💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

🔹የአላህ እዝነት በተመለከተ

➰ክፍል ③⑤➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➲ሸይኽ ፈውዛን - አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና - ዒልም ፈላጊ ተማሪዎችን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፦

➧እውቀትን ከመፈለግ አትሰልች።
አያያዝህ ትንሽ ቢሆን እንኳ እውቀትን ፈልግ። መልካም ስራ ከመስራት ጋር ሲሆን ትንሹም በረካ አለበት።


እውቀት ፍለጋ ላይ መቀጠል ያለጥርጥር ኸይር ነው። እውቀት ፍለጋ ዒባዳ ነው።እውቀት ፍለጋ ግዴታ ካልሆኑ ዒባዳዎች የበለጠ ነው።"

[አልኢጃባቱል ሙሃማህ፡ 84]
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሰላሳ አንድ ➻➻➻➻➻➻➻➻ ➢“ታመን ነበር ፈወሱን፣ ተርበን ነበር አጎረሱን፣ ታርዘን ነበር አለበሱን፣ ነብዩ የኛ ወለላ፣ የፍጡራን ሁሉ ጥላ፣ ጨለማ ውስጥ ላሉ ብርሀን፣ በሽርክ ለተጎሳቆሉ ኢማን፣ ለተሰቃዩ መጠጊያ፣ ለዋለሉት ሁሉ መርጊያ፣ በርሳቸው ጭንቀት በረካ፣ ዓለም…
➳መንዙማ
➬➬➬➬➬

➩ክፍል ሰላሳ ሁለት


➲ ታጥቀን ተሸምረን ዛሬ ጠራናችሁ፣
መቼም ለእርዳታ ነው ጀሊል ሲፈጥራችሁ።”


➧ “እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው፣
እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው፣
እመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፣እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው፣ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፣ አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ፣በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ፣ ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር”
“የፍቅርህን ጥም አይበርድም በውሃ፣
አንተን የወደደ አይባልም ደሃ፣ ትረዳ የለም ወይ ከየትስ በረሃ፣ ሊጋባ ነህ አሉ ያረሱል ያጣሃ” እነዚህን አካላት የሚጣራ ሁሉ ያለጥርጥር ጠላት ነው እያፈራ ያለው
። አላህ እንዲህ ይላል፡-


وَإِذَا حُشِرَ النَّاسُ كَانُوا لَهُمْ أَعْدَاءً وَكَانُوا بِعِبَادَتِهِمْ كَافِرِينَ

➩ ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ (ጣዖቶቹ) ለእነርሱ ጠላቶች ይኾናሉ፡፡ (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡ [አልአሕቃፍ፡ 6]


➧ ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) በዘመቻዎቻቸው፣ በችግሮቻቸው ሲረዳቸው የነበረው አላህ ብቻ ነው። እርዳታን ሲለምኑ የነበረውም ከሱ ብቻ ነበር። ዛሬ “ከኛ ወዲያ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ወዳጅ ላሳር” የሚሉ አካላት ግን በሸሪዐቸው ላይ ሸፍተዋል። እርዳታ የሚጠየቀው ከፍጡራኑ ሁሉ መጠጊያ ከአንድ አላህ ብቻና ብቻ ነው። ሱረቱል ፋቲሃ ላይ “አንተን ብቻ እናመልካለን። በአንተም ብቻ እንታገዛለን” እያልን ቃል ከገባን በኋላ ቃላችንን ብናፈርስ ተጎጂዎቹ እኛው ነን።


➲ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን። እስኪ የተውሒዱን አስተማሪ ነብዩን
የተከተለ ሰው፣ የተውሒዱን ሃይማኖት ኢስላምን የመረጠ ሰው እንዴት ብሎ (صلى الله عليه وسلم) ከአላህ ውጭ በዚህ መልኩ ይጣራል? “ረዳቴ ማን ነው ከናንተ በቀር?”፣ “በናንተ የሸሸ
የቂን ነው ማማሩ”፣ “አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ”፣ “ለቸገረን ሁላ ዛሬ ጠራናችሁ”፣ “በሁሉም ሸሸሁኝ አንድ እንኳን ሳይቀር” ይህን የሺርክ ዶፍ የሚያዘንብ ሰው “በአንተንም ብቻ እንታገዛለን” እያለ ዘወትር በየሶላቱ የሚገባውን ቃል ኪዳን እያፈረሰ ነው
።


➳“በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማመሩ” ይህም ሺርክ ነው። የሚሸሸው ወደ አላህ ብቻ ነው። ከአላህ ውጭ መሸሻ የለም። አላህም “ወደ አላህ ሽሹ” ብሏል። [አዝዛሪያት፡ 50] ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ) ሺህ ጊዜ ቢወተውት የሞተ ፍጡር አይሰማውም። አላህ እንዲህ ይላል፡-



إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا مَا اسْتَجَابُوا لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ


➧ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡ [
ፋጢር፡ 14]


➧“የአበራ ሙዝ አባት የማይደፈር፣
አቤት ይታይልኝ ምነው የኔም ዱር፣
ዙሩልኝ ጌቶቼ በአውን በነስር፣ ከጃችሁ ከጅየ ቆሜያለሁ ከበር፣ በናንተ የሸሸ ምን ጊዜም አያፍር፣ ሀጃየን አውጡልኝ በዟሂር በሲር” የአብሬት ሸይኽ የደርግ መንግስት አፍኖ ወስዷቸው ይሄው እስካሁን ድረስ ያሉበት አይታወቅም።



➲ደርግ እንደገደላቸው ይነገራል። እዚህ መንዙማ ላይ “የማይደፈር” ሲል ይጠራቸዋል። እውነታው ግን ሃይማኖት የለም የሚለው የሶሻሊዝም ተከታይ
የነበረው ደርግ ወስዶ እርምጃ በመውሰድ ስንት ሰው እያመለካቸው ደፈራቸው።


➩ታድያ እንዴት ይሆን ከደርግ እራሳቸውን ማስጣል ያልቻሉትን የአብሬት ሸይኽ “የማይደፈር” የሚሏቸው “ድረሱልን” እያሉ የሚማፀኗቸው? ቢችሉ ከሌላው ቀድሞ ለራሳቸው በተረፉ ነበር። “ከራስ በላይ ንፋስ” ይላል ያገር ሰው።


➧የአበራ ሙዝ አባት በመባል የሚታወቁት የአብሬት ሸይኽ ሁለተኛው ናቸው፡፡ ለእኝህ ግለሰብ እራሳቸውን ታመው በተኙበት ከሙሪዳቸው (ከተከታያቸው) አንዱ ሰባት ጊዜ እሳቸው የነበሩበትን ቤት ዞሮ “ፊዳ ልሁን እኔ” በማለት እራሱን አርዶ ገድሏል፡፡ በሸይኹ ላይ ከባባድ ድንበር ማለፎች ሰዎች ሲፈፅሙ ይታያል፡፡ በተለይ ጉራጊኛ ቋንቋ የሚችሉ የተውሒድ ተጣሪዎች አብሬት አካባቢ የሚሰራው ከባድ ሽርክ ሊያስጠነቅቁ ግድ ይላቸዋል፡፡
◉
◉
◉
◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➷➷➷➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
❥...ሴት ልጂ!
➫➫➫➫➫➫

➴ፀጥ ስትል ብዙ ሚሊዮን ሀሳቦችን እያሰበችና እያብሰለሰለች መሆኑ
ይግባህ።!


➴አፍጣ ስታይህ ለምን እንደዚህ እንደምትወድህ እና ይህን ሁሉ መሰዋትነት እንደምትከፍልህ እያሰበች ነው።!

➴አብሬህ እቆማለሁ ስትልህ ማዕበል እንኳ ቢመጣ አልንቀሳቀስም ማለቷ
ነው።!


➧አትጉዳት ወይም በተሳሳተ መንገድ አታስባት ......አንተ ስትራብ ተርባ ፣
ስትቸገር ተቸግራ ፣ ስትራቆት ተራቁታ ፣ ገበናህን ሸፍና የምትኖረው ሚስትህ
የልጆችህ እናት ሚስትህ ናት።!


➴ኧረ እውነታውን ልንገርህ ☞ሚስትህ ማለት የቤትህ ብርሀን ናት።
ስለዚህ☞አክብራት፣ውደዳት፣ፍቅር ስጣት!።


 https://t.me/Abulabashsen

👆ይቀላቀሉ ጡሩ ጡሩ ትምህርቶችን ያገኛሉ

➛እኔም አልኳችሁ ተግባራዊ አድርጓት አትጎዱም ብትጠቀሙ እንጂ!
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
🌸🌤አሏህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል።በአንተ ለምሽት እንበቃለን። በአንተ ህያው ሆነናል። በአንተም እንሞታለን።መመለሻ ወደ አንተ ነው።
☀️

اللهم نسألك خير مافي هذا اليوم وخير ما بعده وأعوذ بك من شر ما في هذا اليوم وشر مابعده 🌸🌸🌸

አልሀምዱሊሏህ ለንጋት በቅተናል
በእዝነትህክ ውቧን ፀሀይ አይተናል
አመስጋኝ ሁነን አንግተናል
አስታዋሽ አመስጋኞች
ባንተ ትእዛዝም ደስተኞች
ባንተ ተወካዬችም ሁነናል
ምስጋና ስግደት ላንተ ይገባሀል
……!!

ጌታችን ሆይ ከፀጋዎችህ በእኛ ላይ
አድርግ በዱኒያም በአኬራም
ምህረትህን ለግሰን አሚን!

🌹 መልካም ቀን🌹
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
حكم التهنئة بعيد الميلاد (الكريسماس) الشيخ/د.صالح الفوزان 2017
الدعوة والإرشاد - العارضية
✅ ካፊሮች በኢዳችን እንኳን አደረሳችሁ ቢሉን ራሱ በነሱ ኢድ ጊዜ እንኳን አደረሳችሁ ማለት አይፈቀድም። ምክንያቱም ኩፍራቸው ማፅደቅ ስለሆነ

🎙فضيلة الشيخ صالح الفوزان حفظه الله
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

🔹አላህ አዛኝና በእዝነት እንደሚገለፅ

➰ክፍል ③⑥➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✍ ከሚከተሉት ውስጥ መራቲቡ ዲን "مراتب الدين" ከሚባሉት ውስጥ ያልሆነው የቱ ነው⁉️
Anonymous Quiz
19%
ኢስላም
22%
ኢህሳን
3%
ኢማን
56%
ተቅዋ
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➩ክፍል ሰላሳ ሁለት ➲ ታጥቀን ተሸምረን ዛሬ ጠራናችሁ፣ መቼም ለእርዳታ ነው ጀሊል ሲፈጥራችሁ።” ➧ “እኝህን ሳዳቶች ድረሱ አንበላቸው፣ እሱ ወደደና እሱ መረጣቸው፣ እመሀባው ባህር ሺህ አመት አስዋኛቸው፣እሱ ወደዳቸው በፊት ሳይሰራቸው፣ዩሂቡሁም ወዩሂቡነሁ አላቸው ጀባሩ፣ አቤት እርዱኝ ይላል የቤት ልጅ አሽከሩ፣በናንተ የሸሸ የቂን ነው ማማሩ፣ ጥላቸው ጠባቂ በሁለት አገር” …
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

➣ክፍል ሰላሳ ሶስት

➲“ዱርር” ማለት ጉዳት ማለት ነው። ጉዳታችንን እንዲያነሳልን የምንጠይቀው አላህን ብቻ ነው። ይህ ነው የነብያት አስተምህሮት። ብዙ መከራዎችን ስላስተናገዱት ነብዩላህ አዩብ (ዐለይሂ-ስሰላም) አላህ እንዲህ ይላል፡-

۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ

➩አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡



➧"ነስር” ማለት ደግሞ “ድል” ማለት ነው። ሁለቱንም የሚሰጠው አንድየው ጌታ ብቻ ነው"የሀድራ ጦያራ ይዞ የሚበር፣ ሲጠሩት ፈጣን ነው ቶል የሚሀድር፣ ተምኪን የተሰጠው ዟሂር ወባጢን፣ እኔ ያለሁበት እክጀላ በር፣
ቀድሬም አያደርሰኝ መቃም ለመቁጠር፣ ስንቱን አሳደገው ገና በነዞር (በእይታ)፣ ፈይዱ ከአፍ ሲፈልቅ ይዐጂብ ነበር፣ እንኳን ሰው መላኢካ ያደምጠው ነበር።”



➲"አንቱን የሚጠራ እሱ ልቡ ጠራ፣
የለበት መከራ አኼራ ሲጥጠራ”
ለጭንቅ ለችግር የሚጥጠራው አላህ ብቻ ነው። አላህን ትቶ ሌላን የሚጠራ ልቡ በሺርክ የቆሸሸ ነው። ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ መኖርያው እሳት እንደሆነ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ነግረውናል።



➣"እንዳንቱ የሚሆነኝ መቼም አላገኝ፣
ዘይኔ ቅረቡኝ ጣል አታድርጉኝ”
"ካንቱ ጋር የዋለ ምንኛ ታደለ፣
ነቢ ነቢ እያለ ጭንቀቱ ቀለለ፣ እኔም ልጥራዎት ጨንቆኛልና፣ ያምስኪ መዲና ጋየተል ሙና”። ይጣራል ይጮሃል የናንተው ለፍላፊ፣ የሊበኖቹ ልጅ ሙሀመድ ሻፊ፣ በዱንያም በአኼራም ሁኑልን ደጋፊ” እውነት ይሄ ለፍላፊ ያለመውን ያገኛል?
ሃያሉ ጌታ እንዲህ ይላል፡-

أَيُشْرِكُونَ مَا لَا يَخْلُقُ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
وَلَا يَسْتَطِيعُونَ لَهُمْ نَصْرًا وَلَا أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

➧“ምንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ ላይ) ያጋራሉን! ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን?!)”
[አልአዕራፍ፡ 191- 192]

"ና በሉት ኸይረል ወራ፣ ሳልሞት ሳልሄድ አኼራ፣ ያቺን ረውዳ ዚያራ፣ የጀነትዋን አርዴ” "ካልመጣሁኝ መዲና፣እኔስ የለኝም ጤና፣ እንድሆንሎት ደህና፣ ቶሎ ጥሩኝ አህመዴ፣ኒዛሙል መደዴ” "ዘይኔ ይበቃናል ኑ በሉን መዲና፣ ሀይ እንድናደርገው ሁሌ የርሶን ሱና”
"ቀልቤእኮአንቱጋርነው፣ ፍላጎቱ ረውዳ ነው፣ ዘይኔ ና በሉት ፈጥነው፣ የቀረውን ጀሰዴን” መካና መዲና በእሳትና በውሃ ቢታጠርም፣ እርሶ ይጥሩን እንጂ አንቀርም።” ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢ፣ ሃቢቢ ሃቢቢ ሃቢቢ፣ መዲና ና ይበሉኝ”

➲ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ወደ መቃብር ከገቡ በኋላ ይህን የማድረግ ስልጣኑ አላቸውን?በጭራሽ!! ስልጣን እና ድርሻ የላቸውም። አለምን ማስተናበር ህያው የሆነው የማይሞተው አላህ ስልጣን ብቻ ነው።

"የፍቅር ነጋሪ ዝም ብየ ልምጣ፣ “
እባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፣
ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)
◉

◉
◉✍ኢሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይጠቀማሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Kitabu Tewhid #53
Ibnu Munewor
↪️ ተከታታይ የኪታቡ ተውሒድ ደርስ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

↪️ርዕስ باب قول الله تعالى (إِنَّمَا ‌ذَٰلِكُمُ ‌ٱلشَّيۡطَٰنُ يُخَوِّفُ أَوۡلِيَآءَهُۥ فَلَا تَخَافُوهُمۡ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤۡمِنِينَ)

↪️ ክፍል 5⃣3⃣↩️
〰〰〰〰〰〰

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔻حفظه الله تعالى
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✅ اسْتَحْوَذَ عَلَيْهِمُ الشَّيْطَانُ فَأَنسَاهُمْ ذِكْرَ اللَّهِ
◾️በእነርሱ ላይ ሸይጧን ተሾመባቸው፡፡ አላህ ማስታወስን (ዚክር) አስረሳቸው፡፡
✅ أُولَـٰئِكَ حِزْبُ الشَّيْطَانِ
◾️እነዚያ የሰይጣን ጭፍሮች ናቸው፡፡
✅ أَلَا إِنَّ حِزْبَ الشَّيْطَانِ هُمُ الْخَاسِرُونَ
◾️ንቁ! የሸይጧን ጭፍሮች ከሳሪዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡

📚(ሱረቱ አል-ሙጀድላህ - 19)
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③⑦➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➧አላህ ሆይ! በዲናችን ላይ እርግጠኛነትን (የቂንን) ስጠን!!

➲ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሷሊህ አል ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል:–

“አንድ ሰው በቁርኣን ላይ ያለው እምነት በጠነከረ ቁጥር አላህ በሌሎች መፅሃፎች ሊያገኘው የማይችለውን የእርግጠኛነትን ማስረጃ ይከፍትለታል፣ በመሆኑም እናንተንም ራሴንም ቁርኣንን እያስተነተኑ በማንበብ በቁርኣን በመተግበር ላይ ሙሉ የሆነን ማነሳሳትን አነሳሳለሁ፣ እሲቲ ወደ ቁርኣን ተመለስና ለልብህ ከኢማን፣ከልብ መከፈት፣ ከልብ ኑር፣ ከፊት ኑር፣ ምን እንደሚያስገኝልህ ተመልከታት፣ በዚህም ተሞክሮን ውሰድ።”

ምንጭ:– ሸርህ አልካፊየቱ ሻፊያህ 4/166

➧ውድ እህቶቼ በአሁኑ ሰአት ማሻአላህ አብዘሃኞቻች የሱና እህቶች ኪታብን ለመቅራት የምናደርገውን ጥረት ያክል ቁረአን ላይ እያደረግን አይደለም! ኪታብ መቅራታችን እንዳለ ሆኖ እያለ ከቁረአንም መራቅ የለብንም ቁረአንም ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን!

➧መሀፈዙ ቢከብደን በቲላዋ እያስተነተን መቅራት አለብን አላህ ያግራልን ሁላችንንም ቁረአን በመቅራት ላይ አደራ እላችኃለሁ ያአኽዋቲ ቁረአን የደረቀች ልብን ታረጥባለች ወደ ጌታችን ታቃርበናለች!!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➣ክፍል ሰላሳ ሶስት ➲“ዱርር” ማለት ጉዳት ማለት ነው። ጉዳታችንን እንዲያነሳልን የምንጠይቀው አላህን ብቻ ነው። ይህ ነው የነብያት አስተምህሮት። ብዙ መከራዎችን ስላስተናገዱት ነብዩላህ አዩብ (ዐለይሂ-ስሰላም) አላህ እንዲህ ይላል፡- ۞ وَأَيُّوبَ إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ أَنِّي مَسَّنِيَ الضُّرُّ وَأَنتَ أَرْحَمُ الرَّاحِمِينَ…
➭መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሰላሳ አራት
〰〰〰〰〰〰

➲ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ወደመቃብር ከገቡ በኋላ ይህን የማድረግ ስልጣኑ አላቸውን? በጭራሽ!! ስልጣን እና ድርሻ የላቸውም። አለምን ማስተናበር ህያው የሆነው የማይሞተው አላህ ስልጣን ብቻ ነው።

➴“የፍቅር ነጋሪ ዝም ብየ ልምጣ፣
እባካችሁ ይቅር ሌላው ሀተታ፣
ጠዋትም ማታ ጀበል ወትውቱ (አጥብቃችሁ ጠይቁ)” ምንም አይነት ሃተታ፣ ምንም አይነት ውትወታ አይፈይድም።


➛ከኢስላም አምስቱ ማእዘናት አንዱ ሐጅ ነው። ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ያስተማሩት “የቻለ ሰው ቤቱን ይጎብኝ” ብለው ነው እንጂ “ያልቻለ ሰው እኔን ይማፀን” ብለው አይደለም። ውትወታችን ሊሆን የሚገባው ወደ ሁሉን ቻዩ ጌታ ነው።

➴“የአላህ አፈ ንጉስ የአላህ ቢተወደድ፣
ኧረ የት ይገኛል እንደ ሙሐመድ፣


➷➷ወዳጅ የሚረዳው ሲገቡ በላህድ (በቀብር ውስጥ)”

“አንተ የጠይባው ነጋዴ፣
ሰላም በልልኝ አህመዴን፣
አንቱ የጅብሪል ጓደኛ፣
አትርሱን ቀብር ስንተኛ”

➮ቀብር ስንተኛ እራሳችን በነፍስ ወከፍ ለተጠየቅነው ጥያቄ መልስ እንሰጣለን እንጂ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለማንም ቀብር ውስጥ ምንም ማድረግ አይችሉም። እያንዳንዱ ሰው ቀብር ውስጥ መልካምም ይሁን መጥፎ የራሱን ስራ ያገኛል።


➷➷“ያሙሀመዲ ያሀቢቢ፣
ያሙሀመዱ ኩን ጠቢቢ (ዶክተሬ ሁኑ)፣
ወአጂርኒ ሚን ለሂቢ (ከሚንቀለቀለው እሳት ጠብቁኝ)፣
ኢነ አውዛሪ ሲቃል (ወንጀሎች ከባድ ናቸውና)”


➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ግን ዘመዶቻቸው ለሳቸው ባላቸው ቅርበት እንዳይሸወዱ ይልቁንም ተውሒድን በመያዝና ከሺርክ በመራቅ እራሳቸውን እንዲያተርፉ አላህ እንዲህ ሲል አሳስቧቸዋል፡-

وَأَنذِرْ عَشِيرَتَكَ الْأَقْرَبِينَ الشعراء: ٢١٤

“ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህን አስጠንቅቅ!!”
[አሽሹዐራእ፡ 214]

➲ይህቺ አንቀፅ በወረደች ጊዜ ነብዩ (صلى الله عليه وسلم” (የቁረይሽ ህዝብ ሆይ! ነፍሳችሁን ከአላህ ግዙ። ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይዳችሁም። የዐብዱል ሙጦሊብ ቤተሰቦች ሆይ! ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይዳችሁም።የዐብዱል ሙጦሊብ ልጅ ዐባስ ሆይ! ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይድህም። የዐብዱል ሙጦሊብ ልጅ ሶፍያ ሆይ! ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይዳችሁም። የመልእክተኛው ልጅ ፋጢማ ሆይ! ከገንዘቤ የፈለግሽውን ጠይቂኝ። ከስተአላህ በኩል ምንም አልፈይድሽም።” [ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡
206]

➷➷ወንድሜ ሆይ እህቴ ሆይ! ወገኖቼ ሆይ! ከሰማይ በወረደው ማሳሰቢያ መሰረት ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ለቅርብ ቤተሰቦቻቸው ለኔ ባላችሁ ቅርበት እንዳትሸወዱ። በተግባር
እራሳችሁን አትርፉ እያሉ ነው። ለአብራካቸው ክፋይ ለፋጢማ ረዲየላሁ አንሃ ያልፈየዱትን ላንተ የሚፈይዱ ይመስልሃልን? ከልብ ሁነህ አስተውል
!!

➴➴“ነቢ አንቱን እያለ፣
ቀልቤ ጥሎኝ ዋለለ፣
ወዳሉበት ደወለ፣
ሄሎ በሉት አሕመዴ”

➴➴ “አንቱ ኖት ረሃቤ ጥሜ፣
ልንገሮት አስቀድሜ፣
ያላንቱ አይሞቅም ደሜ፣
ግቡልኝ በጀሰዴ”


➴➴“ሰብርም የለኝም አለሁኝ ታምሜ፣
መንገዱ ጠፍቶብኝ አልቻለም አቅሜ፣
ጉልበቴ ብርታቴም ባንቱ ነው መቆሜ”

➴➴“ሳዳቴ አደራ አሁን ለምነናል፣
ሁላችን በጅምላ አድሉን ብለናል፣
ዱስቱር ዱስቱር ብለን እዛው አፍጠናል፣
አትጨክኑብን እርሶን ለምነናል፣
ይኸው ደውለናል በቴሌ ግራሙ ግቡልን፣
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል


➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1