💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
~አንዳንዶችን ምናለ ከአመታት በፊት አውቀናቸው በነበረ እያልን እየተመኘናቸው ነው።  ሌሎችን ደግሞ ምናለ ሳንተዋወቃቸው ቀርተን ቢሆን ኖሮ እንላለን።

وَبَعْضُ النَّاسِ صُحْبَتُهُمْ بَلَاءُ
وَدَاءٌ   مَا لَنَا   مِنْهُ   شِفَاءُ

وَبَعْضُهُمُ إِذَا مَا شِئْتَ شَاؤُوا
أُولَٰئِكَ   لِلْفُؤَادِ   هُمُ  الدَّوَاءُ
=t.me/AbuSufiyan_Albenan
~ከ አላህ በታች ሰበብ ሁነን የ እናቱን እንባ እንበስላት።

ያያችሁት ወይም መረጃ ያላችሁ ሰዎች ከዚህ በታች ባሉት ቁጥር በቀጥታ በመደወል አልያም በቴሌ ግራም መረጃውን ያድርሱን፦
📲 00966504773163
📱 00966578512108

{አላህ የቤተሰብን ችግር አያሳያችሁ}
Forwarded from Ů†ŮŽŮ€Ř­Ů’Ů€Ů†Ů أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے (لَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق)
ከፊሉ አሏህን ፈሪ አድርጎ ሊያይህ ይችላል፣ ሌላው ደግሞ ከዛ ውጭ አድርጎ ሊያስብህ ይችላል፣ ነገር ግን አንተ እራስህን እንዴት ነው የምታየው??

(بَلِ الْإِنْسَانُ عَلَىٰ نَفْسِهِ بَصِيرَةٌ)
" በእርግጥም ሰው በነፍሱ ላይ አስረጅ ነው ፡፡ (አካሎቹ ይመሰክሩበታል) ፡፡"
[ቂያመህ 14]

የአሞጋሾች ሙገሳ እንዳይሸንግልህ!።
የምቀኞች ትችትም እንዳይጎዳህ!።
t.me/abdu_rheman_aman
ፊታችሁ ሸፍናችሁ ግን ሌላዉ ሰዉነት ወጣጥራችሁ የምትሄዱ ሴቶች ግን በሰላም ነዉ?? ሴት ፊቷ ብቻ የሚፈትነዉ ያለዉ ማነዉ? እና ሙሉ ከለበሳችሁ ሙሉ ልበሱ ምንድነዉ ግማሽ ተላጭታ ግማሽ ተቀብታ የምትሆኑ ሆ!!

=
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«ጠቃሚ ኢስላማዊ ትምህርቶች»

© ይቀላቀሉ ሽር ያድርጉ ይጠቀማሉ!
↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣↷⇣⇣
t.me/selahudin_Islamic_knowlages
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝የሙናፊቆች ባህሪያት ❞ ➖〰➖〰➖〰➖ ÂŤ ክፍል  ⓻  Âť ↷በመጨረሻ ዘመን የሙናፊቆች መብዛት↶ ↬በመጨረሻ ዘመን ሙናፊቆች መሪ የሚሆኑበት፣መሀይሞች የሚያስተምሩበት፣አታላዮች የሚታመኑበት፣ታማኞች የሚካዱበት፣አኼራ በዱኒያ የሚሸትበትና የሚለወጥበት ዘመን ይሆናል። فال عمر الخطاب رضي الله عنه: يهدم اللإسلام ثلاث "  زلة عالم ፣ وجدال منافق بالقرآن፣  وأئمة…
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞
➖〰➖〰➖〰➖

«ክፍል  ⓼»

{የሙናፊቆች ልዩ ባህሪ}

☞ሙናፊቆች የማያዉቁትን ያወራሉ፣ሲናገሩ ይዋሻሉ፣ የተከለከሉትን ይተገብራሉ፣ያጠፍሉ ይጠፍሉ፣ በአላህ ላይ ያምፃሉ፣ሰይጣንን ይታዘዛሉ፣ነገር ይሰራሉ፣ሙስሊሙን  ያጣላሉ፣በዉሸት ይመሰክራሉ፣መጥፉ ቃል ይናገራሉ፣ሰዉ ያማሉ።

☛ሙናፊቆች ሙእሚን ጥላታቸዉ፣ካፊር ወዳጃቸዉ፣ ሰይጣን ኋላፊያቸዉ ነዉ።ሙናፊቆች ደረቅ ነዉ ልባቸዉ፣ቆሻሻ ነዉ ምላሳቸዉ፣ የተበላሸ ነዉ ሀሳባቸዉ ፣ዉርደት ነዉ ምስሳቸዉ፣እሳት ነዉ መመለሻቸዉ።

☞ሙናፊቆች ስንቱን የሙስሊም ሀገር አፈራረሱት?ስንቱ የሙስሊም ምሽግ አወደሙት? ስንቱ የእስልምና መለያ ከጠፉት?

☛ሙናፊቆች የአላህን ቅርበት አያዉቁም፣ከአላህ አያፍሩም፣ከመጥፉ ነገሮች አይከለከሉም፣መልካም ስራዎች በጥሩ (ንያ )ሀሳብ አይሰሩም፣ከጥፍታቸዉ አይታረሙም፣ባጠፉት ነገር ላይ አይፀፀቱም፣የአላህ ዉደታ አይፈልጉም፣ምንዳዉንምአይከጅሉም፣ለመጨረሻዉ ቀን አይዘጋጁም። ከእነዚህ እና ከእንደዚህ አይነት የሙናፊቆች ባህሪዎች አላህ ይጠብቀን።

«የሙናፊቆች ባህሪ በቁርአን ዉስጥ »

☛ሙናፊቆች በጣም ብዙና አሳፋ መጨረሻቸዉ  አስፈሪ  የሆኑ ባህሪዎች እንዷቸዉ  በቁርአን ዉስጥ ተጠቅሷል ።ስዉር የሆነዉን አላማቸዉ ተጠቁሟል። ድብቅ የሆነዉ ሚስጥራቸዉ ተጋልጧል። ሙስሊም ሳይሆኑ ሙስሊም መስለዉ የተሸፈኑበት  ሽፍን ተገልጧል፣ የአላህ ባሪዎች ከመናፊቆችና  ከስራቸዉ ይጠነቀቁ  ዘንድ በሰፊዉ ተብራርቷል።

☞ሙናፊቆች ሙስሊም መሳይ ከሀድዎች፣ጨዋ መሳይ መጥፎች፣ለጋሽ መሳይ ስስታሞች፣ነገርአመላላሽ እርኩሶች ፣ ምድርን አበላሽ ፍጡሮች፣ ወደ ሀይማኖት ሲጠሩ አላጋጭ ህዝቦች ናቸዉ።

☛ሙናፊቆች የእምነት ብርሃናቸዉ ጠፍቶባቸዋል ልባቸዉ ታዉሯል። ምላሳቸዉ  እዉነት ከመናገር  ተለጉሟል። አካላቸዉ  አላህﷻ መልዕክተኛዉንﷺ  የላከበትን ቀጥተኛ መንገድ  ከመከተል አስተባብለዋል።ሱና ለመተግበሮ ራሳቸዉ ቀና ማድረግን አሻፈረኝ ብለዋል። ቁርአንና ሱናን ዘደ ኋላቸዉ ወርዉረዉ ጥለዋል። የተቀበሉትንም የተሳሳተ አረዳድ ተረድተዋል።በሰለፎች አረዳድ ሌይ አሹፈዋል። ስሜታቸዉንና ዝንባሌያቸዉን ተከትለዋል።

☞አላህ ﷻባህሪያቸዉን ሲገልፀዉ ጥመታቸዉን ሲያብራራ በእነዚህ አይነት  ምሳሌዎች አስቀመጠ። አንደኛዉን ምሳሌ፦

▸ قال تعالى
:{ مَثَلُهُمۡ كَمَثَلِ ٱلَّذِی ٱسۡتَوۡقَدَ نَارࣰا فَلَمَّاۤ أَضَاۤءَتۡ مَا حَوۡلَهُۥ ذَهَبَ ٱللَّهُ بِنُورِهِمۡ وَتَرَكَهُمۡ فِی ظُلُمَـٰتࣲ لَّا یُبۡصِرُونَ }

✑አላህ እንድህ ይላል፦ምሳሌቸዉ እንደነዚያ እሳትን እንደነደደ ሰዉ በዙሪያዉ ያለዉን ሁሉ ባበራች ጊዜም አላህ ብርሀናቸዉን እንደወሰደባቸዉ በጨለማዎችም ዉስጥ የማያዩ ሆነዉ እንተዋቸዉ ሰዎች ብጤነዉ።( አልበቀራህ :17)

☛ሙናፊቆች እዉነታዉን የማይሰሙ ደንቆሮዎች፣የአላህን ግልፀ ታምራቶች የማያዩ እዉሮች፣ሐቅ የማይናገሩ ዱዳዎች፣ትክክለኛዉ ሃይማኖት ከተገለፀላቸወለ በኋላ የማይመለሱ ደረቆች ፣በስሜት ህዋሳታቸዉ መጠቀም የማይችሉ ፍጡሮች ናቸዉ።

▸ قال تعالى:{ صُمُّۢ بُكۡمٌ عُمۡیࣱ فَهُمۡ لَا یَرۡجِعُونَ }

➭አላህም እንድህ ይላል፦ እነርሱም ደንቆሮዎች እዉሮች ናቸዉ ስለዚህአይመለሱም።{አልበቀራህ:18}

📔ይቀጥላል  ኢንሻ አላህ..........

  ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
❝ቁርዓን ❞
༄༄༄

ቁርዓን ቁርዓን ቁርዓን፣
ድንበር የማይገታዉ የማይሽረዉ ዘመን፣
ዛሬ መመሪያ ለነገዉም ስንቄ፣
ቁርዓንን ልቅራበተጁዊድ ጠንቅቄ፣

ልብ የሚሰረስር የአምላክ ቅዱስ ቃል፣
ንክኪ የለለዉ ታምር ነዉ ይደንቃል፣
ታርክ ስነ ፁሁፍ ሳይንስም በሙሉ
ምንጩ ቁርዓን ነዉ ስልጣኔዉ ሁሉ
እንደ ረሱል ዘመን እንደ ሱሀቦቹ
ጥንት እደነበሩት እንደ ሰለፎቹ

ቁርዓን እንቅራ በቅላፄ ዜማ
በጣም የሚያስደስት በጆሮ ሲሰማ
ስለዚህ በተጅዊድ ቁርዓን እንቅራ
እንድያቀራርበን ከፈጣሪ ጋራ
የኢማን ጥፍጥና በልባችን ገብቶ
በቁርዓን ፍቅር ልባችን ተሞልቶ
በሱ ቃል ስንሰራ አሏህ ተደስቶ
ሰዉ እሱን ከያዘ ሁሉን ነገር ትቶ

ቀርዓን ነዉ ለኔ የሂወት መመሪያ
ባጢልን ከሀቁ እዉነትን መለያ
የደጋግ ባሮች የኢማን መስፈሪያ
አረህማን ጠብቆ ከሁሉም ያላቀዉ
እንከን የለለበት ቁርዓን ኩራት ነዉ

የድካም ማርከሻ የህመሜ ፈዋሽ
ፍቱን መድሀኒት በጭንቀቴ ደራሽ
ለአደም ዘር ያገራዉ ከልጅ እስካዋቂ
ለሰዉ ልጅ ብርሀን ከሳት አስጠንቃቂ
ከአሏህ የተቸረን የሂወት መመሪያ፣
የደስታ ብርሀን የቀልብ ማርጠቢያ፣


✍️𝐒𝚎𝚕𝚊𝚑𝚞𝚍𝚒𝚗 ᴬᴮᵁ 𝚘𝚞𝚋𝚎𝚒𝚍𝚊

𝐓𝐞 √√ t.me/selahudin_Islamic_knowlages
እስፖርት።
~
እስፖርት(የአካል እንቅስቃሴ) ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው።ለአዕምሮ መነቃቃት፣ለተሳሰረ ሰውነት የማፍታታት፣የድካም ስሜትን የመቅረፍ አቅም አለው።ከአላህ ቡሃላ በሽታዎችን ከምትከላከልባቸው መንገዶች አንዱ እስፖርት ነው።

"ምክር ለማካፈል ቀድሞ መሆን ግድ አይደለም"።

አቡ ዑበይዳ
t.me/AbuOubeida
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞ ➖〰➖〰➖〰➖ «ክፍል  ⓼» {የሙናፊቆች ልዩ ባህሪ} ☞ሙናፊቆች የማያዉቁትን ያወራሉ፣ሲናገሩ ይዋሻሉ፣ የተከለከሉትን ይተገብራሉ፣ያጠፍሉ ይጠፍሉ፣ በአላህ ላይ ያምፃሉ፣ሰይጣንን ይታዘዛሉ፣ነገር ይሰራሉ፣ሙስሊሙን  ያጣላሉ፣በዉሸት ይመሰክራሉ፣መጥፉ ቃል ይናገራሉ፣ሰዉ ያማሉ። ☛ሙናፊቆች ሙእሚን ጥላታቸዉ፣ካፊር ወዳጃቸዉ፣ ሰይጣን ኋላፊያቸዉ ነዉ።ሙናፊቆች ደረቅ ነዉ ልባቸዉ፣ቆሻሻ ነዉ…
❝የሙናፊቆች ባህሪያት❞
➖〰➖〰➖〰➖

«ክፍል  ⓽»

【የሙናፊቆች ባህሪ በቁርአን ዉስጥ ከባለፈ የቀጠለ..1】

ሁለተኛ ዉምሳሌ፦እዉነትና ዉሸቱ፣እምነትና ክህደቱ፣ቀንና ሌሊቱ፣ነጭና ጥቁሩ፣ሰማይና ምድሩ፣ ተቀላቅሎበት መለየት ተስኖት የሚይዘዉን  የሚጨብጠዉ ጠፍቶ እንደሚደናበር ደንባራ ነዉ።

◂ قال تعالى : { أَوۡ كَصَیِّبࣲ مِّنَ ٱلسَّمَاۤءِ فِیهِ ظُلُمَـٰتࣱ وَرَعۡدࣱ وَبَرۡقࣱ یَجۡعَلُونَ أَصَـٰبِعَهُمۡ فِیۤ ءَاذَانِهِم مِّنَ ٱلصَّوَ ٰ⁠عِقِ حَذَرَ ٱلۡمَوۡتِۚ وَٱللَّهُ مُحِیطُۢ بِٱلۡكَـٰفِرِینَ } { یَكَادُ ٱلۡبَرۡقُ یَخۡطَفُ أَبۡصَـٰرَهُمۡۖ كُلَّمَاۤ أَضَاۤءَ لَهُم مَّشَوۡا۟ فِیهِ وَإِذَاۤ أَظۡلَمَ عَلَیۡهِمۡ قَامُوا۟ۚ وَلَوۡ شَاۤءَ ٱللَّهُ لَذَهَبَ بِسَمۡعِهِمۡ وَأَبۡصَـٰرِهِمۡۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءࣲ قَدِیرࣱ }

➲አላህ እንድህ ይላል፦ወይም ምሳሌቸዉ  ከሰማይ እንደወረደ ዝናብ[ባለቤቶች] ነዉ። በርሱ በዳመናዉ ዉስጥ ጨለማዎች ነጓድጓድም ብልጭታም ያሉበት ሲሆን ከመብረቆቹ  ሞትን ለመፍራት ጣቶቻቸዉን በጆሮቸዉ ዉስጥ እንደሚያደርጉ ቢጤ ነዉ። አላህም  ከሀድዎችን ከባቢ ነዉ። ብልጭታዉ አይኖቻቸዉን ሊነጥቅ ይቀርባል ለነርሱ ባበራላቸዉ ቁጥር በርሱ ዉስጥ ይሄዳሉ በነሱም ላይ ባጨለመ ግዜ ይቆማሉ አላህም ባሻ ኖሮ መስሜቸዉንና ማያዎቻቸዉን  በወሰደ ነበር። አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነዉና። (አልበቀራህ:19_20)

በቁርአን ዉስጥ ከተጠቀሱ ባህሪዎቻቸዉ ዉስጥ ጥቂቱን እንመልከት፦

1▸ ምድር ላይ ማጥፍትና ማበላሸት፦ የማስመሰያዉና የስሜቱ በሽታ ልባቸዉን አፍኖ ገሎታል። መጥፉ ፍላጎታቸዉ ሀሳባቸዉን አበላሽቶታል።ብልሽቱ በወረርሽኝ መልኩ ተንሰራፍቷል  ሃኪሞት መደሀኒት አጥተዉለት ወደ ጥፍት ቀርቧል።

▪قال تعالى:{ وَإِذَا قِیلَ لَهُمۡ لَا تُفۡسِدُوا۟ فِی ٱلۡأَرۡضِ قَالُوۤا۟ إِنَّمَا نَحۡنُ مُصۡلِحُونَ } { أَلَاۤ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلۡمُفۡسِدُونَ وَلَـٰكِن لَّا یَشۡعُرُونَ }

◄ አላህ እንድህ ይላል፦ ለእነርሱም በምድር ላይ አታበላሹ በተባሉ ግዜ አሳማሪዎች ብቻ ነን ይላሉ። ንቁ እነሱ አጥፊዎች እነሱዉ ናቸዉ ግን አያዉቁም። (አል_በቀራህ :11_12)


2▸ ወደ እስልምና ሲጠሩ ማሾፍና ማላገጥ፦ በቁርአን እና በሱና ላይ በማሾፍ እምቢተኝነታቸዉን አሳይተዋል ።እነሱ ዘንድ ባለዉ እዉቀት በመደሰት ትእቢታቸዉን ገልፀዋል። ጠፊ የሆነችዉን ንግድ ለመፈለግ ባህርን ስንጥቀዋል፣ጋራን ወጥተዋል፣ ቁልቁለትን ወርደዋል።ጥርጣሬቸዉ የቅዠትን  ማዕበል ያማታቸዋል። የጭንቀትን  ማቅ ያለብሳቸዋል።

▪قال تعالى:{ وَإِذَا قِیلَ لَهُمۡ ءَامِنُوا۟ كَمَاۤ ءَامَنَ ٱلنَّاسُ قَالُوۤا۟ أَنُؤۡمِنُ كَمَاۤ ءَامَنَ ٱلسُّفَهَاۤءُۗ أَلَاۤ إِنَّهُمۡ هُمُ ٱلسُّفَهَاۤءُ وَلَـٰكِن لَّا یَعۡلَمُونَ }

➲አላህ እንድህ ይላል፦ ለእነርሱም ሰዎች እንዳመኑ እመኑ በተባሉ ግዜ ቂሎች(ሞኞች) እንዳመኑ እናምናለን? ይላሉ {አዋጅ}  ንቁ!እነሱ ቂሎች እነሱ ናቸዉ ግን አያዉቁም። (አል በቀራህ:13)

ሙናፊቆች  ነጭና ጥቁር ሁለት ፊት ያላቸዉ ሲሆኑ አማኞች የሚያታልሉባቸዉ እና ቢጤዎቻቸዉን የሚቀላቀሉበት ነዉ። እንደዚሁም  ሁለት ምላስ ሲኖራቸዉ፦አንዱ አማኞችን አምነናል በማለት የሚስማሙበትና ሁለተኛዉ  በልባቸዉ የተደበቀዉን ክህደት  የሚያንፀባርቁበት ነዉ።

▪قال تعالى:{ وَإِذَا لَقُوا۟ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ قَالُوۤا۟ ءَامَنَّا وَإِذَا خَلَوۡا۟ إِلَىٰ شَیَـٰطِینِهِمۡ قَالُوۤا۟ إِنَّا مَعَكُمۡ إِنَّمَا نَحۡنُ مُسۡتَهۡزِءُونَ }

▸አላህ እንድህ ይላል፦ እነዚያ ያመኑትን በተገናኙ ጊዜ አምነናል ይላሉ ወደ ሰይጣኖቻቸዉ ባገለሉ  ጊዜ እኛ ከናተ ጋር ነን(በርሱ) ተሳላቂዎች ብቻ ነን ይላሉ። <አል_ በቀራህ :14>

📔ይጥላል ኢንሻ አላህ........

⇊↶⇣⇣↶⇊↶⇣⇣↶⇊↶⇣⇣↶⇊↶
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/https_Asselefya1
~ሁሉ አማረሽ እትሁኑ እእ ልበሱ በቃ ሰጠኋችሁ¡