የሸይኸ ፈውዛን ምክር
العلامة الفوزان
ልብ በሉ አድምጡት_ራሳችንን እንፈትሽ!!?
#እውነት ምን_እየሰራን_ነው!??
በሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን አንደበት(ሀፊዞሁሏህ)
- ሱንዮች አትበታተኑ
-`ጥፋት ካለ_ተመካከሩ
-#ራስ በራሲችሁ ህሜትን_ራቁ
#የወንድማችሁን ስጋ_አትብሉ
↷⇣🌹⇣↶
https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/11140

Audio
AudioLab
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሃፊዘሁላህ
https://t.me/iliyasNassir/3203
https://t.me/iliyasNassir/3203
Audio
AudioLab
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሃፊዘሁላህ
https://t.me/iliyasNassir/3204
https://t.me/iliyasNassir/3204
Audio
AudioLab
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሃፊዘሁላህ
https://t.me/iliyasNassir/3205
https://t.me/iliyasNassir/3205
ለኢማናችን መድከም መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው ?
እምነት ከሌላቸው ሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜያቶች መቀመጥ
ይህ ለአንድ ሰው ኢማን መቀነስ ምክንያት ነው፡፡ አማኝ ምንጊዜም በራሱ ደካማ ነው ነገር ግን ከሙስሊም ጓደኞቹ ጋር ጠንካራ ነው፡፡ ሀሰነል በስሪ(አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለው ነበር “ወንድሞቻችን ከቤተሰቦቻችን የበለጠ ለኛ ቅርብ ናቸው፡፡ ቤተሰቦቻችን ይህን አለም ሲያስታውሱን ሙስሊም ወንድሞቻችን ግን አሄራን ነው ሚያስታውሱን” ብለዋል፡፡ ታዲያ የሙስሊሞች ቀረቤታ ከኛ ከራቀን በዱንያ ውዴታ ስካር ውስጥ ገብተን ኢማናችን ባዶ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡
ሷሊህና አዋቂ ከሆኑ ሰዎች መራቅ
ከደጋግ የአላህ ባሮች ብዙ ትምህርት ይወሰዳል፤ ትምህርት ብቻ ሳይሆን በጎ ተግባርና ጥሩ ባህሪ ይወረሳል፡፡ ይህን ያስለመደ ሰው ከዛ ደግ ሰው የተለየ ጊዜ ኢማኑ እንደሚወርድ አጣራጣሪ አይደለም፡፡ ልበ ደረቅነትና ግድየለሽነት ተያይዘው መምጣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ለዚህም ነው ነብዩ ሙሐመድ(ሰላትና ሰላም በርሰቸውላይ ይሁንና) ሞተው የተቀበሩ ጊዜ ባልደረቦቻቸው “ልባችንን ስንመለከት ትልቅ ለውጥ እንዳመጣን ይታወቀናል” ያሉት፡፡
ከሀዲስና ከቁርዐን መራቅ
የእምነት ምንጭ ከሆኑት ቁርዐንና ሀዲስ ተርቆ ኢማንን ማሰብ ማለት “ወጥ የለም እንጂ እንጀራ ቢኖር እንበላ ነበር” እንደተባለው ተረት ከመሆን በቀር ፋይዳ የለውም፡፡ በአሁኑ ሰዐት የሚታየው ከባድ ችግር አንዱ ይህ ነው፡፡ አዛዡን በአግባቡ ሳናውቅ ወደ ትዕዛዙ መሮጥ ከተያያዝነው ሰነበትን፡፡ ለማለት የፈለኩት እስልምና አላህ ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን አላህ ምን እንዳልሆነም ጭምር በቁርዐንና በሀዲስ በሚገባ ተንትኖልናል፤ ግን እኛ እውን አላህን በሚገባ አውቀነዋል ወይ ? ለኢማን መውረድ ዋናው ሰበብ አላህን አለመፍራት ነው፡፡ ጥያቄው አላህን በሚገባ ሳናውቀው እንዴት እንፈራዋለን ነው ? ለዛም ነው እልቅናው ከፍ ያለው ጌታችን አላህ “እኔን የሚፈሩኝ የሚያውቁኝ ብቻ ናቸው” ያለው፡፡ በአሁኑ ሰዐት እኛ የተጠመድነው ከእስልምና በሗላ በተፈበረኩት በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፍልስፍና፣ በሳይኮሎጂ፣ ልብወለድና ጥቅም በሌላቸው መጽሔቶችና ጋዜጣዎች ላይ ነው፤ እነዚህ በራሳቸው በኢማናችን መድከም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው፡፡
ወንጀል በተሞላበት አካባቢ መኖር
ዙሪያህን ረጋ ብለህ ቃኘው...አንዱ ጠጪ፣አጫሽና ቃሚ፤ሌላኛው በዘፈንና በፊልም ድንዝዝ ያለ፤ በሌላ በኩል በተቃራኒ ፆታ የተለከፈና አላስፈላጊ ፎቶዎችና ምስሎች ሲያይና ሲያነብ የሚውል፤ ወሬያቸው ሀሜት፣ ሰው መቦጨቅ ወሬ ማመላለስ፤ ዛሬ አርሰናል ማን ገባ ነገ ማን ወጣ....ተገልፆ አያልቅም፤ አንዳንድ አካባቢዎች ይህን ብቻ ያስታውሱሃል፡፡ አንዳንድ አካባቢ ደግሞ ቢዝነስ ብቻ ሚወራበት ቦታ...ስራ፣ ብር፣ ኢንቨስትመንት የመሳሰሉት...እኛ የቤታችን ውጠት ቤታችን ደግሞ የአካባቢያችን ውጤት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ታዲያ በአሁኑ ሰዐት የሙስሊም ቤት ስንገባ ብዙ አሳፋሪ ኮተቶች ማየት የተለመደ ነው፡፡ አሳፋሪ ሙዚቃዎች፣ ፊልሞች፣ የተከለከለ የሴትና የወንድ መቀላቀል...የመሳሰሉት፡፡ በእንደዚህ አካባቢ መኖር ልባችን እንደ እንጨት መድረቁ ጥርጥር የለውም፡፡
ልባችን የርሷ ባሪያ እስክንሆን በዱንያ ስራ መጠመድ
ነብዩ ሙሀመድ(ሰላትና ሰላም በርሰቸውላይ ይሁንና) “የዲናርና የዲርሃም ባሪያ ጠፋ” ማለታቸው በሰሂህ በቡሀሪ ተዘግቧል፡፡ የምትፈልገው ቦታ የሚያደርስህ ስንቅ በቂህ ነው ምክንያቱም ነብዩ መሐመድ(ሰላትና ሰላም በርሰቸውላይ ይሁንና) “የሰው ልጅ አንድ ሸለቆ ወርቅ ቢሰጠው ሌላ ሁለተኛ ይመኛል፤ የሰውን ልጅ ሆድ ሚሞላው አፈር ብቻ ነው” ብለዋልና፡፡ ይህ እውነታ በሁላችንም ላይ አለ፤ ይህን ስል አንድ ቃለ ምልልስ አስታወሰኝ...የአለማችን አንደኛው ሃብታም ተጠየቀ “ያንተ ገንዘብ እኮ አንተንና ካሁን በሗላ ለሚመጡት መቶ ዘሮችህ አንደላቆ ያኖራል፤ ለምን ትሰራህ ?” ሲባል “ሁለተኛው ሀብታም እንዳይደርስብኝ ነው” ብሎ መለሰ፤ ሁለተኛው ሀብታም ተመሳሳይ ጥያቄ ሲጠየቅ እሱም “አንደኛው ሀብታም ላይ ለመድረስ ነው ምሰራው” አለ፡፡ ታዲያ ነብዩ ያሉት እውነታ አልተገለፀላችሁም ? ዱንያ አንስራ የሚል ቃል አልወጣኝም ለማለት የፈለኩት ኪሳችን ላይ እንጂ ልባችን ላይ አደላድለን አናስቀምጣት ነው፡፡
ከብዙ በጥቂቱ የኢማናችን መድከም ሰበቦች ይህን ይመስላሉ፤ ይህን በሽታ እንዴት ማከም እንደምንችል ኢንሻአላህ በሚቀጥለው ክፍል እናቀርበዋለን፡፡
✏️✏️✏️✏️✏️✏️
https://t.me/httpsLatahzen

Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
#አልሀምዱሊላሒ
ሱብሀን የኛ ጌታ ጥበቡ ገራሚ
እጅግ አዛኝ ሆኖ ተመልካችም ሰሚ
ለሰውልጅ በማሰብ ስለሆነ ደካማ የማይችል ልፍስፍስ
ለድካሙ እረፍት እንቅልፍ ፈጠረለት ህሊናው እንዲያድስ።
የጀሊሉ ትዕዛዝ ወቅቷንም ጠብቃ
ይኸው ብቅ ብላለች የማለዳ ጀንበር አማምራ ደማምቃ
የምድር ፍጥረታት ቀሰቀሰችው በብርሃን አሙቃ
#አልሀምዱሊላሒ ህያው ላደረገን ከሞታችን በኋላ ዳግም ላነቃን
ስራችን እንድናስውብ ሌላ እድል ለሰጠን፣
ወደ እሱ ነውና የኛ መሰብሰቢያ መመለሻችን።
በአዝካር በቁርኣን እሱን በማወደስ
ምሽቱን አሳይቶን ለንጋት እንድንደርስ
ላበቃን ጌታችን ምስጋናን በማቅረብ
ውሎአችን እንጀምር አላማን በማንገብ
ለአኼራው ቤታችን ስንቅን ለመሰብሰብ።
መልካም ውሎ 🥀🥀🌴
ሱብሀን የኛ ጌታ ጥበቡ ገራሚ
እጅግ አዛኝ ሆኖ ተመልካችም ሰሚ
ለሰውልጅ በማሰብ ስለሆነ ደካማ የማይችል ልፍስፍስ
ለድካሙ እረፍት እንቅልፍ ፈጠረለት ህሊናው እንዲያድስ።
የጀሊሉ ትዕዛዝ ወቅቷንም ጠብቃ
ይኸው ብቅ ብላለች የማለዳ ጀንበር አማምራ ደማምቃ
የምድር ፍጥረታት ቀሰቀሰችው በብርሃን አሙቃ
#አልሀምዱሊላሒ ህያው ላደረገን ከሞታችን በኋላ ዳግም ላነቃን
ስራችን እንድናስውብ ሌላ እድል ለሰጠን፣
ወደ እሱ ነውና የኛ መሰብሰቢያ መመለሻችን።
በአዝካር በቁርኣን እሱን በማወደስ
ምሽቱን አሳይቶን ለንጋት እንድንደርስ
ላበቃን ጌታችን ምስጋናን በማቅረብ
ውሎአችን እንጀምር አላማን በማንገብ
ለአኼራው ቤታችን ስንቅን ለመሰብሰብ።
መልካም ውሎ 🥀🥀🌴
እስቲዓና፦ማለት የዱኒያም ሆነ የአኽራን ጉዳይ ለማሳካት እገዛ መፈለግ ማለት ሲሆን የዚህም ብዙ ክፍሎች አሉት (1)እገዛ ከአላህ መፈለግ (2)በሚችሉት ነገር ብቻ ከፉጡር እገዛን መፈለግ (3)በሕወት ያለና አጠገቡ ባለ ሰው ግና ደካማ በሆነ ሰው መደገፍ(4)በሟች መታገዝ(5)በጅኖች መታገስ(6)አላህ ዘንድ በሚወደዱ ሥራዎች
(1)እገዛ ከአላህ መፈለግ ፦ይህም ባሪያዉ ጉዳዩን በሙሉ ወደ አላህ በመተናነስ በመቅረብ እርዳታን መጠየቅ ነው፡፡ ይህም ባሪያዉአላህ ብቻዉን የሚፈልገውን እገዛ እንደሚሰጠዉ ሙሉ በሙሉ በማመን መሆን አለበት፡፡አላህ እንዲህ ይላል((ኢያ ከነእቡዱ ወእያ ከነስተኢን))አንተን ብቻ እንገዛለን፤አተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡እብኑል ቀይም እስትዓና በአላህ ላይ ያለንን እርግጠኝነት በሱ ላይ መደገፋችን ያሣያል ብለዋል እገዛ የሚፈልግ ሁሉ ከአላህ ብቻ ይፈልግ እሱ ብቻ ነው የሰዎችን የእገዛ ጥያቄ ለመመለስ አቅም ያለዉ ለዚህ ነውሙሣ(ዐ ሰ)ለህዝቦቹ እንዲ በማለት መልዕክት ያስተላለፈዉ ለአላህ ተገዙ ታገሱም ምድር ለአላህ ናት ፡፡ከባሮች ለሚሻው ያወርሣታል፡፡ምስጉንዋም ፍፃሜ ለጥንቁቆች ናት አላቸው☝️((አል-አዐራፍ 128))
(2) ከሚችሉት ነገር ብቻ ከፉጡራን እገዛ መፈለግ፦እገዛ በተፈቀደ ነገር ከሆነ አላህ እንዲ ይላል በበጎ ነገር አላህን በመፍራት ተረዳዱ፡፡ግን በኃጢአት ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡አላህንም ፍሩ፡፡አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡(አል ማዕዳህ፡2)በሀራም ላይ ከሆነ በሁለቱም (በአጋዥና ተጋዥ )ላይ ሀራም ነው የተወደደ በሆነ ነገር ከሆነ አጋዥ አጅር ያገኝበታል፡፡በአላህ መንገድ ለግሱ፡፡በእጆቻችሁንም(ነፍሶቻችሁን)ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡በጎ ስራንም ስሩ፤አላህ በጎ ሰሪዎችን ይወዳል፡፡(አል በቀራ 195)
(3)በሕይወት ያለና አጠገቡ ባለ ሰው ግና ደካማ በሆነ ሰው መደገፍ፦ይህ ጫወታ ነው ለምሣሌ፡በጣም ደካማ የሆነን ሰው ትልቅ ሸክም አሸክመኝ ብሎ መጠየቅ፡፡✍✍ኑርአህመድ
(4)በሟች መታገዝ፦ይህ ክልክል የሆነ የእገዛ አይነት ነው፡፡ድርጊቱም ሽርኩል አክበር (ትልቁ ሽርክ)ነው፡፡አላህ ብቻ ማድረግ የሚችለዉ ነገር ከሞተ ሰው መጠየቅ ትልቅ በደል ነው፡፡ሙታኖች ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡የሞቱ ሰዎች ነብያቶች ሆኑ ወሊዮች እንዲሁም ሌላ ተራ ሰው በዚህ ዘርፍ እኩል ናቸዉ፡፡ከነዚህ እገዛ የፈለገ ሰው ሙሽሪክ ነው፡፡☞♥ልብ በሉ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዋች ከሚገኙ አናጅና(ባሌ የሚገኘዉ የሼክ ሁሴን መሥጂድ)፣በገታ(ወሎ የሚገኘው የገታ ሼክ ቀብር)በጉራጌ ዞን የአብሬትናየቃጥባሬ ቀብር በርካታ መሠል ቦታዎች ይኖራሉ፡፡ወደነዚህ ቦታዎች በመሄድ ከነሱ በሆነ ነገር እንዲረዳቸዉ መለመን ትልቁ ሽርክ ነው፡፡ ከእስልምና ያስወጣል፡፡ከሰዉ ሁሉ በላጭ የሆኑት ነብዩ ቀብር በመሄድ እርዳታን መለመን ከትልቁ ሽርክ ነው ታዳ ለነብዩ ሽርክ ከሆነ ለተራ ሰው እንዴት እገዛን እንጠይቃለን እንደዉ ከኛ ዱዐን እገዛን ይፈልጋሉ እንጂ::✍✍ኑርአህመድ
ከሰዎችና ከሌሎች ከሚችሉ አካላት እገዝ መጠየቅ የሚፈቅደው ሶስት ነገሮች ሲሟሉ ብቻ ነው ፦ 1 በሕይወት መኖር አለበት 2 በአጠገቡ መኖር አለበት 3የሚችል መሆን አለበት ✍✍ኑርአህመድ
በማይችል አካል ያለ አንዳች ድብቅ እምነት ድረሱልኝ ማለት ይሄ ጨዋታ ይሆናል፡፡ ለምሣሌ ፦ለአንድ ሰውነቱ የደነዘዘ ሰው፣ ጉድጓድ ዉስጥ እየሰመጠ አድኑኝ ብሎ ጩኸት ማሰማት፡፡ ሰውየዉ ራሱ ፓራለይዝድ ሆኖ ተቀምጧልና ይህ ደካማ የማይችል ሰውመለመን ትርጉም የለውም ማለት ነው፡፡ባጠቃላይ የማይችል አካል ድረሱልኝ ብሎ መለመን፣ እስረኛ ለእስረኛ ከእስር ቤት አዉጣኝ ብሎ እንደ መለመን አይነት ማለት ነው ሟችን የሚለምን እንደዚህ ሰው አይነት ነው፡፡ምክኒያቱም ሰዉየዉ ከእስር እሱን ማዉጣ ቢችል ኖሮ ራሱ በወጣ ነበርና፡፡ ሌላ ምሳሌ፦ባህር ዉስጥ እየሰመጠ ያለ ሰው ሌላ እየሰመጠ ያለዉን ጓደኛዉን አድነኝ ብሎ መለመን ነው፡፡✍✍ኑርአህመድ
ኧረ በአላህ ይሁንብን እስቲ ቁጭ ብለን እናስብ ከአላህ ውጭ ያሉ ነገራቶች ምን ብለን ነው ወደነሱ ምንቃረበዉ እነሱ ሁላቸዉም ተሰባስበው አንድ ቁንጫ ሊፈጥሩ አይችሉም አላህ ያለምንም ረዳት ሰማይናምድር በዉስጧም ያሉ ነገራቶች የፈጠረ እሱን ትተን ወዴት የዉመል ቂያማ እነሱ ናቸዉ እንዴ ሚቀሰቅሱን ወይስ አላህ ነው ሱብሀን አላህ ራሳቸዉ ተቀስቅሰዉ የሰሩት ስራ ይሰጣቸዋል እንኳን ሊቀሰቅሱ ይቅርና እና በምን አይነት ሁኔታ ነው ያለነዉ አባታች ፣እናታችን ቀብር ዝየራ ብለዉ ጓዛቸዉ ይዘዉ ሲሄዱ ሚያዝገነዝብላቸዉ ጠፍቶ ሳይሆን ሀቅ ሚቀበል ታጣ አላህ ከዚህ ነገር ያዉጣን✍✍ኑር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ④
በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
#ፍቅርን_ፍቅር_ከሆነ_ሰው_ተማር
በሌሊት ስግደት ከጌታቸው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ቤታቸው ጠባብ ነበረችና ባለቤታቸው ዓኢሻ እግራቸውን ዘርግተው በተኙበት የአላህ መልክተኛ ወደሱጁድ ሲወርዱ እግራቸውን እንዲሰበስቡ የመእመናንን እናት ዓኢሻን ቆንጠጥ ያደርጓቸዋል ረዘም ላለ ሰዓትም በስግደት ላይ ስለሚቆሙ የምእመናን እናት ዓኢሻ እግራቸውን መልሰው ይዘረጉታል።
አንድ ወንድ ሚስቱን የመኪና በር ከፍቶ ሲያሰገባት ሲያይ ለሚስቱ ባለው ክብር ይደነቃል ነገርግን የአላህ መልክተኛ ﷺ 'በኸይበር' ዘመቻ ላይ ሚስታቸውን ሶፍያን በተከበረው ጭናቸው ላይ ቆማ ግመል ላይ እንድትወጣ አድርገዋል ይህ በዘመቻ ወቅት ለሚስታቸው ያላቸውን ክብር ያሳዩበት ነው። ይኽንን ግን አያስተውልም!
ለሚወዱት ሰው አበባ ወይም ጥሩ ሽታ ያላቸው ተክሎችን መስጠት የምዕራባውያን ፈለግ እንደሆነ አድርገው የሚገመቱ አሉ ነገርግን የአላህ መልክተኛ ﷺ << ለሱ 'ረይሐን' (የተክል አይነት) የተሰጠው ሰው አይመልሰው (ይቀበል) ቀላልና ሽታዋ ውብ ነውና >> ብለዋል ። 🌷
የስጦታ ትንሽ እንደሌለውም እያስተማሩን ነው!
የአላህ መልክተኛ ﷺ ከምእመናኖች እናት ዓኢሻ ጋር ሆነው መጠጣት በፈለጉ ጊዜ ዓኢሻ የጠጡበትን እቃ ይዘው በጠጡበት ቦታ ይጠጡ ነበር ።ይኽ በትዳር ሕይወት ውስጥ ፍቅርን መተማመንን አንደሚጨምር ጥርጥር የለውም ።
ይኽ ታላቅ ነብይ ለሚስት የምናጎርሰው ጉርሻ ራሱ ሰደቃ እንደሆነ ያስተምሩናል ።🍶
የምእመናን እናት ዓኢሻ የአላህ መልክተኛ ﷺ ቤት ውስጥ የሚያደረጉትን ተጠይቀው ' ልብሳቸውን ይሰፉ ፤ ወተት ያልቡ እራሳቸውንም ቤተሰቦቻቸውንም ይረዱ ነበር ' ትላለች። የሴት ስራ ነው ተብሎ የሚተው ነገር እንደሌለም እያስተማሩ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
🌹ፍቅርን ፍቅር ከሆነ ሰው ተማር!
🖊ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
በሌሊት ስግደት ከጌታቸው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ቤታቸው ጠባብ ነበረችና ባለቤታቸው ዓኢሻ እግራቸውን ዘርግተው በተኙበት የአላህ መልክተኛ ወደሱጁድ ሲወርዱ እግራቸውን እንዲሰበስቡ የመእመናንን እናት ዓኢሻን ቆንጠጥ ያደርጓቸዋል ረዘም ላለ ሰዓትም በስግደት ላይ ስለሚቆሙ የምእመናን እናት ዓኢሻ እግራቸውን መልሰው ይዘረጉታል።
አንድ ወንድ ሚስቱን የመኪና በር ከፍቶ ሲያሰገባት ሲያይ ለሚስቱ ባለው ክብር ይደነቃል ነገርግን የአላህ መልክተኛ ﷺ 'በኸይበር' ዘመቻ ላይ ሚስታቸውን ሶፍያን በተከበረው ጭናቸው ላይ ቆማ ግመል ላይ እንድትወጣ አድርገዋል ይህ በዘመቻ ወቅት ለሚስታቸው ያላቸውን ክብር ያሳዩበት ነው። ይኽንን ግን አያስተውልም!
ለሚወዱት ሰው አበባ ወይም ጥሩ ሽታ ያላቸው ተክሎችን መስጠት የምዕራባውያን ፈለግ እንደሆነ አድርገው የሚገመቱ አሉ ነገርግን የአላህ መልክተኛ ﷺ << ለሱ 'ረይሐን' (የተክል አይነት) የተሰጠው ሰው አይመልሰው (ይቀበል) ቀላልና ሽታዋ ውብ ነውና >> ብለዋል ። 🌷
የስጦታ ትንሽ እንደሌለውም እያስተማሩን ነው!
የአላህ መልክተኛ ﷺ ከምእመናኖች እናት ዓኢሻ ጋር ሆነው መጠጣት በፈለጉ ጊዜ ዓኢሻ የጠጡበትን እቃ ይዘው በጠጡበት ቦታ ይጠጡ ነበር ።ይኽ በትዳር ሕይወት ውስጥ ፍቅርን መተማመንን አንደሚጨምር ጥርጥር የለውም ።
ይኽ ታላቅ ነብይ ለሚስት የምናጎርሰው ጉርሻ ራሱ ሰደቃ እንደሆነ ያስተምሩናል ።🍶
የምእመናን እናት ዓኢሻ የአላህ መልክተኛ ﷺ ቤት ውስጥ የሚያደረጉትን ተጠይቀው ' ልብሳቸውን ይሰፉ ፤ ወተት ያልቡ እራሳቸውንም ቤተሰቦቻቸውንም ይረዱ ነበር ' ትላለች። የሴት ስራ ነው ተብሎ የሚተው ነገር እንደሌለም እያስተማሩ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
🌹ፍቅርን ፍቅር ከሆነ ሰው ተማር!
🖊ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
☞ረመዳን እየመጣ ነው ሰማታቹኃል አይደል…እና ወዳጆቼ እስከዛሬ ከነበርንበት ቀልብ እና የኢማን ደረጃ በጣም ከፍ ብለን መልካም ስራን ተላምደን ከወድሁ የዘጋጁተን ልንጠብቀው ግድ ይላል።የኢማን ደረጃችንን ከፍ ለማድረግ ፕሮግራም አውጥተን ብንጠቀም መልካም ነው እላለው፡፡
📄እኔ ለምሳሌ ይህንን ፕሮግራም አውጥቻለው(ከተስማማችሁ መልካም… ምክኒያቱም የሁሉም ሰው የስራ ዘርፍ እና ክፍት ክፍለ ግዜ ይለያያል እና…)
① ማታ አራት ሰዓት እንተኛለን፡፡
② ሌሊት አስር ሰኣት አሊያም ዘጠኝ ሰዓት ተኩል እንነሳለን፡፡ ለኔ ዓይነቱ ደካማ ሰው በአንድ ምሽት ዉስጥ 6 ሰዓት ከተኛ በቂ ነው፡፡
③ ከዉዱእ በኋላ ለሀያ ወይም ለአርባ ደቂቃ ዊትር እንሰግዳለን፡፡ እንደ ከእንቅልፍ አነሳሳችን እና አቅማችን ማድረግ እንችላለን፡፡
④ እስከ አሥራ አንድ ከሩብ ድረስ በኢስቲግፋርና በዚክር እንቆያለን፡፡ ይህ ከንጋት በፊት ያለው ሰዓት እጅግ የተወደደና ዱዓዉም ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በጣም ልንጠቀምበት ይገባል ። ስሜቱም ደስ ይላል። መስገጃችን ላይ ሆነን ወይም ጋደም ብለን ዚክር ዱዓና ኢስቲግፋር እናብዛ።
⑤እስከ አሥራ አንድ ሰዓት ተኩል ሱብሒ እንሰግዳለን፡፡ የሱብሒን ሱንና መርሳት የለብንም፡፡
⑥ከዚያ በኋላ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ባንተኛ መልካም ነው፡፡ ለዚክርና ዱዓ የሚወደድ ሰዓት ነውና እንድሁም ቁርኣንን ልንቀራበት የሚገባ ሰኣት ነው፡፡
⑦ከዚያ ተነስተን ቤተሰብ እናግዛለን፤ ወደ ት/ት መሄድ ካለብን እንሄዳለን ቤታችንን እናስተካክላለን፤ ለዕለት ዉሏችን መስመር እንሲዛለን፡፡
⑧ምሳ ከበላን ብኃላ የተወሰነ 30_40 ደቂቃ ያክል አረፍ ብንል ይህ አንድም ማታ ላይ ስንሰግድ እንቅልፍ እንዳያሸንፈን ያግዘናል፡፡ የቀይሉላ ሰዓትም ነዉና ሱናዉን አገኘን ማለት ነው፡፡
⑨ከዐስር በኋላ እስከ መግሪብ ባለው ሰኣት ሁሉም እንደ ፕሮግራሙ… በዚህ ሰኣት ክፍት ክፍለ ግዜ ያለው መስጁድ ቁጭ ብሎ የ ዒልም ሀለቃን ቢጣድ ለሱ የተሻለ ነው።
⑩አስራ አንድ ሰኣት ተኩል አከባቢ የማታ ዚክር(አዝካረል_መሳእ) እናድርግ።
⑪ሦስት ሰዓት ላይ እራት ብንበላ፡፡ ጎን ለጎን ኘሮግራሞች ካሉ መርጠን እናስኪድ። ከእራት በኋላ ባናመሽ መልካም ነው፡፡
♻️እናንተስ ምን አሰባቹህ? ይህ እኔ ያሰብኩት ነው(አላህ ኢኽላስን እና በተናገርኩት መተግበርን ይስጠኝና)
“ለናንተም ቢጠቅማቹህ ብየ ነው ያካፈልኳቹህ”
✍በወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድ
https://t.me/httpsLatahzen
📄እኔ ለምሳሌ ይህንን ፕሮግራም አውጥቻለው(ከተስማማችሁ መልካም… ምክኒያቱም የሁሉም ሰው የስራ ዘርፍ እና ክፍት ክፍለ ግዜ ይለያያል እና…)
① ማታ አራት ሰዓት እንተኛለን፡፡
② ሌሊት አስር ሰኣት አሊያም ዘጠኝ ሰዓት ተኩል እንነሳለን፡፡ ለኔ ዓይነቱ ደካማ ሰው በአንድ ምሽት ዉስጥ 6 ሰዓት ከተኛ በቂ ነው፡፡
③ ከዉዱእ በኋላ ለሀያ ወይም ለአርባ ደቂቃ ዊትር እንሰግዳለን፡፡ እንደ ከእንቅልፍ አነሳሳችን እና አቅማችን ማድረግ እንችላለን፡፡
④ እስከ አሥራ አንድ ከሩብ ድረስ በኢስቲግፋርና በዚክር እንቆያለን፡፡ ይህ ከንጋት በፊት ያለው ሰዓት እጅግ የተወደደና ዱዓዉም ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በጣም ልንጠቀምበት ይገባል ። ስሜቱም ደስ ይላል። መስገጃችን ላይ ሆነን ወይም ጋደም ብለን ዚክር ዱዓና ኢስቲግፋር እናብዛ።
⑤እስከ አሥራ አንድ ሰዓት ተኩል ሱብሒ እንሰግዳለን፡፡ የሱብሒን ሱንና መርሳት የለብንም፡፡
⑥ከዚያ በኋላ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ባንተኛ መልካም ነው፡፡ ለዚክርና ዱዓ የሚወደድ ሰዓት ነውና እንድሁም ቁርኣንን ልንቀራበት የሚገባ ሰኣት ነው፡፡
⑦ከዚያ ተነስተን ቤተሰብ እናግዛለን፤ ወደ ት/ት መሄድ ካለብን እንሄዳለን ቤታችንን እናስተካክላለን፤ ለዕለት ዉሏችን መስመር እንሲዛለን፡፡
⑧ምሳ ከበላን ብኃላ የተወሰነ 30_40 ደቂቃ ያክል አረፍ ብንል ይህ አንድም ማታ ላይ ስንሰግድ እንቅልፍ እንዳያሸንፈን ያግዘናል፡፡ የቀይሉላ ሰዓትም ነዉና ሱናዉን አገኘን ማለት ነው፡፡
⑨ከዐስር በኋላ እስከ መግሪብ ባለው ሰኣት ሁሉም እንደ ፕሮግራሙ… በዚህ ሰኣት ክፍት ክፍለ ግዜ ያለው መስጁድ ቁጭ ብሎ የ ዒልም ሀለቃን ቢጣድ ለሱ የተሻለ ነው።
⑩አስራ አንድ ሰኣት ተኩል አከባቢ የማታ ዚክር(አዝካረል_መሳእ) እናድርግ።
⑪ሦስት ሰዓት ላይ እራት ብንበላ፡፡ ጎን ለጎን ኘሮግራሞች ካሉ መርጠን እናስኪድ። ከእራት በኋላ ባናመሽ መልካም ነው፡፡
♻️እናንተስ ምን አሰባቹህ? ይህ እኔ ያሰብኩት ነው(አላህ ኢኽላስን እና በተናገርኩት መተግበርን ይስጠኝና)
“ለናንተም ቢጠቅማቹህ ብየ ነው ያካፈልኳቹህ”
✍በወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድ
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
🖌🖌🔖የአደም ልጅ ሆይ‼️🖌🖌
✏️💦የትላንት ትላንት ምንም አልነበረህም፤ ምንም ሳትይዝ፣ ራቁትህን ነው ይችን ዓለም የተቀላቀልከው፤
🔑 ይሁንና ትላንት ያጣኸውን ዛሬ አግኝተሃል፣ ዛሬ ያጣኸውን ነገ ታገኘዋለህ፣ ሁሉንም ደግሞ የነገ ነገ ታጣዋለህ።
🔑 ባጭሩ አንድ ቀን ሁሉንም ትተህ ትሞታለህ።
✏️💦ከሞትክ በኋላስ?
🔑 ከ3 ቀን በኋላ የጣቶችህ ጥፍሮች መወዳደቅ ይጀምራሉ።
🔑 ከ4 ቀን በኋላ የራስ ቅልህና ሰውነትህ ላይ ያሉ ጸጉሮች በሙሉ ይረግፋሉ።
🔑ከ5 ቀን በኋላ አንጎልህ መርገብ ይጀምራል፣ የሰውነትህ ሥጋ ይጠወልጋል፤ መቀመጫህ፣ ጡትና ኃፍረተ-ስጋህ ይበሰብሳል።
🔑 ከ6 ቀን በኋላ ቆዳህ መሳሳትና ቀስ በቀስም ከአጥንትህ ላይ መለያየት ይጀምራል።
🔑 ከ7 ቀን በኋላ ሆድህ ይቀልጣል፣ መጥፎ ጠረንም ማውጣት (radiate ማድረግ) ይጀምራል።
🔑 ከሞትክ ከ60 ቀን በኋላ መላው የሰውነትህ አካል ወዳልነበር ይለወጥና "አንተ" ማለት "አጥንት" ብቻ ትሆናለህ:-
🖌🌺ታዲያ🌺🖌
🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ትእቢት?
🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ራስ ወዳድነት?
🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ክርክር፣ ጭቅጭቅና ንትርክ?
🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ቅናት?
🔑 ለምንስ ይሆን ይሄ ሁሉ ጥላቻ?
🔑 እኮ ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ የክፋት ሥራ?
🔑 ጥለህ ለምትሄደው አለም? እስኪ ለሞት ሩብ ጉዳይ እንደቀረው ሰው እንኑር!!
🔑ደሃ ሃብታም እያልክ ሳታደላ፣ የተማረ ያልተማረ ብለህ ሳትለይ፣ መልከ መልካም መልከ ጥፉ ሳትል፣ ባለስልጣን ተራ ሰው ብለህ ሳትመርጥ...እኩል- ተመልከት፣ ሰዎች ዘንድ በሚኖራቸው ደረጃ ሳይሆን አላህ ዘንዳ ሊኖራቸው የሚችል ደረጃ አታውቅምና አስተንትን!!
🔑 አንድ ቀን የሁላችንም ፍጻሜ አንድ ሥፍራ- መቃብር ነውና!። -
🔑 በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። ራስህንም በዚህ ምድር ብቻ አትለካው፣
፧ 🔑 ከዚህ አለም ወዲያ ያለውን ህይወት አስብና ጊዜህ ሳያልቅ ወደ አላህ ተጠጋ!!
አላህ ያግራልን!!
🔄🔄➨➨➧➧

✍ሲራጥ ምንድን ነው?
🌷👉 ሲራጥማለት በጃሀነም ጀርባ የተሰራ ድልድይ ነው ሲራጥ መነሻው የሰዎች መሰብሰቢያ ሲሆን መጨረሻው ደሞ የ ጀነት ደጃፍ ነው ማነው በዚ መንገድ የሚያልፈው ከ አደም አለይሂ ሰላም እስከ ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ኡመት ማለትም ሁሉም የሰው ዘር መቼ ነው የሚያለፉት ሁሉም ተበታትነው ፍርድ ከተሰጣቸው ቡሀላ የጀነት ሰዎች ትክክለኛውን መንገድ ይዘው እና እያበሩ ይጓዞሉ የጀሀነም ሰዎች ደሞ ወደ እሳት ይወድቃሉ አለህ ሱብሀነሁ ወተአላ እንዲ ብሏል ከናተ ውስጥ አድም ሰው የለም በዚ በ ሲራጥ የሚያልፍና የሚሄድ ቢሆን እንጂ ኢሄ በጊታህ ዘንድ አስቀድሞ የተወሰነና የተፈረጀ ነው ከዛህም ጌታቸውን ፈሪ የነበሩትን እናድናቸዋለን በደለኛ እና ካሂዲያዊያንን አዛው በተበረከኩበት እንዲቀሩ አርገን እተዋቸዋለን
#ሱረቱል_መርየም (71_72) ማነው መጀመሪያ በ ሲራጥ ላይ የሚያልፈው የነብያቶች መደምደሚያ የሆኑት ሀቢቡላህ ሙሀመድ ሰ አ ወ እና ኡመቶቹ አማቹም ካሀዲውም አጠቃላይ የ ረሱላችን ኡመት የሆነው ያልፋል ማለት ነው እነዚያ አለህን ፈሪ እና ሰላታቸውን የሚሰግዱ በሰላም ያልፋሉ ከሀዲያን አመፀኞች በ ቀኝ እና በግራ ይከባለላሉ ልክ እንደ ቢራቢሮ ቡሀሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ የ አላህ መልክተኛ ሰ አ ወ ሲራጥ በ ጀሀነም ጀርባ ይዘረጋል እኔ እና ኡመቶቼ መጀመሪያ ምናልፍ ይሆናል የዛን ቀን ከ መልእክተኞች ውጪ ማንም አይናገርም የ ረሱሎችም ጥሪ ምድነው አላሁ ሰላምህን አውርድ ብለው መለመን ብቻ ሲራጥ ምንይመስላል ሲራጥ ማለት ከ ሰይፍ የሳለ እና ከ ፀጉር የቀጠነ ጀለሶች እንግዲ አስቡት አሄን ሲራጥ ኢማን ካልሆነ ምንም አያሳልፈንም እንዲሁም ሰዎች እንደ ኢማናቸውና እንደ ስራቸው በ ሲራጥ ላይ የመሄዳቸው አይነት ይለያያል ከነዚውስጥም እንደ አይን ቅፅበት የሚያለፈው አለ አይኑን ከድኖ እስኪ ገልጥ ማለት ነው እንዲሁም እንደ መብረቅ ብልጭታ የሚያልፍ አለ እንደ ንፋስም የሚሄድ አለ እንደ ሚጋለብ ፈረስም የሚያፍ አለ እንደ ግመል ጋላቢም ዱብዱብ እያሉም እንዲሁም ኖርማል እርምጃና የመጨረሻው ተበርክኮ የሚሄድ ሲሆን ከዛ በታችም ያለው ተበርክኮ ጀሀነም እሳት ውስጥ የሚገባው ነው አዚ ዱኒያ ላይ ለ አላህ ብሎ እሱ በሚያዘው መልኩ ቀውጢ መሳጭ ዘናጭ እና አሪፍ ስራ የሰራ በ ሲራጥም አረፊ ቀጥ ያለመንገድ ይጓዛል በተቃራኒው ደሞ ከ እስልምና የራቀ እና የ አላህን ትዛዝ የማይፈፅም በ ሲራጥ ተበላ እሳትም ገቢ ነው በሲረጥም ጀሀነም የገቡት አማኞች እና አመፀኞች ይለያያሉ አማኞች ከፊት ሲሆኑ አመፀኞች ከ ሁዋላ ይሆናሉ አማኞች ጋ እንዳይደርሱ በ መሀላቸው መጋረጃ ይለቀቃል ሀያሉ ከ አርሽ በላይ ያለው ጌታችንም እንዲህ ይላል ወንድ መናፍቃን እና ሴት መናፍቃን ባሉ ጊዜ ለነዚያ ለ አማኞች አባካችሁን ጠብቁን ከናንተ ብርሀን አየሾፍን እያየን እድኔድ አማኞችም በዛ ሰአት አሉ ወደሁዋላ ተመለሱ ወደ ዱኒያ ሂዱና የሰራቹትን ስራ ኢዛቹ ኑ ጌታችን ለኛ ያበራልን በዱኒያ በሰራነው ስራ ነው በመሀከላቸው መጋረጃ ይጋረዳል ደጃፍ አለው ውስጡ የ ጀሊሉ ራህመት ያለበት ከፊትለፊቱ ቅጣት ያለበት ማለት ነው አማኞች ወደ ጀነት አመፀኞች ወደ ጀሀነም ይሄዳሉ ማለት ነው
አላህ
ከሲራጥ ይጠብቀን
ከ ጀሀነም እሳት ይጠብቀን
ከ ቀብርውስጥ ቅጣት ይጠብቀን
አላህን ከ ማሻረክ
ከክፍርና
ከ ቢድአ
አላህ ይጠብቀን አሚንንንን

🕌ሰ...ላ...ት...ን_ አ...ደ...ራ...🕌
🍃 ሶላት _ ያለ ራዕይ የተደነገገች ብቸኛዋ አምልኮ...)
የሶላትን ክብደት ከሚያመለክቱ ነገሮች መካከል በኢስራእና ሚዕራጅ #ሌሊት የተደነገገች ብቸኛዋ የአምልኮ ተግባር መሆኑ ነው። ያውም በመካከል አስተላላፊ መልዓክ ሳይኖር (ያለ ራዕይ)።
ሶላት በመልክተኛው ﷺ እና በሕዝቦቹ ላይ ያለ ጅብሪል (ዐ.ሰ) መልዕክት ነጋሪነት የተደነገገች ናት። መጀመሪያ ላይ ሀምሳ ሆና ነበር የተደነገገችው። ሆኖም ግን ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ለነብያችን በመከሩት መሰረት ነብያችን አላህ (ሱ.ወ) ዘንድ ተመላልሰው ወደ አምስት ዝቅ ተደረገች። የፈጠረን አምላክ አላህ (ሱ.ወ) እዝነቱ ሰፊ ነው። ታዲያ የግዴታ ሶላት በቁጥር አምስት ብትሆንም በምንዳ ግን የሃምሳ ሶላት ደረጃ የምትስተካከል መሆኗን ልብ ይሏል። ይህም አላህ ዘንድ የተፃፈ ድንጋጌ ነው። ("አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
ወዳጆቼ ! በቀን ውስጥ ግዴታ የተደረገብን ሶላት ብዛት ሀምሳ ቢሆን ኖሮ ማን ይችል ነበር ?… ፈፅሞ አይታሰብም። ያኔ በየስላቱ መካከላቸው ሊኖር የሚችለው የሰዓት ልዩነት ግፋ ቢል ሰላሳ ደቂቃ ብቻ መሆኑን እናስተውል። ዛሬ ግን ከሁለት እና ሦስት አራት ሰዓት ከዚያም በላይ በሆነ ልዩነት መካከል የምንሰግዳቸውን ሶላቶች መሳነፋችንና ባአግባቡ መወጣት አለመቻላችን የሚገርምና የሚያሳዝን ነው።
በዚህ መልኩ የእዝነቱ አምላክ አላህ (ሱ.ወ) እዝነቱንና ርህራሄውን አሳየን። ሆኖም ግን ብዙዎቻችን እፍረትና ጨዋነት የሚባል ነገር የተፈጠረብን አንመስልም። የአምላካችንን እዝነት አስተውለን ከኛ የሚጠበቅብንን አናደርግም።
<ላ ሐውለ ወላ ቁወተ ኢልላ ቢልላህ !> አላህ ይዘንልን።
♻️ይቀላቀሉን♻️