قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
913 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
🧷የኔ ጀግና እህት

ነገሮችን ባላየ ማለፍን ልመጂ የማይጠቅሙሽን ነገሮች ህይወትሽ ላይ ምንም የማይጨምርና የማይቀንሱን ነገሮች በመዝለል ላይ በርቺ

ትተሽ ያለፍሻቸውን ነገሮች ዞረሽ ባለማየት ላይ ጀግኚ ላልሆንሻቸው ስያሜዎችሽ መልስ በመስጠት ላይ አትገኝ በቀኖችሽ ውስጥ የሚጠቅምሽን ብቻ ዝገኚ

እህቴ ትኩረት አልባ ሁኚ ማለቴ አይደለም ነገር ግን መርጠሽ ትኩረት ስጪ የማይጠቅምሽን እያሰብሽ እንቅልፍ አተሽ አትደሪ ነቃ በይ። 


🎀
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አይ የዘመኑ ወንድ_ የዛሬ_አፍቃሪ


🧷ለንግግር ማማር ቃላትን ይመርጣል

በወሬወች መሀል ለማሳቅ ይቆርጣል 

የፍቅሩን መጠን ከሰማይ አስፍቶ

ከዋክብት ጨረቃን ሁሉንም አካቶ

ወደድኩሽ ይላታል በቅቤ ምላሱ

ፍቅርን ይሰብካታል ምናለበት እሱ

እሷም እውነት መስሏት ልቧ ጮቤ ረግጦ አንዴ እጁ ከገባች

ውበቷ ይረግፋል ባህሪዋ ግራ መጥፎ ትመስለዋለች

አይ የዘመኑ ወንድ -የዛሬ አፍቃሪ እንዲህ ሁኗል ለካ

ፍቅር በስሜት ጫፍ ባልጋ ላይ ሲለካ።

https://t.me/https_Aselefya
👍1
🔎ምን ነካሽ እህትዓለም❓

=• ፍቅር በገንዘብ ድለላ?
=•ትዳርን በብር?

አንች የስደቷ እህቴ ምን ሆንሽብኝ እውነት ገንዘብሽ ተርፎሽ ነው?

ወይስ አልደከምሽበትም?
ወይስ ድጋፍሽ የሚያስፈልገው ቤተሠብ የለሽ ሆኖ?

ለመተዛዘንም የማይመች ሆነ እኮ ገንዘብሽን ሁሉ ከስረሽ ያመጣሽው ወንድ ባል ሊሆንሽ ነው?

ተው እህቶቼ በአንዷ እህታችን በሚደርሠው እኛም እንማርበት ለምን ሁላችንም እናለቅሳለን አይ የእኔው እንደዚህ አያደርግም ይሉታል
ምን አሳወቀሽ? ኣ

ወንድሞቻችን ስንወቅሳቸው ወዳ ላደረገችው የሚል መልስ ይመጣል ተው እህቶቼ ልብ እንበል

የወደደሽ ወንድ አጅ ነብይጋ እየተጋፋሽ ሸቅይና ለእኔ ኢቃማ ግዢ አይልሽም ገንዘቡን ይዘሽው ነው ተብቃቅተን እንኖራለን ይልሻል እንጅ

ለወንድምሽ የማታደርጊውን ለገናው ባል የሆነኛል ብለሽ የምታፈሺው ብር አልደከምሽበትም?

እህቴ እህቴ ብሎ አላቅሶሽ አዛኝ ቅቤ አንጓች እኔ ግን እንደሌሎቹ አይደለሁም ሲልሽ አመንንሽው? እንደት ተዋጠልሽ?

በስደት ጉልበታችን የልጅነት ወዛችን ውበታችን ረገፈ ከዛ በገንዘብ ይሉኝታ የያዝሽው ወንድ እንደዚህ ስላደረገችልኝ እንጅ ማለት ይጀምራል

እህቶቸዋ ስለዚህ ጉዳይ እንወያይበት እስከመቼ እንሸወዳለን?

ባል ይሆናል ላልሽው የምታፈሽውን ገንዘብ ሀገርሽ ላይ የሆነ ነገር አድርጊና ግቢ

አፈቀርኩት ብለሽ በብርሽ ለመግዛት አትሞክሪ እህቴዋ ልብሽንም የደከምሽበትን ብርሽንም አትዘረፊ
القارئ : ماهر المعيقلي




https://t.me/https_Aselefya
እኛ በተራመድንበት ጫማ እስካልተራመዱ ድረስ፣ የኛ ጉዳትም ሆነ  ህመም ማንም ሊገባዉና ሊረዳ አይችልም

ህመምህን ለታመመ አልያም ታሞ ለሚያቅ ብቻ ነዉ ማስረዳት ከዛ ዉጭ አጉል ድካም ትርፍ ነዉ
.....💧

منقل

🎀
👍1
قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
አይ የዘመኑ ወንድ_ የዛሬ_አፍቃሪ 🧷ለንግግር ማማር ቃላትን ይመርጣል በወሬወች መሀል ለማሳቅ ይቆርጣል  የፍቅሩን መጠን ከሰማይ አስፍቶ ከዋክብት ጨረቃን ሁሉንም አካቶ ወደድኩሽ ይላታል በቅቤ ምላሱ ፍቅርን ይሰብካታል ምናለበት እሱ እሷም እውነት መስሏት ልቧ ጮቤ ረግጦ አንዴ እጁ ከገባች ውበቷ ይረግፋል ባህሪዋ ግራ መጥፎ ትመስለዋለች አይ የዘመኑ ወንድ -የዛሬ አፍቃሪ እንዲህ ሁኗል…
🧷አይ የዘመኑ ወንድ የዛሬ ፍቅረኛ

ለንግግር ማማር ቃላት ይመርጥና

ወደድኩሺ ይላታል ቃላት ያሳካና

በወሬው መሀል ሳቁን ይመርጥና

እሷን ለማታለል በጣም ይስቅና

እወድሻለሁኝ ይላል እንደገና

የሷን ልብ ለመሳብ በደንብ ይጥርና

ካንች ውጭ ወደውጭ አልፈልግም ሌላ

ብሎ ቃል ይገባል ይምልላትና

የሚፈልገውን ጥሮ ያገኝና

ከዛማ በኋላ ዘወር ይልና

ቃሉን አፍርሶ ይፈልጋል ሌላ

ሌላዋን አውርቶ ዳግም ያታልና

በመርዝ ምላሱ ቃላት ይረጭና

ቀምሞ መጥኖ ቃላት ያወጣና

ወደድኩሽ ይላታል ሌላዋን ዳግመኛ

ትዳር አይፈልግም ይሄማ ጥቅመኛ

ያችንም ይችንም ያተራምስና

ቁጥቧን ይመኛል ዳግም እንደገና

ነገውን የረሳ በዛሬ ጥቅመኛ

አይ የዘመኑ ወንድ የዛሬ ፍቅረኛ።


https://t.me/https_Aselefya
💯2👍1
🧷"لو كانَ هذا العلمُ يحصلُ بالمُنى
ما كان يبقى في البريَّة جاهلُ

اجهد ولا تكسل ولا تكُ غافلاً
فندامةُ العُقبى لمَن يتكاسل."

እዉቀት በምኞት ቢገኝ ኖሮ ምድር ላይ ጃሂል ባልኖረ ነበር ይልቁን  ከአላህ ተዉፊቅ በታች በጥረት በከፍተኛ ትግል የሚገኝ ዉድ ነገር ነዉ....

https://t.me/https_Aselefya
አንዴ ነው ይሉኛል በፍቅር መጓዳት


🧷 አንዴ ነዉ ይሉኛል በፍቅር መጎዳት
አንዴ ነው ይሉኛል ባመኑት መከዳት

እኔ ግን አላምንም


ካለፈ ህይወቴ  አላውቅም ተምሬ
አውቃለሁኝና
ብዙ ተጎድቼ  ብዙ ጊዜ አፍቅሬ

በፍቅር መንገድ ላይ ተጉዤ ተጉዤ
የማውቃቸው ሁሉ
የሸለሙኝን መልክ  ጠባሳ ልብ ይዤ

አንተ ጋራ ስደርስ
ልብህና ልቤ  እንደተሳሳበ
እንዳዲስ ሳፈቅር
ወደ ነፍሴ ምድር  ጥያቄ ዘነበ

ቆይ ስንቴ ነው መውደድ  ስንቴ ነው መጎዳት
ቆይ ስንቴ ነው ማመን ስንቴ ነው መከዳት?
ለስንት ጊዜ ነው?
ሲሄዱ መራገም  ሲመጡ  መመረቅ
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?

እርሜ ነው እያሉ በመሃላ መታረቅ?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?
መተው መርሳት ሲቻላ በማስታወስ ማፍቀር
ስንቴ ነው መታቀፍ  ስንቴ ነው መገፍተር?
ቆይ ስንት ጊዜ ነው?!
በብቸኝነት ውስጥ  በአብሮነት መቀጣት?


ለካን ስለካንስ
   ለመንገደኛ ልብ
ተራ ጥያቄ ነው  መሄድና መምጣት
አቦ ወግድልኝ
መልስ ነው በራሱ
ለተራ ጥያቄ  ተራ መልስ ማጣት።


አለች ገጣሚዋ ህዕ👓

https://t.me/https_Aselefya
👍1