💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑦➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሁለት ➲ጠቃሚ እውቀት ለባለቤቱ የሚመራበት ብርሃንና ነጸብራቅ ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ…
➭የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት

➲የዓሊምን ደረጃና ቦታ በተመለከተ
“ሙስነድ” እና ሌሎች የሐዲስ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ሐዲሶች አብራርተውት ይገኛሉ፡፡ረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይና ታላቅ በሆነው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

➧“እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው ፤ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ ያመቻችለታል፡፡
የሚሰሩትን ስራ በመውደዳቸው መላኢካዎች ለእውቀት ፈላጊዎች ክንፋቸውን ያኖራሉ፡፡


➭ለዓሊም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ፤ በባህር ውስጥ የሚገኙት አሳዎች ሳይቀር ኢስቲግፋር (ይቅርታን) ይጠይቁላቸዋል፡፡ እውቀት ያለው ዓሊም ፣ እውቀት ከሌለው የአላህ ባሪያ ጋር ያለው ልዩነት ልክ በበድር (ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት) ሌሊት በሚወጣው ጨረቃና በሌሎች ከዋክብት መካከል እንዳለው ልዩነት ነው፡፡ ዑለሞች የነብያቶች ወራሾች ናቸው፡፡

➛ነብያቶች ዲናርም ፣ ዲርሃምም አላወረሱም፡፡ ያወረሱት ዒልምን ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ (ከዒልም) የያዘ ፣ የተነባበረ ድርሻ ያዘ፡፡” አህመድ፡21715 አቡዳውድ፡ 3641 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አቡዳውድ፡3671

➳አቡ ሁረይራ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ እንዳስተላለፉ:- ጦበራኒ “አውሰጥ” በተባለው የሐዲስ መዛግብት “ሀሰን” በሆነ ደረጃ ዘግበውታል፡፡ አቡሁረይራ በመዲና ገበያ መካከል ሲያልፍ ፣ ለተወሰነ ሰዓት ቆም አለ፡፡ “እናንተ ገበያተኞች ! ምን ደካማ አደረጋችሁ!” በማለት ተናገረ፡፡

➧“አቡሁረይራ ሆይ! ምንድን ነው?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁት፡፡ “የረሡል صلى الله عليه وسلم ንብረት እየተከፋፈለ የእናንተን ድርሻ ሳትይዙ ከዚህ ሆናችኋል!?” በማለት ምላሽ ሰጣቸው፡፡ “የት ነው ያለው?” በማለት ጠየቁት፡፡ “መስጅድ ውስጥ ነው” አላቸው።ወደ መስጅድ ፈጥነው ገሰገሱ፡፡ ደርሰው እስኪመለሱ ድረስ ቆሞ ጠበቃቸው፡፡ “ለእናንተ ምን አላችሁ?!” አላቸው፡፡ “አቡሁረይራ ሆይ! መስጅድ ሄድን ከውስጥ ገባን ፤ የሚከፋፈል ነገር ማየት አልቻልንም” አሉት፡፡

አቡሁረይራም “ከመስጅድ ውስጥ አንድንም አላያችሁ?!” በማለት ጠየቃቸው፡፡ “ከፊሎቹ ሶላት እየሰገዱ ፣ከፊሎቹ ቁርኣን እየቀሩ ፣ ከፊሎቹ ስለሀላልና ስለሀራም እያወሱ አይተናል” በማለት ምላሽ ሰጡት፡፡ አቡሁረይራ “ወዮላችሁ! የረሡል صلى الله عليه وسلم ውርስ ብሎ ማለት እኮ እርሱ ነው” በማለት መልስ ሰጣቸው፡፡ ጦበራኒይ ፊል አውሰጥ፡ 1429 ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል ሶሂህ ተርጊብ ወተርሂብ፡83

➛ይህ ነው የነብያት ውርስ ማለት፡፡ ነብያቶች የወርቅ ወይም የብር ገንዘብ አያወርሱም፡፡ ነብያቶች እውቀትን ነው የሚያወርሱት፡፡ የአንድ ሰው የእውቀት ድርሻው ከፍ ባለ ቁጥር ፣ ከነብያቶቸ ውርስ ድርሻው ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል”
ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡1037
◍
◍
◍
◍🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል


📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
♦️ تلاوة من سورة الواقعة
♦️ القارئ: #إبراهيم_البصيلي
•••━══❁✿❁══━•••
➲ቤትህን በቁርአን አድምቀው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

◾️ ‏قال الشيخ سليمان الرحيلي :

◀البَيْتُ الذي تُقرأُ فِيه سُورة البقرة تَفِرُّ مِنهُ الشياطين،ولكِن مَنْ الذي يَقرأُ سُورة البقرة في بَيْتِه اليوْم ،أَفْذَاذٌ مِنَ النَّاس قِلَّة! ولِذلِك اِسْتَوْطَنَت الشياطين كثيرًا مِن البيُوت

➧ሸህ ሱለይማን አሩሀይሊይ (አላህ ይጠብቃቸው) እንዲህ ይላሉ።

➳ሱረቱል በቀራ የሚቀራበት ቤት ሸይጣን አይገባም በሩቁ ይሸሻል
➳ነገር ግን በአሁን ሰአት ማን ነው ሱረቱል በቀራ በቤቱ ሚቀራው?
➳ይህንን ተግባራዊ ሚያደርጉና ሚተገብሩት ግን ጥቂት ሰዎች ናቸው
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬➬ ➲ክፍል ሀያ አራት ➧በአላህ ፍቃድ በክፍል ሁለት መፀሀፉ በዋናነት የተዘጋጀበት አርእስት ግልፅ ብሎ የሚወጣበት ይሆናል። እሱም አገራችን ላይ ያሉ መንዙማዎች እና መፀሀፍት ላይ የሚገኙ ክህደቶች፣ ሺርኮች፣ በአላህ እና መልክተኛው ላይ የተዋሹ ውሸቶች፣ ተረተረቶች እና መንዙማ ምን ያህል አገራችን ላይ የሙስሊሙን እምነት የሚንዱ ስንኞች እንዳሉት የሚዘረዘሩበት እና በአላህ ፍቃድ…
➧መንዙማ
➫➫➫➫➫

➻ክፍል ሀያ አምስት
➛➛➛➛➛➛➛➛

➤ነብዩ صلى الله عليه وسلم በህይወት በነበሩ ጊዜ አይደለም የሁሉ ቀላቢ የራሳቸውም ቀላቢ አልነበሩም። እሳቸውንም ሆኑ ፍጡራኑን ሁሉ የሚቀልበው፣ ከእርሳቸው በፊትም ይሁን
ከእርሳቸው በኋላ ያሉትን ፍጡሮቹን የሚቀልበው አላህ ብቻ ነው።
የሁሉ ቀላቢ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፦

۞ وَمَا مِن دَابَّةٍ فِي الْأَرْضِ إِلَّا عَلَى اللَّهِ رِزْقُهَا وَيَعْلَمُ مُسْتَقَرَّهَا وَمُسْتَوْدَعَهَا ۚ كُلٌّ فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ

“በምድርም ላይ ምንም ተንቀሳቃሽ የለችም ምግቧ በአላህ ላይ ያለ ቢሆን እንጂ።ማረፊያዋንም መርጊያዋንም ያውቃል። ሁሉም ግልጽ በሆነው መጽሐፍ ውስጥ ነው።”
[ሁድ፡ 6]

➭ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ይላሉ “አንዲት ነፍስ ሲሳይዋን ተመግባ ሳትጨርስ አትሞትም።” እስቲ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ በሰጠን ንፁህ አእምሮ እናስበው።እንዴት ብሎ ነው እነዚህ የራሳቸውን ሲሳይ በልተው ጨርሰው የሄዱ ሰዎች ቀብር ውስጥ ገብተው ከስራቸው ተገናኝተው ሲያበቁ “ዱንያ ስጡን” እየተባሉ የሚጠየቁት? ሲሳይ የሚጠየቀው ሲሳይ የማያልቅበት አላህ ብቻ ነው።ሌላ ጉድ ይመልከቱና ህዝባችን ያለበትን ጉድ ይታዘቡ፦

➧“አገር የጀበል፣ ጊዜው የጀበል፤
ደውላው የጀበል፣ እባክህ ጀበል በል፣
በፍቅሩ ታጠብ ጠጣ ወተቱ

➛እዚህ ደግሞ አገር ምድሩ፣ ጊዜው ሳይቀር ሁሉ ነገር ለአቡ ጀበል ተሰጥቷል
።ሁሉ በእጁ የሆነው ጌታ ግን እንዲህ ይላል፡

وَالَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِ مَا يَمْلِكُونَ مِن قِطْمِيرٍ

“እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳን አይኖራቸውም።” [ፋጢር፡ 13]

➧ወገኔ ሆይ! ከላይ ባለመንዙማው
“እባክህ ጀበል በል” እያለ የሚጎጉትህን እንዳትሰማ።መቀመቅ ይከትሃል። “አቡል ጀበል” ጥቅምና ጉዳት ቀርቶ የተምር ፍሬ ሽፋን የለውም እያለን ነው የኔም ያንተም የጀበልም ጌታ። ባለ ጀበሉ ይቀጥላል፡

“ጥንትም እሱ ነው፣ አሁንም እሱ፣
ዛሬም ወደፊት እሱ ነው እሱ፣
ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ”

➲ይሄ በምንም መልኩ ህያው የሆነው ፈጣሪ መገለጫ እንጂ የደካማውና ሙት የሆነው አቡል ጀበል መገለጫ አይደለም። እንዲህ አይነቱን የኩፍር ቃላት ላኢላሀ ኢልለላህ ከሚል ሰው መስማት እጅጉን ያማል።

➳እንዲህ አይነቱን ፅንፍ የደረሰ ጥፋት
የተውሒዱን ሃይማኖት ኢስላምን የሚከተል ሰው በፍቅር ሲያዳምጠው መመልከት ውስጥን ያቆስላል። ሁሉን ቻዩ እና የሁሉ ፈጣሪ አላህ ግን ምን ነበር ያለው?


لَهُ مُلْكُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ يُحْيِي وَيُمِيتُ ۖ وَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ ⓶هُوَ الْأَوَّلُ وَالْآخِرُ وَالظَّاهِرُ وَالْبَاطِنُ ۖ وَهُوَ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ⓷الحديد ٢-٣

“የሰማያትና የምድር ንግስና የርሱ ብቻ ነው። ህያው ያደርጋል፤ ይገድላልም። እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። እርሱ ፊትም ያለ፣ ኋላም ቀሪ፣ የበላይ፣ ቅርብም ነው። እርሱ ነገሩን ሁሉ አዋቂ ነው
።” [አልሐዲድ፡ 2-3

➧አቡል ጀበል ካልነበር የተገኘ ነውና ጥንት አልነበረም። ፍጡር ነውና ይሄው ሞቷል። ዛሬም የለም። አላህ ከቀብር እስከሚቀሰቅሰው ድረስም ቂያማ ድረስ አይኖርም።ታዲያ “ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ” ማለት ምን የሚሉት ቅጥፈት ነው?!! አይደልም አቡል ጀበል ነብዩ (صلى الله عليه وسلم (እንኳን ሞተዋልኮ።
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ!!


ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➧አትራፊ የንግድ ማዕከላት
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

✅ተከታታይ አድስ ፅሁፍ
〰〰〰〰〰〰〰〰

➧ክፍል አንድ

➛በዚህ ምድራዊ ዓለም በተለያዩ ስራዎች ላይ ተሰማርቶ ለመነገድና ትርፍ ለማትረፍ ሁሉም ደፋ ቀና ይላል ፤ ይሽቀዳደማል፡፡ ሁሉም በግዥና በሽያጭ ላይ ተሰማርቶ ይታያል፡፡ ነፍሱን ለሽያጭ አቅርቦ ሁሉም ማልዶ ከቤቱ ይወጣል፡፡

➭ መልካም ስራ በመስራት ነፍሱን ከቅጣት ነጻ የሚያደርግ አለ ፤ በአንጻሩ የአላህን ትዕዛዝ በመንቀፍ ነፍሱን ለጥፋት የሚያጋልጥ አለ፡፡ በዚህ ኪታብ ውስጥ የምንነጋገረው አብዛኛው ሰው የዘነጋው ፣ ነገር ግን ሁሉም ሰው ሊሽቀዳደምበት የሚገባ በዱንያ መልካም ህይዎትን በአኼራ ደግሞ ዘላለማዊ ህይዎትን የሚያወርስ የሆነውን “አትራፊ የንግድ ማዕከላት”ነው፡፡

በመልካም ስራ ትርፍ የሚገኝበት የአኼራ ንግድ የሶላት ንግድ ነው ፤ የጾም ንግድ
ነው ፤ የሶደቃ ንግድ ነው ፤ ባሪያው ወደጌታው የሚቃረብበት በአጠቃላይ የመልካም ስራ ንግድ ነው፡፡ በዱንያ ንግድ ውስጥ ትርፍና ኪሳራ እንዳለ ሁሉ በአኼራውም ንግድ ትርፍና ኪሳራ አለ፡፡

በአላህ አምኖ መልካምን ስራ የሰራ ታላቅ ምንዳ ይኖረዋል ፤ከኢማን እና ከመልካም ስራ የራቀ ግልጽ የሆነ ኪሳራ ይገጥመዋል

➲የመልካም ስራ ደረጃ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧መልካም ስራ በቁርኣን ውስጥ ከሰማንያ በላይ የተወሳ ሲሆን ከኢማን ጋር ተጣምሮ ሰባ ሶስት ቦታዎች ላይ ተወስቷል፡፡ መልካም ስራ ከኢማን ጋር ተቆራኝቶ በመጣበት የቁርኣን አንቀጽ እንኳ በመልካም ስራ የሚገኘው ምንዳ በስፋት ተወስቷል፡፡

➧መልካም ስራ የአላህን ምህረት ፣ እዝነት እና ውዴታ እንደሚያስገኝ ፤ በመልካም ስራ ምድር ላይ የፍስሃና የደስታ ህይዎት እንደሚያስገኝ ይገልጻል፡፡ መልካም ስራ ሰርተው ያለፉ አማኞች በዚህ ምድራዊ ዓለም ያሳረፉትን መልካም አሻራ ያወሳል፡፡

➭ይህ ሁሉ በግልጽ የሚጠቁመው መልካም ስራ በዲናችን ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ እንዳለው ነው፡፡ ባሪያው ይህን ሲሰማ ለመልካም ስራ ፊቱን ያዞራል ፤ ፍላጎቱም ይጨምራል ፤ የመነቃቃት ስሜት ይታይበታል፡፡ ሙስሊም የመልካም ስራ ጥቅሞችን ፣ ፍሬዎችን ፣ ፋይዳዎችንና መልካም አሻራዎችን ከተገነዘበ ፍላጎቱ የላቀ ፣ በማሕበራዊ ህይዎቱ ውስጥ የመልካም ስራ ሚናው ከፍተኛ ይሆናል፡፡

➭ለመልካም ስራ ቸልተኛነት ካሳየህ ደካማ ትሆናለህ ፤ በማይጠቅሙ ነገሮች ትጠመዳለህ፡፡ አንድ ሰው ከመልካም ስራ ተዘናግቶ ህይዎቱን ካጠናቀቀ ጸጸት በማይጠቅምበት ቀን ተጸጻች ይሆናል፡፡
◉
◉
◉
◉🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
♦️ تلاوة من سورة الأحقاف
♦️ القارئ: #صالح_الطوالة
•••━══❁✿❁══━•••
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➻ክፍል ሀያ አምስት ➛➛➛➛➛➛➛➛ ➤ነብዩ صلى الله عليه وسلم በህይወት በነበሩ ጊዜ አይደለም የሁሉ ቀላቢ የራሳቸውም ቀላቢ አልነበሩም። እሳቸውንም ሆኑ ፍጡራኑን ሁሉ የሚቀልበው፣ ከእርሳቸው በፊትም ይሁን ከእርሳቸው በኋላ ያሉትን ፍጡሮቹን የሚቀልበው አላህ ብቻ ነው። የሁሉ ቀላቢ የሆነው አላህ እንዲህ ይላል፦ ۞ وَمَا مِن دَابَّةٍ…
➳መንዙማ
➬➬➬➬


➧ክፍል ሀያ ስድስት

አቡል ጀበል ካልነበር የተገኘ ነውና ጥንት አልነበረም። ፍጡር ነውና ይሄው ሞቷል። ዛሬም የለም። አላህ ከቀብር እስከሚቀሰቅሰው ድረስም ቂያማ ድረስ አይኖርም።


➧ታዲያ “ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ” ማለት ምን የሚሉት ቅጥፈት ነው?!! አይደልም አቡል ጀበል ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ሞተዋልኮ።

የልቅናው እማ አሁን ልፈስረው፣
የአላህ ሹም እኮ ነው ሸልሞ የፈጠረው፣ በፊት የሰራው ጉድ አሁን ልናገረው፣ የአደም ጭቃ ነው እጁን ያጠቆረው፣ ነበር ያሳመረ ሌሎች አቡል ጀበል ግርማ አለው ለመልኩ”


➳ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን!! እስቲ አሁን ይሄ ብልግና አይደለም ወይ?!!

‎كَبُرَتْ كَلِمَةً تَخْرُجُ مِنْ أَفْوَاهِهِمْ ۚ إِن يَقُولُونَ إِلَّا كَذِبًا

➲ከአፎቻቸው የምትወጣውን ቃል ምን አከበዳት! ውሸትን እንጂ አይናገሩም፡፡
(ሱረቱ አል ከህፍ፡-5) አላህ ግን አደምን (ዐለይሂ-ስሰላም) በሁለት እጆቹ እንደፈጠረ እንዲህ ሲል ይነግረናል።

قَالَ يَا إِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَيَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ الْعَالِينَ

➩(አላህም) «ኢብሊስ ሆይ! በሁለት እጆቼ (በኃይሌ) ለፈጠርኩት ከመስገድ ምን ከለከለህ? (አሁን) ኮራህን? ወይስ (ፊቱኑ) ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡
(ምዕራፍ ሱረቱ ሷድ-75)

➧አቡል ጀበል አይደለም አደም ሲፈጠር ሊኖር ቀርቶ የራሱንም አፈጣጠር አላየም። ለዚህም ማስረጃችን የሚከተለው የጌታችን አላህ ቃል ነው

۞ مَّا أَشْهَدتُّهُمْ خَلْقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَلَا خَلْقَ أَنفُسِهِمْ وَمَا كُنتُ مُتَّخِذَ الْمُضِلِّينَ عَضُدًا

➲የሰማያትንና የምድርን አፈጣጠር አላሳየኋቸውም፡፡ የነፍሶቻቸውንም አፈጣጠር (እንደዚሁ)፡፡ አሳሳቾችንም ረዳቶች አድርጌ የምይዝ አይደለሁም፡፡[አልከህፍ፡ 51]

➩ሌላው ደግሞ እንዲህ ይላል፡-
“ይመነጥቁታል ያወጡታል ከጭንቅ” እውን ከጭንቅ የሚያወጡት እነሱ ናቸው?

أَمَّن يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ ۗ أَإِلَـٰهٌ مَّعَ اللَّهِ ۚ قَلِيلًا مَّا تَذَكَّرُونَ

➳ወይስ ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣልን ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን ጥቂትን እንጂ አትገሰፁም
?” [አንነምል፡ 62]

➲የቦረናው ጌታ ነው እንደ ጡላጊ፣
ትንሹን ጠቃሚ ትልቅ አሳዳጊ”
ትንሹን ጠቃሚ ትልቁን አሳዳጊ አላህ ብቻ ነው
። አላህ ግን እንዲህ ይላል፡-

قُلِ اللَّهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ

➧(ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»[አሊ ዒምራን፡ 26]

➩ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው።
ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው።

◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
➧ምርጥ የማለዳ የቲላዋ ግብዧ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ቁረአን ማንበብና እንድሁም በትኩረት ማዳመጥ ትልቅ ኢባዳ ነው!

♦️ تلاوة من سورة الحشر
♦️ القارئ: #مختار_الحاج
•••━══❁✿❁══━•••
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
በኢማን ላይ መጠራጠር
እና ወስዋስ (ጉትጎታ ) የተለያዩ ነገሮች ናቸው
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑧➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➭የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሶስት ➲የዓሊምን ደረጃና ቦታ በተመለከተ “ሙስነድ” እና ሌሎች የሐዲስ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ሐዲሶች አብራርተውት ይገኛሉ፡፡ረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይና ታላቅ በሆነው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡- ➧“እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው ፤ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ ያመቻችለታል፡፡ የሚሰሩትን ስራ በመውደዳቸው…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል አራት

➲ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ 71ሙስሊም፡1037

➧“ኸይረን” የሚለው ቃል በነኪራ (ሁሉን በሚያካትት ቃል) መምጣቱ ክብደትን እና
ልቅናን እንዲሁም በአላህ ዲን የታነጸ ሰው የሚለቅመው ጠቃሚ ፍሬ ከፍተኛ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ዕውቀትን በመፈለግ ላይ እንቅስቃሴ ከጀመረ አላህ መልካሙን እንደሻለት የሚያመክት ነው ማለት ነው፡፡

➲ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“በዚህ ሐዲስ የተፈለገው ተግባርን ያጣመረ የዲን እውቀት ነው፡፡ ከተግባር ነጻ የሆነ
እውቀትን የፈለገ ሰው አላህ መልካም ሽቶለታል ማለትን አያመላክትም፡፡”

➭ይህ ማለት ፣ ዲንን ሊገነዘብና ወደተግባር ሊቀይረው ይገባል ማለት ነው፡፡ የመማሩ ዋናው አላማ ከራሱ ላይ ማህይምነትን ማስወገድ ፣ በእውቀት ላይ ተንተርሶ አምልኮን ለአላህ ብቻ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ አይነት ባህሪ ላይ ከሆነ መልካምን ለማግኘት ተገቢ ይሆናል ማለት ነው፡፡


➛ለተግባር እውቀት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ እውቀት ፣ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ነው ከተግባር በፊት እውቀት ተቀዳሚ የሆነው፡፡ ተግባር፣ አምልኮ ፣ ወደአላህ መቃረብ ከአላህ ኪታብና ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱና በመነጨ ጠቃሚ እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ሚፍታህ ዳሪ አስ ሳዓዳ፡1/65

➧በዚህ ታላቅ ርዕስ ዙሪያ ጥቅል መረጃዎችን እና ታላላቅ የሰለፎችን ንግግር ያካተተ“ኢቅቲዷኡል ዒልም አልዓመል” የተባለ ምርጥ መጽሐፍ ኸጢብ አል'በግዳድይ -ረሂመሁሏህ - ጽፈዋል፡፡

➲“ኢቅቲዷኡል ኢልም አልዓመል” የተባለው ኪታብ የእውቀት አላማው ተግባር እንደሆነ ፣ በእውቀትና በማስረጃ ላይ በመንተራስ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ማረጋገጥ እንደሚገባ ትኩረት ይሰጣል፡፡ አንድ ባሪያ እውቀት ኖሮት ስራ ከሌለው ፣እንዲሁም ያለእውቀት ተግባር ብቻ ከሆነም አምልኮ በትክክል ተረጋግጧል ማለት አይቻልም፡፡

➧የአላህ አምልኮ በሁለት ነገሮች ካልሆነ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ በጠቃሚ እውቀት እና በመልካም ተግባር፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ

“እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልእክተኛው (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡” አት ተውባህ፡33

➭“ሁዳ” ፡ ማለት ጠቃሚ እውቀት ማለት ነው፡፡ “ዲኑል ሐቅ” ማለት ደግሞ ወደአላህ የሚያቃርብ መልካም ተግባር ማለት ነው፡፡“ዲኑል ሐቅ” ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲሁም አጠቃላይ ነብያቶች የተላኩበት ነው፡፡
◉
◉
◉
◉✍እንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑨➰
〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➳መንዙማ ➬➬➬➬ ➧ክፍል ሀያ ስድስት አቡል ጀበል ካልነበር የተገኘ ነውና ጥንት አልነበረም። ፍጡር ነውና ይሄው ሞቷል። ዛሬም የለም። አላህ ከቀብር እስከሚቀሰቅሰው ድረስም ቂያማ ድረስ አይኖርም። ➧ታዲያ “ይኖራል ነግሶ አለምን ገዝቶ” ማለት ምን የሚሉት ቅጥፈት ነው?!! አይደልም አቡል ጀበል ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ሞተዋልኮ። የልቅናው እማ አሁን ልፈስረው፣…
➧መንዙማ
➬➬➬➬➬

➳ክፍል ሀያ ሰባት

➲ይሄ ስንኝ በግልፅ የአላህን መብት አሳልፎ ለቦረናው ሸይኽ እየሰጠ ነው።
ጠቃሚ ጎጂ፣ ሰጪ ነሺ አላህ ብቻ ነው።

➩ይሁንቦት በነሰይድ ዳና፣ መደሻችን (መደሰቻችን) ይሁን ያለንበት ዘመን፣ ቆሞ ቀር ሆነናል ባለንበት ዘመን፣እኩሉን ሞሽሩን እንዳንቀር ተርበን” ከአላህ ተዓምር ውስጥ ወንድ እና ሴትን ማጋባቱ በመካከላቸው ውዴታና መተዛዘንን ማድረጉ ነው።

➧ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) እንኳን ትዳር የሰጣቸው አላህ ነው። ዛሬ ግን ይሄው እዚህ ላይ እንደምናየው “እኩሉን ሞሽሩን” ብለው ነብዩን (صلى الله عليه وسلم) ዳሩን ሲል፤ ከአላህ ውጭ ይጠይቃሉ። አላህ ብቻ ሊያደርገው በሚችለው ጉዳይ ፍጡራንን መጥራት ሺርክ እና ኩፍር ነው።

➲የአላህ መልክተኛ (صلى الله عليه وسلم) “ከአላህ ውጭ ያለን እየጠራ የሞተ እሳት ገባ” ብለዋል። አላህ ከፍጡሮቹ ስልጣኑን አሳልፎ የሰጠው አለን?

➩የአላህ ጌትነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ከላይ አሳልፈናል። አገራችን ላይ ካሉ መንዙማዎች ውስጥ ለምሳሌነት የሚከተሉት አላህ ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ እንደሰጠ ይዋሻሉ። ጥያቄው አላህ ምን ሆኖ ነው ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ የሚሰጠው? ጌታችን አላህ ማለት ህያው፣ የማይሞት፣ በራሱ የተብቃቃ ፍጡራኑን የሚያብቃቃ፣ አሸናፊ፣ የማይተኛ፣ የማያንቀላፋ፣ ሿሚ፣ ሻሪ፣ የፍጡራኑ ሁሉ መጠጊያ ነው።

➲ አላህ ከእርሱ ውጭ የሚመለኩት በሰማይም በምድርም ምንም እንደማይችሉ፣ ሽርክናም እንደሌላቸው፣ አጋዦቹም እንዳልሆኑ፣ እርሱ ከፈቀደ በኋላ ቢሆን እንጂ እንደማያማልዱም እንዲህ ሲል ይነግረናል፡-

قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِ اللَّهِ ۖ لَا يَمْلِكُونَ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ فِي السَّمَاوَاتِ وَلَا فِي الْأَرْضِ وَمَا لَهُمْ فِيهِمَا مِن شِرْكٍ وَمَا لَهُ مِنْهُم مِّن ظَهِيرٍ

«እነዚያን ከአላህ ሌላ (አማልክት ብላችሁ) የምታስቧቸውን ጥሩ፡፡ በሰማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ክብደት ያክል ምንንም አይችሉም፡፡ ለእነርሱም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም፡፡ ከእነርሱም ለእርሱ ምንም አጋዥ የለውም፤» በላቸው፡፡[ሰበእ፡ 22]


وَلَا تَنفَعُ الشَّفَاعَةُ عِندَهُ إِلَّا لِمَنْ أَذِنَ لَهُ ۚ حَتَّىٰ إِذَا فُزِّعَ عَن قُلُوبِهِمْ قَالُوا مَاذَا قَالَ رَبُّكُمْ ۖ قَالُوا الْحَقَّ ۖ وَهُوَ الْعَلِيُّ الْكَبِيرُ


➳ምልጃም እርሱ ለፈቀደለት ሰው ብቻ ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም፡፡ ከልቦቻቸው ላይ ድንጋጤው በተገለጸም ጊዜ (ተማላጆቹ) «ጌታችሁ ምን አለ?» ይላሉ፡፡ (አማላጆቹ) «እውነትን አለ፤ እርሱም ከፍተኛው ታላቁ ጌታ ነው» ይላሉ፡፡ [ሰበእ፡ 23]

የሚከተሉት ስንኞች ላይ አላህ ስልጣኑን ለፍጡራኑ አሳልፎ እንደሰጠ ተደርጎ ይቀጠፍበታል። አላህ ላይ መዋሸት ደግሞ ከባድ ቅጥፈት ነው።
እስኪ አላህ ይህንን እንዳለ ምን አሳወቀው

أَطَّلَعَ الْغَيْبَ أَمِ اتَّخَذَ عِندَ الرَّحْمَـٰنِ عَهْدًا

ሩቁን ምስጢር ዐወቀን ወይስ አልረሕማን ዘንድ ቃል ኪዳንን ያዘ [
መርየም፡78]

➣ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉✍

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➛አንብብ ያነበበ ተጠቀመ!

➧ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1