La tehzen
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል አስራ ሁለት ➧ሰባተኛው፡ ተግባር ፣ እውቀት በአዕምሮ ውስጥ ሰርጾ እንዲገባና የጸና ተግባር ከቀረ እውቀትም ይጠፋል፡፡ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡- ▪️"هتف بالعلم العمل، فإن أجابه وإلا ارتحل" “እውቀት ለተግባር ጥሪ ያደርጋል ፤ ከተቀበለ (መልካም) ካልተቀበለ ግን ጥሎት ይሄዳል”…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭
➻ ክፍል አስራ ሶስት
➫➫➫➫➫➫➫➫
➧አንድ ሰው የመልካም ባህሪያት ሁሉ ከእርሱ ላይ ካልተሰባሰቡ ከኢማምነት
ደረጃዎች ሊደርስ አይችልም፡፡ በመልካም ባህሪያቶች ለሰዎች አርአያ ሊሆን ይገባል፡፡
➛የእውቀት አይነቶችን እየሰበሰበ ነገር ግን የተግባር ሰው ካልሆነ ይህ ሰው እርሱ እንዳልተጠቀመ ሁሉ በእውቀቱ ሌሎች ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡
✅ተጽእኖ አሳዳሪ አንድ ታሪክ ላውራ፡-
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➲አንድ ጊዜ እድሜያቸው የገፋ ሰው መስጅድ ውስጥ አገኘሁና ዘየርኳቸው፡፡ እኒህ ሽማግሌ አላህን በጣም ይገዙ ነበር፡፡ ሶላትን መስጅድ ውስጥ ሁልጊዜ ይጠባበቃሉ፡፡አሰላሙ ዓለይኩም አልኳቸውና ከሰውየው ጋር ንግግር ጀመርኩ፡፡ “በእናንተ መንደር
እውቀት ፈላጊዎች በብዛት አሉ” አልኳቸው፡፡ “በዚህ በመንደራችን?” አሉኝ። አዎ! አልኳቸው፡፡ “ማሻአላህ የእውቀት ፈላጊዎች በርካታ ናቸው” አልኳቸው፡፡
➧“በዚህ በመንደራችን!” በማለት መልሰው ጠየቁኝ፡፡ የተቃውሞ ይመስላል፡፡ እኔም
“አዎ” አልኳቸው፡፡ ከዚያም “ልጀ ሆይ ከጀመዓ ጋር ሶላትን የማይጠባበቅ ሰው
እውቀት ፈላጊ አይባልም” በማለት መልስ ሰጡኝ፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ሰው ዒልም ፣ ሂፍዝ ፣ እና ዳዕዋ ማድረግን ያበዛል፡፡ ነገር ግን ፈጅር ሶላት ላይ ግን አታገኘውም፡፡ ብዙ ጊዜ ታጣዋለህ፡፡
➧ሶላት ደግሞ ከሸሀደተይን በኋላ የኢስላም ትልቁ ማዕዘን ነው ፣ የቂያማ ቀን መጀመሪያ የምንጠየቅበትም ነው፡፡ ሶላትን ካጠፋ የእውቀት አሻራው የት ላይ ነው ያለው ? የሶሃቦችን ባህሪ ኢብን ዑመር ረድየሏሁ አንሁማ እንደሚከተለው ይናገራል፡
▪️"كنا إذا فقدنا الرجل في الفجر والعشاء أسأنا به الظن"
➲“አንድ ግለሰብ በሱብሂም ይሁን በዒሻ ካጣነው በእርሱ መጥፎን እንጠራጠር ነበር፡፡” ( ጦበራኒይ ፊሙዕጀም አል ከቢር፡12/271 ኢብኑ ኹዘይማ፡ 1405 ኢብኑ ሂባን፡ 2099 ላይ አውርተውታል)
▪️وفي الحديث " إن أثقل صالة على المنافقين صالة الفجر وصالة العشاء"
➧በሐዲስ ረሡል صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“በሙናፊቅ ላይ ከሶላት ከባዱ የፈጅርና የዒሻ ሶላት ነው፡፡” ቡኻሪ፡ 757 ሙስሊም 651
➧አሁን ባለንበት ወቅት በብዛት እየተስተዋለ ያለው ችግር የፈጅር ሶላት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በዲን እውቀት እየተከራከሩ ያመሻሉ፡፡ ከዚያም የፈጅርን ሶለት ሳይሰግዱ ይተኛሉ፡፡ አንድ ሰው በፈጅር ሂሳብ ቁርኣን እየቀራ ወይም እየሀፈዘ ሌሊትሙሉ ቢያመሽ ማምሸቱ ሀራም ነው የሚሆንበት፡፡ እርሱ ሐጢያተኛ ይሆናል፡፡
➲በዚህ ዘመን በአብዛኛው ውድቅ እየተደረገ ያለው ከሶላቶች ሁሉ በላጭ የሆነው የፈጅር ሶላት ነው፡፡
▪️የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-
▪️"أفضل الصلوات عند الله صالة الصبح يوم الجمعة في جماعة"
➧“ከአላህ ዘንድ ከሶላቶች ሁሉ በላጭ ጁሙዓ የፈጅር ሶላትን በጀመዓ መስገድ ነው፡፡” ሂልየቱ አል አውሊያእ፡ 7/207 አልባኒ ሐዲሱን ሶሂህ ብለውታል ሲልሲለቱ አሰ ሶሂህ፡1566
➧የጁሙዓ ቀን የሱብሂ ሶላትን በጀመዓ መስገድ በአብዛኛው እየተዘነጋ የሄደበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ እስኪ የመስጅድ ኢማሞች ይጠየቁ፡፡ ምክንያቱም (በዓረብ አገሮች) የጁሙዓ ሌሊት የፈቃድ ሌሊት ነው፡፡ የጁሙዓ ሌሊት የወሬ ሌሊት ነው፡፡
➠ሰዎች እስከመጨረሻው ሌሊት ያመሻሉ ፤ ከዚያም የፈጅርን ሶላት ሳይሰግዱ ይተኛሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል ጥሩ የሚባለው ዘግይቶና ከዚያም ቅንጭላቱ በእንቅልፍ ናውዞ የሚሰግደው ነው፡፡
➭የመስጅዱ ኢማም “ሱረቱ ሰጅዳ” እና “ሀልአታ” ሱራዎችን በመቅራት የታወቀ ከሆነ ሁለተኛው ረከዓ መጨረሻ ላይ መጠው የሚሰግዱ ሰዎችም አሉ፡፡
ችግሩ ያለው የትንሳኤ ቀን ከእርሱ መጀመሪያ የሚጠየቅበት የሆነው ፈርድ ሶላት ላይ ከሆነ ፣ የእውቀት ፍሬው የት ላይ ነው ያለው? ሶላትን ካጠፋ ሌላውን ማጥፋቱ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡
〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰
➧ኢንሻአላህ ክፍል አስራ አራት ይቀጥላል◉◉◉✍
ኑርአህመድ🖊
【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚
➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen

Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
La tehzen
➧ከተውሂድ አርማዎች ➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➛ክፍል ስድስት ➭➭➭➭➭➭➭➭ ➧የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➲የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم” ወላጆቹ ሙስሊም ያደርጉታል” የሚል ሳይሆን “ወላጆቹ አይሁድ ወይም ክርስቲያን ወይም መጁስ ያደርጉታል” የሚል ቃል ነው የተናገሩት፡፡ ምክንያቱም ያደገው የተወለደው በተፈጥሮ እምነቱ ላይ ነው፡፡ ➭ተውሒድ…
➧ከተውሂድ አርማዎች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➻ክፍል ሰባት
➛➛➛➛➛➛
➧የተውሂድ መለያዎችና ትሩፋቶች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱
➲ሰባተኛው፡- በዚህ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም በዘውታሪነትና በቀጣይነት በትክክል የሚያስተሳስር እርሱ ብቻ ነው፡፡ እንደተውሒድ በሰው ልጆች መካከል እርስ በርስ የሚያስተሳስር አንድም ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ተውሒድ በኢማን ባለቤቶች መካከል በዚህ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም ቀሪ ፣ ቀጣይነት ያለውና ዘላለማዊ የሆነ የማስተሳሰሪያ ገመድ ነው፡፡
➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯ
▪️الْأَخِلَّاءُ يَوْمَئِذٍ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ عَدُوٌّ إِلَّا الْمُتَّقِينَ
“ወዳጆች በዚያ ቀን ከፊላቸው ለከፊሉ ጠላት ነው፡፡ አላህን ፈሪዎች ብቻ
ሲቀሩ፡፡” አዝ ዙኽሩፍ፡ 67
▪️وَتَقَطَّعَتْ بِهِمُ الْأَسْبَابُ
“በእነርሱ መካከል ምክንያቶች በተቆረጡ ጊዜ (የሚሆኑትን ባወቁ ኖሮ በተጸጸቱ ነበር)፡፡” አል በቀራህ፡166
➧ይህ ማለት በመካከላቸው የነበረው ትስስር በተቋረጠ ጊዜ ማለት ነው፡፡በተውሒድ እና በኢማን የተመሰረተ ግንኙነት እና ውዴታ ካልሆነ በቀር ማንኛውም ግንኙነት ይቆራረጣል ፤ በመካከል ያለው ፍቅር ይወገዳል፡፡
➧ለአላህ የሆነው የትስስር ገመድ ይዘወትራል ፣ ግንኙነቱ የተቀጠለ ይሆናል፡፡ በሌላ ኣላማ ላይ የተመሰረተ የትስስር ገመድ ይቆራረጣል ፤ ይለያያል፡፡ ግንኙነቱ የፈለገው ጠንካራና ጥልቅ ቢመስል እንኳ ፣ በተውሒድ ወይም ባማረ ኢማን የተመሰረተ ካልሆነ በቀር በዚህ ምድራዊ ዓለምም ወይም በወዲያኛው ዓለም መቋረጡ አይቀርም፡፡የተውሒድ ውዴታ ግን በዚህ ምድራዊ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም ቀጣይነትና ዘውታሪነት አለው፡፡
➲ስምንተኛው፡- የተውሒድ ምንጭ ሰላማዊ ነው፡፡ ተውሒድ የተቀዳው ከጥሩና ከጣፋጭ ምንጭ ነው፡፡ እርሱም ከአላህ ኪታብና ከልብ ወለዳቸው ከማይናገሩት ረሡል صلى الله عليه وسلمሱና የተቀዳ ነው፡፡
➲ዘጠነኛው፡- ተውሒድ ጽኑ እንዲሁም ጥብቅ ነው፡፡ ተውሒድን ወይም ዲኑን እስከትንሳኤ ቀን ድረስ በጽናት ሊያቆየውና ሊጠብቀው አላህ ዋስትና ወስዷል፡፡
➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡
▪️هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ
➲“እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሐይማኖት ላይ ከሃይማኖቱ ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡” አት ተውባህ፡33
۞ إِنَّ اللَّهَ يُدَافِعُ عَنِ الَّذِينَ آمَنُوا ۗ
“አላህ ከእነዚያ ካመኑት ላይ ይከላከልላቸዋል፡፡” ሐጅ 38
▪️يُثَبِّتُ اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا بِالْقَوْلِ الثَّابِتِ فِي الْحَيَاةِ الدُّنْيَا وَفِي الْآخِرَةِ ۖ
“አላህ እነዚያን ያመኑትን በቅርቢቱም ሕይወት በመጨረሻይቱም (በመቃብር) በተረጋገጠው ቃል ያረጋቸዋል፡፡” ኢብራሒም፡27
➲አሥረኛው፡ ተውሒድ በርካታ ፍሬዎችንና ትሩፋቶችን የሰበሰበ ነው፡፡ በዚህ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም የተለያዩ መልካም አሻራዎች አሉት፡፡
◉
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል
🖊🖊ኑርአህመድ
【አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል】

➲የጥንቶቹ ሙሽሪኮች ሽርክና የዘመናችን ሺርክ መመሳሰል!!
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫
➧ክፍል አንድ
➠ነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም ሲላኩ የነበሩት ሙሽሪኮች በአላህ ማመንና በአላህ ማጋራትን ባንዲ ላይ ቀላቅለዉ የያዙ ሰዎች ነበሩ። በጌትነቱ ያምናሉ። በአምላክነቱ ያጋራሉ። ይህን ሲያመላክት ጌታችን (አብዘሃኞቹ እያጋሩ እንጂ አያምኑም)ይላል።[ዩኑስ:106] ስለዚህ ያምናሉ ግን ሲያምኑ እያጋሩ ነዉ ማለት ነዉ።
➲ኢብኑ አባስ፣ከሐሰነል በስሪ፣ከሙጃሂድ፣ከዓሚር አሸሽዕይ፣ ባጠቃላይ ከብዙሃኑ ሙፈሲሮች እንዴተላለፈዉ የዚች አንቀፀ መልዕክት ከሃዲዎች በአላህ ጌትነት ያምናሊ። ነገር ግን በአምላክነቱ ሌሎችን ያጋራሉ።(አድዋኡል በያን፡2/218)
➧እነዚያ በስነ ፁሁፍ የመጠቁ አረቦች እራሳቸዉ ጠርበዉ፣ጠጥፈዉ ለሰሯቸዉ ጣኦታት ያጎበዲዳሉ፣ያርዱ፣ይሳሉ፣ ይሳለሙ ነበር። በየቀበሌዉ ጠንቋይ፣በየ አካባቢዉ ጣኦት ነበራቸዉ።
➲ዛሬም በተመሳሳይ በአላህ ጌትነት አምነዉ ከፊል ዲንጋጌዎቹን እየፈፀሙ በጎን አምልኮትን ለፍጡር በመስጠት የሚያጋሩ ብዙዎች ናቸዉ።
ስኒ የሚዘቀዝቁ፣ ጀበና የሚያመልኩ፣ ለጠንቋይ የሚያጎበዲዱ፣በየ መዉሊድ በሺርክ በታጀቡ መንዙማዎች የሚያረግዱ፣ከነብዩ ሰለላህ አለይሂ ወሰለም አልፎ በመሻይኾች የሚምሉ፣ልጂ ፍለጋ፣ የስራ እድል እድከፍትላቸዉ የሚሳሉ፣ለአድባሩ፣ለቆሌዉ፣ለጂኑ ከዶሮ እስከ ከብት የሚያርዱ፣በፍጡር የሚመኩ፣ከየጠንቋዩ ከየ አስማተኛዉ ፊት ክብራቸዉን አራግፊዉን የሚንበረከኩ፣በጉጉት ጩሀት የሚንበረከኩ፣ በቁርዓን አያዎች ከታጀበ የተዉሒድ ምክር ይልቅ በዉሸት ቂሳዎች በታጨቁ ሺርካ ሺርኮች የሚረኩ፣እልቆ መሳፍርት ሙሐመዶች፣ ኸዲጃዎች ኦዳሉ የአደባባይ ሚስጥር ነዉ። በብዙ አካባቢዎች የጣኦት አምልኮት ሰዎችን የሚያስጠነቅቁት አስተማሪዎች ግን ከጥቂትም የቀለሉ ናቸዉ።
➧ይሄ እንግዲህ ልክ እንዴ ጥንቱ ዛሬም እየተፈፀመ ያለ ያፈጠጠ ያገጠጠ ሺርክ ነዉ።
◉
◉
◉✍ይቀጥላል ኢንሻ አላህ
➛ተዉሒድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለዉ መፀሃፍ ከኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ የተወሰደ
➢ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ ተጠቃሚ ይሆናሉ SHAR
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

አስተውይ እህቴ‼️
➖➖➖➖➖➖
✅ ለምን ይመስልሻል⁉️
〰〰〰〰〰〰〰〰
↪️ በሸሪአችን ሴት ልጅ፦
➲ነብይ ወይም ረሱል ተደርጋ ያልተላከችው
➲ቃዲ ሆና ፍርድ ሰጪ ያልተደረገችው
➲ኢማም ሆና ሰዎችን የማታሰግደው
➲ለሶላት እንድትጠራ ሙአዚን ያልተደረገችው
➲የሶላት ማእዘን የሆነውን ፋቲሀ ወንዶች ባሉበት ድምፇ ከፍ አድርጋ መቅራትን የተከለከለችው
➲ኢማሙ ቢሳሳት እንድታጨበጭብ እንጂ በድምፅ መመለስ ያልተፈቀደላት
➲በሀጅ ተልቢያ (ለበይከላሁመ ለበይክ) ስትል ድምፃ ከፍ እንዳታደርግ የታዘዘችው
➲በተከበረው ቁርአን ድምፃችሁ አታለስልሱ የተባለው
➡️ለምን ይመስልሻል⁉️
◾️መልሱ፦ የሴቶች ድምፅ ወንዶችን ስለሚፈትንና ስለሚያሳስት ነው። በዚህ ሰበብ ጥፋት ላይ ላለመውደቅ በሩን ለመዝጋት ሲባል ነው።
💢 ታዳ አላፊ አግዳሚው ባለበት፣ የሴት ልጅ አዳኝ ጠላቶች በበዙበት፣ ካፊር ፋሲቅ ሙናፊቁና የሁዳ በግልፅ በሚታይበት በየ ሚዲያው ድምፅሽን የምትለቂው፣ በቪድዮ የምትቀርቢው፣ ከወንዶች ጋር ያለሀጃ እንደፈለግሽ የምታወሪው እህቴ ሆይ ተይ ተመከሪ። ነገ አላህ ፊት ቆመሽ ከመጠየቅሽ በፊት ዛሬውን ተመለሺ። ዝናው፣ ጥቅሙ፣ ዳእዋውም፣ ለሴቶች ያለሽ ተቆርቋሪነቱም ቀርቶብሽ ባንቺ ድምፅም ሆነ በሌላ ነገር ወንዶች እንዳይፈተኑብሽ ማድረግሽ ይህ ትልቅ ጅሀድ ነው። አላህም ያዘዘሽ በዚሁ ነው። ማስተማርና መምከርም ከፈለግሽ ሴቶች ብቻ ባሉበት ወንዶች በማይገኙበት ቦታ ይሁን።

▪አንዲት ገጠሬ ሴት!!
➬➬➬➬➬➬➬➬
➧ባልሽን እንደዚህ ልታፈቅሪው የቻልሽበት ምክንያት ምንድን ነው ተብላ ስትጠየቅ:-
1► ሲወጣም ሲገባም በፈገግታ በመሆኑ
2► ቤት ያፈራውን ያለወቀሳ በመመገቡ
3► በጠፋ ነገር ባለመውቀሱ ብላ መለሰች።
▪በተመሳሳይ ሚስቱን በእጅጉ የሚያፈቅርን ገጠሬ ለምን እንዳፈቀራት ሲጠይቁት፦
1► በኢስላም ጥላ ስር በመጠበቋ
2► ቃላቶቿ ለስላሳና ማራኪ በመሆኗ
3► ስህተቶችን ስታገኝብኝ አይኖቿን ዝቅ በማድረጓ (ባለመከታተሏ)
4► ክብር የሚያጎድፉ ነገራቶችን ባለመፈፀሟ ነው ብሎ መልስ ሰጠ ይባላል።
👇👇👇👇👇👇👇

💢ሶላት የሌለው ሰው ዲን የለውም
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
ሶላት የዲን ምሰሶ ነው (الصلاة عماد الدين)
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
◾️قال الشيخ صالح الفوزان حفظه الله 【الَّذِي لا يُصَلِّي لا يَقُومُ لهُ دِينٌ، وإنْ شَهِدَ أنَّ لا إِلهَ إلَّا الله وأنَّ مُحمّدًا ﷺ رسولُ الله ،لأنّهُ يحتاجُ إلى عُمُودٍ يُقِيمُ عليهِ الدِّين، وهو لا يُوجَدُ إلا بِالصَّلاة】
➲ሸኽ ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸውና እንዲህ ብለዋል።
✅ ሰላት የማይሰግድ ሰው ሸሀደተይን (ላኢላሀ ኢለላህ ሙሀመድ ረሱሉላህ) ቢል ራሱ ዲኑን (እስልምነውን) አይቆምለትም። ምክንያቱም ዲኑን የሚያቆምበት ምሰሶ የግድ ያስፈልገዋልና። የዚህ ማቆምያ ምሰሶ ደሞ ከሶላት ውጪ ምንም የለም።
📚(شرح الأصول الثلاثة - ص ٢٤٢)

👑መልእክት ለሙእሚና እህት!!
✍️ሼኽ አብድረዛቅ አልበድር {ሀፍዘሁላህ} እንዲህ ይላል፦
~~~~
➤"ሙእሚና እህት ሁሉንም ሴቶች ጓደኛ አርጋ መያዝ የለባትም" ነገር ግን ጎደኛ አድርጋ መያዝ ያለባት ሙእሚን የሆነችውን ጠቃሚ የሆነች በዲን ላይ እምታጠነክራትን ጠቃሚ እውቀትን በኸይር እምታዛትን ከሚጠቅማት ሴቶች ጋር አብራ መሆን አለባት ፦
<< يَنِفُعٌهّآ عٌنِدٍ آلَلَهّ تٌبًآرکْ وٌتٌعٌآلَﮯ.. >>
➤አንድ ሙስሊም ወሙስሊማ ሁሉጋ መደባለቅ የለበትም ነገር ግን መደባለቅ ፋይዳ ጠቃሚ የሆኑ ጋር ይቀላቀል ።
الفضيل بن عياض رحمه الله
እንዲህ ይላል
አማኝ ከሚፈልገው ሁሉ ጋር መቀመጥ የለበትም ።
✍️,,አንዳድ ቀደምት ሰለፎች ፦
አማኝ ከሚፈልገው ጋር መሄድ የለበትም,
➧ለእምነቷ እና ጥንካሬዋ የምትጥር ታማኝ እህት ሁሉንም ሴቶች ጎደኛ አርጋ መያዝ የለባትም።
➧ይልቁን ጓደኛ አድርጋ መያዝ ያለባት እነሱጋ መቀራረብን አብሮ መሆንን ኸይር ያላቸው ሴቶች ጥቅም ያላቸው አላህሱበሀነሁ ወተአላ ሰሚና ታዛዥ የሆኑ ጓደኛ አርጋ ትያዝ።

Forwarded from ኑሩተውሂድ የግጥም ቻናል
"ምነው ኡስታዞቼ"ክፍል ①
ምነው ኡስታዞቼ እንደው ምን ነካቹ፣
በሆነው ባልሆነው መነታረካቹ፣
እኛ ምን እንማር ምን እንውረሳቹ፣
እንደዚያ በጋራ ሱናን አንግሳቹ፣
አሁን ላይ ምን መጣ ምንስ ተከሰተ፣
በውዶቼ መሀል ነገር ተጎተተ፣
እንትና ከእንትና ተብሎም ታተተ፣
በሱንዩች መሀል ፊትና ተከሰተ፣
እንዴት እናርግበው እንዴት ብሎ ይፍረስ፣
ወጣቶች ተነሱ ይህን ለመገርሰስ፣
እነሱን አስማምቶ ፊትናን ለማስተንፈስ፣
ከዛም አልፎ ተርፎ ሱናውን ለማንገስ፣
እንደው ምን ይለናል የኢኽዋን ግሳንግስ፣
ይህንን ቢሰማ ከቶ አይችል መታገስ፣
እኔን ሚያበሽቀኝ ከስር ሚያናፍስ፣
ለአንዱ ወግኖ ሌላኛውን ሚከስ፣
ልክ እውቀት እንዳለው ኡስታዝ ላይ ሚነሳ፣
አልፎም የሚያጣጥል ስሙን የሚያሳሳ፣
የዚ አይነቱ በዝቶ ሆነብን ነቀርሳ፣
ያለ እውቀት የሚዘል የኡማው አበሳ።
ጌታችን ባክህን ኡስታዞቻችንን፣
በሀቅ በእውነት አንተው አስማማልን፣
ወሬ አቀባባይ ከመሀል አውጣልን፣
በእነሱ እውቀትም እኛን አስጠቅመን።
✍ኑርአህመድ
https://t.me/httpsnurahemd
https://t.me/httpsnurahemd
ምነው ኡስታዞቼ እንደው ምን ነካቹ፣
በሆነው ባልሆነው መነታረካቹ፣
እኛ ምን እንማር ምን እንውረሳቹ፣
እንደዚያ በጋራ ሱናን አንግሳቹ፣
አሁን ላይ ምን መጣ ምንስ ተከሰተ፣
በውዶቼ መሀል ነገር ተጎተተ፣
እንትና ከእንትና ተብሎም ታተተ፣
በሱንዩች መሀል ፊትና ተከሰተ፣
እንዴት እናርግበው እንዴት ብሎ ይፍረስ፣
ወጣቶች ተነሱ ይህን ለመገርሰስ፣
እነሱን አስማምቶ ፊትናን ለማስተንፈስ፣
ከዛም አልፎ ተርፎ ሱናውን ለማንገስ፣
እንደው ምን ይለናል የኢኽዋን ግሳንግስ፣
ይህንን ቢሰማ ከቶ አይችል መታገስ፣
እኔን ሚያበሽቀኝ ከስር ሚያናፍስ፣
ለአንዱ ወግኖ ሌላኛውን ሚከስ፣
ልክ እውቀት እንዳለው ኡስታዝ ላይ ሚነሳ፣
አልፎም የሚያጣጥል ስሙን የሚያሳሳ፣
የዚ አይነቱ በዝቶ ሆነብን ነቀርሳ፣
ያለ እውቀት የሚዘል የኡማው አበሳ።
ጌታችን ባክህን ኡስታዞቻችንን፣
በሀቅ በእውነት አንተው አስማማልን፣
ወሬ አቀባባይ ከመሀል አውጣልን፣
በእነሱ እውቀትም እኛን አስጠቅመን።
✍ኑርአህመድ
https://t.me/httpsnurahemd
https://t.me/httpsnurahemd
Forwarded from ሀቅን ፍለጋ ከቁርዐንና ከሀዲስ አርባ ምንጭ ዪኒቨርስቲ AMU chamo Campus 2009
ከዛሬ ገጠመኞች ውስጥ
ገራሚ ገጠመኝ በጉራጌ ዞን ዛሬ
ነገሩ እረጅም ነው ሳሳጥረው ግን
ፈገግታ ሱና ነው ፈገግ በሉ
" ኡስታዝ ሳዳት ከማል ለአንድኛው ሰውዮ ስለተውሒድ እና ስለ ሽርክ አንዳንድ ነገር እያለው አይ ዛሬ ቃጥባሪ መውሊድ ስላለ ከዚያ አልቀርም እያለው ለኡ/ሳዳት ከዚያ ኡስታዝ ጨመር አድርጎ ስለ ሽርኩም ሰለ አንዳንድ ሁኔታዎች ሲነግረው (ሰፋ ይላል ብያችሗለሁ) ይሄንማ ሳዳት ከማል ነግሮናል ብሎት እርፍ (ኢንካር በማድረግ ቀስድ ሳይሆን አውቀናል ለማለት ነው) ከዚያማ ለሰውየው ኡስታዝ ሳዳት እኮ እሱ እራሱ ነው ሲሉት ሌሎች በሳቅ "
ታሪኩ ምን እንዳስታወሰኝ ታውቃላችሁ ነብዩ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንጨት የተሸከመችውን ሴትዮ .........
ለፈገግታ ያክል ነው
Source ከቦታው ካለው ወንድሜ
ለማንኛውም ዳዕዋዎቹን እንለቅላችሇለን ጠብቁ
https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/11010

♻️🔺 የጥሩ ባል መገለጫዎች♻️🔺
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
♻️🔺 ጥሩ ትዳር መስርቶ መኖር የማንኛዋም ሴት ምኞት ነው፣የጥሩ ትዳር መሰረቱ ጥሩ ባል ነው፣ከጥሩ ባል መገለጫዎች በጥቂቱ እነሆ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⏬ በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል
⏬ ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል
⏫ በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል
↕️ ለሚሰትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⏬ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም)
↕️ ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል
↕️ ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል
↕️ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል
↕️በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም
↕️ ትርፍ ቃል ከመናገር በመታቀብ በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
↕️ ሚስቱ አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም
↕️ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ ስሜቷን ይጋራል
〰〰➰➰➰➰➰〰〰〰〰
↕️ቤቷን ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም አልፎ የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል
↕️ለቤቱ በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ያመሰግናታል ድምበር ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል
↕️ በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና ትዕግስትን ተላብሶ ይኖራል
↕️አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም ሚስቱን እንደ እህቱ በመቁጠርና ለሷ በማዘን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና ቁጣውን ዋጥ በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል::
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
↕️ ከሚስቱ ጋር በመተባበር ልጆቹን በኢስላማዊ አደብና እውቀት ቀርጾ ያሳድጋል
↕️ ሚስቱ ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይሄን ያደርጋል የመላ ሰውነቱን ንጽህናም ይጠብቃል
ወንድሞች አላህ መልካም ወንድ ያድርጋችሁ
https://t.me/httpsLatahzen
➖➖➖➖➖➖➖➖➖
♻️🔺 ጥሩ ትዳር መስርቶ መኖር የማንኛዋም ሴት ምኞት ነው፣የጥሩ ትዳር መሰረቱ ጥሩ ባል ነው፣ከጥሩ ባል መገለጫዎች በጥቂቱ እነሆ
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⏬ በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል
⏬ ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል
⏫ በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል
↕️ ለሚሰትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⏬ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም)
↕️ ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል
↕️ ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል
↕️ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል
↕️በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም
↕️ ትርፍ ቃል ከመናገር በመታቀብ በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
↕️ ሚስቱ አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም
↕️ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ ስሜቷን ይጋራል
〰〰➰➰➰➰➰〰〰〰〰
↕️ቤቷን ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም አልፎ የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል
↕️ለቤቱ በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ያመሰግናታል ድምበር ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል
↕️ በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና ትዕግስትን ተላብሶ ይኖራል
↕️አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም ሚስቱን እንደ እህቱ በመቁጠርና ለሷ በማዘን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና ቁጣውን ዋጥ በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል::
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
↕️ ከሚስቱ ጋር በመተባበር ልጆቹን በኢስላማዊ አደብና እውቀት ቀርጾ ያሳድጋል
↕️ ሚስቱ ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይሄን ያደርጋል የመላ ሰውነቱን ንጽህናም ይጠብቃል
ወንድሞች አላህ መልካም ወንድ ያድርጋችሁ
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
«የቲምን አደራ»
የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን✌️ያሉት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።
💦💦💦💦💦💦💦💦
✍✍ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን✌️ያሉት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።
💦💦💦💦💦💦💦💦
✍✍ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
☆ዲን ያላትን ምረጥ☆
ዲን ያላትን ምረጥ የተሞላች በእውቀት፣
ዝም ብላ የማትሮጥ ወደየ ሞቀበት፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሜካፕና ሽቶ የማይነካት ኮተት፣
ዲኗን ምታከብር ምትወድህ የእውነት፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ቤተሰቧን ሁላ ወዳጅና አክባሪ፣
ረጋ ሰከን ያለች ባለ ድንቅ ባህሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ድንቅ አመለ ሸጋ የሆነች ታታሪ፣
ለሀቅ ለእውነት ታጋይ ተቆርቋሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የተሳፈረች ናት በተውሂዱ ጋሪ፣
የማትለብስ የነሱን የሀራም አክራሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የምትለብሰው ኒቃብ ካልሆነ ነው ጅልባብ፣
የማያታልላት የጓደኛ እባብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እጅግ የምታምር ያለች ሰብ ረገብ፣
የማትለይህ ናት ሁሌ ካንተ አጠገብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በዒባዳስ ቢሆን ምታበረታታህ ምታስርልህ ወገብ፣
የዝች አይነቷ ሁብ ይግባ ከሁሉም ቀልብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የዝች አይነት ያየ ያሳየኝ አደራ፣
እሷኑ አግብቼ በደስታ ልኑራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ከሷ ጋር ይሆናል ህይወቴ የደራ፣
ሰምታ እህቴ አለች ስለዚህ ሲወራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እኔ ምፈልገው በእውቀት ያበራ፣
እኔን የሚወደኝ ሀራም ማያይ ተራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
አጅነቢ ማትቀርበው አላህን ሚፈራ፣
እኔን ሚያስቀራኝ እጅጉን የቀራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እኔን እና ዲኑን እጅግ ያፈቀረ፣
ሸሪአ ሚመራው በዲን የታሰረ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ስለመልኩስ ቢሆን እጅጉን ያማረ፣
ፂሙን የማይላጭ ሱሪ ያልዘረረ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በሱና ተውቦ ህይወቱን የኖረ፣
እሱንስ ካገኘሁ ህይወቴ ሰመረ፣
የዚ አይነቱን ይስጠኝ ካገባሁ ካልቀረ።
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
🖊ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
ዲን ያላትን ምረጥ የተሞላች በእውቀት፣
ዝም ብላ የማትሮጥ ወደየ ሞቀበት፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሜካፕና ሽቶ የማይነካት ኮተት፣
ዲኗን ምታከብር ምትወድህ የእውነት፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ቤተሰቧን ሁላ ወዳጅና አክባሪ፣
ረጋ ሰከን ያለች ባለ ድንቅ ባህሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ድንቅ አመለ ሸጋ የሆነች ታታሪ፣
ለሀቅ ለእውነት ታጋይ ተቆርቋሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የተሳፈረች ናት በተውሂዱ ጋሪ፣
የማትለብስ የነሱን የሀራም አክራሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የምትለብሰው ኒቃብ ካልሆነ ነው ጅልባብ፣
የማያታልላት የጓደኛ እባብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እጅግ የምታምር ያለች ሰብ ረገብ፣
የማትለይህ ናት ሁሌ ካንተ አጠገብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በዒባዳስ ቢሆን ምታበረታታህ ምታስርልህ ወገብ፣
የዝች አይነቷ ሁብ ይግባ ከሁሉም ቀልብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የዝች አይነት ያየ ያሳየኝ አደራ፣
እሷኑ አግብቼ በደስታ ልኑራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ከሷ ጋር ይሆናል ህይወቴ የደራ፣
ሰምታ እህቴ አለች ስለዚህ ሲወራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እኔ ምፈልገው በእውቀት ያበራ፣
እኔን የሚወደኝ ሀራም ማያይ ተራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
አጅነቢ ማትቀርበው አላህን ሚፈራ፣
እኔን ሚያስቀራኝ እጅጉን የቀራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እኔን እና ዲኑን እጅግ ያፈቀረ፣
ሸሪአ ሚመራው በዲን የታሰረ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ስለመልኩስ ቢሆን እጅጉን ያማረ፣
ፂሙን የማይላጭ ሱሪ ያልዘረረ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በሱና ተውቦ ህይወቱን የኖረ፣
እሱንስ ካገኘሁ ህይወቴ ሰመረ፣
የዚ አይነቱን ይስጠኝ ካገባሁ ካልቀረ።
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
🖊ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
“ሴት“
አልሀምዱሊላሂ ልጀምር በስሙ፣
ሴት ልጅን ለሰጠን ሀምድ ይግባው ረሂሙ፣
በሁሉም ዘርፍ ላይ ናት የተዋጣላት፣
ቢወራስ አያልቅም የእሷኮ ማንነት፣
ነች እኮ ወድ እናት አምሳያ የሌላት፣
ደሞ በእህትነት ለወንድሟ ምትሞት፣
እንደው ምን ልበላት ቃላት አጣሁላት፣
ጀሊሉ በቁድራው በጀነት ይካሳት፣
ሚስትም ትሆናለች የባል ተፈቃሪ፣
በጦርነት ላይም ምን ባትሆን ወራሪ፣
ወንዱን ታጅባለች ከጎን አባሻሪ፣
ተወዳጇ ሴት ልጅ አባቷን አክባሪ፣
ኧረ ማነው እስቲ ቦታዋን ሚተካ፣
አልፎ ተረማምዶ ነው ክብሯን ሚነካ፣
ነች እኮ ክብር ያላት የቤተሰብ ዋርካ፣
አላህ ይዘንላት ይሙላት በበረካ።
ልክ እንደ ዓኢሻ በእውቀት የተካቡ፣
አሉ በዘመኑም በኢማን ያበቡ፣
በኒቃብ በሂጃብ እጅግ የተዋቡ፣
ሚናቸው አያልቅም ቢከተብ ኪታቡ፣
ልምከርሽ እህቴ ምን ብዙ ባልቀራ፣
ካየሁ ከሰማሁት በጥቂቱ ላውራ፣
በዲን በክብርሽ ላይ አደራ አደራ፣
ከአላህ እንዳይገጥምሽ የስቃይ መከራ፣
እንዳይታለዪ ዘመኑ ባመጣሽ፣
ገዜ እንዳታጠፊ ምንም በማይጠቀምሽ፣
አልፎ ተገልብጦ አንቺን በሚጎዳሽ፣
እንዳትሸወጂ አደራ ልበልሽ፣
እኔም በዚው ላብቃ ግጥሙም ሳይንዛዛ፣
ራህማኑ ይክፈልሽ ሚያምረውን ጀዛ።
✍ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
አልሀምዱሊላሂ ልጀምር በስሙ፣
ሴት ልጅን ለሰጠን ሀምድ ይግባው ረሂሙ፣
በሁሉም ዘርፍ ላይ ናት የተዋጣላት፣
ቢወራስ አያልቅም የእሷኮ ማንነት፣
ነች እኮ ወድ እናት አምሳያ የሌላት፣
ደሞ በእህትነት ለወንድሟ ምትሞት፣
እንደው ምን ልበላት ቃላት አጣሁላት፣
ጀሊሉ በቁድራው በጀነት ይካሳት፣
ሚስትም ትሆናለች የባል ተፈቃሪ፣
በጦርነት ላይም ምን ባትሆን ወራሪ፣
ወንዱን ታጅባለች ከጎን አባሻሪ፣
ተወዳጇ ሴት ልጅ አባቷን አክባሪ፣
ኧረ ማነው እስቲ ቦታዋን ሚተካ፣
አልፎ ተረማምዶ ነው ክብሯን ሚነካ፣
ነች እኮ ክብር ያላት የቤተሰብ ዋርካ፣
አላህ ይዘንላት ይሙላት በበረካ።
ልክ እንደ ዓኢሻ በእውቀት የተካቡ፣
አሉ በዘመኑም በኢማን ያበቡ፣
በኒቃብ በሂጃብ እጅግ የተዋቡ፣
ሚናቸው አያልቅም ቢከተብ ኪታቡ፣
ልምከርሽ እህቴ ምን ብዙ ባልቀራ፣
ካየሁ ከሰማሁት በጥቂቱ ላውራ፣
በዲን በክብርሽ ላይ አደራ አደራ፣
ከአላህ እንዳይገጥምሽ የስቃይ መከራ፣
እንዳይታለዪ ዘመኑ ባመጣሽ፣
ገዜ እንዳታጠፊ ምንም በማይጠቀምሽ፣
አልፎ ተገልብጦ አንቺን በሚጎዳሽ፣
እንዳትሸወጂ አደራ ልበልሽ፣
እኔም በዚው ላብቃ ግጥሙም ሳይንዛዛ፣
ራህማኑ ይክፈልሽ ሚያምረውን ጀዛ።
✍ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
#ይሔ_ነው_ባል_ማለት__!!
-----------------------------------
የትዳርን ትርጉም ያወቀ ጠንቅቆ፡
ደግነት የሞላው ከክፋት ተላቆ፡
መጥፎን አስወግዶ በበጎነት ደምቆ፡
በፍቅር የሚኖር ቤቱ የደመቀ፡
ሚስቱን ከማስከፋት የተጠነቀቀ፡
በጥብጦ የጠጣ የፍቅርን ጭማቂ፡
ውድ ባለቤቱን ዘወትር ናፋቂ፡
ሙሉ እንቅስቃሴው ለሚስቱ የሚመች፡
ለርሷ ምንም ቢሆን ሁሌም የማይሰለች፡
----------------------------------------------
የሱና ጠበቃ የተውሒድ ሰባኪ፡
ከቢዲዐ ከሽርክ የሌለው ንክኪ
በውቀት የተካነ እጂጉን የነቃ፡
የመዘሀበል ሀቅ የሱና ጠበቃ፡
ፀባዩ ማራኪ እጂግ የረቀቀ፡
ንግግሩ ቁጥብ ኢልሙ የመጠቀ፡
በመልካም ትውስታ ስሙ የገነነው፡
የመንሐጅ ጠበቃ ባል ማለት እሱ ነው፡፡
~~~~
ጭቅጭቅ ንዝንዝ ፈፅሞ የማይወድ፡
ቆፍጣናና ጀግና በቃ ይሔ ነው ወንድ፡
ፈጣን እና አስታዋይ እጂጉን ቀልጣፋ፡
ግሩም-መልከ ቀና አቋመ-ዘንጣፋ፡
ሚስቱ ካይኑ ስትርቅ ቅናት የሚይዘው፡
እውነተኛ ፍቅር የሚወዘውዘው፡
-------------------------------------------
(አልቃሻ!? ሚስኪን ሲያሳዝን!?)
ሚስቱ ስትናፍቀው የሚፈሰው እንባው፡
ያሳለፈው ጊዜ ሆዱን እያባባው፡
በቃ ይህ ነው ለኔ ባልነት የገባው፡
ከቤት እስኪመጣ ከስራ ቆይቶ፡
ሲቃ የሚይዘው ናፍቆቱ በርክቶ፡
ስለርሷ እሚጨነቅ ሁሉን ነገር ትቶ፡
በሆነ አጋጣሚ ከጠፋች ከጎኑ፡
የትዳር አጋሩ የመውደድ ልሳኑ፡
በልቶና ጠጥቶ ምንም የማይመስለው፡
የትዳር አጋሩ ናፍቆት እያየለው፡
ሁሌም የፍቅር ሰው መውደድ የተጠማ፡
መልክና ቁመናው ውብ ማራኪ ዞማ፡
--------------------------------------------
የባልነት መስፈርት ሸርጡ የተሟላ፡
ቃሉ እማይታጠፍ ከገባ መሀላ፡
ከሚስቱ በስተቀር የማያስብ ሌላ፡
ጀግና መልከ-መልካም ገራገር ሸበላ፡
---------------------------------------------
ህዝቦቹ ባንድ ድምፅ የመሰከሩለት፡
መልካም ሰው ነህ አንተስ ብለው ያዜሙለት፡
የሰውነት ሚዛን ይሔ ነው ባል ማለት፡
----------------------------------------------
#ኑር_

የውዱ ነብይ{ﷺ}ምክር
(ትዳርን ላሰቡ ሰዎች)!
➀ ነብይ{ﷺ}እንዲህ አሉ:-
ድንግሎችን አግቡ እነሱ{ድንግሎች} አንደበታቸው እጅጉን ጣፍጭ እና በጥቂት የሚደሰቱ ናቸው።
ምንጭ:-(ሶሒሁል ጃሚዕ)
⓶ ጃቢር ኢብኑ አብደላህ እንዲህ አሉ:-ረሱል ''አገባህ''? አሉኝ አዎን አልዃቸው ቢክራ ወይስ ሰይብ አሉኝ ''ሰይባ''አልዃቸው ከዚያም ቢክራ አታገባም ነበርን የምታጫውታት የምታጫውትህ የምትሆነዋን አሉት።
⓷ ኢማሙ አህለሱና ወልጀምዓ አሕመድ ብን ሀንበል (ረሒመሁላሁ ተዓላ) እንዲህ ይላሉ:-
ቢክር ድንግል የሆነችዋን አግባ።
ምንጭ:-አል ኣዳቡ ሸርዒያ(204-2)
✅ኢስሃቅ ኢብኑ ሀሳን እንዲህ አሉ:-ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሃንበል ስለ ትዳር አማከርኩትና እንዲህ ሲል መከረኝ ቢክራ{ድንግል} የሆነችዋን አግባ እናት የሌላትን{እናቷ የሞተችባት}ለማግባት ጉጉት ይኑርህ።
✅ ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ:-
ልጃገረድ ድንግል የሆነችን ማግባት በላጭ ነው ምክንያቱም እሷ ከሱ በፊት ወደ ሞከረቻቸውና ወዳየቻቸው ወደ ቀመሰቻቸው ወንዶች አትጓጓም ከሱ በፊት በማንም ላይ በአንድም ሰው ላይ ልቧ አይንጠለጠልም።ምክንያቱም ከወንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ እሷን የሚገናኛት ይህ ወንድ ነው ብዙ ትንጠለጠልበታለች። ለነዚህ ምክንያቶች ቢክርን ማግባት በላጭ ነው።
الشرح الممتع (١٢_١٥)
አደራህን #ዲን_ያላት_አግባ!
ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ:-
#እወቅ! አንተ የነብይ{ﷺ} ምክር ሰምተህ (ዲን ያላትን መርጠህ ካገባህ) ቆንጆ ያልሆነችውን አላህ ቆንጆ ያደርግልሃል።
ምንጭ:-(ሸርሁ ሙስሊም)
ግልፅ ነው ወንዶች መልክ መልክ እያልክ እድሜህን ለምን ትፈጃለህ ዲን ያላትን ምረጥ ውበቱን ቤትህ ውስጥ ታገኘዋለክ
➲ የአላህ ነብይ{ﷺ}እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር:-
ጌታዬ አላህ ሆይ የመሸበቻ ጊዜዬ ከመድረሱ በፊት እንድሸብት ከምታደርገኝ ሚስት በአንተ እጠበቃለሁኝ።
ምንጭ:-አስ ሶሒሀህ-3137-
ይሔን ዱዓ ስንቶቻችን ነን በዱዓችን ውስጥ የምናስገባው #ራሳችንን_እንፈትሽ
➲ ሙሃመድ ኢብኑ ሁሰይን እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር:-
ጌታዬ አላህ ሆይ! ሳያት የምታስደስተኝ ሳዛት የምትታዘዘኝ ስርቅ{ክብሬንና ክብሯን እና ገንዘቤን}የምትጠብቅልኝ የሆነችዋን ሚስት ስጠኝ።
ምንጭ:-በህጀቱል መጃሊስ{183}📚📚📚📚📚📚📚📚

➧ከተውሂድ አርማዎች ➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ክፍል ሰባት ➛➛➛➛➛➛ ➧የተውሂድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➲ሰባተኛው፡- በዚህ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም በዘውታሪነትና በቀጣይነት በትክክል የሚያስተሳስር እርሱ ብቻ ነው፡፡ እንደተውሒድ በሰው ልጆች መካከል እርስ በርስ የሚያስተሳስር አንድም ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ተውሒድ በኢማን ባለቤቶች መካከል በዚህ ዓለምም…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭
➭ክፍል ዘጠኝ
➧የተውሂድ ምንነትና እውነታ
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱
➲አንደኛው ተውሒድ አር'ሩቡብያ፡ አላህ በመፍጠርም ፣ ሲሳይ በመስጠትም ፣ ሁሉን ተቆጣጣሪ በመሆኑም ፣ ጸጋን በመስጠቱና ሁሉን በማገለባበጡ ብቸኛ መሆኑንና በእነዚህ ነገሮች ምንም አይነት ተጋሪ የሌለው መሆኑን አምኖ ብቸኛ ማድረግ ማለት ነው፡፡
➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጾቹ የሚከተለውን ተናግሯል፡
▪️قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ ۚ
“የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?” በላቸው፡፡ “አላህ ነው” በል፡፡ አር ረዕድ (16)
◀قُل لِّمَنِ الْأَرْضُ وَمَن فِيهَا إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ ◆سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ◆قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ ◆سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ◆قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ
➲“ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትሆኑ (ንገሩኝ)” በላቸው፡፡ “በእርግጥ የአላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “ታዲያ አትገሰጹምን?” በላቸው፡፡“የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?”በላቸው፡፡ “በእርግጥ አላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “እንግዲያ አትፈሩትምን?” በላቸው፡፡ “የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው?የምታውቁ እንደሆናችሁ (መልሱልኝ) በላቸው፡፡ አል ሙእሚኑን፡(84__88)
▪️ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ فَتَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ
“ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ፡፡” ጋፊር፡64
➧ሁለተኛው ክፍል፡ ተውሒዱል አስማእ ወስ'ሲፋት በቁርኣን በሐዲስ በመጡ መልካም ስሞቹና ከፍተኛ የሆኑ መገለጫዎች አላህን ብቸኛ ማድረግ ማለት ነው፡፡
➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጾቹ የሚከተለውን ተናግሯል፡
▪️اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ
“አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት፡፡”
ጦሃ፡(8)
◀قُلِ ادْعُوا اللَّهَ أَوِ ادْعُوا الرَّحْمَٰنَ ۖ أَيًّا مَّا تَدْعُوا فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ
➧አላህን ጥሩ ወይም አር'ረሕማንን ጥሩ ፤ (ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ (መልካም ነው)፡፡ ለእርሱ መልካም ስሞች አሉትና” አል ኢስራእ (110)
▪️هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ ۖ هُوَ الرَّحْمَٰنُ الرَّحِيمُ ◆هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ ◆هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
➧እርሱ አላህ ነው ፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ ፤ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የሆነ ነው፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ ነው፡፡ እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ ፤ ንጉሱ ከጉድለት ሁሉ የጠራው ፣ የሰላም ባለቤቱ ፣ ጸጥታን ሰጭው ፣ ባሮቹን ጠባቂው ፣ አሸናፊው ፣ ሃያሉ ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊና ጥበበኛም ነው፡፡”ሐሽር፡(22__24)
〰 〰 〰 〰 〰 〰 〰
◉
◉
◉
◉✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል
✍ኑርአህመድ
【አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል】
➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
➴ https://t.me/httpsLatahzen

🔹ሰላትን አደራ!🔹
ወደ አላህ መሸሻ:
አጅር ያለው ጉርሻ:
የሩህ መናፈሻ:
የመንፈስ ማደሻ:
ጎዶሎን መካሻ:
ወደ አላህ ማልቀሻ:
ለሌላ ዒባዳ ቀልብን ማነሳሻ:
🍀
ቀልብህ እንዲራራ:
እንዳይሆን መራራ:
በሀራም በረራ:
ከፉጃሮች ተራ:
እኔም በዚው ላብቃ ብዙ ሳላወራ:
ወንድሜ ልምከርህ ሰላትን አደራ!!
✍ኑርአህመድ
ወደ አላህ መሸሻ:
አጅር ያለው ጉርሻ:
የሩህ መናፈሻ:
የመንፈስ ማደሻ:
ጎዶሎን መካሻ:
ወደ አላህ ማልቀሻ:
ለሌላ ዒባዳ ቀልብን ማነሳሻ:
🍀
ቀልብህ እንዲራራ:
እንዳይሆን መራራ:
በሀራም በረራ:
ከፉጃሮች ተራ:
እኔም በዚው ላብቃ ብዙ ሳላወራ:
ወንድሜ ልምከርህ ሰላትን አደራ!!
✍ኑርአህመድ
📖እውቀትን ላወቀ📖
እውቀት ብርሀን ነው:
የእውነት ለተረዳው:
ኻሊቁ ላቃናው:
ለሀቁ ላገራው።
የሰው ልጅ ህይወቱ:
ያለ እውቀት ነው ከንቱ:
በተለይ ለሙስሊም:
ለሱ እንደ እውቀት የለም:
ዱንያዊቷም አለም:
መዝርያ ለዘላለም:
እንደሆነች አውቆ:
ከሀራም እርቆ:
ለእውቀት ተጨንቆ:
ለመቅራት ተዋድቆ:
ምርጥ ሀሳብ ሰንቆ:
እንደዚህ ነው ማወቅ:
ራስህን አርገህ ዝቅ:
ለአኼራህ ሰንቅ:
ከእሳት ለመጠንቀቅ:
በጀነት ለመላቅ:
ዝምምም ብሎ ማወቅ:
ወንድሜ አስተውለው:
ኡስታዝህስ ማነው:
ያ ሀቅ የተማረው?
አቂዳው የነፃው?
ከሽርክ ቢድዓው:
አብዝቶ የራቀው?
ወይንስ ሌላኛው ነው?
ቅጠል የሚበላው:
ስሜት ያታለለው:
በምርቃና ሲለው:
ኻሊቅ ሚሰራራው:
ኧረ የትኛው ነው?
አስተውለህ ምረጠው!?
ሗላ ላይ እንዳቶን ከልብ የሚቆጨው።
ከዚም በመቀጠል:
ኒያ ነው ሚከተል:
ኒያን ያሳመረ:
ሀሳቡ ሰመረ:
ካልተጭበረበረ:
ከነፈ በረረ በእውቀት አበረ:
አላህ እውቀት ይስጠን:
ብለን ዱዓ አድርገን:
እሱም ተቀብሎን:
በእውቀት አልቆን:
ከእሳቱ አርቆን:
ጀነት አስገብቶን:
በፊርደውስ አኑሮን:
የሱን ፊት ያሳየን።
ጌታችን ሆይ አሚን
✍ኑርአህመድ
እውቀት ብርሀን ነው:
የእውነት ለተረዳው:
ኻሊቁ ላቃናው:
ለሀቁ ላገራው።
የሰው ልጅ ህይወቱ:
ያለ እውቀት ነው ከንቱ:
በተለይ ለሙስሊም:
ለሱ እንደ እውቀት የለም:
ዱንያዊቷም አለም:
መዝርያ ለዘላለም:
እንደሆነች አውቆ:
ከሀራም እርቆ:
ለእውቀት ተጨንቆ:
ለመቅራት ተዋድቆ:
ምርጥ ሀሳብ ሰንቆ:
እንደዚህ ነው ማወቅ:
ራስህን አርገህ ዝቅ:
ለአኼራህ ሰንቅ:
ከእሳት ለመጠንቀቅ:
በጀነት ለመላቅ:
ዝምምም ብሎ ማወቅ:
ወንድሜ አስተውለው:
ኡስታዝህስ ማነው:
ያ ሀቅ የተማረው?
አቂዳው የነፃው?
ከሽርክ ቢድዓው:
አብዝቶ የራቀው?
ወይንስ ሌላኛው ነው?
ቅጠል የሚበላው:
ስሜት ያታለለው:
በምርቃና ሲለው:
ኻሊቅ ሚሰራራው:
ኧረ የትኛው ነው?
አስተውለህ ምረጠው!?
ሗላ ላይ እንዳቶን ከልብ የሚቆጨው።
ከዚም በመቀጠል:
ኒያ ነው ሚከተል:
ኒያን ያሳመረ:
ሀሳቡ ሰመረ:
ካልተጭበረበረ:
ከነፈ በረረ በእውቀት አበረ:
አላህ እውቀት ይስጠን:
ብለን ዱዓ አድርገን:
እሱም ተቀብሎን:
በእውቀት አልቆን:
ከእሳቱ አርቆን:
ጀነት አስገብቶን:
በፊርደውስ አኑሮን:
የሱን ፊት ያሳየን።
ጌታችን ሆይ አሚን
✍ኑርአህመድ
Forwarded from Deleted Account
ከእሳት ለመጠበቅ!
....ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿اتَّقُوا النّارَ ولو بشِقَّةِ تَمْرَةٍ، فمَن لَمْ يَجِدْ شِقَّةَ تَمْرَةٍ فَبِكَلِمَةٍ طَيِّبَةٍ﴾
“በግማሽ ቴምርም ቢሆን የጀሃነምን እሳት ተከላከሉ። ግማሽ ቴምር ማታገኙ እንኳ ቢሆን መልካም በመናገር ተከላከሉ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 3595
┄┄┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉┄┄