💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
~ አንዳንድ ጊዜ alarm ሲጮህ ስናደድ ለሚያየኝ ሰዉ እኔ የሞላሁት አልመስለም እኮ🖐

መልካም አዳር ይሁንላችሁ 🌸

=
«ስንቱ ተዋርዶ በሚያድርበት ምሺት ተሰትሮ ማደርን ያክል ፀጋ የለም።አሁንም ሲትራህ ያ ረሕማን !

=
t.me/https_Asselefya1
«ጥንካሬ ሁል ጊዜ በምንናገረዉ እና በምናደርገዉ ነገር ላይ አይደለም አንዳንድ ጊዜ ዝም ያልነዉ፣ የምንተወዉ ወይም ችላ የምንለዉ ላይ ነዉ።

=
t.me/https_Asselefya1
መተዉ ስንጀምር  መኖር እንጀምራለን ‼️

=
የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

أفْضَلُ الأعمالِ إِدخالُ السرورِ على المؤمِن؛ كسوتَ عورَتَه، وأَشبعتَ جوعتَهُ، أو قَضَيْتَ له حاجةً

“ከስራዎች ሁሉ በላጩ አንድን አማኝ ማስደሰት ነው። ይህም ነውሩን በመሸፈን፣ ረሃቡን በማብላት ወይም ጉዳዩን በመፈፀም ነው።”

አልባኒይ ሶሒሕ ነው ብለውታል። [አት-ተርጊብ፡ 2090]
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
ዐቅላችን ዐቅል እንዳያስተን
~

ዐቅል አላህ ለሰው ልጅ የሰጠው ትልቅ ስጦታ ነው። የሰው ልጅ በዐቅል ያመዛዝናል፣ ያገናዝባል። ይሁን እንጂ ዐቅል በወሕይ ካልታገዘ ደካማ ነው። ስለዚህ ከዐቅል ይልቅ ቀዳሚው ወሕይ ነው፣ ቁርኣንና ሶሒሕ ሐዲሥ። ዐቅልን ፈራጅ ቀዳጅ ማድረግ እና ከወሕይ በላይ ማንገስ ዐቅልን ጣዖት አድርጎ መያዝ ነው የሚሆነው። ሸሪዐዊ ማስረጃን ገሸሽ በማድረግ "እኔኮ ዐቅል አለኝ፤ ሁሉንም በራሴ ነው የምወስነው" አይነት ልክፍት ከተሰማህ በራስ መኮፈስ፣ ዐቅልን ማምለክ ውስጥ ገብተሃል። ይሄ በዐቂዳ ጉዳይ ላይ ዐቅልን እናስቀድማለን የሚሉት የአሻዒራና የማቱሪዲያ ቡድኖች የወደቁበት ጥፋት ነው። ከዐቅል ጋር አይገጥሙም በሚል ሃሰተኛ ምክንያት ቁርኣንና ሐዲሥን በመግፋት የአላህን ሲፋት ሲያስተባብሉ ይታያሉ። ሌሎች በቀደዱላቸው እየፈሰሱ እንጂ ከዐቅል ጋር የማይሄደው የነሱ ፍልስፍና ነው።

በተጨማሪም ዛሬ ዛሬ አካዳሚ ትምህርት ገፋ ያደረጉ አንዳንድ አካላት ዐቅልን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ የሸሪዐ ጉዳዮች ላይ አፈንጋጭ አቋሞችን የሚያራምዱበት ሁኔታ አለ። አንዳንዶች የትምህርት ማእረጋቸው ብቅል ሆኖ ይፈትናቸዋል። አካዳሚ ስለተማሩ ብቻ ያላቅማቸው በየዘርፉ ጥልቅ የሚሉ የ'ርጎ ዝንብ ይሆናሉ። እየውልህማ አባኪያ!

1. ዐቅል በቂ ቢሆን ኖሮ ነብይ አይላክም ነበር። ነብይ የሚላከው ሰዎች የማያውቁትን መለኮታዊ ነገር ለማስተማር ነው።
2. ዐቅል በቂ ቢሆን ኖሮ ቁርኣን ባልወረደ ነበር። በዐቅል ብቻ ሌላው ህዝብ ቀርቶ ነብያችን ﷺ እንኳ የኢማንን ዝርዝር አያውቁም ነበር። አላህ እንዲህ ይላል፦
{ وَكَذَ ٰ⁠لِكَ أَوۡحَیۡنَاۤ إِلَیۡكَ رُوحࣰا مِّنۡ أَمۡرِنَاۚ مَا كُنتَ تَدۡرِی مَا ٱلۡكِتَـٰبُ وَلَا ٱلۡإِیمَـٰنُ وَلَـٰكِن جَعَلۡنَـٰهُ نُورࣰا نَّهۡدِی بِهِۦ }
"እንደዚሁም ወደ አንተ ከትእዛዛችን ሲሆን መንፈስን (ቁርኣንን) አወረድን፡፡ መጽሐፉም እምነቱም ምን እንደሆነ የምታውቅ አልነበርክም፡፡ ግን (መንፈሱን) ከባሮቻችን የምንሻውን ሰው በእርሱ የምንመራበት ብርሃን አደረግነው፡፡" [አሹራ፡ 52]

3. ዐቅል ልክ እንደሌሎች የስሜት ህዋሳት ወሰን (limit) አለው። ጆሮ ድምፅ በራቀው ቁጥር መስማቱ እየቀነሰ እየቀነሰ ሄዶ መጨረሻ ላይ ይጠፋበታል። አይን ካጠገቡ ያለ ነገር በራቀ ቁጥር እያነሰ ሄዶ ከነ ጭራሹ ከእይታ ይሰወርበታል። አእምሮም እንደዚያው ነው። ሁሉን ነገር የመረዳት አቅም የለውም።

4. ዐቅል ከስህተትና ከጉድለት ፍፁም አይደለም። "ከሰው ስህተት ከብረት ዝገት " የሚባለው ያለ ምክንያት አይደለም። ፍፁም የሆነው ማስረጃ ወሕይ ነው፣ መለኮታዊ ራእይ። ዐቅል በኋላ ታሪክ፣ በአስተዳደግ፣ በትምህርት፣ በልማድ፣ በአካባቢ፣ ... ተፅእኖ ስር ይወድቃል። በዚህ የተነሳ ነው አረዳዳችን የሚራራቀው። ይህም እውነታ ዐቅል ወጥ የሆነ መለኪያ እንደሌለው ያሳያል። ወጥ ቢሆን ኖሮ በህንድ ፍልስፍና፣ በግሪክ፣ በሮማ፣ በፋርስ፣ በቻይና፣ እንዲሁም በዛሬው የምእራቡ ዓለም እና በምስራቁ ዓለም ፍልስፍናዎች መካከል ልዩነቶች ባልተንፀባረቁ ነበር። የነዚህ ሃገራት ፈላስፎችም ለተውሒድ በተመሩ ነበር።.

5. ዐቅል አጥጋቢ መለኪያ ቢኖረው ኖሮ ዐቅልን እንከተላለን የሚሉት ጀህሚያዎች፣ ሙዕተዚላዎች፣ አሻዒሪዎችና ማቱሪዲያዎች ባልተለያዩ ነበር። ዐቅል በቂ አጥጋቢ መለኪያ ቢሆን ኖሮ ሌላው ቀርቶ በአንድ ቡድን ውስጥ እንኳ መለያየት ባልኖረ ነበር። አሻዒራን እንውሰድ። ሙፈዊዳ እና ሙአዊላ ተብለው ለሁለት ይከፈላሉ። ሁለቱ ተቃራኒ መንገዶች ናቸው። በሌላ በኩል የቀደሙት አሻዒራዎች የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ጨምሮ በርካታ የአላህን ሲፋት ያፀድቃሉ። የኋለኞቹ ያስተባብላሉ። ወደ ግለሰብ ዝርዝር ብንገባ ደግሞ ልዩነቱ ይሰፋል።

6. ዐቅል አስተማማኝ መለኪያ ቢሆን ኖሮ ግለሰቦች ከአንድ አቋም ወደ ሌላ ባልተገላበጡ ወይም በተለያዩ ከታቦቻቸው ላይ የተለያዩ አቋሞችን ባላንፀባረቁ ነበር። ኢብኑል ጀውዚን ምሳሌ መውሰድ ይቻላል። አንዴ ተእዊል፣ አንዴ ኢሥባት፣ ሌላ ጊዜ ተፍዊድ ላይ ተወዛውዘዋል።

7. ዐቅል በቂ መለኪያ ቢሆን ኖሮ በዐለም አቀፍ ደረጃ ፖለቲከኞች እና ኢኮኖሚስቶች ወጥና የጋራ መስመር መንደፍ በቻሉ ነበር። እውነታው ግን ሌላ ነው። የካፒታሊዝምና የሶሻሊዝም ፍጥጫ ለዚህ ሁነኛ ማሳያ ነው። በሀገራችንም በ1960ዎቹ እና ሰባዎቹ እንደ አሸን የፈሉ የፖለቲካ ቡድኖች ሁሉም ለማለት በሚቀርብ ሶሻሊስቶች ነበሩ። ነገር ግን መማራቸውም ዐቅላቸውም ያላግባባቸው የሚጠፋፉ ቡድኖች ነበሩ።

ስለዚህ በዐቅል እያመሀኙ ከቁርኣንና ሐዲሥ ማስረጃዎች መራቅ ከራሱ ከዐቅል ጭምር መራቅ እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል። ሲጀመር ጤነኛ ዐቅል ከትክክለኛ ወሕይ ጋር አይጋጭም። ስለሆነም ለወሕይ እጅ ለመስጠት መድረቅረቅ አይገባም። በዚህ ረገድ የኢማን የስኬት ማማ ላይ የደረሱትን የሰለፎችን አቋም እንመልከት፦

1. ዑመር ብኑል ኸጣብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
‏إياكم وأؾحاب الرأي، فإنهم أؚداإ السنن، أعيتهم الأحاديث أن يحفظوها فقالوا بالرأي، فضلوا وأضلوا
“ከአስተያየት ባለቤቶች ተጠንቀቁ። ምክንያቱም እነሱ የሱና ጠላቶች ናቸው። ሐዲሦችን መያዝ ስለተሳናቸው በራሳቸው አስተያየት ወሰኑ፣ በመሆኑም እነሱም ጠመሙ፣ ሌሎችንም አጠመሙ።” [ኡሱል አል-ኢዕቲቃድ፣ አላለካኢይ፡ 57]

2. ዐሊይ ብኑ አቢ ጣሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፦
لو كان الدينُ بالرأي لكان أسفلُ الخفِّ أولَى بالمسحِ من أعلاهُ ، وقد رأيتُ رسولَ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلم يمسحُ على ظاهرِ خفَّيهِ
“ሃይማኖት በራስ አስተያየት የሚመራ ቢሆን ኖሮ፣ የጫማ ታችኛው ክፍል ከላይኛው ክፍል ይልቅ ለማበስ ቅድሚያ ይኖረው ነበር። ነገር ግን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ የጫማቸውን የላይኛው ክፍል ሲያብሱ ነው ያየሁት።” [አቡ ዳውድ፡ 162]

ስለዚህ የመፍትሄው ቁልፍ አቅምን ማወቅ ነው። ነፍሲያን መርገጥ።

(ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 22/1447)
=
የቴሌግራም አድራሻ
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
#አደራ_የባለቤትህን_ልብ_ተንከባከበው በመካከላችሁ ያለውን ፍቅር አጠናክረው፡፡

1. የህይወትን ነፃነት ስጣት
2. ስጦታ ግዛላት
3. ስሟን አቆላምጠህ ጥራት
4. መልካምን ሰላምታ ተለዋወጣት
5. ወደ ቤት ስትገባ ሳማት
6. ድንገተኛ የምትመኘውን እና የምትፈልገውን አድርግላት
7. መግባባትን መርህህ አድርግ
8. የሚያነቃ ልቧን የሚያንጠለጥል ታሪክ አስተምራት
9. ወደ ቤት ስትገባ ስለ ስራህ ሳይሆን ስለ ውሎዋ አዳምጣት
10. ወደ ቤት ስትገባ ሳሎን ቤት በነፃነት ብዙ ተቀመጥ
11. የሰራችውን ምግብ በአድናቆት ተመገብ
12. ልብሱ ያምራል በላት
13. ስታረግዝ ተንከባከባት
14. ስጦታ ስትሰጥህ በጣም በፀጋ ተቀበላት
15. ስታናግራት በልዩ በሚማርክ በመስህብ በመልካም አገላለፅ አናግራት
16. የምትወድልህን ልብስ ልበስላት
17. ከቻልክ ስለ እርሷ ቁንጅና ተክለ ቁመና የሚገልፅ ግጥም ፃፍላት
18. ስትለብስ በጣም እንደሚያምርባት ንገራት
19. በማክበር የፍቅር ቃላቶችን በመጠቀም ልቧን አስደስታት
ከልብህ ከሆነ መንገድ አታጣም
ከልብህ ካልሆነ  ለመተዉ ሰበብ አታጣም።

=
t.me/https_Asselefya1
~ እከሌ ልቤ ሰበረኝ ሸወደኝ አታለለኝ....እያላችሁ የምታለቃቅሱ ስንተየ ተመከረ ተዘከረ ለምን አሰሙም አታነቡም ግድ እናንተ ላይ እስኪደርስ ለምን ትጠብቃላችሁ አረ ተዉ እባካችሁ አንብቡ አድምጡ ሁሌ ወቀሳ ሁሌ ለቅሶ አይበቃም ወይ ይህ ነገር ?!

=
~ ማንም ሰዉ እኮ እንደ ልእልት አድርጌ አኖርሻለሁ ሊልሽ ይችላል በዚህ ጉዳይ ቃሉን የማያጠፋዉ «አባትሽ» ብቻ ነዉ።

=
t.me/https_Asselefya1
🔖መዉሊድ እና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም !

«በሺርክ  የተወረወረዉን፣ በኹራፋት ያበደዉን፣ በመዉሊድ የታጀበዉን  የሱፍዮች እስልምና "ነባሩ  እስልምና" እያሉ የሚያሞካሹ  ጩኸቶችን አልፉ አልፉ  እንሰማለን።  ይህንን የማይቀበለዉን "ወሃቢ" በማለት  በሙሐመድ ኢብኑ አብዲል ወሓብ  የተጠነሰሰ መጤ ኢስላም እንደሆነ ሊነግሩን ነዉ ። ይሄ "ነባሩ" የሚሉት ኢስላም ግን  በፍፁም  እንግዳ የሆኑ  መጤ አስተሳሰቦችን  አጭቆ የያዘ"ኢስላም"ነዉ።  የዚህ ፎርጅድ "ኢስላም" አብይ መገለጫ የሆነዉን መዉሊድ እንደ አብነት ብንወስድ  ደጋፊዎቹ ሳይቀሩ  ከነባሩ ኢስላም ዉስጥ  የማይታወቅ መጤ እንደሆነ መስክረዋል። ለምሳሌ፦

❶.ÂŤ አቡ ሻማህ፦ በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ተግባሮች ያማረ ከሆነዉ  የላቀዉ አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ  በያመቱ ከነብዩ  የልደት ቀን ጋር በሚገጥመዉ ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎችና፣በጎ ነገሮች ፤ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነዉ። (አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢድዕ ወልሐዋዲሥ:95) የተመሠረተበት አስተዉሉ።

❷. ኢብኑ ሐጀር አል ዐስቀላኒ፦ የመዉሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐህ ነዉ። ከሶስቱ ክፍለ_ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም። {አልሓዊ ሲልፈታዊ:1/88}

❸. ሰኻዊ፦ የተከበረዉ መዉሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ_ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተዉ ከዚያ በኋላ ነዉ። {ሱቡሉል ሁዳ ወርረሻድ:1/439}

➍.« አትተዝመንቲ፦ የመዉሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም። {አስሲረቱ አሽሻኒያህ:1/441}

❺.« አልሓፊዝ አልዒራቂ፦ ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናዉቅም። (ተስኒፉል አዛን:136)

✍ኢንሻ አላህ ይቀጥላል...

=
t.me/https_Asselefya1
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦

"ዓኢሻ ሆይ! ምስኪንን አትመልሺ፣ በተምር ክፋይ እንኳ ቢሆን (አስተናጋጂ)። ዓኢሻ ሆይ! ምስኪኖችን ውደጂ። አቅርቢያቸውም። አላህ በትንሳኤ ቀን ያቀርብሻልና።" [ሶሒሑ ተርሚዚይ፡ 2352]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ሚስት ከሆንሽ ባልሽን ባል ከሆንክ ደግሞ ሚስትህን ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ዐይኗን በስስት የመመልከት ልማድ አዳብር ። በዐይኗ ውስጥ ሩኋን ፈልግ ። እየተመለከትካትም ስለሷ መልካም ነገሮችን አስብ ።

ወዳጄ ፍቅር እንደ ጭቃ ተጠፍጥፎ የሚሰራ የልፋት ውጤት ነው ።በጥረታቸሁ ልክ በትዳርና የፍቅር ግንኙነታችሁ ትደሰታላችሁ  ።

ባረከሏሁ ፊኩም ያላገባችሁ ወንድምና እህቶች ለጊዜው መስታወት ፊት ቆማችሁ እራሳችሁ ላይ ማፍጠጥ ትችላላችሁ  ....