قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
914 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
12--አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ(ሙኽተሶር)
በ ወንድም አቡ ሱፍያን
📚 አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ(ሙኽተሶር)
مختصر الداء والدواء

-ክፍል 12-
🎙በ ወንድም አቡ ሱፍያን
t.me/Sle_qelbachn1
ተግባር ያበላሸውን ንግግር አያሥተካክለውም።

~
أشغلي نفسكِ بما ينفعكِ في الدارين، تزودي بالعلم النافع والعمل الصالح ولا تكوني من الغافلين في ثوب العابدين.

https://t.me/https_Aselefya
هذه الحياة الدنيا تبدأ ببكائك وتنتهي بالبكاء عليك"

የዱኒያ ህይወት ባንተ ለቅሶ ትጀምርና
ባንተ ላይ በማልቀስ ታልቃለች ።
 
~         
💯3
Forwarded from ስለ ቀልባችን
ራስን በራስ ማርካት!–ክፍል 1―
~
በርግጥም የምንኖርበት ዘመን ከባድ ነው። ቴክኖሎጂው የመጣው ህይወትን ሊያቀል ነበር፤ ነገር ግን ሰይጣን ለክፉ ተጠቅሞበት በጣትህ ጫፍ በሚነካ ስክሪን አማካኝነት ወደ መኝታህ ገብቷል። ዛሬ ላይ ብዙ ወጣቶች በድብቅ የሚያለቅሱበት፣ ከሰው ተደብቀው አንገት የሚደፉበት፣ የህሊና እረፍት ያጡበት ትልቁ በሽታ «ኢስቲምናእ» (ራስን በራስ ማርካት) አንዱና ትልቁ የወጣቱ ችግር ነው።

ይህ ተግባር ዝም ብሎ መጥፎ ልማድ ብቻ አይደለም፤ የወጣትነትን ወዝ የሚጠጣ፣ ከአላህ የሚያጣላ፣ የነገን ተስፋ የሚያጨልም «የድብቅ ካንሰር» ነው። እስቲ ቆም ብለህ ተመልከት! ጌታችን አላህ የሰው ልጅን ሲፈጥር ክብር ሰጥቶታል። ስሜትንም የሰጠህ ለተፈቀደ ትዳርና ለዘር መተካት እንጂ በእጅህ ልትጫወትበት አይደለም። በቁርኣን ውስጥ አማኞችን ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-

«እነዚያም እነሱ ብልቶቻቸውን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ በሚስቶቻቸው ወይም እጆቻቸው በያዙት (ባሮች) ላይ ሲቀር፡፡ እነርሱ (በነዚህ) የማይወቀሱ ናቸውና፡፡ ከዚያም ወዲያ (ሌላን) የፈለጉ ሰዎች እነዚያ እነሱ ወሰን አላፊዎቹ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አል-ሙእሚኑን 5-7)

ከዚህ አያ መረዳት እንደምንችለው ከትዳር ውጪ ስሜትን ማውጣት «ወሰን አላፊነት» ነው። ነብያችን(ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ወጣቶችን አግብተው ራሳቸውን እንዲጠብቁ፣ ካልቻሉ ደግሞ እንዲጾሙ አዘዋል እንጂ ራስን በራስ ማርካትን አልፈቀዱም።

ውድ ወንድሜ! ስሜትህን በተከለከለ መንገድ ባወጣህ ቁጥር፣ ከአላህ እዝነት ትርቃለህ። ዱዓህ እንዳይሰምር፣ ዒባዳህ እንዳይጣፍጥህ የሚያደርገው ይሄው የረከሰ ተግባር ነው።አላህ የሰጠህን የተከበረ አካል ማርከስ በእስልምና የተጠላ ተግባር ነው።

ከ አላህ ጋር ከማጣላቱ ባሻገር ይህ ሱስ ከአደንዛዥ ዕፅ ባልተናነሰ በአእምሮ ላይ ከባድ ተጽእኖ አለው። ዶክተሮች ይህን ተግባር በሚፈፅሙ ሰዎች ላይ የሚከተሉትን አደጋዎች ያስቀምጣሉ፡-

📎1ኛ―የአእምሮ ባርነት (Addiction): ልክ እንደ ኮኬይን አእምሮህ ላይ የደስታ ሆርሞን (Dopamine) በውሸት እንዲረጭ ስለሚያደርግ፣ አእምሮህ ይደነዝዛል። ነገ ከትዳር አጋርህ ጋር የምታገኘው ተፈጥሯዊ ደስታ አይጣፍጥህም።

🕹2ኛ―የማስታወስ ችሎታ መቀነስ እና የመርሳት ችግር፡ አእምሮ ሁሌም በወሲባዊ ቅዠት ስለሚጠመድ፣ ለትምህርትና ለቂርኣት እንድሁም ለቁምነገር የሚሆን ቦታ ያጣል። ብዙ ተማሪዎችም ሆኑ ብዙ ዒልም ፈላጊዎች ትምህርታቸውን እና ዒልም መማራቸውን የጠሉት በዚህ ምክንያት ነው።

😞3ኛ―የጭንቀት እና የደብርት በሽታ (Depression): ድርጊቱን ከፈጸምክ በኋላ የሚሰማህ የጥፋተኝነት ስሜት ራስን መጥላትና ባዶነት ወደ ድብርት ይወስዳል። "እኔ ርካሽ ነኝ" ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል።

👨‍👦4ኛ―የትዳር ህይወትን ማበላሸት፡ ራስን በራስ በማርካት የለመደ ሰው፣ በትዳር ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ግንኙነት መፈጸም ይከብደዋል (Sexual Dysfunction)። ለወንዶች የቶሎ መጨረስ ችግር (Premature Ejaculation) ዋነኛ መንስኤው ይህ መጥፎ ልማድ ነው።

🎯5ኛ―የሰውነት መዛል እና የጀርባ ህመም፡ የወጣትነት ጉልበትህን በከንቱ እያፈሰስክ ስለሆነ፣ ለእድገት የሚሆን ጉልበት ታጣለህ። አይንህ ይቦዝዛል፣ ጉልበትህ ይንቀጠቀጣል፣ኑርህም ይጠፋል…ከሁሉም በላይ የሚያስፈራው ግን የአኼራ ጉዳይ ነው።

ውድ ወንድሜ! እስኪ ለአፍታ ቆም ብለህ አስብ!ያ በጨለማ የቆለፍከው በር ሰዎች እንዳያዩህ ነው አይደል? ግን የዓለማቱ ጌታ አላህ እየተመለከተህ እንደሆነስ ዘነጋህን? እጅህ፣ እግርህና ብልትህ ነገ በአላህ ፊት «እንዲህ አደረገብን»ብለው ሲመሰክሩብህ ምን ልትመልስ ነው? ያንተ እኩዮች ቁርኣን ሲያነቡ፣ ኢልም ሲቀስሙ፣ በትዳር ሲረጋጉ፤ አንተ ግን መጸዳጃ ቤት ውስጥ ወይም አልጋህ ላይ ከራስህ ጋር ትታገላለህ። ይህ ላንተ ክብር አይመጥንም!

የወደፊት ሚስትህ ንጹህ ሆና እየጠበቀችህ፣ አንተ ግን አላህ በሐላል ላይ እንድታውለው የሰጠህን ውድ ስጦታ በቆሻሻ ቦታ እያፈሰስከው ነው። ነገ ትዳር ስትይዝ የምትሰጠው ፍቅር፣ የምትሰጠው ጉልበት ከየት ይመጣል? ጨርሰህው እኮ ነው!

ሞት በዚያ ሁኔታ ውስጥ ቢመጣስ?
አላህ ይጠብቀንና፣ ያንን ቆሻሻ ቪዲዮ እያየህ ወይም ያንን ሐራም እየፈጸምክ ነፍስህ ብትወጣ፣ ከአላህ ጋር እንዴት ትገናኛለህ? ወንድሜ... እህቴ... ይሄ ጉዳይ ቀልድ አይደለም። የእሳትና የጀነት ጉዳይ ነው።

🔍መፍትሄው ምንድን ነው?
☑ተስፋ አትቁረጥ! አላህ መሐሪ ነው። ዛሬውኑ ቆርጠህ ከተነሳህ መመለስ ትችላለህ።ወሏሂ ከዚህ ሱስ መውጣት ከባድ እንደሆኑ ብታስቡም በ አላህ ከታገዛችሁና ከወሰናችሁ እጁግ በጣም ቀላል ነው።

☑በንፁህ ልብ አልቅሰህ አላህን ምህረት ጠይቅ። «ጌታዬ ሆይ! ተሸነፍኩ፣ አቅም አነሰኝና እርዳኝ» በለው።

☑ብቸኝነትን አጥፋ። ይህ ሱስ የሚመጣው ለብቻ ስትሆን ነው። ከሰዎች ጋር ተቀላቀል። ስልክህን መኝታ ቤት አታስገባ።

☑የአይን ዚናን ተጠንቀቅ።እይታህን ስበር። በቲክቶክና በፌስቡክ የሚመጡ ስሜት ቀስቃሽ ምስሎችን አግድ (Block)። አይን የልብ መስኮት ናት።

☑ጾም እና ስፖርት ስራ። ነብያችን እንዳሉት ጾም ጋሻ ነው። ስፖርት ደግሞ ትርፍ ጉልበትህን በጥሩ ነገር እንድታወጣው ይረዳሃል።

☑ትዳርን አስብ። አቅሙ ካለህ አግብ። ካልቻልክ እራስህን ለትዳር አዘጋጅ እንጂ በሐራም አትጨርስ።

🫀ያ አላህ! በዚህ የሱስ ሰንሰለት ተጠፍረው የሚሰቃዩ ወንድም እህቶቼን አንተ ድረሰላቸው። በወንጀል የጠቆረውን ልባቸውን በምህረትህ ብርሃን አፅዳው። የዚህን ሱስ አስከፊነትና አስጠያፊነት አሳይተህ፤ ከልባቸው ጠልተው እንዲርቁትና በምትኩ የአንተን ፍቅርና የኢማንን ጣፋጭነት አላህ ይለግሳቸው። አላህ ሆይ! ወዳንተ መመለስን ለከበዳቸው ሁሉ እጃቸውን ይዘህ ወደ ብርሃን ማውጫው መንገድ ምራቸው።
t.me/Sle_qelbachn1
t.me/Sle_qelbachn1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍1💯1
🧷መልካም ትዕግስት ብሎ ማለት  በችግር መሀል ሁነሽ እየተፈተንሽ"
ልብሽ ግን አልሀምዱ ሊላህ ሲል ነዉ።

https://t.me/https_Aselefya
💯1
🧷ችግር እንደ ማዕበል ነው ፤ ታግሰው ከጠበቁት ያልፋል

ፈተና እንደ ዱላ ነው፣ ጨክነው ከቻሉት ይሰበራል

መከራ እንደ ፍጡር ሁሉ ነው፣ አጀልና የጊዜ ገደብ አለው ያበቃል፡

የጠበበ ነገር መስፋቱ አይቀርም
አንቆ የያዘህ ነገር ይረግባል
ያሳሰበህ እንደ ጉም ይተናል
ያስጨነቀህ ጉዳይ እፎይታ ይኖረዋል

አንዳንድ ጊዜ ተስፋ"አንዳንዴ ደግሞ ባዶነት
አንዳንዴ ጨለማ" አንዳንዴ ደግሞ ብርሃን እየታየን
ዕድሜያችንን በዚሁ መሃል እንጨርሳለን"

ህይወት በእየፍርጇ ለየቅል ናት" አንዳዱ የሚታከምበት ገንዘብ ሀብት ኑሮት ከማይድን በሽታ ጋር ይሰቃያል"
አንዳንዱ ደግሞ በገንዘብ እጥረት ምክኒያት ታክሞ መዳን የሚችለውን በሽታውን  ተው ማረኝ እያለ  አብሮት ይኖራል።

~
~ ምቀኛ ሰው ቁጭቱ ረጅም እድገቱ ምንም ነው።
ኢማም አሽሻፊዒይ (ረሒመሁላህ)

🍁
🍓1
🧷የኔ ውድ እህት "

አማኝ ሰው መቸም ቢሆን ከአላህ እዝነት ተስፋ አይቆርጥም"
ጠካራ ሁኚ አብሽሪ ተስፋሽ ቃሉ ነዉ።


https://t.me/https_Aselefya
🧷قَالَ شَيِّخ الإِسَلام ابن تَيِّمَية-رَحِمَهُ اللَّه-:

«أَن حَقيقة التَوحِيد أَن تَعبد اللَّه وحدهُ ، فَلا يُدعى إِلَّا هُوَ ، ولا يَخشى إِلا هُو ، ولَا يَتقى إِلَّا هَو ، ولا يتوكل إِلَّا هُوَ ، ولا يَكُون الدين إِلا لَهُ ، وأَلا نَتخذ الملائكة والبنين أَربابًـا فكيف بالأئمة والشُيُّوخ والعُلمَاء والمُلوك وغيرهم»

  مِنهاج السُّنة(٣/٤٩٠)

https://t.me/https_Aselefya
🧷ትዳር ውስጥ ከመግባት በፊት"
ትዳር ምንድን ነው የሚለውን ማወቅ እና አርቆ ማሰብ ለትዳር መስተካከል ዋና መሠረት ነው።


https://t.me/https_Aselefya
(رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ.)

አሁን ያላችሁበት ጥሩ ሁኔታ ወደ አላህ ፈላጊ ከመሆን አያግዳችሁ።ሁሌም ዱዓእ አድርጉ። በበራፉ ላይ ብዙ ቁሙ፣እስኪከፈትላችሁ ድረስ አንኳኩ።

አላህ ሆይ ወደእኔ ለምታወርደው መልካም ነገር ሁሉ ፈላጊ ነኝ።

#ማስታወሻ
🍓1
«وَ أعْظمُ الحُبِّ ، حُبُّ الرُوحِ لِرُّوحِ،

«ትልቁና የላቀው ፍቅር አንድኛው ነፍስ ለሌላኛው ነፍስ ያለው ፍቅር ነው።

=
t.me/https_Asselefya1
👍2
🧷كَانَ مِن دُعَاء مُوسَى عَليهِ السَّلام:
«اللهُمَّ ليِّن قلبِي بالتَوبَة، ولَا تَجعَل قلبِي قَاسياً كالحَجَر».

الزُّهد لأَحمَد بنُ حَنبَل (٣٥٠)

~
‏« وكما أن تقوى الله مَجلَبة للرزق، فتركُ التقوى مجلبة للفقر. فما استُجْلِبَ رزقُ الله بمثل ترك المعاصي »

• ابن القيم | الداء والدواء صـ (١٣٣)

~
🧷ሚስት በባል ላይ ያላት መብት ምግብ፣ ልብስና ወጪ ብቻ አይደለም።
»»ይልቁንም የዲን_የአቂዳ_የሱና_ትምህርቶች_ርህራሄ_እንክብካቤ_ፍቅር_ስሜት_መከባበር_ሀሳቧን_መቀበል እነኚ ነገሮች ማግኘት ይበልጥ አለባት
»»ምክንያቱም ከኪስ ልግስና ይልቅ የልብ ልግስና ያማረ ነው።


~
🍓4