መንሀጀሠለፍን ኑሩበትእጂ አታስመስሉበት
416 subscribers
126 photos
112 videos
272 links
ይህቻናል ዋናአላማው ዳእዋሠለፍያን ለቀጣይትውልድ ተደራሽእድትሆን ታስቦ የተከፈተነው
ተውሒድ የሁለት አገር ብርሃን ነው .!!!
التوحيد أولا
ከሱፍያ ወደ ኢኽዋንያ ፣ ከኢኽዋንያ ወደ ጀምዒያ ፣ ያደረከው ጉዞ ለለውጥህ መነሻ ሊሆንህ ይችላል እንጅ ንፁኋን ሰለፍያን እስከምትይዝ ድረስ ገና አልተለወጥክም.!!!

ከዶርህ አጎብዳጅነት አውጥተህ ለድሞክራሲ ደሪህ ካ
Download Telegram
7ቱ_ቁርአን ውስጥ_ የተጠቀሱ ከንቱ ምኞቶች

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ تُرَٰبًۢا﴾
" ዋ ምኞቴ! ምነው አፈር በሆንኩ "
[ሱረቱ ነበእ 40]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى قَدَّمْتُ لِحَيَاتِى﴾
" ዋ እኔ! ምነው በሕይወቴ (መልካምን ሥራን) ባስቀደምኩ ኖሮ "
[ሱረቱል ፈጅር 24]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى لَمْ أُوتَ كِتَٰبِيَهْ﴾
" ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ "
[ሱረቱል ሃቀህ 25]

⇦ ﴿يَٰوَيْلَتَىٰ لَيْتَنِى لَمْ أَتَّخِذْ فُلَانًا خَلِيلًۭا﴾
" ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ አድርጌ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ "
[ሱረቱል ፉርቃን 28]

‏⇦ ﴿يَٰلَيْتَنَآ أَطَعْنَا ٱللَّهَ وَأَطَعْنَا ٱلرَّسُولَا۠﴾
" ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ "
[ሱረቱል አህዛብ 66]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى ٱتَّخَذْتُ مَعَ ٱلرَّسُولِ سَبِيلًۭا﴾
" ዋ ምኞቴ! ከመልክተኛው ጋር ቀጥተኛን መንገድ ይዤ በሆነ "
[ሱረቱል ፉርቃን 27]

⇦ ﴿يَٰلَيْتَنِى كُنتُ مَعَهُمْ فَأَفُوزَ فَوْزًا عَظِيمًۭا﴾
" ወይ ምኞቴ! ታላቅ ዕድልን አገኝ ዘንድ ከነሱ ጋር በሆንኩ "
[ሱረቱ ኒሳእ 73]

☞ ሁሉም የሟቾች ምኞት ናቸው ቀብር ውስጥ ያሉት ሰዎች ምኞታቸው ወደ ዱንያ አንዴ መጥተው ለአኺራቸው ጥሩን ነገር መስራት ነው ...

☞ ቀብር ገብተህ/ሽ አንተም.አንቺም ይህን ከምትመኝ/ኚ ነፍስህ/ሽ አካልህ/ሽ ውስጥ እስካለች ድረስ ለአኺራህ አስቀድም/ሚ።

አላህ ሆይ! ከነዚህ ከንቱ ምኞቶች በእዝነትህ ጠብቀን አሚን ያረብ
━━━━━🍃🌸🍃━━━━━
👍32
ጂብሪል አለይሂ ሰላም አንድ ቀን ያለወትሮው ረሱል ﷺ ዘንድ ፊቱ ጠቁሮ መጣ።

ረሱል ﷺ በዚህ ሁኔታ ሲያዩት ግዜ፦"አንት ጅብሪል ምነው ፊትህ
እኮ ተቀየሯል?" አሉት።

ጅብሪልም፦"አንተ ሙሀመድ አሁን የመጣሁት ሰዐት የጀሀነም አቀጣጣዮችን አላህ እንዲያቀጣጥሏት ባዘዛቸው ሰዐት
ነው።

ጀሀነም እውነት መሆኗን ላወቀ፣

እሳትም እውነት መሆኗን ላወቀ፣

የቀብር ቅጣት እውነት መሆኑን ላወቀ፣

የአላህ ቅጣት ትልቅ መሆኑን ላመነ ሰው ከሷ መትረፉን ሳያረጋግጥ መረጋጋት የለባትም" ብሎ መለሰላቸው።

ረሱል ﷺ፦"አንተ ጅብሪል እስቲ ስለጀሀነም ንገረኝ" አሉት።

ጅብሪልም አለይሂ ሰላም ፦"አዎ አላህ ጀሀነምን 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ቀይ እስክትሆን ድረስ፡፡

ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ነጭ እስክትሆን ድረስ

ከዚያም 1ሺህ አመታት አቀጣጠላት ጥቁር እስክትሆን ድረስ....

.አሁን /ጀሀነም ጥቁር ጨለማማ ናት።ነበልባሏ እና ፍሟ አይጠፋም

ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አሏህ እምላለሁ. የመርፌ ቀዳዳ ያህል ጀሀነም ብትከፈት ዱንያ ላይ ያለ ነገር ሁሉ ከሙቀቷ ብዛት ይቃጠል ነበር።

ያ በዕውነት ነብይ አድርጎ በላከህ አሏህ

እምላለሁ.ከጀሀነም ሰዎች ልብስ አንዷ በሰማይና በምድር መሀከ

ብትንጠለጠል ከግማቱ የተነሳ ምድር

ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይሞት ነበር።

ያ በዕውነት ነቢይ አድርጎ በላከህ አሏህ

እምላለሁ...አላህ ቁርአን ላይ የጠቀሰው

የጀሀነም ሰንሰለት አንዷ እንኳን በተራራ

ላይ ብትቀመጥ ተራራው እስከ ሰባተኛው

መሬት ድረስ ይቀልጣል።

ያ በዕውነት በላከህ አሏህ እምላለሁ.

በምዕራብ አንድ ሰውዬ በጀሀነም ቢቀጣ

ኖሮ በምስራቅ ያለው ሰው ከሙቀቷ ብዛት

ይቃጠል ነበር።

ሙቀቷ ጠንካራ ነው፣ጥልቀቷ እሩቅ/ስምጥ ነው፣ጌጧ ብረት

ነው፣መጠጧም የፈላ ውሀ እና ምግል

ሲሆን፣ልብሷም ከእሳት የተለካ ነው።

7 //በሮች አሏት። ለያንዳንዱ በር የተለያዩ

በሮችም አሏቸው ለሴቶችም ለወንዶችም"

ብሎ መለሰላቸው።

ረሱልም ﷺ ፦"እኛ እንደምንጠቀመው

አይነት በር ነው?" ብለው

ሲጠይቁት

ጅብሪልም አለይሂ ሰላም፦" አይ አይደለም

ከላይ ወደ ታች የተደረደረ በር

ነው።ከአንደኛው በር ወደ ሌላኛው በር

ያለው ርቀት 70 አመት ያስኬዳል።


እያንዳንዱ በር ከሌላኛው በር ግለቱ በ70 እጥፍ ይበልጣል።

የአላህ ጠላቶች ወደጀሀነም ይነዳሉ። ልክ በሯ ላይ እንደደረሱ ዘባኒያ የተባሉ የጀሀነም ወታደሮች በሰንሰለት ይቀበሏቸዋል። ሰንሰለቱን በአፋቸው አስገብተው በመቀመጫዎቻቸው ያስወጡታል።

ግራ እጁ ከአንገቱ ጋር ይጠፈራል ቀኝ እጁም ከልቡ ጋር ተጠፍሮ
ይታሰራል።

እያንዳንዱ ሰው ከሸይጧን ቁራኛው ጋር በሰንሰለት ይጠፈራል።

ከዚያም በፊቶቻቸው እየተጎተቱ መላዕክት ደግሞ ከብረት በሆነ መዶሻ ይመቷቸዋል።

ከዚህ ጭንቀት ለመውጣት ሲሞክሩ ወደዛው ይመልሷቸዋል"ብሎመለሰላቸው።

ነቢያችንም ﷺ፦"በነዚህ በሮች የሚገቡት እነማን ናቸው?" ብለው ጠየቁት።

ጅብሪልም አለይሂ ሰላም "በታችኛው በር የሚገቡት

1//ሙናፊቆች

2//በዒሳ አለይሂ ሰላም ማዕድ የካዱት

3//"የፊርዐውን ቤተሰቦች...ሲሆኑ የበሩ ስም ሀዊያ ይባለል።

ሁለተኛው በር ስሙ ጀሂም ሲሆን በሱ የሚገቡት ሙሽሪኮች ናቸው።

ሶስተኛው በር ሳብያኖች ነው የሚገቡበት ስሙም ሰቀር ይባላል።

በአራተኛው በር ኢብሊስ እና ተከታዮቹ መጁሶችም ይገቡበታል ስሙም ለዟ ይባላል።

አምስተኛው በር የሁዶች የሚገቡበት ሲሆን ስሙም ሁጠማ ይባላል።

ስድስተኛው በር ስሙ ዐዚዝ ሲሆን የሚገቡበት ክርስቲያኖች
ናቸው።"ብሎ ከዘረዘረላቸው በኋላ ሰባተኛውን ለመጥቀስ ፍርሀት
ያዘው።

ነቢያችንም ﷺ፦"ሰባተኛውን በር ለምን አትነግረኝም?" ብለው
ሲጠይቁት

ጂብሪልም አለይሂ ሰላም፦"በሱ በር

የሚገቡት ካንተ ዑመት የሆኑ ትላልቅ

ወንጀሎችን ሰርተው ሳይቶብቱ/ሳይፀፀቱ

የሞቱ ናቸው" ብሎ ሲመልስላቸው

ረሱል ﷺ እራሳቸውን ስተው ወደቁ።

ከዚያም ጅብሪልም የረሱልን ﷺ

ጭንቅላት ታፋው ላይ አሳረፈ።ልክ ሲነቁ

ቀና አሉና፦"አንተ ጅብሪል ችግሬ በዛ

ሀዘኔም በረታብኝ ከኔ ኡመት ጀሀነም

ሚገባ አለ እንዴ?" ብለው ሲጠይቁት

ጅብሪልም አለይሂ ሰላም፦" አዎን ካንተ

ኡመት የትላልቅ ወንጀል ባለቤቶች

ይገባሉ"ብሎ መለሰላቸው፣

የዐይናችን ማረፊያ ከእናት ከአባት በላይ ለኛ አዛኝ የሆኑትም ነቢይ ﷺ ይሄን

ሲሰሙ ተንሰቅስቀው ማልቀስ

ጀመሩ።ጅብሪልም አብሯቸው አለቀሰ።

/ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱለሏህ/

ረሱል ﷺ ይህኔ፦"ያጅብሪል አንተም

ታለቅሳለክ?" አሉት ።
ጅብሪልም፦"እንዴት አላለቅስ የኔንስ

መጨረሻ በምን አውቃለሁ?

እብሊስ እኮ ከመላእክት በላይ አላህን ይገዛ ነበር አላቸው ።
__መጨረሻችንን አላህያሳምርልን ከጀሀነብቅጣት
አላህይጠብቀን💦💦
-------------------
━━━━━🍃🌸🍃━-----
👍21
Audio
🌸ዉብ የሆነ ቲላዋ🌸

     🌸 መልካም ለይልይሁንላችሁ🌸

🌸ቁርአን የልባችን መዳኒት 🌸
🌸የጭንቀት ሁሉ መፈወሻ መዳኒት🌸

      🌹🌸

               🌹🌸

                    🌹🌸

                        🌹🌸

                            🌹🌸

                               🌹ኝ    ✍️

https://t.me/httpsLuqmane

https://t.me/httpsLuqmane
👍31
القارئ إسلام صبحي | الذي خلقني فهو يهدين والذي هو يطعمني ويسقين
💭🌸خدمة تلاوات🎧
﴿ٱلَّذِى خَلَقَنِى فَهُوَ يَهْدِينِ ۝ وَٱلَّذِى هُوَ يُطْعِمُنِى وَيَسْقِينِ ۝ وَإِذَا مَرِضْتُ فَهُوَ يَشْفِينِ ۝ وَٱلَّذِى يُمِيتُنِى ثُمَّ يُحْيِينِ ۝﴾



➹እርሱ ያ የፈጠረኝ ነው፡፡ እርሱም ይመራኛል፡፡
ያም እርሱ የሚያበላኝና የሚያጠጣኝ ነው፡፡
በታመምኩም ጊዜ እርሱ ያሽረኛል፡፡

➹ያም የሚገድለኝ ከዚያም ሕያው የሚያደርገኝ ነው፡፡ ሱረቱ አልሹዐራ {78-110}


https://t.me/httpsDAWASELFABEWBITAWLO


https://t.me/httpsDAWASELFABEWBITAWLO
الــــســـلام عـــلــــكـــم
ورحـــمــــة اللـه وبـــركـــاتــه
بــســم اللـه الــرمن الــرحــيـم

🔺🔺🔺 እነሆ ዛሬ የጀግናዉን እና
የአይበገሬዉን የጦር ሜዳ ጀግና የሆነዉን
🔺🔺🔺🔺🔺ኹበይብ ረደላሁ አንሁ
ታሪክ ቀንጨብ አደርጋለሁ

እደሚታወቀዉ የነብያችን ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም
ሰሀቦች ከልጅ:ከቤተሠብ:ከንብረት : ከእረፍት አኼራን ያስቀድሙ ነበር። የቁጥር ማነሳቸዉ ሳይገድባቸዉ ለወጡበት ለተነሡበት አላማ ድልን ተጎናፃፊ ነበሩ።
ነፍሳቸዉን አሳልፈዉ ለአላህ ትእዛዝ ይሰጡ ነበር።
ከነዚህ ከዋክብት ሰሀቦች መካከል ታዋቂዉና ሁሌ ታሪኩ ቢሰማ የማይጠገበዉ ኹበይብ ረደላሁ አንሁ ታሪክ እነሆ እያልኩኝ እደሚከተለዉ አቀርባለሁ።

➤ ዉዱ ጀግናችን ኹበይብ በአንድ ጀሐድ ላይ ነፍሱን ለአላህ ሰጥቶ እስልምናን የበላይ ለማድረግ የካፊሮች የቁጥር ብዛት ከምንም ሳይቆጥር በአላህ ፍቃድ ታግዞ ካፊሮችን መድረሻ ሲያሳጣቸዉ በፊትም በሗላ በቀኝም በግራ በየ አቅጣጫዉ ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች በሚገባ መልኩ አገታቸዉን እየቀላ መጣል ጀመረ። የሚገርመዉ እርሱ ብቻ ሳይሆን በዚህ ሁኔታ ላይ ፈረሷ ሳትቀር ተቆጥታ ብዙ ካፊሮችን ገድላለች።
የሆነዉ ሆነና የኹበይብን የጦር ስልት በማየት ግራ የገባቸዉ ካፊሮች ዘዴ መዘየድና ኹበይብን በእጃቸዉ ማስገባት ፈለጉ። ከብዙ ድካም በሗላ ኹበይብ በካፊሮች ቁጥጥር ስር ሆነ ኹበይብን በእጃቸዉ ያስገቡት ካፊሮች ኹበይብ ጦር ሜዳ ላይ ያደረሠዉን ጥቃት ለመመለስ መማረክና መያዝ በቂ ሆኖ ስላልታያቸዉ። ኹበይብን ቀላል በሆነ መልኩ መግደል የለብንም አሉ እና አሰቃይተ ነዉ መግደል ያለብን ብለዉ
ወሰኑ። ኹበይብን በእረሀብና በዉሀ ጥማት አስቃይተን መግደል አለብን አሉ።
ለዚህም ሲባል ኹበይብን ከሰዉ ጋ በማይገናኝበት መልኩ ደባቃማ ጎጆ ዉስጥ ከዉሀና ከምግብ አግልለዉ አገቱት። ለ15ቀን ያክል አቆዩት እነዚያ ካፊሮች ከ15ቀን በሗላ ኹበይብ ሞቷል በሚል ተስፋ ወደታሰረበት ጎጆ ሲሔዱ
ኹበይብ የበለጠ አምሮበታል
ያአላህ። በዚህ ጉዳይ ግራ ተጋብተዉ ካፊሮቹ🔺 የኹበይብን ሚስጥር ለማጥናትና አስካሁን ያልሞተበትን ምክንያት ለማወቅ ሲባል በድብቅ
የሚከታተል ሰዉ መርጠዉ አስቀመጡ።
የኹበይብን ሚስጥር ሊከታተል የተቀመጠዉ ሰዉ ያየዉን አስከራሚ ነገር ለሰዎቹ እድህ ሲል ነገራቸዉ።
△△ማን እደሚያመጣዉ ባይታየኝም ለኹበይብ ሁልጊዜ አድስና የሚያምር የሆነን የወይን እሸት ሲመጣለትና ሲቀበል አየሁ ዉሀ በጠማዉ ጊዜና መስገድ በፈለገ ጊዜ እንድሁ የሠማይ ዳመና ወደ ኹበይብ ተሰባስበዉ በመግባት ሲዘነበሉለት አየሁ አለ>>
በዚህ መልኩ ኹበይብን ማጥፋት እደማይችሉ የተረዱት ካፊሮች ሌላ ዘደን መዘየድ ፈለጉ ።
ይህም ኹበይብን በስቅላት መግደል ነበር።
የሆነዉ ሆነና ኹበይብን ወደ ስቅላት ቦታ ወሰዷቸዉ።
ክፍል ሁለት ይቀጥላል።

🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ክፍል ሁለት ይለቀቅ 👍
አይ አይለቀቅ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/httpsLuqmane
👍5
‏﴿وَالَّذينَ يَقولونَ رَبَّنا هَب لَنا مِن أَزواجِنا وَذُرِّيّاتِنا قُرَّةَ أَعيُنٍ
وَاجعَلنا لِلمُتَّقينَ إِمامًا﴾
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉ቁርአን በትኩረት ማዳመጥ ምንዳ የምናገኝበት ትልቅ ኢባዳ ነው።

🌹"ምርጥ ቲላዋ



      "🌹🇸🇦
         "🌹🇸🇦
             "🌹🇸🇦
                 "🌹🇸🇦
                    "🌹🇸🇦
                       "🌹🇸🇦

መልካም ውሎ ተመኘሁላችሁ
ቁርዓን የልብ መድሃኒት !

🌺 ዑስማን ኢብኑ አፋን እንዲህ አለ፦ቀልባችን(ልባችን) ከኃጢአት ብትፀዳ ኑሮ የጌታችንን ንግግር/ቁርኣንን ባልጠገብነው ነበር።
                    

https://t.me/elefiyabemrtikos

https://t.me/httpsLuqmane
1
رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ🌺
🍃🌻
Audio
ሱረቱል አል _ዒምራን

ቃሪዕ

ሚስባህ ሳኒ ሀፊዘሁሏህ

🌹ጥፍጥ ያለች የንጋት ግብዣ
                   

      ➘➘ተጋበዙልኝ➘➘
                   

     ቁርአን የልብ መድሃኒት ነው❗️
                   

      🌹መልካም ውሎ ይሁንላችሁ🌹
                   
=====◉◉◉🌺🍃◉◉◉=====◉

ትደመጥ ትደመጥ

Like, share, join

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/httpsLuqmane

https://t.me/elefiyabemrtikos
https://t.me/httpsLuqmane
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በውዱ ነቢያችን ላይ ሰለዋት አውርዱ

اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمد
اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمدﷺ
اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمدﷺ
اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمدﷺ
اللهم صّلِ وسَلّمْ عَلۓِ نَبِيْنَا مُحَمدﷺ


  ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
👍3