La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
«ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104)
🍁ረመዳን ሸህሩን ሙባረክ🍁
====================
★ ረመዳንን ከሌሎች ወሮች የሚለዮ 10 ነገሮች★


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ሁላችንም እንደምናውቀው ውዱ የበረካ ወር የሆነው ረመዳን ለተጠቃሚዎች በበረካው ሊያምበሸብሻቸው አንድ ሁለት እያለነው ረመዳን በአመት ውስጥ ካሉ 12 ወራቶች አንዱ ነው እንዲሁም ቁርአን ውስጥ ከተጠቀሱት 4 የላቁ ወራትም አንዱ ነው። ረመዳን ከሌሎች ወሮች ለየት የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉ ከነዛም ዉስጥ
① ፆም መደንገጉ ፦ የረመዳንን ወር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች መሀከል አንዱና ዋነኛው ወሩን እንድንፆም መታዘዛችን ነው
ፆም አላህ ዘንድ በጣም ከፍተኛ ቦታ ካላቸው ኢባዳዎች መሀከል አንዱ ነው ፆም የሱና እና ዋጂብ የሚባሉ ክፍሎችም አሉት የሱና ፆም የሚባለው መፆም የተከለከለ ባቸው ጊዜያት ሲቀሩ በማንኛውም ቀን መፆም የሚቻል ሲሆን ዋጂብ ወይም ፈርድ(ግዴታ) የሚባለው ፆም ደግሞ አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገው የፆም አይነት ነው አላህ ፆምን በኛላይ ግዴታ ማድረጉን ሲናገር እንዲ ይላል
(يا ايها الذن امن كتب عليكم اصيم كما كتب اللذين من قبلكم لعلكم تتقون)
(እናንተ ያመናችሁ ሆይ ፆም በናንተ ላይ ግዴታ ተደርጓል ልክ ከናንተ በፊት በነበሩት ግዴታ እንደተደረገው) ከዚ የቁርዓን አያ የምንማረው የመጀመሪያው ከኛበፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ መደንገጉን እና በኛም ላይ መደንገጉን ነው።
② የቁርአን መውረድ፦ ቁርአን ለሰውልጆች መመሪያና ማስተማሪያ ነው እንዲሁም ከዚበፊት የሆኑ ፣አሁን እየሆኑያሉና ወደፊት የሚሆኑ ለኛ አስተማሪና አስጠንቃቂ የሆኑ ነገሮችን የያዘ ነው። የዚህ ዉድ ቁርአን በረመዳን መውረድ ረመዳንን ከሌሎች ወሮች ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው። እና እኛ በዚ በረመዳን ቁርአንን ልንቀራ ይገባናል
ቀደምት ደጋግ ቀደምቶች በረመዳን እስከ 60 ጊዜ ያኸትሙ ነበር።አኛስ?
③ የሰይጣን መታሰር፦ በረመዳን ወርየጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ አመፀኛ ሰይጣናትም ይታሰራሉ። ነብያችን ሰ,ዐ,ወ እንዲህ ይላوغلقت السماء، ابواب فتحت رمضان إذا دخل إذا رواية وفي الشياطين وسلسلت جهنم،ابواب الجنة ابواب فتحت رمضان جاء

" ረመዳን ሲገባ የሰማይ በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ ሰይጣናትም ይቀፈደዳሉ ።’’ በሌላ ዘገባም” የጀነት በሮች ይከፈታሉ” ብለዋል(ቡኻሪና ሙስሊም)

④ የስራዎች ምንዳ መደራረብ፦ በረመዳን ወር የሐሰናት ወይም የመልካም ስራዎች ምንዳ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ተጠይቀው ከሰደቃዎች ሁሉ በላጩ የቱ ነው ተብለው "በረመዳን የሚሰጥ ነው ብለዋል"
⑤ ከአንድሺ ሌሊቶች በላጭ የሆነችው ለይለትል ቀድር፦ አላህ ከአንድ ሺህ ሌሊቶች ያስበለጣት ሌሊት ናት እንዲሁም የአመቱን ጉዳዩች የሚፅፍባት የተበረከች ሌሊት ናት "ليلة القدر خير من الف شهر"
" ሌሊቶችም በላጭመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ናት"

⑥ መላኢኮች በብዛት ወደ መሬት መውረድ፦ አላህ አንዲ ይላል ፦تنزل الملاإكة والروح فيها بإذن ربهم من كل أمر"
"በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ "
⑦ ሱሁር (የሌሊት ምግብ) ፦ ሱሁር ካለፍት ህዝቦች ፆም የኛን የሚለይና ብዙ በረካዎችን የያዘነው ነብዩ ሰ,ዐ,ወ እንዲህ ይላሉ "تسحروا فإن في السحور بركة"
"ሱሁርን ብሉ ሱሁር መብላት
በረካ አለውና "
⑧ የተራዊህ ሰላት፦በረመዳን ብቻ በጀማአ የሚሰገደው የሱና ሰላት የሆነው ተራዊህ አንዱ ረመዳንን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው። ከረመዳን ውጭ ይህ ሰላት አይሰገድም ።
⑨ የኡምራ ትሩፋት፦በረመዳን ወር ኡመራ ማድረግ ከነብዩ ሰ,ዐ,ወ ጋር ሀጅ እንደ ማድረግ ነው።"عمرة في رمضان تعدل حجة او قال حجة معي"
"በረመዳን የሚደረግ ኡምራ ከሀጅ ጋር እኩል ነው ወይም ከኔጋር ከሚሰራ ሀጅ እኩል ነው"ብለዋል
¹⁰ ወንጀል ማበሻ፦ረመዳን ወንጀል እንዲታበሱ ከሚያደርጉ ነገሮች መሀል አንዱና መሰረታዊው ነው።
" الصلوات الخمس ولجمعة الى الجمعة ورمضان الى رمضان مكفرات لما بينهن إذا اجتنبت الكبائر"
"ታላላቅ ወንጀሎች ከተራቁ አምስት ወቅት ሰላቶች ከጁምአ እስከ ጁምአ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመሀከላቸው ያለውን ወንጀል ያስምራሉ"

አላህ ካለ ከረመዳን ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዩች ላይ ክፍል ሁለት ይቀጥላል።

@Nurahend




https://t.me/httpsIBNumuhammed
«ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104)
📿የጧት ዚክር📿

سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ: عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ. (3× إذا أصبح)

‹‹ለአላህ ጥራት ይገባው፡፡ ምስጋናም፡፡ በፍጡራኑ ቁጥር ልክ፤ ነፍሱ በወደደችው ልክ፤ በዙፋኑ ክብደት ልክ፤ በቃላቱ ብዛት ልክ፡፡›› ሦስት ጊዜ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ عِلْمًا نَافِعًا، وَرِزْقًا طَيِّبًا، وَعَمَلاً مُتَقَبَّلاً. (إذا أصبح)

‹‹ኣላህ ሆይ! ጠቃሚ እውቀትን, መልካም የሆነ ሲሳይን, ተቀባይነት ያለውን ተግባርን እጠይቅሀለሁ።
((سُبْحانَ رَبِّيَ الْعَظِيمِ))
🍃🌻
((سُبْحَانَكَ اللَّهُمَّ رَبَّنَا وَبِحَمْدِكَ، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي)).
🍃🌻
🌿🌿🌿🍃ጥቆም🍃🌿🌿🌿

💫ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-

"አንድ ሰው ዕውር ካለ መሆኑም ጋ ዐይኖቹን ቢጨፍናቸው ምንም ነገር ማየት እንደ ማይችለው ሁሉ፤ቀልብም በሚሸፍናት የወንጀል ጨለማ ምክንያት ሐቅን መመልከት አትችልም።"

🔻አይን ኖሮን ከመታወር ቀልብ ኖሮን ከመደናበር እናስተውል።አላህም ይጠብቀን።
سورة الملك
القارئ عبدالعزيز الغنام
🌹ዉብ ቲላዋ

📚አይጠገብም የጌታችን ቃል

ስንደጋግመዉ የበለጠ ፍቅሩ የሚጨምር እደቁርዓን የለም!

🍃ሁሉም ሲበዛ ይመራል ቁርዓን ግን ይጣፍጣል በደጋገምነዉ ቁጥር!!

https://t.me/httpsLatahzen
#ጊዜህን ተጠቀምበት

➡️እስልምና ሙሉ የህይወት ህግ ነው እና ጊዜን ማባከን ወይም ጊዜን ማጥፋትን በማይጠቅሙ ነገሮች ላይ በጣም ከባድ በሆኑ ማስታወሻዎች ላይ ተናግሯል ። የመጨረሻው የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም)ም አስጠንቅቀውናል።

➡️ማስጠንቀቂያው የጊዜ ብክነት የሚያስከትለውን አሉታዊ ተፅእኖ አስመልክቶ ሲሆን ከጥቅም ውጭ በሆኑ እና በሃራም እንቅስቃሴዎች ውስጥ ያለውን ጊዜ ፍጆታ መቀነስ ላይ አፅንዖት ሰጥቷል።

🍃እንደምናውቀው አለም በጊዜያዊነት የተፈጠረች እና የሁሉም ሙስሊም ፈተና ናት።

🍃ዓለም ጊዜያዊ ቦታ እና ከዚህ በኋላ ህይወት መሆኗን የመገንዘቡ እውነታ እራሱ ለዘላለም ሊቆይ የሚገባው ነገር ጊዜያችንን በተቻለ መጠን ጠቃሚ የማድረግ እውነታ ላይ ያጎላል።

🔑በወጣትነት ፣በጉልበት እና ሙሉ ህይወት ባለንበት ወቅት በእጃችን ከነበሩት የታላቁ አላህ ፀጋዎች አንዱን እናጠፋለን ይህም ጤናማ አካል ጥሩ ጤና እና ጊዜ ማለት ነው ።በተለይ በእርጅና እና በምንደክምባቸው ጊዜያት ረዘም ላለ ጊዜ ጥቅም በሚሰጡ ነገሮች ላይ ጊዜዎን ማዋል አስፈላጊ ነው።

💦ለመኖር በጣም የተገደበ ጊዜ ተሰጥቶናል ስለዚህ ከፍተኛ ጥረታችን በእስልምና አስተምህሮ እና በሱና መሰረት ህይወታችንን መምራት አለብን።

💦ህይወታችን ለታናናሾቻችን አርአያ እንዲሆንልን አብረን ዱዐእ እናድርግ።ይህም ለብዙዎች አበረታች ከሆነው የጥሩነት እና የጤንነት ስፋት በስተቀር ሌላ አይደለም።

✏️በበቂ ሁኔታ ልናመሰግነው የማንችለው የአላህ በረከቶች እና ፀጋዎች ብዛት ተሰጥቶናል ስለዚህ ህይወታችንን ጠቃሚ ማድረግ እና ለሌሎችም አዎንታዊ ተጽእኖ መፍጠር አለብን


➡️ አስቸጋሪነት ቀደም ሲል የሠራናቸው የብዙ መጥፎ ወይም ጥፋቶች ውጤቶች ናቸው።ህይወት ሊተነበይ የማይችል እና ሞት የቀን መቁጠሪያ ስለሌለው በተቻለ ፍጥነት ለኃጢአታችን ይቅርታ እንድንጠይቅ ይመከራል።


የጊዜ በረራ የግድ እና አስቀድሞ የተወሰነ ነው። እኛ ነን ወደ ኋላ የቀረን እና በሰአት መሮጥ የሚገባን።

የወዲያኛው ሕይወት ማለቂያ የሌለው የጊዜ መንገድ ተብሎ ታውጇል እናም አሁን ያለው ሕይወት ሌላ አይደለም ነገር ግን ወደፊት የሚሄድ እና በቅርቡ ያልፋል ጊዜያዊ ምዕራፍ ነው እናምአጽንዖታችን መሆን ያለበት ለቀጣዩ ሕይወት ለመዘጋጀት ነው።


عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لِرَجُلٍ وَهُوَ يَعِظُهُ اغْتَنِمْ خَمْسًا قَبْلَ خَمْسٍ شَبَابَكَ قَبْلَ هَرَمِكَ وَصِحَّتَكَ قَبْلَ سَقَمِكَ وَغِنَاكَ قَبْلَ فَقْرِكَ وَفَرَاغَكَ قَبْلَ شُغُلِكَ وَحَيَاتَكَ قَبْلَ مَوْتِكَ‎


ረሱል አለይኺ ሰላት ወሰላም ከኢብኑ አባስ ተይዞ እንዳስተላለፉት፦«አምስት ነገሮች ከአምስት ነገር በፊት ተጠቀምባቸው።


🍃ወጣትነትህ ከእርጅናህ በፊት

🍃ጤናህ ከበሽታህ በፊት

🍃ሃብትህ ከድህነትህ በፊት

🍃ነፃ ጊዜህን ከመጠመድህ በፊት

🍃ህይወታችሁን ከመሞታችሁ በፊት» ብለዋል።

( አል ሀኪም) ዘግበውታል 📚📚


عَنْ ابْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ نِعْمَتَانِ مَغْبُونٌ فِيهِمَا كَثِيرٌ مِنْ النَّاسِ الصِّحَّةُ وَالْفَرَاغُ‎

ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁ)እንዲህ አሉ ረሱል (صلى الله عليه وسلم) እንዲህ አሉ፦«ብዙ ሰዎች የሚያጡት ሁለት በረከቶች አሉ። (እነሱም) ጤና እና መልካም ለመስራት ነፃ ጊዜ ናቸው።»

(ቡኻሪ 8/421)
((سُبُّوُحٌ، قُدُّوسٌ، رَبُّ المَلاَئِكَةِ وَالرُّوحِ)).
🍃🌻
ምክር ለ ኒቃብ እና ጂልባብ ለባሾች እንዲሁም ኒቃብ ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ ነው ለምትሉ እህቶች‼️
➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩

➲ ኒቃብ እና ጅልባብ በሚለብሱ እህቶች ልጀምር
➼ በመጀመርያ ይህንን የተከበረ ልብስ እንድትለብሱ ልባቹሁን ክፍት ያደረገላችሁን አላህ ልታመሰግኑት ይገባል። ይህን የተከበረ ልብስ ስትለብሱ ፅናት ሊኖራቹህ ይገባል። ይህን ልብስ በመልበሳቹህ ብቻ የተለያዩ ሰዎች ከእውነታው የራቀ ትችት ሊሰነዝሩባችሁ ይችላሉ ምናልባት 'ፋራ' ሊሏቹህ ይችላሉ ራሳቸውን 'አራዳ' አድርገው በማሰብ ' ገጠሬ ' ይሏችኋል 'ከተሜ ' የሆኑ መስሏቸው የመሳሰሉ የተለያዩ ትችቶችን ይሰነዝራሉ ይሄኔ ግን እናንተ እውነታው ባገልባጩ መሆኑን ተረድታችሁ በፅናት ወደፊት ልትጓዙ ይገባል። ፋራዎች ተባልን ብላቹህ የለበሳችሁትን ኒቃብ አሊያም ጂልባብ እንዳታወልቁ። አይደለም ፋራ ሌላም ሊሏቹህ ይችላሉና!!!

➭ ሁሌም ሐቅ ላይ ያለ ሰው መተቸቱ የማይቀር ነው ነገር ግን ሐቅ ላይ እስከሆነ ድረስ ትችቱ አይጎዳውም።

➪ ሰለፎች ሐቅ ላይ የነበራቸውን ፅናት ተመልከቱ አይደለም ስድብ ስንት ድብደባ እና ግርፋት ደርሶባቸው ከአቋማቸው ዘንበል አላሉም ። ስለዚህ አርአያዎቻችሁን አላህ ያወደሳቸውን ትውልዶች በማድረግ ከአቋማችሁ በትንሽ ድግሪ እንኳን እንዳትዘነበሉ።

➺ ሶስተኛው እና ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ደሞ የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ማንኛውንም ኢኽላስ የሌለውን ስራ አላህ እንደማይቀበለው ተናግሯል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ኒቃቡን አሊያም ጂልባቡን የለበሳችሁት የአላህን ፊት ፈልጋችሁበት እንጂ የሰውን ፊት ፈልጋችሁበት ሊሆን አይገባም።

➲ ኒቃብ የለበስሽው እገሊት ኒቃብ ለባሽ ናት እንዲሉሽ ከሆነ ትልቅ አደጋ ላይ ነሽ። ይህን ርእስ ብዙ ኒቃብ እና ጂልባብ ለባሾች የተዘናጉበት ጉዳይ ነው።

➻ ከላይ ስታያቸው ማሻአላህ ኢማነኛ ናቸው ነገር ግን ከሰው ተደብቀው የሚሰሩት ስራ ግን በጣም የሚያሳዝን ሆኖ ታገኘዋለህ። አላሁል ሙስተዓን! ለዚህም ይመስለኛል አንዳንድ ጂልባብ ለባሾች በሚሰሩት ስራ ብዙ እህቶች ለምን ጂልባብ ወይም ኒቃብ አትለብሱም ሲባሉ ኢማን በልብ ነው የሚሉት እናም እህቶቼ ሆይ! ኒያችሁንም አስተካክሉ ለልብሱም ክብር ስጡት።

➨ ኒቃብ ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ ነው ወደምትሉ እህቶች ልምጣ ይህ ንግግር በመሰረቱ ችግር ያለበት ንግግር ነው። ምክንያቱም የአህለሱናዎችን ዓቂዳ ይቃረናልና። እንዴት ከተባለ አህሉ ሱናዎች ኢማን በልብ ብቻ ሳይሆን ከስራ ጋርም የተቆራኘ በመሆኑ ነው የሚያምኑት።

➽ ኢማን እና ስራ የተለያዩ ናቸው ኢማን በልብ ብቻ እንጂ ከስራ ጋር ቁርኝት የለውም ብለው የሚያምኑ 'ሙርጂአ' የሚባሉ ጠማማ አንጃዎች አሉ። ስለዚህ ባለማወቅ የነሱን እምነት እያንፀባረቅን ነውና ከዚህ ንግግራችን ልንቆጠብ ይገባናል። እናም እህቶቼ ሆይ! አላህ ያዘዘበት ነገር እስከሆነ ድረስ የአላህን ትእዛዝ ለመፈፀም ስትሉ ኒቃባችሁን ልበሱ። የሚል መልእክት አስተላልፍላችኋለው።

#ወላሁ አዕለም!

ወንድማችሁ ....
La tehzen
➲የተዘረጋ የአላህ ገመድ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➳ክፍል ሁለት ➧ይህ ፣ የተዘረጋ ገመድ (ቁርኣን) የሰውን ልጅ ለመምራት ፣ ለማስተካከል አማኞችን ለመገሰጽ ፣ በደረቶች ውስጥ ያለውን በሽታ ለመፈወስ ፣ ለቁርኣን ባለቤቶች በረከትን ፣ ብርሃንን እና ነጸብራቅን ለማጎናጸፍ አላህ ያወረደው መንገድ ነው፡፡ ➧አሏህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡ كِتَابٌ أَنزَلْنَاهُ…
➭የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት

➲የዓሊምን ደረጃና ቦታ በተመለከተ
“ሙስነድ” እና ሌሎች የሐዲስ መዛግብት ላይ የሰፈሩ ሐዲሶች አብራርተውት ይገኛሉ፡፡ረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይና ታላቅ በሆነው ሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

➧“እውቀትን ፍለጋ የተጓዘ ሰው ፤ ወደጀነት የሚወስደውን መንገድ ያመቻችለታል፡፡
የሚሰሩትን ስራ በመውደዳቸው መላኢካዎች ለእውቀት ፈላጊዎች ክንፋቸውን ያኖራሉ፡፡

➭ለዓሊም በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ፤ በባህር ውስጥ የሚገኙት አሳዎች ሳይቀር ኢስቲግፋር (ይቅርታን) ይጠይቁላቸዋል፡፡ እውቀት ያለው ዓሊም ፣ እውቀት ከሌለው የአላህ ባሪያ ጋር ያለው ልዩነት ልክ በበድር (ጨረቃ ሙሉ በምትሆንበት) ሌሊት በሚወጣው ጨረቃና በሌሎች ከዋክብት መካከል እንዳለው ልዩነት ነው፡፡ ዑለሞች የነብያቶች ወራሾች ናቸው፡፡

➛ነብያቶች ዲናርም ፣ ዲርሃምም አላወረሱም፡፡ ያወረሱት ዒልምን ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ (ከዒልም) የያዘ ፣ የተነባበረ ድርሻ ያዘ፡፡” አህመድ፡21715 አቡዳውድ፡ 3641 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሶሂህ አቡዳውድ፡3671

➳አቡ ሁረይራ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ እንዳስተላለፉ:- ጦበራኒ “አውሰጥ” በተባለው የሐዲስ መዛግብት “ሀሰን” በሆነ ደረጃ ዘግበውታል፡፡ አቡሁረይራ በመዲና ገበያ መካከል ሲያልፍ ፣ ለተወሰነ ሰዓት ቆም አለ፡፡ “እናንተ ገበያተኞች ! ምን ደካማ አደረጋችሁ!” በማለት ተናገረ፡፡

➧“አቡሁረይራ ሆይ! ምንድን ነው?” በማለት ሶሃቦች ጠየቁት፡፡ “የረሡል صلى الله عليه وسلم ንብረት እየተከፋፈለ የእናንተን ድርሻ ሳትይዙ ከዚህ ሆናችኋል!?” በማለት ምላሽ ሰጣቸው፡፡ “የት ነው ያለው?” በማለት ጠየቁት፡፡ “መስጅድ ውስጥ ነው” አላቸው።ወደ መስጅድ ፈጥነው ገሰገሱ፡፡ ደርሰው እስኪመለሱ ድረስ ቆሞ ጠበቃቸው፡፡ “ለእናንተ ምን አላችሁ?!” አላቸው፡፡ “አቡሁረይራ ሆይ! መስጅድ ሄድን ከውስጥ ገባን ፤ የሚከፋፈል ነገር ማየት አልቻልንም” አሉት፡፡

አቡሁረይራም “ከመስጅድ ውስጥ አንድንም አላያችሁ?!” በማለት ጠየቃቸው፡፡ “ከፊሎቹ ሶላት እየሰገዱ ፣ከፊሎቹ ቁርኣን እየቀሩ ፣ ከፊሎቹ ስለሀላልና ስለሀራም እያወሱ አይተናል” በማለት ምላሽ ሰጡት፡፡ አቡሁረይራ “ወዮላችሁ! የረሡል صلى الله عليه وسلم ውርስ ብሎ ማለት እኮ እርሱ ነው” በማለት መልስ ሰጣቸው፡፡ ጦበራኒይ ፊል አውሰጥ፡ 1429 ሐዲሱን አልባኒ ሐሰን ብለውታል ሶሂህ ተርጊብ ወተርሂብ፡83

➛ይህ ነው የነብያት ውርስ ማለት፡፡ ነብያቶች የወርቅ ወይም የብር ገንዘብ አያወርሱም፡፡ ነብያቶች እውቀትን ነው የሚያወርሱት፡፡ የአንድ ሰው የእውቀት ድርሻው ከፍ ባለ ቁጥር ፣ ከነብያቶቸ ውርስ ድርሻው ከፍ እያለ ይሄዳል፡፡

ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ ሙስሊም፡1037



🖊ኢንሻአላህ ይቀጥላል


📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ

➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴



https://t.me/httpsLatahzen
🔰The Hadith of the Day🔰


▪️የአላህ መልክተኛ(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ከዕለታት አንድ ቀን ከባለደረቦቻቸው ቁጭ ብለው ሳለ፦
# “ድሐ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ?”
በማለት ይጠይቃሉ።
ሰሐቦችም ፦
#“እኛ ጋር ድሀ ማለት ምንም ንብረትና ገንዘብ የሌለው ነው።” በማለት ይመልሳሉ።
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ግን፦
# “ከኡመቴ ደሀ ማለት የትንሳኤ ቀን በብዙ
#ሰላቶች፤ ዘካዎችና፤ ፆሞች የሚመጣ ሰው ነው፣ግና ይህ ሰው አንድ ወንድሙን ሰድቧል፣ ሌላው ላይ ዋሽቷል፣የአንዱን ገንዘብ ያለአግባብ ወስዷል፣የሌላውን ደም አፍስሷል፣አንዱን መትቷል፣ በሌላው ላይም ድንበር አልፏል፣ ያኔም (የትንሳኤ ምርመራ ቀን ) የራሱን ጥሩ ሥራዎች ለበደላቸው በካሳ መልክ አሳልፎ ይሰጣል፣ጥሩ ሥራው ለመካሻ አልበቃ ይለውና የበደላቸውን ሰዎች ኃጢያት ይሸከማል። ከዚያም ወደ ጀሀነም ይወረወራል።”
በማለት መለሱላቸው።

📚(ሙስሊም ሀዲሰ ቁ.6531)

📩አላህ ከክስረት ይጠብቀን 🤲በሰዎች ጉዳይ አያገባንገብተን በምላሳችንም ሆነ በእጆቻችን አንድንአማኝ ከመጉዳት አላህ ይጠብቀን 🤲🤲

•════•••🌺🍃•••════•
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል አራት

➲ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ትክክለኛ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

"من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين"

“በእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ዲንን ያስገነዝበዋል” ቡኻሪ፡ 71ሙስሊም፡1037

➧“ኸይረን” የሚለው ቃል በነኪራ (ሁሉን በሚያካትት ቃል) መምጣቱ ክብደትን እና
ልቅናን እንዲሁም በአላህ ዲን የታነጸ ሰው የሚለቅመው ጠቃሚ ፍሬ ከፍተኛ መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው ዕውቀትን በመፈለግ ላይ እንቅስቃሴ ከጀመረ አላህ መልካሙን እንደሻለት የሚያመክት ነው ማለት ነው፡፡

➲ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“በዚህ ሐዲስ የተፈለገው ተግባርን ያጣመረ የዲን እውቀት ነው፡፡ ከተግባር ነጻ የሆነ
እውቀትን የፈለገ ሰው አላህ መልካም ሽቶለታል ማለትን አያመላክትም፡፡”

➭ይህ ማለት ፣ ዲንን ሊገነዘብና ወደተግባር ሊቀይረው ይገባል ማለት ነው፡፡ የመማሩ ዋናው አላማ ከራሱ ላይ ማህይምነትን ማስወገድ ፣ በእውቀት ላይ ተንተርሶ አምልኮን ለአላህ ብቻ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ አይነት ባህሪ ላይ ከሆነ መልካምን ለማግኘት ተገቢ ይሆናል ማለት ነው፡፡

➛ለተግባር እውቀት በጣም ተፈላጊ ነው፡፡ እውቀት ፣ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ለማድረግ አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህ ነው ከተግባር በፊት እውቀት ተቀዳሚ የሆነው፡፡ ተግባር፣ አምልኮ ፣ ወደአላህ መቃረብ ከአላህ ኪታብና ከነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱና በመነጨ ጠቃሚ እውቀት ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት፡፡ ሚፍታህ ዳሪ አስ ሳዓዳ፡1/65

➧በዚህ ታላቅ ርዕስ ዙሪያ ጥቅል መረጃዎችን እና ታላላቅ የሰለፎችን ንግግር ያካተተ“ኢቅቲዷኡል ዒልም አልዓመል” የተባለ ምርጥ መጽሐፍ ኸጢብ አል'በግዳድይ -ረሂመሁሏህ - ጽፈዋል፡፡

➲“ኢቅቲዷኡል ኢልም አልዓመል” የተባለው ኪታብ የእውቀት አላማው ተግባር እንደሆነ ፣ በእውቀትና በማስረጃ ላይ በመንተራስ አምልኮን ፍጹም ለአላህ ብቻ ማረጋገጥ እንደሚገባ ትኩረት ይሰጣል፡፡ አንድ ባሪያ እውቀት ኖሮት ስራ ከሌለው ፣እንዲሁም ያለእውቀት ተግባር ብቻ ከሆነም አምልኮ በትክክል ተረጋግጧል ማለት አይቻልም፡፡

➧የአላህ አምልኮ በሁለት ነገሮች ካልሆነ ሊረጋገጥ አይችልም፡፡ በጠቃሚ እውቀት እና በመልካም ተግባር፡፡

አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

هُوَ الَّذِي أَرْسَلَ رَسُولَهُ بِالْهُدَىٰ وَدِينِ الْحَقِّ لِيُظْهِرَهُ عَلَى الدِّينِ كُلِّهِ وَلَوْ كَرِهَ الْمُشْرِكُونَ

“እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልእክተኛው (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡” አት ተውባህ፡33

➭“ሁዳ” ፡ ማለት ጠቃሚ እውቀት ማለት ነው፡፡ “ዲኑል ሐቅ” ማለት ደግሞ ወደአላህ የሚያቃርብ መልካም ተግባር ማለት ነው፡፡“ዲኑል ሐቅ” ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲሁም አጠቃላይ ነብያቶች የተላኩበት ነው፡፡



እንሻአላህ ይቀጥላል

📚ዓብዱረዛቅ ብን ዓብዱልሙህሲን አል ዓባድ ኪታብ የተወሰደ በየሱፍ አህመድ የተተረጎመ
Nurahemd
➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
ሙሀመድ ሠ.ዐ.ወ
የኔ በ ጅህልና ከቁረይሾች መሀል
እነሡ የሚያውቁት ውበቱ የሚያማል
ሀቀኛ የሆን ሠውን የማያታልል
አላህ ፈለገልና ለዚህ ኡመት መሪ
ሠውን ያሚመራ ህይወትን መርማሪ
ኢሰለምን ሚያሳፋፋ ዲኑን አስተማሪ
ሙሀመድን ላከ ለዚህ ኡመት መሪ
ፅድት ያልኩ ሙስሊም ነኝ

አዎ እኔ ሙስሊም ነኝ
እኔማ ሙስሊም ነኝ ምንም ሽርክ የሌለኝ
ከእስልምና በቀር የኔ ምለዉ የለኝ
ቢርበኝ ቢጠማኝ ዲኔን ብቻ ያለኝ
እኔማ ሙስሊም ነኝ
ከምንም ሚበልጠዉ የእስልምናን አለኝ
በማንኛዉም ጊዜ በደስታ ሚያኖረኝ

እኔማ ሙስሊም ነኝ
፨ ለጦቢብ ሰው እውነተኛ ገንዘቡና
ሃብቱ አራቱ ነገሮች ናቸው ።


1} ከአንድበቱ የሚወጣው ቃል
እውነትመሆኑ

2} ንዴትና ቁጣውን መግዛት መቻሉ ።

3} ለስጋዊ ፍላጎቱ የማይስገበገብ
መሆኑ

4} በሁሉም ነገር ላይ የሚታመን
ሰው መሆኑ
የሰው ዘር መጀመሪያ የሆኑት #አደም

ልዩ የክብር ቦታ የተሰጣቸው #እንድሪስ

950 ዓመታት በማስተማር የቆዩት #ኑህ

ወደዓድ ህዝቦች የተላኩት #ሑድ

ድንጋይ ተፈልቅቆ ግመል የወጣችላቸው #የሰሙዱ ሳሊህ።

የኑምሩድን እሳት ድል በማድረግ የወጡት #ኢብራሒም

መላእክት በእንግድነት ወደቤቱ የገቡት #ሉጥ

በካዕባ ግንባታ የተሳተፉት #ኢስማኢል

የአባታቸው የኢብርሂም ልድ #ኢስሐቅ

የ12 ወንድ ልጆች አባት የሆኑት #ያዕቆብ

እጅግ ታጋሹና ጥበበኛው #ዩሡፍ

መከራን ቻዩና ጸሎተኛው #አዩብ

የሁለት ሴቶች አባት የሆኑት የመደኑ #ሹዓይብ

ባህር የተሰነጠቀላቸው የኢምራን ልጅ #ሙሳና ወንድማቸው #ሐሩን

በዓሣ ሆድ ውስጥ ዚክር ያደረጉት የነይነዋው #ዩኑስ

ብረት እንደጭቃ የሚለዝብላቸው ድምጻዊው #ዳውድ

ንፋስን እንደፈለጉ የሚያዙት ንጉሱ #ሱለይማን

ቁርኣን ስማቸውን እንጅ ያላስዋወቀን አልየሰእ፤ #ኢሊያስና #ዙልኪፍል

አናጺውና የመሪየም አሳዳጊ #ዘከርያ

በልጅነታቸው ነብይነትን የተሰጡት #ያህያ

ያለአባት የተወለዱት ተአምረኛው የመሪየም ልጅ #ዒሣ

ለተልእኳቸው የቦታና የዘመን ግርጾሽ የተነሳላቸው #ሙሐመድ ናቸው።

እንግዲህ ከአላህ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል በተላኩት ነቢያት በሙሉ ያለምንም ልዩነት ማመን ይኖርብናል።
ታላላቅ ነገሮችን የሚያሳጡ ሶሳት
(አደገኛ) ነገሮች ፦
======"""""""""""""""======
1. {ተነሳሽነት ማጣት}
------------------😕------------------------
2. {የእውቀት ማነስና}
____________📘______________
3. {የአስተውሎ ድክመት}
-----------------😮-------------------------
(አቢ ዐብዱላህ አስ-ሳድቅ) °°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°