💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ስድስት ➠በርካታ ሰለፎች የሚከተለውን ይናገሩ ነበር፡ "ليتني أنجو من علمي – يقصد من العلم الذي تعلمه – كفافا ، لا لي ، ولا علي" “ለእኔም ሳይኖረኝ በእኔም ላይ ሳይኖር ከእውቀቴ (ሳልጠየቅ) ነጻ ብሆን እመኛለሁ፡፡” ➛በዚህም ፣ ሰለፎች የተስተካከለ እውቀትና ተግባር እያላቸው ምን…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሰባት
➛➛➛➛➛➛

➲ሶስተኛው፡- በእውቀቱ ለማይሰራ ሰው የተላለፈ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ባወቁት የማይሰሩ ሰዎች ዛቻና ውግዘት በቁርኣንና በሐዲስ ደርሶባቸዋል፡፡ አላህበተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ◆كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማትሰሩትን
ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡”
አስ ሶፍ፡2_3

۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

“እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን?
ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን
?” አል በቀራህ፡44
▪️ስለ ሹዓይብ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል


وَمَا أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَا أَنْهَاكُمْ عَنْهُ

“ከርሱ ወደከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡” ሁድ 88

▪️በዚህ ርዕስ ዙሪያ የቁርኣን ማስረጃዎችን ካቀረብን በኋላ ከሐዲስ ማሰረጃዎችደግሞ የሚከተለውን እናቅርብ፡-

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ኡሳማ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን የረሡል صلى الله عليه وسلم ሐዲስ አስተላልፏል፡- “የትንሳኤ ቀን አንድ ግለሰብ ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል፡፡ አህያ እየዞረ ወፍጮውን እንደሚያንቀሳቅሰው ይህ ሰው በአንጀቱ እየተጎተተ በጀሀነም እሳት ይዞራል፡፡
የእሳት ሰዎች ይመጡና “እከሌ ሆይ! ምን ሆነህ ነው?! በመልካም ስታዘን ከመጥፎ ስትከለክለን አልነበርክም እንዴ?!” ይሉታል፡፡ ግለሰቡም “አዎ! በመልካም አዝዣችሁ እኔ አልፈጽመውም ነበር፡፡ ከመጥፎ ከልክያችሁ ደግሞ እፈጽመው ነበር” በማለት ይመልስላቸዋል
፡፡ ቡኻሪ፡3267 ሙስሊም፡ 2989

▪️በኢማም አህመድ “ሙስነድ” ኪታብ አነስ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

➲“ነብዩ صلى الله عليه وسلم ኢስራእ በተጓዙበት ሌሊት ሰዎች ከእሳት በሆነ መጋዝ አፋቸውና ከንፈራቸው ሲተለተል ተመለከቱ፡፡ “እነዚህ እነማን ናቸው?” በማለት ረሡል ጠየቁ፡፡(ሁለቱ መላኢካዎች) “እነዚህ ከኡመትህ (ከተከታዮችህ) ኸጢቦች (ምክር
ሲመክሩ የነበሩ) ናቸው፡፡ የአላህን ኪታብ ያነባሉ ሰዎችን በበጎ ነገር ያዛሉ ነፍሳቸውን ግን ይረሳሉ፡፡
…” አህመድ፡13515 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሶሂህ፡291

➧በእውቀታቸው ስለማይሰሩ ፤ ሰዎችን ጥሪ እያደረጉ ስለማይተገብሩ ሰዎች በቁርኣን እና በሐዲስ በርካታ ዛቻዎች መጠዋል፡፡ በእውቀታቸው ሰውን የሚጠቅሙ ነገር ግን እነርሱ ምንም የማይጠቀሙ በርካታ ሰዎችም አሉ። የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ ልክ እንደሻማ ነው ፤ ሻማ ለሌላው እያበራ እራሱን ያቀልጣል፡፡

➛ይህን አስመልክቶ አላህን ተገዥና ታማኝ የሆነው ታላቁ ታብዒይ ሙጦሪፍ ብን ዓብዲላህ ብን አሽኺር -ረሂመሁሏህ- ከዚህ ነገር በአላህ ይጠበቅ ነበር፡፡

▪️በዱዓው ውስጥ የሚከተለውን ይናገር ነበር፡-
"اللهم إني أعوذ بك أن يكون أحد أسعد بما علمتني مني، وأعوذ بك أن أكون عبرة لغيري"

“አላህ ሆይ! አንድ ሰው ለእኔ ባሳወከኝ እውቀት ከእኔ የበለጠ እድለኛ ሆኖ ለሌሎች መመከሪያ ከመሆን በአንተ እጠበቃለሁ” ኢማሙ አህመድ ፊዙህድ፡1358

➠ይህ ታላቅ ዱዓ ነው፡፡ ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - ይህን ዱዓ “ከዱዓዎች ሁሉ ምርጥ ዱዓ” በማለት ያወድሱት ነበር፡፡ መጅሙዕ አል ፈታዋ፡14/307
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
📍 قال الشيخ/ سليمان الرحيلي وفقه الله:

فمن تمسك بالحق، فوجدت الذي عنده: قال الله، قال رسوله ﷺ، قال الصحابة، يقرر ما قرره الأئمة، فهؤلاء أهل الحق، ولو كانوا قلة.

📌قناة فوائد الشيخ أ.د. سليمان الرحيلي
Audio
🔹 تلاوة من سورة الزخرف
🔹 القارئ: #سيد_كمال
•••━══❁✿❁══━•••

🔹«وَإِذَا قُرِئَ ٱلْقُرْءَانُ فَٱسْتَمِعُوا۟ لَهُۥ وَأَنصِتُوا۟ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُون»
«ቁርኣንን በተነበበ ጊዜ እርሱን አዳምጡ፡፡ ጸጥም በሉ፡፡ ይታዘንላችኋልና፡፡»
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ④∅➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
◾️ኢማም አልአውዛእይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

✅ ሙስሊሞች ሆይ አላህ ፍሩ። የመካሪዎችን ምክር ስሙ። የገሳጮች ተግሳፅ አዳምጡ። ይህ እውቀት ዲን እንደሆነ እወቁ። በዚህ እውቀት ምን እንደምትሰሩ፣ ከማን እንደምትወስዱት፣ ማንን እንደምትከተሉና በዲናችሁ ጉዳይ ላይ የምታምኑት ማን እንደሆነ ተመልከቱ (አጢኑ)። ምክንያቱም የቢድአ ባለቤቶች ሁላቸውም አበላሾች፣ ቀጣፊዎችና አመፀኞች ናቸውና።

📚تاريخ دمشق [6/362]
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አምስት ➭➭➭➭➭➭➭➭ ➠ይህ አትራፊ የሆነው ንግድ እንጅ ተወጋጅ ፣ ከሳሪ ፣ ጸጋዋና መልካሟ የሚቋረጥ ፣ባለቤቷ በቅርብ እርሷን ትቷት የሚጓዝ የሆነችው ዱንያ ንግድ አይደለም፡፡ባሪያው ከዚህ ከሳሪ የንግድ ውልና ቃልኪዳን ባለቤቶች ሊጠነቀቅ ይገባል፡፡ ▪️ኢማም አሽ'ሻጢቢይ ረሂመሁላህ ዑለሞች ለዚህ ጉዳይ ምሳሌ እንዳደረጉ ገልጸዋል፡…
➲አትራፊው የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ስድስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

➧የዚህ አንጡራ ሐብት ባለቤት ከአላህ የተሰጠውን ይህን ውድ ጸጋና እውነታ
የማያውቅ
፣ ውስጡ በወህይ ኑር ያላበራ ፣ ምስኪንና ቂል ሆኖ እድሜውን በእንቶ
ፈንቶ የሚያሳልፍ ከሆነ ወደቀብር ዜሮ ሆኖ ተጎትቶ ይገባል፡፡
ወንድሞቸ ሆይ! አኼራ መልካም ስራ ለመስራት ፉክክር የሌለባት ፣በመልካም ስራ ድሓ ለሆኑ ሰዎች የማትመች አገር ነች፡፡

በውስጧ ያስቀደመው መልካም ስራ እንጅ ሊያግዝ የሚችል ውድ የሆነ
ጓደኛ የለም ፣ መዋዋስ የለም ፣ ሶደቃ የለም፡፡ በመሆኑም የሰው ልጅ የመልካም ስራ ድሃ ሆኖ ከጌታው ጋር መገናኘት የለበትም፡፡
ውድ የሆነውንና አላህ የሰጣቸውን የጊዜ አንጡራ ሐብት መልካም ስራ በመስራት ይጠቀሙበት፡፡

▪️ለእርሱም ክብር ይስጡ፡፡

إذا كان رأس المال عمرك فاحترز
عليه من الإنفاق في غير واجب


➧“ተጠንቀቅ! እድሜህ ከሆነ አንጡራ ሀብትህ ፤ ዋጅብ ከሆነው ውጭ አታባክን እባክህ)) ነፍሱን መካሪ የሆነ ሙስሊም አላህ የሰጠውን እድሜ ነገ አላህን ሊያስደስት በሚችል መልካም ስራ ብቻ ያሳልፍ፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنظُرْ نَفْسٌ مَّا قَدَّمَتْ لِغَدٍ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ማንኛይቱም ነፍስ ለነገ ያስቀደመችውን
ትመልከት፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡” አል ሐሽር 18

➧የመልካም ስራ ምንነትና ማረጋገጫ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲በዚህ ክፍል መልካም ስራ ምንድን ነው? አንድ ስራ እንዴት ነው መልካም ሊሆን የሚችለው? ለሚሉ ተገቢ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠትና ማብራራቱ የግድ ይሆናል፡፡

➛መልካም ስራ ፡ ማለት ግዴታም ይሁን ግዴታ ያልሆነ አላህና ረሡል صلى الله عليه وسلم ያዘዙትና የሚወዱት ተግባር ነው፡፡ ይህ ሰፊ ሜዳና ሁሉን የሚያስተናግድ በር ነው፡፡ የንግግር እና የተግባር ፤ የውጭና የውስጥ መልካም ስራዎች ሁሉ በዚህ ክፍል ይካተታሉ፡፡

➭ ይህ የንግድ ሜዳ የውድድር
ሜዳ ነው
፡፡ በዚህ ሜዳ ላይ የአላህን ረህመት የሚከጅሉ ፣ ታላቁን ምንዳ ፣ ተጸጽተው በመልካም መመለስን የሚፈልጉ ሁሉ ይሽቀዳደሙ ፣ይወዳደሩ!አንድ ስራ ፍጹም አምልኮ ለሚገባው አምላካችን አላህ እስካልሆነና አፈጻጸሙ
የረሡልን صلى الله عليه وسلم መንገድ እስካልተከተለ ድረስ መልካም ሊሆን አይችልም፡፡


➠ስራን ፍጹም ለአላህ ማድረግ የሁሉም መልካም ስራ መሰረት ነው፡፡ ሁሉም በእርሱ ላይ ነው የሚገነቡት፡፡ መልካም ስራዎች አይነታቸው ቢለያይም ቁጥራቸው ቢበዛም በኢኽላስ
ላይ (ፍጹም ለአላህ በሆነ መልኩ) ካልቆሙ ሰሪው ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡


➻በተመሳሳይ ኢኽላስ ኖሮት ነገር ግን በረሡል صلى الله عليه وسلم መመሪያ መሰረት ካልተፈጸመ ተጠቃሚ ሊሆን አይችልም፡፡ ስለዚህ ተጠቃሚ የሚሆነው ሁለቱንም - ኢኽላስና ሙታበዓን - አጣምሮ ሲጓዝ ነው፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ

“ስራው ይበልጥ ያማረ መሆኑን ሊሞክራችሁ..” አል ሙልክ፡2
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➛ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➧ፅሁፉን በተከታታይ ለማገኘት #Join
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
ኢኽዋን ፣ ሱሩሪያ

የቢድዓ ሰዎች ግለሠቦች ላይ መናገር
➻ዉዷ እህቴ ሆይ

☞ ሰውነትሽ መሸፈንሽ ስልጣኔሽ ሲሆን መገላለጥሽ ደሞ በተቃራኒው መሀይምትሽ ነው!!
ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም!

➲ነብዩﷺ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፦

➲‹‹ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች አሉ። እኔ ያላየኋቸው ወደፊት የሚመጡ! አንደኛቸው ለብሰው ያለበሱ(የለበሰቱ ልብስ ሰውነታቸውን የማይሸፍን) አካሄዳቸው እና እንቅስቃሲያቸው ወደ ፀያፍ ተግባር ያዘነበሉ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ሴቶች ናቸው።

➲እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም፡፡››

📚ሙስሊም ዘግበውታል
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሰላሳ ሰባት ➲ስንታመም የሚያድነን ማን ነው? ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➠የሚከተለው የሺርክ መንዙማ ደግሞ በጉራጊኛ ቋንቋ ከአላህ ውጭ አቡል ጀበል የሚባለው ግለሰብ የእግርም ሆነ የእጅ ቁስላችንን ያድነናል ብለው የሚያምኑበት እና እሱን ሰውየውን በቀጥታ የሚለምኑበት ነው። ➴➴“አቡል ጀበል ሺሊላህ አቡል ጀበል ሺሊላህ፣ አሁን ትሆኝ እና መላ፣ …
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

➳ክፍል ሰላሳ ስምንት
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➧የታደለው ገበር ከአላህ ዘንዳ ሲር”
“ለካ ገረዋ ላይ አብርቷል ጀምበር፣
ሲፈቱ መለኪይ ዛቱ የበሸር፣
ተብሎ አላህ ዘንዳ በሺር ወአንዚር፣
ጎራ እማይጋርደው ይዟል መነጠር፣
ይናገር ነበረ የዟሂር የሲር፣ ይገልጠው ነበረ የኸልቁን ኸጢር”


➲ ለገሂዳም ጃማ ስንቱ ጉድ ነበር፣
እነ ነብዩ ሀድራ የተባሉ አብሽር፣ ባልከው ይሁን ያለው ገና ሲፈጠር” እጣው እንደ ነቢ...” እስኪ ይህን ድፍረት ተመልከቱ፡፡ “ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) አትጣሩ” ሲባሉ “ክብራቸውን አጎደፋችሁ፡፡


➩ እሳቸው እንደኛ ተራ ሰው አይደሉም” እያሉ ፈጥረው የሚወነጅሉ ሰዎች እዚህ ግን አንድን ተራ ምስኪን ከነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ጋር እያመሳሰለ ነው፡፡

➧እነዚህ ስንኞች በደካማ ፍጡሮች ላይ ድንበር ማለፍ፣ የጌታን ክብር ማጉደፍ፣ ፍጡሮችን ከፈጣሪ ጋር ማመሳሰል አለባቸው። በዚያ ላይ ያፈጠጡ ያገጠጡ ውሸቶች ታጭቀውባቸዋል። አላህ እሱ ላይ የሚዋሹ ሰዎችን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፡-

وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۗ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ

➬በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀጾቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው እነሆ በደለኞች አይድኑም።” [አልአንዓም፡ 21]

➲ከኢልመል ገይብ ጋር የሚጋጩ ስንኞች ''ኢልመል ገይብ” ማለት የሩቅ እውቀት ማለት ነው። የሩቅ እውቀት በጠቅላላ የአላህ ነው። አላህ እንዲህ ይላል፡-
قُل لَّا يَعْلَمُ مَن فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ الْغَيْبَ إِلَّا اللَّهُ ۚ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ

«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም» በላቸው፡፡'' [አንነምል፡ 65]

عن ابن عمر رضي الله ‏عنهما ‏أن رسول الله صلى الله، عليه وسلم قال مفاتيح
الغيب ‏خمسة لا ‏يعلمها ‏ إلا الله، لا يعلم ما في غدٍ الا الله، ولا يعلم ما تغ؜ ‏
الأرحام ‏إلا الله، ولا يعلم متى يأتي المطر احد ‏إلا الله، ولا تدري نفس بأي ‏الأرض تموت، ولا يعلم متى تقم الساعة ‏ الا الله،


➩ከዐብደላህ ኢብን ዑመር (ረድየላሁ ዐንሁማ) የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል “የሩቅ ሚስጥር ቁልፍ አምስት ናቸው። አላህ እንጂ ማንም የማያውቃቸው።

➧ ነገ ምን እንደሚከሰት አላህ እንጂ ማንም አያውቅም። ሆድ ውስጥ (የተረገዘው) ምን እንደሆነ አላህ እንጂ ማንም አያውቅም። አላህ እንጂ መቼ እንደሚዘንብ ማንም አያውቅም። ነፍስ የት እንደምትሞት ማንም አያውቅም። የምፅዓት ቀን መቼ እንደምትቆም አላህ እንጂ ማንም አያውቅም።”

➲ኢማሙ አል ቡኻሪ ዘግበውታል።
የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم
) “የሩቅን ሚስጥር (ነገር) ከአላህ ውጭ የሚያውቅ የለም” ብለዋል። ኢማሙ ጠበራኒ ዘግበውታል።

አላህ ከመልክተኞቹ ለፈለገው የፈለገውን የሩቅ ሚስጥር ያሳውቃል። ይህ ሆኖ ሳለ እውነታው ተመልክቱ የሚከተሉት ስንኞች እንዴት ከእስልምና አስተምህሮት እንደሚጋጩ፡-

“አልዩ ሀይደር
ነበረ ለነቢ ማኖሪያ ሚስጥር፣
ኢልመልገይብ ከሱ ይጠየቅ ነበር።”
ማን ነበር ጠያቂው? የታለስ ማስረጃው?


“ሺሊላህ ኢማሙ ግቡልን፣
መተኮስ ጀመረ የፍቅር ተኳሹ፣
በወዳጆቹ ልብ እንደ ምንጭ ፈሳሹ፣
የረሱል ምስለኔ አላጋውን ወራሹ፣
የልብን መርማሪ እሱ ነው ፈታሹ”
“ሺሊላህ ሸህ ሙሃመድ ባህሩ፣
ለጠራው ደራሽ ነው ምን ቢርቅ አገሩ፣
እኔስ ይገርመኛል የሰው ነገር፣

◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
♦️ تلاوة من سورة المؤمنون
♦️ القارئ: #صالح_الفالح
•••━══❁✿❁══━•••
✅ ማራኪ ቲላዋ
✅ የቁርአን ግብዣ
♦️قال ابن القيم رحمه الله:

📌"إنَّ الكريم المحسن أشرح النَّاس صدرًا، وأطيبهم نفسًا، وأنعمهم قلبًا، والبخيل الذي ليس فيه إحسان أضيق النَّاس صدرًا، وأنكدهم عيشًا، وأعظمهم همًّا وغمًّا".

📚(زاد المعاد ج٢ ص٢٢
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
إنا لله وإنا إليه راجعون
اللهم أجرنا في مصيبتنا واخلفنا خيرا منها
توفي شيخنا العلامة صالح اللحيدان عضو هيئة كبار العلماء.

🔶 إن القلب ليحزن وإن العين لتدمع ولا نقول إلا ما يرضي ربنا.
🔹 أعظم الله أجركم يا أهل السنة