La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ (part 1)👌

#ቁርኣን
➲ልብ በይ ውዷ እህቴ
➱➱➱➱➱➱➱➱➱

ሀብታሙን ለማግባት አትድከሚ። ይልቁኑ መልካሙን አግቢ። ሀብታምነት መልካምነትን አይገዛም። መልካም ሲባል ደግሞ በሁሉም ዘርፍ እንከን አልባውን ማለት አይደለም። ይሄማ ከየት ይገኛል? ስለዚህ የሚቻለውን ያክል በመልካም ስራ ላይ የተሰማራውንና እንደጥቅል መልካም ስነምግባር አለው የሚባለውን ነው ማግባት ያለብሽ።

ሸይኽ ሙሀመድ ሷሊህ አልዑሰይሚን رحمه الله
🌙ጨረቃዋ ቀርባለች!!🌙

ወደ ፈጣሪያችን እኛን ልታቃርብ
ደርቆ ያመፀውን ልብን ልታረጥብ
በኢማን ልትሞላን ከወንጀል አርቃ
በሰላት፣በቁርአን፣በዚክር አሸብርቃ
በስሁር፣ በዘካ፣ በተራዊህ ደምቃ
የልባችን ፈዋሽ ቀረበች ጨረቃ
ከኢባዳ ርቀን ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀን
በዲናችን ጉዳይ እጅግ ተዘናግተን
ከኢስላም መርሆች በሩቁ አፈንግጠን
ዱንያ ላይ ተጥደን ሁሉን ነገር ረስተን
ብዙ ስንታትር መንገዱ ጠፍቶብን
ጨረቃ ቀረበች እኛን ልታግዘን
የጠፋውን መንገድ ልታመላክተን
ወደ ጀሊላችን እኛን ልትመልሰን
ልብን በእምነት ሞልታ 1 ልታረገን
በጉጉት ተናፍቃ እኛን ልታልቀን
ሁሉን አሰባስባ በእምነት በጋራ
አንድ ልታረገን ሸይጣንን አባራ
ከውሸት፣ከፈሳድ፣ከሀራም አፅድታን
ለደከመው ኢማን ይዛ መድሀኒትን
የጀሀነምን በር ከሩቁ አስዘግታ
የጀነትን በሮች ለእኛ አስከፍታ
ቀረበች ጨረቃ ብስራቱን ነጋሪ
የወርሃ ረመዳን ጅማሬን አብሳሪ!!!

ሱመያ ቢንት ኑሬ

🌙🦋 "if 🌙ጨረቃዋ ቀርባለች!!🌙

ወደ ፈጣሪያችን እኛን ልታቃርብ
ደርቆ ያመፀውን ልብን ልታረጥብ
በኢማን ልትሞላን ከወንጀል አርቃ
በሰላት፣በቁርአን፣በዚክር አሸብርቃ
በስሁር፣ በዘካ፣ በተራዊህ ደምቃ
የልባችን ፈዋሽ ቀረበች ጨረቃ
ከኢባዳ ርቀን ወንጀል ውስጥ ተዘፍቀን
በዲናችን ጉዳይ እጅግ ተዘናግተን
ከኢስላም መርሆች በሩቁ አፈንግጠን
ዱንያ ላይ ተጥደን ሁሉን ነገር ረስተን
ብዙ ስንታትር መንገዱ ጠፍቶብን
ጨረቃ ቀረበች እኛን ልታግዘን
የጠፋውን መንገድ ልታመላክተን
ወደ ጀሊላችን እኛን ልትመልሰን
ልብን በእምነት ሞልታ 1 ልታረገን
በጉጉት ተናፍቃ እኛን ልታልቀን
ሁሉን አሰባስባ በእምነት በጋራ
አንድ ልታረገን ሸይጣንን አባራ
ከውሸት፣ከፈሳድ፣ከሀራም አፅድታን
ለደከመው ኢማን ይዛ መድሀኒትን
የጀሀነምን በር ከሩቁ አስዘግታ
የጀነትን በሮች ለእኛ አስከፍታ
ቀረበች ጨረቃ ብስራቱን ነጋሪ
የወርሃ ረመዳን ጅማሬን አብሳሪ!!!

hayutii

🌙🦋 "if you like it




🦋🌙
210421_2320
My Recording
#የዛሬው _ሙሐደራ

#ነቢዩﷺቢዚ_አልነበሩምን?(2)

በመልካም ነገራቶች ላይ ለመሳተፍ በስራ ላይ የተወጠርኩ ነኝ ማለት የለብንም!!

ነቢዩ ሙሐመድምﷺ የቡዙ ሚስቶች አስተዳዳሪ ነበሩ

የጦር መሪም ነበሩ

አዳርም ይሰግዱ ነበር

ታማሚም ይጠየይቁ ነበር
La tehzen
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል አስራ አምስት ➧ሱፍያን አስሰውርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናገሩ፡- ▪️"رحم الله أبا حازم قال: "رضي الناس اليوم بالعلم وتركوا العمل" ➲“አባሀዝምን አላህ ይዘንለት! የሚከተለውን ተናገረ “ዛሬ ሰዎች እውቀትን ወደዱ ተግባርን ተው” ኢማሙ አህመድ ፍል ዒለል፡ 2659 ላይ ዘግበውታል ኢብኑ…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➛የመጨረሻው ክፍል ⓵⓺
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲በዚህ ርዕስ ዙሪያ ከሰለፎች ከተገኙት ንግግሮች ሁሉ ያማረው የሚከተለው ነው፡- ሱፍያን ረሂመሁሏህ- “ከአንተ ዘንድ እውቀትን መፈለግ ወይስ መተግበር ፣ የቱ ነው ተወዳጁ?” የሚል ጥያቄ ቀረበለት፡፡ እርሱም እንዲህ አለ ፡-

➧ “እውቀት እኮ የተፈለገው ለስራ ነው፡፡ለስራ ብለህ እውቀትን አትተው፡፡ለእውቀት ፍለጋ ብለህ ስራን አትተው፡፡” (አቡ ኑዓይም “ሒልየት አል’አውሊያእ፡ 7/12 ላይ ዘግቦታል)

ጥልቅ ፣ ጥቅሙ ታላቅ ፣ ተጽእኖ የሚያሳድር በሆነው የኸጢብ አልበግዳዲ “ኢቅቲዷኡል ዒልም አልአመል” በተባለው ኪታቡ ውስጥ የተናገረውን በማቅረብ ንግግሬን እቋጫለሁ፡፡

➲“አንተ የእውቀት ፈላጊ ሆይ! እኔ አደራ እልሀለሁ! እውቀትን ስትፈልግ ኢኽላስ
ይኑርህ፡፡ ነፍስህን በተግባር ላይ አሰልጥናት፡፡ እውቀት ዛፍ ማለት ነው፡፡ ስራ ደግሞ ፍሬው ነው፡፡ አንድ ሰው በእውቀቱ ካልሰራ ዓሊም ተብሎ አይቆጠርም፡፡ ከእውቀት ውጭ ሆነህ በስራ አትደሰት፡፡ በስራህ አጓዳይ ሆነህ በእውቀት አትደሰት፡፡ ከእነርሱ
ድርሻህ ቢያንስ እንኳ ሁለቱን ሰብስብ ፡፡

➧አዋቂ ሆኖ አካሄዱ በመበላሸቱ ምክንያት እውቀቱን ከተውበትና ዒባዳውን ተመልክተው እስከማህይምነቱ ከተከተሉት ሰው የበለጠ አንድም ደካማ ሰው የለም፡፡

➭አላህ በእዝነቱ ከቸራቸውና ፣ ጸጋውን ካሟላላቸው - ከዚህኛውም ይሁን ከዚያኛውም ክፍል - ከአስፈሪ ነገር ነጻ የሚሆኑት ጥቂት ናቸው፡፡ቸልተኛነትና ስንፍናን ማዘውተር ፤ ዝቅተኛነትን መምረጥ ፤ እረፍትና ምቾትን ማብዛት ፍጻሜው አስነዋሪ ፣ ኪሳራ እና አስጠሊታ ነው፡፡ ተግባር ከቅጣት ነጻ ለመሆን
እንደሚፈለገው ሁሉ እውቀት ለተግበር በጣም ይፈለጋል፡፡

➻እውቀት ስራ ካነሰው በዓሊም ላይ ሸክም ይሆናል፡፡ ሸክም ሆኖ ከሚመለስ ፣ ውርደትን ከሚያወርስ ፣ በባለቤቱ ላይ ማነቆ ከሚሆን እውቀት በአላህ እንጠበቃለን፡፡” ኢቅቲዷኡል ዒልም፡ ገፅ 18

➛በዚህ ርዕስ ዙሪያ የተሰጠው ትምህርት ተጠናቀቀ፡፡

➧በእኛ ላይ ሳይሆን ለእኛ ሁጃ እንዲሆን ፤ ባወቅነው እንዲጠቅመን ፤የሚጠቅመንን እንዲያሳውቀን ፤ እውቀትን እንዲጨምርልን ፤ አጠቃላይ ሁለንተናችንን እንዲያስተካክልልን አላህን እንለምናለን፡፡

➳አላህ ለእኔም ለእናንተም ጠቃሚ እውቀትን ይስጠን በእውቀታችንም ለራሳችን ተጥቅመንበት ሰዎችንም የምንጠቅም አላህ ያድርገን!

➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው የሚለው ተከታታይ ፅሁፍ በዚህ ተጠናቀቀ! ለወንድማቹህ የምሰጡት ምክር ፣ እዚህ ቻናል ውስጥ ይሄ ይስተካከል ይምትሉት ካለ በዚህ አድራሻ ጠቀሙት

➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
@Nur4843



➧ኑርአህመድ
【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳድ ሰዎች ይሄን አድርጌ ቢሆን ኖሮ እንደዚህ እንደዚህ ይሆን ነበር ይላሉ ይሄ ንግግር እንዴት ይታያል
መልስ
ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ከዚህ ነገር ከልክለዋል
በሚጠቅምህ ነገር ላይ ትጋ አትሳነፍ
የሆነ ነገር ካገኘህ እንደዚህ እንደዚህ አድርጌ ቢሆን ኖር እንደዚህ ይሆን ነበር አትበል ነገር ግን አሏህ ወሰነ የፈለገዉን አደረገ በል
ቢሆን ኖሮ የሚለዉ ቃል የሸይጧን በር ይከፍታል እና
አድሰ -ተከታታይ- ፁሁፍ
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

☞︎︎︎ ክፍል ➨⓵

➲በሴቶች ምክንያት የሚመጣ ሁከትና[ከወንዶች ጋር]የመቀላቀል ጉዳቱ‼️

بسم الله الرحمن الرحيم

➲ “እስልምና ቀጥ ባለውና ምስጉን በሆነው ትምህርቱ የሙስሊም ሴቶችን ክብር ጠብቋል ለልቅናዋና፣ ለእድለኛነቷ ዋስትና ወስዷል ፤ ከተለያዩ ሁከቶችና ፈተናዎች ነጻ
የሚያደርጋትንና ደስተኛ የሆነ ህይዎት ለመጎናጸፍ የሚያግዟትን ሁኔታዎች ሁሉ
አመቻችቷል፡፡

➧ኢስላም ለሰው ልጆች ትክከለኛውን አቅጣጫ የሚያሳይ የእዝነት ሐይማኖት ነው፡፡ አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ከሰዎች ላይ ብልሹነትን ለማስወገድ ጥመታቸውን
ለማቃናት ይህን ውብ የሆነ ሸሪዓ በነብዩ صلى الله عليه وسلم ላይ አውርዷል፡፡ አላህ የደነገገው ሸሪዓ
ጠንካራ የሆነ አካሄድና አስተዳደር ያለው በወንዶችና በሴቶች መካከል በሚከሰተው
መረን የለቀቀ መቀላቀል ሊፈጠሩ የሚችሉ ህገ ወጥ ተግባራትን ከወዲሁ አከርካሪውን ቆርጦ የሚጥል ፤ አጥፊ ከሆኑና ጸያፍ ስነምግባራትን ሰዎች እንዲርቁ የሚያግዝ ክብራቸውን የሚጠብቅና ከዱንያና ከአኼራ ውርደት የሚያድን ነው፡፡
ሙስሊሟ ሴት በኢስላም ታላቅ ስርዓት ከተመራች ፤ አንጸባራቂ በሆነው የሸሪዓ
ብርሃን ከተጓዘች አስደሳችና መረጋጋት የተሞላበት ህይዎትን በቀላሉ ማጣጣም
ትችላለች፡፡

➵“የሙስሊሟ ሴት ምልክት አፍረተ ገላዋን መሸፈንና ያማረ ሒጃቧን መጠበቅ
ነው፡፡ ጅልባቧ ለንጽሕናዋና ለሷሊህነቷ መስካሪ ነው፡፡ ባንዲራዋ ኢስላም ያጎናጸፋትን
ስነምግባር በማህበረሰቡ መካከል ማሰራጨትና በአቋሟ ላይ መጽናቷ ነው፡፡ አላማዋ አላህ ያጎናጸፋትን ልቅናዋንና ክብሯን መጠበቅ ነው፡፡ ሙስሊሟ ሴት ስነ-ምግባሯ ተስተካክሎ ፤ የአላህንና የረሡልን صلى الله عليه وسلم ትእዛዝ ከጠበቀች ለሸሪዓው ብይን እጅ
ከሰጠች ፤ ፈርዶችንና ዋጅባቶች በቋሚነት ተፈጻሚ ካደረገች ፤ የሰዎች ቸልተኛነት ሳያዘናጋት ፤ በመጥፎ ተጣሪዎች ሳትሸወድ ፤ ከአላህ ጋር መገናኘቷን ተስፋ በማድረግ
በአቋሟ ላይ ከጸናች ፤ የተከበረችና ከሁሉም በላይ ከፍ ያለች ትሆናለች፡፡

➲“በዘመናችን ሴቶች በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥሩት የስነምግባር ብልሹነት ፍጻሜው የማይመሰገን የጉዳቱ መጠን የማይታወቅ በመሆኑ ለኡመቱ ከፍተኛ ስጋት እንደሆኑ ነብዩ صلى الله عليه وسلم በሐዲሳቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ ረሡል صلى الله عليه وسلم ለኡመታቸው አስተማሪ
ታማኝ ፣ መካሪ ፣ አዛኝ ሲሆኑ ፤ መልካም ነገር ኑሮ ለኡመታቸው ያልጠቆሙት
መጥፎ ነገር ኑሮ ያላስጠነቀቁት አንድም ነገር የለም፡፡

◾️”روى البخاري ومسلم من حديث أسامة بن زيد رضي الله عنه قال: "ما تركت بعدي فتنة
هي أضر على الرجال من النساء"
➧“ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ኡሳማ ብን ዘይድ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡

➲“ከእኔ በኋላ ለወንዶች ከሴቶች የባሰ እጅግ በጣም ጎጅ የሆነ ነገር አልተኩም”
📚[ቡኻሪ፡5096 ሙስሊም፡2740]
▪️روى مسلم في صحيحه من حديث أبي سعيد الخدري ريض الله عنه أن النبي صلى الله عليه
وسلم قال: "فاتقوا الدنيا والتقوا النساء ، فإن أول فتنة بني إسرائيل كانت في
النساء"
➧ሙስሊም በዘገቡት አቡሰዒድ አልኹድርይ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
➭“ዱንያን ተጠንቀቁ ፤ ሴቶችን ተጠንቀቁ የበኒኢስራኤሎች የመጀመሪያ ፈተና በሴቶች ነበር፡፡” 📚[ሙስሊም፡2742]

➭“ሙስሊሙን ማህበረሰብ በተለይም ሴቶችን ከተለያዩ ትንኮሳዎች ለመጠበቅና
ከሚደርስባቸው ፈተና ለመንከባከብ አቅጣጫ የሚሰጡ በርካታ ሐዲሶች ከነብዩ صلى الله عليه وسلم
ተላልፈዋል፡፡ ሐዲሶቹ አጠቃላይ ህበረተሰቡን ሴቶችን ደግሞ በተለየ ሁኔታ ከውርደት፣ ከተንኮልና ከሁከት የሚጠብቅ መጥፎ ነገሮች እንዳይሰራጭም የሚያግዝ ነው፡፡ ሴት ልጅ የኢስላምን አስተምህሮ ጠብቃ ከያዘች ከአስቀያሚ ባህሪ ጥብቅ የሆነ ጠንካራ
ኢስላማዊ ማህበረሰብ መመስረት ትችላለች በዱንያም በአኼራም እድለኛ ፣ትሆናለች፡፡ ከዚህ አስተምህሮ ካገለለች ደግሞ ከውርደት ሸለቆ ከፈሳድ አረንቋ ፣ውስጥ ተንከባላ ትወድቃለች ከራማዋን ደረጃዋን ግርማ ሞገሷን ታጣለች፡፡

➭“እንሆ እርሷ ትክክለኛውን ጎዳና ከሳተች ለነፍሷም ለቤተሰቦቿም ለቅርብ ዘመዶቿም ውርደትንና ነውርን ጎትታ ታመጣለች፡፡


➧“ቤተሰቦቿ ክብራቸውን አጥተው አንገታቸውን ሰብረው እንዲሄዱ ታደርጋለች፡፡ በዝሙት ብትጸንስ ጽንሱን ታስወርዳለች ፤ በዚህም
በዝሙትና በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ከባድ አደጋ ውስጥ ትወድቃለች ፤ ልጁ ተወልዶ
ወደቤተሰብ ከተቀላቀለ ደግሞ ዝምድና የሌለው አካል (አጅነብይ) በቤተሰቡ ውስጥ በማስገባት በማህበራዊ ህይዎት ውስጥ ተጨማሪ ቀውስ ትፈጥራለች፡፡
ታሪክን ያስተዋለ የሙስሊሞች ስልጣኔ መውረድ፣ የህብረተሰብ መበታተን ፣የስነምግባር ልቅ መሆን የአስተዳደር መበላሸት ፣ የወንጀል መሰራጨት ምክንያቱ ምን እንደሆነ በቀላሉ ይገነዘባል፡፡




ኢንሻ አሏህ ◦◦◦ይቀጥላል!!

ትርጉም፦ በአቡ ዓብዲልዓዚዝ ዩሱፍ አህመድ 📚

〖አንብብብ ❗️ማንበብ ብዙ እውቀት ያስጨብጣል!!〗

➧ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
የማለዳ ቁርስ

የ ኡለሞች መልስ እንዴት አደራችሁ ሲባሉ ⁉️

#ኢብኑል_ሙጚራም «የሙሀመድ አባት ሆይ እንዴት አደርክ?» ሲባሉ

በአላህ ፀጋ ስር ሰምጠን ማመስገኑ ግን ከብዶን አደርን።

ጌታችን ከሁሉ የተብቃቃ (ከማንም ምንም የማይፈልግ) ሆኖ እርሱ ከእኛ ጋር በፀጋው የሚዋደድ ሰሆን ፤ እኛ ግን ከርሱ (ሁሉን ነገረ የምንከጅል) ሆነን ከእርሱ ጋር በወንጀል እንጣላለን』አሉ።
:==================
በአለም ላይ ያላችሁ ውድ ሰለፍይ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንዴት አደራችሁ

እኔ አልሐምዱሊላህ አላህ እንደኔ ደካማነት በምህርቱ አዘኖልኘሰ ከትንሿ ሞት ህያው አድርጎኝ ይሄው እናንተን ለማገኝተ በቃሁ አልሐምዱሊላህ
https://t.me/httpsLatahzen
ሐቅን ፈልጎ መከተል ግድ ነው ከሐቅም ከባጢልም አልሆንም ማለት ሌላ አዲስ መርህ ነው

አላህ ላመኑት ባሮቹ እናንተ ያመናችሁ ሆይ
አላህን ፍሩ ከእውነተኞችም ሁኑ ነው ያለው

የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም - ከኡመቴ ውስጥ በሐቅ ላይ የሚሆኑ ከመኖር አይወገዱም የተቃወማቸውም ሆነ ችላ ያላቸው የማይጎዳቸው ናቸው ይሉናል ።

ሐቅን ፈልጎ መከተል ግድ ነው ከሐቅም ከባጢልም አልሆንም ማለት ሌላ አዲስ መርህ ነው ።

አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉትና ባጢልን አውቀው ከሚርቁት ያድርገን::
=================



https://t.me/httpsLatahzen
የውሸት ሙፍቲነት

የእዩኝ መጨረሻው:
ሸሽጉኝ ሸሽጉኝ ደብቁኝ ማለት ነው:
የሀገራችን ሰዎች ሲሉ እንደሰማነው:
ደግሞ እኮ እውነት ነው:

ምንም ተረት ቢሆን ቢታይም እንደ ቀልድ:
ማእናው ግን ልክ ነው ራሱን ለሚያካብድ:
ያልሆነውን ሆንኩኝ ብሎ ሚዘላብድ:
ምንም ትልቅ ቢሆን ሰውነቱ ቢከብድ:
ማስተዋል ከሌለው ውስጡ ነው እንደ አመድ:

እንደው ላስታውሳችሁ ያን የእስላም እንቁ:
ስሙ የሚባለው ዑመር አል~ፋሩቁ:
ይፈራ ነበረ ፈትዋን መጠየቁ:
የስም መመሳሰል አያስብልም እንቁ:

ሙፍቲነት ያስፈራል ጀግናው እውነት ብሏል:
ያላወቁት ዘንዳ ከትንኝ ይቀላል:
በዘመናችን ግን ራሱን ይሰይማል:
ሙፍቲ እገሌ ተብሎ በሚድያ ይወራል:
እሱም ይህንኑ ወዶ ተቀብሏል:

ነበሩ ሰለፎች የምርጦቹ ምርጦች:
ለአላህ ደባቂዎች ራስን አቅላዩች:
ጀነት ናፋቂዎች አንቱታን ፈሪዎች:
ታሪክ ላስታውሳችሁ የእነዚያን የምርጦች:

አንድ አሊም ነበሩ ኪታብ የዓለፉ:
ነጠላም አይደለ ሁሉም በየ ዘርፉ:
ተፍሲር ነሽ አቂዳ ነህው ብትል ሶርፉ:
ሰው አያውቅም ነበር ከዱንያ እስኪያልፉ:

ወዳጅ ነበራቸው ሞቱ ሲቀርባቸው:
በፍጥነት አስጠሩ ይህን ወዳጃቸው:
እንዲም ተናዘዙ ስለ ኪታባቸው:
ኪታቦች ፅፌያለሁ ሰው የማያውቃቸው:
አደራ ልበልህ ልሞት ቀርቢያለው:
ሰውየውም አለ እሺ እቀበላለው:

ቀጠል አረጉና እንዲህ ብለው አሉት:
እጄን ትይዛለህ ስቃረብ ወደ ሞት:
እጅህንም ይዤ እንደው ከጠፈርኳት:
አደራ! አደራ! ኪታቧን ደብቃት:
በዚህ ተቃራኒ እጄን ካላላሁዋት:
ያኔ ፈቅጃለሁ ለአንባቢያን አውጣት:
ለምን መሰላችሁ ሸሁ እንደዚ ያሉት?
የሪያእን viruse ከልብ ፈርተዋት:

ማስታወስ ይበጃል መንቀልቀል ይጥላል:
ኢኽላስ ማስተካከል ከሁሉ ይቀድማል:
ኢኽላስ በባህሪው እዩኝን ይጠላል:
የዘመኑ ሙፍቲ ይህን ተግብረሀል
ኑርአህመድ



https://t.me/httpsLatahzen
\\ወደድኳቹ//

ይድረስ ለሀቅ ባለቤቶች
ይድረስ ለሀቅ ተሟጋቾች
" " "አስተማሪዎች
~~~~~
````````````

ወደድኳቹ _እጅግ
ተደሰትኩባችሁ
በአላህ መንገድ_ስለተሟገታችሁ
የያዛችሁት መንገድ_ስለወገናችሁ
ከቢደዓ ባለቤት_ስላስጠነቀቃችሁ
እጅግ በጣም_ወደድኳችሁ
••••••••••••••••••••••••••••••••
ስሙኝማ ኡስታዞቼ _አብሽሩ ለነጌ
ሰብሩ ትካሳላችሀ _በአኼራ ነጌ
የእውነት_ትግላችሁ ለዲን ከሆነ
አካሄዳችሁ_ ዲንን ለመርዳት ከሆነ
አትበገሩ _ለባጢል ባለቤቶች
ሁኑ _የሀቅ የእውነት ባለቤቶች
!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
ኑርአህመድ👇👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
📍የተውበት ኡኡታ📍

እኔስ ዋይ ጥፋቴ:
አቤት ሞኝነቴ:
ላጠፋ ደረስኩኝ የ²ሀገር ቤቴ:
አስቤ አልሜ የአፍታ ስሜቴ:
አላህን ረስቼ እንዲው መዋተቴ:
በሀራሙ ደስታ እራሴን መሳቴ:

ኧረ ምን ይዋጠኝ እንደው ምን ውስጥ ልግባ:
እተዋለሁ ብዬ ቃል እንኳን ብገባ:
ነገ እረሳዋለሁ በስሜት ስገባ:
ለነፍሴ ፈራሁኝ እሳት እንዳልገባ:

ብሄድ በዚ ሁኔታ ምን ይለኛል ጌታ:
እኔስ አፍሪያለሁ መቅረብ እዛ ቦታ:
ምን ማረግ ቢያቅተኝ ሀሳቤም ቢምታታ:
አንድ ሀሳብ አለኝ ማይነፈግ ቦታ:
መመለስ ወደሱ ወደ አንዱ ጌታ:
አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው: በአንድምታ:
ጌታዬዋ ስማኝ የተውበት ኡኡታ:

አማራጭ የላቸው ተሳሳቾች ሁላ:
ወንጀላቸው በዝቶ ምን ባህር ቢሞላ:
ከተውበቱ ውጪ አንድም የለው መላ:
ላይመለስበት ቃል ገብቶ መሀላ።
▼▼▼▼▼▼▼▼▼▼
☞ ኑርአህመድ☜
https://t.me/httpsLatahzen
ተዉ አንዘናጋ

ልክ እንደምናየው ተስፋፍቶ በሀገሩ:
በቀን መቶ መቶ ከዚያም መጨመሩ:
ኬዝ ያልተገኘበት ታማሚ መኑሩ:
ይህ ይጠቁመናል በሽታው ለመብረሩ:


“ታሞ ከመሟቀቅ” ልክ እንደሚባለው:
ቀድሞ መጠንቀቅ ነው ለሁሉ ሚበጀው:
ይሄን ምናደርገው ለሰበብ ሲባል ነው:
ለኛ ያለው እንደው መሆኑ ማይቀር ነው:


እና እላችሇለሁ ርቀትን ጠብቁ:
የአፍ መሸፈኛ በአግባቡ ታጠቁ:
በቤታቹም እርጉ እዚያው ተጠንቀቁ:
አቅልለን አንየው ከባድ ነው እወቁ!
https://t.me/httpsLatahzen
ረመዳን ለነማን
Sadat
ረመዳን ለነማን?
በኡስታዝ ሳዳት ከማል አቡ ኑህ ሀፊዘሁላህ
ረመዳን ታላቁ ወር
Sadat
ረመዳን ታላቁ ወር
ረመዳንን እንዴት እናሳልፍ
Sadat
ረመዳንን እንዴት እናሳልፍ?
#አሁንስናፈቀኝ_!!
-----------------------------
የገጠሩ ህዝቤ ተውሒድን ተረድቶ፡
ሽርክ ቢድዐውን በጥቅሉ ከድቶ፡
ከጎበደን ካድባር ከዚያ ከድሪቶ፡
ከጥመት አረንቋ ከጨለማ ወጥቶ፡
--------------------///---------------
የሰው ዋጋ ወርዶ ኑሮ ሳይወደድ፡
ካገሩ እየወጣ ዑማው ሳይሰደድ፡
በዘር በሀይማኖት ማንም ሳይታረድ፡
ለውጭ ባለሀብት ማንም ሳይሆን ገረድ፡
--------------------------------------------
የግፍ በደል ግንዱ ከስሩ ተነቅሎ፡
የፍትህ ባንዲራ ከፍ ብሎ ተሰቅሎ፡
ሀገሩን የሚሸጥ ለሆዱ የሚያድር፡
ጠላት ባንዳ ጠፍቶ ከሀበሻ ምድር፡
------------------------------------------
ከተራ መግለጫ ፖለቲካው አልፎ፡
ወዳጅ ተደስቶ ጠላት ተጠላልፎ፡
ያጠላብን ሀዘን ፅልመቱ ተገፎ ፡
በረካው ከአሏህ ከላይ ተዘርግፎ፡
መከራ ችግሩ ከምድር ተግፎ፡
---------------------------------------
ገደለው ሰቀለው ቆረጠው ፈለጠው፡
አንደዜ ተያዘ አንደዜ አመለጠው፡
ከሚል ሽብር ወሬ ጆሯችን እርቆ፡
ትንሹም ትልቁም ያላሳብ ቦርቆ፡
~
ሀዘን ዋይታ እሪታ ሳይሰማ መርዶ፡
የበደል የግፉ የጭቆናው ግርዶ፡
ማንም ሳይሰቃይ ከቀየው ተሰዶ፡
ሁሉም በአንድነት ለአሏህ ብቻ ሰግዶ፡
ዋይታና ጫጫታው ካገር ተወግዶ፡
~
የሚስኪን ደም እንባ ከንቱ ሳይፋሰስ
ሁሉም ተመችቶት በቤቱ ሲል ፈርሰስ፡
መች ነው የምኖረው ናፈቀኝ አሁንስ፡
እድገታችን አድጎ ህዝባችን ሳይቀንስ፡
ይህ ጊዜ መቼ ነው ወላሒ ጨነቀኝ፡
እፎይ ያለ ህይወት አሁንስ ናፈቀኝ፡
~
#በኑር
🎋🌿🎋🌿🎋🌿🎋🌿🎋🌿🎋🌿🎋🌿🎋

🌷 የጀነቷ እንስት ሑረል = ዐይን 🌹
🌺🌸ሁረል አይን🌺🌸

~ ክፍል አንድ

~ ዓይናማዎች የኾኑ ነጫጭ ቆንጆዎችም አሏቸው፡፡

~ ልክ እንደተሸፈነ ሉል መሰሎች የኾኑ፡፡

~በዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት ዋጋ ይኾን ዘንድ (ይህንን አደረግንላቸው)፡፡
አል-ዋቂዓህ - 22 = 24

ሑረል ዐይኗን ፈላጊ ሆይ!
================

በኢራቅ ሀገር ውስጥ አላህን አብዝቶ በመገዛቱ ይታወቃል። በእስልምና አስተምህሮት የታነፀ ፣ ኢማን ወደ ልቡ የገባ ድሃ ወጣት ነበር። የእርሱን አይነት ባህሪና ጥንካሬን ሁሉም ይመኛል። አንድ ቀን ከጓደኛው አቡ ሱለይማን ዳረኒ ጋር ወደ መካ ጉዞን ሊያደርጉ ወስነው የሚያደርሳቸውን ቅፍለት መምጣት ይጠባበቁ ይዘዋል። ቀፍላው ደረሰና ጉዞአቸውን ወደ መካ ጀመሩ።

በጉዞአቸው መሃል ላይ የኢራቁ ወጣት የሚያሳያቸው ዒባዳ አስደንቋቸዋል። እነርሱ ሲበሉ እርሱ ይፆማል። ሲተኙ ለሊቱን ወደ ጌታው በመዞር ቂያመ ለይል ያነጋል። ሁኔታው ቢያስገርማቸውም ቀርቦ ምክንያቱን ለመጠየቅ ግን ማንም አልደፈረም። መካ ደርሰው ጉዳያቸውን ፈፅመው በመመለስ ላይ ሳሉ ጓደኛው አቡ ሱለይማን ከጓደኞቹ እርሱን ነጠል አድርጎ ‹ወንድሜ ሆይ! ለዚህ ሁሉ ዒባዳ ያነሳሳህን ነገር ንገረኝ? ለማወቅ ጓጉቻለሁ› በማለት ጠየቀው። እሱም እንዲህ ሲል መለሰ…

‹አንድ ቀን ተኝቼ በህልሜ ከወርቅና ብር የተገነቡ በሉልና በአልማዝ ያሸበረቁ ህንፃዎችን ተመለከትኩ። ከበሩ ደጃፍም ላይ ዓይኗን የነፃ ፀጉሯን የለቀቀች ውብ እንስት ቆማ አየሁ። የለበሰቺው ቀሚስ ከሀር የተሰራና አዝራሩም በወርቅ የተለበጠና ያማረ ልብስ ነበር። እሷን በተመስጦ በመመልከት ላይ ሳለሁ ደስ የሚል ቀልብን የሚማርክ አንደበቷ «እኔን ለማግኘት ከፈለግክ በዒባዳህ ላይ ፅና። በአላህ እምላለሁ እኔ አንተን ለማግኘት በዱኣ እየለፋሁና እየለፋሁና እገኛለሁ። የእኔ መህር የለይል ሶላትና ፆም ነው› አለችኝ አስከተለና ወንድሜ ሆይ! በዚህ በምታየው ዒባዳ እሷን ለማግኘት በመጣጣር ላይ ነኝ።

አቡ ሰለይማን ይህንን ታሪክ ሰምቶ ካበቃ በኋላ «ይህ ሁሉ ትግል ሑረል ዐይን ለማግኘት ከሆነ ከሑረል ዐይን በላይ የሆነው ጀነት ለማግኘት የሚፈልግ ምን ያህል ይለፋ ይሆን? በማለት ተናገረ።

ውቧን ሑረል አይንን ለማግኘት የሚጓጉትን ሰዎች በተስፋ መርከብ ላይ ጭነን ያማረ ጉዞ ማድረግ ጀምረናል።

ኑ ተከተሉን… መንገዳችንን እንቀጥል…
የጀነቱ = አቀባበል…

የአረህማን እንግዶች ከመቃብራቸው ያለምንም ድንጋጤ ተነስተው ቆመዋል።


ታላቁ ድንጋጤ አያስተክዛቸውም፡፡ መላእክትም ይህ ያ ትቀጠሩ የነበራችሁት ቀናችሁ ነው፤ እያሉ ይቀበሏቸዋል፡፡
[ ሱረቱ አል-አንቢያ - 103 ]

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል…

‹ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዮ እምላለሁ! ከመቃብራቸው ሲነሱ የወርቅ ግላስን የለበሱ ክንፍ ያላቸው ነጫጭ በቅሎዎች ፊት ለፊታቸው ይቀርብላቸዋል… የጫማቸው ክር ብርሃን ያብለጨልጫል።

እነዚያ አላህን የሚፈሩ ባሮች በቡድን በቡድን ሆነው ወደ ጀነት በመጓዝ ላይ ናቸው።

አላህም እንዲህ ይላል…

وَسِيقَ الَّذِينَ اتَّقَوْا رَبَّهُمْ إِلَى الْجَنَّةِ زُمَرًا

እነዚያም ጌታቸውን የፈሩት የተከፋፈሉ ጭፍሮች ኾነው ወደ ገነት ይንነዳሉ፡፡
[ አል-ዙመር - 73 ]

የጀነቱ በር በመከፈት በመጠባበቅ ላይ ናቸው በዙሪያው ተሰብስበው ቆመዋል ማንም ያላየውን ከአእምሮ እሳቤ በላይ የሆነውን ውድ ቤታቸውን በግል ቁጥጥራቸው ውስጥ ለማስገባት በጣም ጓጉተዋል። የጀነቱ ጠባቂ መላኢካ በእንግዶቹ መምጣት ፊቱ በደስታ ፈክቶ ይታያል። በእጁም የበሩን ቁልፍ ይዞል። በሩ ተከፈተ የአረህማን ባሮች ወደተዘጋጀላቸው መስተንግዶ በማቅናት ላይ ናቸው። ከመላኢካዎች በሚሰነዘርላቸው ሰላምታ እየታጀቡ ወደ ውስጥ ገቡ።

ዘበኞችዋም ለእነርሱ «ሰላም በናንተ ላይ ይኹን፡፡ ተዋባችሁ፡፡ ዘውታሪዎች ኾናችሁ ግቧት» በሏቸው ጊዜ (ይገቧታል)፡፡
[ አል-ዙመር - 73 ]

ወደ ደስታዋ ሀገር ጀነት በሃሳብችን ገብተን በቀልባችን እንመልከታት አላህ ፈቅዶ በአካላችን እስክገባት ጀምሮ

እግራቸው ከሚስክና ከዘዕፈራን የተሰራውን መሬትም እንደረገጠ ፊታቸው በእንባ ተሞልቶ ምስጋናን ማቅረብ ጀምረዋል።

«ምስጋና ለአላህ ለዚያ ተስፋ ቃሉን ለሞላልን፡፡ የገነትን ምድር በምንሻው ስፍራ የምንሰፍር ስንኾን ላወረሰን ይገባው» ይላሉም፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ ምን ያምር!
[ አል-ዙመር - 74 ]

ሙእሚኖች ልባቸው የጓጓለት ዘወትር የሚናፍቁት ሀገራቸው ጀነትን ፤ በውስጧ ከተዘጋጀላቸው ፀጋዎች ውስጥ አንዷ የሆነችውን ሑረል ዓይንን ለማግኘት ቀልባቸው ተንጠልጥሎል።

የጀነት እንግዶች ወደ ውስጥ በመራመድ ላይ ናቸው። ከበስተግራ በኩል ከወተት የነፁ ጅረቶች ይፈሳሉ። ከበስተቀኝ በኩል ከወርቅና ብር የተሰሩ ህንፃዎች ይታያሉ። ፊት ለፊት ለፏፏቴ አለ። በፏፏቴው ዙሪያ ውቧ እንስት ሑረል ዐይን ቆማለች። የባሏን በመምጣት በጉጉት ትጠባበቃለች ። በጣፋጭና ልብን በሚሰልብ ድምጿን ታዜማለች። እንደማር በሚጣፍጥ አንደበቷ እንዲህ እያለች ትዘምራለች።

የዱኒያ ድሎት የማይወዳደረው
ጀነት ምነኛ ያማረ ትልቅ ፀጋ ነው

ዓይኗ በጣም በናፈቀችው ውድ ባሏ አረፈ በሩጫም ወደርሱ አመራች

‹አንተን በመጠበቅ ረጅም ዘመናትን አሳለፍኩ። ሁሌም ወዳድ ፤ የማልጠላ ፣ ዘውታሪ የማልሞት በቤት ውስጥ የረጋሁ አንተን ጥዮ የማልሄድ ፣ ፍቅሬ ውዴ ናልኝ ናፍቀኸኛል› በማለት ተጠመጠመችበት ተቃቅፈው ጉዟቸውን ሽቅብ ቀጠሉ።

በል ና ተከተል ወንድሜ… ጡቶቿ እንደ ፓም ፍሬ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙትን የጀነቷን እንስት ሑረል አይንን እንግለፃት።

ቀልብህን ከፍተህ በጆሮህ ስማኝ…
በዓረበኛ ቋንቋ حور ሑር የሚለው ቃል የአይኗን ብርሃን በጣም አንፀባራቂ ጥቁረቱ ደማቅ ከወተት በላይ ነጭ ቆንጆ ማለት ሲሆን عين አይን ማለት ደግሞ ዓይኗን ማለት ደግሞ ዓይኗ ጎላ ብሎ የሚታይ ውብ ሴት ማለት ነው።
.
.
ይቀጥላል…




https://t.me/httpsLatahzen
ምክር ለሱና ወንድሞቼ

የሱና ወንድሞቼና እህቶቼ አንድ ነገር ላስታውሳችሁ እወዳለሁ እሱም በየጉሩፑ የምትወያዩ ወንድሞችና እህቶችን የሚመለከት ነው።

ብዙ ጊዜ ከሱና ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር ስንወያይ አላማችንን እና ማድረግ ያለብንን ማወቅ ያስፈልጋል።
ይህም ሲባል ከነሱ ጋር ቀርበን ስንወያይ አላማችን ሊሆን የሚገባው የእነሱን አካሄድ መንቀፍ፣መዝለፍ፣ ማዋረድ አስበን ሳይሆን ሀቅን ማስረዳት ብቻና ብቻ ነው መሆን ያለበት አሁን ላይ እያየን ያለነው ግን ከዚ በተቃራኒ ነው።

ከዚያም ባለፈ ደግሞ እኔ እነሱ ለሚጠይቁኝ ጥያቄ ተገቢውን መልስ መመለስ እችላለሁኝ ተናግሬስ እነሱን ማሳመን እችላለሁ ወይ የሚለውን ጥያቄ ራሳችንን ልንጠይቅ ይገባል ይህ ሳይሆን ግን በደመ ነፍስ ምንከራከር ከሆነ
የሱና ሰዎችን ነው የምናሰድበው
አልፈን እኛ የምንሳደብ ከሆነ ደግሞ የባሰ ነው የሚሆነው ስለዚህ እነዚህን ነጥቦች አስተውለን ልንወያይ ይገባል አላለሁ።

ولله تعلا اعلم
🖌nur
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የማለዳ የቁርአን ግብዣ👇

وَهِيَ تَجْرِي بِهِمْ فِي مَوْجٍ كَالْجِبَالِ وَنَادَىٰ نُوحٌ ابْنَهُ وَكَانَ فِي مَعْزِلٍ يَا بُنَيَّ ارْكَب مَّعَنَا وَلَا تَكُن مَّعَ الْكَافِرِينَ

እርሷም እንደ ተራራዎች በሆነ ማዕበል ውስጥ በእነርሱ (ይዛቸው) የምትንሻለል ስትሆን (በአላህ ስም ተቀመጡባት)፡፡ ኑሕም ልጁን ከመርከቢቱ የራቀ ሆኖ ሳለ «ልጄ ሆይ! ከኛ ጋር ተሳፈር ከከሓዲዎቹም አትሁን» ሲል ጠራው፡፡

قَالَ سَآوِي إِلَىٰ جَبَلٍ يَعْصِمُنِي مِنَ الْمَاءِ ۚ قَالَ لَا عَاصِمَ الْيَوْمَ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ إِلَّا مَن رَّحِمَ ۚ وَحَالَ بَيْنَهُمَا الْمَوْجُ فَكَانَ مِنَ الْمُغْرَقِينَ

(ልጁም) «ከውሃው ወደሚጠብቀኝ ተራራ እጠጋለሁ» አለ፡፡ (አባቱም)፡- «ዛሬ ከአላህ ትዕዛዝ ምንም ጠባቂ የለም (እርሱ) ያዘነለት ካልሆነ በቀር» አለው፡፡ ማዕበሉም በመካከላቸው ጋረደ፡፡ ከሰጣሚዎቹም ሆነ፡፡

11:42-42
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉መቀናት (መመራት) በአላህ ነውና እርሱ ቀጥተኛውን መንገድ ይምራን በእርሱም ላይ ያፅናን።
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
💻መልካም ውሎ💻

https://t.me/httpsLatahzen