La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
50 አመት መቃም
Sadat
50 አመት መቃም
ጥናተ መንዙማ ክ 6
Sadat
ጥናተ መንዙማ ክ 6
ተፈሪ ቦጋለ
Sadat
ተፈሪ ቦጋለ።
ስለ ሸህ ሁሴን ጂብሪል በአጭሩ ስሙና እውነቱን ፍረዱ።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በደንብ ሼር አድርጉት። ዲናችንን ከመፈራረስ እንታደግ።
ጥናተ መንዙማ ክ 8
Sadat
ጥናተ መንዙማ ክ 8
ዞር በልልኝ
Sadat
ዞር በልልኝ
ጫትና መንዙማ
Sadat
ጫትና መንዙማ
ቤተሰብ ይወቀው
Sadat
ቤተሰብ ይወቀው
እጅ ከፍንጅ ክፍል 7
Sadat
እጅ ከፍንጅ ክፍል 7
አላህ ያደረገልን
Sadat
አላህ ያደረገልን
አህባሽ አቤት ውሸት
Sadat
አህባሽ አቤት ውሸት
የህዝቡ ስቃይ
Sadat
የህዝቡ ስቃይ
በማስረጃ
Sadat
በማስረጃ
ጥናተ መንዙማ ክ 9
Sadat
ጥናተ መንዙማ ክ 9
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: 10]👌

#ቁርኣን
ነቢዩﷺ እንዲህ አሉ፦
[[ሁሉም ኡመቶቼ(ህዝቦቼ) ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሰው ሲቀር፤]
ለነቢዩም ተባሉ፡ ማነው ጀነት ግባ ተብሎ እምቢ የሚለው?
እሳቸውም [እኔን የታዘዘኝ ሰው በእርግጥ ጀነት ገባ ፤እኔን ያመፀኝ(ትእዛዜን) አልቀበልም ያለው ሰው እምቢ ብሏል።]]
ቡኻሪዘግቦታል።
⚘ ንፁህ ወረቀቶች በጣም የሚጎዳቸው የእርሳሶቹ ጫፍ ነው። ጥሩ ልብን የሚሰብረው ደሞ ብዙ ጊዜ ይቅርታ ማብዛት ነው።
La tehzen
🌹🌸🌹🌸🌹🌸🌸🌹🌸🌹🌸🌹 🌹🌸ሁረል = ዐይን🌺🌹 ~ ክፍል ሁለት የጀነቷ አበባ ======== የአላህ መልእክተኛ (ሰ ዐ ወ) እንዲህ ብለዋል… ‹ከጀነት እንስቶች መካከል አንዲት ሀውራ ወደ ምድር ብትመለከት ከምስራቅ እስከ ምእራብ ብርሃኗ ያንፀባርቃል ፣ ባማረ ሽታም ምድርን ባወደች ነበር። በጭንቅላቷ ላይ የምታደርገው ከዱኒያና ከውስጧ ካለ ሁሉ የተሻለ ነው› ቡኻሪ ዘግበውታል ሻሾ ከዱኒያና በውስጦ…
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

🌹ሑረል ዓይን🌹

~ ክፍል ሶስት (3)

የጀነቱ ሙሽራ የልቡ በር ተከፍቶ በሰፊ ደረቱ ላይ አስተኝቶት ንግግሯና ጨዋታዋ አስደስቶት ይስማታል። ከሑረል ዐይኗ ጋር በመሆኑ እርካታ ተሰምቶታል።


አንድ ለሊት በጀነት ውስጥ

በአላህ የእዝነት ስረገላ ላይ እየጋለብን ጉዞአችንን ቀጥለናል። የጀነቱ ሙሽራ ከወርቅ የተሰሩ ደረጃዎችን እየረገጠ ወደተዘጋጀለት ፎቅ አመራ። በፎቁም ውስጥ ከውጪ ውስጡ ከሚታይ ከውስጡ ውጩ የሚታይ ዙሪያው በከበረ ድንገይ ያሸበረቀ ጣራው በአልማዝ ያጌጠ ልዩ ወደሆነ ክፍል አቀና። በክፍሉ ውስጥ ክንፍ ያለው አልጋ አለ። ሰባት መቶ ፍራሽ ተደራርቦበታል። የብርሃኑም አንሶላ ከፍራሹ ላይ ተነጥፎበታል።


በወርቅ የተንቆጠቆጡ ካባና ጫማውን ለብሶ… በለሰለሰ የሀር ምንጣፍ ላይ እግሮቹን ዘርግቶ አናቱን ከለሰለሰ ትራስ ላይ አሳርፎ በተኛበት ቆንጆዋ ሚስቱ ሑረል አይን ዳሌዋን እያወዛወዘች መጣች። ወደሶው ሲዞር ፊቱን በጉንጮቹ ላይ እንደመስታወት ተመለከተ። ከመስታወትም የበለጠ ንፁህ ነበር። መዳፏን ሲዳብስ ከሀር የበለጠ ለስላሳ ሆኖ አገኘው። የባቷ መቅኔ ከአጥንቷና ስጋዋ በላይ ይታያል።


የውድ ሚስቱን ደረት ተደግፎ ዝርግትግት ብሎ ተኛቶል። ጣፋጭ ከሆነ አንደበቷ ማራኪ ዘፈኗን በጆሮው ስታንቆረቁረው ልቡ ጠፍቶ በደስታ ያዳምጣል።

በአልጋው ላይ አንገት ለአንገት ተቃቅፈወወ አርባ አመት ካስቆጠሩ በኃላ ጭንቅላቱን ወደ ላይ ከፍ ሲያደርግ ሌላኛዋ የጀነት ሚስቱ በፈገግታ ታጅባ ‹አንተ የአላህ ወዳጅ ለኛስ ተራ አይደረሰንምን› በማለት ትጠይቃለች። ከፍ ባለ ድምፆ ትጣራለች። እሱም ማንነቷን ይጠይቃል። እንዲህ ስትልም ትመልሳለች።

እኔ ማለት አላህ እንዲህ በማለት ከጠቀሳቸው እንስቶች መካከል ነኝ።

…وَلَدَيْنَا مَزِيدٌ

…እኛም ዘንድ ጭማሪ አልለ፡፡
[ቃፍ 35]

አልጋው በክንፎቹ ወደ እርሶ ይበራል። እዚያ እንደደረሰም መጀመሪያ እንደተመለከታት በመቶ ሺህ እጥፍ አምራ ያገኛታል። ዞማ ጸጉር ፣ ቀይ መልከ መልካም ቁመናዋ የሚማርክ በተለይ አይኗ! ዓይኖቹ ዓይኖቿን ሲመለከቱ ፈዘው ቀሩ። ከኮቡም በላይ ያምራሉ። የሚሰማው ድምፆ በደም ስሩ ሰርፆ መንፈሱን አድሶታል። ከሶ ጋርም ተቃቅፈው አርባ አመትን ያስቆጥራሉ። ከአርባ አመት ቡሃላ ጭንቅላቱን ወደ ላይ ሲያቀና የቤቱን ጣራ ሰንጥቆ የሚገባን ብርሃን ይመለከታል። በእይታው ባገኘው ብርሃን ተገርሞና ተደንቆ ጠባቂውን መላኢካ ይጠይቀዋል። መላኢካውም። ‹የዱኒያ ሚስትህ ከጀነቷ ሑረል ዐይን ጋር ተቃቅፈህ ስትመለከት ፈገግ አለች። የምታየውን ወደ ውስጥ ሰርፆ የገባው ብርሃን የፊት ለፊት ጥርሷ ያመነጨው ነው። ከአንተ ጋር በድሎት ሀገር አብራህ ትኖራለች።› በማለት ይመልስለታል።

እርሷ ወዳለችበት አቅጣጫ ያቀናል። ቀልበን በሚሰነጥቅ አንደበቷ ‹አንተ የአላህ ወዳጅ የኔ ተራ አልደረሰምን? ትለዋለች። እሱም ማንነቷን ይጠይቃታል።።እሷም ትመልሳለች ‹እኔማ አላህ እንዲህ ብሎ ከገለፃቸው መካከል አንዷ ነኝ…


ከዓይኖች መርጊያ ለእነርሱ የተደበቀላቸውን (ጸጋ) ማንኛይቱም ነፍስ አታውቅም፡፡
[ሱጃዳህ 17]

አልጋው በሮ ያለችበት ቦታ እንደደረሰም ከመጀመሪያ ቁንጅናዋ መቶ ሺህ እጥፍ አምራ ያገኛታል።

ውጫዊ ውበቷ ይቅር……

የፊቷ ውበት ሲገለፅ ምህዋሯን ለቃ ትሄዳለች ፤ ፈገግታዋ እንደመብረቅ ብልጭታ ያበራል› ከባሏ ጋር ስትተቃቀፍ ፀሀይና ጨረቃ በጋራ ለምድር የሰጡትን ብርሃን ይመስላል።…


ጣፋጭ ህልም… ሁሁሁ

ወፍቅና ያረብ አሚን አትሉም ወይ ያ ጀምዓ…

ቤተሰቦቼን ተሰናብቼ ወደ ሐጅ በማድረግ ላይ ነኝ። በመንገዴ ላይ ያጋጠሙኝን ውጣ ውጣውረዶች አልፌ መካ ገባሁኝ። የአላህን ቤት በመዞር ላይ ሳለሁ አንድ ሰው ቀልቤን ሳበው። ወደ እርሱም ቀረብኩና የሚያደርገውን ዱዓ ለመስማት ጆሮዮን ቀሰርኩኝ።

«ጌታዮ ሆይ! የጓደኞቼን ሀጃ ፈፅመሃልና የኔን ጉዳይ ፈፅምልኝ። እያለ በለቅሶ ጌታውን ይለምናል። ከዚህ ውጭ ሌላ ዱዓን አይጨምርም። ምክንያቱ ምን አደሆነ ለማወቅ ብዮ ጠያቅኩት። እሱም «ከሩሞች ጋር ለመዋጋት ሰባት ጓደኛሞች ሆነን ከሀገራችን ወጣን። ሁላችን በጥላቶቻችን ተማረክን። ስለመሸ አንድ ክፍል ውስጥ አስረውን በሩን ቆልፈው ሄዱ።


በህልሜ የሰባቱ ሰማይ በሮች ተከፍተው በራፍ ላይ በእጃቸው ፎጣን የያዙ እንስቶች ቆመዋል። የጓደኞቼ አንገት ተራ በተራ በሰይፍ ሲቀላ የጀነት እንቡጥ ፅጌረዳ እንስቶች ተራ በተራ እየወረዱ በያዙት ፎጣ አንገታቸው ላይ ያለውን ደም ጠርገው ይመለሳሉ። በሩም ይዘጋል። አንድ የሰማይ በር ብቻ እንደተከፈተ ቀርቷል።


በእድሜ ከሌሎቹ አነስተኛ ስለነበርኩኝ አንድ የሮም ጦር አዛዥ አዝኖ አስለቀቀኝ። ክፋቱ የሰማይ በር ላይ ፎጣ ይዛ የምትጠባበቀኝ እንስትም እንዲህ ስትል ሰማኃት… ምነኛ ምርጥ ነገር ነው ያመለጠህ አይኔ እያየ በሩ ተዘጋ። በህልሜ ያየሁት ክስተት ጠዋት በእውን ተፈፀመ። የምታየው ዱኣም ባመለጠኝ እድል ቁጭት የተነሳ ዘወትር የሚደረገው ነው። በማለት መለሰለኝ።

ይቀጥላ ውድ የኢስላም ልጆች በአላህ መልካም መገጠም ከሆነ…

እናም ውዶቼ የመልካም ስራ ትንሽ የለውምና በመልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ይኖርብናል!!

ውድ ስጦታ ከጀነቱ ሙሽራ…

ለውድ ሚስቱ ለቆንጆዋ ንግስት ሑረል ዓይን ስጦታን ሊያበረክትላት አስቧል። ከምንም በላይ ያማረና እሷን በጣም የሚያስውባትን ውድ ጌጥ ሊሰጣት ፈልጓል።

ውድ ነገሮች ሁሉ ለውዶቻችን የተገቡ ናቸው አይደል እናማ ተከተሎኝ…

ሁለት እርምጃ እንደተራመደ አገልጋዩ ያሰበውን ከአእምሮው አንብቦ የጌጣጌጥ ማስቀመጫ የሆኑ ብዛት ያላቸው ካዝናዎችን እየከፋፈተ የሚፈልገውን እንዲመርጥ በታላቅ ትህትና ጋበዘው።

ከአልማዝ ከሉል የተሰሩት ጌጣጌጦች አፍዝዘውት ለረዥም ግዜ ሲያማርጥ ቆየ። ፈገግ አለና እፁብ ድንቅ የሆነ ከአልማዝ የተሰራ የአንገት ጌጥ በቀይና በአረንጓዴ ክፋይና ሀር የተጌጠ የፀጉር ሪቫን እንዲሁም ውብ የሆኑ ሸዋሊያና ቀለበቶችን መርጦ መያዝ ወደ ሁረል ዓይኗ ሚስቱ ሄደ።

እሷ ጋርም እንደደረሰ በስስት እየተመለከታት በፍፁም የደስታ ስሜት ተውጦ ዓይኗን እንድትጨፍን ካደረገ በኋላ ጌጣጌጦቹን አውጥቶ በአንገቷ ላይ ሐብሉን በጣቷ ላይ ቀለበቱን አጠለቀ።

ዐይኗን ልትገልጽ ስትል በእጁ ካስጨፈናት በኋላ ሸዋሊያውን አደረገላት። ምንም እንኳ ጌጣጌጦቹ በጣም ድንቅ ቢሆኑም የእርሷ ቁንጅና በቃላት ስለማይገለጽ በውበቷ የተዋጡ መሰሉ። በዕርግጥም ተውጠዋል።

አንገቷ ስር ከሳማት ቡሃላ ወደ ጆሮዋ ተጠግቶ እንዲህ አላት…
«አንቺን የመሰለች ቆንጆ ሚስት ጌታዮ ስለጠኝ ምስጋና ይገባዋል።

«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፡፡ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው»…
አል ዙመር =74

ይቀጥላል በአላህ መልካም ፍቃድ!

#share #ሼር

https://t.me/httpsLatahzen
📡 ኢስላማዊ ሥነ-ምግባር 🌹
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉┄┄

「』(ክፍል 1) 『」
┉┉✽̶»̶̥🌼»̶̥✽̶┉┉

ሥነ-ምግባር ቁርዐን ውስጥ
┉┉✽̶»̶̥🌸»̶̥✽̶┉┉

ሃያልና አሸናፊው አላህ የተከበረ ቁርዐኑን ያወረደው ለነብያቱ መሪ መንገድን ሊያበራላቸው ሲሆን ይህ ብርሃን ከመንገዶች ሁሉ ሙሉ ወደሆነው የሚመራቸውና የተመረጠም ነው። ይህ መንገድ መልካም ስነምግባርን የሚያላብስ፣ ጉብጠትን የሚያርቅ፣ ብልሹውን የሚስተካክል ነው። ስለሆነም ያማረ ስነ-ምግባርን በሚመለከት የመልካም ስነ-ምግባር ባለቤትን የሚያሞካሽና መልካም ስነ-ምግባር የሚሠሩትን የሚያሞግሱ በርካታ መረጃዎች በቁርዐን ውስጥ መምጣታቸው የሚደንቅ አይደለም። እንዲሁም በጣም በርካታ የቁርኣን መረጃዎች የአላህ ባርያዎች የአላህን ውዴታና ከአላህ የሚገኘውን ምንዳ ያገኙ ዘንድ ሊላበሷቸው ስለሚገቧቸው ባህሪያት አትተዋል።

የሉቅማን ምክሮች
┉┉✽̶»̶̥🌹»̶̥✽̶┉┉

ሃያልና አሸናፊው አላህ፣ ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ጥቅል የሆኑ ምክሮችን በመከሩበት አጋጣሚ ስለባህርይው ይነግረናል። ቁርኣን በሉቅማን ምዕራፍ ቁጥር 13 ላይ:-

وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ ۖ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ
“ሉቅማንም ለልጁ እርሱ የሚገሥጸው ሲኾን ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣኦትን) አታጋራ። ማጋራት ታላቅ በደል ነውና። ያለውን (አስታውስ)”
(📕ሉቅማን 31፤13)

ሉቅማን ምክራቸውን የጀመሩት ከሁሉም የላቀና የከበደ የሆነውን እንዲሁም አጥብቆ ሊይዙት የሚገባ የሆነውን ሃያልና አሸናፊው አላህን ብቻ ማምለክ እንዳለበት ነው። ይህም የነገሩ ሁሉ ቁንጮና የኢስላም መሠረት ነው። ከዚያ የጥራትና የልዕልና ባለቤት የሆነውን አላህን ታላቅነቱን፣ በሁሉም ነገሮች ላይ ያለውን እውቀት፣ ያብራሩለታል፡-

يَا بُنَيَّ إِنَّهَا إِن تَكُ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ فَتَكُن فِي صَخْرَةٍ أَوْ فِي السَّمَاوَاتِ أَوْ فِي الْأَرْضِ يَأْتِ بِهَا اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ
“(ሉቅማንም) ልጄ ሆይ! እሷ (ደጊቱም ሠናይቱም ሥራ) የሰናፍጭ ቅንጣት ክብደት ያህል ብትኾንና በቋጥኝ ውስጥ ወይም በሰማያት ውስጥ ወይም በምድር ውስጥ ብትኾን አላህ ያመጣታል። አላህ ሩህሩህ ውስጠ ዐዋቂ ነውና”
(📕ሉቅማን31፤16)

ከዚያም ሉቅማን ልጃቸውን ሃያልና አሸናፊው የሆነው አላህ ያዘዘውን ግዴታ እንዲወጣ ምክራቸውን ቀጥለው፣ ሶላት ላይ ቀጥ እንዲል፣ በመልካም እንዲያዝ፣ ከአፀያፊ ተግባር እንዲርቅ፣ በሚያጋጥሙት ችግሮች በትዕግስት እንዲወጣቸው ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-

يَا بُنَيَّ أَقِمِ الصَّلَاةَ وَأْمُرْ بِالْمَعْرُوفِ وَانْهَ عَنِ الْمُنكَرِ وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ
“ልጄ ሆይ! ሰላትን አስተካክለህ ስገድ፤ በበጎ ነገርም እዘዝ፤ ከሚጠላው ሁሉ ከልክል በሚያገኝህ መከራ ላይ ታገስ ይህ በምር ከሚይያዙ ነገሮች ነው” (📕 ሉቅማን31፤17)

ይህ ቁርኣናዊ መልዕክት አማኝ አንቀጹ ውስጥ የተወሱትን ተግባሮች የግዴታ መፈጸም እንዳለበት ጠቋሚ ነው። ዐብደላ ኢብኑ ዐባስ አላህ ሥራቸውን ይውደድላቸውና:-

من حقيقة الإيمان الصبر على المكاره

“ከእምነት የእውነትነት መገለጫ ውስጥ መካከል በሚጠሉት ነገር ላይ የሚደረግ ትዕግስት ነው” ይላሉ።

አሁንም ሉቅማን ምክራቸውን በመቀጠል ልጃቸው ከአንዳንድ መጥፎ ባህሪያት መራቅ እንዳለበት እንዲህ ይመክሩታል፡-

وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ
“ጉንጭህንም (በኩራት) ከሠዎች አታዙር በምድርም ላይ ተንበጥርረህ አትሂድ አላህ ተንበጥራሪን ጉረኛና ሁሉ አይወድምና” (📕ሉቅማን31፤18)።

በመጨረሻም እራሡን እንዲያስተናንስ፣ በአረማመዱ የኩራተኛ አካሄድን እንዳይሄድ፣ ድምጹን ዝግ እንዲያደርግ ይመክሩታል፡-

وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِن صَوْتِكَ ۚ إِنَّ أَنكَرَ الْأَصْوَاتِ لَصَوْتُ الْحَمِيرِ
“በአካሄድህም መካከለኛ ኹን ከድምፅህም ዝቅ አድርግ ከድምጾች ሁሉ አስከፊው የእህዬች ድምጽ ነውና” (📕ሉቅማን፣ 19)።

ኑርአህመድ
ኢንሻአላህ ይቀጥላል ,,,,,,

https://t.me/resulinn
#እህቴ ሆይ! ለምን እራስሽን ትሸዉጃለሽ? ይህ
የሼይጧን ሴራ መሆኑን እረሳሽ!?

ምንም ሃጃ ሳይኖርሽ.....!!
ሙስሊም ወንድሜ ነው እንድትይ የሚያደርግሽ
#ዉዷ እህቴ ልብ በይ ከአጅ ነብይ ወንድ ጋር ምን ታደርጊያለሽ?!


#አስተዉይ ብዙ እህቶች እሱ ሙሲሊም
ወንድሜ ስለሆነ ብቻ ነው የማወራው
ደግሞ በፅሁፍ እንጂ በድምፅ ኣናወራም!?
የምትይው በፅሁፍ እንዲታወሪ ማን ፈቀደልሽ?

በዙ እህቶች የከሰሩት በዚህ እንደሆነ አታስተዉይምን?!
ብልጥ ከሆንሽ በሰዎች ትማርያለሽ

ሞኝ ከሆንሽ በራስሽ ሲደርስ ትማርያለሽ
እሱም ካላረመሽ

የሰዎች መታረሚያ ትሆኛለሽ
ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት

ጥንቃቄ አድርጊ
ለኔም ላንችም ነው

https://t.me/httpsLatahzen