La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
''ሂጃብ ነው ውበትሽ''

ቢስሚላሂ ብዬ፣በስሙ ልጀምር
ለአላህ ይገባው፣ምስጋናና ክብር

ያሄራዋ እህቴ፣የያዝሽው ውብ መንገድ
የአላህ ሰላምታ፣በአንቺ ላይ ይውረድ

እስቲ ትንሽ ስሚኝ፣እንመካከር
ስለሂጃባችን፣እኛው እንዘክር

ባለንበት ሀገር፣በአሁኑ ዘመን
እኛን ለፈተና፣ሞልቶአል ሚጋብዘን

መሰልጠን እያሉ፣ብሎም እኩልነት
እርቃናችን እንድኔድ፣ይለፋሉ በእውነት

እኛ ግን እህቴ፣ከቶ አንሰማቸውም
የመጣው ቢመጣ፣ሂጃብን አንተውም

ምራቅ ቢተፉብን፣በምላስ ቢዘልፉን
እንዳንቀሳቀስ፣መንገድ ቢዘጉብን
አንቺ ድንኳን ለባሽ፣የተጨኮንሽ ቢሉን
ብሎም ለመኮነን፣አሸባሪ ብለው እኛን ቢሰይሙን
ቆራጥ ይሁን አቋማችን፣ያሉትንም ይበሉን
አድምጭኝ እህቴ
ሙስሊም በመሆንሽ፣ሂጃብ በመልበስሽ
ከስራ ከትምህርት፣ካገር ቢያስወጡሽ
አብሽር አትዘኚ፣ፈፅሞ አይክፋሽ
ሁሉንም ተመልካች፣አራህማን አለልሽ

ይልቅ ብለሽ በይው

አትንካው ሂጃቤ፣የኔነቴ አርማ
የፈገግታዬ ምንጭ፣የውበቴ ግርማ
አላህ ነው ያዘዘኝ፣አርሃመ ሩሃማ
ከቶ አልሰማህም፣አትምጣ በሱማ

በአራህማን ትእዛዝ፣አልደራደርም
እምነቴን ሆኜ እንጂ፣አስመስዬ አልኖርም

ኢስላሜ ድንቅ ነው፣ውድ አርጎ ይዞኛል
በሂጃብ ሸፍኖ፣ከመጥፎ አርቆኛል
ሳልሞት ከመቀበር፣ኢስላም አድኖኛል
አልሃምዱሊላሂ፣አላህ አልቆኛል
ከአይን በሽታ፣እሱ ሰትሮኛል
ደግሞም ሲያድለኝ፣ሙስሊም አድርጎኛል

በይው አስደንግጭው፣ከቶ አታድምጭው
ሊገልሽ ሲመጣ፣ቀድመሽ አንቺ አምልጭው

እናማ እህቴ፣እኔ የምነገርሽ
በሙሉ ኩራት፣ልበሽው ሂጃብሽ
እርቃንሽ አትውጪ፣ለሰው ወሬ ብለሽ
ሂጃብ ነው ውበትሽ፣ሂጃብ ነው ህይወትሽ
በዱንያም በአሄራም፣ነፃ የሚያወጣሽ
ከፈጠረሽ አላህ፣የሚያስታርቅሽ
አው እሱ ብቻ ነው፣ጀነትን ለማግኘት ሰበብ የሚሆንሽ
ካንቺ በላይ ባላውቅ፣አውቄም ባልሰራ
የምነግርሽ ይህ ነው፣ሂጃብሽ አደራ

እርቃንሽ አትውጪ፣ለብሰሽ ብጣቂ ጨርቅ
እንደ ሻኛ አይቁ፣ይውረድ ፀጉርሽ ይውደቅ

ልበሽው ጅልባብሽ፣ደርቢው ኒቃብሽ
እመኚኝ እህቴ፣እሱ ነው ውበትሽ
ደብቂው ውብገላሽ፣ያ ጅብ እንዳይበላሽ
ባመረ መሳይ ቃል፣እንዳይሸነግልሽ
የጠቀመሽ መስሎ፣በቁም እንዳይቀብርሽ

ለሂጃብ ስትለፊ፣ወድቀሽ ስትነሺ
አላህ ዘንዳ ላንቺ፣ጂሀድ ነው አትርሺ
የትላንት ጀግኖች፣ሶሀቦች አስታውሺ
የነሱን አርአያ፣ፈለግ ተላበሺ

በሂጃብ አብቢ፣በሂጃብ ድመቂ
በሱ ተሰተሪ፣በሱ ተደበቂ
አምረሽ እንድትታይ፣ሂጃብን አጥልቂ
ጀነት እንድታገኝ፣ሂጃብን ጠብቂ

አላህ ይሰትረን፣እኔንም አንቺም ንግግሬን ቋጨሁ
ወቢላሂ ተውፊቅ፣አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ

بنت قمر
አሁን ደሞ አንድ ምክር ጀባ ልበላቹ


9ቁጥር 8 ቁጥርን በጥፊ መታው 8 ለምን ትመታኛለህ ብሎ ሲጠይቀው ከኔ በታች ሰለሆንክ ብሎት እርፍ
ይሄን የሰማ 8 ቁጥር 7 ቁጥርን በጥፊ ይመተዋል ምን አደረኩኝ ቢለው ከኔ በታች ስለ ሆንክ ይለዋል
ሰባትም በተራው ስድስትን ስድስትንም አምስትን አምስት አራትን አራት ሶስትን ሶስት ሁለትን ሁለት አንድን የበታቼ ነህ እያሉ ይመቱ ጀመር ።
ከሁለት ቁጥር የመመታት አደጋ የደረሰበት አንድ ቁጥር 0 ሊመታ አሰበና ለምን በፍቅር አላሸንፈውም ብሎ ና ከጎኔ ቁም ቢለው 10 ሆኑና ልቀው ታዩ ።

ከፍቅር የማይገኝ ትርፍ የለም!!
ላስተዋለና ላስተነተነ ሰው ሁሉም የአላህ ፍጡር የእራሱን የሆነ ልዩ ውበት አለው !🍃🍂
ከሰው ልጆች መካከል ግን አንጸባራቂውና በውበት ላይ ውበትን የሚጨምረው ያ! በመልካም ሥነ-ምግባር የታነጸው ብቻ ነው... !🍃🍂
አንት የሱና ወጣት የት ላይ ነው ያለህው⁉️

እየቀራህ ነው⁉️

እየተማርክ ነው⁉️

ቤትሰብ እየረደህ ነው⁉️

ትዳር እየመራህ ነው⁉️

ደዕዋ እያደክ ነው⁉️

እየነገድክ ነው⁉️

እያረስክ ነው⁉️

ሙያ እየለመድክ ነው⁉️

👉ወይስ👈

ቦዝነሃል⁉️

ስራ ፈተሃል⁉️

ቂርአት ትተሃል⁉️

ከመስጊድ ቀርተሃል⁉️

ደዕዋ አቁመሃል⁉️

ማንበብ ትተሃል⁉️

መማር ትተሃል⁉️

ትዳር ፈተሃል⁉️

በጥቅሉ>=

ጓደኛህ ማን ነው⁉️

ስራህ ምንድነው⁉️

መዋያህ የት ነው⁉️

ማደሪያህ የት ነው⁉️

አላማህ ምንድን ነው⁉️

መልስ ከሁላችንም ይጠበቅብናል አሁን ላይ ታውቃላቹህ ⁉️

የትምህርት ተቋማቶች ተዘግተው

መድረሳዎች ተዘግተው

አብዛኞቹ የስራ መስኮች ተዘግተው

የመንግስት ቢሮዎች ተዘግተው ነው ያሉት

ታዲያ በዚህ ጊዜ ቦዘኔው ስራ አጡ ሌባው አጭበርባሪው ይበዛል ያኔ ታዲያ አንተ ምን ማድረግ አለብህ⁉️

ጓደኛ መምረጥ

ትንሽም ብትሆን ስራ መፍጠር

ውስጥ ለውስጥም ቢሆን ደርሶችን አፈንፍነህ መከታተል

ዒባዳ ላይ ትኩረት ማድረግ ወደ አሏህ የሚያቃርብህን ነገር ፈልገህ መስራት ባገኘህው አጋጣሚ ሱናን ለህዝብህ ለማድረስ ቀና ደፋ በል

አሏህ በመልካም እንቅስቃሴዎች ሁሉ ይረዳሃል
@strong_iman
ትንሽ እንተዋወስ
ጊዜ ወስደን እናስብ፣ እናስተንትን፡፡ ከ100 ዓመት በኋላ የት ነን ብለን እንጠይቅ
እስቲ፡፡ ሁላችንም ምድር ላይ የለንም፡፡ አድራሻ እንቀይራለን፡፡ ከቀደሙንም ሆነ
አብረውን ካሉ ወዳጆችና ዘመዶች ጋር መሬት ሥር እንሆናለን፡፡ አዎን ብንፈልግም
ባንፈልግም፣ ብንወድም ባንወድም መሬት ሥር ነን፡፡ በዘመናት ልፋት የገነባነውን
ቤታችንን ሰው ይገባበታል፡፡ ላባችን ጠብ አድርገን ያፈራነዉን ንብረታችን ሌላ
ሰው ይወርሰዋል፡፡ ምናልባት ፈጽሞ የማናውቀው ሰው፡፡
ለምሳሌ አሁን እኛ ወረስን ብለን የምንኖርበትን ቤት ከየት ነው እንዳመጣነው
እንጠይቅ፡፡ አያታችን ቀይ ይሁን ጥቁር የማናውቅ ስንቶቻችን ነን!፡፡ አዎ ሁላችንም
እንዲሁ ነን፡፡ በጊዜ ብዛት ተረሺዎች ነን፡፡ በሥራው ሕያው የሆነ አላህ ያለለት
ጥቂት ሰው ሲቀር፡፡
እና ታዲያ ሰውን ለምን እንገፋለን? አላህ የሚረዝቃቸዉን ሰዎች ለምን ለማየት
እንጠላለን ? ፡፡ ከፍጥረተ ዓለሙ አንፃር ስንታይ እኛ እኮ ምንም ነን፤ ወላሂ
ምንም፡፡ የዱንያ ላይ ቆይታችንም ዐይን ከፍቶ የመዝጋት ያህል ትንሽ ነው፡፡ ከኛ
በኋላ ሌሎች ትውልዶች ይመጣሉ፡፡ ዱንያ የኛ ብቻ አይደለችም፡፡ ዘላለማዊ
አገርም አይደለችም፡፡ ሁሉም እየተጣደፈ ይመጣል፣ እየተጣደፈም ይሄዳል፡፡
የሕይወትን ባንዲራ ለባለተራው ያስረክባል፡፡ ያዉም ያሰበዉን ምኞቱን ሩቡን ያህል
እንኳ ሳያሳካ ዕቅዱን በዉስጡ እንደያዘ ይሞታል፡፡
ስለሆነም ራሣችንን ሁሌም ማስታወስ ይኖርብናል፣ ዱንያ እኮ ዱንያ ናት፣ እኛ እኮ
ሟቾች ነን፡፡
ልካችንን መረዳት፣ የዕድሜያችንን አጭርነት ማወቅ ግድ ይለናል፡፡ ወላሂ
ከምናስበው በታች ነን፡፡ በጣም!
ከዱንያ ቀናት በአንዱ ቀን እዚህ ጨለማ ዉስጥ ብቻችንን እንሆናለን፡፡ ያኔ ዱንያ
በርግጥም ምን ያህል አጭር እንደሆነች እንረዳለን ፡፡ ምኞታችን ከንቱ እንደነበርም
እናውቃለን፡፡ ያኔ ምናለ የዱንያ ላይ ሙሉ ዕድሜያችንን በመልካም ሥራ አሳልፈን
በሆን ኖሮ ማለታችን አይቀርም፡፡
ኢላሂ ኻቲማችን ባንተ እጅ ነው..!!!
ከጥርጣሬ ራቅ!
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በኾነው፡፡
እስልምናችን ካስተማረችን ጥሩ ስነ-ምግባራት ኣንዱ ከጥርጣሬ መራቅን ነዉ፡፡
አላህ(ሱወ) እንዲህ ይለናል :-
ﻳَٰٓﺄَﻳُّﻬَﺎ ﭐﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺀَﺍﻣَﻨُﻮﺍ۟ ﭐﺟْﺘَﻨِﺒُﻮﺍ۟ ﻛَﺜِﻴﺮًﺍ ﻣِّﻦَ ﭐﻟﻈَّﻦِّ ﺇِﻥَّ ﺑَﻌْﺾَ ﭐﻟﻈَّﻦِّ ﺇِﺛْﻢٌۖ ﻭَﻟَﺎ ﺗَﺠَﺴَّﺴُﻮﺍ۟ ﻭَﻟَﺎ ﻳَﻐْﺘَﺐ ﺑَّﻌْﻀُﻜُﻢ
ﺑَﻌْﻀًﺎۚ ﺃَﻳُﺤِﺐُّ ﺃَﺣَﺪُﻛُﻢْ ﺃَﻥ ﻳَﺄْﻛُﻞَ ﻟَﺤْﻢَ ﺃَﺧِﻴﻪِ ﻣَﻴْﺘًﺎ ﻓَﻜَﺮِﻫْﺘُﻤُﻮﻩُۚ ﻭَﭐﺗَّﻘُﻮﺍ۟ ﭐﻟﻠَّﻪَۚ ﺇِﻥَّ ﭐﻟﻠَّﻪَ ﺗَﻮَّﺍﺏٌ ﺭَّﺣِﻴﻢٌ
49:12:" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! # ከጥርጣሬ_ብዙውን_ራቁ ፤
# ከጥርጣሬ_ከፊሉ_ኃጢአት_ነውና ፡፡ ነውርንም አትከታተሉ፡፡ ከፊላችሁም ከፊሉን
አይማ፡፡ አንደኛችሁ የወንድሙን ስጋ የሞተ ኾኖ ሊበላው ይወዳልን? (መብላቱን)
ጠላችሁትም፤ (ሐሜቱንም ጥሉት)፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ
ነውና፡፡
ታላቁ ነብያችንም እንዲህ ይሉናል " ﺇﻳﺎﻛﻢ ﻭﺍﻟﻈﻦ ﻓﺈﻥ ﺍﻟﻈﻦ ﺃﻛﺬﺏ ﺍﻟﺤﺪﻳﺚ "
"ከጥርጣሬ ራቁ ! ጥርጣሬ የዉሸት ወሬ ነዉ"ብለዉናል፡፡
በጥርጣሬ ፣ በመሰለኝና ደሳለኝ ብዙ ከምናወራ እራሳችንን ብንቆጥብ መልካም
ይሆንልናል፡፡ በተለይ በቅርቡ በሃገራችን በተከረተዉ ነገር ላይ ብዞዎቻችን
በጥርጣሬ ዉስጥ ተዘፍቀን እየተራራቅን እንገኛለን፡፡ ነገር ግን ይህ የመጨረሻ
ዉርደት ነዉ፡፡ በጥርጣሬ ከምንሮጥ ረጋ ብለን ብንረዳዳ መልካም ነዉ፡፡
አላህ ከመጥፎ አረዳድ ፣ ከወረዱት አስተሳሰብና ከመጥፎ ነገራት በሙሉ
ይጠብቀን፡፡አሚን!
ይሄን መልዕክት የምታስተላልፉ አላህን ፍሩ ከ ➓ ከ➎ በኋላ መልካም ነገር ትሰማላቹህ ታያላቹህ እያላቹህ የምትለቁ
ምክኒያቱም ገይብን እናቃለን ያላቹህ ነዉ ከ ➓ ከ➎ ደቂቃ የሚሆነዉ ነገር ምን አሳወቃቹህ ?

አላህ ሱበሀነ ወታአላ
እንዲህ ይላል

۞ وَعِندَهُ مَفَاتِحُ الْغَيْبِ لَا يَعْلَمُهَا إِلَّا هُوَ ۚ وَيَعْلَمُ مَا فِي الْبَرِّ وَالْبَحْرِ ۚ وَمَا تَسْقُطُ مِن وَرَقَةٍ إِلَّا يَعْلَمُهَا وَلَا حَبَّةٍ فِي ظُلُمَاتِ الْأَرْضِ وَلَا رَطْبٍ وَلَا يَابِسٍ إِلَّا فِي كِتَابٍ مُّبِينٍ

[ ሱረቱ አል-አንዓም፣ - 59 ]
የሩቅ ነገርም መክፈቻዎች እርሱ ዘንድ ናቸው፡፡ ➤🌸ከእርሱ በቀር ማንም አያውቃቸውም🌸፡፡ በየብስና በባሕር ያለውንም ሁሉ ያውቃል፡፡ ከቅጠልም አንዲትም አትረግፍም የሚያውቃት ቢኾን እንጅ፡፡ ከቅንጣትም በመሬት ጨለማዎች ውስጥ የለም ከእርጥብም ከደረቅም አንድም የለም ግልጽ በኾነው መጽሐፍ ውሰጥ (የተመዘገበ) ቢኾን እንጅ፡፡


ከመልክቶች መካከል ለምሳሌ
ያክል
👇👇👇👇👇👇

አሰላሙ አለይኩም
ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
*የአላህ ስም *
/አል ረህማኑ /
/አል ማሊኩ/
/አል ቁዱሱ/
/አል አሀዱ/
/አል ሰመዱ/
/ አል ረዛቁ/
/አል ከሪሙ/
ይህን የአላህ ስም ለ9 ሰው ከላክ በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያስደስት ነገር ታያለህ ትደሰታለህ እንደቀልድ ካየሀው ደግሞ 9 አመት ቻንስ ታጣለህ ቶሎ ብለህ ለምትወደው ሰው ላክ አላህ ከአንተጋ ከአንቺጋ ይሁን አሚን


አሰታዉሉ ወንድም እህቶቼ
Forwarded from ikhlas Tube (Mᴜᴀᴢ)
#የዛሬ_3_ምርጥ_ምርጥ_መክሮች

〽️የምታውቀውን ሁሉ መናገር ላይጠበቅብህ ይችላል የምትናገረውን ሁሉ ግን ማወቅ አለብህ

〽️ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ለሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ

〽️ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም
ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ እንጂ

መልካም ሰኞ ተመኘሁላቾሁ
@ikhlasstudents
@ikhlasstudents
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ስድስት

➠በርካታ ሰለፎች የሚከተለውን ይናገሩ ነበር፡
"ليتني أنجو من علمي – يقصد من العلم الذي تعلمه – كفافا ، لا لي ، ولا علي"

“ለእኔም ሳይኖረኝ በእኔም ላይ ሳይኖር ከእውቀቴ (ሳልጠየቅ) ነጻ ብሆን እመኛለሁ፡፡”

➛በዚህም ፣ ሰለፎች የተስተካከለ እውቀትና ተግባር እያላቸው ምን ያክል አላህን እንደሚጠነቀቁና እንደሚፈሩ ያመላክታል፡፡

▪️ሀሰን አል'በስርይ -ረሂመሁሏህ- የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"إن المؤمن جمع بين إحسان ومخافة ، والمنافق جمع بين إساءة وأمل"

“ሙእሚን መልካምንና ፍርሀትን አጣምሮ ይዟል፡፡ ሙናፊቅ ደግሞ ክፉ ስራንና መልካም ተስፋን አጣምሮ ይዟል፡፡” አዝ ዙህድ ሊብኒ አል ሙባረክ፡985

▪️ዓብደሏ ብን አቢ'ሙለይካ -ረሂመሁሏህ- ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል፡-
"أدركت أكثر من ثلاثين صحابيا كلهم يخاف النفاق على نفسه"

➤“ሁሉም ኒፋቅን በነፍሳቸው ላይ የሚፈሩ ከሰላሳ የሚበልጡ ሶሃቦችን አግኝቻለሁ፡፡”ቡኻሪ በሶሂህ ታባቸው ኪታቡ አል ኢማን ባቡ ኸውፉል ሙእሚን ላይ በተዕሊቅ አውርትታል

➲ለአማኞች በአንድ ላይ ሁለት ታላላቅ ደረጃዎችን አጣምሮላቸዋል፡፡ በመልካም መታዘዝንና ያማረ ተግባርን እየሰሩ ስራችንን ከእኛ አይቀበልም ብለው አላህንእንዲፈሩ አድርጓቸዋል፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል

وَالَّذِينَ يُؤْتُونَ مَا آتَوا وَّقُلُوبُهُمْ وَجِلَةٌ أَنَّهُمْ إِلَىٰ رَبِّهِمْ رَاجِعُونَ

እነዚያም የሚሰጡትን ነገር እነርሱ ወደ ጌታቸው ተመላሾች መኾናቸውን ልቦቻቸው የሚፈሩ ኾነው የሚሰጡት፡፡አል ሙዕሚኑን 60

➲“እነዚህ አስካሪ መጠጥ የሚጠጡ ፣ ዝሙት የሚፈጽሙ ፣ የሚሰርቁ ናቸው?” በማለት ስለዚህ ቁርኣናዊ አንቀጽ ትርጓሜ ረሡልን صلى الله عليه وسلم ጥያቄ አቀረብኩላቸው ትላለች ዓኢሻ ረድየሏህ አንሃ ረሡልም صلى الله عليه وسلم፡ - “አይደለም፣ የ (አቡበክር) ሲዲቅ ልጅ ሆይ! ነገር ግን እየጾሙ፣ እየሰገዱ ፣ እየሶደቁ ከእነርሱ ይህን መልካም ስራችንን አላህ ላይቀበለው ይችላል ብለው ስጋት ያደረባቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች በመልካም የሚሽቀዳደሙ ናቸው፡፡” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ አህመድ፡25263 ቲርሚዚይ፡ 3175ኢብኑ ማጀህ፡4198

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናገረ፡

وَإِسْمَاعِيلُ رَبَّنَا تَقَبَّلْ مِنَّا ۖ

“(ኢብራሂምና) ኢስማኢልም “ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበል፡፡” አል በቀራህ፡127

➧ውሀይብ ብን አልወርድ- ረሂመሁሏህ- ይህን የቁርኣን አንቀጽ አነበበና አለቀሰ፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ተናገረ፡-

"يا خليل الرحمن ترفع قوائم بيت الرحمن وأنت مشفق أن لا يقبل منك!"

➭“የአላህ ወዳጅ (ኢብራሒም) ሆይ! የአላህን ቤት መሰረቶች ከፍ ታደርጋለህ፡፡
እንደገና ይህን ስራየን አላህ ላይቀበለኝ ይችላል ብለህ ትጨነቃለህ፡፡” ተፍሲር ኢብኑ ከሲር፡1/206


ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ
ኑርአህመድ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሰባት
➛➛➛➛➛➛

➲ሶስተኛው፡- በእውቀቱ ለማይሰራ ሰው የተላለፈ ዛቻና ማስጠንቀቂያ ባወቁት የማይሰሩ ሰዎች ዛቻና ውግዘት በቁርኣንና በሐዲስ ደርሶባቸዋል፡፡ አላህበተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لِمَ تَقُولُونَ مَا لَا تَفْعَلُونَ◆كَبُرَ مَقْتًا عِندَ اللَّهِ أَن تَقُولُوا مَا لَا تَفْعَلُونَ
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! የማትሰሩትን ነገር ለምን ትናገራላችሁ? የማትሰሩትን
ነገር መናገራችሁ አላህ ዘንድ መጠላቱ ተለቀ፡፡” አስ ሶፍ፡2_3

۞ أَتَأْمُرُونَ النَّاسَ بِالْبِرِّ وَتَنسَوْنَ أَنفُسَكُمْ وَأَنتُمْ تَتْلُونَ الْكِتَابَ ۚ أَفَلَا تَعْقِلُونَ

“እናንተ መጽሐፉን የምታነቡ ሆናችሁ ሰዎችን በበጎ ስራ ታዛላችሁን?
ነፍሶቻችሁንም ትረሳላችሁን?” አል በቀራህ፡44
▪️ስለ ሹዓይብ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል


وَمَا أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَا أَنْهَاكُمْ عَنْهُ

“ከርሱ ወደከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡” ሁድ 88

▪️በዚህ ርዕስ ዙሪያ የቁርኣን ማስረጃዎችን ካቀረብን በኋላ ከሐዲስ ማሰረጃዎችደግሞ የሚከተለውን እናቅርብ፡-

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ኡሳማ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን የረሡል صلى الله عليه وسلم ሐዲስ አስተላልፏል፡- “የትንሳኤ ቀን አንድ ግለሰብ ተይዞ ይመጣና እሳት ውስጥ ይጣላል፡፡ አህያ እየዞረ ወፍጮውን እንደሚያንቀሳቅሰው ይህ ሰው በአንጀቱ እየተጎተተ በጀሀነም እሳት ይዞራል፡፡
የእሳት ሰዎች ይመጡና “እከሌ ሆይ! ምን ሆነህ ነው?! በመልካም ስታዘን ከመጥፎ ስትከለክለን አልነበርክም እንዴ?!” ይሉታል፡፡ ግለሰቡም “አዎ! በመልካም አዝዣችሁ እኔ አልፈጽመውም ነበር፡፡ ከመጥፎ ከልክያችሁ ደግሞ እፈጽመው ነበር” በማለት ይመልስላቸዋል፡፡ ቡኻሪ፡3267 ሙስሊም፡ 2989

▪️በኢማም አህመድ “ሙስነድ” ኪታብ አነስ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

➲“ነብዩ صلى الله عليه وسلم ኢስራእ በተጓዙበት ሌሊት ሰዎች ከእሳት በሆነ መጋዝ አፋቸውና ከንፈራቸው ሲተለተል ተመለከቱ፡፡ “እነዚህ እነማን ናቸው?” በማለት ረሡል ጠየቁ፡፡(ሁለቱ መላኢካዎች) “እነዚህ ከኡመትህ (ከተከታዮችህ) ኸጢቦች (ምክር
ሲመክሩ የነበሩ) ናቸው፡፡ የአላህን ኪታብ ያነባሉ ሰዎችን በበጎ ነገር ያዛሉ ነፍሳቸውን ግን ይረሳሉ፡፡ …” አህመድ፡13515 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል አስ ሶሂህ፡291

➧በእውቀታቸው ስለማይሰሩ ፤ ሰዎችን ጥሪ እያደረጉ ስለማይተገብሩ ሰዎች በቁርኣን እና በሐዲስ በርካታ ዛቻዎች መጠዋል፡፡ በእውቀታቸው ሰውን የሚጠቅሙ ነገር ግን እነርሱ ምንም የማይጠቀሙ በርካታ ሰዎችም አሉ። የእነዚህ ሰዎች ምሳሌ ልክ እንደሻማ ነው ፤ ሻማ ለሌላው እያበራ እራሱን ያቀልጣል፡፡

➛ይህን አስመልክቶ አላህን ተገዥና ታማኝ የሆነው ታላቁ ታብዒይ ሙጦሪፍ ብን ዓብዲላህ ብን አሽኺር -ረሂመሁሏህ- ከዚህ ነገር በአላህ ይጠበቅ ነበር፡፡

▪️በዱዓው ውስጥ የሚከተለውን ይናገር ነበር፡-
"اللهم إني أعوذ بك أن يكون أحد أسعد بما علمتني مني، وأعوذ بك أن أكون عبرة لغيري"

“አላህ ሆይ! አንድ ሰው ለእኔ ባሳወከኝ እውቀት ከእኔ የበለጠ እድለኛ ሆኖ ለሌሎች መመከሪያ ከመሆን በአንተ እጠበቃለሁ” ኢማሙ አህመድ ፊዙህድ፡1358

➠ይህ ታላቅ ዱዓ ነው፡፡ ሸይኹል ኢስላም ብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - ይህን ዱዓ “ከዱዓዎች ሁሉ ምርጥ ዱዓ” በማለት ያወድሱት ነበር፡፡ መጅሙዕ አል ፈታዋ፡14/307



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ
ኑርአህመድ
➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ
እናት............ክፉ አይንካት 💕💕💕
እናት............ሁሌም ደስ ይበላት 😘😘
እናት............ፍቅር ይክበባት 😍😍
እናት..........እድሜዋን እልፍ ያድርግላት😍
እናት............የምትሰጠው አያሳጣት😍😍
እናት.............ፈገግታዋ አይለያት😍😍😍
እናት.............ጭንቀት አያግኛት😍😍😍😍
እናት............ ሰላሟ ይብዛላት😍😍😍😍😍
እናት............ጤናዋ ይትረፍረፍላት😍

🥀🥀🥀🥀🥀
ከሴቶች ሁለት ነገርን ተጠንቀቁ!
አንደኛ፦ ድግምት!
ድግምት ቋጣሪዎች አብዛኛዎቹ ሴቶች ናቸው። በተለይ ከትዳርና ገንዘብ ጋር
በተገናኘ እስከ እብደት የሚደርስ ድግምት ይሰራሉ። ባሎቻቸውን በፍቅር ለመያዝ
ብለው በድግምት ለሞት የዳረጉም እንዳሉ ይታወቃል። አላህ ይህንን ሲገልፅ
እንዲህ አለ፡-
‹‹በል! በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ። ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት።
ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤ በተቋጠሩ ክሮች ላይ ተፊዎች ከሆኑት ደጋሚ
ሴቶችም ክፋት።›› (ፈለቅ 1-4)
ሁለተኛ፡- ውለታ-ቢስነት!
አብዛኛዎቹ ሴቶች ውለታ-ቢስ ናቸው። ከአፈር አንስቶ ለወግ ያቃቸውን ሰው
በትንሽ ግጭት ማንነቱን እስከመካድ ሊደርሱ ይችላሉ። ነቢዩ (ዐሰወ) ስለዚህ
ሲናገሩ፡-
‹‹ጀነት ሄድኩኝ፤ ወራሾቿ አብዛኛዎቹ ደሃዎች ናቸው። ጀሐነም ወረድኩኝ! ነዋሪዎቿ
አብዛኛዎቹ ሴቶች ናቸው። አሉ። ሰሃባዎችም፦ በአላህ አያምኑም እንዴ? አሏቸው።
ነቢዩም (ዐሰወ) አይደለም! በጌታቸው ያምናሉ ነገርግን ባሎቻቸው በደግ ጊዜ
ያደረጉላቸውን ውለታ ክፉ ቀን ሲመጣ ከአንተ አንድም ደግ ነገር አግኝቼ
አላውቅም በማለት ስለሚክዷቸው ነው። አሉ።›› (ቡኻሪ 29)
እርግጥ ይህ ሁሉንም ሴቶች አይገልፅም። ተመሳሳዩን የሚያደርጉ ከወንዶችም
አሉ። ሴቶች በጀሐነም ቁጥራቸው ቢበዛም እንዲሁ በጀነትም ሴቶች ይበዛሉ።
ነገርግን እነዚህን ሁለት አስከፊ የሴቶች መለያ ባህሪ ማወቁ ለወንዶች
ትዳራቸውን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው ይጠቅማቸዋል ብዬ ነው።
አንድ ቀን ቀትር ላይ ነቢዩ (ዐሰወ) ከቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ ዑመር (ረዐ) እና
ሌሎች ሰሃባዎች ሊጠይቋቸው መጡ። ነቢዩም (ዐሰወ) ከመኝታቸው ሲነሱ
የዘንባባው ቅርንጫፊ ከሰውነታቸው ላይ ሰንበር ሰርቶ ይታይ ነበር። ዑመር (ረዐ)
በጣም አዘነና ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለምን ሌሎች ንጉሶች እንደሚያደርጉት
የሚቀመጡበት ወንበር አንሰራላችሁም!›› አላቸው። ነቢዩም (ዐሰወ) ‹‹እኔ ከዱንያ
ምን አለኝ! የእኔና የዱንያ ዝምድና እኮ አንድ መንገደኛ በጉዞው መሀል አረፍ
እንደሚልበት ጥላ ነው።›› አሉት።
ከነቢያትም፤ ከንጉሶችም፤ ከባለሟሎችም ሁሉ የበላይ የሆኑት አሽረፈል ኸልቅ
(ዐሰወ) አረፍ የሚሉበት ወንበር እንኳን አልነበራቸውም። ፍራሻቸውም ሰሌን
የለበሰ የዘንባባ ዝንጣፊ ነበር።
እኛ ከሰሌን የተሻለ መኝታ የለን ይሆን? የምንቀመጥበት ወንበር አጥተን ይሆን?
የእያንዳንዳችን ንብረት ቢሰላ ነቢዩ (ዐሰወ) በህይወት ዘመናቸው ሁሉ ከነበራቸው
ገንዘብ ሳይበልጥ አይቀርም።
ታዲያ እኛስ ለኢስላም ምን ሰራን? እንዳንሰራስ ምን አገደን? ወላሂ ከስንፍናና
ከልብ በሽታ በቀር አንድም ሰው ምንም ምክንያት የለውም።
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➳ክፍል ስምንት

➲አራተኛው፡ - ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው ወደአላህ የሚያቃርቡ ተግባራቶች የትንሳኤ ቀን ባሪያው በአላህ ውዴታ የሚጎናጸፍበት በጀነት ድልብ ሀብት ሆኖ እንደሚቆየው የሸሪዓ መረጃዎች ሁሉ ይጠቁማሉ፡፡

➧በቁርኣን ፣ ተግባር በኢማን ስም ከመግባቱ በተጨማሪ ኢማን እናተግባርን በማጣመር የሚገኘውን ምንዳ ፣ የሁኔታቸውን ታላቅነት እና ደረጃ በማብራራት አምሳ የሚሆኑ አንቀጾች መጠዋል፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِّن ذَكَرٍ أَوْ أُنثَىٰ وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً ۖ وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُم بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ

“ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሰሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን፡፡” አን ነህል ፡97

وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ

“እነዚያም ያመኑት በጎ ስራዎችንም የሰሩት እነዚያ የጀነት ባለቤቶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውሰጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው፡፡” አል በቀራህ፡82

وَنُودُوا أَن تِلْكُمُ الْجَنَّةُ أُورِثْتُمُوهَا بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ
“ይህች ጀነት ትሰሩት በነበራችሁት ተሰጣችኋት በማለት ይጠራሉ፡፡” አል አዕራፍ፡43

الَّذِينَ تَتَوَفَّاهُمُ الْمَلَائِكَةُ طَيِّبِينَ ۙ يَقُولُونَ سَلَامٌ عَلَيْكُمُ ادْخُلُوا الْجَنَّةَ بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُون

“እነዚያ በመልካም ሁኔታ ላይ ሆነው መላእክት “ሰላም በእናንተ ላይ” እያሉ የሚገድሏው ናቸው፡፡ “ትሰሩት በነበራችሁት ስራ ጀነትን ግቡ” (ይባላሉ)፡፡” አን ነህል፡32

➧በዚህ ትርጉም ላይ የመጡ አንቀጾች በርካታ ናቸው፡፡ ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው፡፡ ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"لن يدخل أحدا عمله الجنة"

➛“አንድ ሰው ስራው ፍጹም ጀነት ሊያስገባው አይችልም፡፡” ሶሃቦች “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንተም?!” በማለት ጠየቁ፡፡ “እኔም ብሆን ፤ አላህ በችሮታውና በእዝነቱ ካልሸፈነኝ በቀር፡፡” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ ቡኻሪ፡ 5673 ሙስሊም፡2816

➲ተግባር ከጀነት ምክንያቶች አንዱ ምክንያት ነው፡፡ የዚህ ሐዲስ መንፈስ ፣ ጀነት የሚግገባው በአላህ እዝነት እንጅ በዱንያ ላይ የሰራው መልካም ስራ ለውጥ ሆኖት ጀነት ያስገባዋል ማለት አይደለም፡፡

➧ተግባር ለውጥ ወይም ቅያር ሆኖ ጀነት አያስገባም፡፡ ጀነት የሚገባው በአላህ እዝነት እና ችሮታ ነው፡፡ይልቁንም ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው፡፡ባሪያው የሚተገብረው መልካም ተግባርም ቢሆን በአላህ እዝነትና በአላህ ችሮታ ነው፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

۞ وَلَوْلَا فَضْلُ اللَّهِ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَتُهُ مَا زَكَىٰ مِنكُم مِّنْ أَحَدٍ أَبَدًا وَلَٰكِنَّ اللَّهَ يُزَكِّي مَن يَشَاءُ ۗ

“በእናንተም ላይ የአላህ ችሮታና እዝነቱ ባልነበረ ኖሮ ከናንተ አንድም ፈጽሞ ባልጠራ ነበር፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያጠራል፡፡” አን ኑር፡21


ኢንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ
ኑርአህመድ
➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

አድስ ተከታታይ ፅሁፍ


➲ከተውሂድ አርማዎች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል አንድ

➲“ተውሒድ” የዲኑ መነሻም መድረሻም ፤ ውስጡም ውጩም ነው፡፡ተውሒድ የመልእክተኞች ሁሉ የመጀመሪያም የመጨረሻም ጥሪ ነው፡፡ ተውሒድ “ላኢላሃ ኢል'ለሏህ” ለሚለው ቃል ትርጉም ነው፡፡ ለተውሒድ ሲባል ፍጥረታቶች ተፈጠሩ ፣ መልክተኞች ሁሉ ተላኩ ፣ መጽሓፎች ሁሉ እንዲወርዱ ተደረገ፡፡ በተውሒድ ምክንያት ሰዎች አማኝና ከሐዲ ፣ መልካምና ጠማማ ፣ የጀነትና የእሳት በሚል ከሁለት ተከፈሉ፡፡

➧ተውሒድ ለአካለ መጠን በደረሱ ሰዎች ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ነው፡፡ተውሒድ አላህ ከእርሱ ውጭ የማይቀበለው የሆነ ትክክለኛ የእስልምና እምነት ነው፡፡ተውሒድ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ፣ ስለርሱ ማወቅና መተዋወስ ለእኛ በጣም
አስፈላጊያችን የሆነ ጉዳይ ነው፡፡በመሆኑም በዚህች “ሚን መዓሊሚ አት'ተውሒድ”በተባለች አጭር ኪታብ ውስጥ የሚከተሉትን አንኳር ነጥቦች መሰረት ያደረጉ የተውሒድ አርማዎችና ምልክቶች ማብራሪያ በዝርዝር ይገኛሉ፡

➲የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች
➲ የተውሒድ ትርጉምና እውነታ
➲ ተውሒድን ማረጋገጥና ማሟላት
➲የተውሒድ አፍራሾችና አጉዳዮች
➲የተውሒድ ምንጭና መነሻ
➲የተውሒድ ፍሬዎችና ፋይዳዎች
በዚህች አጭር ኪታብ የምንነጋገረው ከላይ በተጠቀሱት ስድስት አንኳር ነጥቦች ዙሪያ ይሆናል፡፡

➭እነዚህ አንኳር ነጥቦች በስፋት መብራራት የሚፈልጉ ሲሆኑ ነገር ግን በአላህ ፈቃድ የተፈለገውን አላማ በሚያሳካ መልኩ እጥር ምጥን አድርጌ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡እግገዛን ፣ ከመጥፎው መንገድ ጠብቆ የመልካሙን መንገድ እንዲያመቻችልን አሏህን ሱብሃነሁ ወተዓላ - ብቻ እንማጸናለን፡፡


ኢንሻአላህ ይቀጥላል

🖊ኑር አህመድ

📚አንብብ፦ ያነበበ ተጠቀመ ያላነበበ ተጎዳ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➳ክፍል ስምንት ➲አራተኛው፡ - ተግባር ጀነት ለመግባት ምክንያት ነው ወደአላህ የሚያቃርቡ ተግባራቶች የትንሳኤ ቀን ባሪያው በአላህ ውዴታ የሚጎናጸፍበት በጀነት ድልብ ሀብት ሆኖ እንደሚቆየው የሸሪዓ መረጃዎች ሁሉ ይጠቁማሉ፡፡ ➧በቁርኣን ፣ ተግባር በኢማን ስም ከመግባቱ በተጨማሪ ኢማን እናተግባርን በማጣመር የሚገኘውን ምንዳ ፣ የሁኔታቸውን…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ዘጠኝ


አምስተኛው፡ - ሰለፎቹ ባወቁት ለመስራት ተሸቀዳዳሚ ነበሩ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲ይህን ደረጃ ከሚያብራሩ ነጥቦች መካከል፡ የሰለፎች አስደናቂ ባህሪያቸው ነው፡፡ሰለፎቹ ተግባርን በቋሚነት ለመፈጸም ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡ ከረሡል صلى الله عليه وسلم የሰሙትን ፈጥነው ለመተግባር ይቸኩሉ ነበር፡፡

➭በዚህ ትርጉም ላይ ሰለፎቹ ምን ያክል ባወቁት ለመተግበር ፍላጎቱ እንደነበራቸው ብርቱ ትኩረት እንደሚሰጡ የሚገልጹ በርካታ መረጃዎች መጠዋል፡፡ከዚህ መካከል ቡኻሪና ሙስሊም ላይ ተዘግቦ የሚገኘው ሐዲስ ነው፡፡ የረሡል صلى الله عليه وسلم ልጅ ፋጢማ ረድየላህ አንሃ አገልጋይ ፈልጋ ለአላህ መልእከተኛ ጥያቄ አቀረበች፡፡

▪️የአላህ መልክተኛም صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምላሽ ሰጧት፡- “ለአንች ከአገልጋይ የተሻለውን ልጠቁምሽ?” አሏት፡፡ (ለመተኛት) ወደፍራሽ በተጠጋሽ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሃን አሏህ ፣ አልሀምዱ ሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ፤ አሏሁ አክበር ሰላሳ ሶስት ጊዜ በይ” አሏት፡፡ ባለቤቷ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"فما تركتها منذ سمعتها من رسول الله صلى الله عليه وسلم"

“ከረሡል ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቸው አላውቅም” ከመካከላቸው አንዱ “አስቸጋሪ ሌሊት ላይ እንኳ ቢሆን? - ማለትም ሰው በሚዘነጋበት ሰኣት ላይ እንኳ ቢሆን? - ይህን ዚክር ረስቶት አያውቅም?” ፤ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን?!” - ይህ ሌሊት የታወቀ ጦርነት ነው - የሚል ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን” በማለት ምላሽ ሰጧል፡፡ ቡኻሪ፡ 5362 ሙስሊም፡2727

➧ዓንበሳህ ብን አቢ ሱፍያን -ረሂመሁሏህ- በሞተበት በሽታ ላይ ሆኖ ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሰማሁ ብላ የሚከተለውን ሐዲስ ነገረችኝ ብሎ ለእኔ አስተላልፎልኛል ይላል ዓምር ብን አውስ፡፡

"من صلى اثنتيني عشرة ركعة في يوم وليلة بني له بهن بيت في الجنة"

▪️“አስራ ሁለት ረከዓዎችን በሌሊትና በቀን የሰገደ ሰው በእነርሱ አማካኝነት በጀነት ቤት ይገነባለታል፡፡” ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ የሚከተለውን ተናግራለች ፡-
"فما تركتهن منذ سمعتهن من رسول الله"

➧“ከረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰማሁ ጀምሬ (እነዚህን አስራ ሁለት ረከዓዎች) ትቻቸው አላውቅም” አንበሳህ ደግሞ በተመሳሳይ “ከኡሙ ሀቢባ ከሰማሁ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም”ይላል፡፡ ዓምር ብን አውስ ደግሞ “ከአንበሳህ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል፡፡ ኑዕማን ብን ሳሊም ደግሞ “ከዓምር ብን አውስ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል፡፡ ሙስሊም፡728

➠ይህ ፍጥነትን እና በቋሚነት መፈጸምን ያጣመረ ታላቅ ወኔ ነው፡፡ ለስራ መፍጠን ፣ቋሚ ደምበኛ ለመሆን መሽቀዳደም፡፡

▪️ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ አቡሁረይራ ረዲየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"أوصاني خليلي بثلاث لا أدعهن حتى أموت: صوم ثلاث أيام من كل شهر ، وصالة الضحى ، ونوم على وتر"

➲“ወዳጀ እስከምሞት ድረስ የማልተዋቸው በሆኑ ሶስት ነገሮች አደራ አለኝ፡፡ ከየወሩ ሶስትቀናቶችን (እንድጾም) ፣ የዱሃ ሶላት (እንድሰግድ) ፤ ዊትር ሰግጀ እንድተኛ” ቡኻሪ፡1178



ኢንሻአላህ ይቀጥላል
ሰለፍዩ አንተ ማለት ለኔ

#ጀግና_ነህ_አንበሳ
-------------------------
ለመንሀጀ ሰለፍ ስንት አመት ሰርተሀል፡
ተውሒድ በመስበክህ ስንት ተብለሀል፡
እውነትን ለማድረስ ስንት ሀገር ዞረሀል፡
በጥመት ቡድኖች ስንት ተብለሀል፡
ስንቱ ለግድያ ጦሩን ሰብቆብሀል፡
በአሏህ ጠላቶች ስንቱ ደርሶብሀል፡
አንተ ግን ያን ሁሉ ታግሰህ አይተሀል፡
ብዙው ሽሽት ሲሮጥ አንተ ግን ቆመሀል፡
ሀቅ ለመመስከር ክብር ይገባሀል፡
ጀግና ነህ አንበሳ ብልህ ምን ያንስሀል፡
#ስለዚህ___!!
ከአማኝ ገፅ ላይ ሁሌ እማትረሳ፡
የጠማማን ሴራ ሳትፈራ ወቀሳ፡
የወዳጅህ ብስራት ሳይስብህ ሙገሳ፡
ማዕበሉን ሰንጥቀህ እንደ ዶልፊን አሳ፡
ሱናን ለማስፋፋት አይተሀል ሀበሳ፡
ቆራጥ ልበ ሙሉ ጀግና ነህ አንበሳ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
🖊ኑርአህመድ
🍁ረመዳን ሸህሩን ሙባረክ🍁
====================
★ ረመዳንን ከሌሎች ወሮች የሚለዮ 10 ነገሮች★


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ሁላችንም እንደምናውቀው ውዱ የበረካ ወር የሆነው ረመዳን ለተጠቃሚዎች በበረካው ሊያምበሸብሻቸው አንድ ሁለት እያለነው ረመዳን በአመት ውስጥ ካሉ 12 ወራቶች አንዱ ነው እንዲሁም ቁርአን ውስጥ ከተጠቀሱት 4 የላቁ ወራትም አንዱ ነው። ረመዳን ከሌሎች ወሮች ለየት የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉ ከነዛም ዉስጥ
① ፆም መደንገጉ ፦ የረመዳንን ወር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች መሀከል አንዱና ዋነኛው ወሩን እንድንፆም መታዘዛችን ነው
ፆም አላህ ዘንድ በጣም ከፍተኛ ቦታ ካላቸው ኢባዳዎች መሀከል አንዱ ነው ፆም የሱና እና ዋጂብ የሚባሉ ክፍሎችም አሉት የሱና ፆም የሚባለው መፆም የተከለከለ ባቸው ጊዜያት ሲቀሩ በማንኛውም ቀን መፆም የሚቻል ሲሆን ዋጂብ ወይም ፈርድ(ግዴታ) የሚባለው ፆም ደግሞ አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገው የፆም አይነት ነው አላህ ፆምን በኛላይ ግዴታ ማድረጉን ሲናገር እንዲ ይላል
(يا ايها الذن امن كتب عليكم اصيم كما كتب اللذين من قبلكم لعلكم تتقون)
(እናንተ ያመናችሁ ሆይ ፆም በናንተ ላይ ግዴታ ተደርጓል ልክ ከናንተ በፊት በነበሩት ግዴታ እንደተደረገው) ከዚ የቁርዓን አያ የምንማረው የመጀመሪያው ከኛበፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ መደንገጉን እና በኛም ላይ መደንገጉን ነው።
② የቁርአን መውረድ፦ ቁርአን ለሰውልጆች መመሪያና ማስተማሪያ ነው እንዲሁም ከዚበፊት የሆኑ ፣አሁን እየሆኑያሉና ወደፊት የሚሆኑ ለኛ አስተማሪና አስጠንቃቂ የሆኑ ነገሮችን የያዘ ነው። የዚህ ዉድ ቁርአን በረመዳን መውረድ ረመዳንን ከሌሎች ወሮች ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው። እና እኛ በዚ በረመዳን ቁርአንን ልንቀራ ይገባናል
ቀደምት ደጋግ ቀደምቶች በረመዳን እስከ 60 ጊዜ ያኸትሙ ነበር።አኛስ?
③ የሰይጣን መታሰር፦ በረመዳን ወርየጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ አመፀኛ ሰይጣናትም ይታሰራሉ። ነብያችን ሰ,ዐ,ወ እንዲህ ይላوغلقت السماء، ابواب فتحت رمضان إذا دخل إذا رواية وفي الشياطين وسلسلت جهنم،ابواب الجنة ابواب فتحت رمضان جاء

" ረመዳን ሲገባ የሰማይ በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ ሰይጣናትም ይቀፈደዳሉ ።’’ በሌላ ዘገባም” የጀነት በሮች ይከፈታሉ” ብለዋል(ቡኻሪና ሙስሊም)

④ የስራዎች ምንዳ መደራረብ፦ በረመዳን ወር የሐሰናት ወይም የመልካም ስራዎች ምንዳ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ተጠይቀው ከሰደቃዎች ሁሉ በላጩ የቱ ነው ተብለው "በረመዳን የሚሰጥ ነው ብለዋል"
⑤ ከአንድሺ ሌሊቶች በላጭ የሆነችው ለይለትል ቀድር፦ አላህ ከአንድ ሺህ ሌሊቶች ያስበለጣት ሌሊት ናት እንዲሁም የአመቱን ጉዳዩች የሚፅፍባት የተበረከች ሌሊት ናት "ليلة القدر خير من الف شهر"
" ሌሊቶችም በላጭመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ናት"

⑥ መላኢኮች በብዛት ወደ መሬት መውረድ፦ አላህ አንዲ ይላል ፦تنزل الملاإكة والروح فيها بإذن ربهم من كل أمر"
"በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ "
⑦ ሱሁር (የሌሊት ምግብ) ፦ ሱሁር ካለፍት ህዝቦች ፆም የኛን የሚለይና ብዙ በረካዎችን የያዘነው ነብዩ ሰ,ዐ,ወ እንዲህ ይላሉ "تسحروا فإن في السحور بركة"
"ሱሁርን ብሉ ሱሁር መብላት
በረካ አለውና "
⑧ የተራዊህ ሰላት፦በረመዳን ብቻ በጀማአ የሚሰገደው የሱና ሰላት የሆነው ተራዊህ አንዱ ረመዳንን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው። ከረመዳን ውጭ ይህ ሰላት አይሰገድም ።
⑨ የኡምራ ትሩፋት፦በረመዳን ወር ኡመራ ማድረግ ከነብዩ ሰ,ዐ,ወ ጋር ሀጅ እንደ ማድረግ ነው።"عمرة في رمضان تعدل حجة او قال حجة معي"
"በረመዳን የሚደረግ ኡምራ ከሀጅ ጋር እኩል ነው ወይም ከኔጋር ከሚሰራ ሀጅ እኩል ነው"ብለዋል
¹⁰ ወንጀል ማበሻ፦ረመዳን ወንጀል እንዲታበሱ ከሚያደርጉ ነገሮች መሀል አንዱና መሰረታዊው ነው።
" الصلوات الخمس ولجمعة الى الجمعة ورمضان الى رمضان مكفرات لما بينهن إذا اجتنبت الكبائر"
"ታላላቅ ወንጀሎች ከተራቁ አምስት ወቅት ሰላቶች ከጁምአ እስከ ጁምአ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመሀከላቸው ያለውን ወንጀል ያስምራሉ"

አላህ ካለ ከረመዳን ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዩች ላይ ክፍል ሁለት ይቀጥላል
ረመዳንኮ ሊገባ ነዉ፡፡ (ደስ ይላላ)
በሉ አዉፍ በሉኝ
ቂም ይዞ ጾም አይታሰብም፡፡ ጥላቻን አስወግደን በፍቅርና በመtሳሰብ የአጅር መአት የምንሰበስብበት ምርጥ ወር፤ ቀሽት ረመዳን ይሁንልን! ⭐️🌙 ከታች ከተዘረዘሩት ቁጥሮች ውስጥ አንድ ቁጥር በመምረጥ ለረመዷን ፆም ማስያዣ ስጦታ ትሰጠኛለክ ማለት ነው እንቢ ማለት አይቻልም
1💝2💝3💝4💝5💝6💝7💝8💝9💝10💝11💝12💝13💝14💝15💝16💝17💝18💝19💝20💝