قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
912 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
🎚️አንድ ሰዉ አቅሙ ካለዉ ወጣትም ቢሆን ሐጅ የማድረግ ግዴታ አለበት ❔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🧷‏ قَالَتْ عَائِشَةٌ - رَضِّيَ الله عَنْهَا - :

አኢሻ ረደላሁ አንሀ እንድህ አለች

( يَا مَعْشَرِ ‎النِّسَاءَ ، لَوْ تَعْلَمَنَّ بِحَقِّ أَزْوَاجِكُنَّ عَلَيْكُنَّ ،
لِجَعِلَتْ‎ المَرْأَةُ مِنْكُنَّ تَمْسَحُ الغُبَارُ عِنْدَ قَدَمَيْ زَوَّجَهَا بِحُرِّ وَجْهِهَا ).


እናንተ ሴቶች ሆይ  ባሎቻችሁ በእናንተ ላይ ያላቸውን ሀቅ ብታውቁ ኑሮ
ከእናንተ አንድኛችሁ የባሏን እግር አቧራ በፊቶቿ በአበሰች  ነበረ አለች


رواه اِبْن أَبِي شَيْبَة ‹ ٢٠٥/٤ ›

ትኩረት

የባል ሀቅ ማለት የሚገባውን ሀቅ አውቀሽ ሀቁን መስጠት እንጂ እንደፈለኩ እሆናለሁ፣አንቺ ላይ ጢባጢቤ እጫወታለሁ ሲል፣ሀቅሽን አልጠብቅ ብሎ ሲረግጥሽ  ዝም ማለት አይደለም

ሀቁን ጠብቂ ሀቅሽን ይጠብቅ።

~
🧷ጉዳዩን ሁሉ ለአላህ የተወ አሏህ እሱ ከተመኘው በላይ ይሰጠዋል...!!
                     
https://t.me/https_Aselefya
🧷አብደላህ ኢብኑ መስዑድ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል-
'አላህን በማስታወስ ላይ የሚያግዝህን
ቢሆን እንጂ ጓደኛ አትያዝ'።

ምንጭ;-📚الزهد لأبي داود ١٢٦/١
                 

https://t.me/https_Aselefya
🧷በምትወደው ነገር ላይ አላህ እንዲያዘወትርህ የምትፈልግ ከሆንክ
አላህ በሚወደው ነገር ላይ ዘውትር።


       /ኢማሙ አሕመድ/


https://t.me/https_Aselefya
🧷 አራዳ ብሎ ማለት ለምን እንደተፈጠረ እና ማን እንደፈጠረው አውቆ አምኖ ተቀብሎ በብቸኝነት አሏህን የሚገዛ ነው።

https://t.me/https_Aselefya
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🧷لَّقَد كُنت فِي غَفْلَةٍ مِّنْ هَـٰذَا فَكَشَفْنَا عَنكَ غِطَاءَكَ فَبَصَرُكَ الْيَوْمَ حَدِيدٌ
«ከዚህ ነገር በእርግጥ በዝንጋቴ ውስጥ ነበርክ፡፡ ሺፋንህንም ካንተ ላይ ገለጥንልህ፡፡ ስለዚህ ዛሬ ዓይንህ ስለታም ነው» (ይባላል)፡፡
[ ሱረቱ ቃፍ - 22 ]

በዝንጋቴ ውስጥ ሆነን እንጅ የአኸይራው ጉዳይ የበለጠ አሰፈሪ ነው።

ሞት በዛው መቅረት ፥ ሳይመጣ በድንገት፣
ቆሞ መጠባበቅ ፥ ይሻል መዘጋጀት!!

وَ
اعْبُدْ رَبَّكَ حَتَّىٰ يَأْتِيَكَ الْيَقِينُ
❝ እውነቱም (ሞት) እስኪመጣህ ድረስ ጌታህን ተገዛ፡፡ ❞ [ ሱረቱ አል-ሒጅር - 99 ]


كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ ۖ ثُمَّ إِلَيْنَا تُرْجَعُونَ
❝ ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ከዚያም ወደኛ ትመለሳላችሁ፡፡ ❞
[ ሱረቱ አል-ዐንከቡት - 57 ]

قُلْ إِنَّ الْمَوْتَ الَّذِي تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُ مُلَاقِيكُمْ ۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
❝ ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው፡፡ ❞ [ ሱረቱ አል- ጁሙዓህ - 8 ]

وَجَاءَتْ سَكْرَةُ الْمَوْتِ بِالْحَقِّ ۖ ذَٰلِك مَا كُنتَ مِنْهُ تَحِيدُ
❝ የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች፡፡ (ሰው ሆይ)፡- «ይህ ያ ከርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው» (ይባላል)፡፡ ❞ [ ሱረቱ ቃፍ - 19 ]

~
🌴ኢማም ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

❝ዱኒያ ጥንብ ናት አንበሳም በጥንብ ላይ አይወድቅም።❞
📚الفوائد لابن القيم ٨٠
══════ ❁ ══════
https://t.me/Mohammedseid21
💯በእስልምና ሐይማኖት አስተምህሮ መሰረት ዒሳ (ኢያሱስ) አልተሰቀልም ⁉️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🧷ሀሰኑል በስሪይ ቀብር አጠገብ ቆመው አጠገባቸው ያለን ሰው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት

ይህ የተቀበረ ሰው ወደ ዱኒያ ቢመለስ ምን የሚሰራ ይመስልሃል? ብለው ጠየቁት
ሰውዬውም -በዒባዳ ይጠመድ ነበር አላቸው-
ይህ ዕድል እሱን አምልጦታል አንተም እንዳያመልጥህ አሉት።

https://t.me/https_Aselefya
🧷ሸይኽ አብዱረዛቅ አሏህ ይጠብቀውና እንድህ ይላል -
እድለኛ ብሎ ማለት ከሰዎች የተመከረ ነው -እድለቢስ ብሎ ማለት ደግሞ ከሱ ውጭ ያሉ ሰዎች በሱ የሰመከሩበት ነው።መውዒዞቱ ኒሳእ-36-

የኔ ውድ እህት በአሏህ ታግዘሽ ሰበቡን አድርሽ-ሁሌም ቢሆን-በሰዎች የምትመከሪ ጮሌ ሁኚ- መቸም ቢሆን ሰዎች ባንቺ የሚመከሩብሽ እንዳትሆኚ።

https://t.me/https_Aselefya
🧷 الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي هَدَانَا لِهَٰذَا وَمَا كُنَّا لِنَهْتَدِيَ لَوْلَا أَنْ هَدَانَا اللَّهُ 🍂
🧷ፊርዓውን ስልጣኑን ለማስጠበቅ በሚል በርካታ ሺህ ህፃናቶች አርዷል። ሙሳ በስህተት አንድን ሰው ገደለ።

ከዝያም ፊርዓውን ለሙሳ እንዲህ ይለዋል፦
📖{وَفَعَلْتَ فَعْلَتَكَ الَّتِي فَعَلْتَ وَأَنتَ مِنَ الْكَافِرِينَ}
  {ያቺ የሰራሃትን አልሰራህምን? አንተ ከውለታ ቢስ (ከከሀዲዮች) ነህ።}

       [አል_ሹዓራእ:¹⁹]



  እውነታን መገልበጥ፤ ራስን አጥርቶ ሌሎች መወንጀል ሁሌም የሙጅሪሞች አካሄድ ነው።
🌴ሱፍያን አል-ሠውሪይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፡-

❝እውቀትን ተማረው  ከተማርከውም ከሳቅ እና ከጨዋታ ጋር አትቀላቅለው ሸፍነው አለበለዚያ ልቦች አይቀበሉትምና።

የዕውቀት ምሳሌ በሽታው ባለበት ቦታ ላይ ብቻ መድኃኒት  እንደሚያደርገው ዶክተር ነው።እውቀትን መፈለግ ከእከሌ ወደ እከሌ መዘዋወር (ብቻ) ሳይሆን እውቀትን መፈለግ አላህን መፍራት ነው።

አንድ ሰው ልጁን ሐዲስ እንዲማር እንዲፈልግ ማስገደድ አለበት። ምክንያቱም ተጠያቂው እሱ ነውና።❞

📚فوائد من كتاب الزهد
══════ ❁ ══════
https://t.me/Mohammedseid21