💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
☞እንዲህም አይነት ደስታ አለ
~
ደግ ልብ በሌሎች ደስታ ይደሰታል። በሌሎች ማዘን ያዝናል። ምቀኛና ክፉ ልብ ደግሞ በሌሎች ደስታ ይከፋል። በሌሎች መጎዳት ይፈነጥዛል። "ምቀኛ ከራሱ ማግኘት ይልቅ የጓደኛው ማጣት ነው የሚያስደስተው" ይባል የለ?
በወገኖቹ ደስታ የሚረካ፣ በሃዘናቸው የሚያዝን ሰው ምንኛ የታደለ ነው?! ከወገኖቹ ልብ ውስጥ ደስታን ለማስገባት የሚተጋ አማኝ ምንኛ የላቀ ነው?! ታላቁ ታቢዒይ ሙሐመድ ብኑል ሙንከዲር - ረሒመሁላህ - "ከዱንያ ሁሉ የሚያስደስትህ ምንድነው?" ተብለው ሲጠየቁ "ሙእሚንን ማስደሰት'' ብለው ነበር የመለሱት። [ቀዷኡል ሐዋኢጅ፣ ኢብኑ አቢ ዱንያ፡ 33]

ከደጋጎቹ_ቀዬ

=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
☞የሞራል ከፍታ
~
የሆነ ሰው ሰልማን (አልፋሪሲይ) - ረዲየላሁ ዐንሁ - ዘንድ ገባ። እሳቸው ሊጥ እያቦኩ ነበር።

* "ምንድነው ይሄ?" አላቸው። እንዴት ይህንን ትሰራለህ ማለቱ ነው።
ሰልማን በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉት፡-
"አገልጋያችንን ለሆነ ስራ ልከነዋል። ሁለት ስራ ልንደርብበት ደግሞ አልፈለግንም።" [ሒልየቱል አውሊያእ፡ 1/2ዐ1]

ከደጋጎቹ_ቀዬ
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
✍ ጉደኛው ግመል .... የወሎ ትውስታ ክፍል 2 !!

☞ ይገርማል እንደ ሀገሩም የሰው ሁኔታ ልማድ እና ወግ ይለያያል ወገን እኔማ ብዙ የማላውቃቸውን ነገራቶች የተማርኩበት ግዜ ነበር ።

☞ የሚገርም ነገር ላጫውታችሁ ለፈገግታ ያክል እህት ወንድሞች ፈገግታ ሱና ነው ።

☞ በሰሜን ወሎ #ውርጌሳ ከተማ ላይ ከከተማይቱ ከወደ ላይ በኩል ትልቅ ተራራ አለና ወደዛ መሄድ ከጀልኩና ከአንድ ሰው ጋር ሄድን ሓቂቃ በጣም ይገርማል መንገዱ !!

☞ተራራውን ከታች ሁናችሁ ስታዩት በቀላል መድረስ የሚቻል ይመስላል ግን ጠጋ ብለን ስናየው በጣም ከባድ ነበር

☞ እንደምንም ብለን ግማሹ አከባቢ ደርሰን ትንሽ አረፍ ብለን ወደ ታች ተመለስን ግን ጉዳዩ ስንመለስ ነበር ።

☞ ስንመለስ እየመሸ ነበርና ጫካም ስለነበር ቶለ ቶለ እያልን ቁልቁለቱን እየወረድን ነው ድንገት ግን መንገዳችንን የሆነ ነገር ዘጋብን ምን አትሉኝም ..??

☞ ትልቅ ወንድ ግመል መንገዳችንን ዝግት በየት እንለፍ ?? መንገድ እንዳንቀይርም ከጎን እና ጎን ቤት አለ እኛም #ሼም ያዘን እና ዝም አልን አሳፍሮን ድንጋይ ብንወረውርም አይሰማም ግመሉ ..!!

☞ያለን አማራጭ ቢኖር በድፍረት ማለፍ ብቻ ነበር ከዛም እንደምንም ብለን እየፈራንም ቢሆን አለፍን ግመል ሳይ ያቺ ክስተት ትዝ ትለኛለች ።

☞ የአከባቢውን ባህል እና ወግ ያለመደ ሰው አስቸጋሪ ነው ወገን !!

✍ አቡ ዑሰይሚን

t.me/abuUseyminabdurehman
🎈ሰባት የኢድ አልፈጥር በአል ሱናዎች
〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰

①) ተክቢራ፦ የመጨረሻው የረመዷን ቀን ፀሀይ ከጠለቀችበት ጊዜ ጀምሮ ኢማም ለሶላት እስኪነሳበት ጊዜ ድረስ ማለት ይችላል።

②) ዘካተል ፊጥር ማውጣት፦ ይህም ኢድ ሁለት ቀን አለው ሲባል ጀምሮ ሶላት ተሰግዶ ከመጠናቀቁ በፊት መሆን አለበት።

③) ተምር መብላት፦ ይህም ለኢድ ሶላት ከመውጣታችን በፊት ሲሆን በነጠላ ቁጥር መብላት የተወደደ ነው።

④) ያማረ ልብስ መልበስና ሽቶ፦ ይህ ለወንዶች ሲሆን ሴቶች ግን ሽቶና የሚስብ ልብስ ልትጠነቀቅ ይገባል።

⑤) ገላን መታጠብ፦ ኢብኑ ኡመር ይታጠብ ነበር። ኢማሙ ነወውይ የተወደደ ተግባር በመሆኑ ስምምነት አለ ብሏል።

⑥) መንገድ መቀየር፦ ወደ ኢድ የሄደበት መንገድ ትተን በሌላ መንገድ ወደ ቤት መመለስ። መልእክተኛው ይቀይሩ እንደነበር ተዘግቧልና።

⑦) እንኳን አደረሳችሁ መባባል፦ ሶሀባዎች እርስ በርስ ሲገናኙ የእንኳን አደረሰህ መልእክት ይለዋወጡ ነበር። የተወደደ የሚሆነው ሶላት ከተሰገደ በኋላ ጀምሮ ባለው ጊዜ ነው።

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10557
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10557
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢያንስ ለመስጂዶች ክብር ይኑረን እንጂ
~
መስጂዶች የተከበሩ የአላህ ቤቶች ናቸው። ለዒባዳ የተገነቡ ክቡር ስፍራዎችን የመቃሚያ ቦታ ማድረግ የሚሰቀጥጥ ተግባር ነው። ከጥፋት መታቀብ ቢያቅተን ቢያንስ ለጥፋት ቦታ ልንመርጥ ይገባል።
ወገናችንን ከዚህ መርዝ ቅጠል ይገላግለው። ለዚህ ሁሉ ህዝብ በዚህ ቅጠል ሱስ መለከፍ ቀዳሚ ተጠያቂዎች ዱዓቶችና መሻይኾች ናቸው። ለወገኑ ከልቡ የሚቆረቆር እውነተኛ አስተማሪ ማለት መሬት ላይ ባለው ተጨባጭ ተሸንፎ ህዝብን የሚያስደስት ፈትዋ የሚሰጥ ሳይሆን የአላህ ፍራቻን አስቀድሞ ያለውን መራር እውነታ የሚጋፈጥ ነው። የወገኑ ጉዳት የሚያመው ሁሉ! በሚችለው መድረክ ሁሉ ከዚህ መርዛማ ቅጠል ሰዎችን ሊያስጠነቅቅ ይገባል። በዚህ ቅጠል የተለከፉ ወገኖችን ከሱስ ማውጣት ቢያቅተን እንኳ ቢያንስ ልጆቻቸውን በሚጠብቁበት መልኩ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ብናደርግ ቀላል ስኬት አይደለም።
~
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
تلاوة جميلة رائعة و رهيــــــــــــبة !!! (سعد الغامدي )
esmailtube
اللهم اجعل القرآن ربيع قلبي
ونور صدري وجلاء حزني
وذهاب همي وغمي ..
يارب
እንባህን ለመደበቅ ስትል
ልትስቅ ትችላለህ እንዲሁም ደህና መሆንህን
ለማሳየት ፈገግ ልትልም ትችላለህ‥
⇘
ነገር ግን ውስጥ አዋቂ የሆነ ምትደብቀውንና
ግልፅ የምታወጣውን የሚያውቅ ጌታ አለህና
ጭንቀትህንና ሀዘንህን ለጌታህ ንገረው

( إِنَّهُ يَعْلَمُ الْجَهْرَ وَمَا يَخْفَىٰ )
" እርሱ ግልጹን የሚሸሸገውንም
ሁሉ ያውቃልና ፡፡"
[አል-አዕላ 7]

𝐓𝐞~ t.me/selahudin_Islamic_knowlages
ቁርአን ጁዝ ➁➈
الشيخ علي الحذيفي
❝ቁርአን በረመዷን አብረንእናኽትም!❞


☞ጁዝ  ሃያ ዘጠኝ

▪الليلة(28)  رمضان

🎙الشيخ علي الحذيفي حفظه الله


ከሱረቱል ተህሪም አንቀፀ
13 እስከ ሱረቱል ሙርሰላት አንቀፀ 50

   ⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘⇘
t.me/https_Asselefya1/12046
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
Photo
❝ይድረስ ለኢድ ሶላት ለሚወጡ እህቶች❞
〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖〰➖

☞ የኢድ ሶላት ለወንድም ለሴትም የተደነገገ ኢባዳ ነው። ሴቶች ልክ እንደ ወንዶቹ ለኢድ ሰላት መውጣታቸው የተወደደ ተግባር ነው። እንዲወጡም ታዘዋል። ነገር ግን በምትወጣበት ሰአት እነዚህን መስፈርቶች ልትጠብቅ ይገባል።

①⇘ወፍራም፣ ሰፊ፣ ረጅምና ሁሉ ሰውነቷን የሚሸፍን አለባበስ መልበስ አለባት!
②⇘ሽቶ የሚባል ነገር በፍፁም ሊነካት አይገባም
!
③⇘አቅሟ በቻለው ሁሉ ከወንዶች መራቅና ከነሱ ጋር ሳትጋፋ የመንገዱን መሀል ሳይሆን ጫፍ ጫፋን ይዛ መሄድ አለባት!
④⇘በተክቢራም ይሁን በሌላ ፅምፇን ዝቅ ማድረግ አለባት!
⑤⇘ጫማዋ ከፍ ብሎ ሲንቋቋ ሰውን የሚጣራ መሆን የለበትም!
⑥⇘የልብሷ ከለር ደመቅ ብሎ የሰውን አይን የሚስብና ጌጣ ጌጦች ያሉበት መሆን የለበትም!
⑦⇘እራሷ ከመፈተንና ሰውን ከመፈተን ጥንቃቄ ልታረግ ይገባል!
⑧⇘ በአረማመዷ፣ በአነጋገሯና በእይታዋ ሀያእ የተላበሰች ልትሆን ይገባል
!

☞ምክንያቱም ኸይር እሰራለሁ ብላ ወንጀል ከመሸከም፣ የጀነት ሰበብ አደርሳለሁ ብላ የጀሀነም ሰበብ እንዳታደርስ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባታል።

☞ በአሁን ሰአት ግን ለኢድ ሶላት ብለው በሚመጡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶች እያፈርን አንገታችን እየተደፋ ነው። እስልምና እንዲሁም ሙስሊሞችን እያሰደቡ ነው።

☞ልብሷ ከራሷ ተጣብቆ፣ ሰውነቷን ወጣጥራ፣ ፊቶቿ እግሮቿና እዶቻን ከፍታ፣ ሽቶ ተለቅልቃ፣ ቻፕስቲክ ተቀብታ፣ ቅንድቧን ተቀንድባ፣ የተቀባችውን ሂና እያሳየች፣ የኢትዮጵያ ባንድራ ግምባራ ላይ አስራ፣ ወደ ግራና ቀኝ የሚያወዛውዝ ጫማ ለብሳ፣ ድምፇ ከፍ አድርጋ እየሳቀች፣ ከወንዶች እኩል እየተጋፋች፣ ወንዶችን አፍጣ እያየች፣ በየሱቁ እየተዘዋወረችና ሌሎችም ሙሀለፋቶች በመፈፀም እራሷም ተፈትና ሌላውንም ፈትና፣ እራሷ ወንጀል ውስጥ ከታ ሌላውንም ዘፍቃ የወንጀል መአት ተሸክማ ወደ ቤቷ የምትመለስ አለች።

✑እንዲህ አይነቷ እህት ምናለ እቤቷ በተቀመጠች‼️

✍️ሸር በማድረግ ለሁሉም ሙስሊም ሴት አድርሱ!!
⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱⟱
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10570
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/10570
✍️ከወንጀል አትጠራምና ተውበትን አብዛ!!

📍‏قال الشيخ صالح الفوزان :

لا أحَد يَسْلَم مِن المعاصي ،
ولكِن بابُ التوبة مفتُوح ولله الحمد .

ሸህ ፈውዛን (حفظه الله) እንዲህ ይላል።

ማንም ሰው አላህን ከማመፅ (ከወንጀል) ሊጠራ አይችልም። ነገር ግን ለአላህ ምስጋና ይገባውና ወደርሱ እንመለስ ዘንድ የተውበት በር ክፍት አድርጎልናል።

📚(إغاثة اللهفان - ١٨جمادى الأولى١٤٣٩)

https://t.me/https_Asselefya1
ሰበር!
~
ሰዑዲያ ዒድ ነገ ጁመዐ እንደሆነ አውጃለች። [ምንጭ:- አሰዑዲያ የዜና ወኪል https://twitter.com/SaudiNews50/status/1649070246681104386?t=gjVElwU_nLMs-1Vy-cEDSg&s=19
]
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል።
=
ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፦

{ وَٱلۡقَمَرَ قَدَّرۡنَـٰهُ مَنَازِلَ حَتَّىٰ عَادَ كَٱلۡعُرۡجُونِ ٱلۡقَدِیمِ }
"ጨረቃንም የመስፈሪያዎች ባለቤት ሲሆን እንደ ዘንባባ አሮጌ ቀንዘል እስኪሆን ድረስ (መሄዱን) ለካነው።" [ያሲን፡ 39]

የጨረቃ መስፈሪያዎች የተባሉት በየ ወሩ ለ 28 ቀን የሚያልፍበት ቆይታ ነው። ቀጭን ሆና ጀምራ እያደገች ትሄድና ሙሉ ጨረቃ ትሆናለች። እንደገና እያነሰች ሄዳ በምስሉ ላይ እንደሚታየው ልክ እንደ ደጋን የጎበጠ የተምር ቀንዘል ጎብጣ ትቀጥናለች። በመጨረሻ ትጠፋለች።
ወሩ 30 ቀን ሲሆን ጨረቃ ለ 2 ሌሊቶች ትደበቃለች (አትታይም)። ወሩ 29 ቀን ሲሆን ደግሞ ለ 1 ሌሊት ትደበቃለች።
ኢስላማዊው የቀን መቁጠሪያ የጨረቃን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገ ነው። ስለሆነም ዘካ የሚወጣው፣ የልጆች ለአቅመ መጠን መድረስ የሚወሰነው በጨረቃ አቆጣጠር መሰረት ተሰልቶ ነው። በጨረቃው አቆጣጠር አንድ አመት 354 አካባቢ ቀናት ሲኖሩት የፀሐዩ አቆጣጠር ደግሞ 365 አካባቢ ቀናት አሉት። ስለዚህ የ 11 ቀን ልዩነት አለ ማለት ነው።

ማስታወሻ፦
አንዳንዶች የጨረቃን መውጣት ስንከታተል "ጨረቃን ታመልካላችሁ" እያሉ ይከስሳሉ። ለነዚህ አላዋቂዎች የምንላቸው እናንተ የፀሐይን እንቅስቃሴ መሰረት ያደረገውን መቁጠሪያ የምትጠቀሙት ፀሐይን ስለምታመልኩ ነው እንዴ? ለምን በራሳችሁ ላይ ትተኩሳላችሁ?
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor