La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
#ያኔ___አልቅስ!!!
#ነፍስህ ስሜትህን ከመቆጣጠር #ደካማ ሆና! በሀራም ስራ ላይ #ጠንክራ ስታገኛት! #ያኔ__አልቅስ!
#መጥፎ ስራ አይተህ #በማትጠላበት ጊዜ! እንዲሁም!
መልካም ስራን በምታሳንስበት ጊዜ! #ያኔ__አልቅስ!
ነፍስህ መሳጭ የሆነ ፊልም #አይታ ወይም ዘፈን #ሠምታ በምታለቅስበት ጊዜ!
እንዲሁም #ለቁርዐን በማታለቅስበት ጊዜ!
#ያኔ__አልቅስ!
#ሶላትህ ከአምልኮ ወደ #ባህል!
እንዲሁም!
#ከማረፊያ ወደ #መቸገሪያ ሲቀየርብህ!
#ያኔ__አልቅስ!
#የዕድሜያችን ብዙ ክፍል በማለፍ ላይ እያለ! እኛ ግን???????

https://t.me/httpsIBNumuhammed
<< << < ጊዜና ልጅነት > >> >>
ቀን ቀንን ሲተካ ሲከንፍ እንደዋዛ
ሲመለሱ አይኖርም ያረገፉት ጤዛ
እንዲህ ነው ልጅነት በቀን የሚጨልም
ካለፈ በኃላ የማይኖሩት አለም
የማለዳም ፀሀይ አምሮባት የዋለች
ሠዓቷን ጠብቃ ማታ ትጠልቃለች
ጊዜው እየሮጠ እድሜ እየከነፈ
ከቀን ጋር ተዋግቶ የለም ያሸነፈ
ልጅነት በጊዜ ጦር እየተመታ
የማለዳ ውበት አይገኝም ማታ
የሠው ልጅ ሁልጊዜ ልጅነት ቢመኝም
ልጅ እንጅ ልጅነት ዳግም አይገኝም።


https://t.me/httpsLatahzen
▫️ጃዕፈር ኢብን አቡጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

ክፍል አንድ 1⃣
✿•••✿•••✿

《ጀዕፈርን፥ ጀነት ውስጥ ሁለት በደም የደመቀ ክንፎች ባለቤት ሆኖ አየሁት።》
«🎤ነብዩ ሙሐመድ ﷺ»

ምንም እንኳን በቁረይሾች ታላቅ የክብር አይን ቢታዩም የረሱል ﷺ አጎት አቡ-ጧሊብ በሀብት ረገድ ድሀ ነበሩ።

ቤተሰባቸውን መቀለብ የተሳናቸው የብዙ ልጆች አባት የሆኑት አቡጧሊብ ምድረ ዓረቢያን ድርቅ ሲመታት ችግሩ ተባባሰባቸው። ሰብሎችን ያጠፋውና ከብቶችን የፈጀው ረሃብ፥ ህዝቡ ከሞት ለማምለጥ ሲል አጥንት እንዲቆረጥም አስገድዶት ነበር። ነብዩ ረሱል ﷺ ለነብይነት ገና ባልታጩበት በዚህ ቀውጢ ወቅት አጎታቸውን አባስን «የወንድምህ የአቡ-ጧሊብ ቤተሰቦች ብዙ ናቸው። ሰው በረሃብ እያለቀ ስለሆነ የተወሰኑትን በመውሰድ እንርዳው» በማለት ሀሳብ አቀረቡ።

አባስም በሀሳቡ ተስማማ አባስ ከረሱል ﷺ ጋር ወደ አቡ ጧሊብ ሄደው ሀሳባቸውን አቀረቡ። አቡ ጧሊብ የዓሊይን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ታላቅን አቂልን ትተው ከሌሎቹ መርጠው መውሰድ እንደ ሚችሉ ነገሯቸው።

ረሱል ﷺ #ዓሊይን ረ.ዐ አባስ ደግሞ #ጃዕፈርን ረዲየሏሁ ዐንሁን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል ወሰዷቸው።

ከሃሺም ጎሳ #አምስት ሰወች ነብዩ ሙሀመድን ﷺ በመልክ በጣም ይመስሉ ነበር ይባላል።

ያጎታቸው ልጆች #አቡሱፍያን ኢብን አል-ሃሪስና #ቁሳም ኢብን አል አባስ፤ የኢማሙ ሻፊኢይ አያት #አስ-ሳኢብ ኢብን ኡበይድ እንዲሁም ከሁሉም በጣም የሚመስሏቸው የልጃቸ ው ልጅ #ሐሰን ኢብን ዓሊይና የአጎታቸው ልጅ #ጀዕፈር ኢብን አቡ ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁም ነበሩ።

የትዳር እና የኢስላም ህይወት
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ በወጣት እድሜው #አስማ ቢንትዑመይስን ረዲየሏሁ ዐንሀ አግብቶ ከአባስ በመለየት ጎጆ መሰረተ። በአቡበክር አስ-ሲዲቅ ረዲየሏሁ ዐንሁ አማካኝነት ከሚስቱ ጋር ኢስላምን በመቀበል ከመጀመሪያወቹ ሙስሊሞች ሆነ። የጀነት መንገድ በሾክ መሞላቷን የተረዱት ጀዕፈርና ሚስቱ ረዲየሏሁ ዐንሁም በቁረይሽ የሚደርስባቸውን ጭካኔና ግፍ በትዕግስት ሊወጡት ቢሞክሩም ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ የመጣው የ ቁረይሽ ሴራ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ ፦
«ጌታችን አላህ አንድ ነው» ስላሉ ብቻ በደል እየተፈፀመባቸው ያሉት ንፁሃን ሰዎች ዕጣ ያሳዘናቸው ነብይ ﷺ ወደ ሀበሻ እንዲሰደዱ ትዕዛዝ ሰጡ።

▫️ ስደት ወደ ሐበሻ ▫️
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

በጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ መሪነት ወደ አቢሲኒያ (ኢትዬጵያ) የመጀመሪያው ስደት ተደረገ። በፍትሀዊው የኢትዮጵያ ንጉስ ነጃሺ ጥላ ስር በመሆን ሃይማኖታ ቸውን በነፃነት በመተግበር አላህን የመገዛትን ጣዕም ሊቀምሱ ቻሉ። የስደተኞቹ በሰላም መኖር የእግር እሳት የሆነባቸው የቁረይሽ ሹማምንት ወደ መካ የሚመልሱባቸውን መንገድ ያውጠ ነጥኑ ጀመር።

ለዚህ ተግባር የቁረይሽ ግፈኞች #አምር ኢብን አልአስና #አብዱላህ ኢብን አቢ ራቢያን በመወከል ከበርካታ ስጦታወች ጋር ወደ ንጉሱና ጳጳሳቱ ላኩዋቸው።

ኢትዮጵያ እንደደረሱ ለስጦታ ያመጧቸውን ንብረቶች ለጳጳሳቱ በመለገስ «በንጉሱ መሬት የሚንቀሳቀሱ አመፀኛ ወጣቶች አሉ። በአባቶቻቸው ሀይማኖት ላይ ያፌዛሉ፣ ይኮንኑታልም። በህዝባችን መካከል ሁከትና መከፋፈልን ፈጥረዋል። ንጉሱን ስናነጋግር ስለ ሃይማኖታቸው ምንነት ሳይጠይቋቸው እንዲያስረክቡን ጎትጉቱልን። የተከበሩት የህዝባችን መሪወች ስለ እነሱም ሆነ ስለ ሀይማኖታቸው ከሁሉም በላይ ያውቃሉ» አሏቸው። ጳጳሶቹም ተስማሙ።

📦 አምርና ዐብደላህ ብስጦታቸው ለተደሰተው ነጃሽ 《ንጉስ ሆይ! ርኩሳን ወጣቶች ከኛ አምልጠው ወደ ግዛተዎ መጥተዋል። እኛም እርሶም የማናውቀውን ሃይማኖት ይከተላሉ። በወላጆቻቸው እና በህዝባቸው ላይ ያመፁ አፈንጋጮች እንድትመልሱልን የተከበሩ መሪዎቻችን ልከውናል።» ሲሏቸው ንጉሱ ወደ ጳጳሳቱ ዞር ብለው ሲመለከቷቸው።

«ንጉስ ሆይ! እውነታቸውን ነው የተንናገሩት። በህዝባቸው ላይ ምን ፈፅመው እንደመጡ ስለሚያውቁ ለፍትሀዊ ፍርድ ወደነርሱ ይላኩዋቸው» አሉ።

🎙 በአስተያየታቸው የተቆጡት ንጉስ ነጃሽ «በፈጣሪ ይሁንብኝ! ለምን እንደተወነጀሉ እራሴ ሳላጣራ አሳልፌ አላስረክባቸወም። እነዚህ ሁለት ሰዎች የሚሉት እውነት ከሆነ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ። ካልሆነ ግን የእኔን ጥበቃ እስከፈለጉ ድረስ በኔ ምድር ይኖራሉ።» በማለት አስደነገጧቸው።

ንጉሱ ሙስሊሞቹ ለችሎት እንዲቀርቡ
አዘዙ። ሙስሊሞቹ ከመሄዳቸው በፊት እነሱን ወክሎ #ጀዕፈር ኢብኑ አቢ-ጧሊብ ረዲየሏሁ ዐንሁ ብቻ እንዲናገር ተስማሙ በንጉሱ ቤተ መንግስት ጳጳሳቱ የሚያምር አረንጓዴ ልብስና ማራኪ ቆብ ደፍተው ከንጉሱ ወንበር ግራና ቀኝ ቁጭ ብለዋል ሙስሊሞቹ ሲገቡ ቁረይሾቹ ቦታቸውን ይዘው ነበር። ንጉሱ መጡ።

ቀሳውስት፣ ጳጳሳት፣ ቁረይሽ ወዘተ.. ከሙስሊሞች በስተቀር ሁሉም ለንጉሱ አጎነበሱ።

ንጉሱ ሙስሊሞቹን ለምን የክብር ሰላምታ እንዳልሰጡ ሲጠይቋቸው

🎤 «እኛ ለአላህ እንጅ ለሌላ የማናጎነብስ ህዝቦች ነን። »በማለት ነበር በታሪክ የማይረሳውን ቃል ጀዕፋር ረዲየሏሁ ዐንሁ የመለሱት።

🎙 ንጉሱ በመገረም «ለመሆኑ ከህዝቦቻችሁ ጋር ሆድና ጀርባ ያደረጋችሁ እምነት ምን አይነት ነው? ወደ እኔ ወይም ወደ ሌላ ህዝቦች ሃይማኖት ለምን አልገባችሁም?» በማለት ጠየቁ።

ጀዕፈር ረዲየሏሁ ዐንሁ ወደፊት ቀረብ በማለት በቅን ልሳን የመካ ሰውን ሁኔታ፣ የኢስላምንና የረሱልን ﷺ ሚና ቁልጭ አድርጎ አቀረበ።


🎤 እንዲህ ነበር ያለቸው፦ «ንጉስ ሆይ! በድንቁርናና በምግባረ ብልሹነት የተዘፈቀን፣ ጣዖት አምላኪ፣ የሞተ እንስሳ ተመጋቢ፣ አሰቃቂ እና አፀያፊ ስራወችን የምንፈፅም፣ ዝምድናን የምንቆርጥ፣ እንግዳ የምናስከፋ ህዝቦች ነበርን። ኃይለኛውም ደካማውን የሚበዘብዝ በት ሁኔታ ነበር። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን አላህ ማንነቱን፣ ቤተሰቡንና እውነተኝነቱን የማንክደው መልእክተኛ ላከልን።
እሱም ፦ እውነትን ብቻ እንድንናገር፣ ውለታችንን እንድናከብር፣ ለዘመድ መልካም እንድንውል፣ ጎረቤቶቻችንን እንድንረዳ፣ ከተከለከሉ ነገሮች ሁሉ እድንርቅ፣ ያለ አግባብ ደም ከማፍሰስ እንድንታገድ፣ ከብልግና ተግባሮች እንድንርቅ፣ በውሸት እንዳንመሰክር፣ የሙት ልጅ ሀብት አጭበ ርብረን እንዳንወስድ፣ የንፁህ ሴቶችን ስም እንዳናጠፋና በሀሜት እንዳንለውስ፣ በአላህ ሳናጋራ እሱን ብቻ እንድናመልክ፣ ሶላት እንድንሰ ግድ...አዘዘን። ያዘዘንን በመስራት፥ ከከለከለን ነገር በመከልከል ከእሱና ከአላህ በመጣልን መልዕክት አመን።»

« ክቡር ንጉስ ሆይ! ህዝባችን አሰቃየን ሃይማኖታችንን ክደን ወደድሮው አስፀያፊ ጣዖት አመልኮት እንድንመለስ ለማድረግ አሰቃቂ ቅጣቶች ፈፀመብን። ጨቆነን። ህይወታችንን መምራት አቃተን።የእምነታ ችንን ግዴታወች ማከናወን ተሳነን ለዚህ ነው ሀገራችንን ጥለን በመሰደድ ከሁሉም በፊት እርሰወን መርጠን በመሬትዎ በፍትህና በሰላም ለመኖር የመጣነው።»

▫️ንጉሱ በገለፃው ተማርከዋል። ቢሆንም ነገሩ በዚህ አልተገታም፦

።።ክፍል ሁለት

ይቀጥላል ኢንሻ አላህ






https://t.me/httpsLatahzen
🌿 ረመዳን 🌿
––––––––––

ረመዳን መጣ ሁሉም ሰው ይደሰት፣
ይዘጋጅ ካሁኑ ራሱን ለማንፃት፣
እንጠቀምበት ይህን የራህመትወር፣
ኸይር ስራ ሰርተን ለማግኘት ብዙ አጅር፣
አይሁን መገለጫው ቴምርና ሾርባው፣
ለስላሳ ኩኪሱ እንዲሁም ሳምቡሳው፣
ይህ አይደለም እኮ የረመዳን ገፅታ፣
ባይነት ማዘጋጀት የምግብ ጋጋታ፣
አይጥፋ ጊዜያችን በመስራት ምግቦችን፣
አይጠቅመንምና ለአኼራ ቤታችን፣
ከልብ አስተውለን እንጠቀምበት፣
ጀነትን እንናፍቅ ዱንያን ትተናት፣
የልመና ወር ነው የምናለቅስበት፣
ወንጀላችን እንዲማር የምንጠይቅበት፣
የበረካ ወር ነው ሪዝቅ የበዛበት፣
ትንሿ ለብዙ የምትበቃበት፣
የ ቀርዓን ወር ነው የትግስት የፅናት፣
የአላህ ራህመት በዝቶ ሚታይበት፣
በዚ በበረካ በዚ በእዝነት ወር፣
ይሞላ ውስጣችን በዱአ በዚክር፣
እንፍጠን እንቅደም ራህመት ለማግኘት፣
ካሁኑ እንነይት ለመሆን የጀነት፣
ካለፈ በኃላ ዞሮ ከመቆጨት፣
ወሩን ከኸይር ስራ እንጠቀምበት።
@Nurahend



https://t.me/httpsIBNumuhammed
•:
አራቱ የአላህ ﷻ ቃልኪዳኖች

1• ብታመሰግኑኝ እጨምርላችኃለው።

2• አስታውሱኝ አስታውሳችኃለው።

3• ጠይቁኝ እሰጣችኃለው።

4• ምህረት ጠይቁኝ እምራችኃለው።
አሪፍ የሆነች ሰለፊይ ሴት ስታገባ፤ ልክ እንደዚህ ምግብ ስታቀርብ ራሱ አላህን እንድትፈራና ቀብርን እንድታስታውስ ታደርግሀለች።


እህእ ፎቶው ተመችቶኛልስ¡
ኢስቲቃማ

አላህ ባዘዘን ላይ ስንገኝ ቆመን
የ ተከለከልነውን ስንገኝ ርቀን
ኢስላም ባፀደቀው በሁሉም ካመን
ባመነው ነገረ ላይ ከዛም ቀጥ ካልን
ጀናን በአሏህ ፈቃድ እናገኛታለን
➧የቁርኣን ሰዎች ማን ናቸው?
🌸🍃

➧ኢብኑል ቀዪም እንዲህ አሉ:-

🌹የቁርኣን ባልተቤቶች ማለት:- ቁርኣንን በልባቸው ሸምድደው ባይዙም እንኳን የቁርኣንን መልእክት የተረዱና በቁርኣን ውስጥ በተጠቀሱ ብይኖች የሚሰሩ ናቸው።
ቁርኣንን ሓፍዞ (ሸምድዶ) መልእክቱን ያልተረዳና በቁርኣን ውስጥ በተጠቀሱ ድንጋጌዎች የማይሰራ የቃላት አሰካኩን አሳምሮና ቀጥ አድርጎ ቢያነበንበውም በፍፁም የቁርኣን ሰው አይባልም።"

📚ዛዱ'ል መዓድ

ﺯﺍﺩ ﺍﻟﻤﻌﺎﺩ [٣٢٧/١]
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
ነብዩ ﷺ በመሰደባቸው የተቆጣው ውሻ
━━━━━━✦✿✦━━━━━━

: ከሞጎላዊያን አንድ ባለስልጣን የክርስትናን ሃይማኖት ከተቀበለ ጥቂት ጊዜያት በኋላ ሀይማኖቱን መቀበሉን አስመልክቶ በተዘጋጀ ድግስ ከተወሰኑ ቄሳውስቶች ጋር ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። ከአቅራቢያቸው አንድ ለአደን የተዘጋጀ ውሻ ታስሯል።
: በወቅቱ ከነበሩ ቄሶች አንዱ ለዓለማት እዝነት የተላኩትን ታላቁን ነቢ ሙሀመድ ﷺ በመጥፎ ማንሳትና መተቸት ብሎም መሳደብ ጀምሯል። ታዲያ ይህንን ሲሰማና ሲታዘብ የነበረው ውሻ እጅግ ተቆጣ ፤ ወዲያውኑ በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸ ተሳዳቢውን ቄስ ዘሎ ነከሰውና አቆሰለው ፤ በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎችም ተረባርበው አዳኑት ። ሰዎቹም፦ "ውሻው የምትናገረው ነገር አልተስማማውምና ሰለ ሙሀመድ (ﷺ) መጥፎ ከመናገር ተቆጠብ" ይሉታል ፤ ሰውየው ግን ፦ "አይ ችግሩ ከምናገረው አይመስለኝም ባይሆን በምናገርበት ወቅት እጄን ስዘረጋና ሳንቀሳቅስ ስለነበር እሱ ላይ የጠቆምኩበት መስሎት ነው" በማለት ስድብና ትችቱን ቀጠለ። ውሻው ግን ከመጀመሪያው በከፋ መልኩ በከፍተኛ ቁጣና ንዴት ዘሎ ጉሮሮውን በመንከስ ሰውየውን ገደለው።

👉 ይህ ክስተት በጊዜው የነበሩ ሰዎችን በከፍተኛ መልኩ አስገርሞ ነበር ፤ በዚህም ውሻ ምክንያት በወቅቱ ወደ 40 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ።

👉 ክስተቱን ታላቁ አሊም ኢብኑ ሀጀር "አዱረሩል ካሚናህ" በተባለው መፅሃፋቸው አስፍረውታል።

የአላህን ሰራዊቶች እርሱ እንጂ ማንም አያውቃቸውም


ﺍﻟﻠﻬﻢّ ﺻﻞِّ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﻤّﺪ ﻋَﺒْﺪِﻙَ ﻭﻧَﺒِﻴِّﻚَ ﻭﺭﺳﻮﻟِﻚَ ﺍﻟﻨﺒﻲِّ
ﺍﻷمي"
➪ባለቤትሽን ስለ መልካምነቱ ማመስገንሽ ፍቅራችሁን ከማጎልበቱና እሱን
ለበለጠ መልካምነት ከማበረታታቱ ባሻገር አላህን ማስደሰት ነው!!
ﻗﺎﻝ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ : ‏(ﻻ ﻳﻨﻈﺮ ﺍﻟﻠﻪ ﺇﻟﻰ ﺍﻣﺮﺃﺓ ﻻ ﺗﺸﻜﺮ ﻟﺰﻭﺟﻬﺎ ﻭ ﻫﻲ ﻻ
ﺗﺴﺘﻐﻨﻲ ﻋﻨﻪ ‏) ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﻨﺴﺎﺋﻲ ﻭ ﺻﺤﺤﻪ ﺍﻷﻟﺒﺎﻧﻲ ﻓﻲ ﺍﻟﺼﺤﻴﺢ 289
𒊹︎︎︎የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤
«ከባሏ የማትብቃቃ ስትሆን ባሏን የማታመሰግን ሴት፣ አላህ በእዝነት አይኑ
አይመለከታትም።”
𑁍 ኢማሙ ነሳኢ ዘግበውታል፤ አልባኒም ሰሒህ ብለውታል
🔻የምፈራላችሁ ነገር ቢኖር ስሜትን መከተልንና ምኞትን ማስረዘም ነው።

🔻ሰሜትን መከተል ሐቅን እንዳንቀበል ያረጋል።
ምኞትን ማስረዘም አኺራን ያስረሳል።

🔻ዱንያ ጀርባዋን ሠጥታን እየሄደች ነው፤
አኺራ ፊቷን ወደኛ አዙራ እየመጣች ነው፤
የአኺራ እንጂ የዱንያ ሰው አትሁኑ ፤

🔺ዛሬ ሥራ እንጂ ምርመራ የለም፤
ነገ ምርመራ እንጂ ሥራ የለም።

🔺ዐልይ ኢብኑ አቡ ጧሊብ ረደሏሁ አንሁ
اللَّهُ أَكْبَرُ كَبِيرَاً، اللَّهُ أَكْبَرُ كَبِيراً، اللَّهُ أَكْبَرُ كَبِيراً، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثيراً، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثيراً، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثيراً، وَسُبْحَانَ اللَّهِ بُكْرَةً وَأَصِيلاً
🍃🌻
⛔️ከሰዋች ሁሉ ሌባ ማን ነው⁉️

♻️ነብዩ ( صلى الله عليه وسلم )፡- #በስርቆት አደገኛው ሰው ማለት ከሠላቱ ላይ የሚሰርቅ ነው፡፡; ሲሉ፦
🔰ሠሓቦች፡ «ከሰላቱ ላይ የሚሰርቀው እንዴት ነው?» በማለት ጠየቁ፡፡
♻️እሳቸውም፡ #ሩኩኡንም ሱጁዷንም በማጓደል ነው። በማለት መለሱላቸው
📚 (አህመድ 22642)

በሠላት ውስጥ የማይረጋጋ ሰው፣ በሠላቱ ሊመሰጥ አይችልም፡፡ ምክንያቱም መፍጠን መመሰጥን ስለሚጻረር ነው፡፡ እንደ አሞራ ጎንበስ ቀና ማለት ምንዳን ያሳጣል፡፡

ነብዩ ( صلى الله عليه وسلم ) ሠላትን ሲሰግዱ፣ በሩኩዓቸውም በሱጁዳቸውም ውስጥ፣ እያንዳንዱ መገጣጠሚያቸው ወደ ቦታው እስኪመለስ ድረስ በመረጋጋት ነበር፡፡ ሠላቱን ማሳማር ያልቻለውን ሰውዬ፣ በሠላቱ ውስጥ በሚፈፅማቸው ተግባሮችን በሙሉ በእርጋታና በዝግታ እንዲፈፅም አዘውታል፡፡ መቻኮልን ከልክለዋል፤ችኮላን ከአሞራ ውሃ አጠጣጥ ጋር አመሳስለውታል፡፡
🔰🔰የዕለቱ ሀዲስ🔰🔰

"▪️ከአቡሁረይራ በተዘገበ ሀዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፤

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ : ”...احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ وَاسْتَعِنْ بِاللهِ وَلَا تَعْجَزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَرٌّ فَلَا تَقُلْ لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا وَكَذَا قُلْ قَدَّرَ اللهُ وَمَا شَاءَ اللهُ فَعَلَ، فَإِنَّ لَوْ تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَانِ“ رَوَاهُ مُسْلِم
ٌ
«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አትሰላች፤ መጥፎ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ፤ ‘ይህን ነገር እንዲህ ወይም እንዲያ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል


📝አላህ ተቅዋን እና መልካም ስራን ያግራልን!

وصلَّى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم
የቲም

🏷የቲም ማለት:– ሴትም ሆነች ወንድ ለአቅመ አደም ሳይደርሱ አባታቸው የሞተባቸው ናቸው። እነሱም የሚታዘንላቸው የእዝነት ስፍራዎች ናቸው፣ ምክንያቱም ልባቸው በአባታቸው ሞት ተሰብራለች፣ አጋዥም ሆነ ተንከባካቢ ከአላህ በስተቀር የላቸውም።


⛔️የወላጅ አልባ (የቲም) ህፃናትን ሀቅ መብላትና እነሱንም መበደል ነው።‼️

⚠️4፥2 *"የቲሞችንም ገንዘቦቻቸውን ስጡ፡፡ መጥፎውንም በመልካሙ አትለውጡ፡፡ ገንዘቦቻቸውንም ወደ ገንዘቦቻችሁ በመቀላቀል አትብሉ እርሱ ታላቅ ኃጢአት ነውና"*፡፡

وَآتُوا الْيَتَامَىٰ أَمْوَالَهُمْ ۖ وَلَا تَتَبَدَّلُوا الْخَبِيثَ بِالطَّيِّبِ ۖ وَلَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَهُمْ إِلَىٰ أَمْوَالِكُمْ ۚ إِنَّهُ كَانَ حُوبًا كَبِيرًا


﴿إِنَّ الَّذينَ يَأكُلونَ أَموالَ اليَتامى ظُلمًا إِنَّما يَأكُلونَ في بُطونِهِم نارًا وَسَيَصلَونَ سَعيرًا﴾ النساء ١٠
⚠️“እነዚያ የየቲሞችን ገንዘብ በመበደል የሚበሉ: በሆዶቻቸው ውስጥ የሚበሉት እሳት ብቻ ነው፣ እሳትንም በእርግጥ ይገባሉ።” (ኒሳእ 10)

⚠️ከ7ቱ አጥፊ ወንጀሎች አንዱ ነው።
የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
"ሰባት አጥፊ ወንጀሎችን ራቁ።" ሶሐቦች ምንድን ናቸው? ሲሉ ጠየቁ። የአላህ መልዕክተኛ: "በአላህ ማጋራት ፣ድግምት ፣በህግ ቢሆን እንጅ ያችን አላህ እርም ያደረጋትን ነፍስ መግደል፣ ወለድ መብላት ፣ #የየቲምን_ገንዘብ_መብላት፣ የጦርነት ቀን መሸሽ እና ጥብቅ፣ ከዝሙት የዘነጉ ምእምናትን መስደብ ናቸው።" አሉ። "

📚ቡኻሪ ዘግበውታል።

⚠️ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 33, ሐዲስ 22
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"አላህ ሆይ! ምስክር ሁን! እኔ ያስጠነቀቁት ሁለት ድኩማን ጉዳይ አሉኝ፥ እነርሱም የቲም እና እንስት ናቸው"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ اللَّهُمَّ إِنِّي أُحَرِّجُ حَقَّ الضَّعِيفَيْنِ الْيَتِيمِ وَالْمَرْأَة


ነቢያችን"ﷺ" አባታቸው በሞት ያጡት እናታቸው ሆድ ውስጥ እያሉ ነበር፥ እናታቸውን ያጡት ደግሞ በተወለዱ በስድስት ዓመታቸው ነበር።
አምላካችን አላህ ስለ እርሳቸው የቲምነት ሲናገር፦
93፥6 *የቲም ኾነህ አላገኘህምና አላስጠጋህምን?* ፡፡ أَلَمْ يَجِدْكَ يَتِيمًۭا فَـَٔاوَىٰ


🕸የቲምን መንከባከብ

የቲምን መንከባከብ በጎ አድራጎት እና ከአላህ ዘንድ አጅር አለው፥ በጀነት የነቢያችን"ﷺ" ጎረቤት ለመሆን ጉልህ ሚና አለው፦
4፥36 አላህንም አምልኩ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ በወላጆችና በቅርብ ዝምድና ባለቤትም፣ *"በየቲሞችም፣ በምስኪኖችም፣ በቅርብ ጎረቤትም፣ በሩቅ ጎረቤትም፣ በጎን ባልደረባም፣ በመንገደኛም፣ እጆቻችሁም ባደረጓቸው ባሮች፣ መልካምን ሥሩ"*፤ አላህ ኩራተኛ ጉረኛ የኾነን ሰው አይወድም፡፡

وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا ۖ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا وَبِذِي الْقُرْبَىٰ وَالْيَتَامَىٰ وَالْمَسَاكِينِ وَالْجَارِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَالْجَارِ الْجُنُبِ وَالصَّاحِبِ بِالْجَنبِ وَابْنِ السَّبِيلِ وَمَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ مَن كَانَ مُخْتَالًا فَخُورًا

76፥8 *"ምግብንም ከመውደዳቸው ጋር ለድኻ፣ ለየቲምም፣ ለምርኮኛም ለእስረኛም ያበላሉ"*፡፡ وَيُطْعِمُونَ الطَّعَامَ عَلَىٰ حُبِّهِ مِسْكِينًا وَيَتِيمًا وَأَسِيرًا


عن سهلِ بن سعدٍ رضي اللَّه عنه قال: قال رسول اللَّه ﷺ:
(أَنَا وكافلُ الْيتِيمِ في الجنَّةِ هَكَذَا) وأَشَار بِالسَّبَّابَةِ وَالْوُسْطَى، وفَرَّجَ بَيْنَهُمَا.
📚رواه البخاري.

ከሰህል ቢን ሰዕድ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተላለፈው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–
[እኔ እና የቲም ተንከባካቢ በጀነት ውስጥ እንደዚህ ነን።] በመጠቆሚያ ጣታቸውና በመሀል ጣታቸው ትንሽ ከፈት አድርገው ጠቆሙ።
📚ቡኻሪ ዘግበውታል ።

#ልቡ_የደረቀበት_ሰው_የቲሞችን_ያስጠጋ
አንድ ሰው ወደ አቢ ደርዳእ (ረዲየላሁ ዐንሁ) መጣና (ወሲያ) ምክር ብጤ ኑዛዜ ንገረኝ? አለው: አቢ ደርዳም እንዲህ አለው:– ለየቲም እዘን፣ ወዳንተም አስጠጋው፣ ከምግብህም አብላው፣ እኔ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዘንድ አንድ ሰው መጥቶ ልቡ ስለመድረቁ ስሞታ ሲነግራቸው ሰምቼ የሚከተለውን ብለውታል:– (ልብህ እንዲረጥብ ከፈለግከ የቲምን ወዳንተ አስጠጋ፣ ፀጉሩን አባብሰው፣ ከምግብህም አብላው፣ ይህ ልብህን ያረጥበዋል፣ ጉዳይህንም ማሳካት ትችላለህ።) [ኢማሙ አህመድ 2/263፣ በይሀቂ በሹዐብ 11034 የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒ በሶሂሁል ጃሚዕ 1410 ሶሂህ ነው ብለውታል።]


============
አንዳንድ ለየቲሞች ኀላፊ የሆኑ ሰዎች (አላህ ይጠብቀንና) የየቲሞችን ገንዘብ ለራሳቸው ይበደሩታል፣ለራሳቸው ይጠቃቀሙበታል፣ ስራ የሚሰሩበት፣ የሚገባዩበት ለራሳቸው ነው፣ የየቲሞች ገንዘብ ግን ለነሱ የሚጨምር ነገር የለም። ይህ የከፋ ወንጀል ነውና እጅግ በጣም ልንጠነቀቅ ይገባል።
Audio
🔹ከካፊሮች ጋር መመሳሰል
🔹የፍቅረኛሞች ቀን ማክበር
🔹ኢስላማዊ አመት በአሎች

♦️በድጋሚ የተለቀቀ

🎙 አቡ አብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1672
t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/1672
ዱንያ_አኼራ

🌺ሀሰን_አልበስሪ እንዲህ አሉ { የዱንያ እና የአኼራ ምሳሌ ልክ አንደ ምስራቅ እና ምዕራብ ነው። ወደ አንዳቸው መቅረብን ስትጨምር ከሌላኛው ደግሞ መራቅን ትጨምራለህ!!}

መልካም ምሽት😘
«ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104)