💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15.1K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Video message
📖 قال الله تعالى:

﴿ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تُسِرُّونَ وَمَا تُعْلِنُونَ ۝ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَا يَخْلُقُونَ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ ۝ أَمْوَاتٌ غَيْرُ أَحْيَاءٍ ۖ وَمَا يَشْعُرُونَ أَيَّانَ يُبْعَثُونَ ۝ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ ۚ فَالَّذِينَ لَا يُؤْمِنُونَ بِالْآخِرَةِ قُلُوبُهُم مُّنكِرَةٌ وَهُم مُّسْتَكْبِرُونَ ۝ لَا جَرَمَ أَنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا يُسِرُّونَ وَمَا يُعْلِنُونَ ۚ إِنَّهُ لَا يُحِبُّ الْمُسْتَكْبِرِينَ ۝﴾.

🎙 تلاوة من سورة النحل [من الآية ١٩ إلى الآية٢٣]
=
√ ከተብቃቃህ ትንሹ ብዙ ነዉ።
√ ከተስገበገብክ ብዙዉ ትንሽ ነዉ።
√ ከወደድክ ሩቁ ቅርብ ነዉ
√ ከጠላህ ቅርቡ ሩቅ ነዉ።


=
t.me/https_Asselefya1
« የራስህን ትኩስ እንጀራ ለመጋገር ስትል የሌላዉን ቂጣ አትርገጥ።»

=
<<<አለው በፍለጋ>>>

ልቡ ጥሩ አሳቢ ምላሱ የገራ፣
ብዙ የሚሰራ ትንሽ የሚያወራ፣

ፈገግታው የሚስብ ከሩቅ የሚጣራ፣
ፊቱ በተዋዱዕ በኢማን ያበራ፣

በፈርዱ የቆመ ከሱናውም ያለ፣
ደበረኝ ሰለቸኝ ደከመኝ ያላለ፣

ለረጅሙ ጉዞው ጥሩ የሰነቀ፣
ለማይቀረው ዓለም መሄዱን ያወቀ፣

ፀባዩ የሚጥም ወግ አመሉ ሸጋ፣
እኔስ ሰው ጠፍቶኛል ገጥሞኛል አደጋ፣
የምኞቴን አጣሁ እንሂድ ፍለጋ፣

ልቤን ሰውሰው አለው የኢማን ጓደኛ!
የፉላን እናት.......✍️
«እድሉ ቢኖረኝ እቅፍህ ዉስጥ ሁኜ ብዙ የምነግርህ ነበረኝ። »
#أبي حبيبي 🌸

=
t.me/https_Asselefya1
"ارغبْ إلى الله في ذِكـرٍ تردِّدُهُ
إنَّ القلوبَ بِذكرِ اللهِ ترتـاحُ "
ሰውየው ሚስት አገባና ጥሩ ጥሩ ምግብ እየሰራች ሰጠችው አሉ።በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ደበደባትና "ምነው?" ብትለው "እስከ ዛሬ እንዲህ ስጎዳ የት አባሽ ከርመሽ ነው?" ብሏት እርፍ።

منقول
=
t.me/https_Asselefya1
↝ድንገት ያለ ምንም ምክንያት ከልክ በላይ ከምትወዳቸዉ ነገሮች ጀርባ መሮጥ ታቆማለህ።  የምትፈልገዉ ብቸኛ ነገር ሰላም መሆንና የልብ መረጋጋት ይሆናል።

=
t.me/https_Asselefya1
➡ወንዶች እንዳትቆጡ እሽ...⁉️

ሚስት የለም አትበል‼️
-------------------

ተፈርዶብን እንጂ፤
ወንድ ሆነን ሴትን እንዳናመሰግን፡
ባል ነኝ ለሚል አካል፤
ሚስት ጠፍቶ ነው ግን⁉️


......እ....

አይደለም አይደለም አይደለም በፍፁም፡
ከአማኝ ጋር አይሔድም የመጥፎነት ቅርፁም፡
እስኪ ከመጥፎ ቃል ከንግግር እንፁም⁉️

በቅጡ ሳትወስን፤
ግራ ቀኝ ሳታይ ዘለህ እንደ ጦጣ፡
ሰው መሆን ሲሳንህ፤
ሀላፊነት ይዞህ መሔጃ ስታጣ፡
ሚስት የለም አትበል፤
ወንድ ሆነህ ሳትገኝ ባል ሆነህ ሳትመጣ፡
በቅጡ ሳታውቀው፤
የጥምረትን ሚስጥር የትዳርን ጣጣ፡


በውል ሳትረዳ፤
የፍቅርን ከፍታ የኑሮን ፈተና፡
የህይወትን መስመር፤
የባልን ማዕረግ የአባወራ ሚና፡
የሰው ወሬ ይዘህ፤
በእህቶቻችን ላይ አታብዛ ትንተና፡
የተለያየ ነው ዛሬም ትላንትና!!
ልክ እንደሚራራቅ አምና እና ካቻምና፡


የከበደህ ጊዜ፤
የራስህን ጥፋት አምኖ ለመቀበል፡
ማንነት ሲለካ፤
ወንድነት ሲጎድልህ እሷን ለማባበል፡
ሴትን ልጅ አትውቀስ፤
ሚስት የለም አትበል፡

በኢስላም ቀኖና በእምነት መሰረቶች፡
በአደብ ያደጉ አሉ ብዙ እንስቶች፡

በአንዳንድ መጥፎወች፤
አትበል ሚስት የለም፡
ሚስት የመሆን ምርጫ፤
እንደዚህ አይደለም፡

ባል ሆኖ ለመጣ በእውነተኛ ፍቅር፡
ለተውሒድ አንበሳ ለሱና ሽቅርቅር፡
ህይወትን ለመምራት ኑሮን ለማጣጣም፡
ማንም በንያው ልክ አጣማጅ አያጣም፡

ብቻ አንተ ወንድ ሁን ውጣ ከጥርጥር፡
እንቁ ሴት ሞልታለች ደስታ የምትፈጥር፡
ወደ ስኬት ማማ የምታስፈነጥር፡

እንጂማ ወዳጄ፤
በማታውቀው ገብተህ አታጥፋ የሰው ስም፡
ባንተ መጥፎ ነገር፤
ስንት አለ መሰለህ ሳይደርስ የሚከስም፡
እስኪ መጀመሪያ፤
ራስህን ፈትሽ ከአቋም አትዘንበል፡
የትም እየዋለልክ፤
ሴትን አትናገር ሚስት የለም አትበል‼️

«በኑረዲን አል-አረብ»

http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➡️ከሰኞ እስከ ሰኞ ተከታታይ ወርቃማ ቀናት ከፊታችን፦ √ ሰኞ: የሙሐረም 9ኛ ቀን፣ √ ማክሰኞ: የሙሐረም 10ኛ ቀን → የዐሹራእ ጾም፣ √ ረቡዕ : የዐሹራእ ቀጣይ ቀን፣ √ ሐሙስ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን፣ √ ጁሙዓህ: የአያሙልቢዽ የመጀመሪያ ቀን (ሙሐረም 13) √ ቅዳሜ: አያሙልቢዽ፣ √ እሁድ: አያሙልቢዽ፣ √ ሰኞ: ሥራዎች ወደ አላህ የሚቀርቡበት ቀን አላህ አላህ! እንኳን ተጨማሪ…
──────⊹⊱✫⊰⊹──────

الحمدُ للهِ الَّذي بِنعمَتِه تَتمُّ الصَّالحاتُ .

አልሐምዱሊላህ! በፀጋው መልካም ነገሮች ሁሉ ይሳካሉ፡፡

──────⊹⊱✫⊰⊹──────
ሴት ወንዶችን ማከም
~
ጥያቄ፦ አድማጭ እንደምትለው እድሜዋ ሃያ ስድስት አካባቢ የሆነች ወጣት ነች። በስርአት የለበሰች ናት። በዚህም ጌታዋን ታመሰግናለች። ክሊኒክ ውስጥ ነርስ ሆና ትሰራለች። ቁስለኞችን ታክማለች። እንዲሁም ለሴቶችም ለወንዶችም መርፌ ትወጋለች። በዚህን ጊዜ መድሃኒቱን ለመስጠት ስትል የህመምተኛውን አካል ትነካለች። "ስራዬ ይሄ ነው። ሌላ የሪዝቅ ሰበብ የለኝም። የተከበሩ ሸይኽ ሆይ! ይሄ ስራዬ ችግር አለበትን? አላህ ይመንዳዎትና ይመልሱልኝ" ትላለች።

መልስ፦
ይሄ ስራዋ ምንም ችግር የለበትም። ምክንያቱም ሴት ወንድን እንድታክም የሚገፋ ምክንያት ከኖረ በዚህ ላይ ችግር የለምና። በዚህ ላይ አካሉን እንድትነካው የሚያስገድድ ሁኔታ ኖረም አልኖረም ችግር የለውም። ነገር ግን ከወንዶች ጋር በተያያዘ ቀጥታ አካል እንዳትነካ ጓንቶችን ልትለብስ ይገባታል።

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን
ከዌብሳይታቸው የተወሰደ
=
* ቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
* ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
* ዋትሳፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫       ➧አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል ሶስት 👑አቡ በከር ረዲየላሁ አንሁ የለይልን ሰላት በቤታቸው ጣሪያ ላይ ሆነው ሲሰግዱ ከታች የልጃቸው የአብደላን ድምፅ ይሰማሉ። ከዚያም ጣሪያ ላይ ሆነው ወደታች ሲመለከቱ አብደላና ሚስቱ በአንድ ግርግዳ ተለያይተው እርሷ ከውጭ ሆና ጆሮዋን ግርግዳው ላይ ለጥፋ አብደላ በዛኛው ጎን ሆኖ ቀሰራው ባጎደለው…
➲ቆንጆ ናት ግን ያገባት ሁሉ ሸሂድ ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

      ➧አቲካ ቢንት ዘይድ ክፍል አራት

➩አብደላ ሊሞት ነው? መቼ? እንደት? የሚለው ጥያቄ አጨናነቃት። ከባሏ የሚመጣላት አንዳንድ ምልክቶች ከቀን ወደ ቀን እያስጨነቃት ይሄዳል። በቅርቡ ሳልሞት አልቀርም ማለት ምን ማለት ነው? የሰው ልጅ በዚህ ለጋ እድሜው ካለምንም በሺታ የሚሞትበት ቀን መቃረቡን የሚሰማው ከመቸ ጊዜ ወድህ ነው? የአብደላህ ሚስት ጭንቀቱ በዛባት አብደላ ጠላቶች ይኖሩት ይሆን? እሺ ያ ከሆነ ለምን መድናን አንለቅም በማለት ከራሷ ጋር ትማጎታለች። አብደላህ ከውጭ ሲመጣ ያ የነበረው ጨዋታና ደስታ ከቤቱ ተኖ በምትኩ ሀዘንና ውጥረት ስፍኖበታል። የአብደላ ንግግር አንድ ጥያቄ ላይ አተኮረ።

➾ሀቢብቲ ከሞትኩ በኃላ ሌላ ባል ታገቢያለሺ?እስኪ ቃል ግቢልኝ ከእኔ በኃላ ሌላ ባል እንድነካሺ በፍፁም አልፈልግም። ፍፅሞም አያስደስተኝም ይላታል። የአብደላ ሚስት ችግሯ ይህ አይደለም። ችግሯ አብደላ ጋር ያላት ትዳር ፍቅር መተሳሰብና መተዛዘን ለምን ይቀጭ የሚል ነበር። በስምንተኛው ዓመተ ሒጅራ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ጧኢፍን ሊወሩ ለጅሀድ ሰው እንድዘጋጅ ከፍተኛ ጥሪ ይደረጋል። ሶሀቦች ሙሃጅሮችና አንሷሮች የተውጣጡበት መሪው ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም የሆኑበት በ 12000 የሚገመቱ ከፍተኛ ጦር ይዘጋጃል ከጦሩም ውስጥ አንደኛው አብደላህ ኢብኑ አቡበከር አልሲድቅ ረዲየሏሁ ዐንሁማ ነው።

➩ያቺ ታሪካዊ ቀን አብደላህ ከሚስቱ የሚለያይበት ቀን ከተፍ አለች። የአብደላህ ሚስት በልቧ ማሰላሰል ጀመረች ያአብደላህ ያ አንተ ልሞት ነው የሚለው ስጋትህ ገባኝ። ይህማ ማንም ወታደር በጦርነት ላይ የሚሰማው ስሜት ነው። ነገር ግን ምንም ሳትሆን እንደምትመለስልኝ እርግጠኛ ነኝ በማለት እራሷን አፅናናች።  ያቺ አብደላ ለመጨረሻ ጊዜ ሚስቱን የሚያይበት እርሷም ባሏን ለመጨረሻ ጊዜ የምታይበት ሰዓት መጣች። አብደላህ የሚስቱን አይን ማየት አልቻለም። እንባ አይኑን ጋረደው። ይህንን ጨረቃ የሚመስለውን ፊቷን ለመጨረሻ ጊዜ ለማየት ሞከረ የአይኑ ላይ እንባ አልተባበረውም።

➙መሰናበቱን ጥሎ በተደጋጋሚ ስሟን ብቻ ነበር የሚጠራው። ኑዛዜም አልነበረውም በልቡ ግን ብዙ እያለ ነው ሌላ ባል አታግቢ አላህ ወፍቆኝ ሻሂድ ከሆንኩ ጀነት ውስጥ እጠብቅሻለሁ። ሚስቱም እራሷን ሰብሰብ አድርጋ የአይኗን የልቧን የምላሷን ጉልበት አሰባስባ በሰመመን አንድበት አንድ ጥያቄ ትጠይቀዋለች። ግን ትመለስልኛለህ አይደል? ሄደህ እስከምትመለስ ናፍቆቱ ስለሚያስቸግርህ ነው እንድህ ተረብሸህሌ የምታነባው ትለዋለች። አብደላህ የዚህን ጥያቄ መልስ ለመመለስ አቅምም ሆነ ጊዜ አልነበረውም።ጦሩ ሊንቀሳቀስ ነው።
◉
◉
◉
◉
ኢንሻ አላህ ይቀጥላል

➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷➴➷
https://t.me/https_Asselefya1
https://t.me/https_Asselefya1
➾ሶብር

በማንኛውም ሁኔታ ላይ ሆነህ በሚመጣብህ ችግር ላይ ሶብር አናድርግ ችግሮች ቢደራረቡም !!ትዕግስት አድርጉ የእኛ ጌታ መካሻው እኛ ያላሰብነው፣ያላለምነው፣ ለካስ እንደዚህም አለ እንደ? ጌታየ!! በዚህ ሊክሰኝ ከሆነ በፈተኝስ ምን ቸግር አለው እስከምንል ድረስ ነው።
‏ابن القيم رحمه الله



من رحمة الله بعبده أن يبتليه ببلاء لا يستطيع البوح به،
ولا يجد من يفهمه في تفاصيله؛
حتى لا يكون في قلبه تعلُّقٌ بأحدٍ غير الله يشكو إليه .

( الوابل الصيِّب || ص ٣٥)


=
t.me/https_Asselefya1
የአላህ ግን ምን ጉድ ነዉ ! ለምን ግን ተጨካከን በራሳችሁ እህት እንድሆን የማትፈልጉትን ለምን በሰዉ እህት ላይ ❓

=