መንሀጀሠለፍን ኑሩበትእጂ አታስመስሉበት
417 subscribers
125 photos
112 videos
272 links
ይህቻናል ዋናአላማው ዳእዋሠለፍያን ለቀጣይትውልድ ተደራሽእድትሆን ታስቦ የተከፈተነው
ተውሒድ የሁለት አገር ብርሃን ነው .!!!
التوحيد أولا
ከሱፍያ ወደ ኢኽዋንያ ፣ ከኢኽዋንያ ወደ ጀምዒያ ፣ ያደረከው ጉዞ ለለውጥህ መነሻ ሊሆንህ ይችላል እንጅ ንፁኋን ሰለፍያን እስከምትይዝ ድረስ ገና አልተለወጥክም.!!!

ከዶርህ አጎብዳጅነት አውጥተህ ለድሞክራሲ ደሪህ ካ
Download Telegram
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿نضَّرَ اللهُ امرأً سمِعَ مَقالتي فبلَّغَها﴾

“አላህ ፊቱን ያብራለት ንግግሬን ሰምቶ ላደረሰው (ላስተላለፈው) ሰው።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 189
Audio
ጣፋጭቲላዋ🎧🎧🎧

ሱረቱል አል ማኢዳህ ቃሪዕ

ሚስባህ ሳኒ ሀፊዘሁሏህ🌺🌺



▪️ጆሮ በቁርዓን ሲሞላ ይብቃቃል
▪️ልብ በቁርዓን ሲበራ ይፈወሳል
▪️አይን ወደ ቁርዓን መመልከት ሲያበዛ ይጠራል
▪️ምላስ በቁርዓን ሲረጥብ ይዋባል
▪️ቁርዓንን ስትጎዳኝ ነፍስህ ይፀዳል!!!

            መልካም ቀን

 

https://t.me/httpsLuqmane

https://t.me/httpsLuqmane
1
👉10 የልብ ህመሞች ✏️

──────⊱◈◈◈⊰──────

1…… በአላህ (ሱብሀነ ወተአላ) እናምናለን እንላለን ነገር ግን ትዕዛዙን አንተገብርም።
──────⊱◈◈◈⊰──────

2….. ረሱልን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንወዳሉን እንላለን ግን የሳቸውን ፈለገ ሱናቸውን በመተግበር አልተከተልንም ።
──────⊱◈◈◈⊰──────

3….. ቁርዐን እንቀራለን ነገር ግን ወደተግባር አንለውጠውም።

4….. የአላህ (ሱወ) ፀጋ ሁሌ ይደርሰናል ነገር ግን አመስጋኝ አልሆንም።
──────⊱◈◈◈⊰──────

5…. ሸይጧን ጥላታችን እንደሆነ እንናገራለን ግን ከእርሱ ተቃራኒ አልቆምንም።
──────⊱◈◈◈⊰──────

6…. ጀነት መግባትን እንፈልጋለን ነገር ግን ለመግቢያ የሚያግዘን ስራ እየስራን አይደለም።
──────⊱◈◈◈⊰──────

7…. ጀሀንብ መግባትን አንፈልግም ነገር ግን ከሱ ለመራቅ ምንም አይነት ሙከራ አላደረግንም።
──────⊱◈◈◈⊰──────

8…. ሁሉም ህይወት ያለው ነገር እንደሚሞት እናውቃለን ነገር ግን ለሞት እየተዘጋጀን አይደለም።
──────⊱◈◈◈⊰──────

9…. ሰዎችን እናማለን ስህተታቸውን ለማውጣት እንጥራለን ነገር ግን የራሳችንን ጥፋትና ወንጀል እረስተናል።
──────⊱◈◈◈⊰─────

10…. ሙታንን እንቀብራለን ነገር ግን ከዚህ ተግባራችን ትምህርት አንወስድም
──────⊱◈◈◈⊰──────

«✆አንዲትም መልዕክት ብትሆን ከኔ አድርሱ» የሚለውን ነብያዊ ትዕዛዝ
ለማድረስ ብዮ ነው።
──────⊱◈◈◈⊰──────
የእሁድ ፕሮግራም


ተጀመረ

ተጀመረ

ተጀመረ


ሸይኻችን ገብቷል
👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አላህን በዚክር ማውሳት እና አለማውሳት በሕይወት እና በሞት ነው የተመሰለው

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿مَثَلُ الذي يَذْكُرُ رَبَّهُ والذي لا يَذْكُرُ رَبَّهُ، مَثَلُ الحَيِّ والمَيِّتِ.﴾

“ያ! ጌታውን የሚያወሳ እና ያ! ጌታውን የማያወሳ ሰው ምሳሌው፦ እንደ ህያው እና ሙት ነው።”

📚 ቡኻሪ (6407) ሙስሊም (779) ዘግበውታል

እንግዲህ ይሄንን ሐዲስ አይተን ራሳችንን እንፈትንሽ እኔ አልሞትኩም በሕይወት አለው ብለን የምናስብ ከሆነ አላህን በማውሳት ቀናችንን እንጀምር ሙሉ በሆነው በሱ ቃል እንጠበቅ ::

የጠዋት ዚክር ማለትን አትርሱ ከመጥፎ ነገሮች በሱ ቃል ተጠበቁ
የላቀው አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ

🌹🌹🌹 ሰባኸል ኸይር 🌹

https://t.me/httpsLuqmane

https://t.me/httpsLuqmane
2
✍️ ታላቁ ዓሊም ሱፍያን አል-ሰውሪ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ
🔻አንድን አማኝ (ሙእሚን) ከመክዳት ተጠንቀቅ! አማኝን የከዳ ሰው አላህንና መልእክተኛውን ﷺ እንደከዳ ይቆጠራል።
🔺 ወንድምህን ለአላህ ብለህ ከወደድከው፤ ስለ እርሱ ስትል ነፍስህንም ሆነ ገንዘብህን ለግስ (አትሰስት)።
🔺ከጠብ፣ ከከንቱ ክርክርና ከድርቅና ተጠንቀቅ! (እነዚህ ውስጥ ከገባህ) በደለኛ፣ ከዳተኛና ወንጀለኛ ትሆናለህና።
➡️ በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ትዕግስትን (ሶብርን) አጥብቀህ ያዝ፤ ትዕግስት ወደ መልካም ስራ (ቢር) ይመራል መልካም ስራ ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል።
ምንጭ፦ ሒልየቱል አውሊያእ (7/82)
➡️እውነተኛ ወንድማማችነት በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የሚገለጽ ነው። ለአላህ ብሎ መዋደድ ማለት ለወንድምህ መቆምና መደገፍ ነው።
➡️ ክርክርና ጭቅጭቅ ልብን ያድፋሉ፤ ሰላማችንን ያጠፋሉ። በሐቅ ላይ ብንሆን እንኳ ክርክርን መተው ለልብ ጥንካሬ ትልቅ ሚና አለው።
➡️ ትዕግስት (ሶብር) የሁሉም ስኬት መጀመሪያ ነው። ዛሬ የምናልፍባቸው ፈተናዎች በትዕግስት ካሳለፍናቸው ነገ የጀነት መግቢያ መንገዶቻችን ይሆናሉ።
"🫧በሕይወትና በሞት መካከል ምርጫ የለህም፤ በመጨረሻው መንገድህ ላይ ሞት አይቀሬ ነውና።

🍃በዱንያ ላይ ዘለዓለማዊነት የለም፤ እያንዳንዱ ነፍስ ሞትን ቀማሽ ናት!

🍃ነገር ግን በሐቅ መንገድ ወይም በጥመት መንገድ ላይ በመጓዝ መካከል ምርጫ ተሰጥቶሃል።

🍃አላህ ለባሮቹ የመዳኛ መንገዶችን ግልጽ አድርጓል፤ ከጥፋት መንገዶችም አስጠንቅቋቸዋል።

🍃የተጓዦች ቁጥር ማነስ ሳይበግርህ የመዳኛውን መንገድ ተከተል፤ የጥፋተኞች ብዛትም ሳያታልልህ ከጥፋት መንገድ ራቅ።"



👇👇👇𝚓𝚘𝚒𝚗
╭┅━━━━•🌸🌸•━━━━━┅┐
⚘ ⚘ 
https://t.me/httpsLuqmane
╰┅━━━━•🌸🌸•━━━━━┅╯