💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ከሚያስደስትህና ከሚደሰትልህ ጋር ሁን!

||
t.me/https_Asselefya1
🛑👉የረመዷን ወር አቀባበል


ሲያም (ጾም) በቋንቋ ትርጉሙ ኢምሳክ ወይም መታቀብ ማለት ነዉ።

إِنِّی نَذَرۡتُ لِلرَّحۡمَـٰنِ صَوۡمࣰا
እኔ ለአረሕማን ዝምታን  ተስያለሁ !

ከንግግር  ለመታቀብ ተስያለሁ ማለት ነዉ ። እዚህ ቦታ ላይ ግን ፆም _ከኒያ ጋር ንጋት ከቀደደ አንስቶ እስከ ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ፆምን ከሚያፈርሱ ነገሮች  መታቀብ ነዉ።

የፆም ትሩፋቱ ፦

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: (قال الله عز وجل: كل عمل ابن آدم له إلا الصيام؛ فإنه لي وأنا أجزي به، والصيام جنّة، وإذا كان يوم صوم أحدكم فلا يرفث، ولا يصخب، فإن سابّه أحد أو قاتله فليقل: إني امرؤ صائم، والذي نفس محمد بيده لخلوف فم الصائم أطيب عند الله من ريح المسك، للصائم فرحتان يفرحهما: إذا أفطر فرح، وإذا لقي ربه فرح بصومه) رواه البخاري ومسلم.

አቡ  ሑረይራ  እንደዘገቡት የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ አላህ እንድህ አለ፦  ሁሉም የሰዉ ልጅ  ስራ ለርሱ ነዉ ፆም ሲቀር እርሱ ግን ለእኔ ነዉ። እኔም ነዉ በርሱ የምመነዳዉ። ፆም ጋሻ ነዉ።  የእያንዳዳችሁ የፆም ቀን ሲሆን የወሲብ ወሬ አታዉሩ፣  አትንጫጩ አትጃጃሉ፣አንድ ሰዉ ከተሳደበዉ ወይም ከተጋደለዉ ሁለት ጊዜ እኔ ፆመኛ ነኝ ይበል።  የሙሀመድ ነፍስ  በእጁ በሆነዉ ጌታ እምላለሁ፦ የፆመኛ አፍ ሽታ አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽቶ ይበልጥ የጣፈጠ ነዉ። ፆመኛ  ሁለት ደስታዎች አሉት፦ ሲያፈጥር በፊጥሩ ይደሰታል። ጌታዉንም ሲገናኝ በፆሙ  ይደሰታል።

ورواية البخاري  .وأبي  داود " الصيام جنة، فإذا كان أمدكم صائما فلا يرفث ، ولا يجهل ، فإن امرؤ  قاتله، أو شاتمه  فليقل.إني صائم. مرتين،  والذي  نفس محمد بيده، لخلوف فم الصائم أطيب عند الله من ريح المسك، يترك طعمه وشرابه  وشهوته من أجلى. الصيام لي . وأنا أجزي به .ولحسنة بعشرة أمثالها ،

በቡዃሪ በአቢ ዳዉድ ዘገባ ደግሞ እንድህ ተዘግቧል፣  ፆም ጋሻ ነዉ ከእናንተ መሀል አንዳችሁ ፆመኛ ብትሆኑ ብልግናን እንዳትሰሩ እንዳትናገሩም አንድ ሰዉ ቢጣላችሁ ወይም ቢሰድባችሁ "እኔ ፆመኛ ነኝ" በሉ ደጋግማችሁ በሉ “የሙሐመድ ነፍስ በእጁ በሆነው እምላለሁ!  ከፆመኛ ሰዉ አፍ ዉስጥ የሚወጣዉ ሽታ ለአላህ ከሚስክ የበለጠ ነዉ። ምግቡን መጠጡን፣ ስሜቱን ለኔ ሲል ይተዋል። ፆም የእኔ ነዉ የምከፍለዉ እኔዉ ነኝ የአንድ በጎ ነገር ምትክ ክፍያዉ በአስር ነዉ።

ይቀጥላል......✍️

=
http://t.me/https_Asselefya1
ፖስፖርት አስቸኳይ ቀጠሮ እንድያዝላችሁ ለምትፈልጉ እህታችንን አናግሯት
~የራሷን ሀላፊነት መሸከም ከተሳናት ሴት ጋር አትጣመር:: ለራሷ ያልሆነች ለአንተም ሆነ ለልጆችህ አትተርፍም:: በራስህ ብትጨክን እንኳ ለልጆችህ እዘን::
~
t.me/https_Asselfya
"ፍቅር ማለት በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ቦታ መውሰድ አይደለም......ፍቅር ማለት ማንም ሊወስደው የማይችለውን ቦታ መፍጠር ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
🔖 ሴቶች አትሞኙ የፍቅር ሀብታም አግቡ ልባችሁ በደስታ ፈንድቆ ይኖራል። ዱኒያ አብረሽ ስረተሽ ማንጣት ትችያለሽ ። የገንዘብ ሀብታም ግን ዉጫዊ ደስታ ቢሰጥሽ እንጅ ዉስጣዊ ደስታ የለም። በዚች ምድር ላይ ደግሞ የዉስጥ ደስታን የመሰለ ነገር የለም።

=
🎓مبروك🎓

ለዉዷ ባለቤቴ  ለ ዶ/ር ፈትሂያ ዑመር
እንኳን ደስ አለሽ, እንኳን ለዚህ አበቃሽ !
ከብዙ ልፋትና ድካም በኋላ ለዚህ ላበቃሽ ለ አምላካችን አላህ ምስጋና ይገባው!
በሙያሽም ኡማውን በቅንነት የምታገለግዪ ያድርግሽ ::
أبو العباس ناصر
•• أصلح نفسك قبل رمضان

❍ كان عمرو بن قيس رحمه الله :

إذا دخل شعبان أغلق تجارته وتفرَّغ لقراءة القرآن؛ وكان يقول: طوبى لمن أصلح نفسه قبل رمضان.

‏‌لطائــف المعــارف (١٣٨)


=
t.me/https_Asselefya1
በየሚዲያው የሚናፈሱ ወሬዎች (መታኝና አለቀሰ ቀደመኝና ከሰሰ) ያለው ቢጤ ናቸው ከአንድ ጎን ብቻ ሰምታችሁ አትፍረዱ።

t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )
በየሚዲያው የሚናፈሱ ወሬዎች (መታኝና አለቀሰ ቀደመኝና ከሰሰ) ያለው ቢጤ ናቸው ከአንድ ጎን ብቻ ሰምታችሁ አትፍረዱ። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
🛑👉ብዙ ጊዜ ወንድ ልጅ ነገሮች በዝምታ ስለሚያልፍ። እንደ ሴት ስለማያለቅስ። የሆነ ነገር በመጣ ቁጥር ወንዶች እየተባለ ይዘመራል ለምን !? ከሆነሽ ሆነ ካልሆነሽ ገልል በይ ከሂወቱ የተተፋ ምራቅ አይዋጥም ። ጥለሺዉ የሄድሽዉን ሰዉ ባገኘሽበት መጨቅጨቅ መዘመር አይከብድም!? ይሄ የራስሽ ክብር እያቀለልሽ መሆኑ ተረጅ ! ጀግና ሴት የተበደለች ብትበደል ሁሉንም በሆዷ ይዛ ከበፊቱ የተሻለ ማንነት እና የተሻለ ሂወት ለመመስረት የምትጥር ነች። በሚድያ እየወጡ መነፋረቅ መጃጃል ይሄ የሞኝ ሴት ሞያ ነዉ። ራሳችሁ ከዚህ ተግባር አርቁ ሴቶች ብልጥ ሁኑ ! ወንድ ያዋረድሽ የጎዳሁ መስሎሽ ራስሽ ያዋረድሽ እና የጎዳሽ። በሚድያ እየወጡ መጃጃል ትርፍ ወሬ ማብዛት ፣ድንበር ያለፈ ነገር መለቅለቅ ሀቂቃ በጣም የሚቀፍ ነገር ነዉ ከዚህ ነገር ራሳችሁ አርቁ ሴቶች ። የፈለገ ብትበደይ ለሰዉ ሳይሆን ለአላህ ንገሪ በደልሽ እሱ ይክስሻል። ለሰዉ ግን ክብርሽ ጥለሽ ስም ወጥቶልሽ ተዋርደሽ ትቀሪያለሽ። ✍️
ምን ሁኖ ይሆን፡ምናልባት ለማለት የፈለኩትን ሳይረዳኝ ቀርቶ ተቀይሞ ይሆን?ወይስ ሰዎች አሳስተው ነገሩት?ምናልባት የራቀው የተቀየምኩ መስሎት ይሆን የሚሉ ከቅን ሰዎች ውስጥ ያሉ ቅን ልቦች አሉ።ይሄ የመልካምነታቸው ማሳያ፡የደግነታቸው ምልክት ነው።ግና ምን ያደርጋል እነርሱ እንዲህ ይጨነቃሉ ሰው ግን አይረዳቸውም።ይባስ ብሎ ባልገባው በመተርጎም በክፋት ይከሳቸዋል።

አቡ ኡበይዳ
t.me/AbuOubeida
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🛑👉የረመዷን ወር አቀባበል ሲያም (ጾም) በቋንቋ ትርጉሙ ኢምሳክ ወይም መታቀብ ማለት ነዉ። إِنِّی نَذَرۡتُ لِلرَّحۡمَـٰنِ صَوۡمࣰا እኔ ለአረሕማን ዝምታን  ተስያለሁ ! ከንግግር  ለመታቀብ ተስያለሁ ማለት ነዉ ። እዚህ ቦታ ላይ ግን ፆም _ከኒያ ጋር ንጋት ከቀደደ አንስቶ እስከ ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ፆምን ከሚያፈርሱ ነገሮች  መታቀብ ነዉ። የፆም ትሩፋቱ ፦ عن أبي…
🛑👉የረመዷን ወር አቀባበል

وعن عبد الله بن عمرو ان النبي ﷺ قال : الصيام  ولقرآن  يشفعان  للعبد يوم القيامه ، يقول الصيام  رب منعته الطعم  .والشهوات  بنهار .فشفعني به . ويقول القرآن : منعته النوم  بالليل، فشفعني  فيه فيشفعان "  رواه أحمد بسند صحيح

ከዐብዱላህ  ቢን ዐምር እንደተዘገበዉ  የአላህ ነብይ ﷺ እንድህ ይላሉ፦ ፆም እና ቁርአን የቂያም ቀን ለባሪያዉ ምልጃ ይሆናሉ። ፆም እንድህ ይላል፦ ጌታዬ ሆይ በቀን ምግብ እና ስሜቶቹን ከለከልኩት ይላል።  ቁርአን ደግሞ ጌታዬ ሆይ በሌሊት ከመተኛት  አገድኩት። አማልደን ይላሉ። ምልጃቸዉም ተቀባይነት ያገኛል።  አሕመድ በሶሒሕ ሰነድ ዘግበዉታል።

وعن أبي أمامة  قال : أتيت  رسول الله ﷺ  فقلت:  مرني بعمل يدخلني  الجنة : قال  عليك باصوم فإنه لا عدل له " ثم  أتيت الثانية ، فقال : عليك باصيام ، رواه أحمد ، النسائي، والحاكم، وصححه.

ከአቢ ኡማማ እንደዘገበዉ የአላህ መልእክተኛ ጋር መጣሁና "ጀነት የሚያስገባኝን ስራ ንገሩኝ አልኳቸዉ  እርሳቸዉም "በፆም አደራ፣ እርሱ እኩያ የለዉም አሉኝ።  ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ መጣሁና ጠየኳቸዉ "በፆም አደራ አሉኝ። አህመድ፣ ነሳዒይ እና ሐኪም ዘግበዉታል። ሀኪም ሶሂህ አድርገዉታል።

وعن أبي  سعيد  الخدري  رصي الله عنه : أن النبي ﷺ قال  لايصوم عبد يوما في سبل الله إلا باعد الله بذلك  اليوم النار  عن وجهه "  سبعن خريفا" رواه الجماعة  إلا أبي داود.

አቢ ሰኢድ  አል ኹድሪ «رضي الله عنه» በዘገቡት ዘገባ  ነብዩ ﷺ እንድህ አሉ፦ አንድ ሰዉ  በአላህ መንገድ ላይ  እያለ አይፆምም  በእለቱ አላህ ከእሳት ሰባ አመት ቢያርቀዉ እንጅ። "አቢ ዳዉድ ሲቀር  ሁሉም ዘግበዉታል።"

وعن سهل  بن سعد  أن النبي ﷺ قالإن للجنة بابا , يقال  له  الريان  يقال يوم  القيامة  أين الصئمون ? فإذا دخل آخرهم  أغلق ذلك الباب " رواه البخاري ومسلم"

ከሰህል ቢን ሰእድ «رضي الله عنه » እንደተዘገበዉ  መልእክተኛዉ  ﷺ እንድህ ይላሉ፦   ለጀነት በር አለዉ _ረያን ይባላል። ትንሳኤ ቀን እንድህ ይባላል  ፆመኞች የታሉ?   የፆመኞች  መጨረሻዎቹ  ከገቡ በኋላ በሩ ይዘጋል" ቡዃሪና ሙስሊም ዘግበዉታል።

                   ይቀጥላል.......✍️
=
https://t.me/https_Asselefya1
«የላጤወች ፀፀት!!

«ولقدْ شُتمتُ بألفِ سطرٍ كلُّها
هانتْ سوى في قولهم يا أعزبُ!»

በብዙ አልፍ ስድቦች ተሰድቤያለሁ ግን #ላጤ እንደሚባለው ስድብ ያመመኝ የለም።

ይልቅ ጊዜው ሔደ አግባና ተሰተር፡
በላጤነት ስቃይ ሁሌ አትኮማተር፡
ፊትና ነው ላጤነት ምን ብትኮሳተር፡

እኛ አግቡ ብለናል በል ወደ ትዳር ዳይ፡
እንቢ ካላችሁ ግን የራሳችሁ ጉዳይ፡
አምናና ካች አምና አለፈ በምፀት፡
ዘድሮም ይሔው ነው የላጤወች ፀፀት፡

t.me/nuredinal_arebi
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
🛑👉የረመዷን ወር አቀባበል وعن عبد الله بن عمرو ان النبي ﷺ قال : الصيام  ولقرآن  يشفعان  للعبد يوم القيامه ، يقول الصيام  رب منعته الطعم  .والشهوات  بنهار .فشفعني به . ويقول القرآن : منعته النوم  بالليل، فشفعني  فيه فيشفعان "  رواه أحمد بسند صحيح ከዐብዱላህ  ቢን ዐምር እንደተዘገበዉ …
🛑👉የረመዷን ወር አቀባበል


የፆም ዓይነቶቹ ፦ ፆም ሁለት ዓይነት ነዉ። ግደታ(ፈርድ) የሆነ እና ትርፍ (ተጠዉዕ) ፆሞች ናቸዉ።

ግዴታ  ፆም ለሶስት ይከፈላል፦

. የረመዷን ፆም
. የከፋራ(የመቀጫ) ፆም
. የስለት ፆም


እነዚህ ክፍል ዉስጥ የምንማረዉ ስለረመዷን  ፆም እና ስለ ሱና(ትርፍ) ፆም ብቻ ነዉ። ስለ ሌሎቹ የፆም ዓይነቶች በቦታዉ ይነገራል።

የረመዷን ፆም፦  ብይኑ ረመዷንን መፆም በቁርአን ፣ በሐዲስ እና በዑለሞች ስምምነት (ኢጅማዕ) ግደታ መሆኑ የተረጋገጠ ነዉ።

ከቁርአን ብንጀምር( አላህ እንድህ ይላል፦

یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَیۡكُمُ ٱلصِّیَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِینَ مِن قَبۡلِكُمۡ لَعَلَّكُمۡ تَتَّقُونَ

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ፆም
በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት(ሕዝቦች) ላይ  እንደተፃፈዉ በናንተም ላይ ተፃፈ  ልትጠነቀቁ ይከጀላልና። "አልበቀራህ 183"

እንድህም ብሏል፦

شَهۡرُ رَمَضَانَ ٱلَّذِیۤ أُنزِلَ فِیهِ ٱلۡقُرۡءَانُ هُدࣰى لِّلنَّاسِ وَبَیِّنَـٰتࣲ مِّنَ ٱلۡهُدَىٰ وَٱلۡفُرۡقَانِۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهۡرَ فَلۡیَصُمۡهُۖ

" እንድተፆሙ የተፃፈባችሁ ያ እርሱ ዉስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እዉነት ከዉሸት)  ከሚለዩም ገላጮች (አንቀፆች) ሲኾን   ቁርኣን የተወረደበት የረመዷን ወር ነዉ። ከእናንተም  ወሩን ያገኘ ሰዉ ይፁመዉ ። (አል _በቀራህ 185)

ወደ ሐዲስ ስንዞር ደግሞ ተከታዩ የነብዩ ﷺ ንግግር እናገኛለን

بني  الإسلام  على خمس:شهادة أن لا إله إلا الله وأن محمداً رسول الله، وإقام الصلاة، وإيتاء الزكاة، وصوم رمضان، وحج البيت من استطاع إليه سبيلاً»،

"እስልምና በአምስት ማእዘኖች ተገንብቷል። ከአላህ ሌላ በሀቅ የሚመለክ አለመኖሩን መመስከር እና ሙሐመድ የአላህ መልእክተኛ መሆናቸዉ መመስከር ላይ፣ ሶላትን በመስገድ፣ዘካን በመስጠት ፣ ረመዷንን በመፆም እና በቤቱ ሐጅ በማድረግ

وفي حديث  طلحة  بن عبيد الله،  أن رجلا سأل البي ﷺ  فقال : يا رسول الله أخبرني  عما فرض الله علي  من الصيام ? قال  شهر  رمضان  قال  :هل علي غيره  ? قال : لا أن تطع .

በጦልሐ  ቢን ዑበይዱላህ ሐዲስ ላይ እንደተጠቀሰዉ ፦ አንድ ወደ ነብዬ ﷺ መጣና _ የአላህ መልእክተኛ ሆይ አላህ ግዴታ ያደረገዉን ነገር  ንገሩኝ አለ። እርሳቸዉም
_የረመዷን ወር አሉት
። ሌላስ አለብኝ ? አላቸዉ። የለብህም ፤ አንተ ካልከጀልክ በቀር። አሉት።

የረመዷንን ወር መፆም ግዴታ በመሆኑ ላይ ሙስሊሞች ሁሉ ይስማማማሉ።  የኢስላም አንዱ ማዕዘን በመሆኑም ላይ ልዩነት የለም።  ይኸዉም ከዲን እንደሚቆጠር  በተለምዶ የሚታወቅ  (አል_ማዕሉም ቢደሩራ)በመሆኑ እርሱን ያስተባበለ ይከፍራል፤ ከሃዲም ይባላል።

የረመዷን ግዴታነት  የተደነገገዉ  ሰኞ ዕለት ከሻዕባን ወር ሁለት ቀን ቀርቶት ከሂጅራ በኋላ ሁለተኛዉ ዓመት ላይ ነዉ።

                     ይቀጥላል......✍️

=
https://t.me/https_Asselefya1