قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
915 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
የማይነጉ የሚመስሉ ሌሊቶች ይነጋሉ የማያልፉ የሚመስሉ ቀናቶች ያልፉሉ

አይለየኝም፣አይዋሸኝም ብለን በጣም የተማመንበት ሰዉ ፊቱን ያዞርብናል

ግን ህይወት ትቀጥላለች ሁሉንም ወደኋላ ትተን እንጒዛለን።እነዛ ነገሮች ትዝታችን ሁነዉ ያልፋሉ

እና በህይወታችን ጥሩ ትምህርት እንማራለን የዛኔ እድሜ ሰጥቶ ሁሉንም ያሳየንን ፈጣሪያችንን እናመሰግነዋለን

በመቀጠልም~ በህይወትችን ያለፈዉን ሰዉ እናመሰግነዋለን ወይም......

http://t.me/https_Aselefye

~🌸
አንቺ የኔ ንግስት አንቺ የእኔ ፀዳል
ያ የሞቀ አልጋዬ ያላንቺ ይበርዳል
የተለያየን'''ለት ሰው ሞቴን ይረዳል
የሚጥም ልሳንህ ሲል እንዳል ነበረ
ይሄው ዘመን ሽሮት ቃልህ ተቀየረ
.....
ተንኮልን ፀንሰህ በቀል እየወለድክ
አምኖ ሚወድህን ህያው ልብ ገደልክ
በማስመሰል ባሩድ በክህደት ጥይት
ለካ አቁስለኸኛል አወይ እኔ ልጅት
ስንት ግዜ ልዳን ስንት ጊዜ ልሙት
ይሄን ያህል ስቃይ ይሄን ያክል በደል
በዕምነት የኖረ ልብ በክህደት መግደል
ኸረረረ
.
ለኔ መውደድ ምላሽ ክህደት ከሆነ
ልቤን አስረክቤህ ልብህ ከመነነ
ኋላ ግን ፀፅቶህ ብትመጣ ወደኔ
ሁሉን ያጣ አፍቃሪ ትሆናለህ ያኔ
ባይገባህ ነው'ንጂ ቢጠፋብህ እምነት
ባታቀው ነው እንጂ ልብህ ደርቆ ካለት
የቁም ሞት ሞቻለሁ አንተ የከዳህኝ ለት
.
ምን ብበድልህ ነው
ልቤ ምን አርጎ ነው
ይሄን ያህል ስቃይ ይሄን ያክል በደል
በ'ምነት የቆመ ልብ በክህደት መግደል
ምን የሚሉት ስቃይ ምን የሚሉት ፍቅር
ጅምር ላይ ሰልችቶ ፍፃሜ ላይ ማፍቀር
.
አታስብ ስለኔ ሂድ መንገድህ ይቃና
እንዳንተ ሌላ ውብ ዕልፍአዕላፍ አለና
🍃እጀምረዋለው ፍቅሬን እንደ ገና🍃
እርሜን አውጥቻለሁ እርምህንም አውጣ

http://t.me/https_Aselefye

🌸.....
ደና ነኝ እላለው መድከም የት አባቱ
ገደለኝ አልልም ሰበረኝ ናፍቆቱ
ልክ እንደ ጀግና ሲዋሽልኝ አፌ
ደና ነኝ እላለው ትዝታን ታቅፌ

http://t.me/https_Aselefye

~💦
ይቀመጡልኝ 🌸
👍2
የሰሞን አመሌ ልቤን እየነሳ
ያደክመኝ ጀምሯል አንተን እያወሳ
ሀሳቤ ተጓዡ ከደጅህ ደራሹ
ላያመጣህ አንተን እምባዬን አፍሳሹ

እስኪ ይሁን እንዳልከው
ቢለውም ልቤን ቅር
እኔ እንዳልኩት ምንም አይሆን
አይረጋም ያንተ ፍቅር......ልል ነበር ተውኩት

http://t.me/https_Aselefye

~🌸
🌺የኔ ውድ እህት🌺

ዛሬም አንድ ነገር ላስታውስሽ የምትፈልጊውን ውጤት እስክታገኚ መትጋትሽን ቀጥዪበት እሺ!

http://t.me/https_Aselefye

~🌸
👍1
ታገስ !

የታገሰ መልካሙን ፍሬ ይበላል፤ለጠበቀ ሰው ሁሉ መልካም ነዉ፤በጌዜው የማይሆን አንዳች ነገር ለማይኖር በችኮላ ለፀፀት የሚዳርግህ ነገር ውስጥ አትግባ ለሚያልፍ ዛሬ የማያልፍ ታሪክን አትፃፍበት ትንሽ ብቻ ታገስ ብዙ ታተርፋለህ !

http://t.me/https_Aselefye

~🌸
💯1
መንገድ ያመጣል መንገድ ይመልሳል እንደሚባለው ልብሽ መቀበልን እንደሚያውቅ ሁሉ መሸኘትንም አስተምሪው!

~🌸
💯1
🌹🍃


التوحيد: لا معبود بحق إلا الله
السُّنة: لا متبوع بحقٌّ إلا رسول اللهﷺ،
المنهج: لا فهمًا صحيحًا للكتاب والسنة إلا فهمُ السلف.


~🌸
“ታላቅነት ያለው ባለመውደቅ ውስጥ ሳይሆን ወድቆ ባለመቅረት ውስጥ ነው”

~🌸
🍓1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"በዝናብ ቀጥረኝ"

የሠማይ መስኮቶች በተከፈቱበት፣
በረዶ ያዘለ ዶፍ በሚወርድበት፣
እመጣለሁ ፍቅሬ ቀጥረኝ በክረምት፣

የበረዶው ክምር ጣቶቼን ይንዘረኝ፣
የቆምኩበት ቦታ እንዳይታወቀኝ፣
ግዴለህም ፍቅሬ በዝናብ ቀጥረኝ፣
ብትቀርስ’ አትበል አልቀርም እመነኝ፣

ምንም አይመስለኝም ይጣል ዶፍ በረዶ፣
ይመጣል አይቀርም ልቤ አንተን ወዶ፣

ውሽንፍሩ ይምታኝ ጠል ይውረድ በላዬ፣
እጠብቅሃለሁ እቆማለሁ ችዬ፣

የዳመናው ኩርፊያ ቁጣ ጉርምርምታ፣
አያሸብረኝም የመብረቅ ብልጭታ፣

ቅሩ አይታወቀኝ ብርዱን መች ‘ፈራለሁ፣
ፍቅርህን እንዴ’ልባስ ተከናንቢያለሁ፣

ሳይመችህ ቀርቶ ድንገት እንኳን ብትቀር፣
አይዞህ አልከፋም አይለኝም ቅር ቅር፣

ይልቅ…
እተካክዛለሁ ዝናቡን ታድሜ…
ስሜቴን በእንባዬ አጥበዋለሁ ቆሜ…
ንዴቴ እንዲያልፍልኝ እንዳልሄድ አቂሜ…

ብቻ ስለሁሉም በዝናብ ቀጥረኝ፣
ትቀራለች ብለህ እንዳትጠረጥረኝ፣

ጭጋግ ይሸፍነኝ ይጥፋኝ ያለሁበት፣
አልቀርም መጣለሁ በመውደድህ ስበት፣

መጠለያ ታዛ ሥፍራ በሌለበት፣
አውላላ ሜዳ ላይ ቀጥረኝ በክረምት፣
ያኔ ታውቀዋለህ…
የመውደዴን ጥልቀት…
የማፍቀሬን ጽናት....ልል ነበር ተውኩት።


http://t.me/https_Aselefye

~🌸
👍3