💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
✍️የቱ ጋር ነዉ ክብርሽ?!
➬➫➬➫➬➫➬➫➬

የወጣሽበትን አላማ ዘንግተሽ፣
የልፈት እንግልት ዉጤቱ ሳይገባሽ፣
በሚድያዉ አልም አብደሽ እየሰከርሽ፣
ያን የወንድ አልጫ ሂደሽ እያባበልሽ፣
ተግባሩ ሳታይ ወይ አንች ሳይገባሽ፣
ለጥሎሽ አታስብ እኔ እጥላለሁ አልሽ፣?!

በስደቱ አለም ላይ እዛዉ እያገባሽ፣
ዘወር በይ እያለ መልሶ ሲፈታሽ፣
ክብሬን አጣሁ አትበይ ክብርሽን እያጣሽ፣
ያ ሜስኬን አባትሽ ተይ ልጄ እያለሽ፣
እኔ ከወደድኩት ምን አገባዉ እያልሽ፣

ተግባሩን ሳታይ በድምፁ እየሰከርሽ፣
ክብሬን አጣሁ አትበይ ክብርሽን እያጣሽ፣
መቶ ሲጠይቅሽ ያንች ክብር ሁኖ፣
በቁጥብነትሽ በራሱ ተማምኖ፣
አሏህ ሲፈቅድ ብለሽ ከዘጋሽ ከበርሽ፣
ያ ነዉ ያንች ክብር የሴትነት ወግሽ፣

  
«ግን ካልሆነ እህቴ ..!!»

የለለሽን ነገር ጨምረሽ ጨማምርሽ፣
እሱን ለማማለል ድምፅ ከቀያየርሽ፣
እመኝኝ እህቴ አንች ነሽ የከሰርሽ፣
ያልሆንሽዉን ሁነሽ ለምን ትቀርቢያለሽ፣
አንችዉ በር ከፍተሽ ይኸ እኮ ትያለሽ፣

ድያ ላይ ማግባት ብዙ ሁኖ ዉሸት
ተግባሩ ሳይታይ ቡሓላ መፀፀት


        
«እናማ ልምከርሽ..!!»

የወጣሽበትን አላማ አስበሽ፣
ላንች እሚጨነቁ ቤተሰብን ናፍቀሽ፣
የተማርሽዉን ድን ተግባር ላይ አዉለሽ፣
የተከበርሽ እንስት ቁጥብ እቁ ሁነሽ፣

ሀገር ስትገቢ ክብርሽን ጠብቀሽ፣
ላንች የታዘዘ ጀግና ታገኛለሽ፣
ወይም ከጠበቀ በተግባር ታያልሽ፣


      
«ካልሆነ ግናማ...!!»

በስደት አለም ላይ ፈጥነሽ እያገባሽ፣
ሳምንት እየቆየ መልሶ ከፈታሽ፣
ክብሬን አጣሁ አትበይ ክብርሽን እያጣሽ፣


✍️ሶላሁድን አቡ ዑበይዳህ

𝐓𝐞 « t.me/selahudin_Islamic_knowlages
SadatKemal Abu Meryem
Video
yes !

እማማ ኢክራም አላህ ይህ ወንድማችን ሰበብ አድርጎ ወደ ድንሽ እንደምትመለሽ ተስፍ አደርጋለሁ ¡ በጣም ነበር ያሳዘንሺኝ የምሰሪያቸዉ ስራዎችሽ.....¡

ኢላሂ ሌሎችም ብዙ መንገድህ የጣሱ ባሮችህ አሉ አንተ መልሳቸዉ .....!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ኡስታዝ ሳዳት ከማል ይቅር ባይ ነህና አላህ ይቅር ይበልህ!

አህሉ ሱናዎች ከሚታወቁበት ገፀ-ባህሪዎች መካከል «ይቅር» ባይነታቸው አንዱ ነው።

|•| የእይታህ አድማስ በሰፋ ቁጥር…ከበደል ትርቃለህ፣ ለበደለህ ምክንያት ትፈልግለታለህ፣ ባንተ ላይ ላጠፋብህ ጀሊሉ ያዝንለት ዘንድ ዱዓ ታደርግለታለህ፣ ሥምህን በክፉ ያነሳን የአላህን ይቅርታ ትለምንለታለህ። ይህ ነው የ ሱና ሰዎች መገለጫቸው!

«ይቅርታ የጠየቀህን ሰው በፈገግታ ተቀበለው»
ይሉ ነበር አህነፍ ቢን ቀይስ―
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
የመስጂድ ውስጥ ልመና
~
ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
ﺃﺻﻞ اﻟﺴﺆاﻝ ﻣﺤﺮﻡ ﻓﻲ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﻭﺧﺎﺭﺝ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﺇﻻ ﻟﻀﺮﻭﺭﺓ ، ﻓﺈﻥ ﻛﺎﻧﺖ ﺿﺮﻭﺭﺓ ﻭﺳﺄﻝ ﻓﻲ اﻟﻤﺴﺠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﺆﺫ ﺃﺣﺪاً ﻛﺘﺨﻄﻴﻪ ﺭﻗﺎﺏ اﻟﻨﺎﺱ ، ﻭﻟﻢ ﻳﻜﺬﺏ ﻓﻴﻤﺎ ﻳﺮﻭﻳﻪ ﻭﻳﺬﻛﺮ ﻣﻦ ﺣﺎﻟﻪ ﻭﻟﻢ ﻳﺠﻬﺮ ﺟﻬﺮاً ﻳﻀﺮ اﻟﻨﺎﺱ ﻣﺜﻞ ﺃﻥ ﻳﺴﺄﻝ ﻭاﻟﺨﻄﻴﺐ ﻳﺨﻄﺐ ، ﺃﻭ ﻭﻫﻢ ﻳﺴﻤﻌﻮﻥ ﻋﻠﻤﺎً ﻳﺸﻐﻠﻬﻢ ﺑﻪ ﻭﻧﺤﻮ ﺫﻟﻚ ﺟﺎﺯ .
"ልመና በመሰረቱ በመስጂድም ውስጥ ይሁን ከመስጂድ ውጭ ለአስገዳጅ ሁኔታ ካልሆነ በስተቀር አይፈቀድም። አስገዳጅ ሁኔታ ኖሮ መስጂድ ውስጥ ቢለምን
- ማንንም ካላስቸገረ - የሰዎችን ጫንቃዎች መረማመድን ይመስል፣
- በሚያወራው ላይ ካልዋሸ ፣ ማለትም ያለበትን ሁኔታ ብቻ ከጠቀሰ፣
- ሰዎችን በሚጎዳ ጩኸት ካልጮኸ - ለምሳሌ ኸጢቡ ኹጥባ ላይ እያለ መለመንን ይመስል፣ ወይም ዒልም እያደመጡ ካልረበሻቸው ፣ ወዘተ
(መለመን) ይቻላል።"
[ጊዛኡል አልባብ፣ አሰፋሪኒይ፡ 2/267]

Ibnu Munewor

=
▸ የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

▸ የዋትሳፕ ቻናል፦
https://whatsapp.com/channel/0029VaA3X1e5kg7BlsJboa2M

* ፌስቡክ
https://www.facebook.com/Ibnu.Munewor?mibextid=ZbWKwL
አል ካፊያ ሸሪዓዊ ሩቃ ቤት

ሸሪዓውንና ሱናን በጠበቀ መልኩ የቁርአን ህክምና የሚሰጥበት አል ካፊያ ሩቃ ቤት በመምጣት በአሏህ ፍቃድ ሰበብ እንሆነዎታለን።

አድራሻ  ኮ/ቻ ቀበሌ 08 ድልድዩን ተሻግሮ ሁለተኛው ቅያስ ገባ ብሎ። ወይም ከሩሃማ መስጂድ በቀኝ በኩል ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር ➴➴➴
0960243692~ 0915508640

ለማንኛውም ጥያቄ➴➴➴
@abureyyis ~ @abureyyis

ቴሌግራም ግሩፕ ➘➘➘➘➘➘
https://t.me/al_kafia_ruqyeh_bet
https://t.me/al_kafia_ruqyeh_bet
የሱና ወንድምህን ክብሩን እወቅለት!!!

በአሏህ ዲን ላይ መዋደድ በተውሒድ በሱና መዋደድ በመንሓጅ መዋደድ ከዓርሺ ጥላ ስር ከሚሆኑ ሰዎች መካከል እንድንሆን የሚያደርግ ትልቅ ዒባዳ ነው።

ስለ ሱና ወንድምህ ክብር ምን ያክል ታውቃለህ ? እሱንስ ምን ያክል ሓቁን እየተወጣህ ነው ??

የሱና ወንድምህን ከቻልክ እገዘው ካልቻልክ ግን እባክህን እባክህን ጋሬጣ አትሁንበት ክፍተት ካየህበት በአቅምህ ያክል ክፍተቱን ሙላለት !! ።

እንኳን የሱና ወንድምህን አይደለም ለማንኛውንም ሰው ጋሬጣ መሆን አይፈቀድም ስህተት ላይ ካለ እረመው ቀስ ብለህ !!

ለሰው መልካም መሆን ትልቅ ደረጃ እንዳለው ሁላ ለሰው መጥፎ መሆን ምቀኛ መሆን ደግሞ ትልቅ ወንጀል ነው  !!

መቼም የሰው ልጅ ከስህተት አይፀዳምና በሱና ወንድምህ ላይ ስህተት ካገኘህበት ምከረው በአደባባይ ከማውጣቱ ይሁን  ከማውጣትህ በፊት!!

ከዝህ ውጭ ሳይጠሩ ሰርግ እንደሚሄዱ ሰዎች ሳይበላህ እያከክ የግል ሂወቱ ውስጥ እየገባህ ያለ ሙያህ አታቡካ ሊጡን ታበላሻለህና !!!

የሱና ወንድም ክብሩን ምን ያክል አውቀናል ግን ወገን  ?? የሱና ወንድም ሲያዝን በቻልከው ያክል ማገዝ እሱን ማበረታታት ሲገባህ እንዴት እንዴት ለሱ ጋሬጣ ትሆናለህ ? ?

ለሱና ወንድም ክብር ይኑረን የሱ ደስታ የኛም ደስታ ነው ፣ የሱ ትካዜ የኛም ትካዜ ነው ትክክለኛው ውዴታ ከሆነ ።

« الله في عون العبد ما کان العبد في عون أخیه »
ውዱ ነብያችንﷺ  ብለው ይሉናል ፦

" አሏህ አንድን ባሪያ እንዳገዘው ነው ይህ ባሪያ ወንድሙን ባገዘ ቁጥር "

የሱና ወንድምህን ማገዝ ችግሮቹን ተባብረህ መፍታትህ አሏህ ዘንድ ትልቅ ደረጃን ያስገኝልሀል ፤  በተጨማሪም ያላችሁ ውዴታም እንዲጨምር ያደርጋል ከዝህ በላይ ምን ፈለግክ ? !!

ከአርቴፊሻል ወንድምነት አሏህ ይጠብቀን በስ !!

ወንድምህ አብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

𝐓𝐞« t.me/abuUseyminabdurehman
ሱቅ በደረቴ

ቁርአን ,ኪታብ,ጂልባብ,ኒቃብ,የሶላት ጨርቆች ሽሮ ,በርበሬ,ቆሎ,በሶ,የተለያዩ የፀጉር ቅባቶች,ሌሎችም ተጨማሪ የፈለጉት ከሱቃችን መጠቀም ይችላሉ.........!!

አገልግሎት የምንሰጥባቸዉ ከተሞች
➘➚➘➚➘➚➘➚➘➘➚
➘➚➘➚

①) ጅዳ
②) መካ
③) መዲና
④) ሪያድ
⑤) ጣኢፍ
⑥) ጂዛን
⑦) ደማም ናቸው።


«ለበለጠ መረጃ ወደ ግሩፓችን ጎራ ይበሉ!»
   ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/suk_bederete123
https://t.me/suk_bederete123
በጥሩ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል
Daru tewhid
ባይተዋር የሆነው አርዕስት....?

ዛሬ እኮ ሰዎች በድፍረት የኛ ቋንቋ የጀነት ቋንቋ ነው ሚሉ ደፋሮቾ መጥተዋል

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ

        t.me/Darutewhide
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሁ ወበረካትሁ

እደናችሁ እኔ አልሀምዱሊላህ ጓደኛየን አፋልጉኚ
ስሟ ያስሚ ኡሙ ካሊድ ዱባይ ነበረች ሀገር ገብታለች ሀገሯ ጉራጌ ነዉ የኡስታዝ ሳዳት ዋትሳፕ ግሩብ  ቅድሚያ ለተዉሂድ የሚለዉ ኮድ 12 ላይ አድሚን ነበረች የምታዉቋት አፋልጉኚ!! ሀያት ኡሙ ማሒር እህትሽ ነኝ

@As_selefyaa1_bot
@As_selefyaa1_bot

እህት ያስሚ ሆይ ጓድሽ እየፈለገችሺ ነዉ መልእክቱ እንደደረሰሽ በቦት ብቅ በይ👆
🛑👉 ሚስጥር መጠበቅ የደጋጎችና የውድ የአላህ ባሮች ባህሪ ሲሆን የሰውን ሚስጥር ማውጣትና ለሌላ መንገር የሸረኞች ባህሪ ነው።

{حفظ الأسرار خلق الأبرار ، وإفشاؤها خلق اﻷشرار .﴾

📍ሚስጥርህ የማይጠብቅ ሰው አማና የለውምና ራቀው።

قال ابن بطال رحمه الله تعالى


▫️ኢብኑ በጣል አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል።

السر أمانة وحفظه واجب ، وذلك من أخلاق المؤمنين ، وقد روى عن أنس أنه قال : خدمت النبي عشر سنين ، فقال : احفظ سري تكن مؤمنًا.
👉ሚስጥር አማና ነው። መጠበቁ ግዴታ ነው። ይህም የሙእሚኖች ባህሪ ነው። ነብዩን አስር አመት ሀድሚያለሁ። "ሚስጥሬን ጠብቅ ሙእሚን ትሆናለህ" ብለውኛል የሚል ዘገባ ከአነስ ኢብኑ ማሊክ ተወርቷል።

📚شرح صحيح البخاري (9/64) :

☑️ አሁን ላይ የምናየውና የምንሰማው ግን በጣም የሚያሳዝንና ልብን የሚሰብር ነው። በሰላሙና በደህናው ጊዜ ቀርቦ ሚስጥርህና ጉዳይህ በሙሉ አጥቦ ይወስድና ልክ የተጣላህና ያኮረፈህ ቀን ሚስጥርህ አደባባይ ያወጣዋል። ግራ ጎንህን ተጠቅሞ ይጎዳሀል። አንዳንዱማ የሌለውም ጨማምሮ ያወራብሀል። አንዳንዱ ደግሞ ሚስጥር እንደነገርከው ወዲያው ከሌላ ያወራዋል። ለደቂቃ እንኳ አይታገስም። ምንም መቋጠሪያ የለውም። አትንገርብኝ ብሎ ይናገርብሀል። ሚስጥር ከማይጠብቅ ጓደኛም ሆነ የትዳር አጋር አላህ ይጠብቀን።

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ከድጡ ወደ ማጡ ይላል የሀገሬ ሰዉ።

በኢኽዋኖች ስንጠላ ስናወግዝ የነበረ ተግባር ዛሬ የሱና ወንድ ነኝ ሴት ነኝ የሚሉ ሲሰሩት ማየት እጂጉን ያሳፍራል።አላሁመ ሙስተአን......!!

=
ይህ ግሩፕ የአረብ ሀገርን ሴት ክብር ማስከበሪያ ግሩፕ ሳይሆን ‼️

ወንድና ሴቱን ባንድ አምገው(ቀላቅለው) እንካስላንቲያ በማለት  ፈሳድ እሚያሰራጩበት ግሩፕ ስልሆነ ሁላችሁም እዚህ ያላችሁ የሱና እህቶች አላህን ፈርታችሁ ውጡ ‼️

በአረብ ሀገር ያሉ እህቶችም ሆነ በአለም ላይ ያሉ ሙስሊም እህቶቻቸው ክብራቸው የሚከበረው መጀመሪያ ራሳቸውን ሲያከብሩ ነው። ራሴን አስከብራለሁ ተብሎ ከወንድ ጋር ተሰልፎ ማውራት ይህ ራስን ማስረከብ ነው ። ሰምታቸኋል‼️
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
ይህ ግሩፕ የአረብ ሀገርን ሴት ክብር ማስከበሪያ ግሩፕ ሳይሆን ‼️ ወንድና ሴቱን ባንድ አምገው(ቀላቅለው) እንካስላንቲያ በማለት  ፈሳድ እሚያሰራጩበት ግሩፕ ስልሆነ ሁላችሁም እዚህ ያላችሁ የሱና እህቶች አላህን ፈርታችሁ ውጡ ‼️ በአረብ ሀገር ያሉ እህቶችም ሆነ በአለም ላይ ያሉ ሙስሊም እህቶቻቸው ክብራቸው የሚከበረው መጀመሪያ ራሳቸውን ሲያከብሩ ነው። ራሴን አስከብራለሁ ተብሎ ከወንድ ጋር ተሰልፎ…
ሢጣሩ ሠምቸ  እያሉ ኑግቡ፣
ምክራቸውን ልቀስም ገባሁ ከግሩቡ፣
ጀግኖችንም አየሁ  የተሠበሰቡ፣
በሳል እህቶቸን ሱናን ያነገቡ፣

ደሥ አለኝ በሩቁ ርእሱን አንብቤ፣
እጠባበቅ ጀመር ተግሳፅን ተርቤ፣


ሰአቱ ደረሠ  ማስታወስ  ጀመሩ፣
በሴቶች ተመራ ወንዶች ተሠተሩ፣
እንቁ የተማሩት  ብዙወቹ አፈሩ፣
ግራ በመጋባት ጥያቄ አሠፈሩ፣
መልስ ሣያገኙ  ወጡ ተባረሩ፣


ቃላታቸው እሬት ወሬያቸው መራራ፣
ስራቸው አያምር  ከአደብ የጠራ፣
ውይይት በሚልሥም ካጂነብይጋራ፣
ትመላለሣለች  ሴት ልጅ በደበፈራ፣
ታይ ለምን ስትባል ድምፄ አይደለም አውራ፣
አውቃለሁ ባይ ሆነች ከሷጋ ማን ያውራ፣
ስርዓት የጣሠ  መሠረቱ ደራ፣
እኔን አሳቀቀይ የያዙት ፉከራ፣


የሡናዋ እህቴ የምልሽ አደራ፣
ፈጥነሽ ተለያቸው አያጋቡሽ ግራ፣
ሀሣብሽ ቢገለፅ እሮሮሽ ቢወራ፣
ያሣለፍሽው ችግር  ያገኘሽ መከራ፣
1.    2  .ብለው ቢጠቅሱ በተራ፣
ቢያሥቡ ቢያሠሉ ትርፍ ከኪሣራ፣
ትተሽ ገለል በይ ሚሥጥሩ እስኪጣራ፣

🤙ውይይት ከተባለ ቅዲሚያ  የሠወችን ሀሣብ ለመቀበል ፍቃደኛ ሁኖ መገኘት ግድ ይላል። በተለይ የሡና እህቶቻችን የሡና ወንድሞቻችን  ለሚናገሩን ንግግር የተለየ ቦታ ሠጥተን በጥሞና አዳምጠን   ለሀሣባቸው ምላሽ መሥጠት እዳለብን  ማሥተዋል ለሚችል ሠው የሚሠወር አይደለም።

👍ለየት ያደረገው ነገር ቢኖር   እኔም በጣም የደነቀኝ ነገር እደት የሡና እህት ወንድሞችን በዚህ መልኩ እናያቸዋለን  ለምን ጥቅር ብሎ አይቀርም  እዲህ አይነቱ ምክር  እህቶቸ   ከእነኝህ ኸይርን አጠብቁ  እዳውም ተማሪን እና አስተማሪን ሊለያዩበት የተሤረ ሴራ ይመሥላል። በብዙ ርዕስ ብዙ ጊዜ ተመክረናል  እዲህ አይነት ጉዲ አላየንም።


🤙በቦት ከደረሰኝ ምርጥ ግጥም በጥሞና አንብቧት!! እህታችን አህሰንቲ 👍


=
📍ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

«እውቀት ከበላጭ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱ ነው። በጣም የላቀና ከጥቅም በኩል እጅግ ተገዘፈ ኢባዳ ነው። ለዚህም ነው ሸይጧን ሰዎችን ከእውቀት በማገድ ላይ እጅግ ብርቱ የሆነው።»

📚فتاوى نور على الدرب / ج2 / ص12.

📍ኢብኑል ጀውዝይ "አላህ ይዘንለት" እንዲህ ብሏል።

«እወቅ! ኢብሊስ በሰዎች ላይ ከሚያለባብሳቸው ማለባበሶች ውስጥ አንዱና ዋናው፦ ሰዎችን ከእውቀት መንገድ መዝጋት ነው። ምክንያቱም እውቀት ብርሀን ነው። ይህንን የእውቀት ብርሀናቸው ካጠፋባቸው በኋላ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንደፈለገ "በቀላሉ" ይጥላቸዋል።»

📚تلبيس إبليس (1/289)

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
ይህ ግሩፕ የአረብ ሀገርን ሴት ክብር ማስከበሪያ ግሩፕ ሳይሆን ‼️ ወንድና ሴቱን ባንድ አምገው(ቀላቅለው) እንካስላንቲያ በማለት  ፈሳድ እሚያሰራጩበት ግሩፕ ስልሆነ ሁላችሁም እዚህ ያላችሁ የሱና እህቶች አላህን ፈርታችሁ ውጡ ‼️ በአረብ ሀገር ያሉ እህቶችም ሆነ በአለም ላይ ያሉ ሙስሊም እህቶቻቸው ክብራቸው የሚከበረው መጀመሪያ ራሳቸውን ሲያከብሩ ነው። ራሴን አስከብራለሁ ተብሎ ከወንድ ጋር ተሰልፎ…
አያዉቁኝም በሚል ስምና አካዉንት ቀይሮ አላስፈላጊ ድርጊት መፈፀም የትም አያደርስም ማንነት የታወቀ ቀን ዉርደት መከናነብ ነዉ። ስንት የተጎዱ እህቶች አሉ በየ ቤቱ ግን ነገራቸዉ ወደ አላህ አስጠግተዉ በአደብ የተቀመጡ! አላህ ይጠብቃቸዉ። አሁን ሳይሞቅ ፈላ የራስን ብሶት በስመ አረብ ሀገር ሴት ገብቶ ከወንድ ፊት እንካ ስላንቴ መግጠም ይሄ የሌለ ጅልነት ነዉ። አሁንም አልመሸም ከዚህ ተግባራችሁ ተመለሱ። ለእህቶች ታስቦ ከሆነ ብዙ ሴቶች ለብቻ ያለበት መድረክ አለ ኑ እናመቻቻለን እህቶች ምከሩ እንመከራለን አለዛ ግደታ ወንድ ፊት ታላወራሁ ያዙኝ ልቀቁኝ ወንዱን ና አዉራ በግድ በመድረክ ማለት ይሄ አጉል ግብዝነት ነዉ።አንድ የሱና ወንድም ገብቶ ተዉ ይሄ ነገር ሲልም እሱን መስደብና አላስፈላጊ መናገር በአደባባይ ይሄ የመጨረሻ ጋጠ_ወጥነት ነዉ። የትም አያደርሳችሁም።


=