💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

የመጀመሪያዋ ሰመዓት እሙ አማር ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ትባላለች። ከእስልምና በፊት የአቡ ጀህል አገልጋይ ባሪያ ነበረች። አላህ ሱበሃነሁ ተአላ ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን እስልምናን አሲዞ በላከ ጊዜ እሷ፣ባሏና፣ ልጇ ሰለሙ። ቤተሰቧ ደሃና የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ችግርተኛ ቤተሰብ ነው። ሀብት የለው! ወገን የለው!

እስልምናን በተቀበሉ ወቅት አቡ ጀህል ይሄንን ቤተሰብ ይፈታተን ጀመር። ከያዙት እምነት እንዲመለሱ በመሻት ያለማቋረጥ የቅጣት ማአቱን ያወርድባቸው ነበር። በቃጠሎና በጥም ነፍሳቸውን እስኪስቱ ድረስ ያሰቃያቸዋል።በከባድ የበረሃ ሀሩር ላይ ያስራቸዋል። የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እነርሱ እየተቀጡ ባሉበት ሁኔታ በአካባቢው ያልፉ ነበር። ስቃያቸው በርትቶ ደማቸውም ሰውነታቸው ላይ ሲፈስ ያያሉ። በቅጣትና ግርፋት ብዛት የሰውነት ቆዳቸው ገርጥቶ ደግሞ ስቃያቸውን አባብሶታል። ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተከታዮቻቸውን ሁኔታ እያዩ ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው በእጅጉ ያዝናሉ። በህመማቸው ይታመማሉ።  "የያሲር ቤተሰቦች ሆይ"! ታገሱ ቀጠሯችሁ ጀነት ነው። ከማለት ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም

➪መካ በዘመነ ጃህልያ እንድህ ነበረች። ሀብታሙ ደሃውን የሚቀጣበት። ጉልበት ያለው ደካማውን የሚሰብርባት ነበረች። በመካ የተከታዮቻቸውን ስቃይ ለመከላከል ጉልበት ያልነበራቸው ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም በዚች ቃል ውድ ሰሀቦቻቸውን ያፅናናሉ። ከተስፋዎች ሁሉ ምርት በሆነው የጀነት ተስፋ ሞራላቸውን ይገነባሉ። እነርሱም በርሳቸው ቃል ይበረታታሉ። እርሳቸውን ሲያዩ በተስፋ ይሞላሉ።ውስጣቸው በደስታ ይፍነከነካሉ።


ወዲያውኑ የዚህ ኡመት ፊርዓውን የተባለው የተረገመው አቡ ጀህል ብቅ ይላል።ሲያያቸው ንደቱ ይጨምራል። ቁጣውም ያይላል ቅጣቱንም ከፍ ያደርግባቸዋል።ሙሀመድና ጌታውን ስደቡ። የሁበልና የኡዛን ጣኦት ስም ከፍ አድርጉ። በማለት ያሰቃያቸዋል።ቅጣቱ ፅናትና ትዕግስት እንጂ አይጨምርላቸውም። እልሁ እየተባባሰው መጥፎው ሰው አቡ ጀህል አንካሴውን ያነሳል። ወዲያውኑ በቁጣ ጀግናዋን ሴት በሰው ልጂ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ የጭካኔ አወጋግ ይወጋታል። ብልቷ ስር ነበር የወጋት ደሟ በከፍተኛ ሁኔታ ይፈሳል የእናትነት አጥንቷ ይሰባበራል። ትጮሃለች.........! ያ አላህህ

ልጇና ባለቤቷ ስቃይ ላይ ሆነው ከጎኗ ናቸው። ድርጊቱን በታሰሩበት ሆነው ከመመልከት ውጭ ምንም ሊያደርጉላት አልቻሉም። አቡ ጀህል ይሳደባል፣ ይራገማል፣ እርሷም ሞት አፋፍ ላይ ሆና ፅናቷን ታሳያለች። "አላሁ አክበር" ትላለች።


✍️ይቀጥላል
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
✍️ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲ ይላሉ፦

ሶስት ሴት ልጅ ያለው ሰው በትዕግስት መግቦ አጠጥቶ አልብሶ ያሳደገ ሰው የቂያማ ቀን ከእሳት ግርዶ ይሆኑለታል

📚رواه ابن ماجه وأحمد وصححه الألباني

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
ተዋት ትመርበት


ለሱናዋ ቆንጆ ለሒጃቧ ንግስት
የተውሒድ አርበኛ ሰለፊይዋ እንስት
እንቅፋት አትሁናት ኢልሟን ትቅሠምበት

በተውሒድ ብርሃን ትደግ ትድመቅበት
በንፁሕ ልቧላይ ኢማን ትትከልበት
በአቂዳ ብትር ሽርክን ትግረፍበት

ተው እንቅፋት አትሁን በሕይወት መስመሯ
በቃ እሷ አትንካት ተዋት ትኑር ከእነክብሯ!!
تلاوة من سورة الكهف
Kalido tube
«ለመለየት የሚከብድ ድምፀ ማስመሰል !»

🎙በወንድም ኻሊድ ዑመር

=
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ፈገግም አደረገኝ…«እሄ ገጣጣ ማጭድ¡»

~ብቻ…ስኬት ልፋትን፣ ቁርጠኝነትን፣ እና ሌሎችም ብዙ ነገሮችን የሚጠይቅ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ሁልጊዜ ቀላል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን በመጨረሻ ስኬት ማግኘት ሁሉንም የሚጠይቀውን ዋጋ አለው። እና ሐቢቢ ኢጃዛ ቤቱንም ትደርስበታለህ ጠንክረህ ስራ ሀሀ¡¡
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
«የቁርአን ሀይል»

ፈተናዎች ሲበዙብንና ከብዛታቸዉ የተነሳ  ስንርበተበት ይሄኔ  ከችግራችን ለመዉጣት ወደ ቁርአን እንሽሽ፣ ፀናትና ብርታት የሚኖረን ከቁርአን ጋር ባለን ቁርኝት ልክ ነዉ። ቁርአን ልዩ ልብን የማጠንከር ሀይል አለዉ። ቁርአን ማንበብ፣ ማስተንተንና ህጉን መተግበር ባበዛን ቁጥር የዉስጥ መረጋጋትና ጥንካሪያችን ይጨምራል። የዚህ ሚስጢር ደግሞ ቁርአን እራሱ ከሀያሉ አላህ የመጣ በመሆኑ ዉስጡ ላይ ልዩ ሀይል መኖሩ ነዉ። ለዚህም ነዉ የመካ ከሀዲያን መጀመሪያ አካባቢ ላይ ቤተሰብና ልጆቻቸዉ ቁርአን እንዳይሰሙ ይከለክሏቸዉ የነበረዉና ቁርአን ሲቀራም እንዳይሰማ ይጮኹና ሌሎችም እንድጮሁ ያዙ የነበረዉ። ሆኖም ግንበዉስጡ ላይ የያዘዉ  ሀይልና የመልእክቱ ሐቀኝነት እያሸነፋቸዉ እና  እየሳባቸዉ  ነብዩﷺ ካዕባ  ጋር ሆነዉ ቁርአን ሲቀሩ የሌሊት ጨለማ ላይ እየተደበቁ የሚያደምጡ አምባገነኖች እንደነበሩ አላህ ተናግሯል።

ጂኖችኳ ቁርአንን በሰሙ ጊዜ "ድንቅ ንባብ ሰማን" ነዉ ያሉት።  አሁንም በዘመናችን ብዙ በቁርአን የሚያምኑ  ይሁን የማያምኑ ሲያደምጡት ልዩ ስሜት እርካታ እንደሚሰማቸዉ ገልፀዋል። ይህም ቁርኣን ከንግግሮች ሁሉ የተለየና ልዩ ሚስጥር ያለዉ ንግግር መሆኑን  በግልፀ ያሳያል። ግን ቁርአን በሁለቱም ዓለም የሚጠቅመዉ ሲያምኑበት፤ ልብና ጊዜን ሰጥቶ ሲያጠኑት ህግጋቱን ሲከተሉ ብቻ ነዉ።

=
t.me/https_Asselefya1
القارئ عبدالله الخلف | والذين يحاجون في الله من بعد ما استجيب له…
💭🌸خدمة تلاوات🎧
﴿وَٱلَّذِينَ يُحَآجُّونَ فِى ٱللَّهِ مِنۢ بَعْدِ مَا ٱسْتُجِيبَ لَهُۥ حُجَّتُهُمْ دَاحِضَةٌ عِندَ رَبِّهِمْ وَعَلَيْهِمْ غَضَبٌ وَلَهُمْ عَذَابٌ شَدِيدٌ ۝﴾

🎙قارئ : عبدالله الخلف

«
አንድ ነገር ደጋግመን ስንሰማው እንሰለቻለን የአሏህን ቃል ግን ይበልጥ እናፈቅረዋለን።»

«አሏህ ቁርዓንን የልባችን መርጊያ የመንገዳችን ብርሃን ያድርግልን»

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
•• ومن أنَفع الأدوية :

‏‌‏⤶ الإلحاحُ في الدُعــاء
=
አትሸወድ!
አንድ አንድ ሰው ስታየው ሰው ይመስላል አጢነህ ስታየው ባዶ መሆኑን ትገነዘባለህ።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➾ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬ ➩የመጀመሪያዋ ሰመዓት እሙ አማር ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ ትባላለች። ከእስልምና በፊት የአቡ ጀህል አገልጋይ ባሪያ ነበረች። አላህ ሱበሃነሁ ተአላ ነብዩን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን እስልምናን አሲዞ በላከ ጊዜ እሷ፣ባሏና፣ ልጇ ሰለሙ። ቤተሰቧ ደሃና የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ችግርተኛ ቤተሰብ ነው። ሀብት የለው! ወገን የለው! ➾እስልምናን…
ሱመያህ ቢንት ኸይጥ ረዲየላሁ አንሃ
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰

አቡ ጀህል የተጎዳ አካሏን በጣጠሰው ስጋዋ እዚህም እዛም ተከተፈ። በዚያ መልኩ ስቃይ ላይ ሆና ሞተች። አዎን ሱመያ ሞተች። ዲኗን ይዛ፣ አቋሟን ጠብቃ ወደ መጨረሻው አለም ሄደች። በእስልምና ታሪክ የመጀመሪያዋ ሰመአት ሆነች። አላህ ይዘንላት።

ዛሬ እኛ እንደዋዛ የተመለከትነው እስልምና በዚህና በመሳሰሉት መልኩ ስቃይ ተከፍሎበታል። ከወንድም ከሴትም በርካቶች መስዋት ሆነውለት ነው ከእኛ ዘንድ የደረሰው። እኛ ግን ሌላው ቀርቶ ምንዳ በሚያስገኙልን ሸሪአዊ ድንጋጌዎች ላይ እንኳን መፅናት አቅቶናል። ሂጃብን አስተካክለሺ ልበሺ አለብስም በሚል ግብግብ ውስጥ ነን። ተኳኩለሺ አትወጭም እወጣለሁ በሚል ሰጣ ገባ ውስጥ ነን። ይህ ሁሉ እምነታችንን ደረጃና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ አመልካች ነው። የያሲርና የሱመያን ቤተሰብ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው። የእስልምና ሰማዕታት ታሪክ ሲወሳ መዝገቡ በቅድሚያ የሚጠራው ወንድን ሳይሆን ሴትን ነው። እስልምና ሱመያን የመጀመሪያዋ ሸሂድ ይላታል። አወን ሱመያ ሸሂድ ሆነች። በአላህ መንገድ ተሰዋች። ዲኗን እንደያዘች ዝንፍ ሳትል ተሰዋች። በርግጥም በቀደምት ሙስሊሞች ተጋድሎ ብዙ የምንማራቸው ቁም ነገሮች አሉ

➩ምንኛ እድለኛ ናት በአላህ ጌታዋ የሚፈልግባትን አድርጋ ሞተች። ውዴታዋን የምኞቶች ሁሉ ጣሪያ አድርጋ ሞተች። በሀይማኖቷ ላይ ፀናች። ሀይማኖቷን ይዛ ሞተች። እስልምና ከወጣትም ሆነ ከጎልማሳ ከሴትም ሆነ ከወንድ ብዙ ጀግኖች አፍርቷል። እናት ሱመያ አንዷ ናት። የነ አማር እናት፣ የያሲር ባለቤት ያሰቃዮት ማሰቃየት ግድ አልሰጣትም።


የስቃይ ብዛት ከእምነቷ አልመለሳትም። አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላት። ከምርጥ ጀነቱም ያሳርፋት

➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/https_Asselefya1
ይቅርታ

"ይቅርታ አለማድረግ ትላንት ይቀየራል ብሎ ተስፋ ማድረግ ማለት ነው " ትላንት አንዴ አልፏል ምንም ብናደርግ አንቀይረውም ዛሬ ግን በእጃችን ነው የመረጥነውን የማድረግ እድል አለን ! ነገር ግን ዛሬን ለማዘዝ ነገን መታረቅ የግዴታ ነው ካልሆነ በማንቀይረው ነገር ራሳችንን ስናባክን እንኖራለን !

«መልካም ምሽት ተመኘን!»

=
t.me/https_Asselefya1
«ዛሬን በደንብ ኑር !»

አብዛኞቹ ጭንቀቶቻችን የሚመነጩት ልንሰራ ያሰብነው ነገር ከባድ ወይም ብዙ ስለሆነ አይደለም የጀመርነውን ቀላል ነገር ስላልጨረስን ነው። ትላንት አልፏል አንጨብጠውም ነገንም  ገና አላየነውም ማስተካከል የምንችለው ዛሬን ነው ያውም አሁንን።

=
t.me/https_Asselefya1
.‏{وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا}
قال القرطبي : فلو كان شيء أشرف من العلم
لأمر الله ﷻ نبيه ﷺ أن يسأله المزيد منه
كما أمر أن يستزيده من العلم

📓تفسير_القرطبي
=
➨የገዳ ስርዓት⁉️
🎙በኑረዲን አል አረብ
Keessattuu gootonni Oromoo akka ummanni keenya hin jibbineef haa dammaqnu!!



.....የገዳ-ስርዓት⁉️...

ለኛ ለሙስሊሞች ማዕበል ነው ወጀብ፡
አባ-ገዳ አጠብቅ በኛ እንድትታጀብ፡

ግፍ እየተሰራ በዚህ ሁሉ መዓት፡
የአጋንንት አምልኮ የሸይጦን ግብዓት፡
እንደዚህ ነው ለካ የገዳ ስርዓት⁉️

Nama hunda bira ga'uuf babal'isaa, Irecha Muslimaaf dhimma hin qabu.

🎙በኑረዲን አል አረብ
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
Audio
قال تعالى:مَن عَمِلَ صالِحًا مِن ذَكَرٍ أَو أُنثى وَهُوَ مُؤمِنٌ فَلَنُحيِيَنَّهُ حَياةً طَيِّبَةً وَلَنَجزِيَنَّهُم أَجرَهُم بِأَحسَنِ ما كانوا يَعمَلونَ


🎤الشيخ: أحمد_ديبان
=
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
~በሙስሊሞች የአስተዳደር ዘመን ለመጀመርያ ጊዜ የመሬት መንጥቀጥ የተከሰተው በ20ኛው የሂጅራ አመት በዑመር የኸሊፋነት ዘመን ነው።
በወቅቱም ዑመር(ረድየሏሁ ዓንሁ)በድንጋጤ ህዝቦቹን «ለመሆኑ ምን ምን ግፍ ፈጽማችሁ ነው? ምንስ አድስ መጤ ነገር ተግብራችሁ ነው ይህ አይነት የመሬት መንቀጥቀጥ ፈተና የደረሰብን ብሎ ከጠየቀ በኋላ ወላሂ ዳግም ይህ ክስተት ቢከሰት እኔ ጥያችሁ ነው የምወጣው (ከእናንተ ጋር አልኖራትም) »ብሎ ወንጀልን ከመዳፈር አስጠነቅቃቸው ለነዚያ ለምርጥ ትውልዶች።

📜ኢብኑ አቢ ሸይባ፣በይሀቂይ፣ኢብኑ አቢ ዱንያ እንድሁም ኡብኑ ሙንዚር የዘገቡት ትክክለኛ ንግግር ነው!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
እህቴ ሆይ አላህን ፍሪ!
~
እስኪ ውስጥሽን አዳምጪው። ለማን ነው ይህን ያደረግሽው? አላህ ምን ይለኛል ብለሽስ አስበሻል? ተይው አላህ ዘንድ ሰው ዘንድ ራሱ ያስንቅሻል። ከጌታሽ ተጣልተሽ፣ ሰዎች ዘንድ ትዝብት ላይ ወድቀሽ ምን ትርፍ ታገኛለሽ?

ለማንኛውም ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
" صِنْفَانِ مِنْ أَهْلِ النَّارِ لَمْ أَرَهُمَا ؛ قَوْمٌ مَعَهُمْ سِيَاطٌ كَأَذْنَابِ الْبَقَرِ يَضْرِبُونَ بِهَا النَّاسَ، وَنِسَاءٌ كَاسِيَاتٌ عَارِيَاتٌ، مُمِيلَاتٌ مَائِلَاتٌ، رُءُوسُهُنَّ كَأَسْنِمَةِ الْبُخْتِ الْمَائِلَةِ، لَا يَدْخُلْنَ الْجَنَّةَ، وَلَا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وَإِنَّ رِيحَهَا لَيُوجَدُ مِنْ مَسِيرَةِ كَذَا وَكَذَا "
"ሁለት አይነት ሰዎች ከእሳት ጓዶች ውስጥ ናቸው። እኔ አላየኋቸውም (ወደፊት ይመጣሉ።)
* እንደ ከብት ጅራት ያለ መግረፊያ ይዘው ሰዎችን በነሱ የሚደብድቡ ሰዎች እና
* ለብሰው የተራቆቱ፣ ለሌሎች ጥፋታቸውን የሚያስተምሩ፣ ከአላህ ትእዛዝ ያፈነገጡ፣ ፀጉሮቻቸው እንዳዘነበሉ የተከመሩ የግመል ሻኛዎች የሆኑ ሴቶች ናቸው። እነዚህ ጀነትን አይገቡም። ሽታዋንም አያገኙም። ሽታዋ ከብዙ ርቀት የሚገኝ ነው።"

📚 ሙስሊም ዘግበውታል።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor