قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
1.55K subscribers
2.74K photos
913 videos
318 files
2.39K links
https://t.me/https_Aselefya

وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እናትነትን እንታደግ‼
~
አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱህ።
አላህ በያላችሁበት ሰላሙን፣ ጤናውንና በረከቱን ያብዛላችሁ።

ከፈጣሪ በታች የሕይወታችን ምሰሶ የሆነችው እናታችን ዘውዴ ኢብራሒም ከባድ የጤና ቀውስ ውስጥ ገብታለች።

ሁለቱም ኩላሊቶቿ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ሆነው ከፍተኛ የሕክምና እርዳታ በአስቸኳይ ይፈልጋሉ። ለዚህም በውጭ አገር የኩላሊት ተከላ (Kidney Transplant) እንዲደረግላቸው ከ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል። በተጨማሪም በድንገት የልብ ሕመም (Heart Case) ተጨምሮባቸው የሕክምና ወጪው እየከበደ ነው። ለልብ ሕክምናቸው ብቻ 800,000 (ስምንት መቶ ሺህ) ብር ተጠይቀዋል።

በአጠቃላይ እናታችን ወደ ሕክምና ቦታ ሄዳ ሙሉ አፍያዋን እንድታገኝ 6,800,000 (ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሺህ) ብር በአስቸኳይ ያስፈልጋታል።

አላህ በበሽታ ከመሰቃየት ይጠብቃችሁና፣ ይህች የተከበረች እናት በሕይወት እንድትቆይ ከአሏህ በታች የመጨረሻው ሰበብ የእናንተ ደግ እጅ ነው። ለ አላህ ብላችሁ፣ የእናትነትን ክብር አስባችሁ፣ በቻልነው መጠን ከጎናቸው እንቁም! ለወገን ደራሽ ወገን ነውና፣ በትንሹ የምትሰጡት ኒያ ሰደቃ በእናታችን ሕይወት ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

የምትችሉትን ያህል በገንዘብ ርዷቸው።በዱዓችሁም አትርሷት!

♻️የእርዳታ አካውንት፦ 1000267498621
ስም፦ ALI MOHAMMED

✉️ለበለጠ መረጃ፡
0942679458
0960958675
ጀዛኩሙሏሁ ኸይራ! አላህ ምንዳችሁን በሰፊው ይክፈላችሁ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
صفات الزوج الصالح مع زوجته: حقوق الزوجة.
-فضيلة الشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله.
👍1
ሁሌም ከአሏህ ተስፋ አደርጋለሁ እውቀትን እንድለግሰኝና ከዘሮቸም ፣እናቴ ይሄን ዕውቀት ሰጠችኝ ይሄን አወረሰችኝ እያለ በመልካም ዱዓ ሁልጊዜ የሚያወሳኝን እንድሰጠኝ።

~
💯3👍1
ሁሉም ሰው የሚወድህ ለራሱ ጥቅም ሲል ነው።ለራስህ ጥቅም ብቻ የሚወድህ አላህ ብቻ ነው።
ዛሬ ላይ የሚጠሉህን ሰዎች ምክንያታቸውን መለስ ብለህ ብትመለከት ምክንያታቸው ሚፈልጉትን ስላላደረግክላቸው ብቻ ነው።

كلُّ مَن تحبُّه مِن الخلق ويحبُّك إنَّما يريدك لنفسه وغرضه منك، والله سبحانه وتعالى يريدك لك، كما في الأثر الإلهي: "عبدي، كلٌّ يريدك لنفسه، وأنا أريدك لك

ابن القيِّم رحمه الله،

~
💯6
🔖ተግባር አላህ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው ከሚያግዙ ነጥቦች ውስጥ:-
    


ማንኛውም ተግባር በመጭው አለም ምንዳ አንደሚሰጠው ማመንና ራስን ማዘጋጀት
ተግባርን ከይስሙላና ታይታ መሰወርና የነፍስያ  ዝንባሌን መጠንቀቅ

በራስ ከመደነቅና ለነፍስ ትልቅ ግምት ከመስጠት መቆጠብ
ከሰዎች አቅጣጫ  በሚመነጭ ውዳሴ አለመሸንገል
ውጫዊም ሆነ ውስጣዊ ሁኔታዎችን ወጥ ማድረግ(አለማስመሰል)::

https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/UstazKedirAhmed
- الهَاتِف!ጀዋል 📲
🧷ችግሮች ሲደራረቡብሽ የችግርሽን ሳይሆን የአላህን ታላቅነት ተመልከች
ለሱ አንዳች ነገር እሚያቅተው የለም

ችግሮችሽ ይወገዱ ዘንድም አላህን ተገቢውን ፍራቻ ፍሪው ለምኚው።

إِنَّهُ مَن يَتَّقِ وَيَصْبِرْ فَإِنَّ الله
لَا يُضِيعُ أَجْرَ الْمُحْسِنِينَ

~
👍5
ሀሜት ምንድን ነው


ከአቡ ሁረይራ ተይዞ: ረሱል እንዲህ ብለዋል፦

﴿أتَدْرُونَ ما الغِيبَةُ؟ قالوا: اللهُ ورَسولُهُ أعْلَمُ، قالَ: ذِكْرُكَ أخاكَ بما يَكْرَهُ قيلَ أفَرَأَيْتَ إنْ كانَ في أخِي ما أقُولُ؟ قالَ: إنْ كانَ فيه ما تَقُولُ، فَقَدِ اغْتَبْتَهُ، وإنْ لَمْ يَكُنْ فيه فقَدْ بَهَتَّهُ﴾

“ለሶሀቦች ‘ሀሜት ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁን?’ ብለው ጠየቁ። ሶሀቦችም፦ ‘አላህና መልዕክተኛው ከማንም ይበልጥ ያውቃሉ’ በማለት መለሱ። እሳቸውም፦ ‘ወንድምህን በሚጠላው ነገር ማውሳትህ ነው’ አሉ። የምናገረው በወንድሜ ላይ ያለ ትክክለኛ ነገር ከሆነስ ተብለው ተጠየቁ? ረሱልም እንዲህ አሉ፦ ‘በእሱ ላይ ያለውን የምትናገር ከሆነ በእርግጥም አምተኽዋል’ የምትናገረው በእሱ ላይ የሌለን ነገር ከሆነ በእርግጥ ስሙን አጥፍተህዋል።”

ሙስሊም ዘግበውታል: 2589


~
🔖  ሸይኽ አብዱረዛቅ አል-በድር (አላህ ይጠብቃቸው) እንዲህ ብለዋል፡-

« አንዲት ሴት የእስልምናን ትምህርት ስትከተል፦ ክብር፣ ሙሉነት፣ ውበት እና የጡቡቅነት ሕይወት ትኖራለች።»

#موعظة النساء ص ٣٦



t.me/https_Asselefya1
قُلِ الحمدُ لله 🌷
🧷قَال ابْنُ قُدَامَةَ المَقْدِسِيّ -رَحِمَهُ الله- تعالى: 
ኢብኑ ቁዳመተልመቅደሲ አሏህ ይዘንለትና እንዲህ አለ

واعلم أن أكثر الناس إنما هلكوا لخوف مذمة النَّاس، وحب مدحهم فصارت حركاتهم كُلُّها على ما يوافق رضى الناس، رجاء المدح وخوفا مِنَ الذَمِ، وذلك مِنَ المهلكات فوجبت معالجته،

እወቅ አብዛኛው ሰዎች የጠፉት የሰውን ወቀሳ ፈርተው እና የእነሱን ሙገሳ ፍለጋ ሲሄዱ ነው!!
ያኔ ደሞ ሁሉም እንቅስቃሴያቸው ሰውን ለማስወደድ ሆነ የሰውን ውዳሴ ፍለጋና የነሱን ወቀሳ በመፍራት

ይህ ደሞ ከአውዳሚዎች ነው ይህ ስለ ሆነ ይህነን በሽታ ማከም ግድ ይላል።

📓 [«مختصر منهاج القاصدين» (٢١٢)]

📓 [ሙኽተሰር ሚንሃጁል ቃሲዲን] (212)

https://t.me/https_Aselefya
‏﴿ وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ ﴾

- سُبحان الله
- الحَمد لله
- لا إله إلا الله
- الله أكبر
- أستغفِرُ الله
- لا حَول و لا قوة إلا بالله
- سُبحان الله و بِحمده
- سُبحان الله العَظيم
- اللهم صلِ و سلم على نبينا محمد.

~
Forwarded from قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚 (أُم ؏ـبد اللّٰه زمزم حسن الحبشية)
{وَلَا تَهِنُوا وَلَا تَحْزَنُوا وَأَنتُمُ الْأَعْلَوْنَ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ}
لاتحزن و لاتيأس مهماكانت الخسائر في عمرك؛مهما فاتتك أشياء تحبّها؛مهما طال انتظار الأماني
‏مهما كانت ظروفك صعبة لايهتزّ إيمانك بربك
‏إن مايقضي الله هو الخير لك وسيعطيك أضعاف ماتتمنى مادمت تدعوه وتحسن ظنّك به وسيرضيك رضًاتنسى معه مافات
ዓይኑን የታወረ ሰው የዓይን ብርሃን በሚሰብር የፀሀይ ጨረር ላይ ቢቆም እንኳ ምንም መመልከት እንደ ማይችለው ሁላ፤

አላህ ልቡን ያወረበት የሆነ ሰው የሐቅ ብርሃን ፊት ለፊት ቢቆምም ምንም መመልከት አይችልም። «አላህ ይጠብቀን»

    [ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው]

https://t.me/https_Aselefya
👍3
#እውነተኛው_የጠራ_ፍቅር*

እውነተኛና የጠራ ፍቅር ማለት አንዲትን ሴት እንደ የትዳር አጋርህ አድርገህ መውደድና መመኘት ነው። ነገር ግን ከእርሷ ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ፣ ቀጠሮ ወይም ቀጥተኛ የሆነ ወሬ ሳይኖርህ ማለት ነው። ይልቅስ በየሌሊቱ፣ አልፎ ተርፎም በያንዳንዱ ሱጁድህ (በግንባርህ እየደፋህ አላህን በምትለምንበት ወቅት) ስለ እሷ ለአላህ ታወጋዋለህ፤ ነገሮች እንዲሳኩና እንዲረዳህ ትማጸነዋለህ። ምክንያቱም እርሷ በእርግጥም ሃላል (በእስልምና የተፈቀደ ትዳር) እንጂ ሌላ አይገባትም።

ይህን ካደረግህና አላህም በሃላል መንገድ (በትዳር) ካገናኛችሁ፣ አንተ በእሷ ደስተኛ ትሆናለህ፣ እሷም በአንተ ልቧ በደስታ ይሞላል። ምክንያቱም በእውነት ላይ የተመሠረተ ነገር ሁሉ እውነት ነው፤ ብዙ በረከትና ጸጋም አለው። ስለዚህ መከተል የምትፈልገውን የሕይወት ጎዳና ለራስህ ለይተህ ምረጥ። ደስታን፣ መረጋጋትንና ውስጣዊ ሰላምን ከፈለግህ፣ በሃላልና በንጹህ ጎዳና ላይ መጓዝ ግድ ይልሃል።

t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy