💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
አትጠብቅ !
🔻🔻🔻

«ለችግርህ ጊዜ የራቁህ
ለስኬትህ ዙሪያህን ቢከቡህ አትደነቅ፤ በከባዱ ጊዜህ ትዝም ያላልከቸው በምርጡ ጊዜ ፍቅር በፍቅር ቢሆኑ እንዳይገርምህ።»

«የዛሬም ሺ አመት ሰዎች እንደዚህ ነበሩ፤ ዛሬም ነገም እንዲህ ናቸው። ስለዚህ ከሰው ምንም አጠብቅ! ከአላህ ቀጥሎ ራስህን እመነው! ራስን እንደመጠራጠር ህልም ገዳይ ነገር የለም!»

=
t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
«ቢከፋሽም ጠንካራ ነሽ»

ላየሽ ሁሉ ደስተኛ  ነሽ ትስቂያለሽ፤
 áˆ˜á‹ľáŠ¨áˆáˆ˝áŠ• መከፋትን ማን አዉቆልሽ፤


«የሚገርመዉ.....!»
ባንች መፍካት መቅናታቸዉ፤
አንችን መሆን ምኞታቸው፤

መች ያዉቁና የዉስጥ ህመም ድካምሽን፤
ካገር ወጥቶ የሰዉ ሃገር ብሶትሽ፤

በዉስጥሽ ታጭቆ ሰላም የሚነሳሽን፤
በነጋ በጠባ ሆድ እሚያስብስሽን፣
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባሽን፣


«ግን ያልፍል....»
አዋ ያልፋል ባዘን ፈታ ሳቅ ይተካል
እደታሪክ ትናት ሁኖ ዛሬ ያልፋል
!

✍️𝐒𝐞𝐥𝐚𝐡𝐮𝐝𝐢𝐧 𝐀𝐛𝐮 𝐀𝐮 𝐎𝐮𝐛𝐞𝐢𝐝𝐚

=
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫       ➧አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል ስድስት ➪አቲካ ከዚህ ትልቅ ሳሃባ የመጣላትን የትዳር ጥያቄ እያሰላሰለች ሳለ እነኝህ ሳሃባ ሌላ ሰው ላኩባት። ማን ይሆኑ እነኚህ ሰሃባ? እነኚህ ሰሃባ መንገድ እየሄዱ ሸይጧን ቢያያቸው እርሳቸውን ፍራቻ መንገዱን ቀይሮ በሌላ መንገድ ይሄድ ነበር በማለት ነብያችን አለይሂ ሰላቱ ወሰላም የመሰከሩላቸው የውመል…
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

      ➧አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል ሰባት

➪ሰይድና ኡመርን በሁለቱም በኩል ስለት ባለው ሳንጃው ሶስት ጊዜ ክፍኛ ይወጋቸዋል። አቡ ሉዕሉዕ አል መጁሲ እሳት ከሚያመልኩት ሰዎች አንዱ ነበር የማይሞከር ነገር ሞክሮ ተሳካለት። መፈፀም ያልነበረበትን ወንጀል ፈፀመ ሰይድና ኡመር እንደዚያ ክፉኛ ሲወጉ አንደኛው ከዕንብርታቸው በታች የነበረው አደገኛ ሆኖ አንጀታቸው ይታይ ነበር። ሰይድና ኡመር ረ.ዐንሁ ዘወትር ከሰላታቸው በኃላ ሸሃዳን አላህን ሲጠይቁት ሲለምኑት የነበረውን አላህ እንደተቀበላቸው ተሰማቸው። እስቲ በዚህ መስጅድ ውስጥ እንዳላችሁ ሁናችሁ ይህን አሳዛኝ ነገር ሳሉት። አቡ ሉዕሉዕ ማምለጫ አጥቶ የሰጋጆች ሰይፍ ሊወርድበት ሲል በዚያው ሰይዲና ኡመርን በወጋበት ሳንጃው ሙዕሚኖችን እየመታ አስራ ሶስት ሰዎችን አቁስሎ ከዚያ ውስጥ ስድስቱ ይሞታሉ።

➾ሰይድና አብዱረህማን ኢብኑ አውፍ ረድየላሁ አንሁ በሰይፋቸው አቡ ሉዕሉዕን አንድ ደህና ሞት ሲያሳርፍበት መሬት ላይ ይወድቃል። ሙስሊሞች ከሚገሉኝ ብሎ እራሱን ወግቶ ነፍሱን ያጠፋል። ይህን ሁሉ ሲደረግ አቲካ ረ.ዐንሃ ጉዷን አታውቅም። ኡመርን ሰሃባዎቹ ከበዋቸው ነበር። ልጃቸው አብደላህ ደግሞ የኡመርን ጭንቅላት ደረቱ ላይ ደግፎ አባቱን ያበረታታ ነበር። ሰዎች ትንሺ ወተት አምጥተው ሲያጠጧቸው ያ ወተት በጉሮሯቸው አልፎ ሆዳቸው ላይ በተወጋበት ቀዳዳ ይፈሳል። ይህን ጊዜ ሰሃባዎች ተደናግጠው ያዩዋቸው ነበር።

➩የሰይዲና ኡመር እጅ መሬት ላይ ሲወድቅ እጃቸው መሬት ላይ ያለው ሳር በእጃቸው እፍኝ ወስደው "ምነው የኡመር እናት ኡመርን ባልወለደች ምነው ይሄን ሳር ሆኘ በነበር" ብለው ሰሃባዎችን በሙሉ አስለቀሱ። ኡመር ረዲየላሁ አንሁ ይሄን ያለ እኛ ምን እንላለን በማለት እንጂ ለኡመር ኻቲማ ፈርተው አልነበረም ያለቀሱት። በመቀጠልም ሰይድና ኡመር ልጃቸውን አብደላህን እሙል ሙዕሚኒን አኢሻ ረዲየላሁ አንሁም አጅማኢን ዘንድ ልላክህ ይሉታል። እርሷም ዘንድ ስትደርስ አሚሪል ሙዕሚኒን ላከኝ እንዳትላት። እኔ ከዚች ሰአት ጀምሮ ለእናንተ አሚር አይደለሁም። እርሷም የአሚር ትዕዛዝ ነው ብላ የምጠይቃትን ፈርታ እሺ ልትለኝ ትችላለች።

➙ለማንኛውም ኡመር ከጓደኞቹ ጋር መቀበር በጣም ይፈልጋል በላት አሉት። እዚህ ላይ ማወቅ ያለብን ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የተቀበሩት ይኖሩበት የነበረው አንድ ክፍል ቤታቸው ውስጥ ነው። ከዚያ ሰይድና አቡበከር ከአጠገባቸው ተቀበሩ። አሁን እዚያ ቤት ውስጥ የቀረው የአንድ ሰው መቀበሪያ ቦታ ብቻ ሲሆን ይህም ቦታ የተቀመጠው ለእሙል ሙዕሚኒን ለሰይደ አኢሻ ረዲየላሁ አንሃ ነው። ምክንያቱም እዚያ ቦታ ላይ የተቀበረው አንደኛው ባሏ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሁለተኛው አባቷ አቡበከር ሲዲቅ ነው። ሶስተኛውንና የመጨረሻውን ቦታ ያስቀመጠችው ለራሷ ነበር።

➾ኡሙል ሙዕሚኒን አኢሻስ ይህን መልዕክት ስትሰማ መልሷ ምን ይሆን? ዘወትር የተመኘችውን ቦታ አሳልፋ ትሰጥ ይሆን? አብደላህ ኢብኑ ኡመር ይህን መልዕክት ይዘው ወደ አኢሻ ሲሄዱ አኢሸት ረዲየላሁ አንሃ (ኸበሩ) ዜናው ደርሷታል በጣም አዝና አገኛት። አብደላህ ኢብኑ ኡመርም "አባቴ ኡመር ኢብኑ ኸጣብከጓደኞቼ ጋር መቀበር እፈልጋለሁ ፍቃድ ስጭኝ ብሎሻል" በማለት ይነግራታል። አኢሻም ከሃዘኗ እና ከድንጋጤዋ የተነሳ ሳታመነታ ዑመር የፈለገውን ነገር እንደት አይሆንም ይባላል ማንስ ነው እሱ አይሆንም የሚለው ሂድና ላባትህ ፍቃደኛ ነኝ በለው አለች።

✍የፋሩቅ እናት
◉
◉
◉
◉
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል

➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➻ለገባው ዝምታም መልስ አለው!
ሰምቶ ላዳመጠው አርቆ ላጤነው ዝምታም መልስ አለው።


አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ዝም ስትል ያልተጎዳህ፣ ውስጥህ ያልከፈው ይመስላቸዋል ግን.....የሚረዱት በጣም ጥቂቶች ናቸው።

➾ስንት አለ መሰላችሁ ለመናገር ፈልገን ያልተናገርናቸው.......!?
تلاوة

🎙በኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር አሕመድ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
➲የአላህ ልዩ ሰዎች
➘➘➘➘➘➘➘➘➘

♦️የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:–" ለአላህ ከሰዎች መካከል ቤተሰቦች አሉት፤ እነርሱም የቁርአን ባለቤቶች ናቸው፤ እነርሱ የአላህ ቤተሰቦች እና ልዩ ሰዎች ናቸው።"
(ኢብኑ–ማጃህ ዘግበውታል አልባኒ ሰሂህ ብለውታል)

➛ተሰምቶ የማይጠገበውን የአላህን ቃል ተጋበዙልኝ!

🖊መልካም ቀን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
Audio
🔺ከቁርአን ጋር እንኑር!

تلاوة من سورة المائدة
🎙 القارئ: #علي_الحذيفي

•••━══❁✿❁══━•••
t.me/https_Asselefya1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከሆነ ሰዉ ጋር አብራችሁ መልካም ስራ ስትሰሩ ቆይታችሁ አለመግባባት ሲፈጠር ሰዉየዉ ተዉ እንጅ መልካም ስራችሁ በፍፁም አትተዉ አቅጣጫ ቀይራችሁ በመልካም ስራ ላይ ጠንካራ ሁኑ እሺ ! ብዙ እህቶች ጠፍተዉብናል እንፈልግ ያ ጀመአ የት ናችሁ ?? ብዙ ጠንካራ እህቶች ሚድያ እርቀዉብናል !? ለምን ? ስራችሁ ከአላህ ጋር ነዉ ማቆራኘት ከሰዉ ጋር አታቆራኙ ሰዉ ተገለባባጭ ነዉ ትላት የነበረበት ይረሳል እሺ ! እና አይዟችሁ ጠንክሩ ኸይር ስራ ላይ አትስነፉ እድሉ እንጠቀምበት እሺ ።

✍️أم عثيمين

=
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM