La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
👉⚠️እንጠንቀቅ!!

ዝሙትም ለማስፋፋት እንዲህ የፍቅር ቀን መቁጠሪያ ተዘጋጅቶለታል

የቫላንታይን ካላንደር
🚫🚫🚫🚫🚫🚫
👉February 7-------------የአበባ ቀን
👉February 8------የመተጫጫ ቀን
👉February 9------የቸኮላታ ቀን
👉February 11 -----ቃል የመገባባት ቀን
👉February 12----የመተቃቀፍ ቀን
👉February 13-----የመሳሳም ቀን
👉February 14-----የፍቅር ቀን

👌በዚህ ተግባር የምንሳተፍ ሰለጠን የምትሉ ሙስሊሞች ራሳችሁን ጠብቁ!!

አሏህ ይጠብቀን
👌ግብዣ…!
🌸መሳጭ ቲላዋ!
#أذكار_الصباح
((يَا حَيُّ يَا قَيُّومُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغيثُ أَصْلِحْ لِي شَأْنِيَ كُلَّهُ وَلاَ تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ)).
🍃🌻
( لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَريكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، سُبْحَانَ اللَّهِ، وَالْحَمْدُ للَّهِ، وَلاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، وَاللَّهُ أَكبَرُ، وَلاَ حَوْلَ وَلاَ قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ الْعَلِيِّ الْعَظِيمِ، رَبِّ اغْفرْ لِي ).
🍃🌻
(أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيكَ لَهُ وَأَشْهَدُ أَنَّ مُحَمَّداً عَبْدُهُ وَرَسُولُهُ..).
🍃🌻
◾️እውቀትን የሚያክል ምንም ነገር የለም‼️


ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ።

➧አላህ ሸሪአዊ እውቀት ከሰጠህ፦ አብሽር! ምክንያቱም ይህ ማለት አላህ መልካም ሽቶልሀል ማለት ነው።

ኢማሙ አህመድ እንዲህ ብሏል «ንያውን ለተስተካከለለት ሰው እውቀትን የሚያክል ነገር የለም» አሉ።

➧ የአብደላህ አባት ሆይ፦ እንዴት ነው ታዳ ንያውን የሚስተካከለው? ተብለው ሲጠየቁ፦ «ጅህልና (መሀይምነትን) ከራሱና ከሌሎች ለማንሳት ብሎ ማሰቡ ነው» ብለው መለሱ።

📚(شرح حلية طالب العلم / ص16)

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈
#ከሀዲስ

1) «ከቀብር ቅጣት ነጃ የወጣ ከዛ ቡሀላ ያለው ገር ይሆንለታል፣ ከቀብር ቅጣት ነጃ ያልወጣ ከዛ ቡሀላ ያለው የበለጥ ይጠናበታል»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📔ሶሒሁል ጃሚዕ (1684)

2) ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አሉ፦
«ረሱልን በላጭ የሆነው መልካም ስራ የትኛው ነው ብየ ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ "ሶላትን በወቅቱ መስገድ" ከዛስ አልኳቸው ለወላጆች መልካም መዋል አሉኝ»።
📔ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

3) «ረሱል የሞቱ ቀን አቡበክር ሲዲቅ ወደርሳቸው መጣና ፊታቸውን ገልጦ ግምባራቸውን ሳማቸው ከዛም እንዲህ አለ"አባቴና እናቴ መስዋት ይሁኑሎትና በህይወትም ሳሉ ሙተውም ምንኛ ውብ ናችሁ»።
ምንጭ:-📔ሶሒሁል ቡኻሪ (3667)
ከኢብኑ #ዑሰይሚን ፈገግ የሚያሰኝ የፈትዋ ጥያቄ

ዶሮ እሽቅድምድም?

ጠያቂ፡- በሐዲሥ፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ታዲያ አንድ ሰው በዶሮ ውድድር ወይም በእርግብ እሽቅድምድም ቢሆን ምን አስተያየት አለህ?

መልስ እነሆ፣ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ወይም ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በጦርነት ውስጥ ስለሚውሉ ነው። ዶሮዎ በላዩ ላይ እንዲጋልቡበት በጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ይፈቀዳል! አለበለዚያ አይሆንም….
አሉት።
ከኢብኑ #ዑሰይሚን ፈገግ የሚያሰኝ የፈትዋ ጥያቄ

ዶሮ እሽቅድምድም?

ጠያቂ፡- በሐዲሥ፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ታዲያ አንድ ሰው በዶሮ ውድድር ወይም በእርግብ እሽቅድምድም ቢሆን ምን አስተያየት አለህ?

መልስ እነሆ፣ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ወይም ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በጦርነት ውስጥ ስለሚውሉ ነው። ዶሮዎ በላዩ ላይ እንዲጋልቡበት በጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ይፈቀዳል! አለበለዚያ አይሆንም….
አሉት።
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:

لا تكثروا الكلام بغير ذكر الله؛ فإن كثرة الكلام بغير ذكر الله تعالى قسوة للقلب! وإن أبعد الناس من الله تعالى القلب القاسي.
ነብዩ ሰ.ዐ.ወ.እንድህ ይላሉ፦ ንግግርን አታብዙ።
አሏህን ለማውሳትና ለማወደስ ካልሆነ በስተቀር።ለምን ከተባለ፦ ዝክር ያልሆነ ንግግርን ማብዛት ቀልብን ያደርቃታልና።ከአሏህ ረህመት በጣም የራቀ ሰው ማለት ደግሞ ቀልቡ የደረቀበት ሰው ነው። አሏህ ይጠብቀንና‼️

ስለዝህ በተቻለ መጠን መልካም ንግግርን ለመናገር እንሞክር ።አልያም ዝም እንበል።
👉ከተቻለ ሰዎችን ወደ ኢስላም ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ሱና ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ሷላት ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ እውቀት መድረክ ጋብዛቸው

👉ከተቻለ ከሀሜት እንድ ርቁ ምከራቸው

👉ከተቻለ ከውሸት ራቁ በላቸው

👉ከተቻለ ወደ ተውሂድ ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ዝክር ጥራቸው

👉ከተቻለ እርቅን እንድያሰፍኑ ምከራቸው
👉ከተቻለ ሷደቃ እንድሰጡ አነሳሳቸው

👉ከተቻለ የቲሞችን እንድረዱ አድርጋቸው

👉ከተቻለ ቁርኣንን እንቅራ እናስቀራ

⚠️ከዝህ ውጪ የሆነ ንግግር በሽታ እንጂ የቀልብ ፈውስ አይሰጥህም በደንብ ራቀው‼️

መልካም አዳር‼️

አቡ ሙስሊም ቢን ጋቼኖ
Audio
#የመጨረሻ_ክፍል
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
#የነብዩ_ዩሱፋፍ_(ዐ.ሰ)የህይወት ታሪኩ የመጨረሻ ክፍል ደርሱዋል እስከ ዛሬ ከመጀመሪያው ጀምሮ ስለተከታተላቹን በጣም እናመሰግናለን። ለሌሎችም #ሼር አርጉት እሀንን ጣፋጭ የነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) የህይወት ታሪኩን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከላያቹት በዚ ቻናል ማያት ትችላላችሁ ዉድ ye_ le tahzenቤተሰቦቼ 👉

ሁላቹንም ለአላህ ብዬ እወደቹዋለው።

#ሼር_ሼር_ሼር


https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
ማንኛችሁም ሞትን እንዳይመኝ
ቢስሚላህ
አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ
አሰላሙዐለይኩም
ውዶች ፣
ሰዎች በእይታቸው ከበድ ያለ ችግር ሲገጥማቸው ምነው በሞትኩት፣ይህንን ሳላይ ብሞት ይሻለኝ ነበር።ሲሉ ይደመጣል።ሌላው ሀገራዊ ብሂል "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል
ድሀ ሞኝ ነው ሞትን ይመኛል"
በማለት ዛሬ ከበድ ያለ ችግር ቢገጥምህ ነገ ደግሞ መውጫ ስለሚኖር ተሰፋን አትቁረጥ የተሻለ ነገ ይኖራልና።
ይህን መርሕ ከ 1400 ዓመት በፈት ውዱ ነቢይ
ለ ጓዶቻቸው ሰሐባዎች በተለያዩ ዘገባዎች በገጠማቸው ችግር ሞትን እንዳይመኙ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቁ እንደነበር እንረዳለን።ከእነዚህ ዘገባዎች የሚከተለው የቡኻሪ ዘገባ ይጠቀሳል።
حَدَّثَنَا ابْنُ سَلاَمٍ، أَخْبَرَنَا إِسْمَاعِيلُ ابْنُ عُلَيَّةَ، عَنْ عَبْدِ الْعَزِيزِ بْنِ صُهَيْبٍ، عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ يَتَمَنَّيَنَّ أَحَدٌ مِنْكُمُ الْمَوْتَ لِضُرٍّ نَزَلَ بِهِ، فَإِنْ كَانَ لاَ بُدَّ مُتَمَنِّيًا لِلْمَوْتِ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ أَحْيِنِي مَا كَانَتِ الْحَيَاةُ خَيْرًا لِي، وَتَوَفَّنِي إِذَا كَانَتِ الْوَفَاةُ خَيْرًا لِي ‏"‌‏.‏ اللبخاري 6351

ከአነስ ቢን ማሊክ በተላለፈው ሀዲስ እንደሚከተለው ማለታቸውን ቡኻሪ ዘግበዋል
"አንዳችሁ በገጠመው ችግር የተነሳ ሞትን አይመኝ።የግድ ሞትን የሚያስመኘው ደረጃ የሚያደርሰው ከሆነ አላህ ሆይ መኖሬ ለኔ የሻለ ከሆነ በህይወት አኑረኝ።መሞቴ ለኔ የተሻለ ከሆነ
ሞትን ግጠመኝ ይበል" በማለት ምርጫውን ለአላህ ይስጥ ዘንድ አስተምረዋል።
ቡኻሪ አረብኛ እንግሊዝኛ መድበል ሀዲስ ቁጥር 6351

ከአቢሁረይራ በተወራ ሀዲስ ደግሞ " .....አንዳችሁ ሞትን እንዳይመኝ መልካም ሰሪ ከሆነ የመልካም ተግባር ኪታቡ እንዲጨምርላት መሆኑ በላጩ ነው።በተቃራኒው አመፀኛ / አጥፊ ከሆነ ደግሞ ተውበት ለማድረግ እድል ያገኛልና" ቡኻሪ ሀዲስ ቁ 5671
በሌላ ዘገባ እድለኛ ሰው ማለት እድሜው የረዘመ ነው ።ማለታቸው ተዘግቧል።
ሁላችንም አላህ ረጅም እድሜና መልካም ስራን እንዲያበዛልን እንለምነው።
እርሱ የባሮቹን ልመና ሰሚ ነው
ወሰለላሁመ ወሰሊም ዐላ ነቢዪና ሙሐመድ
ወሰላም
(سُبْحانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتوبُ إِلَيْكَ).
🍃🌻
(بِسْمِ اللَّهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ، وَلَاَ حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ).
🍃🌻
🛏 እነሆ በፍቃዱ አምሽተን አነጋን
ሌላ ቀን እንድናይ አዲስ እድል ሰጠን።

ከሞት በኋላ ሕይወትን ለለገሰን እኛም ወደ እሱ የምንሰበሰብ የሆነው ጌታ ምስጋና የተገባው ነው።


#አልሀምዱሊላህ

💦በእያንዳንዱ እርምጃ አላህን በሃሳብህ ማቆየትህን አስታውስ።

💦 አላህ በእዝነቱ ጉዳቱን እና ተግዳሮቶቹን ሁሉ ይጠብቅልን።

💦በአካባቢያችሁ መልካም እና ደግነት የተሞላበት አስደሳች እና ሰላማዊ ቀን እንዲኖርዎት ቁርኣን በማንበብ በዚክር ጀምሩ እንዲሁም በውሎዋችሁ ሰላምና መፅናናትን ታገኛላችሁና።

💦ከባድ ቀን ቢያጋጥመህም አላህ የሚፈትንህ ብቻ መሆኑን ተረዳ።

💦አዲስ ቀን የአላህን መንገድ ለመከተል አዲስ እድል ነው ስለዚህ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም።

💦ውሎ አችሁ የተባረከ አስደሳች እና ማራኪ ተጠቃሚ ምትሆኑበት እንዲሆን እመኛለሁ
" لا تشغلن بعيب غيرك غافلا
عن عيب نفسك إنه عيبان "

የራስህን ነውር ዘንግተህ በሌሎች ነውር አትወጠር
ይህ ማድረግህ ሁለት ነውር ነው።

1ኛ, የራስህን ነውር መዘንጋትህ
2ኛ, የሌሎችን ነውር መከታተልህ
❀ ወላሂ እጅግ በጣም ቀናሁ. . . .
☞ሰብር አድርጋችሁ አንብቡት ትጠቀማላችሁ ኢንሻ አላሁ ተዓላ !
✿መጪው ዘመን የሚል አንድ ደብዳቤ ላይ አንድ የአረብ ሀገሮች
የመኪና ፍጥነት የሚቆጣጠር ትራፊክ ይህንን ታሪክ ዘግቦታል. . .
>ለናንተ ላካፍላችሁ! ትራፊኩ እንዲህ ሲል ታሪኩን ጀመረ:- "
አንዴ የተለመደውን ስራዬን ቆሜ እየሠራሁ እንዳለ አንድ መኪና
እንዲሁ ረጋ ብሎ ሲሄድ ነበር ይህ ሰው መኪናው ተበላሸበትና
ከመኪናው ወቶ ወርዶ ለማስተካከል ልክ እንደወረደ ከሁዋላ
መጣችና አንዲት መኪና ወጣችበት ወደቀ ተገጨ
ይህ ሰው ከባድ የሆነ አወዳደቅን ወደቀ እኛም ሩጠን አነሳነውና
መኪና ላይ ሰቀልነው ይሄን ሰው ይህ ሰው ስናየው ገና ለጋ
~ወጣት ነበር ይህ ልጅ የአላህ ባሪያ መሆኑ ፊቱ ላይ ያስታውቃል
``ፂሙ ፊቱ ያበራል የኢማን ኑር ይታይበት ነበር ልክ አንቡላንስ
>መኪና ላይ ስንጭነው ይህን ወጣት አብረነው ስንሳፈር የኾነ
ቃል ይናገር ነበር የሚለውን ግን መረዳት አልቻልንም ነበር ነገር
ግን መኪና ውስጥ አድርገነው ከጎን እኔና ጉዋደኛዬ ትራፊክ
አብረን ከጎን ሁነን መሄድ ስንጀምር ለየት ያለ የሚያምር ድምፅ
መስማት ጀመርን አላሁ አክበር!!!
❀ይህ ወጣት ቁርዓን እየቀራ ነበር ይህ ወጣት በሚያምር ድምፅ
ቁርዓን እየቀራ ነበር ሱብሀንአላህ! በጣም ይገርማል እንደው
የተመታ እንደዚያ አይመስልህም ደም ልብሱን እንዳለ አካላቱን
አልብሶታል አጥንቱ ደቆ ተሰባብሮዋል ልክ ወጣቱን ስታየው ሞት
አፋፍ ላይ ያለ ነው የሚመስልህ ነገር ግን ይህ ወጣት
በሚያምር ድምፅ ቁርዓንን ይቀራ ነበር ሞት አፋፍ ላይ ያለ
ወጣት! አላሁ አክበር!
ተገርመን በጣም ማየት ጀመርን ትንሽ እንደቆየ ፀጥ አለ!ወደ
ሁዋላ ዞር ብዬ ስመለከተው እጁን ወደ ላይ አድርጎ ሸሀዳ እያለ
ነበር :- " አሽሀዱ አላ ኢላሀ ኢለላህ ወአሽሀዱ አነ ሙሀመደን
ረሱሉላህ" ያ አላህ! ሱሀነክ! ;-( ;-( ;-( ከዛም ፀጥ አለብን
ይህ ወጣት እጁን ሂጄ ነካሁት ደረቱን ዳሰስኩት ምንም
የሚንቀሳቀስ ነገር የለም ይህ ወጣት ዱንያን ለቆ ወጥቶ ነበር
ሱብሀነላህ!
ብዙ አተኩሬ ይህን ወጣት ተመለከትኩት ከአይኔ እንባ መርገፍ
ጀመረ ጉዋደኛዬ እንደው መቆም አልቻለም ለቀቀው ማልቀስ
ጀመረ እንዲህ ብሎ ቁርዓን እየቀራ ሲሞት ሆስፒታልም
እንደደረስን ስለዚህ ወጣት ሁኔታ ያገኘነውን ሰው ሁሉ ስለ
ወጣቱ ነገርናቸው አብዛኛዎቹ በጣም ልባቸው ተነካ እንባቸው
መውረድ ጀመረ አንደኛው ታሪኩን እንደሰማ በጣም ተገረመና
ይሄን የአላህ ባሪያ ሄጄ ግንባሩን ነው የምስመው ብሎ ሳመው
አብዛኛዎቹ በቃ ከዚህ ከአላህ ባሪያ ላይ ሶላተል ጀናዛ
ሳንሰግድበት አንሄድም አሉ::
`
ከዛም ከሆስፒታሉ ሰራተኞች ውስጥ አንዱ ወደ ቤተሰቡ ደወለና
ወንድሙ መጣ:- ወንድሙ ነው ይሄን የሚቀጥለውን ታሪክ
የሚናገረው:- "ወንድሜ ሁሌ ሰኞ ሰኞ አንዲት ገጠር አካባቢ
አያቱ አለች እሷን ሊዘይራት ይመላለስ ነበር:: እዛች አገር
ውስጥ ያሉ ሚስኪኖችን የቲሞችን ባል የሞተባቸውን ሴቶችን
እየሄደ ይረዳቸው ነበር:: ያቺ ከተማ ወንድሜን ታውቀው ነበር::
ለዛች አገር ሰዎች ሁሌ ሰኞ ሰኞ ካሴቶች መፅሐፎችን እየወሰደ
እሱ ነበር የሚሰጣቸው::
ሁሌም ወደዛች ሀገር ሲሄድ መኪናው ውስጥ ሩዝ ስኩዋር
ምናምን ሞልቶ ነበር የሚሄደው ለችግረኞች እዛ ሊበትንላቸው
ማለት ነው:: ከረሜላ እንኩዋን ለዛች ሀገር ሕፃናቶች አይረሳም
ነበር:: ሁሌም ታዲያ ሰዎቹ አንተ የዚህን ያህል ጉዞ
ትመላለሳለህ እንዴ! ብለው ለሚተቹትና ሀሳብ ለሚሰጡት
ሰዎች እንዲህ ብሎ ይመልስላቸው ነበር:- " እኔኮ ወደዝች
ሀገር በመመላለሴ በረጅሙ ጉዞዬ ውስጥ ቁርዓንን ለመሐፈዝና
ቁርዓንን ሙራጃ ለማድረግ ለማስታወስ እጠቀምበታለሁ
የሚጠቅም ሸሪጦችን ሙሀደራ እሰማበታለሁ እንደኛ ሙዚቃ
ከፍቶ አይደለም የሚሄደው ይሄ ሁሉ ጎማዬ የሚሽከረከረው
መሽከርከር ከአላህ ዘንድ አጅር አኝበታለሁ ብዬ አምለናለሁ
ይለን ነበር::
እያለ ወንድምየው ነገረን:: ሱብሀን አላህ!!! ትራፊኩ ምን
ይላል:- ሀያቴ ልክ በማዕበል እንደምትናጥ መርከብ እዛ እዚ
እየዋተትኩ ነበር መዋለል ከሁሉ አቅጣጫ ወሮኝ ነበር አላህ
(ሱ.ወ) ን ከራቁት ውስጥ ነበርኩ ወጣቱን ቀብር ላይ ከተነው
በሰገድንበት ጊዜ እሱ የአኼራን የመጀመሪያን ቀን ሲገናኝ እኔ
የዱንያን የመጀመሪያዬን ቀን ተገናኘሁ ወደ አላሁ (ሱ.ወ)
ተመለስኩ አላሁ (ሱ.ወ) ያሳለፍኩትን ይምረኝ ዘንድ ይህንን
ወጣት አሟሟቱ እንዳሳመረው ሁሉ በኸይር ይወስደኝ ዘንድ
አላሁ(ሱ.ወ) እየተማፀንኩ ቶብቼ ተጸጽቼ የዱንያን
የመጀመሪያዬን ቀን ጀመርኩ ይላል::
" መጪው ዘመን በሚል ርዕስ ላይ ይህ ትራፊክ ነው ታሪኩን
የዘገበው እናቶቼ አባቶቼ እህቶቼ ወንድሞቼ ወላሂ የመጨረሻን
ሸሀዳ ማግኘት ከባድ ነው አሁን ምላሳችን ዚክር ያለመደ ከኾነ
ከቁርዓን ጋር ያልኖርን ከሆነ ያኔ ጣዕረሞት ላይ አይመጣልንም
ወላሂ !!! የቁሉላሁ (ተባረከ ወተዓላ) ፊ ሙህከሚ ተንዚሊህ:
- "አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ
ልፋትን ለፊ ነህ! ተገናኚውም ነህ!" ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ 6
ያ አላህ!!! ያ አረሕማን!!! ያ ዘልጅላሊ ወል ኢክራም!!! ያ
አርሀሙ ራሒሚን!!! አሟሟታችንን አሳምርልን!!! ኑሮአችንን
በኢባዳ ሞታችንን በሸሀዳ አድርግልን!!! አሚን!!! አላሁመ
አሚን!!!
ሼር ያድርጉ ለሌላውም ያስተላልፉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/httpsLatahzenhttps://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from La tehzen
#ቁርዓኔ
ከአላህ የተላክ ውዱ ደብዳቤዬ፣
መሰረቴ ነህ ሁሌም የልዕልናዬ፣
ፈጥሮካል ኢላሂ እጅጉን ገር አርጎ፣
ሊቀርብክ ላሰበ አኼራን ፈልጎ፣
አትከብድም ሲያነቡህ በጣም ቀላል ነህ፣
እኛው ነን ያከበድንህ ቦታ ሳንሰጥህ፤

#ቁርዓኔ
ታውቃለህ እንደሆንክ የስኬቴ መሰላል፣
ሁሌም ከጎኔ ሁን የፈጣሪዬ ቃል፣
አንተን ስቀርብ ነው ውስጤ ሚረጋጋው፣
ጭንቀቶቼን ትቼ ሰላም የማገኘው፣
በዱንያም በአኼራ ድል የምቀዳጀው፣
ስርቅህ አይደለም እጅግ ስቀርብህ ነው።

#ቁርዓኔ
አንተ ነህ የህይወቴ መመሪያ፣
ሀቅና ባጢሉን አጣርቶ መለያ፤
ምድር ከያዘችው መፅሀፎች መካከል፣
በፍፁም አይገኝም አንተን የሚያክል፤
ካንተ ተፈልጎ የለም የሚታጣ፤
ሁሉን አካተሀል ያለንም ሚመጣ።

#ቁርዓኔ
ህመሜን ምትፈውስ ፍቱን መድሀኒቴ፣
ቁርዓኔ ብቻ ነህ የእድገት መሰረቴ፤
ሰላሙን ተነፍጎ ደስታ የራቀው፣
አንተን ያቅርብና ያድርግ ጓደኛው፤
ምድር ላይ ብቅ ካልህ ሺህ አመታት ቢያልፍም፣
ሁልጊዜ አዲስ ነህ መቼም አትሰለችም።