La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭


አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84 አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል።
ሁላችንም ይመለከታል ።
ኡበይዱላህ ኢብን ኡመር አንድ ጊዜ
እንዲህ ብለው ነበር “ጀምዐ ሰላት
በተለይ ኢሻና ሱብሂ አምልጦኝ
አያውቅም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ቤቴ
እንግዳ መጣና ከርሱ ቆይቼ ኢሻ ሶላት
አመለጠኝ፡፡ ከቤት ወጣሁ፤ ጀምዐ
ሶላት ለማግኘት ብዬ በስራ ከተማ ላይ
የሚገኙ መስጂዶች በሙሉ ዞርኩ፤
ሁሉም መስጂዶች ተሰግዶ አልቋል፡፡
ሰዎቹ ባጠቃላይ ሰግደው
ወደቤታቸው ሄደዋል፡፡ እኔም ወደ
ቤቴ ተመለስኩና ማሰብ ጀመርኩ፤
ለራሴ እንዲህ አልኩኝ ‘በሀዲስ
በግለሰብ ከሚሰገደው ሰላት በጀምዐ
ሚሰገደው በ 27 ደረጃ ይበልጣል
ተብሎዋል፤ ስለዚህ 27 ጊዜ ኢሻን
ሰላት ብሰግደው በጀምዐ ከሰገዱት ጋር
እኩል ይሆናል’ ብዬ በማሰብ
ኢሻን ሰላት በቤቴ 27 ጊዜ ሰገድኩና
ተኛሁ፡፡ በዛው ቀን ለሊት በህልሜ
ከፈረሰኞች ጋር ፈረስ ውድድር
ስንወዳደር አየሁ፤ ፈረሴ ጠንካራ
ብትሆንም
እንኳ ሌሎቹ ላይ ልደርስባቸው
አልቻልኩም፤ ወደ ዃላ ቀረሁ፡፡ ፈረሴ
ትደርስባቸው ዘንድ እደበድባት
ጀመርኩ፤ ነገር ግን ምንም ለውጥ
ልታመጣልኝ አልቻለችም፡፡ አንደኛው
ፈረሰኛ ወደኔ በመዞር “ፈረስህን
አታሰቃያት እኛ ላይ ልትደርስብን
አትችልም” አለኝ፡፡ እኔም “ለምን?”
ብዬ
ስጠይቀው “ምክንያቱም እኛ ኢሻን
ሶላት በጀምዐ ነው የሰገድነው፤ አንተ
ግን ብቻህን ሰገድከው” በማለት
መለሰልኝ፡፡ ከዚህ ትልቅ ትምህርት
ወሰድኩ፤ በጣምም አዘንኩ፡፡” ይለናል
ኡበይዱላህ፡፡
ሱብሃነላህ!!
እኛ ስንት ሶላት ይሆን ጀምዐ
ያመለጠን?? ስንቶቻችን ይሆን በዚህ
ምክንያት ተፀፅተን የምናውቅ??
“አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84
አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል”
መባሉን ምናስታውስ ስንቶቻችን
ነን??
ዛሬውኑ እንነይት “ኢንሻ አላህ ካሁን
በሗላ አንድም ሶላት ጀምዐ
አያመልጠኝም” ብለን…ለኔም
ለናንተም ሰደቀቱል ጃሪያ ይሆናልና
መልክቱን
ሼር እናድርገው —
ያረብ በሰላት ላይ ጥንካሬና ብርታት ስጠን ከሰይጣን ተንኮል ጠብቀን።
ዋ!! ፈራሁልሽ ነፍሴ 😭😭😭
#ቀደር

ገና ድሮ..
ሳትመጣ ለኑሮ
መምጣትህ ተነግሮ
መፈጠርህ ታውቆ
ክፉ ደግህ ፀድቆ
ሪዝቅህ ተወስኖ
ዕድሜህ ተመጥኖ
ሥራህ ተዘርዝሮ
ጉዞህ ተሰድሮ

ፋይልህ ተዘግቷል
ጉዳይህ አብቅቷል

....ገና ድሮ

ሳትጀምር ኑሮ
ሳትወጣ ከማህፀን
እንዲህ ሰው ሳትሆን
ህይወትህ ተረቅቋል
መድረሻህ ታውቋል

ሁኔታህ ተከትቧል
ውሳኔው ተላልፏል
ቀለሙ ተነስቷል
ወረቀቱ ደርቋል

በቃ ተረጋጋ
አትጥራ አደጋ
እርካታ ሲለካ!

ራበኝ በላሁበት፣
ጠማኝ ጠጣሁበት፣
አማረኝ ለበስኩኝ፣
በረደኝ ደረብኩኝ፣
ሰለቸኝ ቀየርኩኝ፣
ወጣሁ ተናፈስኩኝ፣

ሞላ ፍላጎቴ፣
ሠመረ ምኞቴ፣
ተሟላ ጤናዬ፣
ጨመረ ኪሎዬ፣
ሰከነ ሥጋዬ፣
አረፈ ገላዬ፣

ሥጋዬም ረካ፣
ነፍሴስ በምን ትርካ!
አልኮልና ዝሙት
ዉጤታቸው ፀፀት፣
ጫትና አጉል ሱስ፣
አይጠግኑም መንፈስ፣
ወሬ ሙዚቃ ሣቅ፣
ትርፉ ቀልብ ማድረቅ፣
..

እርቀው ቢሄዱ፣
ቢወጡ ቢወርዱ፣
ቢጓዙ ቢደክሙ፣
ቢለፉ ቢተክኑ፣
 
ለቀልብ መድኃኒቱ፣
ለነፍስ ጤንነቱ፣
ለሕይወት ስምረቱ፣
ለምላስ ዕረፍቱ፣
ለቋንቋ ዉበቱ፣
ለሩሕ ምሽግ ቤቱ፣
ለወሬ ድምቀቱ፣
ለፊት ኑር ሞገሱ፣
አስተማማኝ መልሱ፣


ጌታን ማስታወሱ፣
እሱን ማወደሱ፣
ስሙን መቀደሱ፣
ማጥራት ማሞገሱ፣

ለመንፈስ ምግቡ፣
ዚክር ነው ቀለቡ፣
በዚክር ነው ለካ
እርካታ ሲለካ!!
La tehzen
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭 አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84 አመት ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል። ሁላችንም ይመለከታል ። ኡበይዱላህ ኢብን ኡመር አንድ ጊዜ እንዲህ ብለው ነበር “ጀምዐ ሰላት በተለይ ኢሻና ሱብሂ አምልጦኝ አያውቅም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ቤቴ እንግዳ መጣና ከርሱ ቆይቼ ኢሻ ሶላት አመለጠኝ፡፡ ከቤት ወጣሁ፤ ጀምዐ ሶላት ለማግኘት ብዬ በስራ ከተማ ላይ የሚገኙ መስጂዶች በሙሉ ዞርኩ፤ ሁሉም…
➧ሰላት የማይሰግድ ሰው ሸሪዓዊ ብይኑ ምንድን ነው?!

================
ጥያቄ:- አንድ ሰው ቤተሰቦቹ ሶላት እንዲሰግዱ ተደጋጋሚ ምክር ቢመክርም ፈቃደኛ ሊሆኑለት አልቻሉም፡፡ ይህ ሰው ቤቱን ለቆ ይውጣ ወይንስ ከእነር ሱ ጋር ተቀላቅሎ ይኑር?

መልስ:- ቤተሰቦቹ ፍጹም ሶላት የማይሰግዱ ከሆኑ ካፊሮች ወይም ከኢስላም ያፈነገጡ ናቸው፡፡(¹) በመሆኑም ከእነርሱ ጋር በፍጹም አብሮ ሊኖር አይገባም፡፡ ነገር ግን አላህ ወደቅኑ መንገድ ሊመራቸው ስለሚችል ተስፋ ሳይቆርጥ ዳዕዋ ሊያደርግላቸው ይገባል፡፡

ሶላትን ፍጹም የተወ ሰው ከሐዲ ለመሆኑ የሚከተሉት የቁርዓን፣ የሐዲስ፣ የሶሃቦች ንግግር እና የጤናማ አእምሮ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ፡-

➲የቁርዓን ማስረጃ
አላህ ስለሙሽሪኮች የሚከተለውን ቁርዓን ተናግሯል፡-
فَإِن تَابُوا وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ وَآتَوُا الزَّكَاةَ فَإِخْوَانُكُمْ فِي الدِّينِ ۗ وَنُفَصِّلُ الْآيَاتِ لِقَوْمٍ يَعْلَمُونَ (11)
“ቢጸጸቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፡፡ ለሚያውቁ ሕዝቦችም አንቀጾችን እናብራራለን፡፡” (አት'ተውባህ፡ 11)
የዚህ አንቀጽ ግንዛቤ ከላይ አላህ የዘረዘራቸውን ነገሮች (ጸጸት፣ ሶላት እና ዘካን) ካልፈጸሙ ለእኛ ወንድሞች ሊሆኑ እንደማይችሉ ነው፡፡ የተፈጸመው ወንጀል ትልቅ እንኳ ቢሆን ከዲን ወንድማማችነት ሊያወጣ በፍጹም አይችልም፡፡ የዲን ወንድማማችነት የሚፈርሰው ከኢስላም የሚያስወጣ ተግባር ሲፈጽም ብቻ ነው፡፡
➲ከሐዲስ ማስረጃ
የሚከተለው የነብዩ ﷺ ንግግር ነው፡-
"إن بين الرجل وبين الشرك والكفر ترك الصلاة" رواه مسلم
“በግለሰቡ እና በክህደት ወይም በሽርክ መካከል ያለው ልዩነት ሶላትን መተው ነው፡፡”
ቡረይዳ ባስተላለፈው ሐዲስ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"العهد الذي بيننا وبينهم الصلاة فمن تركها فقد كفر"
“በእኛ እና በእነርሱ መካከል ያለው ልዩነት ሶላት ነው፡፡ ሶላትን የተወ በእርግጥ ካደ፡፡”
➲ ከሶሃቦች ንግግር
የሙዕሚኖች አሚር ኡመር رضي الله عنه የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"لا حظ في الإسلام لمن ترك الصلاة"
“ሶላትን ለተወ ሰው በኢስላም ምንም ዓይነት ዕድል የለውም፡፡”
ዓብደሏህ ብን ሸቂቅ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
(كان أصحاب النبي صلى الله عليه وسلم لا يرون شيْا من الأعمال تركه كفر غير الصلاة) (الترمذي : ٢٧٥٧)
“የነብዩ ሶሃቦች ከሶላት ውጭ አንድን ተግባር በመተው ክህደት ውስጥ ያስገባል ብለው አይመለከቱም ነበር፡፡” (አት`ቲርሚዚ : 2757) (²)
➲ የጤናማ አእምሮ ማስረጃ
በልቡ ውስጥ የብናኝ ክብደት ኢማን ያለው ሰው ከፈጣሪው ጋር የሚያገናኘውን ትልቁን የኢባዳ ዘርፍ ሶላትን ይተዋል ተብሎ አይታሰብም፡፡
መረጃዎች ሲፈተሹ ሶላትን የተው ሰዎች ከሀዲ እንደሚሆኑ እና የሙርተድነት አህካሞች እንደሚረጋገጥባቸው የሚገልጹ እንጅ ሙእሚኖች እንደሆኑና ከእሳት ነጻ ሆነው ጀነትን እንደሚወርሱ የሚያረጋግጡ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ሶላትን የተው ሰዎች ከሐዲ እንደሚሆኑ የሚያስረዱ መረጃዎችን ጸጋን መካድ ወይም ከክህደት በታች ያለ ክህደት በማለት የተለየ ትርጉም መስጠት ትክክል አይሆንም፡፡
አንድ ሰው ሶላቱን በመተው ምክንያት የሚከተሉት የሙርተድነት አህካሞች (ህግጋቶች) ይረጋገጡበታል፡-
➀አንደኛ፡- ሙስሊም ሴት ማግባት አይችልም፡፡ ሙስሊም ሴት ኒካህ አድርጎ ከሆነ ኒካሁ ባጢል ይሆናል፡፡ እርሷም ለእርሱ ሀላል (የተፈቀደች) ልትሆን አትችልም፡፡
በዲናቸው ምክንያት የተሰደዱ ሴቶችን አስመልክቶ አላህ ሲናገር፡-
فَإِنْ عَلِمْتُمُوهُنَّ مُؤْمِنَاتٍ فَلَا تَرْجِعُوهُنَّ إِلَى الْكُفَّارِ ۖ لَا هُنَّ حِلٌّ لَهُمْ وَلَا هُمْ يَحِلُّونَ لَهُنَّ ۖ 
“አማኞችም መሆናቸውን ብታውቁ ወደከሃዲዎች አትመልሷቸው፡፡ እነርሱ (ሴቶች) ለእነርሱ የተፈቀዱ አይደሉምና፡፡ እነርሱም (ወንዶቹ) ለእነርሱ አይፈቀዱምና፡፡” ( ሙምተሀሂና፡ 10)
➁ሁለተኛ፡- ግንኙነት ቢያደርግም ባያደርግም ጋብቻ ከፈጸመ በኋላ ሶላቱን ከተወ ባሳለፍነው የቁርዓን ማስረጃ መሰረት ጋብቻው ይፈርሳል፡፡ ሚስቱ ለእርሱ የተፈቀደች አትሆንም፡፡
➂ሶስተኛ፡- ሶላት የማይሰግድ ሰው ቢያርድ እርዱ በክት ይሆናል፡፡
➃አራተኛ፡- ሶላት የማይሰግድ ሰው መካ ወይም በሀረም ክልል መግባት አይችልም፡፡ (³)
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِنَّمَا الْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا الْمَسْجِدَ الْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَٰذَا ۚ وَإِنْ خِفْتُمْ عَيْلَةً فَسَوْفَ يُغْنِيكُمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ إِن شَاءَ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ (28)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም አመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡ ድህነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል፡፡ አላህ አዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡” (ተውባህ ፡ 28)
➄አምስተኛ፡- ዘመዱ ቢሞት ከውርሱ መካፈል አይችልም፡፡ ለምሳሌ አባት ይሰግዳል ልጅ ግን አይሰግድም ድንገት አባት ቢሞት ሶላት የሚሰግድ የአጎት ልጅ ይወርሳል እንጅ ልጅ በፍጹም ሊወርስ አይችልም፡፡
ኡሳማ ባስተላለፈው ሐዲስ ረሱል صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
"لا يرث المسلم الكافر ولا الكافر المسلم" متفق عليه
“ሙስሊም ካፊርን አይወርስም ካፊርም ሙስሊምን አይወርስም፡፡”
➏ስድስተኛ፡- ሶላት የማይሰግድ ሰው ቢሞት አይታጠብም አይከፈንም አይሰገድበትም ከሙስሊሞች መቃብርም አይቀበርም ፡፡ ስለዚህ ምን እናድርግ? ክብር ሊኖረው ባለመቻሉ ከከተማ ውጭ ወስደን መሬቱን ቆፈር ቆፈር አድርገን እስከልብሱ አዳፍነን መመለስ ብቻ ነው፡፡
ሶላት አለመስገዱ እየታወቀ ሙስሊሞች ሶላተል ጀናዛ እንዲሰግዱበት ለማድረግ ከአንዳንድ ሰዎች የሚደረገው ጥረት ትክክል አይደለም፡፡
➐ሰባተኛ፡- የትንሳኤ ቀን ከፊርአውን፣ ከሃማን፣ ከቃሩን እና ኡበይ ብን ኸለፍ ከተባሉ ከሀዲዎች ጋር ይቀሰቀሳል፡፡(⁴)
©≈ ሶላት ለማይሰግድ ሰው እዝነትና ምህረት ከአላህ መለመን በፍጹም የተከለከለ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ብሏል፡-
مَا كَانَ لِلنَّبِيِّ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَن يَسْتَغْفِرُوا لِلْمُشْرِكِينَ وَلَوْ كَانُوا أُولِي قُرْبَىٰ مِن بَعْدِ مَا تَبَيَّنَ لَهُمْ أَنَّهُمْ أَصْحَابُ الْجَحِيمِ (113)
“ለነብዩና ለነዚያ ላመኑት ለአጋሪዎቹ የዝምድና ባለቤቶች ቢሆኑም እንኳ እነሱ (ከሀዲዎቹ) የእሳት ጓዶች መሆናቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ምህረትን ሊለምኑ የሚገባ አልነበረም፡፡” (ተውባ፡ 113)
الله أعلم وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه أجمعين
الشيخ ابن عثيمين – رسالة صلاة النبي . ص (29-30) ومجموع فتاو
በጫማ መስገድና ተያያዥ ነጥቦች!

[ሀ] በጫማ መስገድ ይቻላል?

አንዳንድ ሰዎች በጫማ መስገድ የማይፈቀድ ይመስላቸዋል፡፡ ለዚህ ያደረሳቸው ጉዳዩ በዑለማዎች ሲፈፀም ወይም ሲነገር ስላላጋጠማቸው ነው፡፡ ነገር ግን በጫማ ከመስገድ የሚከለክል አንድም ማስረጃ የለም፡፡ ይልቁንም በተቃራኒው በጫማ መስገድ የማያሻማ ሸሪዐዊ መሰረት ያለው ሱንና ነው፡፡ ይህንን ከሚያረጋግጡ ማስረጃዎች ውስጥ ከፊሉን ብናይ፡-
1. አቡ መስለማ ሰዒድ ኢብኑ የዚድ አልአዝዲ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
سَأَلْتُ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ: أَكَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يُصَلِّي فِي نَعْلَيْهِ؟ قَالَ: «نَعَمْ»
“አነስ ኢብኑ ማሊክን ‘ነብዩ ﷺ በጫማዎቻቸው ይሰግዱ ነበርን?’ ብዬ ጠየቅኩት፡፡ ‘አዎ’ አለኝ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
2. ዐብዱልላህ ኢብን አቢ ሐቢባ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
جاءنا رسول الله صلى الله عليه وسلم في مسجدنا ب ( قباء فجئت وأنا غلام ( حدث ) حتى جلست عن يمينه ( وجلس أبو بكر عن يساره ) ثم دعا بشراب فشرب منه ثم أعطانيه وأنا عن يمينه فشربت منه ثم قام يصلي فرأيته يصلي في نعليه )
“የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቁባእ ወዳለው መስጂዳችን መጡ - እኔ ለጋ ልጅ ነኝ በጊዜው መጣሁና በቀኛቸው በኩል ተቀመጥኩ፡፡ አቡበክር በግራቸው ተቀመጡ፡፡ ከዚያም የሚጠጣ ነገር ጠየቁና ከሱ ጠጡ፡፡ ከዚያም በቀኛቸው ላለሁት ለኔ ሰጡኝና ከሱ ጠጣሁ፡፡ ከዚያም ሊሰግዱ ተነሱ፡፡ በጫማዎቻቸው ሲሰግዱ አየኋቸው፡፡” [አስሶሒሐህ፡ 2941]
3. ከዐምር ኢብን ሹዐይብ ከአባታቸው፣ ከአያታቸው ተይዞ እንዲህ ብለዋል፡-
رأيت رسول الله صلى الله عليه وسلم يصلي حافيا ومنتعلا.
“የአላህ መልእክተኛን ﷺ በባዶ እግራቸውም ተጫምተውም ሲሰግዱ አይቻቸዋለሁ፡፡” [ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 660]
4. አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል፡-
“አንድ ቀን የአላህ መልእክተኛ ﷺ አሰገዱን፡፡ በከፊል ሶላታቸው ላይ ሳሉ ጫማዎቻቸውን አወለቁና በግራቸው በኩል አስቀመጧቸው፡፡ ሰዎች ይህንን ሲያዩ ጫማዎቻቸውን አወለቁ፡፡ ሶላታቸውን ሲያጠናቅቁ ‘ምን ሆናችሁ ነው ጫማዎቻችሁን ያወለቃችሁት?’ አሉ፡፡ እነሱም ‘ጫማዎችህን ስታወልቅ ስናይህ ጫማዎቻችንን አወለቅን’ አሉ፡፡ በዚህን ጊዜ እሳቸው ﷺ እንዲህ አሉ፡-
"إن جبريل أتاني، فأخبرني أن فيها قذراً؛ فألقيتهما، فإذا جاء أحدكم إلى المسجد؛ فلينظر في نعليه: فإن رأى فيهما قذراً؛ فليمسحهما، ولْيصلِّ فيهما"
‘ጂብሪል ከኔ ዘንድ መጥቶ በነሱ (በጫማዎቼ) ላይ ቆሻሻ እንዳለባቸው ሲነገረኝ አወለቅኳቸው፡፡ አንዳችሁ መስጂድ ሲመጣ ጫማዎቹን ይመልከት፡፡ ቆሻሻ ካየባቸው ይጥረጋቸውና ይስገድባቸው፡፡’” [ሲፈቱ አስሶላት፡ 80]
5. ከሸዳድ ኢብን አውስ ረዲየላሁ ዐንሁ ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
«خالفوا اليهود فإنهم لا يصلون في نعالهم ولا خفافهم» .
“አይሁዶችን ተፃረሩ፡፡ እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና፡፡” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 3210]

ማሳሰቢያ፡-

ባሳለፍናቸው አምስት ሐዲሦች በጫማ መስገድ እንደሚቻል አይተናል፡፡ ስላሳጠርኩት እንጂ ማስረጃዎቹ ብዙ ናቸው፡፡ ትንሽ ሰፋ ያለ ነገር የፈለገ የሸይኽ ሙቅቢልን ረሒመሁላህ “ሸርዒየቱ አስሶላህ ፊንኒዓል” ኪታብ ይመልከት፡፡ ነገር ግን
1ኛ፡- የሚሰገድበት ጫማ ንፁሕ መሆን አለበት፡፡
2ኛ፡- በጫማ የሚሰገደው ለመታወቅ ወይም ተለይቶ ለመታየት አይነት ኒያ እንዳይሆን
3ኛ፡- ዛሬ ሰዎች ለሱንናው ባይተዋር ሆነዋል፡፡ ስለሆነም በጫማ በመስገድ የሚነሳ ፈተና ካለ መታቀብ ያስፈልጋል፡፡ ጉዳትን ማስወገድ የሚወደድን/ የሚፈቀድን ነገር ከመፀም ይቀድማልና፡፡ በዚህን ጊዜ ወደ ተግባር ከመግባት በፊት ማስተማር ይቀድማል ማለት ነው፡፡
4ኛ፡- በሶላትም ውስጥ ይሁን ከሶላት ውጭ ከአውሬዎች ቆዳ የተዘጋጀ ጫማ መልበስ አይቻልም፡፡
5ኛ፡- ጉዳት የሚያስከትል ጫማ በሶላትም ይሁን ከሶላት ውጭ መልበስ አይቻልም፡፡

[ለ] በጫማ መስገድ የተፈቀደ ወይስ የተወደደ?

በጫማ መስገድ እንደሚቻል ካለፉት ማስረጃዎች አይተናል፡፡ ግን ከነጫማ መስገድ የሚፈቀድ ብቻ ነው ወይ የሚወደድም ጭምር ነው? ሸይኽ ኢብኑል ዑሠይሚን ረሒመሁላህ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጥንት ጀምሮ ውዝግብ እንደተከሰተ ከጠቀሱ በኋላ “የሚያደላው ይሄ ከሸሪዐዊ ድንጋጌዎች መሆኑ ነው፤ ስለሆነም የተወደደ ነው” ብለዋል፡፡ ለዚህም “አይሁዶችን ተፃረሩ፡፡ እነሱ በጫማዎቻቸውና በኹፎቻቸው አይሰግዱምና” የሚለውን ሐዲሥና ሌላም ማስረጃ ጠቅሰዋለል፡፡ [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ዑሠይሚን] ልብ በሉ! እያወራን ያለነው ስለመቻል አለመቻሉ አይደለም፡፡

[ሐ] በዘመናችን ባሉ መስጂዶች ውስጥ በጫማ መስገድ

በአሁ ሰዓት መስጂዶች ውድ ውድ ምንጣፎች ተነጥፎባቸዋል፡፡ ሰው ሁሉ ከነጫማው ቢገባ ምንጣፎቹ በቆሻሻ ይሞላሉ፡፡ ይሄ ደግሞ ሰጋጆች ላይ ችግር ይፈጥራል፡፡ በዚህም ምክንያት ምንጣፍ በተነጠፉ መስጂዶች ውስጥ ከነጫማ መግባት ተገቢ እንዳልሆነ ዑለማዎች ይገልፃሉ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ ውጭ ከሆኑ (በቤታቸው ወይም ምንጣፍ በሌለባቸው ቦታዎች) ፍላጎታቸው ከሆነ ከነጫማቸው መስገድ ይችላሉ፡፡

[መ] ሶላት ሊሰግድ ሲል ጫማውን ማውለቅ ከፈለገ የት ያድርግ?

በቀኙ በኩል ማድረግ አይፈቀድም፡፡ ስለዚህ በግራው በኩል ማድረግ ይችላል፡፡ በግራው በኩል ሌላ ሰጋጅ ከኖረ በግራ በኩል ማስቀመጥም አይፈቀድም፡፡ ምክንያቱም ለሱ በቀኝ በኩል ይሆንበታልና፡፡ በዚህን ጊዜ በእግሮቹ መሀል ያድርግ፡፡ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “አንዳችሁ መስገድ ካሰበ ጫማዎቹን በቀኙ በኩል አያድርግ፡፡ በግራውም አያድርግ፣ በሌላ ሰው ቀኝ በኩል ይሆናልና - በግራው በኩል ማንም ከሌለ ነው እንጂ፡፡ (በግራ ሰው ከኖረ ግን) በእግሮቹ መሀል ያድርጋቸው፡፡” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 645]
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 17/2010)
{ وَلَقَدْ خَلَقْنَاكُمْ ثُمَّ صَوَّرْنَاكُمْ ثُمَّ قُلْنَا لِلْمَلائِكَةِ…
تلاوة مؤثرة | الشيخ ماهر المعيقلي
قناة القرآن الكريم ..

قناة تلاوات الشيخ ماهر المعيقلي


ቁርዓን ብቸኛዉ የልብ መርጊያ መደሀኒት ነዉ''

🎧 🍀 🎧

በጨለማ ህይወት ዉስጥ የብቸኚነት
ብርሃን ቁርኣን ነዉ

🍀🎧ተ ጋ በ ዙ🎧
🌿
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳድ ሰዎች ይሄን አድርጌ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ እንደዚህ ይሆን ነበር ይላሉ ይሄ ንግግር እንዴት ይታያል
መልስ
ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከዚህ ነገር ከልክለዋል
በሚጠቅምህ ነገር ላይ ትጋ አትሳነፍ
የሆነ ነገር ካገኘህ እንደዚህ እንደዚህ አድርጌ ቢሆን ኖር እንደዚህ ይሆን ነበር አትበል ነገር ግን አሏህ ወሰነ የፈለገዉን አደረገ በል
ቢሆን ኖሮ የሚለዉ ቃል የሸይጧን በር ይከፍታል እና
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: 5]👌

#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ➅]👌

#ቁርኣን
አስተውል ወዳጄ
^^^^^^==^^^^^^
አይንህ ባየው ነገር ከተክለፈለፈ
ምኞትህ ልክ አጥቶ ከዲካው ካለፈ
እጅህ ያለ ድርሻው የሰው ሃቅ ከላፈ
…………
እግርህም ለመንጠቅ ፈጥኖ ከተጓዘ
ህሊና—ቢስ ሁነህ ውስጥህ ከናወዘ
በከንቱ ጥቅማ—ጥቅም ደርሶ ከታዘዘ
………………
አስተውል ወዳጄ ታሟልና ልብህ
ዛሬ ነገ ሳትል ተጣጣር ለጤናህ
……
የለከፈህ ደዌ በወቅት ካልታከመ
የሰራ አካልህን በርዞ ካመመ
ዱኒያም አኼራህም በከንቱ አከተመ።

🖊ኑር
🌹ግጥሜን ተጋበዙልኝ አህባቢ

🦋ቀድር........🦋

ኩንፈየኩን ብሎ ቁርአን ያሰፈረው
የአላህ ውሳኔ እርሱ የደነገገው
ቀድር መቀበሉ የእምነት ማዕዘን ነው
ኸይሩም ሆነ ሸሩ መጨረሻው ውብ ነው
ያሰብነው ባይሳካ ምኞታችን ከስሞ
በአላህ ቀድር ላይ አንዘን ፈፅሞ
ካሰብነው የላቀ ከጠበቅነው በላይ
አላህ ይሰጠናል ሁሉንም ባንድ ላይ
ክፉ ነገር በዝቶ ሀዘን ቢያጋጥመን
ዱንያ ስልችት ብሎን አኼራን ቢያስመኘን
ጨለማ በዝቶብን ብርሀን ቢናፍቀን
ከቶ ተስፋ ሳንቆርጥ በአላህ እንመን
ያማረን ውሳኔ እሱ ይሰጠናል
ከጠበቅነው በላይ ብዙ ይረዝቀናል
የረህማን ውሳኔ እጅግ የበላይ ነው
እኛ ባይመስለንም ለኛው ጠቃሚ ነው
በቀድር እንመን ያላንዳች ብዥታ
ሁሉም ለኸይሩ ነው ብለን እንበርታ
መታመም፣መፈወስ፣ሞት ና ህይወት
መሳቅ እና ማልቀስ ማዘን መደሰት
ሁሉም ነገር ያለው በአላህ ውሳኔ ነው
ከሁሉ አስበልጠን እሱን እንመነው!!!


ኑርአህመድ
أذكار الصباح بصوت وصوره يريح القلب رائعه (مكتوبه) azkar al sabah
Learn Us
🥀 የጧት ዚክር 🌹


ዚክር

ዚክር የልብ ፡ ሀይልና የትኛውንም ጣዕም የማይስተካከለው ምግብ ነው፡

➤ ከዚክር መዘንጋት ደግሞ የልብ ዋነኛ በሽታው ነው፡
ዚክር ማነሱ የንፍቅና ምልክት ነው፡

ዚክርን ማብዛት ደግሞ የዒማንና አላህን
የመውደድ ምልክት ነው፡
ምክንያቱም አንድን ነገር የወደደ ሰው በየጊዜው ያነሳዋልና ፡

የሰው ልጅ ከጌታው ጋር በደስታ ዘመን በማስታወስ ከተዋወቀው በኋላ
በችግር ዕለት ያውቀዋል ፡ በተለይም በሞተ ዕለት፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⑦]👌

#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ➇]👌

#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ➈]👌

እነርሱ በዚህ እድሚያቸውና በዚህ ሁኔታቸው ከቁርኣን ጋር ያላቸው ግንኙነት በዚህ ደረጃ ከሆነ፤ እኛስ⁉️

اللهم اجعل القران العظيم ربيع قلوبنا ونور صدورنا وجلاء أحزاننا وهمومنا ومغفره لذنوبنا!

#ቁርኣን
➭ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 1 ሃሜት ነው።

#ሃሜት_ክፍል_አንድ
#ሃሜት እንደሚታወቀው በእስልምናችን ከባድና የከፋ ወንጀል ነው። ይሁን እንጂ በዚህን ጊዜ ብዙ ሰዎች እንደ ሀላል ከማቅለላቸው አልፈው ተወዳጅ ሲያስመስሉት ይስተዋላል። ይበልጥ የሚከፋው ደግሞ የሱንና ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎችም ሳይቀሩ በዚህ በሽታ መለከፋቸው ነው፣ ወንጀል ማንም ይስራው ማን ወንጀል ነው፣ ነገር ግን የወንጀሉ ክብደት ስለ ዲናቸው በቂ ግንዛቤ የሌላቸው ሰዎች ዘንድ የሚቀለው እነሱ ለዲኑ ግንዛቤ አለው ብለው የሚያምኑበት ሰውና የሱንና ምልክት ያለው ሰው ሲተገብረው ሲመለከቱ ነው። #ሃሜት ማለት የሰውን ስጋ እንደመብላት እንደሆነ ተነግሮናል፣ #ሃሜት በነቢዩ ﷺ አንደበት የሰውን ስጋ መብላት እንደሆነ በተለያዩ ሀዲሶች ተነግሯል። አላህ "ተባረከወተዓላ" በተቀደሰው ቃሉ ርስበርሳችን እንዳንተማማ አንዳችን የሞተውን ወንድሙን ስጋ መብላት እንደሚጠላው ሁላ አሜቱንም መጥላት እንዳለበት እንዲ ሲል ከልክሎናል:–
﴿وَلا تَجَسَّسوا وَلا يَغتَب بَعضُكُم بَعضًا أَيُحِبُّ أَحَدُكُم أَن يَأكُلَ لَحمَ أَخيهِ مَيتًا فَكَرِهتُموهُ وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ تَوّابٌ رَحيمٌ﴾ الحجرات ١٢
“የርስበርሳችሁን ነውር አትከታተሉ። ከፊላችሁ ከፊሉን አይማ። አንዳችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ሆኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን ከጠላችሁትማ አሜቱንም ጥሉት፣) አላህንም ፍሩ አላህ ፀፀትን ተቀባይ አዛኝ ነውና።” አል ሁጅራት 12
አንዳንድ ሰዎች፣ አንድ ሰው ላይ ያለበትን ችግር እውነት ከሆነ ማውራቱ አሜት አይደለም ብለው ያስባሉ። ለመሆኑ አሜት ማለትስ ምን ማለት ነው?? ትክክለኛውን መልሱንና የአሜትን ትርጓሜ ከነቢዩ ﷺ እንማር፣ ሃሜትን አጥብቀንም እንከላከል፣ አቢሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሶሃቦች እንዲህ አሉዋቸው:–
«ሃሜት ማለት ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?፣ አሉ፣ ሶሃቦችም አላህና መልእክተኛው ያውቃሉ፣ አሉ፣ "መልእክተኛው ያውቃሉ የሚለውን ቃል መጠቀም ከሞቱ በኋላ አይፈቀድም!።" (ሃሜት) የወንድምህን ስም በሚጠላው ነገር ላይ ማንሳትህ ነው፣ አሉ፣ በወንድሜ የምናገረው ነገር እሱ ላይ ያለ ተጨባጭ ችግር ከሆነስ? ተብለው ተጠየቁ፣ #በሱ_ላይ_የምትናገርበት ነገር እሱ ዘንድ ያለ ነገር ከሆነ #በእርግጥም_አምተሀዋል!፣ የምትናገረው ችግር እሱ ላይ የሌለ ነገር ከሆነ ደግሞ #የሌለበትን_ውሸት እሱ ላይ #ቀጥፈህበታል።» ሙስሊም ዘግበውታል።
ብዙ ጊዜ አንዳንድ ሰዎች ተው የሰውን ስጋ አትብሉ ሲባሉ፣ በድፍረት ያለበትን ችግር ነው ያወራሁት ብለው መልስ ይሰጣሉ፣ የሰውንም ስጋ ማላመጣቸውን ይቀጥሉበታል፣ አዎ ያወራሀው ያለበትን ሊሆን ይችላል ነገር ግን #ሃሜት_ማለት_እሱ_ራሱ_እንደሆነም_እወቅ!፣ ይሀው አሜት ማለት ምን ማለት እንደሆነ በታላቁ ነቢይ አንደበት ነው ትርጉሙ በዝርዝር የተነገረህ፣ የሌለበትን የምታወራ ከሆነማ #ጭራሹኑ_ቀጣፊ_ውሸታም በሰዎች ክብር የምትረማመድ ነህ!፣ እኔ ሳልሆን ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ ታላቁ ነቢይ ናቸው ያሉት።
#ሃሜት በትንሹም ይሁን በብዛት ክልክል (ሀራም) ነው እናታችን ኣዒሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ባስተላለፈችው ሀዲስ ለነቢዩ ﷺ እንዲህ ማለቷን ትናገራለች:–
«የአላህ መልእክተኛ ሆይ፣ ከሶፊያ እንዲህ እንዲህ ያለው ችግሯ ይበቃሃል፣ አንዳንድ ዘጋቢዎች "ሶፊያ እኮ አጭር ናት፣" ብላ ነው የተናገረችው ይላሉ፣ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለው መለሱላት:– “በእርግጥ የተናገርሻት ቃል በባህር ውሃ ብትቀላቀል ታበላሸው ነበር።” » አቢዳውድ የዘገቡት ሲሆን ሰነዱ ትክክል ነው።

በዚህን ጊዜ አላህ ያዘነለት ሲቀር አንዳንዶች ዘንድ ሀሜት እንደሚበላ አትክልት/ፍራፍሬ ሆኗል፣ ብዙዎች ዘንድ ደግሞ ቡና ቁርስ ነው።አላህ ከዚህ መጥፎ በሽታ ይጠብቀን

===በአላህ ፈቃድ
!===ይቀጥላል

https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➤የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!! ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሶስት ➧እንግዲህ ተመልከቱ የኑህ ህዝቦች በዉሃ ተበልተዉ የጠፉበት ሺርክ በሞት የተለዩዋቸዉን ደጋጎች በማሰብ ይፈፀሙት የነበረ የጣኦት አምልኮ ነዉ። ➧በተመሳሳይ እራሳቸዉ ደጋጎችንም ይሁን እነሱን የሚወክል ወይንም የሚያስታዉስ ሀዉልት ወይንም ዶሪሕ የሚያመልክ…
◈የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሽርክ መመሳሰል!!


ክፍል አራት

➧ዛሬም እንደ ጥንቱ ፀሀይና ጨረቃ የሚያመልክ አለ።

(وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ) فصلت: ٣٧

(ሌሊትና ቀንም ፀሀይና ጨረቃም ከተአምራቱ ናቸዉ። ለፀሃይና ለጨረቃ አትስገዱ። ይልቅ ለዚያ ለፈጠራቸዉ አላህ ስገዱ_እሱን ብቻ የምትገዙ ከሆናችሁ።)ፋሲለት :37

➧ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም መዉጫና መግቢያዋን ጠብቀዉ ለፀሃይ የሚሰግዱ ሰዎች እንዳሉ በነዚህ ስዓታት በመስገድ በነሱ እዳንመሳሰል አስተምረዋል። (ሙስሊም :1967)

➧በሀገራችንም ይሀን እምነት እንደነበረ የታሪክ ድርሳናት ያስረዳሉ። ቁጥራቸዉ ቢቀልም ዛሬም ድረስ ፀሀይና ጨረቃን የሚያመልኩ ሰዎች በሀገራችን ጨምሮ በተለያዩ የአለም ክፍሎች ይገኛሉ።

◈ዛሬም እንዴ ጥንቱ ዲንጋይና ዛፍ የሚያመልክ አለ።

◈ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ዘመን ከድንጋይ ወይንም ከእንጨት የተዘጋጁ በርካታ ጣኦቶች እንደነበሩ ለማንም የማይሰወር ሐቅ ነወ። አንዲ ምሳሌ ብቻ እንመልከት!

➤አቡ ዋቂድ አልለይሢይ ረዲያላሁ አንሁ ባስተላለፎት ታሪክ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ወደ ሑነይን በወጡ ግዜ አጋሪዎች መሳሪያዎቻቸዉን በሚሰቅሉባቴ ዛፍ አጠገብ አለፉ። "መስቀያዋ" ይሏታል። (በቅርብ ከሰለሙት ዉስጥ ከፊሎቹ)"ለኛም መስቀያዋን አድርግልን፣ልክ ለነሱ (ለአጋሪዎቹ) መስቀያ እንዳላቸዉ"አሉ። ይህኔ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦

سُبْحَانَ اللهَ ! هَذَا كَمَا قَّالَ قَوْمُ مُوسَی : ﴿ٱجْعَل لَّنَآ إِلَٰهاً كَمَا لَهُمْ ءَالِهَةٌ ﴾ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِ لَتَرْكَبُنَّ سُنَنَی مَنْ كَانَ قبلكُمْ ،،

(ሱብሓነላህ የተናገራችሁት ልክ የሙሳ ሰዎች(ለነሱ አምላኮች እንዳሏቸዉ ለኛም አምላክ አድርግልን)እንዳሉት ።ነፍሴ በእጁ በሆነችዉ እምላለሁ! በርግጥም ከእናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለግ ትከተላላችሁ።) (ዚላሉል ጀናህ :76)

➤የስም መለዋወጥ እዉነታዉን አይቀይርምና ይሄዉ ዛሬም ድረስ ዛቱ አንዋጥ በብዙ ሙስሊም አካባቢዎች አለች።

➤ዛሬም በተመሳሳይ በተለያዩ አካባቢዎች የስለት ክር የሚተበተብባቸዉ ፣እርድ የሚፈፀምባቸዉ፣ በአመት ተሰባስበዉ የሚያሳልፍባቸዉ ፣ለበረካ የሚታረፍባቸዉ፣ ዛፎች ድንጋዮች ብዙ ነዉ።

ኢንሻ አላህ ይቀጥላል።።።።።።


🇸🇦ተዉሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ ኪታብ የተወሰዴ!!

https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
◈የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሽርክ መመሳሰል!! ክፍል አራት ➧ዛሬም እንደ ጥንቱ ፀሀይና ጨረቃ የሚያመልክ አለ። (وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ…
➲የጥንቶቹ ሙሺሪኮች ሺርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!

➳ክፍል አምስት

ዛሬም እንዴጥንቱ ነብያትን ፣ደጋጎችን ፣ ሙታን የሚያመልክ አለ!

(اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَٰهًا وَاحِدًا ۖ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۚ سُبْحَانَهُ عَمَّا يُشْرِكُونَ)التوبة ٣١

➧ከሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለዉን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃዉንቶቻቸዉንና መነኩሳታቸዉን የመርየምን ልጂ መሲሑንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገዉ ያዙ። ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነዉ። (አትተዉባህ፡31)

➲ኡሙ ሰለማና ኡሙ ሐቢባ ረዲያለሁ አንሁማ በሐበሻ ምድር ሰላዩዋት "ማርያ" የምትባል ቤተክርስቲያን በዉስጧም ስላሉ መስሎች ለነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ያወሳሉ። ይህኔ እሳቸዉ እንዲህ አሉ፦

إنَّ أُولئِك إذَا كَانَ فَيهِمۡ الرَّخُلُ الصَّالِحُ فَمَاتَ بَنَوۡا عَلَی قَبۡرِهِ مَسۡجِدًا وَصَوَّرُوا فَيهِ تِلْكَ الصُّوَرَ فَأُولَئِكَ شِرَارُ الخَلقِ عِندَ اللَّه يَوْمَ القِيَامَةَ

➠እነዚህ ሰዎች በዉስጣቸዉ አንድ መልካም ባሪያ በሞተ ግዜ ቀብሩ ላይ ቤተ አምልኮ ይገነባሉ ።በዉስጡም እነዚያን (ያያችኋቸዉን)ምስሎች ይሰራሉ።እነዚህ አላህ ዘንድ ክፉ ፍጡሮች ናቸዉ።[ቡኻሪ:427 ሙስሊም:528]

➧ከነዚህ ማስረጃዎች የምንረዳዉ በነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ዘመን የነበረዉ ቁርዓን ላይ የተወገዘ ሺርክ አንዳንዶቹ እንደሚያስቡት ጣኦት አምልኮ ላይ ብቻ የተገደበ እንዳልነበር፣ይልቁንም ነብያትንና ደጋጎችን የሚያመልኩ እንደነበር ነዉ።

➳ዛሬም ልክ እንዴጥንቱ የአላህ ነብይ ዒሳንና እናታቸዉ መርየምን የሚያመልክ አለ-ሰላም በሁለቱም ላይ ይሁንና።

➻ልክ እንዲሁ ነብዩ ሙሐመድ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም በተጨባጭ የሚያመልክም በተጨባጭአለ። ይሄ በሰፊዉ የሚታይ ነገር ነዉ።

➭"ኹዝቢየዲ" ያረሱለላህ!!(የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!እጄን ያዙኝ!) እያሉ የድረሱልንጥሪ የሚያሰሙት ቀላል አይደሉም።

➭በየ መዉሊዱ በሚነበበዉ "ቡርዳ" የተሰኘ የቡሶይርይ ግጥም ዉስጥ ያፈጠጡ ያገጠጡ የሺርክ ስንኞች ይገኛሉ።

➻ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም "ካንተ ዉጭ የምሸሺበት የለኝም " የለዉሀል መሕፉዝ እዉቀት ሳይቀር ሁሉን ታዉቃለህ" እያለ መማፀኑ ግልፀ በሆነ መልኩ ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ወደ ማምለክ እንደተገባ ያሳያል።

➧በሀገራችን በስፍት የሚደመጡ መንዙማዎች እንዲሁ ነብዩን ሰለላህ አለይሂ ወሰለም እና ደጋጎቹ በመጣራት የታጨቁ ናቸዉ።

➛ኢንሻ አላህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

📚ተዉሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ ኪታብ የተወሰዴ!

ውደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ይ ጠ ቀ ማ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➲የጥንቶቹ ሙሺሪኮች ሺርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል! ➳ክፍል አምስት ዛሬም እንዴጥንቱ ነብያትን ፣ደጋጎችን ፣ ሙታን የሚያመልክ አለ! (اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ وَمَا أُمِرُوا إِلَّا لِيَعْبُدُوا إِلَٰهًا وَاحِدًا…
➲የጥንቶቹ ሙሺሪኮች ሺርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ስድስት
➛➛➛➛➛➛➛

ዛሬም እንደ ጥንቱ መላእክትና ጂን የሚያመልክ አለ!!


{وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ جَمِيعًا ثُمَّ يَقُولُ لِلْمَلَائِكَةِ أَهَٰؤُلَاءِ إِيَّاكُمْ كَانُوا يَعْبُدُونَ }٤٠ { قَالُوا سُبْحَانَكَ أَنتَ وَلِيُّنَا مِن دُونِهِم ۖ بَلْ كَانُوا يَعْبُدُونَ الْجِنَّ ۖ أَكْثَرُهُم بِهِم مُّؤْمِنُونَ} ٤١ سورة سبٱ ٤٠_٤١

➧ሁሉንም በሚሰበስባቸዉና ከዚያም ለመላእክቱ። "እነዚህ እናንተን ነበር የሚገዙት?" በሚላቸዉ ቀን (የሚሆነዉ አዉሳ)። መላዕክቱም: ጥራት ይገባህ! ከነሱ ይልቅ ረዳታችን አንተዉነህ። ይልቁንም ጂንን ነበር የሚያመልኩት። አብዘሃኞቹ በእነሱ አማኞች ናቸዉ ይላሉ። (ሰበዕ :40_41)

{وَأَنَّهُ كَانَ رِجَالٌ مِّنَ الْإِنسِ يَعُوذُونَ بِرِجَالٍ مِّنَ الْجِنِّ فَزَادُوهُمْ رَهَقًا} سورة الجن ٦

(እነሆ ከሰዎች የሆኑ ወንዶች በወንድ ጂኖች ይጠበቁ ነበር ። መሸበርንም ጨመሯቸዉ። (አልጂን:6)


➲ዛሬም ተመሳሳይ እዉነታ አለ።አድስ ቤት ሰርተዉ ሲገቡ የአካባቢዉ" ቆሌ" እንዳይጣላቸዉ ለመጥበቅ ደም የሚያፈሱ አሉ። ከህመም ለመጠበቅ የተለያዩ መልክና ስያሜዎች ያሏቸዉ ዶሮዎች በላያቸዉ ላይ አዙረዉ የሚለቁ በኋላም በቃላቸዉ የሚያርዱ ሰዎች በሃገራችን በብዛት አሉ።

➲በመንገድ ላይ ሲጓዙ አስፈሪ አካባቢ ሲደርሱ ወይም ከፍ ያለ ዛፍ ሲያገኙ ከስሩ ለበረካዉ ተቀምጠዉ የአካባቢዉን ቆሌና አድባር ከስጋት እንዲጠብቃቸዉ የሚለማመጡ ብዙ ናቸዉ።

➧ታድያ የሚያስቡትን አማን፣ የሚያልሙትን ጤና ሊያገኙ ቀርቶ ሁለየ በስጋት ነዉ የሚኖሩት። ሁለየ ምርኮኛ ሆነዉ ነዉ የሚቀሩት። ከላይ የተጠቀሰዉ የቁርዓን መልዕክትም ይህን ነዉ የሚያስረዳን። ሌላ ማስረጃ እንጨምር

{أُولَٰئِكَ الَّذِينَ يَدْعُونَ يَبْتَغُونَ إِلَىٰ رَبِّهِمُ الْوَسِيلَةَ أَيُّهُمْ أَقْرَبُ وَيَرْجُونَ رَحْمَتَهُ وَيَخَافُونَ عَذَابَهُ ۚ إِنَّ عَذَابَ رَبِّكَ كَانَ مَحْذُورًا} سورة الإسراء ٥٧

➧እነዚያ እነሱ የሚገዟቸዉ ፣ማናቸዉም(ወደ አላህ)ይበልጥ ቅርብ እንደሚሆኑ(መጣር) ወደ ጌታቸዉ መዳረሻን ይፈልጋሉ። እዝነቱም ይከጂላሉተ ቅጣቱንም ይፈራሉ። የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነዉና።{አል ኢስራእ :57}

➲ታላቁ ሶሐቢይ ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ረድያላሁ አንሁ ስለዚች የቁርአን አንቀፀ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ።

"የሆኑ ጂኖች ያመልኩ በነበሩ የዐረብ ክፍሎች ሳቢያ ነዉ የወረደችዉ። ጂኖች ሰለሙ። ያመልኳቸዉ የነበሩ ሰዎች ግን አላወቁም።[ቡኻሪ :4715፣ ሙስሊም 3030]


➲በዚች አንቀፀ ዉስጥ የተጠቀሱት አጋሪዎች ጂኖች ያመልኩ እንዴነበረ በቀላሉ መረዳት ይቻላል ማለት ነዉ። ይሄ ደግሞ ሺርክና ሙሽሪኮቹን የሚያወግዙት የቁርዓን አንቀፆች የወረዱት ድንጋይ ዛፍ በሚያመልኩ ላይ ብቻ እንዳልነበር ፍንትዉ አድርጎ ያሳያል። ዛሬም በተመሳሳይ በሀገራችን" አድባር፣ቆሌ፣ሙወከል፣ዛር፣"ራሄሎ"እየተባሉ ልክ እንዴ ጥንቱ ጂኖች ይመለካሉ።

➧ኢንሻ አላህ ይቀጥላል ◉◉◉◉◉◉◉

➛ተዉሒድ የሁለት ሀገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መፀሃፍ የተወሰዴ!

➭ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ይጠቀማሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
Channel photo removed