💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
ሁሌ ጭቅጭክን፣ አጉል ንትርክንና ብሽሽቅን እንደ ማስቲካ ለሚያመነዠኩ ሰዎች አላህ ይሁናቸው።

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
የምር ግን አንዳንድ ላጤዎች ካገቡ ቡሃላ፡ወጥ መስራት አልችልበትም፤ልብስ አስተጣጠብም አላውቅበትም፡…የሚሏት ነገር¡ የምር ግን ያቺ ድብን እያደረጋችሁ የምትሰሯት ወጥ'ሳ! ልብስ አስተጣጠባችሁስ ቢሆን…! ደግሞ ሚስጥራችንን አገለጥክ ብላችሁ ክሰሱኝ አሏችሁ! ምን ችግር አለው መረዳዳትስ የመልእክተኛው አለይሂ ሶላቱ ወስ'ሰላም ፈልግ አይደል ለምን ታፍራላችሁ?

ለነገሩ አንዳንዶቻቸው የሆነች ስጋት አለችባቸው ይመስለኛል… ደግሞ ይሄንም ተናገር በሉኝ አሏችሁ!

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
علي صلاح العمر
﴿لا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفسًا إِلّا وُسعَها لَها ما كَسَبَت وَعَلَيها مَا اكتَسَبَت رَبَّنا لا تُؤاخِذنا إِن نَسينا أَو أَخطَأنا رَبَّنا وَلا تَحمِل عَلَينا إِصرًا كَما حَمَلتَهُ عَلَى الَّذينَ مِن قَبلِنا رَبَّنا وَلا تُحَمِّلنا ما لا طاقَةَ لَنا بِهِ وَاعفُ عَنّا وَاغفِر لَنا وَارحَمنا أَنتَ مَولانا فَانصُرنا عَلَى القَومِ الكافِرينَ﴾



علي صلاح العمر
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮች    【ክፍል  ⓵⓷】 ⟰──────⟰ ⑤ ﴾መስጅድ  መግባት እና መቆየት﴿ ⇒⊰ሀይድ ላይ ያለች ሴት ለአስፈላጊ ጉዳይ በመስጂድ አቋርጣ መሄድ ትችላለች፡፡ ነገር ግን በምታልፍበት ጊዜ መስጅዱ ላይ ምንም አይነት ደም ሊያርፍእንደማይገባ የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡ መስጅድ ዉስጥ ጦሀራ የሆነውን ምራቅ መትፋትም ተከልክሏልና፡፡ ⇒⊰ሀይድ ላይ ያለች…
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮች


 【ክፍል  ⓵⓸
╰━━━━━╯

⑥ ﴾ግንኙነት መፈፀም﴿

ሀይድ ላይ ያለችን ሴት መገናኘት ክልክል ነው፡፡ ይሄም በግልጽ የቁርአን አንቀጽና በትክክለኛ ሀዲስ እንድሁም በምሁራኖች ሙሉ ስምምነት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡

۞قال تعالى: فَٱعۡتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَاۤءَ فِی ٱلۡمَحِیضِ وَلَا تَقۡرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ یَطۡهُرۡنَۖ

አንድ ሰው በሀይድላይ ያለችን ሴትመገናኘት ይፈቀዳል የሚል እምነት ቢኖረው ወይም በዚህ እምነቱ ምክንያት ሀይድ ላይ ካለች ሴት ጋር ግንኙነት ቢፈጽም ከእስልምና ይወጣል፡፡ ማንኛውም ሃራምነቱ ላይ ምንም አይነት የምሁራኖች ልዩነት ያልተንጸባረቀበትን፣ በቀላሉ ተራው ሙስሊም ማህበረሰብ ሳይቀር የሚያውቀውን ጉዳይ ያስተባበለ ሰው ከእስልምና ለመውጣቱ ምሁራኖች ሁሉ በአንድ ድምጽ ተስማምተውበታል።

۞عن ابي هريرة رضي الله عنه أن النبي ﷺ قال من اتی حائضا  أو أمرأة  في دبرها او كانها فصدقه بما يقول ، فقد كفر بما انزل علی  محمد ،رواه أهل السنن وصحح الألباني

ነገር ግንሀይድ ላይ ያለችን ሴት መገናኘትሀራም መሆኑን ባለማወቁ ወይም ሀይድ ላይ መሆኗን ባለማወቁ ምክንያትግንኙነት ቢፈጽም ወንጀልም ይሁን የማካካሻ ቅጣት የለበትም፡፡ ሀይድ ላይ ያለችን ሴት መገናኘትሀራምመሆኑንከማመኑ ጋር በማወቅናበምርጫው ግንኙነትየፈጸመ ግለሰብ ከተውበትና ከኢስቲግፋር በተጨማሪ ወንጀሉን የፈጸመው የሀይዷ የመጀምሪያው አካባቢ ከሆነ (ደሙ በብዛት በሚፈስበት ወቅት) አንድ ዲናር (15ግራም ወርቅ)፣ የመጨረሻዎቹ አካባቢ ከሆነ ደግሞ ግማሽ ዲናር ምጽዋት የማውጣት ግዴታ አለበት፡፡ ከፊል ምሁራኖች ደግሞ ይህ ቅጣት ከወር አበባዋ ሁኔታ ጋር ሳይሆን ከእሱ የመክፈል አቅም ጋር የተያያዘ ነው የሚልን ሀሳብ ሰንዝረዋል፡፡ የመክፈል አቅሙ ያለው ወንጀለኛ አንድ ድናር፣ የአቅም ዉስንነት ያለበት ከሆነ ደግሞ ግማሽ ድናር ይከፍላል ማለት ነው፡ይህ ቅጣት በወንጀሉ ላይ ፈቃደኛ እስከሆነች ድረስ ሴቷንም በእኩል ደረጃ ይመለከታታል፡፡ ከታች የተጠቀሰውን ሀዲስ ኢብኑል ቀይም ትክክለኛ ብለውታል። ሸይኽ አልባኒ በርካታ መጽሀፍቶቻቸው ላይ ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል። ሸይኽ ኢብኑ ባዝም እንደዚሁ። ኢማሙ አህመድም በዚሁ መሰረት ብይን ይሰጡ ነበር።

۞عن ابن عباس  رضي الله عنهما  : عن رسول الله ﷺ  في  الذي يأتي امرأته  وهي حائض قال ، يتصدق بدينار  او بنصف دينار: رواه الخمسة  وصحح الألباني في الإرواء

ባለቤቱ ሀይድ ላይ እያለች ግንኙነት ፈጽሞ የማካካሻ ቅጣቱን (ከፋራ) ካወጣ በኋላ ሌላ ግንኙነት ቢፈጽም ሌላ አድስ ከፋራ ማውጣት ያስፈልገዋል፡፡ ሁለተኛውን ግንኙነት የፈጸመው ለመጀመሪያው ከፍራ ሳያወጣ ከሆነ ደግሞ ለመጀመሪያው ከፋራ ያላወጣበት ምክንያት ሁለተኛ መፈጸምን አስቦ ከሆነ በፈጸመው ግንኙነት ልክ ተደራራቢ ከፋራ እንድያወጣ ይገደዳል፡፡ ይህም የሆነው ሸሪዓዊ ክልከላዎችን ለመተላለፍ የብልጠት አካሄድን መሄድ አይቻልምና ነው፡፡ ሀይድ ላይ የነበረች ሴት ግንኙነት መፈጸም የሚፈቀድላት ደሙ ካቆመበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ከታጠበችበት ጊዜ ጀምሮ ባለውወቅትለመሆኑ ከኢብኑ ሀዝምዉጭ ያሉ ዑለማኦች ተስማምተዋል፡፡ የቁርአኑ መልእክትም ይሄንኑ ሀሳብ ነው የሚገልጸው።

۞ فَإِذَا تَطَهَّرۡنَ فَأۡتُوهُنَّ مِنۡ حَیۡثُ أَمَرَكُمُ ٱللَّهُۚ

ሚስቱ ከመጽሀፍቱ ባለቤቶች (አህለልኪታብ) ብትሆንም እስካልታጠበች ድረስ ግንኙነት መፈጸም አይፈቀድለትም።ሀይድ ላይ ካለችሴትጋር ደም ከሚፈስበት አካል ዉጭ ያለን ከግንኙነት ዉጭ ያለን? ማንኛውም ቅርርብ መፈጸም ይቻላል፡፡

۞ عن أنس رضي الله عنه..  قال ﷺ.. اصنعوا كل شيءٍ إلا النكاح ...رواه مسلم


ነገር ግን ስሜቱን መቆጣጠር እንደማይችል ስጋት ያለው ሰው ሙሉ በሙሉ መራቅ ወይም ቢያንስ ከጉልበቷ እስከ እምብርቷ ድረስ ያለውን አካሏን መራቅ ይኖርበታል፡፡ ሚስትን ሀይድ ሲያጋጥማት ፍራሽን በመለየት ተራርቆ መተኛትን በተመለከተ የተላለፉ ሀድሶች በሙሉ ደካማዎች ናቸው።  ሀይድ ላይ ያለች ሴት የትዳር አጋሯ አካሏን ቀጥታ እንዳይነካ የሚያግድን ልብስ (የሴት ቱታ፣ ቁምጣ፣ ታይት...) መልበስ ይወደድላታል።

۞عن عائشة رضي الله عنها . كانت إحدانا إذا كانت حائضا ،، فأراد  رسول الله ﷺ أن يباشرها ،أمرها ان تتزر في  فور  حيضتها ثم يباشرها. وأيكم  يملك إربه كما كان  رسول الله يملك إربته . أخرجه مسلم

☞ሀይድ ላይ በነበረችበት ወቅት በተለያዩ ምክንያቶች ጁኑብ ብትሆን ከሀይድ የምትጸዳበትን ጊዜ ከምትጠብቅ ይልቅ ጀናባውን ለማስወገድ በማሰብ ጀነባ በሆነችበት ወቅት መታጠቧ ይወደድላታል።

«ኢንሻ አላህ ይቀጥላል๏๏๏๏

   •━━━ ✽ • ✽ ━━━•
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
አንዳድ ሚድያ ላይ ለሚያቀሩ ወንድሞች..!
~
በመጀመሪያ ይቅርታ! ምን ልል ነዉ አንዳዶች ለራሳቸሁ አስተካክላችሁ መቅራት ሳትችሉ እናቅራ ብላችሁ አትጀምሩ  ብር ክፍያ አለ በኦላይ ስለተባልክ ለራስህ ሳታስተካክል ሰዉ አስተካክላለሁ ብለህ ራስህንም ሰዉንም አታበላሺ አርፈህ ቁጭ ብለህ ራስህ አስተካክል መጀመሪያ።  ሌላዉ  እዉቀት ብቻ ስላለህ አስተካክለህ ስለምትቀራ  አደብ እና ስርአት ሳይኖርህም ባንተ አደብ እና ስርአት ጉድለት ሰዎችን አታበላሺ ሰዉ ከሚዉለዉ ሰዉ ጋር ነዉና የሚመስለዉ ያንተን አደብ እና ስርአት እጥነት ተምረዉ እንድበላሹ ሰበብ አትሁን። ሌላ ራስህን አትቆልል ዝቅ በል ራስ መቆለል ሀቂቃ ለማንም አይጠቅምም ! አጉል ቦታ ወገብህ ያሰብርሀል። ሌላ የምታቀራ ተማሪዎች ላይ አትኩራራ... ተማሪዎችህን አክብር ሁለዬ ጨፍጋጋ አትሁን  ተማሪዎች በሚገባቸዉ መልኩ አስተምራቸዉ.. እንድሁም በምታርም ጊዜ ተስፋ እየሰጠህ ለነገ አስተካክለዉ እንድመጡ እገዛቸዉ አጠናክራቸዉ።  አታስደንግጣቸዉ  መቅራት ቢችሉበት አንተጋ  አስተካክለን ብለዉ አይመጡም ነበር  ። ሌላ በተቻለህ አቅም ተማሪዎችህ ፍሬ እንድያፈሩ እነሱ የተቻለህ አቅም አበራታቸዉ አይዟችሁ በላቸዉ። መልካም ሰዉ ሁን ልክ እንደ አባት ወንድም.ነገ ሌላ ቦታ ሂደዉ የሚያመሰግኑህ እንጅ የሚያማርሩህ አይነት ሰዉ አትሁን!!

የቀረ ካለ ጨምሩ እናተ እኔም ትዝ ካለኝ እጨምራለሁ...✍️


t.me/https_Asselefya1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
اَلسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللهِ وَبَرَكاتُه‎

ሰላም አደራችሁ ቤተሰብ ሁላ 🎇

=
Audio
👉ዉብ ቲላዋ ግብዣ

🎙በወንድም ኢድሪስ አህመድ

=
https://t.me/Abu_yehya
«ወይ'ኔ ሳላገባ 2024 ገባ!» አትበይ፤
ኢትዮጲያ ገብተሽ አግቢ፤ እዛ 2016 ነው!»አለች አንዷ!

ሳዑዲ ደግሞ ገና 1445 ነው!

እያገባችሁ፤ መዘናጋትና መጃጃል ጥሩ አይደለም¡

منقول
እኔ አላልኩም እሺ አሉ ነዉ።
ከአላህ ተዓምራቶች
~
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው። በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ።”  (አርሩም 30፤21)

የጥንዶችን ሕይወት የተሻለ የሚያደርገዉ የቁስ የገንዘብና የዱንያ መጣቀሚያዎች መብዛት ሳይሆን እዝነትና ፍቅር በመካከላቸዉ መብዛቱ ነው።

=
𝐓𝐞⤳ t.me/abuUseyminabdurehman
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮች  【ክፍል  ⓵⓸】 ╰━━━━━╯ ⑥ ﴾ግንኙነት መፈፀም﴿ ☞ሀይድ ላይ ያለችን ሴት መገናኘት ክልክል ነው፡፡ ይሄም በግልጽ የቁርአን አንቀጽና በትክክለኛ ሀዲስ እንድሁም በምሁራኖች ሙሉ ስምምነት የተረጋገጠ ጉዳይ ነው፡፡ ۞قال تعالى: فَٱعۡتَزِلُوا۟ ٱلنِّسَاۤءَ فِی ٱلۡمَحِیضِ وَلَا تَقۡرَبُوهُنَّ حَتَّىٰ…
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮች


  【ክፍል  ⓵⓹】
┗━━━━━━┛

           ⑦﴾ፍች﴿

በሀይድ ላይ ያለችን ሴት መፍታት በጽኑ የተከለከለ ነው፡፡ መጤ ፍቺ (ጦላቀል ቢድዒይ) የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም ላይ የምሁራኖች ስምምነት አለ።

{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّبِیُّ إِذَا طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَاۤءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ وَأَحۡصُوا۟ ٱلۡعِدَّةَۖ   {الطلاق _١}

ሀይድ ላይ እያለች የተፈታችን ሚስት መመለስ ግዴታ ነው፡፡ ከመለሳት በኋላ መፍታት ከፈለገ ደግሞ ግንኙነት ባልፈጸሙበት የንጽህናዋ ወር ወይም በእርግዝና ላይ የምትሆንበት ጊዜ ጠብቆ መፍታት እንደሚችል ተገልጿል፡፡

عن ابن عمر انه طلق إمرأته وهي حائضا فسأل عمر  رسول الله  وقال مره فليراجعها  حتى تطهر  ثم تحيض  حيضة أخرى  ثم تطهر  ثم يطلق  بعد  او يمسك..{أخرجه مسلم}

ሀራም ከመሆኑ ጋር ሚስት ሀይድ ላይ ባለችበት ወቅት ፍቹ ቢፈጸም ግን ፍቹ ይጸናል የሚለው እይታ የተሻለ ነው፡፡ የአብዛኛዎቹ ምሁራኖች ምርጫም ይሄው ነው፡፡ በርግጥ ይህ ጉዳይ በምሁራኖች መካከል እጅግ በጣም ከፍተኛ አለመግባባት ከታየባቸው የፊቅህ አጀንዳዎች ዉስጥ ይመደባል፡፡

عن ابن عمر انه طلق إمرأته وهي حائض فسأل رسول الله وقال: مره فليراجعها ثم ليطلقها  طاهرا أو حاملا : رواه مسلم

فقال ابن عمر (وحسبت علي  بتطليقة ) رواه البخاري )


መመላለስ በሚያስችለው ፍቺ የተፈታች ሴት ባለቤቷ  እንዳይመልሳት በማሰብ ሀይድ ማየት አለማየቷን ወይም መጸነስ አለመጸነሷን ወይም የሚገመተውን የመውለጃ ጊዜዋን መደበቅ ሃራም ተደርጎባታል፡፡

{ وَلَا یَحِلُّ لَهُنَّ أَن یَكۡتُمۡنَ مَا خَلَقَ ٱللَّهُ فِیۤ أَرۡحَامِهِنَّ إِن كُنَّ یُؤۡمِنَّ بِٱللَّهِ وَٱلۡیَوۡمِ ٱلۡـَٔاخِرِۚ  البقرة :٢٢٨

በሀይድ ላይ ያለችን ሴት መፈታት የሚቻልባቸው ሶስት ሁኔታዎች አሉ፡፡ እነሱም፦ ኹልዕ (የፍች ጥያቄው ካሳበመክፈል በራሷ ተነሳሽነት ከቀረበ) መረጃውም ኹልዕ ከፍቺ አለመቆጠሩ ነው።  ሀይድ ያየችው በእርግዝናዋ ወቅት ላይ ከሆነ መፍታት ይቻላል፡፡ መረጃውም መልእክተኛው ለኢብኑ ዑመር በሀይድ ላይ እያለች የፈታትን ሚስቱን እንዲመልሳትና ከነጻች በኋላ ዳግም ሃይድ አይታ እንደነጻች ወይም እርግዝናዋ እንደተረጋገጠ ከፈለጋት እንድይዛት ካልፈለጋት ደግሞ እንዲፈታት መፍቀዳቸው ነው።

ሀይድ ያየችው ከተጋባች በኋላና፤ ከባሏ ጋር ከሰዎች ተገልለው ከማሳለፋቸው በፊት ከሆነ መፍታት ይቻላል፡፡

{ یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوۤا۟ إِذَا نَكَحۡتُمُ ٱلۡمُؤۡمِنَـٰتِ ثُمَّ طَلَّقۡتُمُوهُنَّ مِن قَبۡلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ فَمَا لَكُمۡ عَلَیۡهِنَّ مِنۡ عِدَّةࣲ تَعۡتَدُّونَهَاۖ  أحزاب - ٤٩

ሀይድ ላይ ላይ ያለች ሴት ኒካህ ማድረግ ትችላለች፡፡ ምክንያቱም ይሄን የሚከለክል አንዳችም መረጃ የለም፡፡

قال ابن حزم في المحلى : جائز للحائض  والنفساء  ان يتزوجا

ሀይድና ኒፋስ ላይ ያሉ ሴቶች ማግባት ይፈቀድላቸዋል ይላሉ ኢብኑ ሀዝም።

«ኢንሻ አላህ ይቀጥላል๏๏๏๏✍️

     •━━━ ✽ • ✽ ━━━•
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮች   【ክፍል  ⓵⓹】 ┗━━━━━━┛            ⑦﴾ፍች﴿ ☞ በሀይድ ላይ ያለችን ሴት መፍታት በጽኑ የተከለከለ ነው፡፡ መጤ ፍቺ (ጦላቀል ቢድዒይ) የሚል ስያሜም ተሰጥቶታል፡፡ በዚህም ላይ የምሁራኖች ስምምነት አለ። { یَـٰۤأَیُّهَا ٱلنَّبِیُّ إِذَا طَلَّقۡتُمُ ٱلنِّسَاۤءَ فَطَلِّقُوهُنَّ لِعِدَّتِهِنَّ…
ሀይድ ላይ  ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮች



ክፍል  ⓵⓺
⇗⇗⇗⇗⇗⇗

የሀይድ ማዘግያ ወይም ማፍጠኛ መድሀኒቶችን መጠቀም ﴿

ጤናዋ ላይ የጎንዮሽ ተጽእኖ ወይም ጉዳት እስከሌለው፣ ባለትዳር ከሆነች ባለቤቷ እስከፈቀደላት ድረስ እንድሁም ሸሪዓዊ ድንጋጌዎችን ለማሳለፍ በማሰብ እስካልሆነ ድረስ ሀይድን የሚያፋጥን ወይም የሚያዘገይ መድሀኒት መጠቀም ይፈቀዳል።

۞قل جابر كنا نعزل عل عهد رسول الله  فبلغ ذالك النبي   فلم ينهانا.رواه مسلم

ከላይ የተጠቀሰው ሀዲስ ለወንዶች የዘር ፈሳሻቸውን ከሴቷ ብልት ዉጭ ማፍሰሱ የተፈቀደ ከሆነ ሴቷም ብትሆን ተመሳሳይ አገልግሎት ያላቸውን መድሀኒቶች መጠቀም ትችላለች ማለትን ይጠቁማል፡፡

ሀይድ ማቆሙን ማረጋገጫ መንገዶች
  ┉┄┉┄┉┈┉┈┉┈┉┈┉┈┉

የሀይድ ደም ማቆሙ በሶስት መንገድ ሊረጋገጥ ይችላል፡፡ ይሄውም፦

①ᖳ ⇘የሀይድ ደም መጠናቀቅን ተከትሎ ከማህጸን የሚለቀቅውን ዉሃማ ነጭ ፈሳሽ መፍሰስ አለመፍሰሱን በማረጋገጥ የሀይድን መጠናቀቅ ማረጋገጥ ይቻላል። ቀዳሚውና ከሁሉም የተሻለው ማወቂያ መንገድም ይሄ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ፈሳሽ በአንዳንድ ሴቶች ላይ ሙሉ በሙሉ ላይከሰት ይችላል፡፡ ለሌሎች ደግሞ የሚመጣው ዘግይቶ ሊሆን ይችላል፡፡

« عن عائشة  أن النساء كن يبعثن  إلحها بالدرجة  فيها  الكرسف فيه  الصفرة.  فتقول . لا تعجلن حتی ترين  القصة البيضاء..تُريدُ بذلك الطهر  من الحيضة ..وبلغ ابنة زيد بن ثابت رضي الله عنهما .. أن النساء  يدعون بالمصابيح  من جوف  اليل ينظرن  الی الطهر ، فقالت  .. ما كان النساء يصنعن  هذا ، وعلبت عليهن  ،. فتح الباري في شرح صحيح البخاري »

ᖳ ⇘እንደጥጥ፣ሱፍ ወይም መሰል ልብሶችን በመራቢያ አካል በመጨመር የሀይድ ደም መኖር አለመኖሩን በማረጋገጥ ሀይድ መጨረስ አለመጨረስን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ይሄን ከላይ ከተጠቀሰው መረጃ መረዳት ይቻላል።


ᖳ ⇘አንድ ቀን ከነሌሊቱ ምንም አይነት ፈሳሽ ሳያጋጥማት ከቀረ ሀይድ እንደተጠናቀቀ በመውሰድ መንጻት ይኖርባታል፡፡ ይህ ከዘmeናችን ዑለማኦች የሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ እይታ ሲሆን ከቀደምቶች ደግሞ ኢብኑ ቁዳማ ተጠቃሾች ናቸው፡፡

«ኢንሻ አላህ ይቀጥላል๏๏๏๏๏✍️

«ስለ ሀይድ በዚሁ አጠናቀናል ቀጣይ ስለ(ኢስቲሀዷ(የበሽታ ደም ) እንቀጥላለን»

   •━━━ ✽ • ✽ ━━━•
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
«ነገሩ እንዲህ ነው …

ሚስት በባሏ ተቆጥታ ውላለች፤ ማታ ሲገባ እራት አቅርባለት ዘወር አለች።

ሚስኪኑ ባልም "ውዴ ነይ እንጂ እንብላ!" ሲላት፤
"ውስጤ ጥሩ ስላልሆነ አልበላም!" ትለዋለች።

ወደ ልጁ ዞር ብሎ "ልጄ ነይ እንብላ!" ሲላት፤
"አልበላም፤ ቅድም ከኡሚ ጋር ኩሺና ጠግቤ በልቻለሁ!" አትለውም!»

የተመታች! ጠስቃ በልታ እርሱን ያኮረፈች መስላ ልታጨናንቀው¡
ሴቶች'ኮ በመጥፎ ዓይን አይዩህ¡



https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf
«ሀይድ (የወር አበባ)በተመለከተ የተላለፉ ፁሁፎች፦ »

             ↷⇓⇓↶

የሀይድ ትርጉምና ተያያዥ ነጥቦች ⓵
t.me/https_Asselefya1/16437

የሀይድ ትርጉምና ተያያዥ ነጥቦች ⓶

t.me/https_Asselefya1/16472

ሀይድ እና እድሜ

t.me/https_Asselefya1/16531

ሀይድ እና  የጊዜ ቆይታዉ ⓵

t.me/https_Asselefya1/16585

ሀይድ እና የጊዜ ቆይታዉ ⓶

t.me/https_Asselefya1/16654

ልምድ ያልጠበቀ ሀይድ

t.me/https_Asselefya1/16751

ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተፈቀዱት ነገሮች

t.me/https_Asselefya1/16797

ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ነገሮች

√ሶላት፦ t.me/https_Asselefya1/16848

√ፆም፦ t.me/https_Asselefya1/16870

√ሀጂ፦ t.me/https_Asselefya1/16924

√ቁርአን፦ t.me/https_Asselefya1/16968

√መስጅድ፦ t.me/https_Asselefya1/16988

√ግኑኝነት፦ t.me/https_Asselefya1/17197

√ፍች፦ t.me/https_Asselefya1/17211

የሀይድ ማዘግያ መጠቀም⇓
t.me/https_Asselefya1/17215

ሀይድ ማቆሙ ማረጋገጫ⇓
t.me/https_Asselefya1/17215

ለራስዎ ያንብቡ ከዛ ለሌሎች ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ይሁኑ ! ☜


=
↳ከመኝታዎ በፊት↲

(³³) ግዜ ሱብሓነላህ
(³³) ግዜ አልሐምዱሊላህ
(³³) ግዜ አላሁ አክበር
ማለት እንዳይረሱ።

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ - ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-

«ከመተኛቱ በፊት ተስቢህ ማድረግ የለመደ ሰው፣ ፍላጎቱን ለማሟላት ጉልበትና ጥንካሬ ይሰጠዋል፤ በዒባዳውም ላይ ብርታት ይሰጠዋል።»

=
http://t.me/https_Asselefya1
ጉዳያችሁን ሁሉ ለአላህ ስጡና ተኙ እሺ፡፡

ከማ ቃለ፦ t.me/AbuSufiyan_Albenan/4361

=
_hfzNmilpdQtr-h3
تلاوة تصويريِّة عذبة لوصايا لقمان عليه السلام لابنه
فجر اليوم الثلاثاء ١٤٤٥/٧/٤
من المسجد النبوي

الشيخ أحمد حميد بن طالب

=
📂| قال العلامة #صالح_الفوزان -حفظه الله :

من شذ عن المسلمين وتبع دعاة الضلالة
فإنه يهلك مع الهالكين

📓|شرح حديث انا في جاهلية وشر (25)     
                                          
http://t.me/https_Asselefya1
በስልካችሁ internet ስትጠቀሙ የተለያዩ ማስታዎቂያዎች እንዳይመጡ ለማድረግ የሚከተለውን መንገድ መጠቀም ትችላላችሁ።
1. Settings ላይ ግቡ።
2. Connections
3. More connections
4. Private DNS የሚለውን ንኩና off የነበረውን ወደ Private DNS hostname ቀይራችሁ dns.adguard.com ብላችሁ ፃፉ።
5. SAVE

እንደስልካችሁ አይነት ከላይ የጻፍኩላችሁ step ሊለያይ ይችላል ስለዚህ በቀላሉ settings ላይ ገብታችሁ የsearch bar ላይ dns ብላችሁ ፅፋችሁ ማግኘት ትችላላችሁ።
በውሥጡ ያለ መሰልቸት በስስት  በውብ ተስፋ ሰምጠክበት የምትቀርበው  ሀላል ነገር ብቻ ና ብቻ ነው!

ሀራም ነገር ግን ጊዜያዊ ደስታ፣ የውስጥ መረበሽ ፣ መጨነቅ ፣ መጠበብ ሁሉም ነገር ውስብስብ የሚያደርግ እስር ቤት ነው!


አሏህ ሆይ ከሀረምካቸው ነገሮች አርቀን።
ሀላል ባደረግካቸው ነገሮች አስውበን


~
t.me/Binit_Seid_Al_kelaliya