💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
Audio
2-تجريد المتابعة للرسول-صلى الله عليه وسلم-.


🎙الشيخ سليمان بن سليم الله الرحيلي


http://t.me/https_Asselefya1
የአላህ!

እጃችን አንተ የምትጣላዉን ነገር ከሚጽፍ  አይናችን አንተ የከለከልከዉን ሁሉ  ከማየት አንተ ጠብቅልን ።

✍️
☞ወደ ከፋ ነገር ሳያደርስ የሶሻል ሚድያ ጉዳይ ይታሰብበት‼

~~
☞የሶሻል ሚድያ አጠቃቀማችንን ቶሎ ካላሰብንበት ሊያጠፋን ነው።አንዳች የተጠቀምንበት ነገር ሳይኖር ከዛ ከዚህ ስንበን ጊዚያችንን ጥንቅቅ አድርጎ በልቶታል።ከዛሬ ነገ እንማርበታልን ብለን የገዛነውን ኪታብ አቧራ ቦኖ አጥቁሮታል።የነበረንን ሽርፍራፊ ስዓት ሁሉ አሉ የሚባሉ ሚድያዎችን ተቀራምተንበታል።አንድ ሚሴጅ "ጢርር"ባለች ቁጥር #ፌስቡክ ስንኳትን ከዛ ተመልሰን #ቴሌግራም ስንገባ፡ከዛ ስንወጣ #ዋትስአፕ ትዝ ሲልን፡ብዙ ሳንቆይ #በኢሞ ሲደወል ለርሱም መልስ ስንሰጠ:  አንድ ነገር ሳንጠቀም ይሄው በሚድያው እንደወጣን ቀርተናል።አሏሁል ሙስተዓን።

☞ይባስ ብሎ ሁሉም እንደ ሞባይሉ የደረሰውም ያልደረሰው አንዳንድ #ቻነል፣ግሩፕ በየ'እጁ ያዘ ከዛ ቡኃላ የትም በሚድያው ጽሁፍ ሲያማርጥ ይውላል።አሁን ሁሉም በየግሉ የሚድያ አካውንት ስለከፈተ ፡ና"ተማር ስትለው ቆይ ቢዚ ነኝ ይላል ስትፈልግ ግን የምታገኘው እዚሁ ሰፈር ሲቃብዝ ነው።ሌላኛው እንደምንም እየተልመጠመጥ አንድ ደርስ ይጀምራል ሳያጋምሰው ከስራ ጋር አልተመቻቸልኝም ይላል።እህ" ብለህ ስጠይቅ እዛ #ዋትስአፕ የከፈተው ግሩፕ ላይ የሚለቅበት ነገር ጨንቆት ከዛም ከዚህ ሲመራርጥ ታገኘዋለህ።ሌላኛው #ኢሞ ላይ ተለጥፎ ወጪ ወራጁን ሲመለከት ስዓት ያልፈዋል በዛው ማቆራረጥ ያበዛል ሰልችቶ በዛው ይጠፋል።ይሄ ሁሉ አልላቀቅ ያለን ፈተና ነው።

☞መጥፋት ካለበት እና ካልጠቀመ እንኳን አላቅማችን የተከፈተው ቻናላችን አይደልም።የግል አካውንታችንም ይጠፋል እና የቻነሎችና የግሩፖች ነገር ይታሰብበት።ሳይቀደሙ ነው መቅደም።

✍አቡ_ዑበይዳ ነኝ
https://t.me/AbuOubeida
https://t.me/AbuOubeida
እወድሻለሁ ስትላት  አመሰግናለሁ ከምትል ሚስት ይጠብቃችሁ ሸባቦች¡¡


©መልካም ለይል¡
Forwarded from ÂŤđ“𝐾𝐰𝐮𝐡𝐢𝐝 𝐀𝐧𝐝 𝐒𝐮𝐧𝐧𝐚𝐡 𝐜𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥»
ያአኺ የዲን እውቀት ላይ ጠንከር በል❗️እድሜህ የትኛውም ላይ ይሁን ሀፍረት አያዝህ።ጃሂል ሁኖ እንደመቅረት የሚያሳፍር ነገር የለምና።

➧እነዚያ ከፍ ያለ ቦታ ላይ የነበሩት ሰሃቦች ወደ ኢስላም ሲገቡ እድሜያቸው ምን ያህል ነበር⁉️አሻራቸውስ ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፍ ሁኖ እያየህ አይደል⁉️ አሁን ላይ የምታያቸው ታላልቅ መሻይኾቻችን፣ ኡስታዞቻችን የሆነ ጊዜ እነሱም እንዳንተ ተማሪዎች ነበሩ።

ግን ጠንካራና የማይበገሩ ተማሪዎች።

ከአንተ ብዙ ነገር የሚጠብቁ የበታቹችህ አሉና የዲን እውቀት ላይ ጠንከር በል አደራ❗️

ኢማሙ አሻፊዕ ረሂመሁሏህ እንዲህ ብለዋል፦


   "በኢልም ጥላ ሾር ጥቂት ሰዓታትን መታገስ ያቃተው ሰው እድሜ ልኩን በጃሂልነት ጥላ ሾር ይሶብራል❗️"

ላንችም ነው ያኡኽቲ❗️

➴➴➴➴➴➴
https://t.me/Tewuhid_We_sunnah
☞አሁን ላይ በትዳር ዙሪያ የአብዛኛዉ እህቶች ሀል ያስፈራል! የምናየዉ የምሰማዉ በጣም ያሳፍራል!!


☞ተሯሩጠዉ ይገባሉ ማንነቱን ሳያጣሩ ተሯሩጠዉ ከትዳሩ ይወጣሉ ብዙ ነገራቸዉን ያበላሻሉ።

☞እህቶቸ ለእናተ ይሁን አይሁን የማታቁት ወንድ በስተ ጀርባዉ ምን እዳለ ማንነቱን የማታቁ ወንድ ሀታ ብታቁም ትኩረት ሰታችሁ አትከታተሉት እሱን ለሱ ተወት ራሳችሁን ጠብቁ ትዳር ሂወት ነዉ ዘወ ተብሎ የሚገባበት አይደለም።


☞ራሳችሁን ለፈተና ከሚጥል ነገር ለወንድሞቻችሁ ፈተና ከሚሆን ነገር ተቆጠቡ!!
መልካም ነገር የሚገኘዉ ከአሏህ ነዉ ስለዚህ መልካም ትዳርም የሚሰጠዉ አሏህ ነዉ በዱአ በርቱ ትዳር የሚዘገየዉ ተፈላጊ ስላልሆሺ አይደለም አሏህ በወሰነበት ጊዜ ነዉ የሚ ሆነዉ!
አንዳንድ እህቶች እማ በትዳር ዙሬ በቀደር የማመናቸዉም ነገር ያጠረጥራል አንድ ታዋቂ አዉ እዉቀት አለዉ የተባለ ወንድ ካዩ ሀሳባቸዉ ስለዛ ወንድ ይሆናል ሰበብ አስባብ እየፈለጉ ያንን ሰዉ ለማዉራት ለመቅረብ የማያደርጉት የለም ገብተዉ ግማሹ ምክር ፈልገን ቂረአት እዚህ እዚህ ነበርኩ ቀጥየ ምን ልቅራ ሱባሓን አሏህ እኔማ ገርመዉ ይገርሙኛል በአሁኑ ሰአት ከወንዶች ሀል የሴቶች ያስፈራል እህቴ መልካም ነገር የሚሰጠዉ አሏህ ለአንቺ ከአንቺ በላይ የሚስብልሺ ጌታሺ አሏህ እያለ ዱአ ብዘ ነገሮችን ማስተካከል እየቻለ. ለምን በዱአ አበረቺም? ወንድ ልጅስ ጋር እየተለሳለሺ እድታወሪ ማነዉ የፈቀደልሺ? እደፈለግሺዉ ልታወሬቸዉ የፈለግሺዉን ልጠይቄቸዉ የሚገቡት ወንዶች አባትሺ የእናትሺ ልጅ ወንድምሺ የኒካህ ባልሺ ብቻ ነዉ።።


☞እህቴ ሴት ልጅ እወኝ እዉኝ ስትል ትኩረት ለመሳብ ብላ ወጣ ወጣ ስትል አያምርባትም በተለይ ላጤ ሆና በእርግጥም ብዙ ወንዶች ልፈትኝ ትችያለሽ! ግን እርግጠኛ ሁኘ ነዉ የምነግርሺ ወንድ ልጅ ለትዳር የሚስፈልጋት ሴት በሐያእ የተዋበችዉን ቁጥቧን እና ሰታራዋን ነዉ #ተሰተሪ ካልተፈቀደልሺ ወንዶች ጋር ያለሽን ግንኙነት አቁሚ ዶሩሪ ነገር ካልገጠመሺ በወንዶች በር ብቅ አበይ!


☞ ሰዉ ያሰበዉን አዉ የወደደዉን አያገባም አሏህ የፃፈለትን ብቻ ቢሆን እንጅ አንቺ ከወደድሺዉ ከመረጥሺዉ ደሞ አሏህ የመረጠልሺ ለሂወትሺ መልካም ነዉ ለአንቺ የተባለ ነገር ለአንቺ ከመሆን ዉጪ ምንም አማራጪ የለዉም።ስለዚህ ለአንቺ ከአንቺ በላይ የሚስብልሺ ጌታሺን ጠይቂ የወደድሺዉን ነገር!!
ታሞ ተመሞቀቅ አስቀድሞ መጠቀቅ!!

☞ አንቺ መልካም ከሆሺ የሚጣሺ እንጅ የምታጪዉ ሰዉ አይኖርም።
እጅግ አዛኝ እና ሩህሩህ የሆነዉ ጌታችንም ቃል ገብቶልናል ለመልካሞች መልካም እደሚሰጣቸዉ
!!

وَٱلطَّیِّبَـٰتُ لِلطَّیِّبِینَ وَٱلطَّیِّبُونَ لِلطَّیِّبَـٰتِ

☞መካሪ ሞልቷል ኡስታዞች ወንድሞች እህቶች ይመክራሉ ተመካሪ ነዉ የጠፋዉ!

☞ እኔም የታዘብኩትን ቢጠቅማችሁ ብየ ነዉ ግልባጪ ለወንዶች ይሁንልኝ!!

✍️ኡሙ ዑመር ሰዓዳ

⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘⇙⇘
https://t.me/https_Asselefya1
«ለትዝታ ያክል ወደ ኋላ ልመልሳችሁ እ¡


«ማነዉ ከገጠር አድስ አበባ እንደገባ መኪና ሲያይ
በመሮጥ ይመለጥ መስሎት የሚሮጥ ህዕ¡

«እኔማ አልኳችሁ በዛች በኮንኮ ጫማ ለመሮጥ እሞክር ነበር ህዕ አብሮኝ ያለ እጄ ይዞ ነበር አስባልት የሚያሻግረኝ እላችሁ አለሁ¡¡

ፈገግ በሉ መልካም ምሺት ¡


✍️
እኔ ልቃወማችሁ ነዉ አንዳድ ነጋዴዎች!?

ቆይ ኢትዮ ተቀምጣችሁ በሪያል በድርሀም የምትሸጡት በሰላማችሁ ነዉ!?

ለምን ግን አንተዛዘንም!?

በጣም ስለገረመኝ ነዉ ሀቂቃ!

ብንተዛዘን መልካም ነዉ!!

እህቶች ልትነቁ ይገባል ዝም ብላችሁ ብራችሁ አትስጡ!!ሞኝ አትሁኑ!የሪያል ድርሀም ዋጋ በየ ቀን የሚቀያየር የሚያስማማዉ በኢትዮ ብር ግዙ እቃ ለቤተሰብ ስትገዙ!!

✍
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾

•القارئ: #عبدالبديع_غيلان
የአጧእ ብኑ የሳር እና የቆንጆዋ ገጠሬ ሴት ታሪክ

ኢብኑ አቢ ዱኒያ እንዲህ ያወሳል፦

አጧእ ብኑ የሳር እና ሱለይማን ብኑ የሳር ከባልደረቦቻቸው ጋር ለሀጅ ጉዞ ከመዲና ወጡ። አብዋእ ላይ ሲደርሱ እረፍት አደረጉ።

ሱለይማን እና ባልደረቦቻቸው ለከፊል ጉዳዮቻቸው ሄዱ። አጧእ ከቤት ቀረና ቁሞ መስገድ ጀመረ። ከዚያም አንዲት ውብ የገጠር ሴት ወደ እርሱ ገባች፣ እየሰገደ እያለ ከፊት ለፊት ቁጭ አለች። ጉዳይ ያላ፞ት መሰለውና ሶላቱን አሳጥሮ ጨረሰና ፡— “ጉዳይ አለሽን?” አላት።

እሷ፡— “አዎ”

እርሱ፡— “ምንድን ነው?”

እሷ፡—  “ተነስ! ከእኔ ላይ ጉዳይን ፈፅም፣ ወንድ አስፈልጎኛል፣ እኔ ባል የለኝም።” አለችው። ወደሷም ተመለከተ፣ ወጣት ... እጅግ በጣም ውብ ...

እርሱ፡— “ዘወር በይልኝ! እኔንም እራስሽንም በእሳት አታቃጥይ” አላት። ከነፍሱም ማባበል ጀመረች፣ የፈለገችው ካልሆነ ብላ ችክ አለች።

አጧእ እያለቀሰ፡— “ወዮልሽ! ዘወር በይልኝ! ዘወር በይልኝ!” ይል ጀመር። ለቅሶው በረታ፣ ሴቲቱ ለቅሶውንና ጭንቀቱን ስትመለከት ጊዜ እሷም አለቀሰች!!

በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ሱለይማን ብኑ የሳር ከሀጃው ሲመለስ አጧእን እያለቀሰ ሲመለከት፣ ሴቲቱም በቤቱ ጥግ ላይ ሁና ስታለቅስ ሲያይ ምን እንዳስለቀሳቸው ሳያውቅ እነሱ ስላለቀሱ አለቀሰ።

ባልንጀሮቻቸውም ተራ በተራ መጡ። áŠ áŠ•á‹ľ ሰው መጥቶ ሲያለቅሱ ሲያቸው ጊዜ ስለጉዳዩ ምንም ሳይጠይቅ እሱም እያለቀሰ ይቀመጣል። ለቅሶው በረታ፣ ድምፆችም ከፍ አሉ።

ገጠሬዋ ሴት ይህን ስታይ ተነስታ ወጣች። እሱም ተነሳ፣ ሰዎቹም ገቡ።

ሱለይማን ለወንድሙ ካለው ክብርና ፍራቻ የተነሳ ስለሴትዮዋ ታሪክ ሳይጠይቀው የተወሰነ ጊዜ ቆየ። አጧእ ለሱለይማን ትልቅ ወንድሙ ነው። 

ከዚያም ለሆነ ጉዳያቸው ወደ ግብፅ ሄዱና አላህ የሻውን ያህል ቆዩ። አጧእ በአንድ ሌሊት ተኝቶ ሳለ እያለቀሰ ተነሳ።

ሱለይማን፡— ወንድሜ ሆይ! ምን ያስለቅስሃል?

አጧእ፡— “ዛሬ ሌሊት ያየሁት ህልም”

ሱለይማን፡— “ምንድን ነው?”

አጧእ ፡— “እኔ በህይወት እስካለሁ ድረስ ለማንም እንዳትናገር መስፈርት አርጌ ነው የምነግርህ”

ሱለይማን፡— “መስፈርት ያደረከው አለልህ”

አጧእ እንዲህ አለ፡— “ነቢ ዩሱፍን ዐለይሂሰ፞ላም በህልሜ አየሁት፡ ወደሱ ከሚመለከቱት ጋር እመለከተው ጀመር። ውበቱን ሳይ ግዜ አለቀስኩ፣ ከሰዎች መካከል ነጥሎ ተመለከተኝ።

“አንተ ሰው ሆይ! ምን ያስለቅስሃል?” አለኝ።

እኔም፡— አባቴ እና እናቴ ይሰውልህ የአላህ ነብይ ሆይ! አንተን፣ የንጉሱን ሚስት፣ በእሷ ምክንያት የደረሰብህን ፈተና፣ በእስር ቤት የገጠመህን ነገር እና ከሽማግሌው አባትህ የዕቁብ መለየትህን አስታወስኩ አልኩት።

ዩሱፍም (ዐለይሂሰ፞ላም) ፡— “በአብዋእ የገጠሯ ሴት ባለቤት አትገረምምን?” አለኝ።  ምን ማለት እንደፈለገ አወቅሁ፣ አለቀስኩ፣ እያለቀስኩ ተነሳሁ።

ሱለይማን፡— “ወንድሜ! የዛች ሴት ነገር ምን ነበር?”

አጧእ ታሪኩን ነገረው፤ ሱለይማንም አጧእ እስኪሞት ድረስ ለማንም አልተናገረም፤ አጧእ ከሞተ በኋላ ከቤተሰቡ ለሆነች ለአንዷ ሴት ሾለ ጉዳዩ ነገራት።  [አሪቃ ወል ቡካእ: 199]
•
በቤት ውስጥ ብቻቸውን፣ መንገደኛ፣ ለአገሩ እንግዳ ፣ እሷ እየለመነችው፣ እሱ ግን “እራቂኝ! እራቂኝ! እራቂኝ!” ይላታል። #ጥብቅነት_እንዲህ_ነው
• እኛንም እነሱንም አላህ ይማር።
منقول
https://t.me/https_Asselefya1
هـدايـة الـمـسـتـفـيـد ١٩
𝕬𝖇𝖚 𝖀𝖘𝖊𝖞𝖒𝖎𝖓
☑️አዲስ የተጂዊድ ኪታብ ቂርአት
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

📚ኪታብ ሒዳየቱል ሙስተፊድ

♻️ክፍል  ⓵⓽

📜የኪታብ  pdf👇
t.me/https_Asselefya1/10408

🎤በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

   ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
@Abu_Dujanah_Online_merkez
https://t.me/https_Asselefya1
My bro!! አንተ ማለት ድንቅ ፍጡር
ነህ ጠንካራ ከሆንክ አራት ሴቶችን ከላጤነት ማውጣት ትችላለህ
!!

ማዶ ላይ ተብለሃል እሺ ................¡¡