قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
910 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
ይቀመጡልኝ🌷እንዳነኩ የእህቴ ስጦታ ነው👓
👀5🍓3
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
لو أنكم تتوكلون على الله حقَّ توكُّله؛ لرزقكم كما يرزق الطيرَ: تغدوا خماصًا وتروح بطانًا..
👍4
🧷አንዳንድ ባዶነቶች በጊዜ አይሞሉም"
መኖርን ብቻ እንማራለን"💧


https://t.me/https_Aselefya
قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
🧷አንዳንድ ባዶነቶች በጊዜ አይሞሉም" መኖርን ብቻ እንማራለን"💧 https://t.me/https_Aselefya
🧷አንዳንድ የምናጣቸው ውድ ሰዎች በልባችን የሚተዉት ባዶነት ሙሉ በሙሉ አይጠፋም
ግን ጊዜ እየሄደ ሲሄድ ከዚያ ህመም ጋር መኖርን እንማራለን


አወ

አንዳንድ ሰዎችን አንተካቸውም ናፍቆታቸውን በልባችን ብቻ ይዘን መቀጠልን ግን እንማራለን።

رحمك الله يا أبي💧

https://t.me/https_Aselefya
👍1
🧷መኖር ማለት በእስትንፋስ መቆየት/አለመሞት አይደለም:መኖር ማለት በሀብት የተጥለቀለቀ ጎጆ መምራት ብቻም አይደለም

መኖር ማለት ለአላህ ታዛዥና ታማኝ ባሪያ በመሆን እስከ ህይወት ፍፃሜ ጥረት ማድረግ
መኖር ማለት ትክክለኛ ማንነትን መሆንና አላማ
ያለው ህሊናን በዱኒያ ጥቅም አለመለወጥ
መኖር ማለት ራስን በመልካም ነገሮች በማነፅ ለሌሎች ተምሳሌት ሆኖ መገኘት ነው::

   
https://t.me/UstazKedirAhmed
💯1
🧷ሰዎችን አትከታተል ይልቁንስ የረሳሀት የሆነችውን ነፍስህን ተከታተል ¡

ማለዳ ዐይኑን ከከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ምሽት ዐይኑን እስከሚዘጋበት ጊዜ ድረስ ቀኑን ሙሉ የሰዉን ነዉር ሲከታተልና ሲያነፈንፍ የሚዉል ሰው አለ፡

ምንም ላያተርፍበት ራሱን ትቶ ሌላዉን ይከታተላል ዉድቀቱን- ድልጠቱን- ስህተቱን- እንከኑን ይሰልላል- ዉርደቱን ይጠብቃል፡ የት ዋለ- የት ሄደ፣ የት ገባ-የት ወጣ- ምን አገኘ- ምን አጣ-እያለ ስለ ሰው ይጠበባል፡ የራሱን ትቶ የሌላዉን ሕይወት ይኖራል፡የራሱ አሮበት የሰዉን ያማስላል፡-

ባይሆን ወደራሱ የተመለከተ-በራሱ ጉዳይ ተጠምዶ የዋለ በራሱ ላይ ብዙ ጉድፍ ያያል...¿

https://t.me/https_Aselefya
👌1
🧷በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት  መውሰድ ነው፡
መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም ባወቅን ቁጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል
ሁሌም እንማር
ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንሁን
ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ
ዐዋቂ  ነኝ 
ትክክል ነኝ
እኔ ብቻ የሚል ሳይሆን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር  ለመማር የተዘጋጀ ነው'

ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይሆን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡

ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ  ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር  ሲሆን 'በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው።

https://t.me/https_Aselefya
Forwarded from "ዳሩል -ዒልም የእዉቀት ማዕዲ ! (ሀያት[]~ ሰለፍያ~[] የልባሞች እምነት የጀግኖች ጎዳና መመሪያሽ ቁርአን እንዲሁም ነዉ ሱና)
🔖በዚች ግቡና  አበረታቱኝ  እናንተየዋ  አሯ  ሀላል ስራ የሚሰራን ሰዉ  አጠናክሩ የብርታት ስበብ ሁኑ። 

t.me/Online_Eslamawiy_Market
t.me/Online_Eslamawiy_Market
፡ وكسرها طلاقها 🧷

ሊያኖር ሳይሆን ሊሞክር የሚያገባም እኮ አለ

✔️ ፍች ለሴቶች ከባድ ሙሲባና ህመም ያለው ጠባሳ ነው

✔️ ጫማ እንደማውለቅ ቀላል ነገር አድርገህ አታስበው

ሴት ልጅ ስትፈታ አላህ እንጂ ማንም የማያውቅላት ሀዘንና ጭንቀት ውስጥ ሆና ለረጅም ጊዜ ታሳልፋለች ተበድላ ሲሆን ተጭበርብራ ተክዳ ሲሆን ደሞ ሀዘኗና ቁጭቷ ተወው ከሚባለው በላይ ነው

አንዳንዱ ደሞ በእድሜ ትንሽ የሆነች አባቷ በከረሜላ የሚያባብላት ሴት ፈልጎ ያገባና እንደ እናቱ ሙሉ ሀላፍትና ልትሸከምለት ይፈልጋል ❗️ እንደ እናትህ ልትሆን የእናትህ እድሜ መድረስ አለባት


✅ ነገሩ ሳሳጥረው << ልትፈታ አታግባ >>
አንቺም ደሞ ዘው ብለሽ አትግቢ ከሰውም እኮ ገለባ አለ
።

~
💯2
🧷ምንም ያክል ዱኒያ ልባችንን ብታቆስለው ብታደማው ነገር ግን ጠጋኝ የሆነ ጌታ አለን

الحمد الله


https://t.me/https_Aselefya
👍6
🧷وإذا الشدائدُ أقبلتْ بجنودِهَا
ችግሮች በወታደሮቻቸው ሲመጡ

والدهرُ من بَعد المسرّةِ أوجعَكْ
እና ደስታ ካለፈ በኋላ ጊዜው ቢያምህ

لا ترجُ شيئًا من أخٍ أو صاحبٍ
ከወንድም ወይም ከጓደኛ ምንም ነገር አትጠብቅ

أرأيت ظلّك في الظلامِ مشى معَكْ؟
ጥላህ በጨለማ ውስጥ ከአንተ ጋር ሲሄድ አይተህ ታውቃለህን?

وارفعْ يديكَ إلى السَّماءِ ففوقهَا:
እጆችህን ወደ ሰማይ አንሳ ምክንያቱም ከዛ በላይ

ربٌّ إذا ناديتهُ .. ما ضيَّعَكْ
የምትጠራው ጌታ አለ… እሱም ፈጽሞ አይጥልህም

ولرُبَّ نازلةٍ يضيقُ لها الفتى
ذرعاً وعندَ اللهِ منها المخرَجُ
:دብዙ ጊዜ ሰው በችግርና በመከራ ሲጨነቅ፣
ከአላህ ዘንድ ግን ከእርሷ መውጫ አለ።

ضاقتْ فلمّا استحْكَمَتْ حلقاتها
فُرِجَتْ وكنتُ أظنّها لا تُفْرَجُ:
ጠበበች፣ ነገር ግን ክብደቷ (መከራዋ) ሲጠናከር፣
ተከፈተች (መፍትሄ አገኘች)፣ እኔ ፈጽሞ የማትከፈት መስሎኝ ነበር።


~
-             ውዷ እህቴ

🧷ደስታሽን ለማደብዘዝ ከሚጥሩ ሰዎች ራስሽን አርቂ..¿

https://t.me/https_Aselefya
💯3🍓2
🧷አይ ሰው ¿

ዱርዬ ሆነሽ ሳለ¿
   ሁሉም "አሏህ ሂዳያ ይስጥሽ" እያሉ ዱዐ ያደርጉልሻል¡

አሏህ ሂዳያ ሰጥቶሽ ሀራም ማውገዝ ስትጀምሪ
"አውቃታለሁ ባክሺ ዱርዬ ነበረች  ይሉሻል።

https://t.me/https_Aselefya
👍10
🌷የኔ ሴት🌷

🧷አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በሌላ መልኩ ይረዱሻል¡

ከዚያም ለአንቺ የተለያዩ መግለጫዎችን ይሰጡሻል
ከአንዳንዶቹ ዘንድ መልአክ ልትሆኚ ትችያለሽ

በሌሎች ዓይን ዘንድ ሰይጣን ልትሆኚ ትችያለሽ
ስለዚህ ምስጋናቸው ቢደርስልሽ አትሸወጂ አትመኪበት

ወቀሳቸውም ምንም ይሁን አይጉዳሽ
ነፍስን እንደ ባለቤቷ የሚያውቃት ሌላ አንድም ሰው የለም

ስለዚህ በራስሽ ግምገማ ሚዛን ላይ ሁኚ።

https://t.me/https_Aselefya
👍1💯1