💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወንድምህን አትበድለዉ ! እሱም እንዲበደል አትተወዉ በደሉን መከላከል እየቻልክ በሰዉነቱበገንዘቡበክብሩ እንዲበደል አትተወዉ!

=
t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ ግንኙነትህን ቀንስ ግንኙነት ማብዛት ጥርት ያለ መጥፉ ነዉ ከኋላዉ ምንም ኸይር የለዉ። ጤናን ያጠፋልማስተዋል እና ማስተንተንን ያጠፋልከኋላ ምንም ኸይር አያመጣ። የቻልከዉ ያክል ግንኙነትህ ቀንስ የዉሸት ግንኙነት ምንም ቋሚነት የላትም ልትቆርጣት ግድ ይልሀል።

=
t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ አማኝ ወንድምህ ዝቅ አድርገህ አትመልከት፦ ጉዳዩ ቀላል አይደረግም ሙስሊም አላህ ዘንድ ታላቅ ነዉገንዘብ ባይኖረዉ፣ መከበሪያ ባይኖረዉ አማኝ እስከሆነ ድረስ አላህ ዘንድ ታላቅ ነዉ።

=
t.me/https_Asselefya1
ለአንች የሚጨነቁልሽን ተንከባከቢ  ለቀረዉ  ሰላምታ በቂ ነዉ።

=
የምትወደዉን ሰዉ  ችላ አትበል አንደማትፈልገዉ  ያስብና ትቶህ ይሄዳል።


t.me/https_Asselefya1
ጁዝ አመ መማሪያ ለልጆች መግቢያ
Sadat
መርከዝ ተውሒድ ቤተል ቅርንጫፍ
ጁዝ አመ ትርጉም መማሪያ ለልጆች መግቢያ

=
t.me/SadatKemalAbuMeryem
من حقك أن تكون حـماراً
ولكن ليس من حقـك أن ترفس الآخرين…

አህያ መሆንና እንደ አህያ ማሰብ መብትህ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሌሎችን መራገጥ እንደማትችል መረዳት አለብህ።

t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
الواسطة بين الحق والخلق አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ 【ክፍል  ❶❷】 መልእክተኞች ጥቅም ማምጣት አይችሉም። «وَقَالُوا۟ ٱتَّخَذَ ٱلرَّحۡمَـٰنُ وَلَدࣰاۗ سُبۡحَـٰنَهُۥۚ بَلۡ عِبَادࣱ مُّكۡرَمُونَ } { لَا یَسۡبِقُونَهُۥ بِٱلۡقَوۡلِ وَهُم بِأَمۡرِهِۦ یَعۡمَلُونَ } { یَعۡلَمُ مَا بَیۡنَ…
الواسطة بين الحق والخلق

አል ዋሲጠህ በይነል ሐቂ ወል ኸልቅ


ክፍል ❶❸


🛑👉ዑለማዎች የነብያት ወራሾች ናቸዉ።

«وَمَنْ سِوَی الْأنْبِيَاء ۔ مِنْ مَشَايِخِ  الْعِاْمِ  وَالدِّينِ - فَمَنْ أَثْبَتَهَم وَسَائِطَ بَيْنَ  الرَّسُولِ  وَأُمَّتِهِ يُبَلِّغُنَهُمْ،  وَيُعَلِّمُونَهُمْ ،  وَيُؤدِّبُونَهُمْ ، وَيَقْتَدُونَ بِهِمْ،  فَقَدْ أَصَابَ فِي ذَلِكَ..»

⦘⤑ ከነብያት ዉጭ  ያሉትን " የእዉቀትና የሀይማኖት መሪዎች"  በነብያት እና በሕዝቦቻቸዉ መካከል የሚያደርሱላቸዉ፣ የሚያስተምሯቸዉስርአት  የሚያሲዟቸዉ፣ በእነሱ  የሚመሩባቸዉ አስተላላፊ (ወሳኢጥ) አድርጎ ያፀደቀ  በእዚህ ላይ በእርግጥ ልክ  ነዉ።


«وَهَؤُلاَء  إِذَا  أَجْمَعُوا  فَإِجْمَاعُهُمْ  حُجَّةٌ قَاطِعَةٌ لَا يَجْتَمِعُوُنَ  عَلَی  ظَلَالَةٍ وَإِنْ تناَزَعُوا فِي شَيْءٍ رَدُّوهُ إِلَی اللهِ وَالرَّسُولِ ، إذْ الْوَاحِدُ  مِنْهُمْ لَيْسَ بِمَعْصُومِ  عَلَی الْإِطْلَاقِ ، بَلْ كُلُّ أَحَدٍ مِنْ النَّاسِ يُؤْخَذُ مِنْ كَلَامِهِ وَيُتْرَكُ : إلّا رَسُولُ اللهِ ﷺ .»

⦚ ⤑እነዚህ (የእዉቀትና የሃይማኖት መሪዎች) ከተስማሙ ስምምነታቸዉ የማያወላዉል ማስረጃ ነዉ።  ምክንያቱም በጥመት  ላይ አይስማሙምና። በአንዳች ነገር ላይ ከተወዛገቡ ወደ አላህ ﷻእና ወደ መልእክተኛዉ ﷺ ይመልሱታል።  ከእርሱ  አንዱ(በነፍስ ወከፍ) በጭራሽ ፍፁም  አይደለም። እንዳዉም እያንዳንዱ ሰዉ  ከንግግሩ የሚወሰድና የሚጣል አለዉ። የአላህ መልክተኛ ﷺሲቀሩ።

« وَقَدْ قَالَ النَّبِيُ :  الْعُلَمَاءُ وَرَثَةُ الْأنْبِيَاء  فَإنَّ الْنْبِيَاء لَمْ يُوَرِّثُوا دِينَارًا وَلَا دِرْهَمًا وإِنَّمَا وَرَّثُوا الْعِلْمَ فَمَنْ أَخَذَهُ فَقَدْ أَخَذَ بِحَطِّ وَافِرٍ

( رواه أحمد. وأبو داود، والترمزي. وابن ماجه .  وابن حبان في صحيحه . صححه الألباني :  في صحيح ابن ماجة ، وصحيح الترغيب .)
⦘⤑በእርግጥ ነብዩ እንዲህ ብለዋል፡   ዑለማዎች የነብያት  ወራሾች ናቸዉ። ነብያት ዲናርም ብርም አላወረሱም እንግዲያዉስ እዉቀት ነዉ ያወረሱት።  (እዉቀትን) የያዘ በቂ ድርሻ ያዘ። " አቡ ዳዉድ ቲርሚዚህ ኢብኑ ማጅህ እና ሌሎችም ዘግበዉታል፣ (አልባኒይ ሶሒሕ ብለዉታል። )

«وَإِنْ أثْبَتَهُمْ  وَسَائِطَ بَيْنَ اللهِ  وَبَيْنَ خَلْقِهِ --- كَالْحُجَّابِ الَّذِينَ بَيْنَ الْمَلِكِ وَرَعِيَّتِهِ --  بِحَيْثُ يَكُونُونَ هُمْ يَرْفَعُونَ إَلَی اللهِ حَوَائِجَ خَلْقِهِ ٬ فَاَللهُ  إِنَّمَا يَهْدِي عِبادَهُ وَيَرْزُقُهُمْ  بِتَوَسُّطِهِمْ،  فَالْخَلْقُ يَسْأَلُونَهُمْ  وَهُمْ يَسْأَلُونَ الله ،  كَمَا أَنَّ الْوَسَائِطَ  عِنْدَ الْمُلُكِ  .  يَسْألُونَ الْمُلُوكَ الْحَوَا ئِجَ لِنَّاسِ ، لِقُرْبِهِمْ مِنْهُمْ  وَالنَّاسُ  يَسْألُونَهُم ، أَدِبًا مِنْهُمْ أَنْ يُبَاشِرُوا سُؤَالَ الْمَلِكِ  ، أوْ  لِأَنَّ طَلَبَهُمْ  مِنْ الْوَسَائِطِ أَنْفَعُ لَهُمْ  مِنْ طلَبِهِمْ مِنْ الْمَلِكِ ، لِكَوْنِهِمْ أقْرَبَ إلَی الْمَلِكِ مِنْ الطَّلِبِ لِلْحَوَائجِ .»

⦚ ⤑በአላህ እና በፍጥረቱ መካከል ወሳኢጥ ማፀደቃቸዉ_ በንጉሳንና በማህበረሰባቸዉ መካከል እንዳለዉ አይነት ከሆነና_ እነርሱ የፍጥረታቱን ጉዳይ ወደ አላህ እንደሚያቃርቡና  አላህ ባሪያዎቹን ቀጥተኛዉን መንገድ የሚመራቸዉና የሚመግባቸዉ በእነሱ አማካኝነት ነዉ ከተባለ። በንጉሶች መካከል እንዳለዉ ወሳኢጥ ንጉሳንን ለሰዎች ጉዳይ ይጠይቃሉ። ለእነርሱ ቅርብ በመሆናቸዉ  ሰዎች እነርሱን በሆነ አደብ ቀጥታ ንጉሱን ሳይጠይቁ እነርሱ ይጠይቃሉ ለንጉሱ ቅርብ ስለሆነ። ወይም በዋሲጣ መጠየቃቸዉ  ጠቃሚ ነዉ። እነርሱ ንጉሱን ከመጠየቃቸዉ ወይም ከጉዳይ ፈላጊዉ የበለጠ ለንጉሱ ቅርብ በመሆናቸዉ ።

«فَمَنْ أَثْبَتَهُمْ وَسَائِطَ عَلَی هَذَا الْوجْهِ  : فَهُوَ كَافِرٌ مُشْرِكٌ يَجِبُ أَنْ يُسْتَتَابَ فَئِنْ تَابَ  وَإِلّا قُتِلَ . وَهَؤُلَاءِ  مُشَبِّهُونَ لِلهِ شَبَّهُوا الْمَخْلُوقَ  بِلْخَالِقِ وَجَعَلُوا لِلهِ  أَنْدَادًا .»

⦘ ⤑በዚህ አይነት መልኩ ዋሲጣዎችን ያፀደቀ ሰዉ። እርሱ ከሃዲ አጋሪ ነዉ።  እንድቶብት ተጠይቆ ካልቶበተ ይገደላል። እነዚህ ለአላህ አመሳሳዮች ናቸዉ። ፍጥረትን በፈጣሪ አመሳሰሉ ለአላህም ባላንጣን  አደረጉ።

ይቀጥላል ኢንሻ አላህ ....!

╭┈───────⦁🌺
╰┈➤
t.me/https_Asselefya1
🔖🌱 ؛

قال الشيخ ابن عثيمين - رحمه الله - :

" ينبغي للإنسان أن يجعل له نصيبًا مِن
آخر الليل ولو كان قليلًا، ولا يحقرن
شيئًا، فقد قال النبي ﷺ : «أَحَبُّ الأعمالِ إلى اللهِ أدْومُها و إن قَلَّ»،
لو تجعل لك نصف ساعة مِن آخر الليل
تقوم فيها، وتصلي ما شاء الله، وتختم
الصلاة بالوتر لكان في هذا خير كثير، وكنت من القائمين بالأسحار، المستغفرين بالأسحار، فلا تحرم نفسك الأجر ".
• اللقاء الشهري : (42)
هدايات_القرآن_الكريم_للمرأة_المسلمة.pdf
3.8 MB
•••
- هِدَاياتُ القُرْآن الكريم لَلمرْأة المُسلمة

الشّـيخ عَبد الرّزاق البَدر حفِظه الله

ሴቶች ታነቧት ታስተነትኗት ዘንድ ግብዣዬ ነዉ 🌺


•━━━ ✽ • ✽ ━━━•
ሴቶች አበባ እና ጣፋጭ በጣም ይወዳሉ አሉ ! ባሎችዬ ስጦታ እየገዛችሁ ስጧቸዉ ! ስጦታ ፍቅርን ይጨምራል።

#በፍቅር እደሩልኝ


=
አንዳንድ ሰዎች ግን የሰዉ መድሃኒት ናቸዉ። ከነሱ ጋር ስዓታት ታሳልፋለህ ሁሉ ነገር የተሻለ ሆኖ ይሰማሀል።

#صباح الخير
=
t.me/https_Asselefya1
🔖 ኪታቦች ሲፈልጉ ወደ "ሱቅ በደረቴ" ጎራ ይበሉ «ሁሉም አይነት ኪታብ» ከኛ ዘንድ ያገኛሉ።

╭┈──── ◖🇸🇦
╰┈➢
t.me/suk_bederete123

​ •┈┈•┈┈•⊰✿🇸🇦✿⊱•┈┈•┈┈•
ሳኡድ አረቢያ  ሁሉም ከተሞች እናቀርባለን
ሁለተኛ ማግባት…!?
|
~ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ! በአሁኑ ጊዜ በተለይ በወጣቶች ዘንድ ከአንድ በላይ ሚስቶችን ስለማግባት (ተዐዱድ) የሚፃፈውም የሚወራውም በዝቷል።

ይህ ርዕስ በኢስላም የተፈቀደ ቢሆንም፣ አንዳንዶች ጉዳዩን እጅግ ቀለል አድርገው ሲያቀርቡትና ሲያወሩት ይታያል።

አላህ ከ አንድ በላይ ማግባትን በ ቁርኣን የፈቀደው ከአንድ በላይ ማግባትን ብቻ ሳይሆን፣ ፍትሕን አብሮ በመደንገግ ነው።
«وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانكِحُوا مَا طَابَ لَكُم مِّنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا»

«በየቲሞችም (ፍትሕን) አለማድረጋችሁን ብትፈሩ (ከሌሎቹ) ለእናንተ የተዋበላችሁን (ሴቶች) ሁለት ሁለት፣ ሦስት ሦስትም አራት አራትም አግቡ፡፡ በመካከላቸውም አለማስተካከላችሁን(ፍትህን)ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ወይም እጆቻችሁ የጨበጧትን (ባሪያ) ያዙ፡፡ ይህ ወደ አለመበደል በጣም የቀረበ ነው፡፡» ይላል።

ይህ አንቀጽ የንግግራችን ሁሉ መሰረት ነው። ፍቃዱ ከተሰጠ በኋላ ወዲያውኑ፦
"فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً"
(አለማስተካከላችሁን(ፍትህን)ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ) የሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ ይመጣል።
«ብትፈሩ» (خِفْتُمْ) የሚለው ቃል ጥርጣሬንም ይጨምራል። ፍትሕን ስለማስፈኔ እርግጠኛ ካልሆንኩ ወይም ከተጠራጠርኩ፣ መንገዱ አንድ ብቻ ነው።አንድ ብቻ!
"فَوَاحِدَةً"
📌ፍትሕ እዚህ ላይ የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
① የቁሳቁስ ፍትሕ፦
በሚስቶች መካከል በመኖሪያ ቤት፣ በቀለብ፣ በልብስ እና በሌሎችም ቁሳዊ ፍላጎቶች ላይ ፍጹም እኩልነትን ማሳየት።
② የጊዜ ፍትሕ፦
የማደሪያ ጊዜን በሚስቶች መካከል በእኩልነት መከፋፈል።ይህንን የፍትሕ ሚዛን መሳት የሚያስከትለው ቅጣት እጅግ ከባድ መሆኑን ነብያችን (ﷺ) አስጠንቅቀዋል፦
"مَنْ كَانَتْ لَهُ امْرَأَتَانِ فَمَالَ إِلَى إِحْدَاهُمَا جَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ وَشِقُّهُ مَائِلٌ "
«ሁለት ሚስቶች ኖረውት ወደ አንደኛዋ (በአያያዝ) ያደላ ሰው፣ የቂያማ ቀን አንደኛው የሰውነቱ ክፍል ሽባ ሆኖ (ተዘምሞ) ይመጣል።»
📚(አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ እና ሌሎችም በሰሂህ ሰነድ ዘግበውታል)

እስቲ ለአፍታ ቆም ብለን እናስብ! በዚህ ከባድ ቅጣት ፊት እየቀለድን ነው? የአንዲትን ሀቅ በአግባቡ ሳንወጣ፣ ሁለተኛውን በደል ለመጨመር መሮጣችን ምን የሚሉት ነው።

ቆም ብለን እናስብ! ጉዳዩን የስሜት ማብረጃ ሳይሆን፣ ከባድ የዲን አደራ እንደሆነ እንገንዘብ።
📚ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦
   "والأفضل مع قيامه بحق الواحدة الاقتصار عليها، وإنما أبيح التعدد لمن احتاج إليه ولم ‏يجاوز العدل"

«የተሻለውና በላጩ ሰውየው የአንዷን ሚስት መብት በአግባቡ የሚወጣ ከሆነ በአንዲት ላይ መብቃቃቱ ነው። ከአንድ በላይ ማግባት የተፈቀደው (አስገዳጅ)ፍላጎት ሲኖር እና ፍትሕን የማያጓድል ሲሆን ብቻ ነው።»
 
📚ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) ስለዚህ ጉዳይ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፦
   "إذا كان الإنسان لا يثق من نفسه بالعدل، أو يغلب على ظنه أنه لا يعدل، فإنه لا يجوز له أن يتزوج أكثر من واحدة، لقوله تعالى: (فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً)، فإذا كان يخاف ألا يعدل، فإن التعدد يكون بالنسبة له حراماً."
«አንድ ሰው በራሱ ላይ ፍትሕን የማስፈን ብቃት እንደሌለው ካወቀ ወይም ከጠረጠረ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ለሱ ክልክል (ሀራም) ይሆንበታል። ምክንያቱም ጌታችን አላህ «አለማስተካከላችሁን ብትፈሩ አንዲትን ብቻ ያዙ» ብሏል። ስለዚህ ፍትሕን መተግበር እንደሚፈራ ካወቀ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ለሱ ሀራም ይሆናል።»

ንግግራቸው ግልጽ ነው፤ ፍትሕን የማስፈን ጥርጣሬ ካለ፣ ከአንድ በላይ ማግባት ወደ ሀራምነት ይሸጋገራል።

📍ከአንድ በላይ ለማግባት ስታስብ ራስህን ልትጠይቃቸው የሚገቡ ወሳኝ ጥያቄዎች ይኖራሉ።ይህንን መንገድ ከማሰብህ በፊት፣ ልብህንና አቅምህን በእውነተኛነት ፈትሽ። የሰዎችን ግፊት ወይም የማህበራዊ ሚዲያ ጫጫታወችን ወደጎን ትተህ፣ በእጅጉ ከባድ በሆነው የፍትሕ ሚዛን ራስህን መዝን።

① የመነሻ ዓላማዬ ምንድን ነው?
• የምፈልገው ስሜቴን ለማርካት፣ በጓደኞቼ ፊት ለመፎከር…ወይንስ ከዚህ የጠለቀ፣ የቲሞችን ለመርዳት፣ ያላገቡ እህቶችን ከዝሙት ለመጠበቅ፣ በፍትሕ ላይ የተመሰረተ ቤተሰብን ለማስፋት ያለኝ እውነተኛ የሸሪዓ ፍላጎት ነው?

የመጀመሪያዋ ሚስቴ ሀቅ ሙሉ በሙሉ ተጠብቋል?
• አሁን ላለችው ሚስቴ ሙሉ መብቷን—በቀለብ፣ በጤና፣ በመልካም አኑዋኑዋር፣ በስሜታዊ ድጋፍ…በአግባቡ እየሰጠሁ ነው? በሷ ላይ ያለብኝን ሃላፊነት ሳልወጣ፣ ሌላ ከባድ ሃላፊነት ለመጨመር መሞከሬ በደል ላይ በደል መጨመር አይደለምን?

③ ሁለት ቤቶችን በእኩልነት የማስተዳደር የገንዘብ አቅሜ ምን ይመስላል?
• ሁለት እና ከዛ በላይ የሆኑ ቤተሰቦችን ያለ ምንም ችግር እና በእኩልነት ለማስተዳደር የሚያስችል የተረጋጋ ገቢ አለኝ? አንዷን እያብቃቃሁ ሌላኛዋን የማስርብ፣ ለአንዷ የተሻለ ቤት ሰጥቼ ሌላኛዋን በችግር የማኖር ከሆነ፣ የቂያማ ቀን ሽባ ሆኜ ከሚቀሰቀሱት እንደማልሆን ምን ዋስትና አለኝ?

④ ሁሉንም በእኩልነት የማስተናገድ የአካል፣ የጊዜ እና የስነ-ልቦና ዝግጁነት አለኝ?
• በሁለት ቤቶች መካከል ያለውን ውጣ ውረድ፣ የሁለቱንም ሚስቶች ስሜትና ፍላጎት የማስተናገድ የአዕምሮ ብስለትና ጥንካሬ አለኝ? በሚስቶች እና በልጆች መካከል የሚፈጠሩ ቅናቶችን እና አለመግባባቶችን በፍትሕና በጥበብ የመፍታት ብቃቱስ?

⑤ስለ ፍትሕ ምን ያህል ተምሬአለሁ?
• ቁርኣን እና ሐዲስ ስለ ፍትሕ የሚያስተምሩትን ትምህርት በጥልቀት አጥንቻለሁ? የዑለማዎችን ማብራሪያ አንብቤያለሁ? ፍትሕ ማለት በልብስና በምግብ እኩልነት ብቻ ሳይሆን፣ በመልካም ፊት፣ በንግግርና በአያያዝም ጭምር መሆኑን ተረድቻለሁ?

እነዚህን እና መሰል ጥያቄዎች ቆም ብለን ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል። ምክኒያቱም ከአንድ በላይ ማግባት የእግር ኳስ ጨዋታ አይደለም፤ የጀግንነት መለኪያም አይደለም። በስሜት የሚወሰን ጊዜያዊ ፍላጎትም አይደለም። ይልቁንም፣ የቂያማ ቀን አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ከባድ አደራ እና ሃላፊነት ነው። ስለዚህ፣ ጉዳዩን ቀለል አድርገው ከሚያወሩ ሰዎች ንግግር በመራቅ፣ የዲኑን ጥልቅ አስተምህሮ እንረዳ።

አላህ ሁላችንንም ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይምራን። ሃላፊነታችንን በአግባቡ የምንወጣና እርሱን በሚያስደስት መልኩ የምንኖር ያድርገን።
|•| t.me/AbuSufiyan_Albenan