💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬ ➧ክፍል ሀያ ስድስት አቡል ጀበል ካልነበር የተገኘ ነውና ጥንት አልነበረም። ፍጡር ነውና ይሄው ሞቷል። ዛሬም የለም። አላህ ከቀብር እስከሚቀሰቅሰው ድረስም ቂያማ ድረስ አይኖርም። ➧ታዲያ “ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ” ማለት ምን የሚሉት ቅጥፈት ነው?!! አይደልም አቡል ጀበል ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ሞተዋልኮ። የልቅናው እማ አሁን ልፈስረው፣…
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

➳ክፍል ሀያ ሰባት

➲ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው።
ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው።

➩ይሁንቦት በነሰይድ ዳና፣ መደሻችን (መደሰቻችን) ይሁን ያለንበት ዘመን፣ ቆሞ ቀር ሆነናል ባለንበት ዘመን፣እኩሉን ሞሽሩን እንዳንቀር ተርበን” ከአላህ ተዓምር ውስጥ ወንድ እና ሴትን ማጋባቱ በመካከላቸው ውዴታና መተዛዘንን ማድረጉ ነው።

➧ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ትዳር የሰጣቸው አላህ ነው። ዛሬ ግን ይሄው እዚህ ላይ እንደምናየው “እኩሉን ሞሽሩን” ብለው ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) ዳሩን ሲል፤ ከአላህ ውጭ ይጠይቃሉ። አላህ ብቻ ሊያደርገው በሚችለው ጉዳይ ፍጡራንን መጥራት ሺርክ እና ኩፍር ነው።

➲የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) “ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ እሳት ገባ” ብለዋል። አላህ ከፍጡሮቹ ስልጣኑን አሳልፎ የሰጠው አለን?

➩የአላህ ጌትነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከላይ አሳልፈናል። አገራችን ላይ ካሉ መንዙማዎች ውስጥ ለምሳሌነት የሚከተሉት አላህ ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ እንደሰጠ ይዋሻሉ። ጥያቄው አላህ ምን ሆኖ ነው ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ የሚሰጠው? ጌታችን አላህ ማለት ህያው፣ የማይሞት፣ በራሱ የተብቃቃ ፍጡራኑን የሚያብቃቃ፣ አሸናፊ፣ የማይተኛ፣ የማያንቀላፋ፣ ሿሚ፣ ሻሪ፣ የፍጡራኑ ሁሉ መጠጊያ ነው።

➲ አላህ ከእርሱ ውጭ የሚመለኩት በሰማይም በምድርም ምንም እንደማይችሉ፣ ሽርክናም እንደሌላቸው፣ አጋዦቹም እንዳልሆኑ፣ እርሱ ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጂ እንደማያማልዱም እንዲህ ሲል ይነግረናል፡-

قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍ

«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡[ሰበእ፡ 22]


وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ


➳ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡ [ሰበእ፡ 23]

የሚከተሉት ስንኞች ላይ አላህ ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ እንደሰጠ ተደርጎ ይቀጠፍበታል። አላህ ላይ መዋሸት ደግሞ ከባድ ቅጥፈት ነው።
እስኪ አላህ ይህንን እንዳለ ምን አሳወቀው

أَطَّلَعَ الْغَيْبَ أَمِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا

ሩቁን ምስጢር ዐወቀን ወይስ አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ [
መርየም፡78]

➣ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛አንብብ ያነበበ ተጠቀመ!

➧ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
وَعِبَادُ الرَّحْمَٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا

የአልረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡
وَالَّذِينَ يَبِيتُونَ لِرَبِّهِمْ سُجَّدًا وَقِيَامًا

እነዚያም ለጌታቸው በግንባራቸው ተደፊዎችና ቋሚዎች ኾነው የሚያድሩት ናቸው፡፡

وَالَّذِينَ يَقُولُونَ رَبَّنَا اصْرِفْ عَنَّا عَذَابَ جَهَنَّمَ ۖ إِنَّ عَذَابَهَا كَانَ غَرَامًا

እነዚያም «ጌታችን ሆይ! የገሀነምን ቅጣት ከእኛ ላይ መልስልን ቅጣቷ የማይለቅ ነውና» የሚሉት ናቸው፡፡


إِنَّهَا سَاءَتْ مُسْتَقَرًّا وَمُقَامًا

እርሷ መርጊያና መቀመጫ በመኾን ከፋች! (ይላሉ)፡፡

وَالَّذِينَ إِذَا أَنفَقُوا لَمْ يُسْرِفُوا وَلَمْ يَقْتُرُوا وَكَانَ بَيْنَ ذَٰلِكَ قَوَامًا

እነዚያም በለገሱ ጊዜ የማያባክኑ የማይቆጥቡትም ናቸው፡፡ በዚህም መካከል (ልግስናቸው) ትክክለኛ የኾነ ነው፡፡

وَالَّذِينَ لَا يَدْعُونَ مَعَ اللَّهِ إِلَٰهًا آخَرَ وَلَا يَقْتُلُونَ النَّفْسَ الَّتِي حَرَّمَ اللَّهُ إِلَّا بِالْحَقِّ وَلَا يَزْنُونَ ۚ وَمَن يَفْعَلْ ذَٰلِكَ يَلْقَ أَثَامًا

እነዚያም ከአላህ ጋር ሌላን አምላክ የማይገዙት፣ ያችንም አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ ያለ ሕግ የማይገድሉት፣ የማያመነዝሩትም ናቸው፡፡ ይህንንም የሚሠራ ሰው ቅጣትን ያገኛል፡፡
➛ከቁረእን ጋር እንኑር!!
➛አቡ ሁረይራ አለቀሰ !

እንዲህ ሲባልም ተጠየቀ

يا أبا هُريرة.. أتبكي على الدُّنيا !
አቡ ሁረይራ ሆይ በዱንያ ላይ ታለቅሳልህ?

- لا والله، دُنياكم هذهِ لا تُبكيني ..

አይደለም በአላህ ይሁንብኝ ይህች ዱንያችሁ አታስለቅሰኝም

إنَّما أبكي مِنْ ثِقَلِ الحِمْلِ ، وسوء الرفيق ، وَمِنْ قلَّةِ الزَّاد ، وُبعدِ الطَّريق..


እኔ ማለቅሰው ከሸክሙ ክብደት ከመጥፎ ጓደኛ ከምግብ ማነስ ከመንገዱ ርዝመት ነው ።

أبكي خوفًا مِن أسقُط يوم القيامة مِن على الصراط ولا أدخُل الجنَّة..

ኣለቅሳለው የቂያም ቀን ከሲራጥ ከወደቅኩኝ ጀነትን አልገባመ ብዬ

وَدِدتُ أنِّي لَم أُخلق.

ባልተፈጠርኩ ብዬ ተመኘሁኝ


◂📚 ሲየር አእላም አኑበላእ
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③∅➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧አትራፊ የንግድ ማዕከላት ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ✅ተከታታይ አድስ ፅሁፍ 〰〰〰〰〰〰〰〰 ➧ክፍል አንድ ➛በዚህ ምድራዊ ዓለም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ ለመነገድና ትርፍ ለማትረፍ ሁሉም ደፋ ቀና ይላል ፤ ይሽቀዳደማል፡፡ ሁሉም በግዥና በሽያጭ ላይ ተሰማርቶ ይታያል፡፡ ነፍሱን ለሽያጭ አቅርቦ ሁሉም ማልዶ ከቤቱ ይወጣል፡፡ ➭ መልካም ስራ በመስራት ነፍሱን ከቅጣት ነጻ የሚያደርግ አለ ፤…
➧አትራፊ የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሁለት

➲ኢማንና መልካም ስራ በቁርኣን ውስጥ ተቆራኝተው መምጣታቸው ሁለቱ የጠበቀ ቁርኝት እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡ የቁርዓን አንቀጾችን በደንብ ከተከታተልን አንዳንድ ቦታ ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡ አንዳንድ ቦታ ደግሞ መልካም ስራ ለኢማን መስፈርት ሆኖ ይመጣል፡፡

➭ኢማን ለመልካም ስራ መስፈርት የሆኑባቸው የቁርኣን አንቀጾች የሚከተሉት ናቸው፡
فَمَن يَعْمَلْ مِنَ الصَّالِحَاتِ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَا كُفْرَانَ لِسَعْيِهِ وَإِنَّا لَهُ كَاتِبُونَ
“እርሱ ያመነ ሆኖ በበጎ ስራዎች ማንኛውንም የሚሰራም ሰው ፤ ምንዳውን አይነፈግም፡፡
” አል አንቢያእ፡94


مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን
፡፡” አን ነህል፡97


وَمَنْ أَرَادَ الْآخِرَةَ وَسَعَىٰ لَهَا سَعْيَهَا وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَأُولَٰئِكَ كَانَ سَعْيُهُم مَّشْكُورًا

“መጨረሻይቱንም ዓለም የፈለገ ሰው እርሱ አማኝ ሆኖ ለርሷ (ተገቢ) ስራዋን የሰራም ሰው እነዚህ ስራቸው የተመሰገነ ይሆናል፡፡”
አል ኢስራእ፡19

➧መልካም ስራ ለኢማን መስፈርት የሆኑባቸው የቁርኣን አንቀጾች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡
وَمَن يَأْتِهِ مُؤْمِنًا قَدْ عَمِلَ الصَّالِحَاتِ فَأُولَٰئِكَ لَهُمُ الدَّرَجَاتُ الْعُلَىٰ
“በጎ ስራዎችን በእርግጥ የሰራ ምእመን ሆኖ የመጣውም ሰው እነዚያ ለእነሱ ከፍተኛ ደረጃዎች አሏቸው
፡፡” ጧሃ፡75

إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ

“እነዚያ ያመኑ፡፡ መልካም ስራዎችንም የሰሩ፡፡” አል በቀራህ፡277

إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ

“ግን እነዚያ ያመኑት መልካሞችንም የሰሩት” አት ቲን፡6

إِلَّا الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ
“እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን የሰሩት”
አል ዓስር፡3

➭በልብ ውስጥ ትክክለኛ እና ጤናማ የሆነ እምነት ሳይኖር መልካም ስራ ብቻውን ምንም ጥቅም አይሰጥም።አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል
وَمَن يَكْفُرْ بِالْإِيمَانِ فَقَدْ حَبِطَ عَمَلُهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ

“ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ስራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎች ነው፡፡”
አል ማኢዳህ፡5

➧አንድ ሰው ኢማን ኖሮት መልካም ስራ ከሌለው ከኢስላም ባለቤቶች ሊሆን አይችልም።ምክንያቱም የኢስላምና የኢማን ባለቤቶች አምነው መልካምን ስራ የሰሩት ብቻ ናቸው፡፡ ሁለቱ - ኢማንና መልካም ስራ- ተያያዥ ነገሮች ናቸው፡፡

➲ ከልቡ በትክክል ካረጋገጠና ካመነ መልካም ስራ በአካሉ ላይ ይፋ ይሆናል። የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"ألا وإن في الجسد مضغة إذا صلحت صلح الجسد كله، وإذا فسدت فسد الجسد كله، ألا وهي القلب"

➲“ንቁ! በአካል ውስጥ አንዲት ቁራጭ ስጋ ትገኛለች፡፡ እርሷ ከተስተካከለች አካል ሁሉ ይስተካከላል፡፡ እርሷ ከተበላሸች አካል በሙሉ ይበላሻል፡፡ ንቁ! እርሷ ልብ ነች፡፡”
ቡኻሪ፡52 ሙስሊም፡1599
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➳ክፍል ሀያ ሰባት ➲ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው። ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው። ➩ይሁንቦት በነሰይድ ዳና፣ መደሻችን (መደሰቻችን) ይሁን ያለንበት ዘመን፣ ቆሞ ቀር ሆነናል ባለንበት ዘመን፣እኩሉን ሞሽሩን እንዳንቀር ተርበን” ከአላህ ተዓምር ውስጥ ወንድ እና ሴትን ማጋባቱ በመካከላቸው ውዴታና መተዛዘንን ማድረጉ ነው። …
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሀያ ስምንት
〰〰〰〰〰〰

➭“ለኸልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፣
የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር፣
ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር፣
ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር
”

➭ “ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር፣
ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር፣
ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ፣
አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር፣
ቢያለብስም ቢገፋም ቢያደኸይ ቢያከብር፣ይግባኝ የለበትም በፈረደው አምር፣ ተብሎ አላህ ዘንዳ በሻሀው አብሽር”

➲እንግዲህ ተመልከቱ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እነዚህ ስንኞች ለሙታን የተገጠሙ ናቸው። ይሄ ፍጥጥ ባለ መልኩ ወደ ሙታን አምልኮ መጣራት ነው። የሰው ልጅ ከሞተ ለሌላው ቀርቶ ለራሱም አይሆንም። አገልግሎቱ የማይቋረጥ ቅሪት ከተወ ብቻ ነው ምንዳው የማይቋረጠው።

➧ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ደግሞ እንዲህ ሲሉ ነው ያስተማሩት፡- “የአደም ልጅ ሲሞት ስራው ይቋረጣል።”
[ሙስሊም፡ 2682]

➧እዚህም ላይ የራሱን መልካም ስራ
ለመጠቆም እንጂ ለሌሎች ይደርሳል ለማለት አይደለም።ማልበስ ማጉረስ ማክበር፣ ማደህየት የአላህ ስልጣን ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ይላል “ባሪያዎቼ ሆይ! ሁላችሁም የተራባችሁ ናችሁ እኔ ያበላሁት ሲቀር። አብላን በሉኝ አበላችኋለሁ። ባሪያዎቼ ሆይ! ሁላችሁም የታረዛችሁ ናችሁ እኔ ያለበስኩት ሲቀር። አልብሰን በሉኝ አለብሳችኋለሁ።”
ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል።

➲በፈረደው እና በሚሰራው ነገር ይግባኝ የሌለበት አላህ ብቻ ነው። አላህ
አይደለም ይህን ግለሰብ ውዱን ነብይ صلى الله عليه وسلم እንኳን ሞት እስኪመጣቸው ድረስ አላህን እንዲገዙት እንጂ በሌላ አላዘዘም።

“ጀማሉል አለም صلى الله عليه وسلم፣ ወደ ጀይላኔ ቢወረውረው፣ ለውሀል መህፉዝን አስመረመረው፣ በአለም ተሹሞ ብዙ ጉድ እያስወገዱ፣በባግዳድ ምድር صلى الله عليه وسلم፣ እሳት ነው ፍቅር”

➛ይሄ በጣም ከባድ አባባል ነው። ይሄ በኢስላም ላይ የሚፈፅ ከባድ ቅጥፈት
ነው።


➧ ከአላህ አምላክነት ጋር የሚጋጩ ስንኞች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭የአላህ አምላክነት ማለት እኛ ፍጡሮቹ ለእርሱ የምንፈፅመው ነው። አላህ ልክ በጌትነቱ ሁሉ አንድ እንደሆነው በአማላክነቱም እንደዚሁ አንድ ነው። እኛ የእሱ ባሪያዎች የእሱን ትእዛዝ በማክበር፣ የነብያትን ፈለግ በመከተል ፀሎታችንን፣ መመካታችንን፣ ፍራቻችንን፣መተናነሳችንን፣ውዴታችንን፣ስግደታችንን፣ እርዳታን፣ ህይወታችንን፣ ሞታችንን እና ሌሎችንም አምልኮዎቹ ለእርሱ ብቻ ነው ልንፈፅም የሚገባን። ከእርሱም ውጭ ላለ ለማንኛውም አካል አምልኮን ልንፈፅም አይገባም።

➧ከዚህ በታች ያሉት የቁርኣን አንቀፆች አምልኮ ለአላህ ብቻ ማድረግ እንደሚገባን፣የሺርክን አደጋ፣ የሙሽሪኮችን መጨረሻ የሚገልፁ ይሆናሉ
۞ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ

አላህንም በብቸኝነት ተገዙ። በእርሱም ምንንም አታጋሩ።ሱረቱ ኒሳዕ 36

وَأَنَّ الْمَسَاجِدَ لِلَّهِ فَلَا تَدْعُوا مَعَ اللَّهِ أَحَدًا

እነሆ መስጊዶችም የአላህ ብቻ ናቸው። (በውስጣቸው) ከአላህ ጋር አንድንም
አትገዙ (ማለትም)።
ሱረቱል ጅን 18

قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

“ስግደቴ፣ መገዛቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማት ጌታ ለአላህ ነው” በል።ሱረቱል አንአም 162
لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ

“ለእርሱ ተጋሪ የለውም። በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ። እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ” (በል)።ሱረቱል አንአም 163

➣ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛አንብብ ያነበበ ተጠቀመ!


➧ወደ ቻይናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
✅የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ፦

"🔺ሳቅ አታብዙ ምክኒያቱም ሳቅን ማብዛት ቀልብን ትገድላለችና!"

ኢብኑ ማጀህ ዘግበዉታል።

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ③①➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሀያ ስምንት 〰〰〰〰〰〰 ➭“ለኸልቁ ገበያ መድሀኒት ነበር፣ የቸገረው ሄዶ የለውም ማፈር፣ ከሀያቱ በልጧል ውለታው በቀብር፣ ወዲያልኝ የሱ ጉድ አያልቅም ይቅር” ➭ “ጌታው ሰይድ አህመድ የደባቱ ኑር፣ ዶላል ያስፈቀተው የዲኑ ጨረር፣ ስፍር ቁጥር የለው ስንቱ በእጁ ሻረ፣ አላህ ዘንድ ነበር ተናግሮ የማያፍር፣ ቢያለብስም ቢገፋም…
➧መንዙማ
➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሀያ ዘጠኝ

➲የአላህ ውድ ባሪያ ነብዩ ሙሐመድ (صلى الله عليه وسلم (ለራሳቸው ጥቅም ማምጣት፣ ከራሳቸው ላይ ጉዳትን መከላከል አይችሉም። የሩቅንም አያውቁም። አላህ ነብዩንصلى الله عليه وسلم ይህን አስመልክቶ ግልፅ እንዲያደርጉ እንዲህ ሲል ያዛቸዋል

قُل لَّا أَمْلِكُ لِنَفْسِي نَفْعًا وَلَا ضَرًّا إِلَّا مَا شَاءَ اللَّهُ ۚ وَلَوْ كُنتُ أَعْلَمُ الْغَيْبَ لَاسْتَكْثَرْتُ مِنَ الْخَيْرِ وَمَا مَسَّنِيَ السُّوءُ ۚ إِنْ أَنَا إِلَّا نَذِيرٌ وَبَشِيرٌ لِّقَوْمٍ يُؤْمِنُونَ

“አላህ የሻውን በስተቀር ለእራሴ ጥቅምንም ጉዳትንም ማምጣት አልችልም። ሩቅንም (ምስጢር) የማውቅ በነበርኩ ኖሮ ከመልካም ነገር ባበዛሁና ክፉም ነገር ባልነካኝ ነበር። እኔ ለሚያምኑ ሕዝቦች አስፈራሪና አብሳሪ እንጂ ሌላ አይደለሁም” በላቸው።

[አልአዕራፍ፡ 188]

وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
“አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም። በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።” [አልአንዓም፡17

لَهُ دَعْوَةُ الْحَقِّ ۖ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِهِ لَا يَسْتَجِيبُونَ لَهُم بِشَيْءٍ إِلَّا كَبَاسِطِ كَفَّيْهِ إِلَى الْمَاءِ لِيَبْلُغَ فَاهُ وَمَا هُوَ بِبَالِغِهِ ۚ وَمَا دُعَاءُ الْكَافِرِينَ إِلَّا فِي ضَلَالٍ

“እውነተኛ አምልኮ ለአላህ ብቻ ነው። እነዛ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው በምንም ነገር ምላሽ አይሰጧችሁም። ከአላህ ሌላ የሚያመልኩ ሰዎች ምሳሌያቸው እጁን ወደ ውሀ እነደሚዘረጋ ወደ አፉ ለማድረስ ፈፅሞ ማድረስ አይችልም።” [
አርረዕድ፡ 14]

➧አላህ አሁንም ለሰው ልጆች አዛኝ ነውና በሚገባቸው መልክ ከእርሱ ውጭ
የሚመለኩት እንደ አምላኪዎቻቸው ፍጡር መሆናቸውን እንዲህ ሲል ይነግረናል

إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ

“እነዛ ከአላህ ውጭ የምትጠሯቸው እንደናንተው ባሪያዎች ናቸው ጥሯቸው እስኪ በእውነት እሺ ይበሏችሁ
።” [አእራፍ 194]

حُنَفَاءَ لِلَّهِ غَيْرَ مُشْرِكِينَ بِهِ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ

“ለአላህ ታዛዦች በርሱ የማታጋሩ ሆናችሁ (ከሀሰት ራቁ) በአላህም የሚያጋራ ሰው ከሰማይ እንደ ወደቀና በራሪ እንደምትነጥቀው ወይም ነፋስ እርሱን በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው።
” [አልሐጅ 31]

➭የሚከተሉት ስንኞች መንዙማ ባዮች የአላህን መብት (አምልኮ) ከእሱ ላይ አንስተው ለነብዩ (صلى الله عليه وسلم እና ለሌሎች ፍጡራን የሰጡበት ነው። አንባቢ እነዚህን የመንዙማ ስንኞች ብዙ ቦታ እንደሚሰማቸው እጠብቃለሁ።

➲ የኢስላም አካልም ተደርገው ይወሰዳሉ። ነገር ግን እንዲህ ዝርዝር ብለው ሲቀመጡ ምን ያህል ከምንወደው ጌታችን ጋር ሊያጣሉን እና ሊያራርቁን የሚችሉ በኢስላም ስም የመጡ ግን የሰይጣን ወጥመዶች መሆናቸውን እንረዳለን።

➧“በዝቶብኛልና አያሌ ነገር፣
አቤት ብየ ልጩህ እባሮቹ በር፣
ቀልቤን ወዳሳቸው አድርጌ ሰንዘር፣
አቤት ጮህኩባችሁ ጌቶቼ ዱስቱር፣
ከሙስጠፋ ይዤ እስከ አቡል በሸር፣
አምቢያ ሙርሰልም አንድ እንኳን ሳይቀር”

➛አማኝ የፈለገውን ያህል ችግር ቢበዛበት ሁሉን ነገሩን እንዲያገራለት የሚለምነው ሁሉን ቻይ የሆነውን አጋር የሌለው አንድ አምላክ አላህ ብቻና ብቻ ነው።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➭አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል አራት ➲ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين" “በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ 71ሙስሊም፡1037 ➧“ኸይረን” የሚለው ቃል በነኪራ (ሁሉን በሚያካትት ቃል) መምጣቱ…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

ክፍል አምስት

➛የእውቀት አላማው ተግባር ለመሆኑ ከማስረጃ ጋር በማስደገፍ የተወሰኑ ነጥቦችንመጥቀስ እፈልጋለሁ፡፡

➠የመጀመሪያው፡ እውቀትና ተግባር ሰዎች የተፈጠሩለት አላማ ነው ሁለቱ ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ሲሆን የእውቀት አስፈላጊነቱ ለተግባር ነው፡፡
አላህ ፍጡራንን ሊያውቁት እና ሊግገዙት ፈጠረ፡፡ለመጀመሪያው ማስረጃ የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው፡

اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الْأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الْأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا
“አላህ ያ ሰባትን ሰማያት የፈጠረ ነው፡፡ ከምድርም መሰላቸውን (ፈጥሯል)
በመካከላቸው ትዕዛዙ ይወርዳል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ መሆኑን አላህም
በነገሩ ሁሉ በእውቀት ያካበበ መሆኑን ታውቁ ዘንድ (ይህንን አሳወቃችሁ
)፡፡”
አጥ ጦላቅ፡12

➭እውቀት ፍጡራን የተፈጠሩበት አላማ ነው ለሚለው ደግሞ ማስረጃው የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው፡

وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም
፡፡

➧እውቀትና አምልኮ ሁሉም ሰዎች የተፈጠሩበት አላማ ነው፡፡ ወደአላህ የሚያቃርብ በሆነ ጠቃሚ እውቀት ካልሆነ በቀር አምልኮት አምልኮ ሊሆን አይችልም፡፡ አውቆ የሰራ የተፈጠረበትን አላማ በትክክል አሳክቷል፡፡

➳በዚህ ምክንያት የእውቀት ባለቤቶች የሚከተለውን ይናገራሉ፡-
➧“ለእርሱ ሲባል የተፈጠርንበት ፣ እርሱን ለማረጋገጥ የተገኘንበት ተውሂድ ሁለት ጎኖች አሉት፡፡ የእውቀት ጎንና የተግባር ጎን ናቸው፡፡

➲በእውቀት የምናጸድቀው የተውሂድ ክፍል እና በተግባር ተፈጻሚና ተፈላጊ የሆነው የተውሂድ ክፍል ናቸው፡፡ አምልኮ በተገቢው ሁኔታ ሊረጋገጥ ፣ ባሪያው ለአላህ ትክክለኛ ታዛዥ ይሆን ዘንድ የግድ ሁለቱ መኖርአለባቸው፡፡”

➠ያለተግባር የእውቀት ባለቤት ቢሆን በአላህ ቁጣ ይመለሳል፡፡ ምክንያቱም
የእውቀትን አላማ በትክክል አላረጋገጠም፡፡ ያለእውቀት የተግባር ባለቤት ከሆነ ደግሞ ቀጥተኛ ከሆነው የአላህ መንገድ ይንሻፈፋል፡፡


➭ለዚህ ነው ታላላቅ ዱዓዎችን በውስጧ የሚገኝባትን ፋቲሃ ዘወትር በየሶላታችን
እንድንቀራት በሸሪዓ የተደነገገው፡፡


اهْدِنَا الصِّرَاطَ الْمُسْتَقِيمَ ⓺صِرَاطَ الَّذِينَ أَنْعَمْتَ عَلَيْهِمْ غَيْرِ الْمَغْضُوبِ عَلَيْهِمْ وَلَا الضَّالِّينَ⓻


“ቀጥተኛውን መንገድ ምራን፡፡ የእነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ
ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን ፤ በሉ
)፡፡”አል ፋቲሃ ፡6_7

➠በእነርሱ ላይ ጸጋውን የዋለላቸው ሰዎች የእውቀትና የተግባር ባለቤቶች ናቸው፡፡በእነርሱ ላይ አላህ የተቆጣባቸው ሰዎች ደግሞ ተግባር የሌላቸው የእውቀት ባለቤቶች ናቸው፡፡ የተሳሳቱ የተባሉት ደግሞ ያለእውቀት የሚሰሩ ሰዎች ናቸው፡፡
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w