#ስኬት_በኢስላም
ብዙ ስላወክ ስኬታማ ልትሆን አትችልም፤ የተለየ ነገር ስለሞከርክ ስኬታማ አትሆንም፤ ረጅም ሰዓት በስራ ስላሳለፍክ ስኬታማ ነህ ማለት አይደለም። ስኬት አንድ ነገር ይፈለጋል #ጽናት።
አላህ ዘንድም በላጩ ስራ ትንሽም ብትሆን የተዘወተረበት ስራ ነው።

❤️ውዱ ወንድሜ ሆይ❤️
❥መልካም ሚስት በፍለጋ አትገኝም ስልህ ከዓላህ የምትሠጥ ውድ ሥጦታ ብትሆን እንጂ ማለቴ ነዉ።
ስለዚህ እሷንም በሱጅድህ ውሥጥ ፈልጋት።☜
❤️ወንድሜ ሆይ ያየሃትን ሴት ሁሉ ☞☞ሚስት ለማደድረግ አትሞክር ።
☞የምታያት ሴት ሁሉ ያንተ ሚስት አይደለችም!።
☞የኔ የምትላትን ከእግርህ ሥር ባታገኛትም
በሱጅድ ውሥጥ ፈልጋት ታገኛታለህ። ስልህ መልካም ትዳር የዱአ ውጤት ነው√ ።
☞ላየሃት ሴት ሁሉ ቴክሥት አትፃፍ ማለቴ አስር ያባረረ አንድ አይዝም √☜
❤️ሚሥት አጣሁ አትበል እኔ ባል ነኝ ወይ ብለህ እራሥህ ፈትሽ☜
☞ዓንተ የምትፈላጋትንና የምትወዳትን ሚሥት ለማግኘት በመጀመሪያ አንተ (ዓሏህ) እንደሚፈልገው እንደሚወደው ሆነህ ተገኝ !!
ምክንያቱም አላህ ትዕዛዙን ያሟላ ባሪያውን አያሳፍርም ሊፈትነው ካልሆነ በስተቀር።

ከልብስህ ይልቅ ልብህ እንዳይቆሽሽ ጥንቃቄ አድር
.
ልብስህን ከአቧራ እና ቆሻሻ እንደምትጠብቅ ሁሉ ልብህንም ከተንኮል፣ ከክፋት፣ ከትዕቢት፣ ከሃሜት፣ ከቅናት እና ከምቀኝነት ጠብቃት
.
ልክ እንደ ልብስ ልብም ሲቆሽሽ ጠረን ያመጣል

በኢትዮጵያ " የዶሮ በሽታ " መከሰቱን ተከትሎ መንግስት ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቢያ ተላልፏል ለምን በ @AddisCentralNews ይመልከቱ ‼️
10 የዙል ሂጃ ቀኖች
ዙል-ሒጃህ በእስልምና ወር አቆጣጠር አስራ ሁለተኛው (የመጨረሻው) ወር ነው፡፡ በዚህ ወር ውስጥ ካሉት 29/30 ቀናት ውስጥ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት እጅግ የተከበሩ ቀናቶች ናቸው፡፡ መከበራቸውን ከሚያመላክቱት ውስጥ፡-
ሀ. አላህ የማለባቸው መሆኑ፡-
"በጎህ እምላለሁ። በዐሥር ሌሊቶችም።" ሱረቱል ፈጅር 1-2
ታላቅ የሆነው ጌታችን አላህ የሚምለውም ታላቅ በሆነ ነገር ስለሆነ የቀኑን ክብደት ይገልጽልናል፡፡ እነዚህ አስር ሌሊቶች የተባሉት የዙል-ሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት እንደሆኑ አብዝሓኞቹ የቅዱስ ቁርኣን ተንታኞች ይገልጻሉ፡፡
ለ. እኔን አስታውሱባቸው ማለቱ፡-
" ለነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ፣ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከማለዳ እንሰሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ፣ (ይመጡሃል)፤ ከርሷም ብሉ፤ ችግረኛ ድኻንም አብሉ።" ሱረቱል-ሐጅ 28
"የታወቁ ቀኖች" የተባሉት እነዚሁ አስርቱ ቀናት እንደሆኑ ሙፈሲሮች ያስረዳሉ፡፡ ታዲያ አላህን በማንኛውም ጊዜ ማውሳትና ማወደስ ከመቻሉ ጋር፡ በነዚህ ቀኖች አወድሱት ብሎ ቀኖቹን ለይቶ መጥቀሱ የተለየ ደረጃና ክብር እንዳላቸው ይጠቁማል፡፡
ሐ. ከዱንያ ቀናት ሁሉ በላጭ መሆናቸው፡-
ከጃቢር ኢብኒ ዐብዲላህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በተላለፈው ሐዲሥ ረሱላችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡-" ከዱንያ ቀናቶች ሁሉ በላጩ (የዙል-ሒጃ) አስሩ ቀናት ናቸው " (ሶሒሕ አል-ጃሚዑ ሰጊር 1133)፡፡
በዚህ መሰረት እነዚህ አስርት ቀናቶች ልዩ ክብር የሚሰጣቸው ናቸው፡፡
ምን እንሥራባቸው?
ዐብደላ ኢብኑ አባስ እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም ስራ ከዙል-ሒጃ አስርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" ሶሓባዎችም፡- በአላህ መንገድ ጂሐድም (ጠላትን መታገልም) ቢሆን? ሲሉ፡ እሳቸውም፡- አዎ ጂሐድም ቢሆን ሰውየው ከነፍሱና ከንብረቱ ጋር በዛው ሳይመለስ የቀረ ካልሆነ በስተቀር አይበልጥም" አሉ፡፡ (ቡኻሪይ)፡፡
ታዲያ ያለምንም የመግቢያ ክፍያ እንዲህ ዐይነት ታላቅ ኤግዚቢሽን ከተዘጋጀልን እኛስ ለመሳተፍ ምን ያህል ወስነናል፡፡ ጠላታችን ሰይጣን እንዳንጠቀምበት ደፋ ቀና ማለቱ አይቀርምና እኛም አላህን ይዘን እሱን ድል በመምታት ቀኑን እንጠቀምበት፡፡ ከሚሰሩ መልካም ሥራዎች ውስጥ፡-
1. ሐጅና ዑምራህ፡-
" ዑምራህ መፈጸም ቀጣዩ አመት ዑምራ እስኪመጣ ድረስ (በመሐል ለተፈጸሙ ጥቃቅን ኃጢአት) ማስተሰረያ ነው፣ ትክክለኛ ሐጅ ደግሞ ከጀነት ውጪ ክፍያ የለውም" ቡኻሪና ሙስሊም፡፡
2. ጾም፡-
የፈለገ ሙሉውን ዘጠኝ ቀን ካልሆነም የቻለውን ያክል መጾም ይችላል፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- "መልካም ስራ ከዙል-ሒጃ አስርቱ ቀናት በልጦ አላህ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የሆነበት ቀናት የለም፡፡" በዚህ ሐዲሥ መሰረት ጾም "መልካም ስራ" የተባለው ሐዲሥ ውስጥ ስለሚካተት በጾሙ የቻለውን ያክል መበርታት ይችላል፡፡
3. አላህን ማውሳት፡-

ይህ ቅዱስ አንቀጽ አላህን በነዚህ ቀናት ማውሳት መዘከር እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ባስተላለፉት ሐዲሥ ላይ ነቢዩ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "በነዚህ ቀናት ውስጥ ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢልለላህ)፤ተክቢር (አላሁ አክበር)፤ተሕሚድ (አል-ሐምዱ ሊላህ) ማለትን አብዙ" (አህመድ 7/224)
ዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር እና አቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) ወደ ገበያ በመውጣት በተክቢራ ሲያሞቁት ሰዎቹም የነሱን ተከትለው ተክቢራ ይሉ ነበር (ኢርዋዑል-ገሊል አልባኒይ 651)
4. ተውበት ማብዛት-
"…ምእምናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ።" ሱረቱል አሕዛብ 31
5. መልካም ስራዎችን ማብዛት፡-
በኢስላም የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸው፡፡ ተቆጥረው አይዘለቁም፡፡ ከኛ የሚጠበቀው ስራው ላይ ተሳታፊ መሆን ነው፡፡ ከቤተሰብ ጀምረን እሰከ ሩቅ ሰው ድረስ አቅማችን የቻለውን ያህል በመርዳት ወደ አላህ እንቃረብ፡፡
6. በዒባዳ መጠናከር፡-
ከፈርድ ሶላት ቀጥሎ ያሉትን ሱንና ሶላቶችን ማብዛት፤ቁርኣንን ማንበብና ማዳመጥ፡፡
7. ከሐራም መቆጠብ፡-
ከላይ የተጠቀሱት መልካም ስራዎች ላይ በመሳተፍ የአላህን ተውፊቅ ያላገኘ ሰው ቢያንስ ከሱ እጅና ምላስ ሌሎች ሰላም እንዲሆኑ እራሱን ማቀብ፡፡እሱም ትልቅ ተውፊቅ ነውና፡፡
#ማረድን-የፈለገ፡-
የዒዱል አድሓን እርድ ለመፈጸም የነየተ የአላህ ባሪያ (ወንድም ሆነ ሴት) ወሩ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ፡- የሰውነት ጸጉሩን መላጨትም ሆነ መቀነስ፣ የእጁንም ሆነ የእግሩን ጥፍር ማስተካከል፣ ከገላው ላይ የተወሰነ ቆዳንም ቢሆን ቆርጦ ማንሳት አይፈቀድለትም፡፡ ይህ ብይን የሚመለከተው የዒዱን እርድ በራሱ ወጪ ለማረድ የነየተውን ግለሰብ ብቻ ነው፡፡ ቤተሰቦቹን ብይኑ አይመለከታቸውም፡፡
ሰውየው በቀጥታ እራሱም አራጅ ሆነ፡ ወይም በወኪል ቢያሳርድ ኃላፊው እሱ እስከሆነ ድረስ ብይኑ ይመለከተዋል፡፡ ወኪል ሆኖ የሚያርደውን ሰው ግን ብይኑ አይመለከተውም፡፡
ኡሙ ሰለማህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- "የዙል-ሒጃህን ጨረቃ ካያችሁና አንዳችሁም ኡድሑያን (እርድን) ከነየተ፡ ጸጉሩንና ጥፍሩን (ከመቀነስ) ይቆጠብ" (ሙስሊም 1977)፡፡
በሌላ ዘገባ ላይ ደግሞ ‹‹ከጸጉሩና ከሰውነቱ (ቆዳው) ይቆጠብ›› ይላል፡፡ ስለዚህ ዕለተ ሐሙስ የዚል-ቂዕዳህ 29ኛው ቀን ስለሆነ፡ ወሩ በዚያው ሊጠናቀቅም ስለሚችል፡ የመግሪብ አዛን ከተሰማ በኋላ ያለው ምሽት የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ሆኖ ይጀምራል ማለት ነው፡፡ ወሩ ሠላሳ ከሞላ ደግሞ፡ ከጁምዓህ መግሪብ በኋላ ወሩ የዙል-ሒጃህ 1ኛ ቀን ይሆናል ማለት ነው፡፡ እናም ለዒዱ እርድን የነየታችሁ ወንድምና እህቶች ሆይ! ከዕለተ ሐሙስ መግሪብ አዛን በፊት (የጸጉር፣ የጥፍርና የቆዳ) ጣጣችሁን ጨርሱ፡፡
ሌላው ሊታወቅ የሚገባው ነገር፡ እርዱን የነየተ ሰው፡ በዙል-ሒጃህ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ ጸጉሩን ወይም ጥፍሩን ቢቀንስ፡ ከፋራው ‹ካሳው› ተውበትና ኢስቲግፋር ብቻ ነው በማለት ዑለሞች ፈትዋ ሰጥተዋል (ኢብኑ ቁዳማህ፡ አል-ሙግኒይ 9/346)፡፡
አላህ ተጠቃሚ ያድርገን።
በአቡ ሃይደር።

The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 27 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
The account of the user that owns this channel has been inactive for the last 5 months. If it remains inactive in the next 7 days, that account will self-destruct and this channel may no longer have an owner.
አንድ ሰው ሰደቃን ሲሰድቅ በንጹሕ ፊትና
ልቦና መስጠት አለበት❤️
# ከምጽዋት አሰጣጥ ሥርዓቶች መካከል አንዱ ምጽዋቱ የቱንም ያህል የበዛ ወይም ያነሰም ቢሆን መጽዋቹ በሚለግስበት ጊዜ በበሻሻ ፊትና በንጹሕ ልቦና መሆን አለበት። ከዚህም በላይ በኢስላም አስተምህሮት ፈገግታ😊 እራሱ ሰደቃ ነውና በልግስና ጊዜ ደግሞ በሚገባ መንጸባረቅ አለበት።

ማብዛትን ታሳቢ አድርገዉ አለመለገስ
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል:-
"ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ:(በረከትን) ከትለግስ።"( አል-ሙደሲር 6)
#አንድ ሙስሊም ሰደቃ ሲሰጥ በአጸፋዉ ከሰዉ የበዛ በረከትን ማግኘትን ፈልጎ መሆን የለበትም።የሚመፀዉተዉ ገንዘብ 💵💵 የቱንም ያህል ቢበዛምየተሰጠዉ የአላህን ዉዴታ ለማግኘት እስከሆነ ድረስ ሌላ አላማ አንግቦ ሰደቃን መስጠት የለበትም። በርግጥ ገንዘቡን ነገ በጣም በሚፈልግበት ጊዜ እፈፊቱ ላይ ያገኘዋል።
# ሆኖም ግን መፅዋቹ ሰደቃዉን ተቀባይነት ይኑረው አይኑረው ባላወቀበት አግባብ ዉስጥ የበዛ ችሮታን አገኛለሁ ብሎ መለገስ የለበትም። ከዚህ ይልቅ ሰደቃው ተቀባይነት እንዲያገኝ በመተናነስና የሆነ ነገርን በመጉደሌ አላህ ባይቀበለኝስ በሚል መስጋት አለበት ። ከዚህም በላይ ሰደቃውን ከሰጠ በኋላ ኢስቲግፋር ማድረግ ወይም የአላህን ማህረት መለመን አለበት።

#ምጽዋቱ ለተገቢዉ ሰዉ መሰጠት አለበት
#ምጽዋት ሲሰጥ ከግምት ውስጥ ሊገቡ ከሚገቡ መስፈርቶች መካከል አንዱ ምጽቱን ለሚገባ እና ይበልጥ ተገቢ ለሆነ ሰው መስጠት ነው። ለምጽዋት ይበልጥ ተገቢ ከሆኑ ሰዎች መካከል ደግሞ የቅርብ ዘመዶችን በግንባር ቀደምነትይጠቀሳሉ።
# ከዚህም በተጨማሪ ለቅርብ ዘመዶች የሚሰጥ ሰደቃ ዝምድናንም ያጠናክራል።
ይህን አስመልክቶ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል:-
"ምፅዋት ለሚስኪኑ ሰደቃ ነው። (ሰደቃዉ) ለዝምድና ባለቤት በሚሆንበት ጊዜ ግን (ፋይዳው) መንታ (ጣምራ) ነወ። (እርሱም)ሰደቃና ዘምድናን ናቸው።"(አህመድና ቲርሚዚ የዘገብት)
#ከዚያም ሰደቃው እንደ ሁኔታው ይበልጥ አሳሳቢ ጉዳይ ያለበትና ሲበዛ ፈላጊ ለሆነ ሰዉ ይሰጣል።

#ሙሲባ (አደጋ)
የሰዉ ልጅ ሲሞት ሁለት ሙሲባ (አደጋ)ይወርድበታል። አንደኛው በፀሐይ በብርድ የሰበሰበው እድሜ ልኩን የደከመበት ገንዘቡንና አንጡራ ሀብቱን ጥሎ ይሄዳል። ከርሱ ጋር የሚቀበር ምንም ነገር የለም በጆሮው ላይ የሚደረገው ጥጥ እና የተገነዘበት ከፈን ሲቀር ። ንብረቱን ትቶ ቀብር ይገባል።
#ሁለተኛው አደጋ (ሙሲባ ) ትቶ በሄደው ገንዘብና ንብረት ላይ አላህ (ሱ.ወ) ፊት በገንዘቡ ይጠየቅበታል። ለዚህም ነው አላህ እንዲህ የሚለዉ
"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንደመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።"(አል-ሙናፊቁን 63:10)
#"ከሰጠኋችሁ ጸጋ ሞት ሳይመጣባችሁ ለግሱ ነው" ያለው ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ዝንጉ የሆነው የሰዉ ልጅ ግን ሞት። በሚመጣበት ጊዜ "ጌታዬ ሆይ! ትንሽ ጊዜ ብትሰጠኝ ሰደቃን አደርግ ነበር ሐጅንም እፈጽም ነበር" ይላል። ከንቱ ምኞት ይመኛል። ግን አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ሲል ጥያቄውን ውድቅ ያደርግበታል:-
"ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም።
አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።"(አል-ሙናፊቁን 63:11)
"ከተወሰነች ጊዜ ምንም መዘግየት የለም እኔም የምትሰሩትን ዉስጠ አዋቂ ነኝ" ይላል። ወንድሞች እህቶቼ! አራዳ ወይም ብልጥ ሰው ማለት ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ መልካም ነገርን ያስቀደመ ሰው ነው።

# በሰደቃችን - የዘነጋናቸው - ሰዎች
#እንደሚታወቀዉ የሰዉ ልጅ ባህሪ ይለያያል። ገሚሱ እያለዉ የሚጠይቅ፣ ከፊሉ ሳይኖረውና ቸግሮት የሚጠይቅ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቢቸግረዉም ቢጠመዉም ቢርበዉም ቢያመውም ለማንም አልናገርም ብሎ አንገቱን ደፋቶ የሚቀመጥ ነው። ስለዚህ አሁን የምናየው የተዘነጉ ሰዎች ባህሪ ነው። እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ባህሪያቸው በጥቂቱ እንደሚከተለው፦
1/ ባላቸዉ ነገር ተብቃቅተውና ካላቸው ጋር ተመሳስለው ይኖራሉ። ቢርባቸውም ቢጠማቸዉም ቢያማቸዉን ማንም ሰው አያውቅባቸዉም።
2/ ሰዉን ቸገረኝ ብለው መጠየቅ የሚያሳፋራቸዉ፣ ቢናገሩም የማይሳካላቸዉ ናቸው።
3/ በመብቃቃታቸው እና በቁጥብነታቸው የተነሳ እንደውም ሰዉ የተሞላላቸው እና የደላቸው ሀብታሞች አድርጎ ይቆጥራቸዋል፤ አላዋቂዉ።
#በጣም የሚገርመዉ ዉስጠ ዐዋቂው ጥበበኛው ጌታ ስለ ባህሪያቸው ነግሮናል። ሰዉን ቢለምኑ እንኳን ችክ የማይሉ፣ ከናካቴው የማይጠይቁ ሰምች በሰደቃ ሊዘነጉ አይገባም። በዚህ አጋጣሚ ሊታወቅ የሚገባዉ መሰረታዊ ነገር ቢኖር የሚለምን ሰዉ ሰው ሁሉ ችግርተኛ እንዳልሆነና የዛኑ ያህል ደግሞ የማይለምን ሰዉ ሁሉ ድሎተኛ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ለዚህም ነው እንደነዚህ ሰዎች ሀብታሞች ቢመስሉም በሰደቃ እንዳይዘነጉ ቁርኣንና ሐዲሥም ያስታወሱን።
ወንድሞቻችን አል-ፋቲሁን ጀምዓም ስለነርሱ ባህሪ በነሺዳ እንዲህ ገልጸውልን፦
ሐያእ አድርጎ የሰው ፊት ፈርቶ
ቤቱ ተቀምጦ "ሚበላው ጠፋቶ
ሞቱን ሚጠብቅ ስንት ሰው አለ
ከሰው ላይሻል በአላህ የ...ማ...ለ
ይሄ ነው ድሀ የረሕማን ባሪያ

#በሰደቃ ማስከፋት ማለት ደግሞ ተለጋሾችን በንግግር ማስከፋት አልያም ደግሞ በሰዎች ፊት ልግስናውን ማዉራቱ ነዉ።
#አላህ (ሱ.ወ) ለምፅዋት ሕግና ሥርዓትን ከደነገገባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ተመጽዋቶችን ከዚህ አይነቱ ዳፋ ለመታደግና ክብራቸዉን ለማስጠበቅ ነዉ። አንደሚታወቀዉ ኢስላማዊዉ ሕግ የሰዉን ልጅ ሰብአዊ ማንነቱንና ተፈጥሯዊ ፍላጎቱን እንጂ ዉጫዊ ማንነቱን እና የሀብት ደረጃዉን ከግምት ዉስጥ አያስገባም። ስለዚህ መጽዋቹ የተመጽዋቹን ክብር መጠበቅ አለበት፤ መክንያቱም የሰዉ ልጅ ከአላህ ዘንድ ደረጃ የሚሰጠዉ በሥራው መልካመሰነትና በልቦናዉ ንጽሕና እንጂ በሌላ አይደለምና። ይህንንም በማሰሸመልከት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ መልካችሁንና የሰዉነት ቅርፃችሁን አይመለከትም፤ ነገር ግን እሱ የሚመለከተዉ ልቦነሠችሁን እና ሰራችሁን ነው።"
# ከላይ የተዘረዘሩ ነጥቦች የሰደቃን ተቀባይነት የሚያረጋግጡና በተቃረሠኒዉ ደግሞ ካለሰተሞሉ ሰደቃነሸ የመመየሠመክኑ ነገረሸቸሰ መሆናቸው መገንዘብ አለብን፤ መክንያቱም ለግሰነ መና እነሰዳንሆን መጠንቀቅ ግድ የሰላልና።

# ስንቶቻችን ነን የመስጠትን ዋጋ ምናቀዉ?
# አብዛኞቻችን መስጠትን የምንረዳበት መንገድ የተሳሳተ ነው። እኛ ሰዎች ሰዉን ለመርዳት እንደ መስፈርት ከምንወስድባቸው ነገሮች በዋናኘት የሚጠቀሰዉ መጀመሪያ አኔ ሳይኖረኝ ሌላውን እንዴት አረዳለው፣ ካለን ነገር ግማሹን እንኳን ለመስጠት እንዴት ይሄ ለሰዉ ይሰጣል ከሰጠውማ በደንብ ነው እያልን በትናንሽ ነገሮች የኸይር ስራ በሮችን እንዘጋለን ። ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ አሁንም ቢሆን በአላህ መንገድ ተጉዘን ኸይር ስራዎችን እንዳንሰራ እያደረገን ነዉ።" አንድ ሰው ሰውን ለመርዳት ሰዉ መሆን በቂ ነው ።" ኸይር ስራን ለመስራት ግዴታ ከምንበላው፣ ከምንለብሰው መትረፋ የለበትም ካለችን ላይ መስጠትን ብንለምድ አንድም እናት የልጇን መራብ እያየች አታለቅስም፣ አንድም አባት ልጆቹ ሚጠይቁትን እንደ አባት ባለሟሟላቱ እያሰበ አያዝንም ነበር። አንድም ሕፃን ጓደኞቹ ትምህርት ቤት ሲሄዱ እቤት ኩጭ ብሎ አይተክዝም ነበር። እስኪ ስንቶቻችን ነን የነዚ ሰዎች ህመም ሚሰማ እንዴትስ ነው ከንደዚህ ዓይነት የሰቀቀን ህይወት የምናወጣቸው ? ብለን አስበን እናቃለን ? ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ። ካለን ነገር አካፍለን የመስጠትን ዋጋ ብናዉቃት ምናለ ምናለ ለኔ ቀርቶብኝ ለወንድሜ በሰጠሁ እስከምንል ድረስ ነው። እኛ አንድ ስንሰጥ አላህ (ሱ.ወ) እጥፍ አርጎ ይመልስልናል ዛሬ ካለን ላይ የሰጠናት ነገር ምን አልባት አንድ ቀን ተመልሳ ትመጣለች ። ከሁሉም ግን የአንድ እናት ምርቃት ነፍስ ታድሳለች ምነው ደጋግሜ እየሰጠዉ በኖሩክ ያሰኛል። ብቻ በመስጠት ውስጥ ሰላም፣ በመስጠት ዉስጥ ደስታ ሌላውና ትልቁ በመስጠት ውስጥ ራሳችንን እናገኛለን ለካ ከኔም የባሰ አለ እንድንል ያረገናል። የቲሞችን ወገናችን እናቶችን ከጉናችሁ ብለን አብረናቸው ልንሆን ይገባል። አላህ የምንሰጠውን ከልባችን የምንሰጥ ያርገን።
✍✍✍ Bint mohammed