💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
15K subscribers
4.48K photos
2.09K videos
162 files
12.6K links
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله

ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ↓↓
Download Telegram
እህቴ ሆይ !

እኔኮ ስወድሽ
መልካም ሳስብልሽ
ቁርኣን ሃድሱን
ሲራውን ፊቂሁን
በነብዩ መንገድ
በሱሃባ አረዳድ
በታቢዖች ጽናት
ቢድኣን በተዋጓት
እንድሆን ነው ጉዞሽሁሌም የምመክርሽ
እናም እህት ዓለም ፈተናዎች በዝተዋል
ሊያስቀይሩሽ ድንሽን ይሄው ተነስተዋል
    ስለዚህ
ነቃ በይ ተማሪ ድንሽን
ለዱንያም ለአኼራም ስንቅ የሚሆንሽን
በሰለፎች መንገድ በዛ ጸዳ ባለው
ተራራ ሸንተረር ጎርባጣ በሌለው

✍🏻 Ibnu Seid


https://t.me/https_Asselefya1
📍በጣም የሚዋደዱ ባል እና ሚስት ነበሩ
ሚስት መረቀነች እና ሁለተኛ አግባ አለችው ባል ተይ ይከፋሻል አላት ሚስት በፍጹም አይከፋኝ።

➘አንተን የሚያስደስት ያስደስተኛል አለችው
ባልም እሺ አለና አንድ ቀን ከሌላ ቦታ አደረ ከዚያም በጧት ወደቤት ሲመጣ ከመንገድ እንስራ (ሼክላ)ይገዛናልብስ አለባብሶ ቤቱ አምጥቶ አንደኛው ክፍል ውስጥ ያስገባና ይቆልፍባታል!!

➘መስኮቱን ከፍቶ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግብ እና መጠጥ ስጫት ብሎ ወደስራ ይሄዳል
ማታ ከስራ ሲመለስ ሚስቱ በር ላይ ቁማ እያለቀሰች ጠበቀችውምነው ምን ሆንሽብኝ ሲላት አዲሲቱ ሚስትህ ሰደበችኝ አዋረደችኝ ብላው እርፍ።

➘ከዛ ባልነሽ ብትሩን አንስቶ እንስራውን ከሠከሠው ወደሚስቱ ዘወር ብሎ እህሳ? ሲላት እንዲህ የሚል ስንኝ ቃል ተናገረች

(الضرة مرة ولوكانت جرة)

ጦውንት መራራ ነች እንስራም ብተሆን
!!

🔖እናማ እህቶች እንዳይደርስባችሁ ዱአ አድርጉ
ካመጣውም ሶብሩ

ወበሺሪ ሷቢን የሚለውን አየህ አስታውሱ

ከ © ወንድም ጀማል ዬሱፍ ሐርቡ የተኮረጀ


https://t.me/https_Asselefya1
💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
📍በጣም የሚዋደዱ ባል እና ሚስት ነበሩ ሚስት መረቀነች እና ሁለተኛ አግባ አለችው ባል ተይ ይከፋሻል አላት ሚስት በፍጹም አይከፋኝ። ➘አንተን የሚያስደስት ያስደስተኛል አለችው ባልም እሺ አለና አንድ ቀን ከሌላ ቦታ አደረ ከዚያም በጧት ወደቤት ሲመጣ ከመንገድ እንስራ (ሼክላ)ይገዛናልብስ አለባብሶ ቤቱ አምጥቶ አንደኛው ክፍል ውስጥ ያስገባና ይቆልፍባታል!! ➘መስኮቱን ከፍቶ ለመጀመሪያ ሚስቱ ምግብ…
አይ እኛ ሴቶች አለመሳቅ አይቻልም ህዕ¡

ግን ስለመረቀናችሁ አቅማችሁ የማይችለዉ ነገር ለማድረግ አትሩጡ ሴቶችዬ! ተግባብተናል አይደል¡¿
ባል ከሚስቱ ጋር ስሜታዊ ጣዕምን ለመጠቃቀም ሲል ጡቷን በአፉ አስገብቶ ለአራት የተለያዩ ግዜያት ቢጠባው ሚስቱ ሃራም ትሆንበታለችን?

በሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን(ረሂመሁላህ)

አንዲት እንስት የራሷ ያልሆነን ህፃን ልጅ በደንቡ መሰረት ካጠባች እናት እንደምትሆነው ይታወቃል። ባልስ የሚስቱን ጡት መላሱ ብሎም መጥባቱ እንዴት ይታያል? እንደሚታወቀው ሰዎች እርስ በርሳቸው በጥብቅ ከሚዛመዱባቸው ምክንያቶች አንዱና ዋነኛው መዋለድ መሆኑን ኢስላም የሚያስተምር ሲሆን ቀጣዩ የዝምድና መንገድ ደግሞ ወላጅ እናት ያልሆነችን እንስት ጡቷን በመጥባት የሚገኝ ዝምድና መሆኑን አስምሮበታል። ይህም በህፃንነት የጡት መጥቢያ እድሜ ወቅት ከአምስትና ከዚያ በላይ ለሆነ የተለያዩ ግዜያት ወተት ያለው ጡቷን መጥባቱ መሆኑን ኢስላም በግልፅ ያሰፈረው ጉዳይ ነው። በዚህም ሰበብ ጡቷን ያጠባችው እንስት ለህፃኑ እናት ስለምትሆን ልጆቿም ወንድሞችና እህቶች ይሆኑታል። ሌላውም ዝምድና እንደየ ደረጃው ይቀጥላል። በውልደት ተዛምደው እንዳይጋቡ እንደሚከለከሉ ሁሉ ጡት በመጥባት የተዛመዱትም አንዳቸው አንዳቸውን እንዳያገቡ ይታገዳሉ።

ሌላው ርእስ በባልና ሚስት መሃል የሚፈጠረው እርካታ ሲሆን ከታላላቆቹ የጋብቻ ፋኢዳዎች አንዱና ዋነኛውም ይኸው አንዳቸው ባንዳቸው መርካታቸው፣ መደሰታቸውና ማረፋቸው ነው። ከዚያም ልጅ ማፍራትና ሌሎቹ ተከታይ ጥቅሞች ይሆናሉ። ይህንን የህይወት ማጣፈጫ እርካታ በተፈለገው መልኩ እንድንቋደስ ምንም ጉድለት የሌለበቱ ሸሪዓችን እንዳሻችን እንድንጠቃቀም መንገዱን ጠቁሞናል። ስርኣቱንም አስተምሮናል። በዚህም ዙርያ ከተወረዱት መረጃዎች አንፃር አንዳንድ ሊፈጠሩ የሚችሉ ብዥታዎችንም አስወግዷል።

ለምሳሌነትም ባዕድ የሆኑ ግለሰቦች ሸሪዓዊ ጋብቻን ከመሰረቱ በኋላ የራሱን ወይም የሚስቱን ወይም ለጋራ ስሜት ሲል ባል የሚስቱን ጡት ቢልስ ቢጠባ የሚከሰት ዝምድና ይኖራልን በሚል አንዳንድ ተማሪዎች ምሁራንን መጠየቃቸው አልቀረም። ከተጠያቂ ምሁራን መካከልም አል አል'ላማ ሙሐመድ ቢን ሷሊህ አል ዑሰይሚን የሚባሉ ታላቁ የክፍለ ዘመኑ ፈቂህ አንዱ ናቸው።(ረሂመሁላሁ ተዓላ) ለዚህም ቀጣዩ ጥያቄ ቀረበላቸውና ጥበባዊ ምላሻቸውን ለግሰዋል። “ባል ከሚስቱ ጋር ስሜታዊ ጣዕምን ለመጠቃቀም ሲል ጡቷን በኣፉ አስገብቶ ለአራት የተለያዩ ግዜያት ቢጠባው ሚስቱ ሃራም ትሆንበታለችን? ”

ምላሽ:- "ለአላህ ምስጋና ይገባውና ሃያሉ አምላካችን አላህ … ስሜታቸውን ለማርካት ሲል ባል በሚስቱ እንዳሻው እንዲጠቃቀም የተፈቀደ አድርጎላቸዋል። በምን መልኩ ሊገናኛት እንደሚገባው በተመለከተም ከእንከን ሁሉ ፅዱ የሆነው አምላካችን አላህ “ ሴቶቻችሁ ለናንተ እርሻዎቻችሁ ናቸውና እርሻዎቻችሁን እንዳሻችሁ እረሱት። ” ብሏል። ይሁንና “ እርሻዎቻችሁን እረሱት…።” የሚለውን ቃል ጠንቅቀህ ልትረዳው ይገባል። "እርሻ" የሚለው ቃል የቡቃያ መውጫና ዘር ማፍሪያ ቦታ ማለት ነው። እሱም የሴቷ ብልት ማለት ነው።
ለዚህም ባል ሚስቱን በብልቷ ብቻ በመገናኘት ሊያጣጥሙት ይገባል። በዚህም ሂደት ከፊት ለፊት በኩል ቢገናኛት፣ ከኋላዋ በኩል ቢገናኛት ወይም ቆማም ቢገናኛት እንዲሁም ተጋድማ ቢገናኛት ባጠቃላይ በየትኛውም አኳኋን ቢገናኛት መስፈርቱ በብልቷ በኩል መገናኘቱ ነው። እንዲሁም እንዳሻው ቢያቅፋት፣ ቢስማት፣ ቢተሻሻት ምንም የተገደበ ነገር የለውም። ነገር ግን በየወር አበባዋ ግዜ የሩካቤ ሥጋ ሊፈፅምባት አይገባውም። ልክ እንደዚያው በመቀመጫዋ በኩልም ሊገናኛት ሙሉ በሙሉ አይፈቀድለትም። መልእክተኛው(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ሴቶቻችሁ እርሻዎቻችሁ ናቸውና እርሻዎቻችሁን እንዳሻችሁ እረሱት።” የሚለው የፈጣሪያችን የአላህ አዝዘ ወጀልለ መመሪያ ሲወርድና ለሰሃቦቹ ሲያብራሩት በቡኻሪ [8/154] ና በሙስሊም [4/156] ዘገባ “ብልት ውስጥ እስከ ሆነ ድረስ ከፊትለፊት ሆነ ከኋላ በኩል ተገናኟቸው።” ባሉት መሰረት እንዲሁም ኢብኑ ዐዲይ [1/211] ዘግበውት አል አልባኒይ በአዳቡ-ዝዚፋፍ [105] ላይ ሰሂህ ባሉት መሰረት “ሴቶቹን በመቀመጫዎቻቸው የሚገናኛቸው ሰው እርጉም ነው።” ብለዋልና በየትኛውም አቅጣጫና አኳሃን የዘር መግቢያና የልጅ መውጫ የሆነውን መንገድ (ብልትን) መገናኘት የተፈቀደ ነው። ይህ የትዳር መዘውርና በትዳር ውስጥ የሚከሰቱትን በርካታ ጉድለቶች በመሸፈን የሚያቻችለው የእርካታ ጥበብ ከዚህ ውጪ መንገድ የለውም። እርካታውም የጋራ መሆኑን ልብ ካልነው ከላይ የተነሳው ርእስ ለማረሻውም ሆነ ለእርሻው ግቡን መምታት ምን ያህል አጋዥና አስፈላጊ እንደሆነም በዚሁ አጋጣሚ እንገነዘባለን።

በዚህም መሰረት ይህ አጠቃላይ የሆነ መርህ ነውና አንድ ግለሰብ የሚስቱን ጡት በመላስ፣ በመጥባት ስሜቱን ቢያጣጥመው ምንም ችግር የለበትም። በዚህም ሰበብ (ልክ እንደ ህፃንነቱ ዘመን ሁኔታ) እርም አትሆንበትም። ጡቷን ሲጠባው (ፈሳሽ ኖሮት ቢስበው) እንኳ እርም አትሆንበትም። ይህ አንግዲህ የአብዛኞቹ ሊቃውንት (ጁምሁር አህሉል ዒልም) አቋም ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጡት መጥባት ሰበብ አንዷ በአንዱ ላይ እርም የምትሆንበት መስፈርቱ ከጡት መጣያ ወቅት በፊት (እድሜው ሁለት አመት ከመሙላቱ በፊት) የሆነ እንደሆን ነው። ከጡት መጣል (ከጡት መጥቢያ ዘመን) በኋላ ከሆነ እርም አያደራርግም። ምንም አይነት ተፅዕኖም አይፈጥርም። ስለዚህም ጡት የመጥባት ደንቡ ህፃኑ አምስቴ እና ከዚያ በላይ ለሆነ ግዜ መጥባት ሲኖርበት ከአምስት ግዜ በታች ከሆነ በፍፁም ምንም አይነት ተፅዕኖ አይኖረውም። ይህ ክስተት ያለ ወተት የማይወስድ ህፃን ልጅ ሆኖ እንኳን ከአንዲት ሴት ለአራት ግዜያት ያህል ብቻ ቢጠባ በዚህ ሰበብ ልጇ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም አንዱን ባንዷ ላይ እርም የሚያደራርገው (ወንድምና እህት አደራርጎ ጋብቻ የሚያከላክለው) ለአምስት ግዜያት በመጥባት እንጂ ከዚያ በታች ከሆነ አይደለምና።»

የሸይኽ ሷሊህን መልእክት በቀጣዩ ማስፈንጠርያ ያድምጡት
➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://m.youtube.com/watch?v=pCzIaiqGoH0 2:40 min

Abu fewzan
©ተንቢሃት
ሁሉም ነገር አልፎ መልካም ቀን ይመጣል፡
አላህን ያመነ ምን ፈልጎ ያጣል፡
አደራ ውድዋ ፅናት በዕምነትሽ  ላይ፡
ከጨረቃ በላይ ደምቀሽ እንዲትታይ፡
ሴት ልጅ ወጣ ወጣ ብላ ካልታየች ባል አታገኝም የሚል ማህበረሰብ ውስጥ ስላለን!!
.
.
.
የሀያዕን አስፈላጊነት ደጋግመን እንገልፃለን!!


✍️
📍የሀያዕ አንገብጋቢነት➘➘
t.me/abuUseyminabdurehman/12616

📍ሀያዕ(አይን አፍርነት)➘➘
t.me/https_Asselfya/4090

📍እህቶች አይን አፍሮች ሁኑ!
t.me/https_Asselefya1/7047

📍የእናታችን ዓኢሻ ሀያዕ➘➘
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/5662


✍️ይቀጥላል.............
......''ርዕስ የለውም''....

ብሶት ከውስጤ ላይ እየቆነጠጠኝ፡
መሮኝ ላነባ ስል ሳቄ እያመለጠኝ፡
በፊት በኋላዬ ሀዘን እየፍቀኝ፡
አልመስለውም ለሰው ደስታ የናፈቀኝ

❝ኑር❞
https://t.me/nuredinal_arebi
https://t.me/nuredinal_arebi
هـدايـة المـسـتـفـيـد ١٨
𝕬𝖇𝖚 𝖀𝖘𝖊𝖞𝖒𝖎𝖓
☑️አዲስ የተጂዊድ ኪታብ ቂርአት
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️

📚ኪታብ ሒዳየቱል ሙስተፊድ

♻️ክፍል  ⓵⓼

📜የኪታብ  pdf👇
t.me/https_Asselefya1/10408

🎤በአብዱረህማን አቡ ዑሰይሚን

   ➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
https://t.me/https_Asselefya1
ኡኽታዬ ቆራጥ ጀግና ሴት ሁኝ ለምንም አትሸነፊ ወደፊት እንጂ ወደኃላ አትጓዢ  ሁሌየም ቢሆን እራስሺን ሁኝ በራስሺ ተማመኝ    በእውቅትሺ አትመፃደቂ ነገሮችን ሁሌየም ቀለል አርገሺ እይ  በገንዘብሺ አትመፃደቂ ገንዘብ የሃጥያት ስብስብ ነውና በአግባብ ተጠቀሚበት   ጦይብ ሁሌየ ንፁህ ልብ ይኑርሺ እራስሺን ከማንም ጋ አታንሳፅር የራስሽ ማንነት ይኑሩሽ ቻይ አንጄት ታጋሺ ልብ ሆደ ስፊ ሁኝ በጥንካሪሺ ልክ ተጓዢ  ስትኖሪ የእውነት ኑሪ ስትስሪ ትርጉም ያለው ሾል ሾሪ  ሁሌየም በእምነትሽ ጠካራ ሁኚ ችግርሽን እና ሀዘንሽን ለአሏህ እንጂ ለሰዎች ከመናገር ተቆጠቢ በፍቅር ተማምንሺ ኑሪ! ።

𝐓𝐞 «https://t.me/https_Asselefya1
ማንም ከማንም አይበላለጥም ኢላ ቢተቅዋ
አንች ከማንም መብለጥ ከፈለግሽ አሏህን አጥርተሽ ከማወቅ እና ነብያችን ያሉትን ከመስራት አትዘናጊ አንች ማለት ውድ እንስት ነሽ ኡክቲ ተከብረሽ እምኖሪው ጌታሽ ያዘዘሽን ስታከብሪ እና ወደ ጌታሽ ስትተናነሽ ነው ያንች ተምሳሌቶች እነማን እንዴሆኑ ጠንቅቀሽ ልታቂ ይገባሻል አንች ማለት ውድ የተነጠር ወርቅ ነሽ እህቴ!!


𝐓𝐞« https://t.me/https_Asselefya1
📲 አዲስ አፕልኬሽን ተለቀቀ

📖  الإرشاد إلی صحیح الإعتقاد

➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
t.me/abu_fewzan_abdu_shikur/2955

t.me/abu_fewzan_abdu_shikur/2956
Audio
2-تجريد المتابعة للرسول-صلى الله عليه وسلم-.


🎙الشيخ سليمان بن سليم الله الرحيلي


http://t.me/https_Asselefya1
የአላህ!

እጃችን አንተ የምትጣላዉን ነገር ከሚጽፍ  አይናችን አንተ የከለከልከዉን ሁሉ  ከማየት አንተ ጠብቅልን ።

✍️
☞ወደ ከፋ ነገር ሳያደርስ የሶሻል ሚድያ ጉዳይ ይታሰብበት‼

~~
☞የሶሻል ሚድያ አጠቃቀማችንን ቶሎ ካላሰብንበት ሊያጠፋን ነው።አንዳች የተጠቀምንበት ነገር ሳይኖር ከዛ ከዚህ ስንበን ጊዚያችንን ጥንቅቅ አድርጎ በልቶታል።ከዛሬ ነገ እንማርበታልን ብለን የገዛነውን ኪታብ አቧራ ቦኖ አጥቁሮታል።የነበረንን ሽርፍራፊ ስዓት ሁሉ አሉ የሚባሉ ሚድያዎችን ተቀራምተንበታል።አንድ ሚሴጅ "ጢርር"ባለች ቁጥር #ፌስቡክ ስንኳትን ከዛ ተመልሰን #ቴሌግራም ስንገባ፡ከዛ ስንወጣ #ዋትስአፕ ትዝ ሲልን፡ብዙ ሳንቆይ #በኢሞ ሲደወል ለርሱም መልስ ስንሰጠ:  አንድ ነገር ሳንጠቀም ይሄው በሚድያው እንደወጣን ቀርተናል።አሏሁል ሙስተዓን።

☞ይባስ ብሎ ሁሉም እንደ ሞባይሉ የደረሰውም ያልደረሰው አንዳንድ #ቻነል፣ግሩፕ በየ'እጁ ያዘ ከዛ ቡኃላ የትም በሚድያው ጽሁፍ ሲያማርጥ ይውላል።አሁን ሁሉም በየግሉ የሚድያ አካውንት ስለከፈተ ፡ና"ተማር ስትለው ቆይ ቢዚ ነኝ ይላል ስትፈልግ ግን የምታገኘው እዚሁ ሰፈር ሲቃብዝ ነው።ሌላኛው እንደምንም እየተልመጠመጥ አንድ ደርስ ይጀምራል ሳያጋምሰው ከስራ ጋር አልተመቻቸልኝም ይላል።እህ" ብለህ ስጠይቅ እዛ #ዋትስአፕ የከፈተው ግሩፕ ላይ የሚለቅበት ነገር ጨንቆት ከዛም ከዚህ ሲመራርጥ ታገኘዋለህ።ሌላኛው #ኢሞ ላይ ተለጥፎ ወጪ ወራጁን ሲመለከት ስዓት ያልፈዋል በዛው ማቆራረጥ ያበዛል ሰልችቶ በዛው ይጠፋል።ይሄ ሁሉ አልላቀቅ ያለን ፈተና ነው።

☞መጥፋት ካለበት እና ካልጠቀመ እንኳን አላቅማችን የተከፈተው ቻናላችን አይደልም።የግል አካውንታችንም ይጠፋል እና የቻነሎችና የግሩፖች ነገር ይታሰብበት።ሳይቀደሙ ነው መቅደም።

✍አቡ_ዑበይዳ ነኝ
https://t.me/AbuOubeida
https://t.me/AbuOubeida
እወድሻለሁ ስትላት  አመሰግናለሁ ከምትል ሚስት ይጠብቃችሁ ሸባቦች¡¡


©መልካም ለይል¡