💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሀያ ሁለት ➭አምልኮ እና ጭፈራ የተለያዩ ናቸው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ሶሐባዎች ከማንም በላይ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ወዳጆች ናቸው። አላህ እና መልክተኛው ያላዘዙትን፣ ሶሐባዎች የማያውቁትን በሶለዋት ስም በሸሪዐ ያልተደነገጉ ሺርክ በተቀላቀለባቸው ስንኞች ማዜም፣ ማጨብጨብ፤ ማፏጨት እና መጨፈር ነገ ከአላህ ፊት እንዳንጠየቅበት…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➛ክፍል ሀያ ሶስት

➧በነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ላይ ሰለዋት መቼ እና እንዴት እናውርድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➫➫➫

➳ሰለዋት ማውረድ ማለት ምን እንደሆነ ከላይ አይተናል። አላህ በነብዩ ሙሐመድ(صلى الله عليه وسلم (ላይ የእዝነት ሰላምታውን እንዲያወርድባቸው እየጠየቅነው ነው።

➧ሱናውን ገጥመን በነብዩ صلى الله عليه وسلم ላይ ሰለዋት በምን አይነት ሁኔታዎች ላይ ነው የምናወርድባቸው? መስጊድ ስንገባ፣ ከመስጊድ ስንወጣ፣ ከአዛን በኋላ፣ ተሸሁድ (አተሒያቱ ላይ)፣ ዱዐ መክፈቻ፣ ዲን ትምህርት እየተማርን እና እያስተማርን ሐዲሳቸውን ስናነብ፣ ዱዐ ሲጠናቀቅ፣ ጁምዐ ቀን በበለጠ ሁኔታ፣ የዳዕዋ መክፈቻ ላይ የሳቸውን ስም እናነሳለን፣ ጁመዐ ኹጥባ ላይ፣ የሞተ ሰው ላይ ስንሰግድ፣ ወዘተ።

➲ ሀሙስ ማታ!
➫➫➫➫➫➫

➧በሃገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ብዙ ቤቶች ላይ ሀሙስ ማታ “የአምዋት ቡና
(ለሞቱ ሰዎች የሚፈላ ቡና)” በማለት ጫት ተዘርግቶ፣ ቡና ተፈልቶ፣ እጣን እያጫጫሱ የሚያሳልፉ ሰዎች አሉ። ሌሎች ደግሞ በመስጊድ ደረጃ ሀሙስ ማታ ከመግሪብ እስከ ኢሻ በጀመኣ ሰለዋት እናወርዳለን የሚሉም አሉ
።

➧ ከዚህም አልፈው ሌሊቱን በቂምሃ
(በጫት መቃም) የሚያሳልፉት ብዙ ናቸው። በጣም የሚገርመው ቁጭ ብለው በጀመኣ ሲሉ የነበረውን
“ሶለዋት” ብለው የሚጠሩትን “መርሃባ ነቢ መርሃባ (እንኳን ደህና መጡ ነቢ እንኳን ደህና መጡ!)” የሚለው ላይ ሲደርሱ ከተቀመጡበት ብድግ የሚሉ መኖራቸው ነው።

➽በሰዓቱ ከሚባሉ የመንዙማ ስንኞች የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡-

➧“ነበው ዲጅዋ ዲጁ ነብዮ ዲጅዌ” (በሀደሪኛ)
➧“አርሂቡ ነቢ አርሂቡ ነቢ” (በአማርኛ)
➧“ግቡልን የተንቢ” (በጉራጊኛ
)

➳ይህንንም የሚያደርጉት ነብዩ صلى الله عليه وسلم ይመጣሉ ብለው ስለሚገምቱ ነው። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን! ነብዩ صلى الله عليه وسلم የትም አይመጡም። መዲና ተቀብረዋል። እኛ እሳቸው ላይ ሸሪአ ባዘዘው መልኩ ሰለዋት ስናወርድ መላኢካ ያደርስላቸዋል። ከዚያ ውጭ የትም አይመጡም።

➛ነብዩ صلى الله عليه وسلم አይደለም ሞተው በህይወት እያሉ እንኳን ሰው ከተቀመጠበት ሲነሳላቸው አይወዱም ነበር። ያው በዲን ላይ የሚጨመር ፈጠራ መጨረሻው ይህ ነው። ወደ አላህ እቃረባለሁ ብሎ ከአላህ መራቅ እና ቁጣውን መከናነብ። ነብዩ صلى الله عليه وسلم“የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ተመላሽ ነው ተቀባይነት የለውም።”ብለዋል።

➛ በሃገራችን በተለምዶ “ኸሚስ” እየተባለ ሀሙስ ለጁሙዐ ሰዎች የሚሰባሰቡበት ምሽት ማስረጃ የማይደግፈው በሶሐባዎች ያልተፈፀመ ተግባር ነው።

➳ እንዲያውም ነብዩ صلى الله عليه وسلم በሐዲሣቸው ጁሙዐን ቀኑን በፆም ሌሊቱን በመቆም ከሌሎች ቀናት እንዳትለዩት ካሉት ማስረጃ ጋር የሚቃረን ነው። [ሙስሊም፡ 1144]
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

አንብብ!ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል

➛ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑤➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
☑️ ምቀኝነት
☑️ እዩልኝና ስሙልኝ
☑️ በራስ መገረምና ኩራት


https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ብቻ አላህ አይርሳህ!
~~ ~~~~
ስምህ በታሪክ መዝገብ ውስጥ መስፈር አለመስፈሩ አያስጨንቅህ። እሱ የስኬት መስፈርት አይደለም። አላህ መርጦ ከላካቸው ነብያት ውስጥ ስንቶቹ ናቸው ስማቸው ለታሪክ የቀረው? ከጥቂትም በጣም ጥቂት! ጠቢቡ ጌታ እንዲህ ይላል፦
﴿وَرُسُلًا لَمْ نَقْصُصْهُمْ عَلَيْكَ﴾.
{ባንተ ላይ ያልተረክናቸውም መልእክተኞች (ልከናል።} [ኒሳእ፡ 164]
ግና ታሪክ ባይዘክራቸው፣ ሰው ባያውቃቸውም ሁሉ በእጁ ከሆነው ሃያል ጌታቸው ዘንድ የከበሩ ናቸው፣ ደረጃቸው ከፍ ያለ። አብዛኞቻችን የምንዘናጋበት የኢኽላስ ጉዳይ!
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ✅አድስ ተከታታይ ፅሁፍ 〰〰〰〰〰〰〰〰 ➛ክፍል አንድ ➧በተስተካከለው ዲናችን ውስጥ እውቀት ከፍተኛ ደረጃ የተሰጠው መሆኑ ለማንም የሚሰወር አይደለም፡፡ እውቀት የመጀመሪያው መሰረት ነው፡፡ በእውቀት ካልሆነ በቀር የሰው ልጅ ለእርሷ ሲባል የተፈጠረባት ፣ እርሷን ለማረጋገጥ ሲባል የተገኘባት አምልኮ ሊረጋገጥ ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ሸሪዓ…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሁለት

➲ጠቃሚ እውቀት ለባለቤቱ የሚመራበት ብርሃንና ነጸብራቅ ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ نُورًا نَّهْدِي بِهِ مَن نَّشَاءُ مِنْ عِبَادِنَا ۚ

“እንደዚሁም ወደ አንተ ከትዕዛዛችን ሲሆን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡
መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን)
ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡”
አሽ ሹራ 52

➭እውቀት ለባለቤቱ አንጸባራቂ ብርሃን ነው፡፡ በማህበረሰቡ ውስጥ የሚገኝ ዓሊም ምሳሌው ልክ በጨለማ ውስጥ ባትሪ ይዞ ሰዎች እንቅፋትና አደገኛ ነገሮች እንዳይገጥማቸው በመካከላቸው መብራት እያበራ በቀጥተኛው መንገድ በትክክል እንዲጓዙ እንደሚያደርግ ሰው አምሳያ ማለት ነው፡፡

➧የእውቀትን ደረጃና ክብር እንዲሁም የእውቀት ባለቤቶች የተሰጣቸውን ውዳሴ የሚያብራሩ መረጃዎች በቁርኣንም ይሁን በረሡል صلى الله عليه وسلم ሱና በብዛት መጧል፡፡

➧ትልቅ በሆነው የተውሒድ ጉዳይ የእውቀት ባለቤቶችን ምስክርነት ከእርሱ
ምስክርነት ጋር አቆራኝቶ በቁርኣን መናገሩ ብቻ ለእነርሱ ክብር በቂ ነው
፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ ۚ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

“አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲሆን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ
የሌለ መሆኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የእውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ) ፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ አሸናፊው ጥበበኛው ነው
፡፡”አል ኢምራን፡18

➛የእውቀት ባለቤቶችን ልቅናና ደረጃ በተመለከተ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል


قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ
“እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?” በላቸው፡፡ አዝ ዙመር 9

يَرْفَعِ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا مِنكُمْ وَالَّذِينَ أُوتُوا الْعِلْمَ دَرَجَاتٍ ۚ

“አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን
በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል
፡፡” አል ሙጃደላህ፡11

➛የዚህ ቁርኣን አንዱ ትርጓሜ “አማኝ የሆነውን ዓሊም ፣ እውቀት ፣ ደረጃና ግንዛቤከሌለው አማኝ በደረጃ ከፍ ያደርገዋል፡፡” ማለት ነው፡፡ የደረጃዎች ከፍ ማለት የብልጫ ትልቅነት ፣ የቦታ ከፍተኛነትን ያመላክታል፡፡
◉
◉
◉
◉✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧
ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
➧የሙእሚን ህይወቱ በሶብር፣ በሽኩርና በዱአ የታጠረ ሊሆን ይገባል።

መልካም ነገር ሲገጥመን አላህን ማመስገን
መጥፎ ነገር ሲደርስብን መሶበርና መታገስ
ጉዳያችን ሙሉ ለሙሉ ወደ አላህ ማስጠጋትና ዱአ ማብዛት።
Audio
✅ ፈፅሞ ሊያመልጠን የማይገባ ወሳኝ ዚክር እና ትሩፋቱ

➡️ የእስቲግፋሮች ሁሉ አለቃ!!
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

عَنْ شَدَّادِ بْنُ أَوْسٍ رضي الله عنه، عَنِ النَّبِيِّ -صلى الله عليه وسلم-، قال: ((سَيِّدُ الِاسْتِغْفَارِ ŘŁŮŽŮ†Ů’ تَقُولَ: اللَّهُمَّ أَنْتَ رَبِّي لاَ إِلَهَ إِلَّا أَنْتَ، خَلَقْتَنِي وَأَنَا عَبْدُكَ، وَأَنَا عَلَى عَهْدِكَ وَوَعْدِكَ مَا اسْتَطَعْتُ، أَعُوذُ بِكَ Ů…ِنْ شَرِّ مَا صَنَعْتُ، أَبُوءُ[1] Ů„ŮŽŮƒŮŽ بِنِعْمَتِكَ عَلَيَّ، وَأَبُوءُ لَكَ بِذَنْبِي فَاغْفِرْ لِي، إِنَّهُ لاَ يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا أَنْتَ)).
قَالَ: ((وَمَنْ قَالَهَا مِنَ النَّهَارِ مُوقِنًا بِهَا، فَمَاتَ مِنْ يَوْمِهِ قَبْلَ أَنْ يُمْسِيَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ، وَمَنْ قَالَهَا مِنَ اللَّيْلِ وَهُوَ مُوقِنٌ بِهَا، فَمَاتَ قَبْلَ أَنْ يُصْبِحَ، فَهُوَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ)). أخرجه البخاري

🔺ለሌሎችም በማስተላለፍ የኸይር ሰበብ ይሁኑ!!

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑥➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
✍ ለጌታችን አላህ ሀያልነቱና ልቅናው በተገባና በተስማማ መልኩ ስሞችና መገለጫዎች ማፅደቅ ምን ይባላል⁉️
Anonymous Quiz
8%
النفي
41%
الإثبات
14%
صراط المستقيم
37%
الأسماء والصفات
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➛ክፍል ሀያ ሶስት ➧በነብዩ (صلى الله عليه وسلم (ላይ ሰለዋት መቼ እና እንዴት እናውርድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➳ሰለዋት ማውረድ ማለት ምን እንደሆነ ከላይ አይተናል። አላህ በነብዩ ሙሐመድ(صلى الله عليه وسلم (ላይ የእዝነት ሰላምታውን እንዲያወርድባቸው እየጠየቅነው ነው። ➧ሱናውን ገጥመን በነብዩ صلى الله عليه وسلم ላይ ሰለዋት…
➳መንዙማ
➬➬➬➬➬

➲ክፍል ሀያ አራት

➧በአላህ ፍቃድ በክፍል ሁለት መፀሀፉ በዋናነት የተዘጋጀበት አርእስት ግልፅ ብሎ የሚወጣበት ይሆናል። እሱም አገራችን ላይ ያሉ መንዙማዎች እና መፀሀፍት ላይ የሚገኙ ክህደቶች፣ ሺርኮች፣ በአላህ እና መልክተኛው ላይ የተዋሹ ውሸቶች፣ ተረተረቶች እና መንዙማ ምን ያህል አገራችን ላይ የሙስሊሙን እምነት የሚንዱ ስንኞች እንዳሉት የሚዘረዘሩበት እና በአላህ ፍቃድ ሸሪአዊ መልስ የሚቀርብባቸው ይሆናሉ።


➩እነዚህን መንዙማዎች በዋና ዋና አርእስት ስር ከፋፍያቸዋለሁ። ትኩረት የሚሽቱትን ስንኞች አስምሬባቸዋለሁ። በአላህ ፍቃድ እነዚህን እና መሰል ከኢስላም ጋር የሚጋጩ ስንኞችን እኛም ተጠንቅቀን፣ ቤተሰባችንን እና ማህበረሰቡን ልናስጠነቅቅ ይገባል።

➳ከአላህ ጌትነት ጋር የሚጋጩ ስንኞች
መፍጠር፣ ህያው ማድረግ፣ መግደል፣ ማብላት፣ ማጠጣት፣ መሾም፣ መሻር፣... የአላህ ብቻ ችሎታዎችና ስልጣኖች ናቸው።
እነዚህ መገለጫዎች ተውሒዱ አርሩቡቢያ ማለትም የአላህ የጌትነቱ ተውሒድ አንኳር ነጥቦች ናቸው። ሊሰመርበት የሚገባው ነገር ቢኖር የመካ አጋሪያን በአመዛኙ የአላህን ጌትነት፣ ሁሉን አስተናባሪነት አልካዱም ነበር።

➲የነሱ ከባድ ችግር በአላህ ጌትነት አምነው ነገር ግን አምልኮትን ልክ ለአላህ እንደሚሰጡት ለሌሎች ፍጡርም መስጠታቸው ነው።
በሚያሳዝን ሁኔታ ዛሬ ወገናችን የአላህን የጌትነቱን ስልጣን ሳይቀር ለፍጡር እየሰጠ ነው። መንዙማን እንደምሳሌ ብንወስድ ከአላህ ጌትነት ጋር በሚጋጩ፣ ለብቸኛው ፈጣሪ አላህ ብቻ የሚገባውን መብት ከእርሱ ውጭ ላሉ ፍጡራን በሚሰጡ በርካታ የጥፋት ስንኞች የታጨቀ ነው።

➩አስተዋዮች ያስተውሉ ዘንድ ጥቂት ምሳሌዎችን እንመልከት፡-

አላሁመሰሊ አላ ሙሐመዲ፣
መገን ነቢ የሁሉ ቀላቢ”
ለካም አንቱ ነሁ ያነቢ፣
ለመላው ኸልቅ ቀላቢ፣
ብትን ያለውን ሰብሳቢ፣ በሶፋ ቡራቅ ጋላቢ” እውን ነብዩ (صلى الله عليه وسلم) የሁሉ ቀላቢ ናቸው?
ይሄ የለየለት ቅጥፈት ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-


وَمَنْ أَظْلَمُ مِمَّنِ افْتَرَىٰ عَلَى اللَّهِ كَذِبًا أَوْ كَذَّبَ بِآيَاتِهِ ۗ إِنَّهُ لَا يُفْلِحُ الظَّالِمُونَ وَيَوْمَ نَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ نَقُولُ لِلَّذِينَ أَشْرَكُوا أَيْنَ شُرَكَاؤُكُمُ الَّذِينَ كُنتُمْ تَزْعُمُونَ ثُمَّ لَمْ تَكُن فِتْنَتُهُمْ إِلَّا أَن قَالُوا وَاللَّهِ رَبِّنَا مَا كُنَّا مُشْرِكِينَ انظُرْ كَيْفَ كَذَبُوا عَلَىٰ أَنفُسِهِمْ ۚ وَضَلَّ عَنْهُم مَّا كَانُوا يَفْتَ

➧በአላህም ላይ ውሸትን ከቀጣጠፈ ወይም በአንቀፆቹ ካስተባበለ ሰው ይበልጥ በደለኛ ማነው? እነሆ በደለኞች አይድኑም። ሁላቸውንም የምንሰበስብበትንና ከዚያም ለእነዚያ ለአጋሩት እነዚያ ተጋሪዎች ናቸው ብላችሁ ታስቧቸው የነበራችሁት ተጋሪዎቻችሁ የት ናቸው የምንልበትን ቀን (አስታውሱ)። ከዚያም መልሳቸው በጌታችን በአላህ ይሁንብን አጋሪዎች አልነበርንም ማለት እንጂ ሌላ አትሆንም። በነፍሳቸው ላይ እንዴት እንደዋሹና ይቀጣጥፉት በነበሩት ነገር ከእነሱ እንዴት እንደተሰወረ ተመልከት።” [አልአንዓም፡ 21-24

✍ኢንሻአላህ ይቀጥላል ◉ ◉ ◉ ◉

📚መንዙማ ከሚለው ከሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ

➳አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!


በተለያዩ እውቀቶች ይጠቀሙ ዘንድ ወደ ቻናላችንችይቀላቀሉ!!
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
قَالَ إِنَّمَا أَشْكُو بَثِّي وَحُزْنِي إِلَى اللَّهِ وَأَعْلَمُ مِنَ اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُونَ

«ጭንቀቴንና ሐዘኔንና የማሰሙተው ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ» አላቸው፡፡


يَا بَنِيَّ اذْهَبُوا فَتَحَسَّسُوا مِن يُوسُفَ وَأَخِيهِ وَلَا تَيْأَسُوا مِن رَّوْحِ اللَّهِ ۖ إِنَّهُ لَا يَيْأَسُ مِن رَّوْحِ اللَّهِ إِلَّا الْقَوْمُ الْكَافِرُونَ

«ልጆቼ ሆይ! ሂዱ፤ ከዩሱፍና ከወንድሙም (ወሬ) ተመራመሩ፡፡ ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሓዲዎች ሕዝቦች እንጂ ተስፋ አይቆርጥም» (አለ)፡፡

فَلَمَّا دَخَلُوا عَلَيْهِ قَالُوا يَا أَيُّهَا الْعَزِيزُ مَسَّنَا وَأَهْلَنَا الضُّرُّ وَجِئْنَا بِبِضَاعَةٍ مُّزْجَاةٍ فَأَوْفِ لَنَا الْكَيْلَ وَتَصَدَّقْ عَلَيْنَا ۖ إِنَّ اللَّهَ يَجْزِي الْمُتَصَدِّقِينَ


በእርሱም ላይ በገቡ ጊዜ «አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፡፡ ርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፡፡ ስፍርንም ለኛ ሙላልን፡፡ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና» አሉት፡፡

قَالَ هَلْ عَلِمْتُم مَّا فَعَلْتُم بِيُوسُفَ وَأَخِيهِ إِذْ أَنتُمْ جَاهِلُون

«እናንተ የማታውቁ በነበራችሁ ጊዜ በዩሱፍና በወንድሙ ላይ የሰራችሁትን ግፍ ዐወቃችሁን» አላቸው፡፡


قَالُوا أَإِنَّكَ لَأَنتَ يُوسُفُ ۖ قَالَ أَنَا يُوسُفُ وَهَٰذَا أَخِي ۖ قَدْ مَنَّ اللَّهُ عَلَيْنَا ۖ إِنَّهُ مَن يَتَّقِ وَيَصْبِرْ فَإِنَّ اللَّهَ لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ


«አንተ በእርግጥ አንተ ዩሱፍ ነህን» አሉት፡፡ «እኔ ዩሱፍ ነኝ፡፡ ይህም ወንድሜ ነው፡፡ አላህ በኛ ላይ በእርግጥ ለገሰልን፡፡ እነሆ! የሚጠነቀቅና የሚታገስ ሰው (አላህ ይክሰዋል)፡፡ አላህ የበጎ አድራጊዎችን ዋጋ አያጠፋምና» አለ፡፡

➧እስኪ እነዚህን የቁረአን አያዎች አስተንትኗቸው ምንን ተገነዘባችሁበት?
Audio
◾️ተከታታይ የቂርአት ፕሮግራም
〰〰〰〰〰〰〰〰〰

➡️ ሸርህ አቂደቱል ዋሲጥያ የፈውዛን

➰ክፍል ②⑦➰
〰〰〰〰〰

🎙አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሁለት ➲ጠቃሚ እውቀት ለባለቤቱ የሚመራበት ብርሃንና ነጸብራቅ ነው፡፡ አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል وَكَذَٰلِكَ أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ رُوحًا مِّنْ أَمْرِنَا ۚ مَا كُنتَ تَدْرِي مَا الْكِتَابُ وَلَا الْإِيمَانُ وَلَٰكِن جَعَلْنَاهُ…
➭የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት

➲የዓሊምን ደረጃና ቦታ በተመለከተ
“ሙስነድ” እና ሌሎች የሐዲስ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ሐዲሶች አብራርተውት ይገኛሉ፡፡ረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይና ታላቅ በሆነው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

➧“እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው ፤ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ ያመቻችለታል፡፡
የሚሰሩትን ስራ በመውደዳቸው መላኢካዎች ለእውቀት ፈላጊዎች ክንፋቸውን ያኖራሉ፡፡


➭ለዓሊም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ፤ በባህር ውስጥ የሚገኙት አሳዎች ሳይቀር ኢስቲግፋር (ይቅርታን) ይጠይቁላቸዋል፡፡ እውቀት ያለው ዓሊም ፣ እውቀት ከሌለው የአላህ ባሪያ ጋር ያለው ልዩነት ልክ በበድር (ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት) ሌሊት በሚወጣው ጨረቃና በሌሎች ከዋክብት መካከል እንዳለው ልዩነት ነው፡፡ ዑለሞች የነብያቶች ወራሾች ናቸው፡፡

➛ነብያቶች ዲናርም ፣ ዲርሃምም አላወረሱም፡፡ ያወረሱት ዒልምን ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ (ከዒልም) የያዘ ፣ የተነባበረ ድርሻ ያዘ፡፡” አህመድ፡21715 አቡዳውድ፡ 3641 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አቡዳውድ፡3671

➳አቡ ሁረይራ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ እንዳስተላለፉ:- ጦበራኒ “አውሰጥ” በተባለው የሐዲስ መዛግብት “ሀሰን” በሆነ ደረጃ ዘግበውታል፡፡ አቡሁረይራ በመዲና ገበያ መካከል ሲያልፍ ፣ ለተወሰነ ሰዓት ቆም አለ፡፡ “እናንተ ገበያተኞች ! ምን ደካማ አደረጋችሁ!” በማለት ተናገረ፡፡

➧“አቡሁረይራ ሆይ! ምንድን ነው?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁት፡፡ “የረሡል صلى الله عليه وسلم ንብረት እየተከፋፈለ የእናንተን ድርሻ ሳትይዙ ከዚህ ሆናችኋል!?” በማለት ምላሽ ሰጣቸው፡፡ “የት ነው ያለው?” በማለት ጠየቁት፡፡ “መስጅድ ውስጥ ነው” አላቸው።ወደ መስጅድ ፈጥነው ገሰገሱ፡፡ ደርሰው እስኪመለሱ ድረስ ቆሞ ጠበቃቸው፡፡ “ለእናንተ ምን አላችሁ?!” አላቸው፡፡ “አቡሁረይራ ሆይ! መስጅድ ሄድን ከውስጥ ገባን ፤ የሚከፋፈል ነገር ማየት አልቻልንም” አሉት፡፡

አቡሁረይራም “ከመስጅድ ውስጥ አንድንም አላያችሁ?!” በማለት ጠየቃቸው፡፡ “ከፊሎቹ ሶላት እየሰገዱ ፣ከፊሎቹ ቁርኣን እየቀሩ ፣ ከፊሎቹ ስለሀላልና ስለሀራም እያወሱ አይተናል” በማለት ምላሽ ሰጡት፡፡ አቡሁረይራ “ወዮላችሁ! የረሡል صلى الله عليه وسلم ውርስ ብሎ ማለት እኮ እርሱ ነው” በማለት መልስ ሰጣቸው፡፡ ጦበራኒይ ፊል አውሰጥ፡ 1429 ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል ሶሂህ ተርጊብ ወተርሂብ፡83

➛ይህ ነው የነብያት ውርስ ማለት፡፡ ነብያቶች የወርቅ ወይም የብር ገንዘብ አያወርሱም፡፡ ነብያቶች እውቀትን ነው የሚያወርሱት፡፡ የአንድ ሰው የእውቀት ድርሻው ከፍ ባለ ቁጥር ፣ ከነብያቶቸ ውርስ ድርሻው ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል”
ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡1037
◍
◍
◍
◍🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል


📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
Audio
♦️ تلاوة من سورة الواقعة
♦️ القارئ: #إبراهيم_البصيلي
•••━══❁✿❁══━•••
➲ቤትህን በቁርአን አድምቀው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

◾️ ‏قال الشيخ سليمان الرحيلي :

◀البَيْتُ الذي تُقرأُ فِيه سُورة البقرة تَفِرُّ مِنهُ الشياطين،ولكِن مَنْ الذي يَقرأُ سُورة البقرة في بَيْتِه اليوْم ،أَفْذَاذٌ مِنَ النَّاس قِلَّة! ولِذلِك اِسْتَوْطَنَت الشياطين كثيرًا مِن البيُوت

➧ሸህ ሱለይማን አሩሀይሊይ (አላህ ይጠብቃቸው) እንዲህ ይላሉ።

➳ሱረቱል በቀራ የሚቀራበት ቤት ሸይጣን አይገባም በሩቁ ይሸሻል
➳ነገር ግን በአሁን ሰአት ማን ነው ሱረቱል በቀራ በቤቱ ሚቀራው?
➳ይህንን ተግባራዊ ሚያደርጉና ሚተገብሩት ግን ጥቂት ሰዎች ናቸው