💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.47K photos
2.08K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
L&A 

بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير


ዛሬ አንዷ ጓደ ላጤነትን ተሰናብታለች መንገድህን ጨርቅ ያድርግለህ ብላ በሉ ኑ እናንተም ተቀላቀሉ።

ደስታሽ ደስታየነው ሉሉየ

✍ ኡሙ ዑበይዳ
የሱናዋ~ቆንጆ በተውሂድ ያበበች
L&A  باعك الله لكما وباعك عليكما وجمع بينكما في الخير ዛሬ አንዷ ጓደ ላጤነትን ተሰናብታለች መንገድህን ጨርቅ ያድርግለህ ብላ በሉ ኑ እናንተም ተቀላቀሉ። ደስታሽ ደስታየነው ሉሉየ ✍ ኡሙ ዑበይዳ
ባረከላሁ ለኩማ ወባረክ አለይኩማ ወጀመአ በይነኩማ ፊል ኸይር አላህ ትዳርሺ ያማረ የሰመረ ያድርግልሺ መልካም የትዳር ዘመን እህታችን 🌸🎈 በሉ ወቅቱ በጋ ነዉ አሁን ሰርግ አብሉን ተከተሉ.....! 2016 ላጤ እንዳይተርፍ እ¡
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተፈቀዱ ጉዳዮች ➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖ ❝ክፍል  ⓼❞ ↜↝↜↝ ⎇ሀይድ ላይ ያለች ሴት ከሀይድ ደሟ ዉጭ ነጃሳነት ያለው ምንም ነገር የለባትም፡፡ ምራቋ፣ ላቧ፣ መላ አካላቷ ሁሉ ንጹህ ነው፡፡ ሀይድ ላይ ካለች ሴት ጋር መሳሳም፣ መተቃቀፍ፣ አብሮ መብላት እና አብሮ መተኛት... ባጭሩ ከግንኙነት ዉጭ ያለን ማንኛውንም ጉዳይ መፈጸም እንደሚቻል የሚጠቁሙ ግልጽ ሀዲሶች እንድሁም የዑለማኦች…
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮዎች
➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖
〰

❝ ክፍል   ⓽ ❞
⇡⇢⇠⇢⇠⇡

         ➀⊰ ሶላት፦ ⊱

1☞ሀይድ ላይ ያለች ሴት ግዴታም ይሁን ተጨማሪ የሆኑ ሶላቶችን መስገድ አትችልም፡፡ ብትሰግድም የምታገኘው አንዳችም አጅር የላትም፡፡ ይልቁንም የአላህን ክልከላ ተላልፋ በመስገዷ ወንጀለኛ ነች፡፡ የጌታዋን ክልክላ በማክበር ከሶላት ብትቆጠብ ግን አጅር ታገኝበታለች።

۞عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه  أن النبي صلى الله عليه وسلام  قال..،، أليس ؼذا حا؜ت لم تصل ولم تصم ?? فذالك نفصان دينها .عواو البخاري "

۞قال النووي : في شرح مسلم :أجمع المسلمون أن الحائض والنفساء لا تجب عليهما الصلاة ولا الصوم في الحال""


2☞በሀይድ ምክንያት ያለፏትን ሶላቶች ቀዷእ ማውጣት አይጠበቅባትም፡፡ ቀዷእ ብታወጣም ተቀባይነት የለውም፡፡ እንዳውም ሸሪዓው ያልደነገገውን በመፈጸሟ ተጠያቂነት አለባት፡፡ በሀይድ ምክንያት ያለፉ ሶላቶችን ቀዷእ ማውጣት ኸዋሪጅ የተባሉት የጥፋት አንጃዎች መለያ ነው።

۞قالت ؚا،ش؊ رضي الله عنها: كان  يصيبنا ذالك فنؤمر بقضاء الصوم ولا نؤمر بقضاء الصلاة . متفق عليه

3☞አንድት ሴት የሶላት ወቅት ከገባ በኋላ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሶላቱን ከመስገዷ በፊት የሶላቱ ወቅት ሳያልፍ ሀይድ ቢያጋጥማት ያንን ሶላት ቀዷእ መስገድ አይጠበቅባትም፡፡ ይህ የሀነፊያዎች እና የማሊኪያዎች ምርጫ ነው። ኢብኑ ተይሚያምይሄንኑ ነውየሚያጠናክሩት፡፡ምሳሌ፦ዙህርን አዘግይታ ለመስገድ አቅዳ ከመስገዷ በፊት ሀይድ ቢያጋጥማት ይሄን ሶላት ቀዷእ ማውጣት አለባት የሚሉ ምሁራኖች ቢኖሩም ትክክለኛና ግልጽ መረጃ የላቸውም፡፡ ቀዷእን መደንገግ አድስ ሸሪዓዊ መመሪያን መደንገግ ስለሆነ ትክክለኛና ግልጽ መረጃ ያስፈልገዋል።

4☞በንጽህናዋ ወቅት የረሳችው ሶላት መኖሩን ሀይድ ከጀመራት በኋላ ብታስታውስ ያንን ሶላት መስገድ የምትችለው ከሀይድ ከነጻችበኋላነው፡፡ ምሳሌ፦ ዙህር ሶላት አለመስገዷን የዙህር ወቅት አልፎ ሀይድ ከጀመራት በኋላ ብታስታውስ ከስድስት ወይም ከሰባት ቀን (ከታጠበች) በኋላ ትሰግደዋለች፡፡

5☞አንድት ሴት የነጻችው በሆነ ሶላት ወቅት ላይ ከሆነ ወቅቱን ያገኘችውን ሶላት ብቻ እንጅ ሌላን ሶላት እንድትሰግድ አትታዘዝም፡፡ ሶላቱ ምንም ይሁን ምን ሀይድ ላይ በነበረችበት ጊዜ ወቅቱ እስካለፈ ድረስ ያንን ሶላት እንድትሰግድ የሚያስገድድ ምንም አይነት መረጃም ምክንያትም የለም፡፡ ለምሳሌ፦ በዐስርወቅት ላይ የጸዳች ሴት ከዐስር ሶላት ዉጭ ሌላ ምንም አይነት ሶላትን መስገድ አይመለከታትም፡፡ በዐስር ወቅት የጸዳች ዙህርን፣ በዒሻእ ወቅት የጸዳች መግሪብን መስገድ ይጠበቅባታል የሚል እይታ ያላቸው ከፊል ሰለፎች እንድሁም ምሁራኖች ቢኖሩም ሃሳባቸው ግን ከትክክለኛና ግልጽ መረጃ የራቀ፣ በደካማ መረጃዎች ላይ የተደገፈ እንድሁም ግልጽ የሆኑ መረጃዎች ጋር የሚጣረስ ነው፡፡ ይህ (መስገድ የለባትም የሚለው አቋም) የሀነፊያዎች፣ የዟሂሪያዎች፣ በዘመናችንም የሸይኽ ዑሰይሚኒ አቋም ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከእኩለ ሌሊት በኋላ የጸዳች ሴት መግሪብንም ይሁን ዒሻእን መስገድ አይጠበቅባትም ማለት ነው።

6☞ሀይድ ማጠናቀቋን ያረጋገጠችው በሆነ ሶላት የመጨረሻ ወቅት (አንድ ሙሉ ረከዓ መስገድ በሚያስችል ወቅት) ላይ ቢሆንና እስከምትተጣጠብ ድረስ ወቅቱ ቢያልፍ ታጥባ እንዳጠቀቀች ያለፋትን ሶላት ትሰግዳለች፡፡ ሶላቷም በጊዜው እንደተሰገደ ነው የሚቆጠረው።

۞عن أبي هريرة ان رسول الله قال: من أدرك ركعة من الصلاة فقد أدرك الصلاة. رواه البخاري

«ኢንሻ አላህ ይቀጥላል๏๏๏๏๏๏๏✍️

  •━━━ ✽ • ✽ ━━━•
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
﴿مَنِ اهتَدى فَإِنَّما يَهتَدي لِنَفسِهِ وَمَن ضَلَّ فَإِنَّما يَضِلُّ عَلَيها وَلا تَزِرُ وازِرَةٌ وِزرَ أُخرى وَما كُنّا مُعَذِّبينَ حَتّى نَبعَثَ رَسولًا﴾

إبراهيم مدهش المنصري

=
𝐭.𝐦𝐞/𝐡𝐭𝐭𝐩𝐬_𝐀𝐬𝐬𝐞𝐥𝐞𝐟𝐲𝐚 1
🔖ሸይኽ የህያ አነጅም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

«ወንድ ልጅ ጉዳዩ ሊሟላና ህይወቱ ሊያምር አይችልም በሷሊህ ሚስት ቢሆን እንጂ። ሴት ልጅ ልትረጋጋና ህይወቷ ሊሰምር አይችልም በሷሊህ ባል ቢሆን እንጂ።»

【تأسيس الأحكام 172/4 】
=
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
«በፂም ያሳመረን»
---------------------
ይድረስ ትውስታዬ ፂም ለሚጋጥጡ፡
ሲመክሯቸው ደግሞ እጂግ ለሚቆጡ፡
ሸይጧን ለመከተል ለሚቀላውጡ፡
በጥመት ላይ ሆነው እጂግ ለሚቀብጡ፡
መልዕክቴን አድርሱ በባቡር በፈረስ፡
ፂም የላጩ ሰወች እስኪሰሙ ድረስ፡
------------------------
ሙስሊሞች አድርጎ በፂም ላሳመረን፡
ፂምን አሳድጉ ብሎ ላስተማረን፡
ሙሉ በሆነ ህግ ሁሉን ለነገረን፡
አልሀምዱ ሊላሒ እኛን ለፈጠረን፡
----------------------------
ወንድ ልጅ ተወልዶ ፂሞቹን ከላጨ፡
ፊቱ ዱባ መስሎ ከተቁለጨለጨ፡
ፂሙን ለማፋፋት ከተሙለጨለጨ፡
ጥርጥር የለውም ከአሏህ ጋር ተጋጨ፡
--------------------------
ከኋላ ከፊቱ ሀራም ስዕል ስሎ፡
ሙሀመድ ነኝ ካለ ሙሽሪኮችን መስሎ፡
ወንጀል ነው ተግባሩ በጣም ተሳስቷል፡
የነብዩን መስመር ሱናውን ረስቷል፡
----------------------------
ወንድ ነኝ እያለ ጥምጣም ከወደደ፡
አቡ-ፉላን ሆኖ ፂሙን እየላጨ ከተረማመደ፡
ምኑን ወንድ ሆነ ሴት መስሎ እየሔደ፡
---------------------
ወንድሜ ተመከር ተከልከል ከምላጭ፡
ውበትህ ነውና ፂምህን አትላጭ፡
ወንድ ሁን እባክህ ጀግንነት ይሰማህ፡
የልብህን እምነት ሸይጧን እንዳይቀማህ፡
ስልጣኔ መስሎህ ፂምህን አትጣል፡
ወንጀል ነው እወቀው አሏህን ያስቆጣል፡
------------------------
ያስከብራል እንጂ ፂም አያዋርድም፡
ሱናውን የተወ ነብዩን አይወድም፡
ፊዳከ በማለት ሁሌ ብታቅራራ፡
በየሚዲያው ላይ ሁሌ ብታወራ፡

የፊትህ ገፅታ ሀቅን ካልተጣራ፡
የማይተገበር ወሬ ምን ይሰራል፡
አታላዩ በዛ ከማን ጋር ይኖራል፡
የተቦጫጨቀ ሱሪ እየገተተ፡
የነጮችን ፈለግ ከተመለከተ፡
የጀነቱን መሪ ነብዩን ከረሳ፡
እርቃኑን ከቆመ ከሆነ እንደ እንሰሳ፡
ተንቀሳቃሽ በድን ይባላል ሬሳ፡
---------------------------
ፊዳከ የሚል ጌጥ ፕሮፋይል ሰቅሎ፡
ልብሱን ከገተተ ፂሙን ተጎንድሎ፡
ይህ ሰው ሙሉ አይደለም ይባላል ጎደሎ፡
ፂማችን ውበት ነው ድንቅ መከበሪያ፡
የነብዩን ፈለግ ግሩም መተግበሪያ፡
ውበቱን ግርማውን ሆኖ መተግበሪያ፡
---------------------------
ምን ወንጀል ቢበዛ ሀቁን ባንወጣም፡
በፂማችን ብቻ አጂር ግን አናጣም፡
ምስጋና ይገባው በተውሒድ ያነፀን፡
እኔን ተከተሉ ብሎ ለቀረፀን፡
በአንድ አሏህ እመኑ ብሎ ላስተማረን፡
ጀነት አለላችሁ ብሎ ላበሰረን፡
የአሏህ ሰላም ይሁን በነቢ ሙሀመድ፡
በሀቁ ዘበኛ በኢማኑ ገመድ፡
አወ አልሀምዱ ሊላህ በኢስላም ላኖረን፡
በውት አከናንቦ በፂም ላሳመረን፡
-----------------------------
«በኑረዲን አል አረብ»
---------------------------
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
«ምንም ያህል ወንጀል ቢኖርብህ ግዴታህንም በአግባቡ ባትወጣም ምክርህን ለግስ ገስፅም

«ኢብኑ ረጀብ ረሂመሁላህ እነዲህ ይላሉ፦»

"መምከር ከወንጀል ፍፁም ለሆነ ሰው ብቻ ቢሆን ኖሮ ከአላህ መልክተኛ በኋላ ማንም ባለመከረ ነበር። ምክንያቱም ከነቢዩ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ውጭ ማንም ፍፁም የለምና።"
(ለጣኢፉ አልመአዓሪፍ  ገፅ: 19)

عِظ وانصحْ وإنْ كنتَ مقصرا
ــ قال ابن رجب : لو لمْ يعِظ إلا معصومٌ من الزلل
لم يعِظ الناسَ بعد رسول الله صلى الله عليه وسلم أحدٌ !
لأنه لا عصمةَ لأحدٍ بعده. لطائف المعارف،ص19

=
t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮዎች ➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰 ❝ ክፍል   ⓽ ❞ ⇡⇢⇠⇢⇠⇡          ➀⊰ ሶላት፦ ⊱ 1☞ሀይድ ላይ ያለች ሴት ግዴታም ይሁን ተጨማሪ የሆኑ ሶላቶችን መስገድ አትችልም፡፡ ብትሰግድም የምታገኘው አንዳችም አጅር የላትም፡፡ ይልቁንም የአላህን ክልከላ ተላልፋ በመስገዷ ወንጀለኛ ነች፡፡ የጌታዋን ክልክላ በማክበር ከሶላት ብትቆጠብ ግን አጅር ታገኝበታለች። ۞عن…
ሀይድ ላይ ላለች ሴት የተከለከሉ ጉዳዮዎች
➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰

  ❝ ክፍል  ⓵⓪ ❞
┖━━━━━┚

          ➁ ⊱ፆም፦⊰


⭞ሀይድ ላይ ያለች ሴት መጾም አይፈቀድላትም። ብትጾምም ጾሟ ተቀባይነት የለውም፡፡ እንዳውም የአላህን ክልከላ በመተላለፏ ወንጀለኛ ትሆናለች።

۞عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه  أن النبي صلى الله عليه وسلام  قال..،، أليس ؼذا حا؜ت لم تصل ولم تصم ?? فذالك نفصان دينها .عواو البخاري "

⭞በሀይድ ምክንያት ያለፏትን የጾም ቀናቶች ቀዷእ የማውጣት ግዴታ አለባት፡፡

۞قالت ؚا،ش؊ رضي الله عنها: كان  يصيبنا ذالك فنؤمر بقضاء الصوم ولا نؤمر بقضاء الصلاة . متفق عليه

⭞በረመዳን ጾም ላይ ሆና ጸሀይ ከመጥለቋ ከደቂቃም በፊት ቢሆን የሀይድ ደም ያጋጠማት ሴት ያንን ቀን ቀዷእ የማውጣት ግዴታ አለባት፡፡ አንድ ደቂቃ ሲቀረው ስለሆነ ሀይድ ያጋጠመኝ ጾሜ አይፈርስም የሚል ስሌት ተቀባይነት የለውም፡፡

⭞በረመዳን ቀን ላይ የጸዳች ሴት ሀይድ ካቆመበት በኋላ ያለውን የቀኑን ክፍለ ጊዜ ከምግብ፣ መጠጥና መሰል ጾመኛን ከሚያስፈጥሩ ነገራቶች ሁሉ መቆጠብ አለባት የሚል እይታ ያላቸው ምሁራኖች ቢኖሩም ተቀባይነት ያለው መከራከሪያ ሃሳብ የላቸውም፡፡ በረመዳን ላይ ሴቶች ወይ ጾመኞች ወይም አፍጣሪዎች ናቸው።


⭞ በሁለቱ መካከል የሚገኝ ከፊል ጾመኛ የሚባል ነገር የለም። ስለዚህ በጧቱ ክፍለ ጊዜ በሀይድ ላይ የሆነች ሴት በሰአቱ ክፍለ ጊዜ ብትጸዳ ምግብም መጠጥም...መጠቀም ትችላለች፡፡

⭞ከጸዳች በኋላ የረመዳንን የቀኑን ክፍለ ጊዜ የማክበር ግዴታ አለባት የሚል መከራከሪያ አሳማኝ አይደለም፡፡ ራስን በመጥፎ ላለማስጠርጠር፣ ሌሎችን ላለማደፋፈር ከማሰብ የተነሳ ከሰዎች እይታ ራቅ ብላ መብላትና መጠጣቷ ግን ተገቢ ነው፡፡

⃝ قال ابن عثينين رحمه الله : والقاعدة على هذا القول الرجح ، أن من أفطر في رمضان لعذر يبح الفطر ، ثم زال ذلك العذر أثناء النهار لم يلزمه الإمساك بقية اليوم ، فتاوى الصيام

⭞ከፈጅር በፊት የጸዳች ሴት ከሀይድ ባትታጠብም እንኳጾም መያዝ ትችላለች፡፡መጾምም አለባት።ይህየአብዛኛዎቹ ምሁራኖች ሃሳብ ነው። ጾም ለመጾም የሀይዱ መቋረጥ እንጅ መታጠቡ እንደ ቅድመ ሁኔታ አይወሰድም፡፡

«ኢንሻ አላህ ይቀጥላል๏๏๏๏๏๏๏✍️

   •━━━ ✽ • ✽ ━━━•
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
✅ መልካም ባል የአባት ምትክ ነው።

📍قال عامر بن الظَّرب: [ الزوج الصالح أبٌ بعد أبٍ ]
«መልካም ባል ከአባት በኋላ ሌላ አባት ነው።»

(طبائع النساء: 27)
ቁጥብ እህቶቼን አይመለከትም።

➨«ተይ አላህን ፍሪ»
-----------------------
የምታቃቅሩ ባለ ትዳሮችን፡
ያፈራረቃችሁ ወንድማማቾችን፡
ስንቱን ያጣላችሁ ህፃናት ወጣቱን፡
ስንት ያሰደዳችሁ አፍርሳችሁ ቤቱን፡
ሜዳ ላይ ጥላችሁ ሳትከፍሉት ግምቱን፡
---------------------------
የሸይጧን አገልጋይ ቀጣፊ ሸረኞች፡
ጠቃሚ መሳይ ጎጂ ሴረኛ ምቀኞች፡
ነገ ሞት አለና ተው ነገረኞች!!!!!
---------------------------
በየሚዲያው ላይ ህፀፅ የምትልኩ፡
መረጃ ሲሏችሁ ምታፈተልኩ፡
በተደጋጋሚ የምትሳሳቱ፡
ይመች ይሆን እንደ ጀሀነብ እሳቱ?

--------------------------
ወሬ ከማራገብ ከቆላ እስከ ደጋ!?
ባንች ብሷልና የምላስ አደጋ፡
እባካችሁ እስኪ ትንሽ ተረጋጉ፡
በትንሾች ምላስ ተነሱ ደጋጉ፡
-------------------------
ቅጥፈትን ዘወትር ምታስተናግዱ፡
ከልባችሁ ተንኮል የማታሶግዱ፡
ነገር ለማፈንፈን የምትሰደዱ፡
ለጥፋት ለክፋት ምታጎበድዱ፡
--------------------------!
ነገር ወደ አገር-ቤት ኢንቨስት ያረጋችሁ፡
ስለ ሰወች ማውራት የሆነ ስራችሁ፡
የምላስ አለቃ ሴቶች እባካችሁ፡
አደበኛ እህቶች አለቀሱባችሁ፡
በጣም ረዘመ ከፋ ምላሳችሁ፡
ስንቱ ተሳቀቀ በመጥፎ ስራችሁ፡
ከነገረኝነት ሴቶች እባካችሁ...!?
-----------------------------
በናንተ ምክንያት ስንት ቤት ፈረሰ፡
በስንቱ ወዳጆች ስንት ፀብ ነገሰ፡
ስንቱ ተበተነ ስንቱ ተራራቀ፡
ስንቱ ተለያየ እየተሳቀቀ፡
ትላንት ተዋደው ስንት ጓደኛሞች፡
በነገር ተጣሉ ስንት እህት ወንድሞች፡
ነገር በማራገብ ስንት ግፍ ሰራችሁ፡
የሸይጧን ተልኮ እያስፈፀማችሁ፡
በአሏህ ይሁንብኝ ስንቱን ለያያችሁ፡
ተመከሩ ቢልም ሁሉም እያያችሁ፡
ስራ አድርጋችሁት ነገር ሱስ ሆኗችሁ፡
ምን ብትመከሩ ተግሳፅ እምቢ አላችሁ!?
ኸረ አሏህን ፍሩ ወላሒ እባካችሁ!!
------------------------------
በጀርባችሁ ተንኮል የምታነግቡ፡
ጧት ማታ ውሸትን የምታራግቡ፡
በትዳር መካከል ጥል የምታስገቡ፡
ማር አስመስላችሁ መርዝ የምትመግቡ፡
በወንድምሽ ክፉ የምትናገሪ፡
በየዋህ እህትሽ ቁማር የምትሰሪ፡
ማዕድን ይመስል ሴራ እምትቆፍሪ፡
የሚዲያ እህቴ ተይ አሏህን ፍሪ፡
----------------------------
በኑረዲን አል አረብ
--------------------------
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi
"ማንበብ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ ብቻ ሳይሆን የህይወት ጎዳና ነው።"


=
ዛሬ ለላጤዎች ድምፅ ልሁናቸው ብዬ ነው።

በሉ ማንበብ ብቻ ሳይሆን ወደ ተግባርም ቀይሩት። በዚህ ዘመን የትዳር ጉዳይ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ስለዚህ ከምንም በላይ በዱአ በርቱ። ባይሆን ዱአ ስታደርጉ ሚስት ስጠኝ ብቻ ሳይሆን #ሷሊህ የሆነች ደግ ሚስት ስጠኝ በሉ። ያለበለዛ ሚስት ሊሰጥህ ይችላል። ነገር ግን ሚስጥርህን የማትጠብቅ፣ በአደባባይ የምታዋርድህ፣ ከሌሎች ጋር ሆና የምታማህ፣ ሁሌም በመጥፎ የምታነሳህ፣ ክፋትህ የምትመኝ፣ ስትወጣም ስትገባ የምትነዘንዝህ፣ ጨጓራህ የምትልጥ፣ መቼ ይሁን ከሷ የምገላገለው የምታስብልህ፣ ላጤነትህ የምታስመኝህና የዱንያ ስቃይ በአይነቱ የምታሳይህ ሚስት ሊሰጥህ ይችላል። ምክንያቱም እሷም ሚስት ናትና። ስለዚህ ደግ ሷሊህ መልካም ሚስት የምትለዋ በደምብ አስምሩባት።

ለሴቶችም ቢሆን በተመሳሳይ መልኩ ነው።
ሷሊህ/ደግ ወንድ ከመጣልሺ አግቢ የትም ይሁን ሀገር ጎሳ አትይ ሱንይ የተዉሂድ ጀግና ብቻ ይሁን ። ከወደደሺ ሺር አድርጎ ያኖርሻል ከጠላሺም በሰላም ይመልስሻል አይጎዳሺም።

#ከደጋጎች መንደር
~
የብዙዎች እህቶች ችግር....!?

ስለምታገቢዉ ወንድ ምንነቱ ከመግባትሺ በፊት እንጅ ማጣራት ወስነሺ ከገባሺ በኋላ ስለሱ አትፈላፈሊ አሁን ያለበት ሁኔታ ብቻ ያዢ እንጅ እየተፈላፈልሺ ራስሽን አትረብሺ ቤትሺ አታፍርሺ !! ሰዉ አሁን ያለበት እንጅ ባለፈ ሂወቱ አይመዘንም እሺ።

=
t.me/https_Asselefya1