💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
14.2K subscribers
4.91K photos
2.23K videos
164 files
13.3K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot
Download Telegram
🔖 ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ 

"የሙእሚን ኃይሉ ከልቡ ይመነጫል።
ልቡ በተጠናከረ መጠን ሰውነቱም ይጠነክራል። ፋጅር (አላህን የማይታዘዝ ሰው) ግን ምንም እንኳን በአካል ጠንካራ ቢሆንም፣ በችግርና በፈተና ጊዜ ከሁሉ ይልቅ ደካማ ይሆናል፤ በጣም በሚያስፈልገው ጊዜ የአካሉ ኃይል ይተወዋል። የፋርስና የሮም ንጉሣዊ ኃይሎችን አስተንትን፤ እጅግ ብርቱ ሠራዊትና አካላዊ ኃይል ነበራቸው፣ነገር ግን በጣም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ያ ኃይል አልጠቀማቸውም። አላህም የኢማን ሰዎችን በልባቸው ጽናትና በአካላቸው ብርታት አጠንክሮ በእነርሱ ላይ ድል አጎናጸፋቸው።"

• ابن القيم | الداء والدواء صـ (١٣٦).📚


=
t.me/https_Asselefya1
« ከአላህ ታላላቅ ፀጋዎች መካከል አንዱ፣ ሳትናገር የሚረዳህን ሰው መስጠቱ ነው።
ቃል ሳትተነፍስ ልብህን እንደሚያዳምጥ፣ ውስጥህንም እንደሚረዳ ይሆናል። ለነፍስ ዕረፍት፣ ለልብም እጅግ ውድ የሆነ ሰው ነው። አላህ የምንወዳቸውን ሰዎች በየትኛውም ስፍራ ቢሆኑ ይጠብቃቸው፤ ምክንያቱም በልባችን ውስጥ ልዩና የማይረሳ ስፍራ አላቸው።»

╭┈───────
╰┈➤
t.me/https_Asselefya1   
«መልካም ሥራ ያለው ሰው በዚያ ይበልጥ ይትጋ፤ ወንጀል ውስጥ ያለ ሰው ግን ከወንጀሉ ይራቅ! እኛ ያለነው ዲኑን አጥብቆ የሚይዝ ሰው ትኩስ ፍምን እንደያዘ በሚመስል ፈተና ዘመን ነው።»

=
ቅድሚያ እራሳችንን እንፈትሽ
ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ሙ ኑር
ራሳችንን እንፈትሽ

አሏህን ፍሩ እያልን ወንጀሎችን አናተራምስ !

ከዘረኝነት እያስጠናቀቅን ዘረኛ መሆን ....


https://t.me/MerkezulimamiAhmed
የህይወት እንቅፋቶችን አትጥላቸው።  እነርሱ ላንተ ብለው የተፈጠሩ ናቸው። የህይወትን ጥፍጥና የምትገነዘበው በነርሱ ውስጥ ነው። እንቅፋቶች ባይኖሩ የህይወትን ምንነት መረዳት ይከብድህ ነበር። አስተውል! ጨለማ ሳይኖር የብርሃንን ጥቅም መረዳት ይርቅሃል።
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
🔖 የጓንት መልበስ ሸሪዓዊ ሑክሙ

ጓንት መልበስ ከሴት ሶሓባዎች (አላህ መልካም ስራቸዉ ይዉደድላቸዉና) የተለመደ ልማድ ነበር።

🔖 ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፦
"ሴት ከቤቷ ስትወጣ እጆቿን፣ እግሮቿን እና ፊቷን በሚሸፍን ማንኛውም ነገር መሸፈን ግዴታ ነው። ነገር ግን ከሁሉ የተሻለው ጓንት መልበስ ነው፤ ምክንያቱም ይህ የሴት ሶሓባዎች (አላህ መልካም ስራቸዉ ይዉደድላቸዉና) ከቤት ሲወጡ የነበረ ልማዳቸው ነበር።"

ማስረጃውም የነቢዩ ﷺ ንግግር ነው። ሴት በኢሕራም ሁኔታ ላይ ስትሆን፦"ጓንት አትልበስ።" ብለዋል።
ይህም ጓንት መልበስ በሴት ሶሓባዎች መካከል የተለመደ ልማድ እንደነበረ ያሳያል
።


=
t.me/https_Asselefya1
«ልብህ ሁሉንም ነገር ለመያዝ አይችልም፤ ስለዚህ ለሚያስፈልገው እና አስፈላጊው ነገር ብቻ ቦታ እንዲኖረው አድርግ። »

=
« ገንዘብ ደስታን አይገዛም ያለህ
ሰውዬ እራሱ ልጁን ለደሀ አይድርም‼️

​ወጥተህ ስራ Bro💪

=
«የሚዘገይ ነገር ቢኖር፣ ጌታህ በተሻለ ነገር ሊተካው ስለሚፈልግ ነው። ኸይረኛዉ ጌታ ኸይር ነገር በስተቀር ሌላ አያመጣም።»

=
t.me/https_Asselefya1
" አንዲት ሴት ለልጆቿ የምታበረክተው የመጀመሪያውና ታላቁ ስጦታ፣ ጥሩ አባት መምረጥ ነው።"

=
t.me/https_Asselefya1
«ዕረፍትን የሚፈልግ ሰው፣ ከልቡ ውስጥ የሰዎችን ነገር ያውጣ፤ እውነተኛ ዕረፍትን ያገኛል።»

=
t.me/https_Asselefya1
🔖 የሸይጣን ምክትል ማን እነደሆነ ታውቃላችሁን?!

ኢብኑል ቀዪም(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦

"በምድር ላይ የሽይጣን ምትኮች ማለት፦ ሰዎችን ሸሪዓዊ ከሆኑ ዕወቀት እንዳይገበዩ ዐቀበት የሚሆኑ ሰዎች ናቸው።እንደነዚህ አይነት ሰዎች ከጂን ሸይጣኖች የበለጠ ሰዎችን ይጎዳሉ፣ምክንያቱም በልቦናዎች እና ቅን በሆኑ በአላህ መንገዶች መካከል ጋሬጣዎች ናቸውና።"

«ሚፍታሑ ዳሩ ሰዓዳ"(1/170)»

=
t.me/https_Asselefya1
« ለአፍታ የሚያስደንቅህን ውበት አትፈልግ፤ ይልቁንም ዲን (ሃይማኖት) እና መልካም ሥነ ምግባር ያለውን ሰው ፈልግ፤ እርሱ ዕድሜ ልክ ደስታን ያጎናጽፍሃል። የሰው ደስታ የሚጀምረው በመልካም ምርጫው ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
"ሰዎችን ከሱና ማስወጣት ከባድ ነው" ይላሉ ኢማሙ አሕመድ። ይሄ ንግግር
1. የሱናን ጥብቅ እና ታላቅ ደረጃ ይጠቁማል። የሱናን ትልቅ ዋጋ (ቂማ) የተገነዘበ ሰው ሑክም ማስተላለፍ ላይ ይጠነቀቃል።
2. ሰውን ያላግባብ ከሱና ማስወጣት ምን ያህል ከባድ አደጋ እንደሆነ እንወስዳለን። ጉዳዩ ከግለሰብ አልፎ ደዕዋን ወይም ህዝብን የሚጎዳ አያያዝ ካለው ደግሞ መዘዙ ይበልጥ የከፋ ይሆናል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ወላጆችህን ከቻልክ አቅምህ በሚፈቅደው አስደስታቸው። ካልሆነልህ ግን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የመከፋታቸው፣ የመጨነቃቸው፣ የመተከዛቸው ሰበብ አትሁን። "አይዟችሁ"፣ "ከጎናችሁ ነኝ" ማለት ቢቀር "አትስጉ፣ ደህና ነኝ" ማለት ልናሳጣቸው አይገባም። ሰርቶ ማገዝ፣ ከጎን መቆም ካቃተ፣ ፊትን ከመከስከስ፣ የሻከረ ቃል ከመናገር መቆጠብ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor
t.me/IbnuMunewor
اللهم لا تجعلني من الغافلين،
ولا من المحرومين من لذّة القرب منك،
واغفر لي إن قصّرت،
وأكرمني إن ضعفت،
وأمسِك بيدي إن تعثّرت،
فلا ملجأ لي إلا رحمتك يا الله.
=
🔖 ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፦

«ታገሺ፣ ምንዳሽንም ከአላህ ተስፋ አድርጊ፤ በሸሪዓ በተደነገገው ሒጃብሽ ላይ ጽኑ ሁኚ። ሰዎች ‘አንቺ ጽንፈኛ ነሽ’፣ ‘በጣም ጥብቅ ነሽ’ ወይም ተመሳሳይ ንግግር ቢናገሩሽ አይረብሽሽ። ሀቅን እንድናውቅና እርሱንም እንድንከተል አላህን ለሁላችን እንለምነዋለን።»

[📚 فَتَاوَى نُورٌ عَلَى الدَّرْبِ (١١/١٢٢)].

=
t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ ከአዲስ አበባ ወደ ጃማ ደጎሎ ስንሄድ መንገድ ላይ የተቀረፀ!