጀነት ድልብ ሀብት ሆኖ እንደሚቆየው የሸሪዓ መረጃዎች ሁሉ ይጠቁማሉ፡፡ ➧በቁርኣን ፣ ተግባር በኢማን ስም ከመግባቱ በተጨማሪ ኢማን እናተግባርን በማጣመር የሚገኘውን ምንዳ ፣ የሁኔታቸውን…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ዘጠኝ
〰〰〰〰〰

✅አምስተኛው፡ - ሰለፎቹ ባወቁት ለመስራት ተሸቀዳዳሚ ነበሩ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲ይህን ደረጃ ከሚያብራሩ ነጥቦች መካከል፡ የሰለፎች አስደናቂ ባህሪያቸው ነው፡፡ሰለፎቹ ተግባርን በቋሚነት ለመፈጸም ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡ ከረሡል صلى الله عليه وسلم የሰሙትን ፈጥነው ለመተግባር ይቸኩሉ ነበር፡፡

➭በዚህ ትርጉም ላይ ሰለፎቹ ምን ያክል ባወቁት ለመተግበር ፍላጎቱ እንደነበራቸው ብርቱ ትኩረት እንደሚሰጡ የሚገልጹ በርካታ መረጃዎች መጠዋል፡፡ከዚህ መካከል ቡኻሪና ሙስሊም ላይ ተዘግቦ የሚገኘው ሐዲስ ነው፡፡ የረሡል صلى الله عليه وسلم ልጅ ፋጢማ ረድየላህ አንሃ አገልጋይ ፈልጋ ለአላህ መልእከተኛ ጥያቄ አቀረበች፡፡

▪️የአላህ መልክተኛም صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምላሽ ሰጧት፡- “ለአንች ከአገልጋይ የተሻለውን ልጠቁምሽ?” አሏት፡፡ (ለመተኛት) ወደፍራሽ በተጠጋሽ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሃን አሏህ ፣ አልሀምዱ ሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ፤ አሏሁ አክበር ሰላሳ ሶስት ጊዜ በይ” አሏት፡፡ ባለቤቷ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"فما تركتها منذ سمعتها من رسول الله صلى الله عليه وسلم"

“ከረሡል ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቸው አላውቅም” ከመካከላቸው አንዱ “አስቸጋሪ ሌሊት ላይ እንኳ ቢሆን? - ማለትም ሰው በሚዘነጋበት ሰኣት ላይ እንኳ ቢሆን? - ይህን ዚክር ረስቶት አያውቅም?” ፤ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን?!” - ይህ ሌሊት የታወቀ ጦርነት ነው - የሚል ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን” በማለት ምላሽ ሰጧል፡
፡ ቡኻሪ፡ 5362 ሙስሊም፡2727

➧ዓንበሳህ ብን አቢ ሱፍያን -ረሂመሁሏህ- በሞተበት በሽታ ላይ ሆኖ ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሰማሁ ብላ የሚከተለውን ሐዲስ ነገረችኝ ብሎ ለእኔ አስተላልፎልኛል ይላል ዓምር ብን አውስ፡፡

"من صلى اثنتيني عشرة ركعة في يوم وليلة بني له بهن بيت في الجنة"

▪️“አስራ ሁለት ረከዓዎችን በሌሊትና በቀን የሰገደ ሰው በእነርሱ አማካኝነት በጀነት ቤት ይገነባለታል፡፡” ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ የሚከተለውን ተናግራለች ፡-
"فما تركتهن منذ سمعتهن من رسول الله"

➧“ከረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰማሁ ጀምሬ (እነዚህን አስራ ሁለት ረከዓዎች) ትቻቸው አላውቅም” አንበሳህ ደግሞ በተመሳሳይ “ከኡሙ ሀቢባ ከሰማሁ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም”ይላል፡፡ ዓምር ብን አውስ ደግሞ “ከአንበሳህ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል፡፡ ኑዕማን ብን ሳሊም ደግሞ “ከዓምር ብን አውስ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል
፡፡ ሙስሊም፡728

➠ይህ ፍጥነትን እና በቋሚነት መፈጸምን ያጣመረ ታላቅ ወኔ ነው፡፡ ለስራ መፍጠን ፣ቋሚ ደምበኛ ለመሆን መሽቀዳደም፡፡

▪️ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ አቡሁረይራ ረዲየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"أوصاني خليلي بثلاث لا أدعهن حتى أموت: صوم ثلاث أيام من كل شهر ، وصالة الضحى ، ونوم على وتر"

➲“ወዳጀ እስከምሞት ድረስ የማልተዋቸው በሆኑ ሶስት ነገሮች አደራ አለኝ፡፡ ከየወሩ ሶስትቀናቶችን (እንድጾም) ፣ የዱሃ ሶላት (እንድሰግድ) ፤ ዊትር ሰግጀ እንድተኛ” ቡኻሪ፡1178
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
ክፍል 2️⃣ሂዳየቱል ሙስተፊድ
Voice changer with effects (https://play.google.com/store/apps/…
↪️አድስ ተከታታይ የኪታብ ቁረአት
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

📚 የኪታቡ ስም ሒዳየቱል ሙስተፊድ ፊአህካሚ ተጅዊይድ
📚(هدايةالمستفيد في احكام التجويد)


📝 አዘጋጅ " ሸይኽ ሙሀመድ መህሙድ አቡ ሪማ በመባል የሚታወቁት

📝تأليف، (الشيخ محمد محمود المشهور بأبي ريمة)

▪️ክፍል ሁለት 2⃣
〰〰〰〰〰〰

📕የኪታቧን PDF ለማግኘት ⤵️⤵️

https://t.me/Asselefya1/3340

🎙 አቅራቢ በወንድም አቡ ሒበቲላህ

https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Forwarded from áŠ á‰Ą ሙዓዝ (Abu muaz) (አቡ ሙዓዝ ሀሰን)
إن لله ما أخذ وله ما أعطي وكل شيئ بأجل مسمي

انتقل أخونا سعيد من جماعة كومبولشا إلي الأخرة فجأة رحمه الله تعالي.

ከ ኮምቦልቻ ጀመዓዎች አንዱ የሆነው ወንድማችን ሰዒድ ትናንት ገቢያ ውሎ በድንገት አጀሉ ደርሶ ሂዎቱ አልፏል አሏህ ይዘንለት

ስለሆነም የዛሬው ቀጠሯች ወደ ሳምንቱ እሁድ ተላልፏል አሏህ በሰላም ያድርሰን።

የመጀመሪያውን መልእክት ሼር ያደረገ ሁሉ ይህንንም ሼር ያድርግልን ህዝብ እንዳይለፋብን ባረከሏሁ ፊኩም።
➲ታላቅ ብስራት
➫➫➫➫➫➫

➧በጀነት የሚበሰሩ ሙእሚኖች (ምዕመናን) የሚከተሉትን ባህሪያት በዘውታሪነት ተላብሰዋል።

《ٱلتَّـٰۤىِٕبُونَ ٱلۡعَـٰبِدُونَ ٱلۡحَـٰمِدُونَ ٱلسَّـٰۤىِٕحُونَ ٱلرَّ ٰ⁠كِعُونَ ٱلسَّـٰجِدُونَ ٱلۡـَٔامِرُونَ بِٱلۡمَعۡرُوفِ وَٱلنَّاهُونَ عَنِ ٱلۡمُنكَرِ وَٱلۡحَـٰفِظُونَ لِحُدُودِ ٱللَّهِۗ وَبَشِّرِ ٱلۡمُؤۡمِنِینَ》التوبة :112

《(ከጥፋታቸው) ተመላሾች ፣ አምላኪዎች፣ አመስጋኞች ፣ ጿሚዎች ፣ አጎንባሾች ፣ ሰጋጆች ፣በመልካም አዛዦች ፣ ከመጥፎም ከልካዮች ፣የአላህንም ህግጋት ጠባቂዎች ናቸውና ሙዕሚኖችንም አብስር።》


ሁልጊዜም ተመላሽ ፣
በተውሂድ ላይ ታጋሽ፣
አመስጋኝ ጿሚዎች፣
ከልብ ሰጋጆች፣
ትችትን ሳይፈሩ፣
ለሀቅ ሲጣሩ፣
በኢስላም የኖሩ፣
እንዲህ ተበሰሩ፣✍

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➻➻➻➻➻ ➧ክፍል አርባ አንድ 〰〰〰〰〰〰 “ዝናቡ ዘነበ ጫቱ ለመለመ፣ የሚቅመው ቢያገኝ እያጉረመረመ” ➲ኡመተል ኢስላምን ያሽመደመደው፣ ያጀዘበው፣ የአላህንም የፍጡራንንም ሀቅ እንዲያጓድል ሰበብ የሆነው ይህን አደንዛዥ ቅጠል እንዲህ እያሉ ያስተዋውቁታል። አላህ ወንድም እና እህቶቻንን ከዚህ ሱስ ያውጣልን። “ወጣቶች ዘፈኑ በስልት እያዜሙ፣ እያሉ ይጠሩሃል…
➧መንዙማ
➭➭➭➭➭

➛ክፍል አርባ ሁለት
➫➫➫➫➫➫➫➫

✅“ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል”
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➲እነዚህ የሺርክ መንዙማ ባዮች ሌት ተቀን ከአላህ ሌላ ያለን ነብይ፣ ወሊይ እና
ወሊይ ተብየዎችን ሲጠሩ አይተው ጴንጤዎችም ሙስሊሙን አላህን ትቶ ወደ ነብዩላህ ኢሳ አምልኮ እንዲገባ ጥሪያቸውን በመንዙማ በማቀናበር እያቀረቡ ነው። ለጊዜው እጄ የገባው መንዙማ እንዲህ ይላል፡-

➴➴“ዘይኔው ነብዬ፣
ኢሳ አላህዬ”


➧ሙስሊሙ የጴንጤዎቹን መንዙማ ሲሰማ ያሳየው አቋም እና ቁጣ በጣም
የሚመሰገን ነው። ከባዱ ጥያቄ መንዙማው ተቃውሞ ያስነሳው ኩፍር ስለሆነ ነው ወይንስ ጴንጤዎች ስለዘመሩት? ኩፍር ስለሆነ ከሆነ በጣም ያስደስታል። አብሮ ግን የሚነሳ በጣም ወሳኝ ጥያቄ አለ። እሱም ከላይ ያየናቸው የክህደት፣ የሺርክ፣ የቢድዓ እናሌሎችም መንዙማ እና ነሺዳዎች ሲዘመሩስ ይቆጣሉ ወይንስ አይቆጡም?

ካልተቆጡ ከባድ አደጋ ውስጥ ኖት። ምክንያቱም ዋናው ጠብ ከሺርክ ጋር ነው። ለምሳሌ ከአላህ ውጭ አንድ ሰው መርየምን ቢያመልክ ሺርክ ነው። ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው ከአላህ ውጭ ነብዩን صلى الله عليه وسلم ቢያመልክም ሺርክ ነው።አንድ የማውቀውን እውነተኛ ታሪክ ልጥቀስ።

➧ ልጅቷ ሙስሊም ነበረች። ታሪኳ እንዲህ ነው። አባቷ እሮብ እሮብ በየሳምንቱ የሚያርድ እና በጣም ብዙ ሰዎች ፈርተውት የሚሰግዱለት ግለሰብ ነበር። ይህች ልጅ ይህን ተግባር ህይወቷን ሙሉ ትመለከት ነበር።

➲ስለ ኢስላምም ብዙ እውቀት የላትም ነበር። ከዚያም ጴንጤ ሆነች። ዘመዶች አግኝተው ሲያናግሯት “አይደለም ለእየሱስ ለእኔ አባትም ሰው ይሰግዳል” የሚል አስደንጋጭ መልስ ሰጠች።

➭በርግጥ በአሁኑ ሰዓት ልጂቱ ወደ እስልምና ተመልሳለች። አላህ ፅናቱን
ይለግሳት። ሆኖም ግን ክስተቱ አንድ ቁም ነገር ያስጨብጠናል። እሱም እኛ ሙስሊሞች ጴንጤ እንዲህ አደረገ ብለን ከማለታችን በፊት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከምንም በፊት በተውሒድ ላይ ማነፅ ይገባናል። ያለበለዚያ በመሀላችን የሚገኙ ድንበር ዘለል
አክብሮቶች በራሳቸው በቂ ጥፋት ከመሆን አለፈው ሰፋፊ የጥፋት ሽንቁሮችን ይከፍታሉ።


➲ነብዩን صلى الله عليه وسلم ማሞገስ ለንግድ መጠቀም
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➫➫➫➫➫➫➫

▪️የሚከተለው ጥያቄ ለታላቁ አሊም ሙሐመድ ሷሊህ አል-ኡሰይሚን
(ረሂመሁላህ) ቀረበላቸው


ጥያቄ፡- ነብዩን صلى الله عليه وسلم ማሞገስን በንግድነት መጠቀም እንዴት ይታያል?

➧መልስ፡- ይህ ሐራም ነው። የነቢዩ صلى الله عليه وسلم ሙገሳ በሁለት እንደሚከፈል መታወቅአለበት፡-

➧አንደኛው፡- ሳያጋንኑና ከልክ ሳያልፉ በሚገባቸው ነገር ማሞገስ ነው። ይህ ችግር የለውም። ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ከስነ ምግባራቸው በሚገባቸው ነገር ቢሞገሱ ችግር የለውም።

➧ሁለተኛው፡- ከልክ ያለፈ ሙገሳ ነው። ይህን ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ በማለት ከልክለዋል። “ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ እንዳላቁት (ከደረጃው በላይ ከፍከፍ እንዳደረጉት) አታልቁኝ እኔ ባሪያ ነኝ የአላህ ባሪያና መልእክተኛው በሉኝ” ብለዋል።

➲ነቢዩ صلى الله عليه وسلم እርዳታ የጠየቃቸውን የሚረዱ (የሚደርሱለት) ናቸው። የተቸገረን ሰው ዱዓ ይቀበላሉ። የአዱንያና የአኺራ ተቆጣጣሪ ናቸው። ገይብን ያውቃሉ እና የመሳሰሉትን በማለት ነቢዩን ማሞገስ ሐራም ነው። ከኢስላም ወደ ሚያስወጣው ሽርኩል
አክበር ደረጃም ሊደርስ ይችላል
።

ነቢዩን صلى الله عليه وسلم ከልክ አሳልፎ ማሞገስ አይቻልም።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ!


➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➧አላህ ከልብ ድርቀት ይጠብቀን
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ثُمَّ قَسَتْ قُلُوبُكُم مِّن بَعْدِ ذَٰلِكَ فَهِيَ كَالْحِجَارَةِ أَوْ أَشَدُّ قَسْوَةً ۚ وَإِنَّ مِنَ الْحِجَارَةِ لَمَا يَتَفَجَّرُ مِنْهُ الْأَنْهَارُ ۚ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَشَّقَّقُ فَيَخْرُجُ مِنْهُ الْمَاءُ ۚ وَإِنَّ مِنْهَا لَمَا يَهْبِطُ مِنْ خَشْيَةِ اللَّهِ ۗ وَمَا اللَّهُ بِغَافِلٍ عَمَّا تَعْمَلُونَ

➧ከዚያም ከዚህ በኋላ ልቦቻችሁ ደረቁ፤ እርሷም እንደ ድንጋዮች ወይም በድርቅና ይበልጥ የበረታች ናት፡፡ ከድንጋዮችም ከርሱ ጂረቶች የሚፈሱለት አልለ፡፡ ከነርሱም በእርግጥ የሚሰነጠቅና ከርሱ ውሃ (ምንጭ) የሚወጣው አልለ፡፡ ከነርሱም አላህን ከመፍራት የተነሳ ወደ ታች የሚወርድ አልለ፡፡ አላህም ከምትሠሩት ነገር ዘንጊ አይደለም፡፡
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ④④➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➭➭➭➭➭ ➛ክፍል አርባ ሁለት ➫➫➫➫➫➫➫➫ ✅“ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል” 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ➲እነዚህ የሺርክ መንዙማ ባዮች ሌት ተቀን ከአላህ ሌላ ያለን ነብይ፣ ወሊይ እና ወሊይ ተብየዎችን ሲጠሩ አይተው ጴንጤዎችም ሙስሊሙን አላህን ትቶ ወደ ነብዩላህ ኢሳ አምልኮ እንዲገባ ጥሪያቸውን በመንዙማ በማቀናበር እያቀረቡ ነው። ለጊዜው እጄ የገባው መንዙማ…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧የመጨረሻው ክፍል
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➲ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከልክ አሳልፎ ማሞገስ አይቻልም።ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከልክለውታልና።

➠ወደ ጥያቄው ጭብጥ እንመለስና የሚፈቀደውንም ሙገሳ ቢሆን በንግድነት መጠቀም ሐራም ነው። ምክንያቱም ነቢዩን صلى الله عليه وسلم ከስነ ምግባራቸው፣ ምስጉን ከሆነ ባህሪያቸውና ቅኑን መንገድ ከመምራታቸው በሚገባቸው ነገር እሳቸውን ማሞገስ ኢባዳ ነው።

➭ዒባዳ ደግሞ ወደ አላህ የሚቃረቡበት መንገድ ነው። ስለዚህ ለዓለማዊ ጥቅም
መፈለጊያ መዋል የለበትም። አላህ እንዲህ ይላል።


مَن كَانَ يُرِيدُ الْحَيَاةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا نُوَفِّ إِلَيْهِمْ أَعْمَالَهُمْ فِيهَا وَهُمْ فِيهَا لَا يُبْخَسُونَ◆ أُولَٰئِكَ الَّذِينَ لَيْسَ لَهُمْ فِي الْآخِرَةِ إِلَّا النَّارُ ۖ وَحَبِطَ مَا صَنَعُوا فِيهَا وَبَاطِلٌ مَّا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የሚሹ የሆኑትን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) በእርሷ ውስጥ ወደነሱ እንሞላላቸዋለን። እነሱም በርሷ ውስጥ ምንም አይጎድልባቸውም። እነዚያ እነርሱ በመጨረሻይቱ ዓለም ለእነርሱ ከእሳት በቀር የሌላቸው ናቸው። የሠሩትም ሥራ በርሷ ውስጥ ተበላሸ። (በቅርቢቱ ዓለም) ይሠሩት የነበሩትም በጎ ሥራ ብልሹ ነው።” [ሁድ፡ 15-16]

የሸይኽ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ንግግር እዚህ ጋር አበቃ።

➲ስለዚህ ወገኖቼ! በነቢዩ صلى الله عليه وسلم ስም የሚዜሙ “ሶለዋቶችን” በየካፍቴሪያው፣በየምግብ ቤቱ እየከፈትን ማሻሻጫ አናድርጋቸው።

➧ ማጠቃለያ
➫➫➫➫➫

➲እስካሁን ባሳለፍነው እነዚህ አገራችን ላይ ያሉ መንዙማ እና ነሺዳ እየተባሉ
ቁርኣንን አዘናግተው የሚዘመሩ መዝሙሮች ምን ያህል ሙስሊሙን ከባድ አደጋ ውስጥ እንደከተቱት አይተናል።

➲ይህን ኪታብ አጠር ብሎ እንዲዘጋጅ ስለፈለግኩ በጣም ብዙ የሚባሉ ስንኞችን ትቻቸዋለሁ። ምክንያቱም እነዚህ እራሱ ከበቂ በላይ ናቸውና። አገራችን ላይ እነዚህን አጥፊ እና ሃይማኖት አፍራሽ የሆኑ መንዙማ እና ነሺዳ ባዮች ለማህበረሰባችን እያስተዋወቁ ያሉ ተቋማትም ይሁን ግለ ሰቦች አላህን ፈርተው ለሰዎች መበላሸት ሰበብ ከመሆን ሊመለሱ ይገባቸዋል።

➧ዐሊሞች፣ ዱዓቶች፣ የዲናችን ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሁሉ እባካችሁን ሃላፊነታችንን በአግባቡ እንወጣ። በነዚህ የፈጠራ መንገዶች “ኢስላምን
እናስተምራለን” ብላችሁ የተነሳችሁ ወገኖች ደግሞ እባካችሁን ሸሪአዊ መሰረት ባላቸው የማስተማሪያ ስልቶች ላይ ተገደቡ። ከጥፋት ሃይሎች ጋር አትመሳሰሉ።


➲የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሁላችንም ሀላፍትናችንን እንወጣ። ቤታችን፣ ሱቃችን፣ ምግብ ቤት እና ካፊ ውስጥ እነዚህን መንዙማ እና ነሺዳዎች አንክፈት። ለኢስላም ውለታ እየዋልን መስሎን ኢስላምን የሚያፈርስ ተግባር እየሰራን እንዳይሆን ልንጠነቀቅ ይገባል።
የእውቀት ባለቤቶች ሆይ! አላህን ፍሩ ህዝቡን ወደ ተውሒድ እና ሱና ተጣሩ፣
ከሺርክ፣ ከቢድዓ፣ እንዲሁም ከመተላለፊያ መንገዶቻቸው ሁሉ አስጠንቅቁ።


➧አላህ በተውሒድና በሱና ላይ እጅ ለእጅ ተያይዘን በህብረት የምንጓዝ ያድርገን ።

رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ إِنَّكَ أَنتَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

“ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል። አንተ ሰሚውና ዐዋቂው አንተ ነህና።”አል በቀራህ 127

➛ነፍሴንም እናንተንም እስከ ህይወት ፍፃሜ ድረስ አደራ በተውሒድ፣ አደራ በሱና፣ አደራ የመልካም ቀደምቶቻችንን መንገድ አጥበቆ በመያዝ እላለሁ።

➧አላህ ሆይ! መጨረሻችን አሳምርልን። ምስጋና ሁሉ ለአለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምደሚያ በሙሐመድ በቤተሰባቸው፣ በባልደረባዎቻው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን።

➢መንዙማ የሚለው ፅሁፍ በዚህ ተጠናቀቀ አላህ ባነበብነው በተማርነው ተጠቃሚዎች ያድርገን! ከበደሎች ሁሉ ታላቅ በደል ከሆነው ከሺርክ አላህ ይጠብቀን! በተውሂድና በሱና ላይ አላህ ፅናቱን ይወፍቀን።✍

➧ወ ደ ቻ ና ላች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
አርበዒን 44ኛ ሐዲሥ
ኢብኑ/ሙነወር
↪️አድስ ተከታታይ የኪታብ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ አልአርበዑነ ነወዊያህ ከኢብኑ ረጀብ ጭማሬ ጋር

↪️ ሐዲሥ ቁጥር – 4⃣4⃣

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል ስድስት ➭➭➭➭➭➭➭➭ ➧የዚህ አንጡራ ሐብት ባለቤት ከአላህ የተሰጠውን ይህን ውድ ጸጋና እውነታ የማያውቅ ፣ ውስጡ በወህይ ኑር ያላበራ ፣ ምስኪንና ቂል ሆኖ እድሜውን በእንቶ ፈንቶ የሚያሳልፍ ከሆነ ወደቀብር ዜሮ ሆኖ ተጎትቶ ይገባል፡፡ ወንድሞቸ ሆይ! አኼራ መልካም ስራ ለመስራት ፉክክር የሌለባት ፣በመልካም ስራ…
➧አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ሰባት✍

➲የመልካም ስራ ምንነትና ማረጋገጫ
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

✅ፉዶይል ብን ኢያድ ረሂመሁላህ የዚህን ቁርኣን ትርጉም “አኽለሱሁ ወአስወቡሁ” በሚል አጠር ያለ ቃል ገልጾታል፡፡ “አባዓልይ ሆይ! አኽለስ እና አስወብ ማለት ምንድን ነው?” ተብሎ ተጠየቀ፡፡ እርሱም የሚከተለውን ምላሽ ሰጠ፡-

➠“አንድ ስራ ጥርት ያለ ሆኖ ሶዋብ (ረሡልን የተከተለ) ካልሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡ሶዋብ ሆኖ ደግሞ ኻሊስ (ለአላህ ተብሎ የተሰራ) ካልሆነ ተቀባይነት የለውም፡፡ ኻሊስ እና አስወብ እስካልሆነ ድረስ ተቀባይነት የለውም፡፡ ኻሊስ ማለት ለአላህ የሆነው ነው፡፡
ሶዋብ ማለት ደግም በሱና ላይ የሆነው ነው፡፡”

አላህ የሚወዳቸውና በእርሱም ያዘዘባቸው መልካም ስራዎች በርካታ ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ በዚህ ክፍል ተቀዳሚ እና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡት የኢስላም ፈርዶችና የዲን ዋጅባቶች ናቸው፡፡

▪️በሐዲስ አል'ቁድስ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"ما تقرب إلي عبدي بشيء أحب إلي مما افترضت عليه"

➲“ባሪያየ በእርሱ ላይ ፈርድ ካደረኩበት ውጭ ከእኔ ዘንድ ተወዳጅ ሆኖ የሚቃረብበት አንድም ነገር የለውም፡፡”
ቡኻሪ፡6502

➲የኢስላም ፈርዶችና የዲን ዋጅባቶች ከመልካም ስራዎች ተቀዳሚ ሆነው ነው የሚመጡት፡፡ “የትኛው ስራ ነው በላጭና በጣም ተወዳጅ?” የሚል ጥያቄ ቢነሳ መልሱ ፈርዶች ናቸው የሚል ነው፡፡ነፍል (ትርፍ ስራዎች) ከፈርድ (ግዴታ ከሆኑ ዒባዳዎች) አይቀደሙም፡፡ አንዳንድ ሰዎች ነፍል ወይም ትርፍ በሆኑ ስራዎች ላይ ትኩረት ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡ ከተውሂድ
ቀጥሎ የሚገኙ ታላላቅ ግዴታዎችን ፤ የዲን ምሰሶ የሆኑትን ሶላቶች እያጠፉ ትርፍ ሶደቃዎችን ይሶድቃሉ ፣ ከሰዎች ጋር መልካም ግንኙነት ያደርጋሉ ሌሎችንም መልካም ስራዎችን ይሰራሉ
፡፡

✅የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

▪️"من حافظ عليها كانت له نورا وبرهانا ونجاة يوم القيامة، ومن لم يحافظ عليها لم يكن له نور ولا برهان ولا نجاة، وكان يوم القيامة مع قارون وفرعون وهامان وأبي بن خلف"

➤“(ሶላትን) የጠበቀ ለእርሱ ብርሃን ፣ ማስረጃ ፣ የትንሳኤ ቀን (ከቅጣት) መዳኛ
ይሆነዋል፡፡ (ሶላቱን) ያልጠበቀ ደግሞ ብርሃን የለውም ፣ ማስረጃም (ከቅጣት)
መዳኛም የለውም፡፡ የትንሳኤ ቀን ከቃሩን ፣ ከፊርአውን ፣ ከኡበይ ብን ኸለፍ ጋር
ይሆናል፡፡”
አህመድ፡ 6576 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል መሸካቱ አል መሷቢህ፡578

➲ከመልካም ስራዎች ሁሉ ፈርዶች ይቀደማሉ፡፡ በፈርድ ተጠምዶ ከትርፍ ስራዎች የተዘናጋ ኡዝር ወይም ምክንያት ይሰጠዋል፡፡ በነፍል ወይም በትርፍ ስራዎች ተጠምዶ ከፈርድ ተግባራት የተዘናጋ ተሸውዷል ፣ ተታሏል፡፡ እንዴት ፈርድን ትቶ በነፍል ብቻ ይጠመዳል?

➠ቁርኣን ሲቀራ አድሮ የፈጅርን ሶላት ያሳለፈ ሐጢያተኛ ከሆነ ፣ አላህን
የሚያስቆጣ ተግባር ሲፈጽም አድሮ የፈጅርን ሶላት በእንቅልፍ ያሳለፈ እንዴት ሊሆን ነው? ለመልካም ስራዎች የሰጡት ትኩረትና ግምት የቱ ላይ ነው?!


➧መልካም ስራዎች ይበላለጣሉ፡፡ ቀዳሚ ሆኖ የሚመጣው ፈርድ ነው፡፡ ከፈርዶች በኋላ የትኛው ስራ ነው በላጭ የሚል ጥያቄ ቢነሳ - ሸይኹል ኢስላምና ሌሎችም የእውቀት ባለቤቶች እንደሰውየው ሁኔታና ባህሪ የሚለያይ እንጅ ለዚህ ዝርዝር የሆነ መልስ የለውም ይላሉ፡፡ ነገር ግን ጥቅል የሆነ መልስ መስጠት ይቻላል፡፡ እርሱም በላጭ የሚሆነው በዚያ ወቅት ላይ ተፈጻሚ የሆነው መልካም ስራ ከሱና ጋር የገጠመው ነው፡፡ይህ በላጭ የሆኑ ስራዎችን ለማወቅ የምንጠቀምበት ውድ የሆነ ህግና መርሆ ነው፡፡


➛ኢንሻአላህ ክፍል ስምንት
ይቀጥላል
◉◉◉◉✍

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➧አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል

ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#أذكار_الصباح

▪️«اللَّهُمَّ إنِّي أسْألُكَ عِلْمًا نَافِعًا ، وَرِزْقًا طَيِّبًا ، وَعَمَلًا مُتَقَبَّلًا»

▪️«سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ ، عَدَدَ خَلْقِهِ ، وَرِضَا نَفْسِهِ ، وَزِنَةَ عَرشِهِ ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ»

- ٣ مرَّات.

▪️«اللَّهُمَّ بِكَ أصْبَحْنَا ، وَبِكَ أمْسَيْنَا ، وَبِكَ نَحْيَا ، وَبِكَ نَمُوتُ ، وَإلَيْكَ النُّشُورُ»


▪️«اللَّهُمَّ مَا أصْبَحَ بِي مِنْ نِعْمَةٍ أوْ بِأحَدٍ مِنْ خَلْقِكَ فَمِنْكَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ ، فَلَكَ الحَمْدُ وَلَكَ الشُّكْرُ»


▪️«اللَّهُمَّ إنِّي أصْبَحْتُ أُشْهِدُكَ ، وَأُشْهِدُ حَمَلَةَ عَرْشِكَ ، وَمَلَائِكَتَكَ ، وَجَمِيعَ خَلْقِكَ ، أنَّكَ أنْتَ اللهُ لَا إلَهَ إلَّا أنْتَ وَحْدَكَ لَا شَرِيكَ لَكَ ، وَأنَّ مُحَمَّدًا عَبْدُكَ وَرَسُولُكَ»

- ٤ مرَّات.
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w