💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
~አናልፋቸውም ብለን ያሰብናቸው ስንትና ስንት ችግሮች አልፈዋል። ስንት መከራዎች አልፈው እንዳልተፈጠሩ አድርገን ረስተናቸዋል። በሽታ፣ ሐዘን፣ ኪሣራ፣ የልብ ስብራት፣ መለያየት፣ መከራ ...ባጋጠመን ቁጥር ይህን የቁርአን አንቀጽ እናስታዉስ።
📜﴿ سيجعل الله بعد عسر يسرا﴾
አላህም ከችግር በኋላ እፎይታን ያመጣል።
ባሮቹ ነን።በችግር ዉስጥ አይተወንም።አብሽሩ!
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
አሁን ላይ ያለህበትን ሁኔታ ተመልከት። ለሞትና ለቀብር የሚሆን መልካም ሁኔታ ላይ ከሆንክ በዛው ቀጥል። ለዚህ የማይሆንና መጥፎ ሁኔታ ላይ ካለህ ወደ ጌታህ ተመለስ። ሁኔታህ በማስተካከል ወደ መልካም ተመለስ።
በአንደዬ ስለተጠየቅሺ እሺ አትበይ አስቢበት በደንብ ቶሎ እጅ አትስጪ እ! በሀገራችንኮ መግደርደር የሚባለዉ ነገር አለኮ እ አሁን ደግሞ የድን ተማሪ ነሺ አስቢበት ነገሩ ቶሎ እጅ አትስጪ እሺ።ታዋቂ ሸይኽ ኡስታዝ ቢሆንም እጅ አትስጪ ጀርባዉ ሳታጣሪ እሺ !! ብዙ እህቶች አንደ ተተጠየቁ ሳያጣሩ ሳያስቡበት እሺ ይሉና ከዛ ዋጋቸዉ ይከፍላሉ እ?! አይዞሺ ለአንቺ ከተፃፈ የትም አይሄድ እና ቀስ ኮራ ቀብረር ብለሺ ሰበቡ አድርሺ እንጅ በአንደዬ እሺ አትበይ እሺ !!

~
𝐓𝐞 «t.me/https_Asselefya1
አንተም እሺ ስላለችህ ጀርባዋ ሳታጣራ ቶሎ አትግባ በኋላ ወይኔ ወይኔ ሰራችልኝ አይጠቅምህም ...በደንብ አጣራ ሰዉ እኳን የትዳር አጋር ሀገር ለመቀየርኳ ብዙ ይጠይቃል ስለ ሀገሩ ሁኔታ ሙቀት ወይስ ብርድ ወይስ........! እና እፊትህ ስላገኘሀት በአንደዬ ጥያቄህ ስለተቀበለችህ ምንነቷ ሳታጣራ ዘዉ አትበል እሺ ..!

=
𝐓𝐞« t.me/https_Asselefya1
📍አንድ ሚስት ማስተዳደር አቅቶህ
ሚስትህን ለሾል በሀረብ ሀገር  ልከህ ያለ መህረም  እያንከራተትክ  አንዳንድ ጊዜ ደዩስም አትሁኑ  ነቃ በሉ  ሚስትህ ካንተ ተለይታ ሀረብ ሀገር መጥታ ኑሮን ለመቀየር ብላ   እሰዉ ቤት  እየተጋፋች   እንደምትሰራ ጠፍቶህ አይደለም
ሾለ አራት ሚስት ስታወራ አታፍርም  ቢላሂ ?

የሚገርመዉኮ እንደዉ ሂደሽ ስሪ እኔ እዚህ እንደፈለኩ ልዝለል የሚልጂ ከእኔ አትለይም ሸሪአችንም እርቀሽ ያለመህረም እንድትሄጂ አይፈቅድም እዚህ አብረን እየሰራን እንቀየራለን ሂዎታችንን አላህ በሚዎደዉና በሚፈልገዉ መልኩ እንመራለን የሚል የለም ኢላ መረሂመ ረቢ ::
ታዲያ ይሄ አንዷንኳ በቅጡ ያልያዘ እንደት አራት ያስተዳድራል ተብሎ ይታሰባል ህእ

አንድ ሚስት ራሱ አይገባህም ነበር
መፆም ነዉ ያለብህጂ  ዎንድሜ :::

=

https://t.me/asselfya
እዉቀት ብርሀነዉ ጀህልና ጨለማ
ኸይር ስራን ሁሉ በከንቱ ሚያገማ
አጥብቀን እንያዝ  የተዉሂዱን ማማ
ከእዉቀት ርቀን እንዳንሆን ጠማማ
ጠንክረን እንማር ይሄን የአላህ ኒዕማ
።

~

t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
'ትልቁ ጦርነት በልብ እና በአዕምሮ ያለ ጥያቄና መልስ ነዉ '' አዕምሮ  መተዉ ሲፈልግ  ልብ እንቢ ብሎ መናፈቅ ይጀምራል......!

~
መሆን ያለበት እንጅ መሆን
የሌለበት ሆኖ አያዉቅም !

~
Audio
﴿ أَمَّن یُجِیبُ ٱلۡمُضۡطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَیَكۡشِفُ ٱلسُّوۤءَ وَیَجۡعَلُكُمۡ خُلَفَاۤءَ ٱلۡأَرۡضِۗ أَءِلَـٰهࣱ مَّعَ ٱللَّهِۚ قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ ﴾ [النمل : ٦٢]

ከቁርአን ጋር እንኑር ...!

t.me/https_Asselefya1
▪️قَالَ الشَّيْخُ ابْنُ عُثَيْمِـيْنَ رَحِمَهُ اللّهُ

آيَةٌ وَاحِدَةٌ تَقْرَؤُهَا تَحْمِيكَ وَلَا يَزَالُ عَلَيْكَ مِنَ اللَّهِ حَافِظٌ لَوِ اسْتَأْجَرْتَ أَكْبَرَ الْحُرَّاسِ وَأَكْثَرَ الْحُرَّاسِ عَلَىٰ أَنْ يَقُوكَ مِنْ الشَّيْطَانِ  مَا اسْتَطَاعُوا ..

لَكِنَّ آيَةَ الْكُرْسِيِّ إِذَا قَرَأْتَهَا فِي لَيْلَةٍ مُؤْمِنًا بِمَا جَاءَتْ بِهِ السُّنَّةُ فَإِنَّهَا سَتَحْمِيك .


📓 أَحْكَامُ الْقُرْآنِ ٢/٤٣٧ ]

🍃~
የምትፈራዉን ነገር ደፍረህ ማድረግ
ካልቻልክ ፍርሃት ህይወትህ ይወርሰዋል።

~

t.me/https_Asselefya1
መባልን ሳይሆን ሆኖ መገኘትን ፍሪ !

=
منقول
t.me/https_Asselefya1
አንድ ዛፍ  ሲወድቅ ሁሉም ድምጹን ይሰሙታል፣ ጫካዉ  የሞላዉ ዛፍ  ሲያድግ ግን  ማንም አይሰማዉም  ብዙ ሰዎች የሚመለከቱት  እድገትህን ሳይሆን  ዉድቀትህን በመሆኑ ላለመዉደቅ ጥረት አድርግ።

~
                  t.me/https_Asselefya1
09-العبودية - لشيخ الإسلام ابن تيمية
ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ሸይኽ ኣደም
አዲስ ተከታታይ ትምህርት


📚 العبودية لشيخ الإسلام ابن تيمية

➮ ክፍል 09


ፉሪ አቡበክር አስ-ሲዲቅ መስጂድ

🎙በሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም

𝐓𝐞«t.me/SheikhMuhammedZainAdam
የዓላማ ሰዉ ከሆንሺ ትኩረትሺ ከአላማሺ ጋር ይሁን !

~
ለይላችሁ ያማረ ይሁን ሰላም እደሩልኝ

~
«ዉብ የኢስላም ወጣት ...!!»
•━━━ ✽ • ✽ ━━━•

የተሽቀረቀረች
በጌታዋ ትእዛዝ ታንፃ ያደገች
በተዉሂድ ቀጥ ብላ ሀያዕን የለበሰች
ዉብ አይኖቿን ሰብራ በሂጃብ ያጌጠች
ይህች ናት እህቴ  በእዉቀት ያበበ
ች።

𝐓𝐞⇘ t.me/Ibnu_Teymya_Ye_Ewket_Maed
ወንድ ልጂ ከምንም በላይ በችግሩ ግዜ ከጎኑ የምትቆም ሴት እጂጉን አብዝቶ ይወዳል!!

🎈
ኡኽታ እኔና አንቺስ በችግሩም በደስታውም ጊዜ አብረነው ነን❓

https://t.me/SileTidarEnmekaker
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
እህቴ ⓼ ➭➭➭➭ ⇘የጀነት ሰዎች ነፍሳቸዉ ከፍጥረቱ ዉዴታ ተሳንፋ ወደ ፍጥረቱ ፈጣሪ የተጠናከረች ናት። ጌታቸዉ ከንብረታቸዉ፣ ከቤተሰባቸዉ፣ ከነፍሳቸዉ በላይ እነሱ ዘንድ ተወዳጅ ነዉ። ⇘ምናልባትም በሌሊት ተነስተዉ ለሱ አንሾካሽከዋል፣ ቀንም በሱ ፍራቻ አንብተዋል፣ ዐይናቸዉ እሱ ማየትን ናፍቀዋል፣ ልባቸዉ በሱ ዉዴታ ረፍት አግኝተዋል። ⇘በዱንያ ላይ ልባቸዉ እሱን ማየትን ናፈቀችና አላህም በዚያኛዉ…
እህቴ ⓽
➭➭➭➭

⇛ዛሬ የእዝነትና የፍቅር የአታክልት ስፍራ በሆነዉ (በአቡ ደህዳህ) የአታክልት ስፍራ ዉስጥ ቆይታ እናረጋለን። ያቺ የአታክልት ስፍራ ልብን በሀሴት ምትሞላ፣ ደስታ የምትሰጥ፣ ሰላማዊ አየር ያላት ዉብ የአታክልት ስፍራ ናት። ያየዉን ሰዉ ድንገት ሳያስተዉል ‛ሱብሀነላህ!’ እንዲል ታስገድዳለች። የመዲና ሰዎች አዉርተዉላት የማያበቁ እጅግ ዉብና ምርጥ የአታክልት ስፍራ ነበር።

⇛ከዕለታት በአንዱ ቀን የምድር ሰዎችን እንዳስገረመዉ ሁሉ የሰማይ መልዕክተኞችን አጀብ ማሰኘት የሚችል የሚገርም ክስተት ተከሰተ። ንፁህ ዐይኖችን በእንባ ያጠበ፣ እዚያ የነበሩትን ብቻ ሳይሆን ታሪካቸዉን የሰማዉን ሰዉ በእንባ ያራጨ ገራሚ ክስተት ተከሰተ።

⇛ክስትቱ ወዲህ ነዉ.. አንድ ቀን (አቡ ደህዳህ) በነቢያችን አጠገብ ሲያልፍ የአንድን ታዳጊ ልጅ ለቅሶ ይሰማል። ልጁ የቲም መሆኑን ሲያዉቅ አዘነለትና ቆሞ የልጁን ጉዳይ መስማት ፈለገ። ልጁም ሀዘን በጎዳዉ አንደበት እንባዉ እየቀደመዉ ረሱሉን እንዲህ አላቸዉ..

«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! በአታክልት ስፍራዬ ዙሪያ ግንብ እየሰራሁ እያለ (ግንዱ) የጎረቤቴን አንዲት የተምር ዛፍን ቆረጠበት። እንዲተዉልኝ ወይም እንዲሸጥልኝ ጠየኩት። እሱ ግን እምቢ አለ።»

⇛ረሱሉም (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰሀቦችን ያን ጎረቤቱን እንዲጠሩት አዘዙትና መጣ። ረሱሉም ልጁ የቲም ስለሆነ እንዲሰጠዉ ሌላዉ ቢቀር እንዲሸጥለት ጠየቁት። እሱ ግን እንደማያረገዉ ተናገረ።

⇛ረሱሉም በጣም የሚገርምን ንግድ አመላከቱት.. «ሽጥለት! ለአንተ ደግሞ በምትኩ መቶ የተምር ግንዶች ጀነት ዉስጥ አሉልህ!» አሉት። (ዐዉ ከማ ቃለ)

⇛ሁሉም ሰሀባ በድንጋጤ ክዉ አሉ። ይሄን የመሰለ ግብይት ወደ ቀረበለት ሰዉ ጆሮዎች ዞሩ። እንደሚቀበል ማንም ሸክ አልነበረዉም።

⇛እሱ ግን እምቢ አለ።የቲሙም ልጅ እንባ በእንባ ሆነ። የሰሀቦች ዐይንም ወደ ሰዉዬዉ በግርምት ማየት ጀመሩ። እሱ ግን ምንም አቋሙን አልቀየረም ነበር።

⇛ይሄኔ ነዉ (የአቡ ደህዳህ) ታሪክ ሚጀምረዉ። አቡ ደህዳህ ይሄንን ምልልስ ከሰማ ብኃላ ነፍሱ ወደ ጀነት ናፈቀች። ረሱልንም እንዲህ ሲል ጠየቀ..

«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! የአታክልት ስፍራዬ ሽጬ ለልጁ የተምር ግንዱን ባስመልስለት በጀነት ዉስጥ የተምር ዛፍ አገኛለሁ?»

⇛ረሱሉም ደስታ ፊታቸዉን አፈካዉ። «አዎ!» አሉት። አቡ ደህዳህም ወደ ሰዉዬዉ ዞረና «የአታክልት ስፍራዬን ታዉቀዋለህ?!» አለዉ። ሰዉዬዉም «አዎ!» አለ።

⇛አቡ ደህዳህም «የተምር ግንድህን በአታክልት ስፍራዬ ሽጥልኝ!» አለዉ። ተስማማ ንግዱ ተፈፀመ። (ሱብሀነላህ!)

⇛የልቡ ምት የእግሩን ፍጥነቶች እየቀደመ ወደ አታክልት ስፍራዉ ሮጠ። የመዲና ቤቶች በመላለሱት በተቆራረጠ ድምፅ..
«ኡመ ደህዳህ!..
» ብሎ ሚስቱን ተጣራ።

«ከአታክልት ስፍራዉ ዉጪ! እሱ ለአላህ!» አላት። የደህዳህ እናትም ወዲያዉ ከግዛቷ ተነሳች። እጆቿን ከፍራፍሬዎቹ ላይ አነሳች። በልጆቿ እጅ ላይ የቀሩትን ፍራፍሬ ሳይቀር ቀማቻቸዉና አማና ነዉና አስቀመጠችዉ። የባሏን ትዕዛዝ ከመፈፀሟ በፊት የአላህን ትዕዛዝ «ለበይክ!» አለች። ምንም ሳትጠይቅ፣ ምንም ሳታጣራ በንፁህ ልብ ዉሳኔዉን ተቀበለች። አንድ ነገር ብቻ ነዉ ምታቀዉ። «ለአላህ!» መሆኑን።

⇛ከዚያም ወደ ባሏ ዞረችና.. «ትርፋማ ንግድ ነዉ አቡ ደህዳህ! ትርፋማ ንግድ ነዉ።» አለች።

እቺ እህትሽም የጀነትን ፀጋ በማሠብ ከዱንያዊዉ የአታክልት ስፍራ ወጣች።

ምን አይነት ሚገራርሙ ባልና ሚስት ናቸዉ?!

⇛ልቧ በአታክልት ስፍራዉ ላይ የተንጠለጠለ ቢሆንም ያለ አንዳች ኪላፍና ሙሉ በሆነ ዉዴታ የባሏን ትዕዛዝ አከበረች። ወደደች።

ዛሬ እኔ ምንም አላወራም። ታሪኩ ብቻዉን ለሚገሰፁት በቂ ትምህርት ነዉ።

⇛እህቴ! የፈለገዉን ያህል ፈታኝ ቢሆንም ከዱንያ የአታክልት ስፍራሽ ዉጪና ለአላህ መንገድ ደስ ከሚልሽ ነገር ላይ ለግሺ! ከንብረትሽ፣ ከወቅትሽ፣ ከእድሜሽ ለዚህ ዲን መፅዉቺ!! የአላህን ዉዴታና የጀነቱን የአታክልት ስፍራ በማሰብ በደስታ ካለሽ ላይ ስጪ!!

ጆይን ይበሉ ⇣⇣⇘⇣⇣
http://t.me/https_Asselefya1