قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
912 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
Forwarded from ስለ ቀልባችን
አላገባሽም!
~
ቃል መግባት ማለት ተራ የቃላት ድርድር አይደለም፤ ቃል መግባት የነፍስን ውል መፈረም ማለት ነው። በተለይም ትዳርን የመሰለ የተባረከ ስምምነትን አስመልክቶ ቃል ገብቶ፣ የሴት ልጅን ተስፋ ሰቅሎ፣ ለወራትና ለዓመታት በአጉል ተስፋ አደንዝዞ፣ በመጨረሻም ያለምንም በቂ ምክንያት «አልፈልግሽም» ብሎ መተው በሰውም በአላህም ፊት የሚያስጠይቅ ታላቅ በደል ነው።

አንተ ቃልህን አጥፈህ ጀርባህን ስታዞር፣ የሰረቅኸው የጥቂት ሰዓታት ወሬ ሳይሆን ውድ የህይወት ዘመኗን እንደሆነ ታውቃለህ? ላንተ ስትል ስንት የመጣላትን፣ ስንት የመከሩላትን፣ ስንት የፈለጓትን ትዳሮች «ሰው አለኝ፣ ቃል ገብቶልኛል» በሚል እምነት በሯን ዘግታ ስትጠብቅህ ኖራለች። አንተ ዛሬ «አልሆነም» ስትል እሷ ግን ያመለጧትን እድሎችና የባከነውን ወጣትነቷን የት ታገኘዋለች?

በነገርህ ላይ...የሴት ልጅ እንባ መሬት ላይ አይፈስም፤ በአላህ ፊት ትልቅ ዋጋ አለው። አንተ ዛሬ በምክንያት ብዛት ራስህን ልታታልል ትችላለህ፣ ነገር ግን ልቧን የሰበርከው ያቺ ምስኪን ሴት ሌሊት ላይ አላህ ፊት ቆማ ስታለቅስ በአንተና በእሷ ዱዓ መካከል ምንም መጋረጃ የለም። አላህ «ተበዳይን እረዳለሁ» ብሎ ቃል ገብቷል።የተበዳይ እንባ የሰማይና የምድርን ዙፋን ያናውጣል፤ የዛሬው ቀልድህ የነገው የህይወትህ ጨለማ እንዳይሆን ፍራ!

አላህ ፊት ስትቆም የምትጠየቀው ስለ ሰገድከው ብቻ አይደለም፤ ስለሰበርከው ልብ፣ ስለበላኸው ጊዜ፣ በውሸት ተስፋ ስላቆሰልከው ስሜት ጭምር ነው። በቂ ምክንያት ሳይኖርህ ቃልህን ማፍረስህ "ሙናፊቅነት" እንደሆነ ታውቃለህ? የሙናፊቅ አንዱ ምልክት "ቃል ገብቶ ማፍረስ" ነውና።

ዛሬ አታለልኳት ብለህ ትስቅ ይሆናል፤ ነገር ግን በደል ተራ ላይ ተቀምጣ የምትጠብቅ ዕዳ ናት። በዘራኸው ልክ ታጭዳለህ። ዛሬ በአንተ ምክንያት የወጣው የሴት ልጅ እንባ፣ ነገ በአንተ ህይወት፣ በስራህ፣ ወይም በምትወዳቸው ሰዎች ላይ መቅሰፍት ሆኖ ሊመጣ እንደሚችል አትዘንጋ። የአላህ ሂሳብ ዘገምተኛ ቢመስልም ጥብቅ ነው።

አሁንም ጊዜ አለህ! የሴት ልጅን ህይወት በማበላሸትህ አላህ ፊት ከመቆምህ በፊት፣ ያቺን ምስኪን ይቅርታ ጠይቃት፤ ካልሆነም የበደልከውን በደል ካስ። የሰው እንባ ይዞ መኖር መጨረሻው ጥፋት ነው። ቃል ማፍረስ "ክህደት" ነው፤ ክህደት ደግሞ የጀግና ሳይሆን የፈሪና የባንዳ ስራ ነው።

ልብ በል! ያቺ ዛሬ የምታለቅሰው ሴት፣ ነገ በአላህ ፊት ከሳሽህ ሆና ስትቆም ምንም አይነት የምክንያት ድርድር አይሰራልህም።
~
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
🧷አንዴ የከዳሽ ሰው ሁሌም ይከዳሻል
የባህርን ውሃ ጨዋማነት ለማረጋገጥ
ሁሉንም መጠጣት አይጠበቅብሺ።


https://t.me/https_Aselefya
👍2
' የኔ ውድ እህት '

ጊዜ ወድ ነዉ ጊዜሽን በአግባቡ ተጠቀሚበት🌷

https://t.me/https_Aselefya
"🌷          የኔ ጀግና ሴት       🌷"

ዓላማሽ ትልቅ ሲሆን መንገድሽም ረጂም ይሆናል"
ትልቅ ህልም ካለሽ ትልቅ ህልምና ትዕግስት ይፈልጋል።

" ሁሌም ለዓላማሽ ጠንካራ ሁኚ "

 
https://t.me/https_Aselefya
🧷የተሰበረን የሚጠግን
የወደቀን የሚያነሳ
ያዘነን የሚያፅናና
ያጎነበሰን የሚያቀና
ላጣ የሚሰጥ
አሏህ ሙሉ ምስጋና ይገባው ።

    
https://t.me/https_Aselefya 
💯2
" 🍃                  የኔ ልዩ እህት            🍃 "

🧷ሰዎች ከአንቺ እንዲማሩ እና
አንችም ከእነሱ እንድትማሪ ተቀላቀያቸው

ሰዎች ልክ እንደ ዝግ ሳጥኖች ሲሆኑ
ብርቅዬ የሆኑ ክምችቶችን በውስጣቸው
ታገኛለሽ"
  🍃ከፊሉ ባዶ እንኳን ቢሆኑ
ለምን ባዶ እንደሆኑ ትማሪያለሽ ።

https://t.me/https_Aselefya
🧷  ያልፋል ብለን እንደጠበቅን ብዙ ዘመናት አለፉ''

አሁንም ሀሳባችን አልቀየርንም "
ያልፋል"

https://t.me/https_Aselefya
لا تغتر بهؤلاء الأربع
حاتم الأصم رحمه الله
🧷ክንፏ ተሰብሮ
ሰማይ ሰማዩን እንደምታይ ወፍ
ናፍቆትን የሚገልፅ ነገር አለ ወይ!
💧

https://t.me/https_Aselefya
🍓4
🧷صَاحِب مَن تُصَاحِب
የፈለግከውን ተወዳጅ،

فَواللهِ الذي عَلَىٰ العَرشِ اِستَوَىٰ
በዛ ከአርሹ በላይ ከፍ ባለው ጌታየ እምላለሁ

لَن يُصاحِبكَ فِي قَبرِكَ إِلَّا صَاحِبٌ وَاحِد
በቀብርህ ውስጥ ከአንድ ነገር ውጭ ጓደኛ ሊሆንህ አይችልም"

أَلَا وَهوَ عَمَلكَ الصّالِح
አዋጅ እሱም መልካም ስራህ ብቻ ነው"

فَأَحسِن صُحبتهُ كَي يُحسِن صُحبتك فِي قَبرك،
ጓደኝነትህን አሳምር በቀብር ውስጥ ጓደኛነት ያምርልህ ዘንድ"

https://t.me/https_Aselefya
• قال الشيخ صالح الفوزان - حفظه الله :

ما دام أنّك على الحقّ فلا يهمّك كلام النّاس والمخذّلين، أمّا إن كنت على الخطأ، فتراجع ولو مدحوك، لا تصبر على الخطأ، وتثبت على الخطأ، ولو مدحوك وشجّعوك، لا يغرّك هذا.

|[ شرح فتح المجيد ]|.

(٢٤/ ربيع الأوّل/ ١٤٣٩)
🍓1
🧷የሞኝ ሞኝ ሴት ማለት ሚስቱን ከድቶ 
ከእርሷ ጋር የሆነን ወንድ የምታምን ሴት ናት
ነገም ያንች ተራ ነው እሺ"እህቴ
ሰው የዘራውን ነው የሚያጭደው'
በሰው ትዳር አትግቡ እህቶቼ የራሳችሁን ነሲብ ጠብቁ
።

https://t.me/https_Aselefya
💯4
'            ባል ሁን! '


🧷ምርጥ ባል ማለት ሲሞት ብቻ እንጂ
ሚስቱ የማታለቅስበት ጀግና ወንድ ነው።


https://t.me/https_Aselefya
🧷የዛሬ ትጋት ለነገ እረፍት ነው
መትጋት አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ነዉ"


"የኔ ልዩ ሴት 🌷ሁሌም ቢሆን ለዓላማሽ ተጊ ሁኚ"


https://t.me/https_Aselefya