ዝሙት አፀያፊ ነው አትቅረቡት!
ከከባባድ ወንጀሎች‼ ክፍል #1_(ዚና)_ዝሙት_ነው
ከቁርኣን ህግና ወደ ቀናው መንገድ መምራት የሰው ልጆች በመልካም ስነ–ምግባርና የላቀ በሆነ ስርኣት እንዲጠበቁ ማነሳሳቱና ከልቅናና ከጥብቅነት ከራቀ ባህሪ ማስጠንቀቁ ነው‼
ለዚህም አላህ ዝሙትን (ሀራም) ክልክል አድርጓል! እንዲያውም ከሌሎች ወንጀሎች በተለየ መልኩ አትፈፅሙት ከማለት ይልቅ "ዝሙትን አትቅረቡት" በማለት ገና በርቀት አስጠንቅቋል! ፀያፍ ተግባር መሆኑንም ተናግሯል:–
﴿وَلا تَقْرَبُوا الزِّنَى إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلاً﴾ الإسراء ٣٢
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ ፀያፍ/(ብልግና ነውና)፡ መንገድነቱም ከፋ!" [ኢስራእ: 32]
ጠንካራ በሆነ ተፈጥሮ ላይ ያለ ሁሉ ይፀየፈዋል፣ የንፁህ አዕምሮ ባለቤት የሆነ ሁሉ ይፀየፈዋል። በዚህች ዓለምና በመጨረሻይቱ አለም ቅጣትም ከዝሙት አስጠንቅቋል!! የዚህ ዓለም ቅጣት አግብቶ የማያውቅ ከሆነ በህዝብ ፊት መቶ ግራፋት ተገርፎ ለአንድ አመት ያህል ከሚኖርበት ሀገር ወደሌላ ሀገር ማባረር ሲሆን፣ አግብቶ የሚያውቅ ከሆነ ደግሞ ዝሙት የሰራው፣ ከትዳሩ ተፋቶ ይሁንም አይሁን፣ ሸሪዓዊ ብይኑ እስከሚሞት በዲንጋይ መወገር ነው‼
﴿الزَّانِيَةُ وَالزَّانِي فَاجْلِدُوا كُلَّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا مِائَةَ جَلْدَةٍ وَلا تَأْخُذْكُمْ بِهِمَا رَأْفَةٌ فِي دِينِ اللهِ إِنْ كُنْتُمْ تُؤْمِنُونَ بِاللهِ وَالْيَوْمِ الآخِرِ وَلْيَشْهَدْ عَذَابَهُمَا طَائِفَةٌ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ﴾ النور ٢
"ዝሙተኛይቱና ዝሙተኛው ከሁለቱ እያንዳንዳቸውን (ያላገቡ ከሆኑ) መቶ ግርፋትን ግረፉዋቸው፤ በእነርሱም በአላህ ፍርድ ርህራሄ አትያዛችሁ፡፡ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ እንደሆናችሁ (አትራሩ)፡፡ ቅጣታቸውንም ከምእምናን ጭፍሮች ይገኙበት፡፡" [አንኑር: 2]
የዝሙት ወንጀል አግብቶ ለሚያውቅ ሰው ትዳሩን ፈቶም ይሁን አይሁን በዚህች ዓለም በዲንጋይ ተወግሮ እስከ መገደል የሚያደርስ የከፋ ወንጀል ነው!! በጣም የሚያሳዝነው ወንጀሉ ይህን ያህል የከፋ ከመሆኑም ጋር እንደ ቀላል ከመታየቱም አልፎ አንዳንዶች ዘንድ እንደ ተራ ወንጀል እንኳን አለመታየቱ ነው። (አላህ ሂዳይ ይስጣቸውና) አንዳንድ ወጣቶች ትዳር ብለው ከያዙ በኋላ በትንሽ በትልቁም ነገር ተጨቃጭቀው ተፋተው በዚህ ፀያፍና ብልግና ተግባር ይሳተፋሉ፣ በተለይ አንዳንድ በዱኒያ የሰከሩ ሰዎች! ሀላል ባልሆነ መንገድ ይገናኙና ኒካህ ብለው በአምሳና በመቶ ሺህ ከዛም በላይ በሆነ ከፍተኛ ብር መህር ያስራሉ፣ ኒካሀው ከታሰረ በኋላ እንደምንም ሴቷ ያቺን የመህር ብር በእጇ ካደረገች በኋላ በትንሽ በትልቁ ነገር በጭቅጭቅ አብዋራ ታነሳለች! ገና 15 ቀን/1ወር ሳይሞላቸው ወደ ፍቺ ይሄዳሉ፣ ከዚያ በኋላ ራሷን በቻይና ቀለምና ዱቄት አደማምቃ ለዝሙት በስመ ስራ ለመስራት አደባባይ ብቅ ትላለች፣ እንደ ፌስታል ለጊዜው ተጠቅሞባት ለሚያልፍ ወንድ ሁሉ ታዛዥ ትሆናለች፣ የተከበረውን ገላዋን ካፊር ሙስሊም ሳትል ማንኛውም ወንድ በርካሽ ሳንቲም/በጊዜያዊ ጥቅማጥቅም ምናልባትም በአንድ ቀን ምሳ ግብዣ እንደፈለገ እንዲጫወትበት ታመቻችለታለች፣ የነበራት ሀያዕ ተገፎ እርቃኗን ትቀራለች፣ ልቧም ከዲንጋይ የባሰ ይደርቃል፣ ለጌታዋ ቃል ቁርኣንና ከነ ህይወቱዋ በጉርጋድ እየተቀበረች በነበረችበት ዘመን ላዳኑዋት ለሷ ብለው ለደሙላት ጥርሳቸውን ለተሰበሩላት ነቢይ ﷺ ሀዲስ ልቧ እንደተገለበጠ ኩባያ ይሆናል! የጌታዋ ቃል ሲነገራት ታስተባብላለች፣ ስለ ዝሙት አደገኛነትና ከባድ ወንጀልነት ሲነገራት ምንም አይመስላትም። ይልቅ ታሽሟጥጣለች፣ የሚነግራትም ሰው ለሷ ሙድ ያልገባው ፋራ ነው። (የተገለበጠ ኩባያ ውሃ ቢፈስበትም አይቀበልማ!) ታዲያ ከምን አይነት ሽታው ከሚያስጠላ ፈሳሽ ነገር የፈጠራትን ካልነበረችበት ያስገኛትን ጌታዋን አላህን ረስታ፣ አኬራዋን ረስታ፣ ሂጃቧንና እስልምናዋን አስደፍራ፣ ይህን ሁሉ ስትሆን አላህ የረሳት ይመስላታል: አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ማለቱን ትዘነጋለች:–
﴿وَالَّذينَ كَذَّبوا بِآياتِنا سَنَستَدرِجُهُم مِن حَيثُ لا يَعلَمونَ★وَأُملي لَهُم إِنَّ كَيدي مَتينٌ﴾ الأعراف ١٨٢-١٧٣
“እነዚያንም በአንቀፆቻችን ያስተባበሉትን: ከማያውቁት ስፍራ ቀስ በቀስ ምቾትን በመጨመር እናዘናጋቸዋለን። ባሉበት (ወንጀል) ነገር ላይ ጊዜንም እሰጣቸዋለሁ፣ አያያዜ እጅግ በጣም ብርቱ ነውና‼” አዕራፍ 182–183
ምንም ያህል እንኳን አላህ (ተባረከወተዓላ) በጥበቡ ለወንጀለኞች በወንጀላቸው ጊዜ ቢሰጣቸውም፣ አዎን! አያያዙ ግን እጅግ በጣም የበረታ ነው።
ስንቶች ናቸው በየ መጠጥ ቤቱ ከካፊር ጋር እየዘለሉ መጠጧን እንኳን አንጠጣም ቢሉ ካፊሮቹ ከሚጠጡት መጥ በሙስሊም ተብዬዎቹ ለስላሳ ላይ ድንገት ዘወር ባሉበት ገጠመኝ ጨምረውባቸው ራሳቸውን ስተው የተለያየ ዱኒያዊ ስቃይ ውስጥ የሚወድቁት?? በዝሙት ሰበብ በዛው ከካፊር ወንድ ጋር በገቡበት መጠጡንም ተላምደውት እንደ ሻይ ቡና የሚቆጥሩት ሙስሊም ተብዬ ሴትና ወንድ ቁጥር ስፍር የላቸውም! ስንትና ስንት ሙስሊም ሴቶች ናቸው ከኩፋር ወንዶች ጋር ሲዘሉ በዚህ መልኩ መጠጥ አቅምሰዋቸው በለሊት ከመጠጥ ቤት ወጥተው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በመኪና አደጋ መጨረሻቸው በዊልቸር መገፋት የሆነው?? ስንትና ስንት ሙስሊም ሴቶች ናቸው እንደ #HIV ባሉ ከባባድ በሽታዎች ተጠቅተው ሰው አጠገባቸውን ሊቀርብ የሚፈራው??? ስንቶች ናቸው በበሽታ ባይጠቁ እንኳን ለትዳር የሚፈለጉበትን መልካም ስነ–ምግባር ሀያዕና ስርኣትን በዚህ ፀያፍ ተግባር አጥፍተውት ለትዳር የሚፈልጋቸው የሚያጡት?? ስንትና ስንት ሴቶች ናቸው ለትዳር የሚፈለጉበትን እድሜያቸውን በዚህ ሀራም ተግባር ጨርሰውት ትዳር ህልም ሆኖባቸው የአዕምሮ ቀውስ ውስጥ የገቡትና አላህ ትዳር በማሳጣት በዚህች አለም የሚቀጣቸው?? በራሳቸው እጅ ሰበብ ትዳር ህልም እንዲሆንባቸው ያደርጋሉ፣ በዚህ የተነሳ ይነጫነጫሉ፣ ብሶት ብሶት ይላቸዋል፣ ወደ ሌላ ወንጀል ያመራሉ፣ ከቤተሰብ ይባላሉ፣ በወሬ ዘመድና ዘመድን ያቆራርጣሉ፣ ከጎረቤት ይባላሉ፣ ቤተሰብን ከጎረቤት ያባላሉ፣ ጎረቤትና ጎረቤትን ያባላሉ ያፋጃሉ፣ በወሬ ማመላለስና በሀሜት ይጠመዳሉ፣ ይህ ሌላው ከባድ ወንጀል ነው! መጨረሻቸው ሰው ሁሉ ይጠላቸዋል፣ ከራሳቸው ቢጤ እንኳን አይግባቡም፣ አይ ዝሙት! ሪዝቅን ያጠባል! ፊትን ያኮስሳል! በዝሙት የተበላሸው ፊት ዛሬ ላይ የቄራ ውሻ መስላ ተጨማልቃው የምትወጣው ቀለምና ዱቄት ሁሉ ምንም አይፈይደውም!! ይህ ሁሉ የዝሙት ወንጀል የአኼራውን ሳይጨምር ዱኒያዊ የቅጣት ውጤት ነው!!።
ዝሙት ፀያፍ ተግባር ነው! ጋጠወጥነትና ብልግና ነው! አትቅረቡት‼ እጅግ በጣም ራቁት!! ===በአላህ ፈቃድ===ይቀጥላል…
https://t.me/httpsLatahzen

🎙በጉጉት የሚጠበቅ መድረክ!!!
(የጊዜ ዋጋ!)
💺#በሸይኽ_ኢልያስ_አህመድ
⌚️እሁድ ጧት 3:00
24/8/1443(18/7/2014)
🕌ራህማ መስጂድ
🚖አየር ጤና ቻይና ካምፕ ወደ ጀሞ3 (አዋሽ ዳቦ)
(የጊዜ ዋጋ!)
💺#በሸይኽ_ኢልያስ_አህመድ
⌚️እሁድ ጧት 3:00
24/8/1443(18/7/2014)
🕌ራህማ መስጂድ
🚖አየር ጤና ቻይና ካምፕ ወደ ጀሞ3 (አዋሽ ዳቦ)
ጊዜያዊ ደሥታ ብለሽ ወንዶችን ወደ ዝሙት የሚጣሩ የማይረባ ልብሥ አትልበሺ
ዛሬ ለትንሽ ደቂቃ የሚያልፍ ሥሜት ብለሽ ነገ የሠው ልጆች አምሣ ሺ አመት ያለ ምግብ ያለ መጠጥ የሚቆሙት ቀን አሥታውሺ የዚህ ቀን መከራ የዚህ ቀን ፈተና መውጣት የምትችዩ የጌታሽን ትዛዝ በዱንያ ላይ ሠምቻለሁ ታዝዣለሁ በማለትሽ እና በመተግበርሽ ነው ምትወጩ
እንጂ
የአላህን ትዛዝ ጥለሽ ከሩቁ የሚጣሩ አልባሣት እና ና እያለ የሚጣራው የፈረንሣይ ሽቶ በመቀባት አይደለም ያን እናት ልጅዋን ጥላ ነፍሤ ነፍሤ በምትልበት በዛች ቀውጢ ቀን የምትድኙ ዛሬ ላይ ለአሄራ ብለሽ ባሥቀመጥሽው ሥራሽ ነው።
ወንድሜ ሆይ
ምነካህ
አሥተያት አትሥጣት እሥዋ ያሁሉ መሥታወት እና ያሁሉ ቀለሞች ተቀብታ ዝንጀሮ የመሠለችው የአንተ አሥተያየት ፈልጋ ነው እና አትልከፍ ይህ ከዝሙት ውሥጥ የድርሻህ እየወሠድክ ነው
ጌታችን ሆይ እዘንልን
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ተፈሪ ቦጋለ
Sadat
ተፈሪ ቦጋለ።
ስለ ሸህ ሁሴን ጂብሪል በአጭሩ ስሙና እውነቱን ፍረዱ።
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በደንብ ሼር አድርጉት። ዲናችንን ከመፈራረስ እንታደግ።

ነቢዩﷺ እንዲህ አሉ፦
[[ሁሉም ኡመቶቼ(ህዝቦቼ) ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሰው ሲቀር፤]
ለነቢዩም ተባሉ፡ ማነው ጀነት ግባ ተብሎ እምቢ የሚለው?
እሳቸውም [እኔን የታዘዘኝ ሰው በእርግጥ ጀነት ገባ ፤እኔን ያመፀኝ(ትእዛዜን) አልቀበልም ያለው ሰው እምቢ ብሏል።]]
ቡኻሪዘግቦታል።