💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
◅ውዱ ባለቤቴ!

ውበቴም ድምቀቴም ላንተነው በቤቴ፣
ደስታህን ሳየው ነው የኔ  መደሰቴ፣

ወልደው ካሳደጉኝ ከእናት አባቴ፣
ካደኩበት ሰፈር ካሳደገኝ ቤቴ፣
ሁሉን ነገር ትቼ ካንተጋ መምጣቴ፣
ከሁሉም ተቀደምክ አንተ በሂወቴ፣

ለኔ ትልቅ ሰው ነህ  ውዱ ባለቤቴ፣
የልጆቼ አባት  የፍቅሬ መብራቴ፣
ባንተነው ምታምረው የዱኔያ ሂወቴ፣
ምስጋና ይገባው ለኔ ስላረገህ፣
ውዱ ባለቤቴ የደስታ ምንጬነህ፣
ፈገግታህ አጅቦኝ ስደሰት በሳቅህ፣

የትዳርን ትርጉሙ አወኩት በስምህ፣
ለልጅህ ጥሩ አባት ለኔ ጥሩ ባል ነህ፣
አላህን ምትፈራ በመልካም አዛዥ ነህ፣
ላልጨርስ አልጀምር አንተን የተሰጠህ፣
ቅን አሳቢነትህ ምግባረ ሷሊህ ነህ፣

አልሀምዱሊላህ ወሽኩር ለኔ ያደረገህ፣
አንተ ሳሊህ ሁነህ በመልካም መራሀኝ፣
ድሮማላውቀውን ድኔን አስተማርከኝ፣
ልጆቼን በተግባር በኢልም አነፅክልኝ፣
ውዱባለቤቴ እድሜህ ይርዘምልኝ፣
በዱኒያም ደስታውን ሁሌም አግኝልኝ፣
ባኼራም መኖሪያክ በጀነት ያርግልኝ፣

የልጆቼን አባት   ክፉ አያግኝብኝ፣
የልጆቼን አባት   ክፉ አያግኝበኝ።
             
           
t.me/https_Asselefya1 
◅አላህ ጠይቁኝ ያለው ሊሰጥ ነው‼

قال الله تعالى ﴿ وَاسْأَلُوا اللَّهَ مِن فَضْلِهِ ﴾

قال سفيان بن عيينة رحمه الله:
لم يأمر بالسؤال إلا ليُعطي

تفسير القرطبي ١٦٥ / ٥

t.me/https_Asselefya1
◅ዱንያ ላንተ አደለችም‼

‏قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله:
الدنيا ليست دارًا للمسلم، إنما دار المسلم هي الجنة وهو وُجد في الدنيا من أجل أن يعمل للجنة.

شرح الأربعين ٢٨٥

t.me/https_Asselefya1
ﻭﻟﻴﺲ ﺍﻟﺬﻛﺮ ﻛﺎﻷﻧﺜﻰ"

“ወንድ ልጁ እንደ ሴት ልጁ አይደለም»


ሴት ልጅ በሕይወት ዘመኗ በተለያዩ አካላዊና፣ ሆርሞናዊ ሂደቶች ዉስጥ ታልፋለች፡፡ ለምሳሌ በወር አበባ፣ በእርግዝና፣ በወሊድ፣ በማጥባት፣ በወር አበባ መቋረጥ ወቅት ….  ከባባድ የሆርሞን ለውጦች የሚታዩባቸው ጊዜያቶች ናቸዉና በባህሪዋም ላይ ለውጥ ቢታይ የሚገርም አይሆንም፡፡ እነኚህን ጊዜያት በተለይ የሕይወት አጋራቸው የሆኑ ወንዶች በሚገባ ማስተዋል ይኖርባቸዋል፡፡ ይህን ማስተዋል ከሴት ልጅ አንፃር ለሚወስዱት እርምጃ ምክንያታዊና ትክክለኞች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፡፡ ብትነጫነጭ፣ ብትቆጣ፣ ብትበሳጭ፣ ሆድ ቢብሳት፣ ቢደብራት … ምን አባቷ! ብሎ ከመቆጣት  ይልቅ ምን ሆና ነው!? ብሎ ጠጋ ብሎ ነገሩን መመርመሊ ሳይሻል አይቀርም፡፡

منقول
@https_Asselefya1
◅ማንንም ለመምስል አትጣሪ ራስሽ ብቻ ሁነሺ ኑሪ.....!!
የነገሮችን በፍጥነት መለዋወጥ ስናይ የአላህን ኃያልነትና ችሎታ እንረዳለን፡፡ ለርሱ ምንም ነገር አይሳነውም፡፡ ለርሱ ሁሉም ነገር ቀላል ነው፡፡ ከባዱም ቀላል፣ ቀላሉም ቀላል ነው፡፡

የባሮችን ሁኔታ በፍጥነት እና በማይታመን ሁኔታ ይቀያይራል፤ ሁኔታቸውን ይለዋዉጣል፡፡ ከሕይወት ወደ ሞት፣ ከዉድቀት ወደ ስኬት፣ ከስኬት ወደ ዉድቀት፣ ከጤና ወደ በሽታ፣ ከበሽታ ወደ ጤና፣ ከደስታ ወደ ሐዘን፣ ከሐዘን ወደ ደስታ፣ ከማጣት ወደ ማግኘት፣ ከማግኘት ወደ ማጣት …

ነገሮችን በቅጽበት የምትለዋዉጥ አምላካችን ሆይ! ሁኔታችንን ይበልጥ ወደተሻለ ሁኔታ ለውጥልን፡፡


منقول

@https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
❝ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ምግባሮች❞ ➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰     ÂŤ ክፍል ⓻ Âť 【የአለባበስና የመዋብ ስርዓቶች】 1🍁የተከለከሉ ልብሶችና አለባበሶች መራቅ፦ ሀ//የሀር ልብስ ለወንድ፦ ነብዩﷺእንድህ ብለዋል"ዱኒያ ላይ የሀር ልብስ የሚለብስ በአኼራ እጣ ፈንታ የሌለዉ ነዉ። ለሴት ግን የተፈቀደ ነዉ። ነብዩ  እንድህ ብለዋል ወርቅና ሀር ለሴቶች የተፈቀደ ሲሆን ለወንዶች ግን ክልክል ነዉ። ለ//የወንድ…
❝ኢስላማዊ ስርዓቶችና መልካም ምግባሮች❞
➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖

«ክፍል  ⓼»

        【የአካሄድ ስርዓቶች】

1🍁በብርቱ ሰዉ አረማመድ መጓዝ፦አነስ እንዳሉት ነብዩ ﷺሲጓዙ ቀልጠፍ ይሉ ነበር።

2🍁ከኩራተኞችና ጉረኞች አካሄድ አለመመሳሰል፦ ነብዩ እንድህ ብለዋል አንድ ሰዉዬ ካባ ለብሶ ጉፈሬዉን አበጥሮ በኩራት እየሄዴ ሳለ አላህ መሬት እንድትዉጠዉ አደረገ እስከ ትንሳኤዉ  ዕለት ይምዘገዘጋል።

3🍁ወደ ኋላ አለመዟዟር፦ ጃቢር እንዳስተላለፉት ነብዩ ﷺ ሲጓዙ ወደ ኋላ ዞር ዞር አይሉም ነበር።

4🍁 መኪና ወይም እንስሳ ሲጋለብ የሚከተለዉን ዚክር ማለት፦  

الحمد الله { سبحان الذي  س؎ع لنا هذا وما كنا له مقرنين } وإنا إلى ربنا لمقلبون } الحمد الله. الحمد الله . الحمد الله. الله اكبع .الله اكبع  .الله اكبع  ,سبحانك الهم إني ظلمت نفسي فاغفع لي فإنه  لا يغفر  الذنوب  إلا أنت }

🍁ትርጉም፦ምስጋና ለአላህ የተገባ ነዉ ። ይህንን የማንችለዉን ያገራልን ጌታ  ጥራት  ይገበዉ። እኛ ወደ ጌታችን ተመላሾች ነን።   ምስጋና ለአላህ ይገባዉ  ፣ምስጋና ለአላህ ይገባዉ  ፣ አላህ  ታላቅ ነዉ፣ አላህ ታላቅ ነዉ።   ጌታዬ ሆይ  እኔ ራሴን የበደልኩ ነኝ ከአንተ ሌላም ኋጢያትን የሚመር የለምና ማረኝ።

5🍁 ጉዞ ሲወጣ  የሚከተለዉ ዚክር ማለት፦

«الهم إنا نسألك في سفرنا هذا البر والتقوى  ,, ومن العمل ما ترضى ,, الهم هون علينا سفرنا هذا واءو عنا بعده ،، الهم أنت الصاحب في السفر,,  والخلفية  في الأهل،، الهم  إني أؚوذ بك مز وؚ؍اإ السفر،، وكآب؊ المنظر،، وسوإ المنقلب في المال والأهل Âť

🍁ትርጉም፦ ጌታችን ሆይ! በዚህ ጉዟችን መልካምንና ጥንቃቄን እንለምንሃለን ከስራም የምትወደዉን እንለምንሀለን ጌታችን ሆይ አንተ ጉዞ ላይ አብረህ የምትሆን ትተን የመጣንዉም ቤተሰብ ጠባቂ ነህ። ጌታዬ ሆይ በጉዞ ምክንያት ቤተሰብና ንብረት ላይ ከሚደርስ ችግር ሀዘንና መጥፎ አመላለስን በአንተ እጠበቃለሁ።

6🍁መጓጓዣ  እንስሳ ማሳረፍ፦ ነብዬ  እንድህ ብለዋል  በለምለም ግዜ ስትጓዙ ግመላችሁን እድል ስጧት።

7🍁ተራራ ኩረብታ የመሳሰሉትን ሲወጣና ሲወርድ የሚከተሉትን ዚክሮችን ማለት፦

◅ሲወጣ፦ አላሁ አክበር  (አላህ ታላቅ ነዉ)

◅ሲወርድ፦ ሱብሀን አላህ (አላህ የጠራ ነዉ)

8🍁ሴት ስትጓዝ የመንገድ ጥግ መያዝ፦ ነብዩﷺ እንድህ ብለዋል "ሴት ልጂ መሀል መንገድ ላይ መሄድ የለባትም።

✍️ኢንሻ አላህ  ይቀጥላል.........

✍️أم عثيمين الجامية

⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘
http://t.me/https_Asselefya1
http://t.me/https_Asselefya1
ከሽፉ ሹቡሓት 005
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
🎈መትን ከሽፉ ሹቡሓት

【 ክፍል  ➄ 】

🎙«𝐁𝐲 𝐀𝐛𝐮 𝐑𝐞𝐲𝐲𝐢𝐬 𝐈𝐛𝐧𝐮 𝐢𝐦𝐚𝐦 »

          √ የኪታብ 𝕡𝕕𝕗↓↓
t.me/https_Asselefya1/13134
Forwarded from Ů†ŮŽŮ€Ř­Ů’Ů€Ů†Ů أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے (لَتَرْكَبُنّ‌ طَبَقاً عَنْ طَبَق)
እንደ ጠንቋይ «ጨሌ» ምናምን ያለበትን "ማጎፈርያ" በሚባል (ፀጉር-ማስያዣ) ለምንድን ነው ሴቶች የሚጠቀሙት?

እንደው እኔማ: ማጫወቻ የሚሏትን ትራስ የሚወትፏት ነው የሚመስለኝ!።
:
እንዲህ ያለውን «ፀጉር ማስያዣ» የሚጠቀሙ ሴቶች፣ በራስ መተማመናቸው የጎደላቸውና የሌላትን ፀጉር አላት እንዲባልላት የምትሻ ደካማ ሴት ነች!።
t.me/abdu_rheman_aman
የእዉቀት ባለቤት ባል አግብተሽ ሌላ አጅ ነብይ ወንድ ጋር ሄደሽ ከመቅራት ካላሳረፈሽ በእኔ አይታ ባሉ. . ..........ደዩስ...... ነገር ነዉ። ኖ መንጫጫት¡¡

=
ያገቡ ባለ ትዳር እዉቀት ባለቤት ወንዶች ሚስቶቻቸዉ ለራሳቸዉ ቤታቸዉ ይዘዉ ቢያቀሩ ከሌላ ወንድ እንዳትገናኝ በር ቢዘጉ በትዳራቸዉ ጥሩ ሀያት ይኖራሉ ። ከሌላ ወንድ ከገተናኘች በተለይ በኢንተርኔት ልቧ ይሸፍታል ወደ ዉጭ ጠንቀቅ በሉ ወንዶችዬ!! ኡስታዜም ባሌም የልጆቼ አባትም ነዉ እንድትል ሚስትህ የብቻህ አድርጋት ከሌላ ወንድ በምንም እንዳትገናኝ በር ዝጋባት አጥብቀህ አንተ ብቻ ያዘት። እመነኝ ሴኬታማ እና ሚስትህ ዘንድ ተወዳጅ ትሆናለህ እሺ ¡¡

=

t.me/https_Asselefya1
◅ እፊትህ ሌላ ኡስታዝ ብታሞግስ አይክፍህ አትበሳጭ ሰበቡ ራስህ ነህና መጀመሪያ ለቀሀት ማለት ነዉ ቀድመህ አጥብቀህ ብትይዛት ሌላ እያነሳች አትበጠብጥህም ነበር ቅሬታ አይመጣብህም ነበር። ተፃፈ! በጥቅሉ ወንዶች ሚስቶቻችሁ ጠብቁ ጨርሻለሁ!!

=
◅በጣም ከሚያናድዱኝ እህቶች አንድ ወንድ ከወደዱ እሱ ላይ መጭጭ ከሱ ወጭ የሚሉት ነገር እሱ ጥሏቸዉ ሄዶ ሌላ ሀያት መስርቶ ልጂ ወልዶ አለሙ እየቀጨ እሱ ነዉ የሚሉት ያናድዱኛል!! ከሱ ዉጭ ተብሎ ሙጭጭ የሚባልበት አላህ ብቻ ነዉ። ሌላዉ ይቀየራል ነገራቶች ይቀያየራሉ።

◅እናም ሁለየ አንድ አይነት ሰዉ አትሁኚ የተሻለሽ ሆነሽ ለመገኘት ጠንካራ ሁኚ!! አላህ ከወደድሽዉ የበለጠ ጀግና እንደሚሰጥሽ በጌታሽ ላይ እርግጠኛ ሁኚ ለምኚዉ እሱን የተሻለ ይሰጥሻል ! በቃ ጠንክረሽ የተሻልሽ ጀግና ሁነሽ ያ ጥሎሽ የሄደ ዳግም እስኪመኚሽ ጀግና ሁኚ አታልቅሽ አትዘኝ ብርቱ ሴት ከሆንሽ የሚያጣሽ እንጂ የምታጪዉ አይኖርም!!


◅ልብ የምትሉት ነገር ወንድ ከምታለቅስለት ይልቅ የምታስለቅሰዉ እንሚወዳት እወቁ እኔ አላልኩም ራሳቸዉ ወንዶች ናቸዉ። ስለዚህ ሴቶችዬ ነቃ በሉ እሱ እያላችሁ አታለቃቅሱብኝ........!! እኔ ቆራጥ ሴት አድናቂ ነኝ አንቺ ቆራጧ ጀግና አላህ ይጠብቅሽ!!

t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
◅በጣም ከሚያናድዱኝ እህቶች አንድ ወንድ ከወደዱ እሱ ላይ መጭጭ ከሱ ወጭ የሚሉት ነገር እሱ ጥሏቸዉ ሄዶ ሌላ ሀያት መስርቶ ልጂ ወልዶ አለሙ እየቀጨ እሱ ነዉ የሚሉት ያናድዱኛል!! ከሱ ዉጭ ተብሎ ሙጭጭ የሚባልበት አላህ ብቻ ነዉ። ሌላዉ ይቀየራል ነገራቶች ይቀያየራሉ። ◅እናም ሁለየ አንድ አይነት ሰዉ አትሁኚ የተሻለሽ ሆነሽ ለመገኘት ጠንካራ ሁኚ!! አላህ ከወደድሽዉ የበለጠ ጀግና እንደሚሰጥሽ…
ብዙ ካየህዋቸዉ ገጠመኞች

ብዙ እህቶች የሚወዱት ጥሏቸዉ ሄዶ ነገር ግን እሱ ጥሏቸዉ ከሄደ ጠንካራ ሆነዉ ተቀይረዉ ከሱ የተሻለ አግተዉ የተሻለ ሂወት እየኖሩ ያ ሲፈልጋቸዉ የነበረ ዳግም እንደተመኘ ግን አያገኘት በቁጭት እንደሚኖር ነዉ።

እናም እላችሁ አለሁ እየወደዳችሁት ጥሏችሁ ለሄደ አትከፉ፣ አታልቅሱ፣ ራሳችሁ ለመቀየር የተሻለ ሀያት ለመኖር ጠንክሮ መስራት ብቻ ነዉ።

=
~ሆን ብሎ የገፋን መልሶ አያገኘንም። ለሰው ማጎብደድ የማናውቅ ኩሩ የ አላህ ባሮች ነን!
«ይኸ ይሁን ምርጫሽ»
➭➭➭➭➭➭➭➭➭

መልካም ተናጋሪ አንደበቱ እሩቱ፣
ቁጭ ብሎ የቀራ በግዜ በወቅቱ፣
ኢልምን የተማረ በወጣትነቱ፣
ዝርክርክ ያልሆነ ለድን ለእምነቱ፣
አለሁ ብሎ እሚቆም ለተዉሂድ ለሱና፣
በዉቀት የሚናገር ቆራጥና ጀግና፣
ሊቢድዓ ሰወች የሆነ ገናና፣

ከዉሸት የራቀ ለእዉነት ያደረ፣
በተዉሂድ ጉዳይ ላይ ያልተደራደረ፣
የተውሂድ የሱና ጠባቂ የሚሆን
ካዘዙበት ሁሊም የሚሞሏ ቃሉን
ጠማማውን ሁሉ በሁጃ አንበርካኪ፣
በጣፋጭ አንዴበት እውነትን ሰባኪ፣
ከጠላቶች ሴራ ቃሉ ጋሻ ሁኖ፣
በዴሊል ሲናገር ሰው ሁሉ አምኖ፣

አንተን የሚዘምር በጧትም በማታ፣
ሰወች ካልበዙበት ጭር ካለ ቦታ፣
ሀጥያቱን አስቦ የሚያለቅሰውን፣
ባሪያ በመሆኑ እሚዴሰተውን፣
አሏህን በማዉሳት ነፍሱን ያጠረዉን፣
አይኑን ላክ አድርጎ ወዴ ግዙፍ ሰማይ፣
እባውን ዘርግፎ በሰውነቱ ላይ፣
እባክህ የሚልህን ጭቀቱን እንድ ታይ፣
በጠፊዋ አለምም የሚታገል ለምነቱ፣
ለተውሂድ ለሱና የሚሆን መሰዋቱ፣

ሸሂድ ሁኖ የሚሞት የሚሆን ምኞቱ፣
እዉነት ተናገሪ በተግባር በምነቱ፣
ከመረጥሽስ አይቀር እደዚክ አይነቱ፣


✍️ሶላሁዲን አቡ ዑበይዳህ

𝐓𝐞~ t.me/selahudin_Islamic_knowlages
الزوج المثالي

▪ الزوج المثالي هو الذي يحرِصُ على إحسان قوامتِه على زوجته، فيفيض صدقًا وإخلاصًا، ويتدفَّقُ تضحيةً و بطولة، ويسيل حبًّا وحنانًا، يحقق لها الدفء و الأمان، ويوفر لها الرعاية و السعادة،
❝የሱናዋ ቆንጆ በተውሒድ ያበበች❞
«ሱና ላጣመረን ሁሉ ይሁንልኝ» ''እ''

    «ናፍቀኸኛል እሽ!?Âť
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ርቄህ ከርሜ ገጠር ላይ ስዳክር፡
ስስቴ ናፍቆትህ ብሎብኛል ጥንክር፡
ባያስፈልገኝም ባልቆጥርም ምስክር፡
ነፍስና ስጋዬ ይዘዋል ክርክር፡
ውስጤ በረጋልኝ አይንህን አይቸው፡
ዘይሬህ ባረፍኩኝ አካልክን አግኝቸው፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
...እና...ናፍቀኸኛል.....!!
እንደት ነህ..?መንድሜ እንደምን ከርመሀል?
ከተውሒድ ደዕዋህ ጋር ኑሮ እንደት ይዞሀል!?
ለሐቅ ስትለፋ ቀን ይመሽብሀል..!?
---------------------------------------------------
ምን አስጨክኖህ ነው ጥፍት ያልከኝ ለምን?
እኔማ ቆየሁኝ በናፍቆት ስዳምን፡
ለማየት ጓጉቼ አገናኘኝ ብዬ ፈጣሪን ስለምን!!
      አንተ ጠፋህ ለምን...!?
አንድትን ቀን እንኳን አልደወልክልኝም!!?
እኔ ግን ፃፍኩልህ ያው አላስችለኝም፡
አወ ናፍቀኸኛል ሲያሻህ አታመስግን፡
አልበላሁም እኔ የክፋትን ዝግን።
እውነት ለመናገር ጨካኝ ነህ አንተ ግን!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ዱንያ ላይ ለመኖር፤
አሏህ በወሰነው በተሰጠን እድሜ፡
እንኳን ካንተ ርቄ፤
አብሬህ ሆኘ እንኳን ትናፍቀኛለህ የሱናው ወንድሜ፡
ተዋደዱ ብሎ በቁርዐን አንቀፅ አሏህ የነገረን፡
በነቢ ሱና ላይ መንሀጅ ያጣመረን፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በል እስኪ ንገረኝ፤
ይሔ ሁሉ ፀጋ ይተመናል በሽ.!?
አንተ ባትናፍቅም፤
ለኔ ለወንድምህ ናፍቀኸኛል እሽ!?
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
  «ከኑረዲን አል አረቢ»
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi