La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
♣️ለካ እኔ እኔ ነኝ♣️

በምድር ብዘልም:
በጉራ ብሞላም:
ሰውን ባንቋሽሽም:
ጅምሬን ብረሳም:
ራሴን ሰቅዬ መውረጃ ባሳጣም:

ሀቁ አይሻርም:
ከምድር አይዘንብም:
ከሰማይ አይበቅልም:

ጅምሬኮ ያ ነው የማይታሰበው:
ይሆናል ማይባል የማይገመተው:
ንፍጥ ከሚመስል ፈሳሽም ከሆነው:

ይህ ነው ጅምራችን:
ለምን መኩራታችን:
ሰውን መናቃችን:
ደግሞም መርሳታችን:
ያንን መነሻችን።

https://t.me/httpsLatahzen
#ሰው_በሳት_ነደደ__!!
------------------------------------
አስገራሚ ነገር ዘግናኝ ግፍ ጭካኔ፡
ከየት የመጣ ነው ንገረኝ ወገኔ፡
መች ነው የታደልከው እንድህ አይነት ወኔ፡
የሰው ልጅ አርቃኑን በእሳት ሲቃጠል፡
አጥንቱ ሲጠበስ ስጋው ሲንጠለጠል፡
እሳት እፍ እያሉ ሰብስበው ማገዶ፡
በሙቀት መቀቀል ሰውን አስገድዶ፡
እንደ በቆሎ እሸት አገላብጦ መጥበስ፡
መጥፎ ብቻ አስቦ መልካሞችን ማበስ፡
የእውነትን ንግግር በመጥፎ መቀልበስ፡
ከነማን ወረስከው ይህንን ማድበስበስ፡
አንተው አስለቅሰህ የአልቃሽ እንባ ማበስ፡
----------------------------------------
ህዝቤ ፍትህ ጠልቶ ሌባ እያወደሰ፡
መጥፎ ሰሪው ሁሉ እየተቀደሰ፡
በሀበሻ ምድር ተንሰራፋ በደል፡
ሰው የፊጥኝ ታስሮ ተለቀቀ ገደል፡
የምናየው ሁሉ ይህንን እማይደል!?
የሀገሪቷን ታሪክ እየገነደሰ፡
እውነት አፈር ለብሶ ውሸት ከታደሰ፡
በጧትም በማታ ደሟ ከፈሰሰ፡
መሪ የተባለው ይህን ካልዳሰሰ፡
--------------------------------------
እኩል አርጎ ፈጥሮ አሏህ በአክብሮት፡
ቁመቱን ውበቱን አሳምሮ ፈጥሮት፡
ሰይጣናዊ መንገድ ሰውን ግን አስክሮት፡
ፍትህ እኩልነት ከሬት በላይ መሮት፡
ሽርክና ቢዲአ ውስጡን ተብትቦ አስሮት፡
ነብስያ ኩራት ጋር አካሉን ወጥሮት፡
ኸይረኛ እየራቀ ሸረኛው አፍቅሮት፡
-----------//--------------------------
በአሏህ የፍትህ ፍርድ መዳኘት ተስኖት፡
እንጨቱን ጠራርቦ ጌታ ነው ብሎ አምኖት፡
ከተንኮሉ ሸይጧን ዘርግቶ አዘግኖት፡
እየተከተለ የኢብሊስን ፍኖት፡
አለ ዛሬም ድረስ ግፍ እየፈረደ፡
የራሱን መሳይ ሰው ጨክኖ እያረደ፡
እንጨት ቁጭ ብሎ ሰው እየነደደ፡
በጨለማ ጉዞ ቦይ እየቀደደ፡
ህግ አዋቂ ቆሞ ሌባ እየፈረደ፡
ሀሱት ስልጣን ሲይዝ ሀቅ እየወረደ፡
ለአሳ መረብ ጥሎ ሰው እያጠመደ፡
አንበሳ በጅቦች እየተሳደደ፡
ዝሆን እያስገባ ለአይጥ የተቀደደ፡
ሰላም ማህፀኗ ቂም እየፀነሰ፡
ብልፅግና እያሉ እድገቷ ቀነሰ፡
ሰው ሰላም ዘርቶ እሳት እያፈሰ፡
ከወዳ ከወድህ ወሬ እያናፈሰ፡
ይሄ ግፍ ሲሰራ መላ ጠፍቶን እኛ፡
ምነው ብታዝንልን የአለሙ ዳኛ፡
ካንተ ውጭ ሌላ የለንም መዳኛ፡
---------------------------------------
ሁል ጊዜ በተረት እየተቀለደ፡
ፀሀይዋ ጠለቀች ጨረቃው ለገደ፡
ሀበሻዬ ዘነች ህዝቧ ተሰደደ፡
ሀገሬን እያለ ሰው በእሳት ተነደደ፡
----------------------------------------
እሳትን የፈጠረ ቢሆን እንጅ በእሳት የሚቀጣ የለም።
-----------------------------------
በኑር
---------------



https://t.me/httpsLatahzen
ክብርሽን ጠብቂ

እህቴ፣

ያንጋጠጠ ያንጋጥ አብዝቶ ይጣራ
ገንዘብ ቢያፈስልሽ ለዝሙቱ ሴራ

ደግ አይለኝም በይው አማኝ ማንነቴ
መልከስከስ አልወድም ኢስላም ነው እምነቴ
የዓኢሻ ልጅ ነኝ እሷም ተምሳሌቴ
አይረክስም አካሌ ክቡር ሰውነቴ
ዞር በልልኝ ከኔ ጥፋልኝ ከፊቴ



https://t.me/httpsLatahzen
ጊዜህ አይገዝግዝህ

ወንድሜዋ ንቃ:
ልክ እንደ ጥበቃ:
እድሜህ ሳታበቃ:
ስንፈቱ አያጥቃ:

ጊዜ እኮ ወርቅ ነው:
ልክ እንደሚባለው:
በኛው በሀበሻ እንደሚተረተው:
ግን ምን ዋጋ አለው:
ተጠቃሚ የለው:
አላህ ካላደለው:
የሚጠቀምበት አቅለኛ ብቻ ነው:
ኢማሙ ሻፊእይ አሉ እንደሚባለው:
ጊዜ እንደ ሰይፍ ነው:
ሳይቆርጥህ ቁረጠው።

ይህን ትርፍ ጊዜ:
አታጥፋው በአባዜ:
አትሁን ፈዛዜ:
ሓላ አታገኘውም አልፎ ይሄ ግዜ:

ከልብህ አድምጠኝ:
በጊዜህ አትሞኝ:
ካለፈህ አታገኝ:

ደግሞ አትሰላች ደካማ አትሁን:
እሩቅ ህልምን አልም ማያስተኛህ ዛሬን።

ኑር አህመድ


https://t.me/httpsLatahzen
ፍ–ር–ጥ ነው እንጂ!!


የምን መደባበቅ የምን ማለባበስ:
በአይንህ እያየህ ቀብር አፈር የሚልስ:


ከጠቋንቋዩ ቤት በር ሌሊት ሚልከሰከስ:
ሲጨንቀው ሲጠበው ሸሁን ሚያስተውስ:


አይንህም ብሌኑ አይቶ ያን ትርምስ:
ቆይ እንዴት ያስችላል ይህን ማለባበስ?!


ባክህ አቶ ዳዒ ይሻላል ፍርጥርጥ:
የሰውን ውዴታ ትቶ ከመቋመጥ።


https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from Abul Abas Nasir Muhammed
📣ታላቅ የዳዕዋ ድግስ በ مركز أبي موسى الأشعري

♻️♻️

ወድ እና የተከበራቹህ ወንድሞች እና እህቶች በአላህ ፈቃድ ነገ ጁሙዓ ማታ 3:00 ሰአት ላይ በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ ፕሮግራም ተጋብዛቹሀል ።

ተጋባዥ ዱዓቶች

1, ኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁላህ
የዳዕዋው ርእስ - السنة - አስ-ሱናህ

2, ኡስታዝ ኸድር አህመድ ሀፊዘሁላህ
የዳዕዋው ርእስ - الحسد- ምቀኝነት

3, ኡስታዝ አቡ ረይስ ሀፊዘሁላህ
ርእስ - استقبال شهر رمضان -የረመዳን አቀባበል

ዳዕዋው የሚተላለፍበት የመርከዙ አድራሻ ሊንክ
👇👇👇
https://t.me/kurantejwid
https://t.me/kurantejwid
https://t.me/kurantejwid
አንዱ ሊያገባት
Sadat
👆የገባት አንድ ሰው የሚየያት አንድ ሺ ሰው።

-በኡስታዝ ሳደት ከማል ሀፊዛሁሏህ»

https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
La tehzen
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➻ ክፍል አስራ ሶስት ➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧አንድ ሰው የመልካም ባህሪያት ሁሉ ከእርሱ ላይ ካልተሰባሰቡ ከኢማምነት ደረጃዎች ሊደርስ አይችልም፡፡ በመልካም ባህሪያቶች ለሰዎች አርአያ ሊሆን ይገባል፡፡ ➛የእውቀት አይነቶችን እየሰበሰበ ነገር ግን የተግባር ሰው ካልሆነ ይህ ሰው እርሱ እንዳልተጠቀመ ሁሉ በእውቀቱ ሌሎች…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➛ክፍል አስራ አራት


➲ዘጠነኛው፡- በእውቀቱ ለመስራት አላህን መማጸን ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ዱኣ ያዘወትሩ ነበር” ትላለች ኡመ ሰለማ ረዲየሏህ አንሃ

▪️"اللهم إني أسألك علما نافعا، ورزقا طيبا، وعمال متقبال"

“አላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን ፤ ተቀባይነት ያለውን ስራ እጠይቅሃለሁ፡፡” አህመድ፡(26521) ኢብኑ ማጀህ፡( 925) ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ ኢብኑ ማጀህ፡(762)

➲ይህን የተባረከ ዱዓ በቀኑ መጀመሪያ ላይ ማድረጉ ተስማሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ቀን የስራዎች ሜዳ በመሆኑ ነው። የሙስሊም አላማና ግቡ ደግሞ እነዚህ ሶስት ነገሮች ናቸው ፤ ሌላ አራተኛ የለም፡፡ ጠቃሚ እውቀት ፣ ተቀባይነተ ያለው ስራ ፣ መልካም የሆነ ሲሳይ ናቸው፡፡

➧ስለዚህ ፈጅርን ከሰገድክ በኋላ ይህን ዱዓ ማድረግህ በጣም የተስማማ ነው፡፡ በአላህ ታግዘሃል ፤ እውቀትን በመፈለግ ተማጽነሀል ፤ ለስራህ አላህ እንዲያግዝህ ለምነሀል ፤ ሲሳይን ለማግኘት ከአላህ እገዛን ጠይቀሃል፡፡ በቃ ከዚያም የቀን ስራህን በሰላም ትጀምራለህ ማለት ነው፡፡

➲አስረኛው፡- እውቀትን ወደስራ ያልቀየረ የተወገዘ ነው በስራ ላይ ያልተጠመደን ፣ ለስራ ትኩረት ያልሰጠን አካል ሰለፎች ያነወሩበት በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡ ከዚህ መካከል የሚከተለው የአቡሁረይራ ረዲየሏህ አንሁ ንግግር ነው፡-

▪️"مثل علم لا يعمل به كمثل كنز لا ينفق منه في سبيل الله"

➧“በእርሱ የማይሰሩበት እውቀት በአላህ መንገድ ወጭ እንደማይደረግ ድልብ ሐብት አምሳያ ነው፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡ (12) አልባኒ ሰነዱን መውቁፍ ነው ምንም አይልም በለውታል

➧ሀዲስን በብዛት ስለሚጽፍ ሰው ኢማም አህመድ -ረሂመሁሏህ- ተጠየቁ፡፡ከዚያም
የሚከተለውን መለሱ፡-

▪️"ينبغي أن يكثر العمل به على قدر زيادته في الطلب"

➧“እውቀትን በሚፈልግበት መጠን በእርሱ መሰራትን ሊያበዛ ይገባል፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡(12 )ከዚያም አያይዘው የሚከተለውን ተናገሩ፡-

▪️"سبل العلم مثل سبل المال، إن المال إذا ازداد ازدادت زكاته"

“የእውቀት መንገዶች ልክ የገንዘብ መንገዶችን አምሳያ ናቸው፡፡ ገንዘብ በጨመረ ቁጥር ዘካው እየጨመረ ይሄዳል፡፡”

➲ኸጢብ አልበግዳድይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

“ያለወጭ ገንዘብ እንደማይጠቅመው ሁሉ በእርሱ ለሰራበት፣ ዋጅቦችን ተጠባብቆ ለፈጸመ እንጅ እውቀትም እንዲሁ አይጠቅምም፡፡ አንድ ግለሰብ ነፍሱን ይመልከት ፤ወቅቱን ይጠቀምበት ፤ … ጉዞው ቅርብ ነው ፤ መንገዱ አስፈሪ ነው ፤ መታለሉ ብዙ ነው ፤ አደጋው ትልቅ ነው ፤… አላህ በመጠባበቂያ (ቦታ) ላይ ነው ፤ መመለሻው ወደርሱ ነው፡፡ አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡(12)

➤አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ ⓻وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ⓼

➧“የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል፡፡ የብናኝ ክብደት
ያክልም ክፉን የሰራ ሰው ያገኘዋል፡፡” ዘልዘላህ፡(7_8)

▪️ሀሰን አልበስርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"أنزل القرآن ليعمل به، فاتخذ الناس تالوته عمال"
“ቁርኣንን ያወረደው በእርሱ ሊሰሩበት ነው፡፡ ሰዎች ግን ማንበቡን ስራ አድርገው
ይዘውታል፡፡” ይህን ንግግር ብን አልጀውዝ “ተብሊስ ወኢብሊስ” በሚባለው ኪታብ ከዘገበ በኋላ የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

▪️"أنهم اقتصروا على التالوة، وتركوا العمل به"
➲"እነርሱ በንባቡ ብቻ ተገደቡ በእርሱ መስራትን ተው” ተብሊስ ወኢብሊስ፡ ገፅ(137)

➧ለኢብራሂም ብን አድሀም -ረሂመሁሏህ- አንድ ሰው የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበላቸው፡- “አላህ በቁርኣኑ “እኔን ለምኑኝ እቀበላችኋለሁ” ጋፊር፡ (60) በማለት ተናግሮ ሲያበቃ እኛ ዱዓ እያደረግን ለምንድን ነው ዱዓችን ተቀባይነትን ያጣው?” በማለት
ጠየቃቸው፡፡

➲ኢብራሂም ለዚህ ሰው የሚከተለውን መልስ ሰጡት፡-“ዱዓችን ተቀባይነት ያጣው በአምስት ምክንያቶች ነው” በማለት መልስ ሰጡት፡፡እርሱም “ምንድን ናቸው?!” በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም “አላህን አውቃችሁ
የእርሱን ሐቅ አለመወጣታችሁ፡፡ ቁርኣንን አንብባችሁ በእርሱ አለመስራታችሁ፡፡ረሡልን صلى الله عليه وسلم እንወዳለን ብላችሁ ሱናቸውን በመተዋችሁ፤ ኢብሊስን እንራገማለን ትላላችሁ ነገር ግን እርሱን ትታዘዛላችሁ ፤ አምስተኛ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ የሰው ነውር ትከታተላላችሁ፡፡” ጃሚዑ በያኒ አል ዒልም፡(1220)



➧ኢንሻአላህ ክፍል አስራ አምስት ይቀጥላል◉◉◉

➧ኑርአህመድ
【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➛ክፍል አስራ አራት ➲ዘጠነኛው፡- በእውቀቱ ለመስራት አላህን መማጸን ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ዱኣ ያዘወትሩ ነበር” ትላለች ኡመ ሰለማ ረዲየሏህ አንሃ ▪️"اللهم إني أسألك علما نافعا، ورزقا طيبا، وعمال متقبال" “አላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን ፤…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል አስራ አምስት

➧ሱፍያን አስሰውርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናገሩ፡-

▪️"رحم الله أبا حازم قال: "رضي الناس اليوم بالعلم وتركوا العمل"

➲“አባሀዝምን አላህ ይዘንለት! የሚከተለውን ተናገረ “ዛሬ ሰዎች እውቀትን ወደዱ ተግባርን ተው” ኢማሙ አህመድ ፍል ዒለል፡ 2659 ላይ ዘግበውታል ኢብኑ ሀዝም ሰለመት ብን ዲናር አል ዓእረጅ ይባላሉ

➲ማሊክ ብን ዲናር -ረሂመሁሏህ- ደግሞ የሚከተለውን ተናገረ፡-

▪️"إن العبد إذا طلب العلم للعمل كسره علمه، وإذا طلبه لغير ذلك ازداد به فجورا أو فخرا"

➧“አንድ ባሪያ እውቀትን ከፈለገ እውቀቱ ያሸንፈዋል፡፡ ከዚህ ውጭ ከፈለገ አመጽና
ኩራትን ይጨምረዋል፡፡” አል ኸጢብ ፊልኢቅቲዳ፡31,32,33 አልባኒ ሰነዱን ምንም አይልም ብለውታል

▪️ዓብደሏህ ብን ሙዕተዚ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግሯል፡

"علم بال عمل كشجرة بال ثمرة"

“እውቀት ያለስራ ልክ ያለፍሬ ዛፍ ማለት ነው፡፡”

▪️አሁንም በተጨማሪ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️"علم المنافق في قوله، وعلم المؤمن في عمله"
“የሙናፊቅ እውቀት ከንግግሩ ላይ ነው፤ የሙእሚን እውቀቱ ከስራው ላይ ነው፡፡”

➲መዕሩፍ አልኸርኺ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግረ፡- “አላህ ለባሪያው መልካምን የፈለገለት ጊዜ የስራን በር ለእርሱ ይከፍትለታል፡፡ የክርክርን በር ይዘጋለታል፡፡ ለባሪያው መጥፎን አላህ የፈለገበት ጊዜ የክርክርን በር ይከፍትለታል ፤ የስራን በር ይዘጋበታል፡፡”

➧ሰዎች እየተከራከሩ ሀሰን አል’በስሪ -ረሂመሁሏህ- ሰማ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ተናገረ፡-
▪️"هؤلاء قوم ملوا العبادة، وخف عليهم القول، وقل ورعهم فتكلموا"

➲“እነዚህ ሰዎች ዒባዳን የሰለቹ ናቸው፡፡ ንግግራቸው በእነርሱ ላይ ቀለለ፡፡ የአላህ
ፍራቻቸው በመቅለሉ (ምክንያት) ተናገሩ፡፡” ፈድሉ ዒልሚ አስ ሰለፍ፡ ገፅ37

➤ቢሽር ብን አልሀሪስ -ረሂመሁሏህ- ደግሞ የሚከተለውን ተናገረ፡-

"العلم حسن لمن عمل به، ومن لم يعمل ما أضره"

▪️"በእርሱ ለሰራበት እውቀት መልካም ነው በእርሱ ያልሰራ ሰው ምን ጎጅው ሆነ!”
➧ሱፍያን ብን ኡየይናህ -ረሂመሁሏህ- ደግሞ የሚከተለውን ተናገረ፡ "
العلم إن لم ينفعك ضرك"

“እውቀት አንተን ካልጠቀመህ ይጎዳሃል

▪️ከዚህ ንግግር አስከትሎ ኸጢብ -ረሂመሁሏህ- ደግሞ የሚከተለውን ተናገረ፡-
▪️"إن لم ينفعه بأن يعمل به، ضره بكونه حجة عليه"
“በእርሱ ለመስራት ተጠቃሚ ካልሆነ ፣ በእርሱ ላይ ሁጃ በመሆን ይጎዳዋል፡፡”

(ከላይ ተዘረዘሩት ንግግሮች በሙሉ ኸጢብ “ፈልኢቅቲዳኡ አል’ዒልም” ላይ የዘገባቸው ናቸው፡፡)



➧ኢንሻአላህ ክፍል አስራ ስድስት ይቀጥላል◉◉◉

🥢ኑርአህመድ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➲የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!! ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል አንድ ➠ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ሲላኩ የነበሩት ሙሽሪኮች በአላህ ማመንና በአላህ ማጋራትን ባንዲ ላይ ቀላቅለዉ የያዙ ሰዎች ነበሩ። በጌትነቱ ያምናሉ። በአምላክነቱ ያጋራሉ። ይህን ሲያመላክት ጌታችን (አብዘሃኞቹ እያጋሩ እንጂ አያምኑም)ይላል።[ዩኑስ:106] ስለዚህ ያምናሉ…
▼የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!!!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሁለት

➲ይሄ እንግድህ ብዙዎቻችን በገሃድ የምንመለከተዉ የሆነ ''የሓጂ፣ የነከሌ ''ሸይኽ''የነ ''ኡስታዝ'' ሺርክ ነዉ። ወይም ደግሞ'' ሓጂ'' እና ከነ ''ሸይኽ'' እከሌ አይንና አፍንጫ ስር የሚፈፀም "ሃይ" ባይ ያጣ አምልኮ ነዉ። አዎ! የመቃብር አምልኮ ከሙስሊሙ አለም ከተንሰራፍ ዘመናት ተቆጥሯል።

➧ከሞቱ ዘመናት የተቆጠራቸዉን ፣ለሌሎች ቀርቶ ለራሳቸዉ የማይሆኑ፣ እጣ ፈንታቸዉ ጀነት ይሁን ጀሃነብ የማያዉቁትን ሙታኖች የሚማፀኑ መሀይማን እጂጉን የበዙ ናቸዉ።

➭እንዲያዉም የጠመጠሙና በየ አካባቢያቸዉ በእምነት ጉዳይ ላይ ከፊት ሰልፍ ላይ የሚገኙ በርካቶች የመሪነት ሚናቸዉን በመወጣት ፈንታ በተቃራኒዉ የጥፍቱ ተዋናይ ሲሆኑ መመልከት እጂጉን አሳዛኝ ነዉ።


➧ይባስ ብሎም ሺርክን በመሸላለም፣ ተዉሒዲን በማጠልሸት፣ እንዲሁም ኢስላምን ለሚያጠቃ ሁሉ አፈ_ቀላጤ፣ በመሆን የሚጫዎቱት አፍራሺ ሚና ሞትን፣ የቀብር ቅጣትን፣ቂያማን ፣ሲራጥን፣ ጀሀነብን ከሚፈራ ሙስሊም ፎፁም የማይጠበቅ፣ ህሌና ላለዉ ሁሉ የሚዘገንን ቆሻሻ ምግባር ነዉ።

➧በየ መቃብሩ እየተልከሰከሱ፣ በየ አዉሊያዉ ስም እያለቀሱ"እኛ ቀብሩን ሳይሆን በቀብሩ ያለዉን ሸይኽ ነዉ የምናስበዉ"ይላሉ።'' አልሸሹም ዞር ይሉሃል ''ይሄ ነዉ።እዉነት ብለዋል።

➲ግን የኑሕ ህዝቦች ሲያመልኮቸዉ ከነበሩት ሀዉልቶች ዘንዲ ማንይ አስበዉ ነዉ ሲሰበሰቡ የነበረዉ? በነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ዘመን የነበሩ አጋሪዎችስ?


➧እስኪ ኢብኑ አባስ ረዲያለሁ አንሁ ምን እንደሚሉ እንመልከት፦በኑህ ዘመን የነበሩ ጣኦቶች የኋላ ኋላ ለዐርቦች ዳግም ተመልከዋል።" ወድ" ደዉመቱል ጀንደል ላይ የነበረች የከልብ ጎሳ ጣኦት ነበረች።" ሱዋዕ" የሁዘይል ጎሳ ፣"የጉሥ'' የሙራድ ከዚያም በአልጀዉፍ ሰበዕ አካባቢ የገጢፍ ጎሳ፣ "የዑቅ" የሀምዳን ጎሳ ፣"ነስር" በሒምየር የዚል ከላዕ ጎሳ ጣኦቶች ነበሩ።

➭እነኚህ የጣኦት ስሞች ከኑሕ ሰዎች ዉስጥ የነበሩ የደጋግ ሰዎች ስሞች ናቸዉ።

➲እነኚህ ደጋጎች ሲሞቱ ሸይጧን በሚቀመጡባቸዉ ቦታዎች ሀዉልቶችን እንዲተክሉና ስማቸዉ እንዲሰይሟቸዉ አሰረፀባቸዉ። እዳላቸዉ አደረጉ። በግዜዉ ግን አልተመለኩም። ሀዉልቶችን የተከሉት ሲጠፉና እዉቀት ሲከስም በሂደት ተመለኩ።(ቡኻሪ፡4920)


🖊ይቀጥላል ኢንሻ አላህ!

📚ተዉሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መፀሃፍ የተወሰዴ

➢ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
▼የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!!! ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሁለት ➲ይሄ እንግድህ ብዙዎቻችን በገሃድ የምንመለከተዉ የሆነ ''የሓጂ፣ የነከሌ ''ሸይኽ''የነ ''ኡስታዝ'' ሺርክ ነዉ። ወይም ደግሞ'' ሓጂ'' እና ከነ ''ሸይኽ'' እከሌ አይንና አፍንጫ ስር የሚፈፀም "ሃይ" ባይ ያጣ አምልኮ ነዉ። አዎ! የመቃብር አምልኮ ከሙስሊሙ…
➤የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት


➧እንግዲህ ተመልከቱ የኑህ ህዝቦች በዉሃ ተበልተዉ የጠፉበት ሺርክ በሞት የተለዩዋቸዉን ደጋጎች በማሰብ ይፈፀሙት የነበረ የጣኦት አምልኮ ነዉ።

➧በተመሳሳይ እራሳቸዉ ደጋጎችንም ይሁን እነሱን የሚወክል ወይንም የሚያስታዉስ ሀዉልት ወይንም ዶሪሕ የሚያመልክ ከአላህ ሌላ ያለን አካል የሚጣራ ደግሞ ሺርክ እየፈፀመ እንዴሆነ እጂግ ሲበዛ ግልፀ ነዉ።

➧ዛሬ ዛሬ የቀዲሞዎቹ ሙሽሪኮች በአላህ መኖርና በጌትነቱ ይክዱ እንዴነበር የሚያስቡ ሰዎች ቀላል አይደሉም። እዉነታዉ ግን እንደዚያ አለመሆኑ ነዉ።

➧የቀድሞዎቹ አጋሪዎች ሺርካቸዉ በአምልኮትን ለፈጣሪም ለፍጡርም ከመስጠት ጋር የተያያዘ ነበር። በአላህ ፈጣሪነት ግን ያምኑ ነበር። ይህ እዉነታ ብዙዎቹ ቢዘናጉም ቁርዓን ላይ ፍንትዉ ብሎይገኛል።

➲ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም የአላህ መልዕክተኛ ሆነዉ በተላኩ ግዜ አለም በድቅድቅ ጨለማ ዉስጥ ነበረች።

➤እነዚያ በዲንቁርና የተተበተቡ አረቦች ከእግር ጥፍራቸዉ እስከ አፍንጫቸዉ የባዕድ አምልኮ ዉስጥ የተነከሩ ነበሩ።

የዐረቢያን ልሳነ_ምድር ከጫፍ እስከ ጫፍ በጣኦት የተወረረ ነበር።

➧ግርዲፍ ዳሰሳ ብናደርግ "አልላት" ከጧኢፍ የምትገኝ የመካና የገጥፍን ሰዎች የሚያመልኳት ዲንጋይ ነበረች።

➧" አል ዑዛ" ዐረፍ አቅራቢያ የምትገኝ የመካና የገጥፍን ሰዎች የሚያመልኳት የተምር ዛፍ ነበረች።

➧"መናት" በቀይ ባህር ዳርቻ በመካና በመዲና መሀል በቁደይድ በኩለሰ የምትገኝ የመዲና ሰዎች የሚያመልኳት ድንጋይ ነበረች።

➧"ኢሳፍ" እና ናኢላህ" ሰፍና መርፋ ላይ ይገኙ የነበሩ ጣኦቶች ናቸዉ።

➧የተዉሒድ ተምሳሌት የሆነዉ የተከበረዉ ካዕባ ዙሪያ -ገባዉን በሶስት መቶ ስልሳ ጣኦታት የተወረረ ነበር።


➧ካዕባ ዉስጥ "ሁበል" የተሰኛ ጣኦት ነበራቸዉ። "ወድ" ደዉመቱል ጀንደል አካባቢ ነበር።

በየ አካባቢዉ ፣ በየ ጎሳዉ፣ አልቆ መሳፍርት ጣኦቶች ነበሩ።

➲እነዚህ ከአላህ ጋር አብረዉ የሚመለኩ ጣኡታት በአብዘሃኛዉ ጉኡዛን ነገሮች ነበሩ። ይሁንጂ በግዜዉ የነበረ የባዕድ አምልኮ ዛፍና ዲንጋይ ላይ ብቻ የተገደበ አልነበረም።

➧ጌታችን አላህ በቁርዓኑ ያወገዘዉ ሁሉንም አይነት የባዕዲ አምለኮት ነዉ።

➤ብዙ ሰዎች ካሉበት የባዕድ አምልኮ እንዲታቀቡ ቁርዓንና ሀድስ ሲነበብላቸዉ "ይሄ በጣኡታዊያን አረብ አጋሪዎች ላይ የወረዴ ነዉ። የሚል እነሱን እንደማይመለከታቸዉ ሽንጣቸዉ ገትረዉ ይሟገታሉ።

➧ነገር ግን መዘናጋት የሌለበት ሐቅ ከቁርዓን ከሃድስ የተወገዘዉ የባዕዲ አምልኮ ዛፍና ድንጋይ ማምለክ ብቻ አለመሆኑ ነዉ።



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ተዉሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር መፀሃፍ የተወሰዴ!!

https://t.me/httpsLatahzen
🛑ዳሩል ፊትና🛑

በዱንያ መኖርህ:
ሀብት መንበሽበሽህ:
ድሎት ቢበዛብህ:
ኒእማ እንዳይመስልህ:
🌺🌺🌺🌺🌺
የዱንያ ሀያት:
የፊትና ጊዜ ናት:
አትታለልባት:
ድሎት ብትል ክፋት:
ሁሏም ለፊትና ናት:
🌺🌺🌺🌺🌺
ይህን ተገንዝበህ:
ራስን አዘጋጅተህ:
🌺🌺🌺🌺🌺
ተፈተን ፈተና:
ውጤት ከጅልና።
🌺🌺🌺🌺🌺
@Nur4843
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
▪️ጁሙዓ ነው ፤ ሰለዋት እናብዛ

🔻የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ ሰው ፤ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። ] (ሙስሊም ዘግቦታል).
____
اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد.
___
📣https://t.me/ibnyahya7
Audio
ሱረቱል ከህፍ

ምርጥ ቲልዋ
በወንድም አቡ አይመን
#አንዲት የ 18 አመት ልጅ ድንገት ከትምህርት ቤት እየተመለሰች ሳለ አንድ ባለ መኪና አፍኖ ይዞ ከመኪናው የሗላ ኪስ ይከታታል ከዛው ወደ ጫካ ይዞዋት ይሔዳና ኬሱን ለመክፈት ሲሞክር እምቢ ይለዋል ቢታገል ቢታገል እምቢ ይለዋል አረ ጉድ ሐገር አየኝ ብሎ እዛው አቅራቢያ ወዳለ ገራጅ መኪናውን ይዞ በመሔድ አረ ከጉድ አውጡኝ ይላል: እነሱም በተራቸው ለመክፈት ይታገሉ ጀመር ሊሳካላቸው አልቻለም ከዛው አማራጭ ሲያጣ ልጅቷ ሙታ እንዳይሆን በማለት እጁን ለፖሊስ ለመስጠት ተገደደ ከዛው ፖሊሶቹም ለመክፈት ሲታገሉ ነቀነቅ አላላም ከዛው አንድኛው ፖሊስ አንድ ሐሳብ አመጣ ለኡለማኦች ይነገርና በኪሱ ላይ ቁርአን ይቀራበት አለ በዚሐሳብ ተስማምተው ለአንድ አሊም ተነገራቸውና መጥተው ቁርአን ሲቀሩበት የመኪናው ኪስ ተከፈተ ይሔን ጊዜ ልጅቱ በአፏ ይሆነ ነገር ትላለች በመቀጠል ሸኺየው ለመሆኑ ሰውየው ካፈነሽ ጊዜ ጀምሮ ምን እያልሽ ነበር አሉዋት እሷም እንዲህ አለች:
(አየተልኩርሲይና)
(ሙአወዘተይን)
ማለትም ቁል አኡዙ ቢረቢል ፈለቅ እና ቁል አኡዙ ቢረቢናስ እየቀራሁ ነበር እስከአሁኖ ሰአት ደጋግሚ ሳላቆም እየቀራሁ ነበር ይሔንን ደግሞ "ያስተማረቺኝ እናቴ ናት በማንኛውም ጊዜ ምንምአይነት ችግር ሲገጥመኝ እንድቀራው ትመክረኝ ነበር" አለች::
አላሁ አክበር
#ከአላህ ጋር የሆነ አላህ ከሱጋር ይሆናል
ወንድምና እህቶች
አንድ ነገር ታውቃላችሁ ሁል ጊዜ ከሰላት በሗላ አየተል ኩርሲይ የቀራሕ እንደሆን ጀነት ለመግባት ባንተና በጀነት መሐከል ያለው ሞት ብቻ ነው ስለዚሕ ውዶቼ ሁልጊዜ አየተል ኩርሲይ እንቅረ!

አላህ ተጠቃሚ የድርገን አሚን!!!

https://t.me/httpsLatahzen
Audio
የዛሬው ኹጥባ

ከልዩነት መውጫ መንገዶች

ሸዕባን 15/1443 አ/ሂ