La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
سورة الملك
القارئ عبدالعزيز الغنام
🌹ዉብ ቲላዋ

📚አይጠገብም የጌታችን ቃል

ስንደጋግመዉ የበለጠ ፍቅሩ የሚጨምር እደቁርዓን የለም!

🍃ሁሉም ሲበዛ ይመራል ቁርዓን ግን ይጣፍጣል በደጋገምነዉ ቁጥር!!

https://t.me/httpsLatahzen
#ጊዜህን ተጠቀምበት

➡️እስልምና ሙሉ የህይወት ህግ ነው እና ጊዜን ማባከን ወይም ጊዜን ማጥፋትን በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ በጣም ከባድ በሆኑ ማስታወሻዎች ላይ ተናግሯል ። የመጨረሻው የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም)ም አስጠንቅቀውናል።

➡️ማስጠንቀቂያው የጊዜ ብክነት የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅእኖ አስመልክቶ ሲሆን ከጥቅም ውጭ በሆኑ እና በሃራም እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለውን ጊዜ ፍጆታ መቀነስ ላይ አፅንዖት ሰጥቷል።

🍃እንደምናውቀው አለም በጊዜያዊነት የተፈጠረች እና የሁሉም ሙስሊም ፈተና ናት።

🍃ዓለም ጊዜያዊ ቦታ እና ከዚህ በኋላ ህይወት መሆኗን የመገንዘቡ እውነታ እራሱ ለዘላለም ሊቆይ የሚገባው ነገር ጊዜያችንን በተቻለ መጠን ጠቃሚ የማድረግ እውነታ ላይ ያጎላል።

🔑በወጣትነት ፣በጉልበት እና ሙሉ ህይወት ባለንበት ወቅት በእጃችን ከነበሩት የታላቁ አላህ ፀጋዎች አንዱን እናጠፋለን ይህም ጤናማ አካል ጥሩ ጤና እና ጊዜ ማለት ነው ።በተለይ በእርጅና እና በምንደክምባቸው ጊዜያት ረዘም ላለ ጊዜ ጥቅም በሚሰጡ ነገሮች ላይ ጊዜዎን ማዋል አስፈላጊ ነው።

💦ለመኖር በጣም የተገደበ ጊዜ ተሰጥቶናል ስለዚህ ከፍተኛ ጥረታችን በእስልምና አስተምህሮ እና በሱና መሰረት ህይወታችንን መምራት አለብን።

💦ህይወታችን ለታናናሾቻችን አርአያ እንዲሆንልን አብረን ዱዐእ እናድርግ።ይህም ለብዙዎች አበረታች ከሆነው የጥሩነት እና የጤንነት ስፋት በስተቀር ሌላ አይደለም።

✏️በበቂ ሁኔታ ልናመሰግነው የማንችለው የአላህ በረከቶች እና ፀጋዎች ብዛት ተሰጥቶናል ስለዚህ ህይወታችንን ጠቃሚ ማድረግ እና ለሌሎችም አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር አለብን


➡️ አስቸጋሪነት ቀደም ሲል የሠራናቸው የብዙ መጥፎ ወይም ጥፋቶች ውጤቶች ናቸው።ህይወት ሊተነበይ የማይችል እና ሞት የቀን መቁጠሪያ ስለሌለው በተቻለ ፍጥነት ለኃጢአታችን ይቅርታ እንድንጠይቅ ይመከራል።


የጊዜ በረራ የግድ እና አስቀድሞ የተወሰነ ነው። እኛ ነን ወደ ኋላ የቀረን እና በሰአት መሮጥ የሚገባን።

የወዲያኛው ሕይወት ማለቂያ የሌለው የጊዜ መንገድ ተብሎ ታውጇል እናም አሁን ያለው ሕይወት ሌላ አይደለም ነገር ግን ወደፊት የሚሄድ እና በቅርቡ ያልፋል ጊዜያዊ ምዕራፍ ነው እናምአጽንዖታችን መሆን ያለበት ለቀጣዩ ሕይወት ለመዘጋጀት ነው።


عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِرَجُلٍ وَهُوَ يَعِظُهُ اغْتَنِمْ خَمْسًا قَبْلَ خَمْسٍ شَبَابَكَ قَبْلَ هَرَمِكَ وَصِحَّتَكَ قَبْلَ سَقَمِكَ وَغِنَاكَ قَبْلَ فَقْرِكَ وَفَرَاغَكَ قَبْلَ شُغُلِكَ وَحَيَاتَكَ قَبْلَ مَوْتِكَ‎


ረሱል አለይኺ ሰላት ወሰላም ከኢብኑ አባስ ተይዞ እንዳስተላለፉት፦«አምስት ነገሮች ከአምስት ነገር በፊት ተጠቀምባቸው።


🍃ወጣትነትህ ከእርጅናህ በፊት

🍃ጤናህ ከበሽታህ በፊት

🍃ሃብትህ ከድህነትህ በፊት

🍃ነፃ ጊዜህን ከመጠመድህ በፊት

🍃ህይወታችሁን ከመሞታችሁ በፊት» ብለዋል።

( አል ሀኪም) ዘግበውታል 📚📚


عَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنْ النَّاسِ الصِّحَّةُ وَالْفَرَاغُ‎

ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ)እንዲህ አሉ ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ አሉ፦«ብዙ ሰዎች የሚያጡት ሁለት በረከቶች አሉ። (እነሱም) ጤና እና መልካም ለመስራት ነፃ ጊዜ ናቸው።»

(ቡኻሪ 8/421)
((سُبُّوُحٌ، قُدُّوسٌ، رَبُّ المَلاَئِكَةِ وَالرُّوحِ)).
🍃🌻
ምክር ለ ኒቃብ እና ጂልባብ ለባሾች እንዲሁም ኒቃብ ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ ነው ለምትሉ እህቶች‼️
➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩

➲ ኒቃብ እና ጅልባብ በሚለብሱ እህቶች ልጀምር
➼ በመጀመርያ ይህንን የተከበረ ልብስ እንድትለብሱ ልባቹሁን ክፍት ያደረገላችሁን አላህ ልታመሰግኑት ይገባል። ይህን የተከበረ ልብስ ስትለብሱ ፅናት ሊኖራቹህ ይገባል። ይህን ልብስ በመልበሳቹህ ብቻ የተለያዩ ሰዎች ከእውነታው የራቀ ትችት ሊሰነዝሩባችሁ ይችላሉ ምናልባት 'ፋራ' ሊሏቹህ ይችላሉ ራሳቸውን 'አራዳ' አድርገው በማሰብ ' ገጠሬ ' ይሏችኋል 'ከተሜ ' የሆኑ መስሏቸው የመሳሰሉ የተለያዩ ትችቶችን ይሰነዝራሉ ይሄኔ ግን እናንተ እውነታው ባገልባጩ መሆኑን ተረድታችሁ በፅናት ወደፊት ልትጓዙ ይገባል። ፋራዎች ተባልን ብላቹህ የለበሳችሁትን ኒቃብ አሊያም ጂልባብ እንዳታወልቁ። አይደለም ፋራ ሌላም ሊሏቹህ ይችላሉና!!!

➭ ሁሌም ሐቅ ላይ ያለ ሰው መተቸቱ የማይቀር ነው ነገር ግን ሐቅ ላይ እስከሆነ ድረስ ትችቱ አይጎዳውም።

➪ ሰለፎች ሐቅ ላይ የነበራቸውን ፅናት ተመልከቱ አይደለም ስድብ ስንት ድብደባ እና ግርፋት ደርሶባቸው ከአቋማቸው ዘንበል አላሉም ። ስለዚህ አርአያዎቻችሁን አላህ ያወደሳቸውን ትውልዶች በማድረግ ከአቋማችሁ በትንሽ ድግሪ እንኳን እንዳትዘነበሉ።

➺ ሶስተኛው እና ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ደሞ የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ማንኛውንም ኢኽላስ የሌለውን ስራ አላህ እንደማይቀበለው ተናግሯል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ኒቃቡን አሊያም ጂልባቡን የለበሳችሁት የአላህን ፊት ፈልጋችሁበት እንጂ የሰውን ፊት ፈልጋችሁበት ሊሆን አይገባም።

➲ ኒቃብ የለበስሽው እገሊት ኒቃብ ለባሽ ናት እንዲሉሽ ከሆነ ትልቅ አደጋ ላይ ነሽ። ይህን ርእስ ብዙ ኒቃብ እና ጂልባብ ለባሾች የተዘናጉበት ጉዳይ ነው።

➻ ከላይ ስታያቸው ማሻአላህ ኢማነኛ ናቸው ነገር ግን ከሰው ተደብቀው የሚሰሩት ስራ ግን በጣም የሚያሳዝን ሆኖ ታገኘዋለህ። አላሁል ሙስተዓን! ለዚህም ይመስለኛል አንዳንድ ጂልባብ ለባሾች በሚሰሩት ስራ ብዙ እህቶች ለምን ጂልባብ ወይም ኒቃብ አትለብሱም ሲባሉ ኢማን በልብ ነው የሚሉት እናም እህቶቼ ሆይ! ኒያችሁንም አስተካክሉ ለልብሱም ክብር ስጡት።

➨ ኒቃብ ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ ነው ወደምትሉ እህቶች ልምጣ ይህ ንግግር በመሰረቱ ችግር ያለበት ንግግር ነው። ምክንያቱም የአህለሱናዎችን ዓቂዳ ይቃረናልና። እንዴት ከተባለ አህሉ ሱናዎች ኢማን በልብ ብቻ ሳይሆን ከስራ ጋርም የተቆራኘ በመሆኑ ነው የሚያምኑት።

➽ ኢማን እና ስራ የተለያዩ ናቸው ኢማን በልብ ብቻ እንጂ ከስራ ጋር ቁርኝት የለውም ብለው የሚያምኑ 'ሙርጂአ' የሚባሉ ጠማማ አንጃዎች አሉ። ስለዚህ ባለማወቅ የነሱን እምነት እያንፀባረቅን ነውና ከዚህ ንግግራችን ልንቆጠብ ይገባናል። እናም እህቶቼ ሆይ! አላህ ያዘዘበት ነገር እስከሆነ ድረስ የአላህን ትእዛዝ ለመፈፀም ስትሉ ኒቃባችሁን ልበሱ። የሚል መልእክት አስተላልፍላችኋለው።

#ወላሁ አዕለም!

ወንድማችሁ ....
La tehzen
➲የተዘረጋ የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ሁለት ➧ይህ ፣ የተዘረጋ ገመድ (ቁርኣን) የሰውን ልጅ ለመምራት ፣ ለማስተካከል አማኞችን ለመገሰጽ ፣ በደረቶች ውስጥ ያለውን በሽታ ለመፈወስ ፣ ለቁርኣን ባለቤቶች በረከትን ፣ ብርሃንን እና ነጸብራቅን ለማጎናጸፍ አላህ ያወረደው መንገድ ነው፡፡ ➧አሏህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ…
➭የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት

➲የዓሊምን ደረጃና ቦታ በተመለከተ
“ሙስነድ” እና ሌሎች የሐዲስ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ሐዲሶች አብራርተውት ይገኛሉ፡፡ረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይና ታላቅ በሆነው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

➧“እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው ፤ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ ያመቻችለታል፡፡
የሚሰሩትን ስራ በመውደዳቸው መላኢካዎች ለእውቀት ፈላጊዎች ክንፋቸውን ያኖራሉ፡፡

➭ለዓሊም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ፤ በባህር ውስጥ የሚገኙት አሳዎች ሳይቀር ኢስቲግፋር (ይቅርታን) ይጠይቁላቸዋል፡፡ እውቀት ያለው ዓሊም ፣ እውቀት ከሌለው የአላህ ባሪያ ጋር ያለው ልዩነት ልክ በበድር (ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት) ሌሊት በሚወጣው ጨረቃና በሌሎች ከዋክብት መካከል እንዳለው ልዩነት ነው፡፡ ዑለሞች የነብያቶች ወራሾች ናቸው፡፡

➛ነብያቶች ዲናርም ፣ ዲርሃምም አላወረሱም፡፡ ያወረሱት ዒልምን ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ (ከዒልም) የያዘ ፣ የተነባበረ ድርሻ ያዘ፡፡” አህመድ፡21715 አቡዳውድ፡ 3641 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አቡዳውድ፡3671

➳አቡ ሁረይራ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ እንዳስተላለፉ:- ጦበራኒ “አውሰጥ” በተባለው የሐዲስ መዛግብት “ሀሰን” በሆነ ደረጃ ዘግበውታል፡፡ አቡሁረይራ በመዲና ገበያ መካከል ሲያልፍ ፣ ለተወሰነ ሰዓት ቆም አለ፡፡ “እናንተ ገበያተኞች ! ምን ደካማ አደረጋችሁ!” በማለት ተናገረ፡፡

➧“አቡሁረይራ ሆይ! ምንድን ነው?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁት፡፡ “የረሡል صلى الله عليه وسلم ንብረት እየተከፋፈለ የእናንተን ድርሻ ሳትይዙ ከዚህ ሆናችኋል!?” በማለት ምላሽ ሰጣቸው፡፡ “የት ነው ያለው?” በማለት ጠየቁት፡፡ “መስጅድ ውስጥ ነው” አላቸው።ወደ መስጅድ ፈጥነው ገሰገሱ፡፡ ደርሰው እስኪመለሱ ድረስ ቆሞ ጠበቃቸው፡፡ “ለእናንተ ምን አላችሁ?!” አላቸው፡፡ “አቡሁረይራ ሆይ! መስጅድ ሄድን ከውስጥ ገባን ፤ የሚከፋፈል ነገር ማየት አልቻልንም” አሉት፡፡

አቡሁረይራም “ከመስጅድ ውስጥ አንድንም አላያችሁ?!” በማለት ጠየቃቸው፡፡ “ከፊሎቹ ሶላት እየሰገዱ ፣ከፊሎቹ ቁርኣን እየቀሩ ፣ ከፊሎቹ ስለሀላልና ስለሀራም እያወሱ አይተናል” በማለት ምላሽ ሰጡት፡፡ አቡሁረይራ “ወዮላችሁ! የረሡል صلى الله عليه وسلم ውርስ ብሎ ማለት እኮ እርሱ ነው” በማለት መልስ ሰጣቸው፡፡ ጦበራኒይ ፊል አውሰጥ፡ 1429 ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል ሶሂህ ተርጊብ ወተርሂብ፡83

➛ይህ ነው የነብያት ውርስ ማለት፡፡ ነብያቶች የወርቅ ወይም የብር ገንዘብ አያወርሱም፡፡ ነብያቶች እውቀትን ነው የሚያወርሱት፡፡ የአንድ ሰው የእውቀት ድርሻው ከፍ ባለ ቁጥር ፣ ከነብያቶቸ ውርስ ድርሻው ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡1037



🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል


📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴



https://t.me/httpsLatahzen
🔰The Hadith of the Day🔰


▪️የአላህ መልክተኛ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከዕለታት አንድ ቀን ከባለደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ፦
# “ድሐ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?”
በማለት ይጠይቃሉ።
ሰሐቦችም ፦
#“እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው።” በማለት ይመልሳሉ።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ግን፦
# “ከኡመቴ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ
#ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ግና ይህ ሰው አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣ ሌላው ላይ ዋሽቷል፣የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣የሌላውን ደም አፍስሷል፣አንዱን መትቷል፣ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣ ያኔም (የትንሳኤ ምርመራ ቀን ) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ጥሩ ሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል። ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል።”
በማለት መለሱላቸው።

📚(ሙስሊም ሀዲሰ ቁ.6531)

📩አላህ ከክስረት ይጠብቀን 🤲በሰዎች ጉዳይ አያገባንገብተን በምላሳችንም ሆነ በእጆቻችን አንድንአማኝ ከመጉዳት አላህ ይጠብቀን 🤲🤲

•════•••🌺🍃•••════•
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል አራት

➲ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ 71ሙስሊም፡1037

➧“ኸይረን” የሚለው ቃል በነኪራ (ሁሉን በሚያካትት ቃል) መምጣቱ ክብደትን እና
ልቅናን እንዲሁም በአላህ ዲን የታነጸ ሰው የሚለቅመው ጠቃሚ ፍሬ ከፍተኛ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ዕውቀትን በመፈለግ ላይ እንቅስቃሴ ከጀመረ አላህ መልካሙን እንደሻለት የሚያመክት ነው ማለት ነው፡፡

➲ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“በዚህ ሐዲስ የተፈለገው ተግባርን ያጣመረ የዲን እውቀት ነው፡፡ ከተግባር ነጻ የሆነ
እውቀትን የፈለገ ሰው አላህ መልካም ሽቶለታል ማለትን አያመላክትም፡፡”

➭ይህ ማለት ፣ ዲንን ሊገነዘብና ወደተግባር ሊቀይረው ይገባል ማለት ነው፡፡ የመማሩ ዋናው አላማ ከራሱ ላይ ማህይምነትን ማስወገድ ፣ በእውቀት ላይ ተንተርሶ አምልኮን ለአላህ ብቻ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ አይነት ባህሪ ላይ ከሆነ መልካምን ለማግኘት ተገቢ ይሆናል ማለት ነው፡፡

➛ለተግባር እውቀት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ እውቀት ፣ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ነው ከተግባር በፊት እውቀት ተቀዳሚ የሆነው፡፡ ተግባር፣ አምልኮ ፣ ወደአላህ መቃረብ ከአላህ ኪታብና ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱና በመነጨ ጠቃሚ እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ሚፍታህ ዳሪ አስ ሳዓዳ፡1/65

➧በዚህ ታላቅ ርዕስ ዙሪያ ጥቅል መረጃዎችን እና ታላላቅ የሰለፎችን ንግግር ያካተተ“ኢቅቲዷኡል ዒልም አልዓመል” የተባለ ምርጥ መጽሐፍ ኸጢብ አል'በግዳድይ -ረሂመሁሏህ - ጽፈዋል፡፡

➲“ኢቅቲዷኡል ኢልም አልዓመል” የተባለው ኪታብ የእውቀት አላማው ተግባር እንደሆነ ፣ በእውቀትና በማስረጃ ላይ በመንተራስ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ማረጋገጥ እንደሚገባ ትኩረት ይሰጣል፡፡ አንድ ባሪያ እውቀት ኖሮት ስራ ከሌለው ፣እንዲሁም ያለእውቀት ተግባር ብቻ ከሆነም አምልኮ በትክክል ተረጋግጧል ማለት አይቻልም፡፡

➧የአላህ አምልኮ በሁለት ነገሮች ካልሆነ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ በጠቃሚ እውቀት እና በመልካም ተግባር፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ

“እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልእክተኛው (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡” አት ተውባህ፡33

➭“ሁዳ” ፡ ማለት ጠቃሚ እውቀት ማለት ነው፡፡ “ዲኑል ሐቅ” ማለት ደግሞ ወደአላህ የሚያቃርብ መልካም ተግባር ማለት ነው፡፡“ዲኑል ሐቅ” ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲሁም አጠቃላይ ነብያቶች የተላኩበት ነው፡፡



እንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ
Nurahemd
➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
ሙሀመድ ሠ.ዐ.ወ
የኔ በ ጅህልና ከቁረይሾች መሀል
እነሡ የሚያውቁት ውበቱ የሚያማል
ሀቀኛ የሆን ሠውን የማያታልል
አላህ ፈለገልና ለዚህ ኡመት መሪ
ሠውን ያሚመራ ህይወትን መርማሪ
ኢሰለምን ሚያሳፋፋ ዲኑን አስተማሪ
ሙሀመድን ላከ ለዚህ ኡመት መሪ
ፅድት ያልኩ ሙስሊም ነኝ

አዎ እኔ ሙስሊም ነኝ
እኔማ ሙስሊም ነኝ ምንም ሽርክ የሌለኝ
ከእስልምና በቀር የኔ ምለዉ የለኝ
ቢርበኝ ቢጠማኝ ዲኔን ብቻ ያለኝ
እኔማ ሙስሊም ነኝ
ከምንም ሚበልጠዉ የእስልምናን አለኝ
በማንኛዉም ጊዜ በደስታ ሚያኖረኝ

እኔማ ሙስሊም ነኝ
፨ ለጦቢብ ሰው እውነተኛ ገንዘቡና
ሃብቱ አራቱ ነገሮች ናቸው ።


1} ከአንድበቱ የሚወጣው ቃል
እውነትመሆኑ

2} ንዴትና ቁጣውን መግዛት መቻሉ ።

3} ለስጋዊ ፍላጎቱ የማይስገበገብ
መሆኑ

4} በሁሉም ነገር ላይ የሚታመን
ሰው መሆኑ
የሰው ዘር መጀመሪያ የሆኑት #አደም

ልዩ የክብር ቦታ የተሰጣቸው #እንድሪስ

950 ዓመታት በማስተማር የቆዩት #ኑህ

ወደዓድ ህዝቦች የተላኩት #ሑድ

ድንጋይ ተፈልቅቆ ግመል የወጣችላቸው #የሰሙዱ ሳሊህ።

የኑምሩድን እሳት ድል በማድረግ የወጡት #ኢብራሒም

መላእክት በእንግድነት ወደቤቱ የገቡት #ሉጥ

በካዕባ ግንባታ የተሳተፉት #ኢስማኢል

የአባታቸው የኢብርሂም ልድ #ኢስሐቅ

የ12 ወንድ ልጆች አባት የሆኑት #ያዕቆብ

እጅግ ታጋሹና ጥበበኛው #ዩሡፍ

መከራን ቻዩና ጸሎተኛው #አዩብ

የሁለት ሴቶች አባት የሆኑት የመደኑ #ሹዓይብ

ባህር የተሰነጠቀላቸው የኢምራን ልጅ #ሙሳና ወንድማቸው #ሐሩን

በዓሣ ሆድ ውስጥ ዚክር ያደረጉት የነይነዋው #ዩኑስ

ብረት እንደጭቃ የሚለዝብላቸው ድምጻዊው #ዳውድ

ንፋስን እንደፈለጉ የሚያዙት ንጉሱ #ሱለይማን

ቁርኣን ስማቸውን እንጅ ያላስዋወቀን አልየሰእ፤ #ኢሊያስና #ዙልኪፍል

አናጺውና የመሪየም አሳዳጊ #ዘከርያ

በልጅነታቸው ነብይነትን የተሰጡት #ያህያ

ያለአባት የተወለዱት ተአምረኛው የመሪየም ልጅ #ዒሣ

ለተልእኳቸው የቦታና የዘመን ግርጾሽ የተነሳላቸው #ሙሐመድ ናቸው።

እንግዲህ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል በተላኩት ነቢያት በሙሉ ያለምንም ልዩነት ማመን ይኖርብናል።
ታላላቅ ነገሮችን የሚያሳጡ ሶሳት
(አደገኛ) ነገሮች ፦
======"""""""""""""""======
1. {ተነሳሽነት ማጣት}
------------------😕------------------------
2. {የእውቀት ማነስና}
____________📘______________
3. {የአስተውሎ ድክመት}
-----------------😮-------------------------
(አቢ ዐብዱላህ አስ-ሳድቅ) °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
፨ ሶስት ነገሮችን የተሰጠ ሰው ከሁሉም ሰው የበለጠ የመረነት ተጽእኖ አለው።
-----------===========-----------
1. አዛኝነት
''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''
2. ፍታሃዊነትና
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
3. ለጋስነት
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧

{ አቢ ዐብዱለሂ አስሳድቅ}
፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦፦
አላህን አመሰግን
🙏🙏🙏🙏🙏

እጅ አለን ፤ እግር አለን ፤ ዓይን አለን ፤ ቤተሰብ አለን ፤ እኚህ ደግሞ በሕይወት
ውስጥ ከምንፈልጋቸው በርካታ ሃብቶች ብላይ የሚልቁ ናቸው ። ችግራችን
ግን ምንጊዜም የምናሰበው ያለንን ነገር ሳይሆን የሌለንን ነገር መሆኑ ነው ።
ችግሮችህን ብቻ ሳይሆን አላህ የሰጠህን ፀጋዎች ስታስብና አላህን አመስጋኝ
ስትሆን ፍጹም መከፋትም ሆነ አሉታዊ ስሜቶን ማዳበር አትችልም ።
ምክንያቱም በማንኛውም ሁኔታ ላይ አላህን አመስጋኝ ሆኖ መገኘት ጸረ ምህርዝ
ከትባት ነውና ። አላህን አመስጋኝ መሆን የቆሰለውን ያድናል ፤ የተሰበረውን ይጠግናል ።
For Comment
@Bktibeb
፨ በሰዎች ስሜት ላይ ጉዳት
እንዳታደርስ ጥንቃቄ አድርግ ።
ማለትም ፦

☞ ስለሃብትህ በድሃ ፊት ፤

☞ ስለጤንነትህ በህመምተኛ ፊት ፤

☞ ስለጥንካሬህ በደካማ ፊት ፤

☞ ስለደስታህ በሃዘንተኛ ፊት ፤

☞ ስለነጻነትህ በታሰረ ሰው ፊት ፤

☞ ስለልጆችህ በመካን ፊት ፤

☞ ስለአባትህ በየቲሞች ፊት ፤

☞ ስለትዳርህ ትዳር ባልተሳካላቸው
ሰዎች ፊት አታውር ።
በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!

🌹 .............................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!

🌹 .............................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ


በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!

🌹 .............................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!

🌹 .............................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!

🌹 .............................🌹
ﷺ ﷺ🌹 ..................🌹 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ 🌹.......🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ🌹 ﷺ ﷺ ﷺ
በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ!

.ﷺ 🌹.............................🌹
ﷺ ﷺ🥀 ..................🥀 ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ......🥀 ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ🥀.... ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
.ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

መልካም ጁመአ ውዶች🌹

@Strong_iman
️ትንሺ ግጥም ስለ ተውሒድ!!
*,,,,,,,, ﻧﻈﻢ ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ *
ቢሥሚላሂ ብየ ተውሒድን ልጀምር
ለማሥታወስ ያክል በግጥም ልደርድር!
️ለሙእሚኖች ሁሉ ለሴትም ለወንዱ
እስኪ ላሥታውሳችሁ ተውሒድን ተማሩ!
በአሏህ ማጋራት አስከፊ ወንጀል ነው
እስከ ዘላለሙ መኖሪያው እሳት ነው!
በሺርክ ተጨማልቆ ተውሒድን ችላ ያለ
የጌታውን መብት እጅግ ያጓደለ
በሺርክ ኮረፋት እራሡን ያዞረ
ተውሒድን በመተው ለሺርክ የታገለ
በዱኒያም ከሰረ እጅግ ተዋረደ
በአሔራም ከስሮ ጀሀነም ወረደ
ተውሒድን እንወቅ እንማር በደንቡ
ጌታችንን ነጥለን እናምልክ በወጉ
አምልኮ ፍራቻ ለአሏህ ብቻ ነው
ከዛ የተቀረው ሁሉም ኪሳራ ነው!
ተውሒድን እወቁ በደንብ ለይታችሁ
ተውሒድ ነውና የድናችን መሠረት
እሱን ያላወቀ መቸውም ቢህን አይገባም ከጀነት
ተውሒድ ኡሉህያ ሩብብያውን
ለዩና እወቁ አስማኡ ሲፋቱን
እናተ ሰወች ሆይ እወቁ ጌታችሁን
ሰውንም ጅንንም የፈጠረውም
ሊያመልኩት እንጅ ለሌላ አይደለም
እሱም ብሏልኮ በቁረአን አያ
ሰውንም ጅንንም ሊያመልኩኝ እንጅ አልፈጠርኩም
እናማ አምልኩት ለብቻ ነጥላችሁ
ከሺርካሺርክ ተግባር እጅግ እርቃችሁ
ቃጥባሬ ኑር ሁሴን ማለቱን ተውና
ቀጥ ብላችሁ ቁሙ በነብዩ ሱና
የሰው ልጆችና ጅኖች ምን ሆነዋል
አብዘሀኛወቹ አላማ ስተዋል
ሰባት ሰማያት እንድሁም ምድር
አላህ ፈጠራቸው አዚዙል ጀባር
የአርሹ ባለቤት የጠራ ጌታነው
በሱላይ ማጋራት የጀሀነም እራትነው
ተውሒድን ከያዙ ወድቀውም አይወድቁ
ጌታን በማምለክላይ ደስታን ያገኛሉ
ለጅኖች ማረዱ ይቅርም ስግደቱ
በአላህ ያሻረከ መጨረሻው ነው ከንቱ
ለጅኖች ማጎብደድ አይደለም ለሸኹ
በማንም ማጋራት መች ይፈቅዳል እሱ?
አምልኩኝ ብሎ አዞን ለብቻው ነጥለን
ታዳ ምን አሥፈለገ በሱላይ መደረብ?
ተው ጌታችሁን ፍሩ እሱንም ታዘዙ
ለብቻ ለዩና በአምልኮ ነጥሉ!?
አላህ አምላካችን ነው ለኛ አንድ
እርሱን የሚጋራ አይሆንም ከእኛ
ተውሒድ ምንጫችን ነው የድኑ መሠረት
ጌታን በማምለክላይ ለብቻ በመለየት!
ﺍﻟﺘﻮﺣﻴﺪ ﺩﻋﻮﺓ ﺍﻟﺮﺳﻮﻝ
ተውሒድ የሁሉም ነብያት የመጀመሪያ ጥሪያቸው ነው!
የአላህ መልክተኛ ( ﷺ ) እንዲህ አሉ፡- "በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው
መልካም ነገርን ይናገር ወይም ዝም ይበል፣ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ
ሰው ጎረቤቱን ያክብር፣ በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው እንግዳውን
ያክብር" (ቡኻሪና ሙስሊም) ዘግበውታል፡፡
☞ዝሙት☜
በኢስላም የሌለ ፍቅረኛ የሚባል የካፊር ሱና ነው በሀራም
የተጣመረ ነው፡፡
የዝሙት አደጋው!
©አለኝ የምንላትን ኢማን ያጠፋብናል፥
©ሀራም ነውና የመንፈስ ሰላም አይገኝበትም፥
©ለጭንቅት ይዳርገናል፥
©ከአላህ ራህመት ያስወጣናል፥
©ከሁሉም ነገር ላይ በረካን ያነሳብናል፥
©የነብዩን(ሰ.አ.ወ) ሱናም ይፃረራል፥
©ሰላማችንን ይነሳናል፥
©በራስ መተማመናችን ይቀንሳል፥
©አሏህ ዘንድ ያስቀጣል፥
©በሰው ዘንድም ያስጠላል፥
©የሪዝቅን በር ይዘጋል፥
@ጤናን ያውካል፥
ስለዚህ ወንድሞቼና እህቶቼ ከዚና ራሳችንን እንጠብቅ ከቻልን
ማግባት ካልሆነ ግን አሏህ እስኪዘውጅን ድረስ መሶበር ነው፡፡
ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ማስተዳደር
የቻለ ያግባ ጋብቻ ለአይን ገደብ ነው ብልትንም ይበልጥ ጠባቂ
ነው፡፡ ይህን ያልቻለ ይጹም፡፡
አሏህ ሱ.ወ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይለናል!
ﻭَﻟَﺎ ﺗَﻘْﺮَﺑُﻮﺍ۟ ﭐﻟﺰِّﻧَﻰٰٓ ۖ ﺇِﻧَّﻪُۥ ﻛَﺎﻥَ ﻓَٰﺤِﺸَﺔًۭ ﻭَﺳَﺂﺀَ ﺳَﺒِﻴﻠًۭﺎ
ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ መጥፎ ሥራ ነውና፡፡
መንገድነቱም ከፋ{አል-ኢስራእ፡ 32}
በእርግጥ አሏህ ሱብሀነሁ ወታአላ አትቅረቡ ነው እንጂ ያለው
አትስሩት አይደለም ስለዚህ ወድ ወንድሞቼና እህቶቼ ሁሉም ነገር
ሀላል ሲሆን ነው ደስ እሚለው ለአንድ ቀን ደስታ ብለን የዘላለም
ጸጸት አናትርፍ አሏህ እኮ ለኛ ብዙ ውለታዎችን ነው የዋለልን
ዚናን ሀራም ሲያደርግብን ኒከህን ሀላል አደረገልን ኸምርን
(መጠጥን) ሀራም ሲያደርግብን ወተት የተፈጥሮ ምንጭ የሆነውን
ውሃ ለስላሳ የመሳሰሉትን ሀላል አድረገልን ታዲያ እሱ ሀላል
ያደረገልንን ትተን ለምን ሀራሙ እንመርጣለን? ያ የከለከለን ነገር
እኛን ስለሚጎዳ እንጂ ቢጠቅመን ኖሮ ይፈቅድልን ነበር፡፡
አብዛሀኛውን ግዜ ለዝሙት ምንጋለጠብት መንገድ ከተቃራኒ ጾታ
ጋር ለብቻ አብሮ መቀመጥ ነው፡፡
እህቴ እሱ እንደ ወንድሜ ነው ብለሽ ከሰው ርቀሽ ከተቃራኒ ጾታ
ጋር አብረሽ አትቀመጪ ወንድሜ አንተም ብትሆን እንደ እህቴ ናት
ብለህ ለብቻ ከሷ ጋር አትቀመጥ ምክንያቱም በመካከላችሁ
ሼይጧን ይገባልና፡፡
ሀቢቡና ሙሀመድ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል!
ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ለብቻቸው ከተቀመጡ ሶስተኛቸው
ሸይጧን ነው፡፡
አሏህ ከሸይጧንና ከነፍሲያ ተንኮል እንዲሁም ከመጥፎ ጓደኛ
ይጠብቀን አሚን አሏሁመ አሚን!

ለወዳጅ ዘመድዎ ሸርርርር ያድርጉት በጣም ስስታም ሰው ማለት ለራሱ ብቻ አንብቦ ወይም ተጠቅሞ ለሌላ ሰው የማያካፍል ነው አሉ ከነሱ አይነት ሰዎች አትሁኑ ጆይን

قالَ اللهُ تباركَ وتعالى: ﴿وَتَزَوَّدُوا فإنَّ خَيْرَ الزَّاد التَّقْوَى﴾ [ سورة البقرة،ءاية 197]
ሙሉውን አንብቢው ከዚያም መጨረሻ ላይ ያለውን ቁጥር አይተው ይወስኑ።

የአላህ መልእክተኛ (ሰአወ) እንዲህ ብለዋል ⇣ለምላስ ቀለል ብላ ሚዛን ላይ ከባድ ያለች አላህ ዘንድም የተወደደች ንግግር⇣
*ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም* *ሱበሃን አላህ ወቢ ሃምዲህ ሱበሃን አላህ አል አዚም*
ቢያንስ ለ30 ሰዎች ላክ ቢሉትም (ቢያነቡትም) አምስ መቶ ቢሊዮን ሃሰናትን በአላህ ፈቃድ ታገኛለህ።
እንደዚሁ አንተ የላክላቸው ሰዎች እያንዳንዳቸው ለ30 ሰው ከላኩ አሁንም 4.680.000.000 ሃሰናት ታገኛለህ። መቼ እንደምትሞት አታቅምና ሰደቀተል ጃሪያ አድርጋት።
ለማሰራጨት ደቂቃ እንኳን አይወስድብሽም።
የቅያማ ዕለት ትመሰክርልህ ዘነድ።