La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
La tehzen
🔰 #የእጁጅ_ወመእጁጅ 🔷 ክፍል #አስራ_አንድ 1⃣1⃣ ልጂቱም ፦ አይጁር እወድሀለሁ ነገር ግን ቤተሰቦቼን ትቼ ካንተ ጋር መውጣት አልችልም አለችው፡፡ አይጁርም፦ እነዚህ እኮ ወገኖቻችን አይደሉም፡፡ አታለውናል፤ ሸውደውናል ስለዚህ አታከራክሪኝ ሁሉንም ነገር ከዚህ ስንወጣ አስረዳሻለሁ አሁን ሰዐት የለንም ፈጥነን እንሂድ፡፡አሁን የገፀ ምድር ነዋሪያን የጉድጎዱን መሹለኪያ ሊዘጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው እንሂድ…
#የእጁጅ_ወመእጁጅ

🔷 ክፍል #አስራ_ሁለት 1⃣2⃣

በዚህ ሁኔታ የአመፅን ተስፋ ሰንቀው መውጫ ጉድጎዳቸውን ለብዙ ሺህ አመታትን ከቆፀሩ በኀላ እሱን ትተው ሌላ መውጫ መቆፈር ይጀምራሉ፡፡
ምንም እንኳን ከቀላጭ ነበልባሉ ሽሽት ሌላ ቦታ ለመቆፈር ቢሞክሩም ምድሪቱን መውጫ ጫፍ ሲቃረቡ እንደ በበፊቱ የቀላጭ ናዳ ይዘንብባቸዋል፡፡ በዚን ጊዜ ለቁጥር የሚያዳግቱ ያእጁጃውያን ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ የሞቱትንም በጅምላ በማከማቸት ለምግብነት ያዉሉታል፡፡
ምንም እንኳን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ያእጁጃውያን በየሰከንዱ የቀላጩ ሰለባ ሁነው ቢሞቱም ብዛታቸው ግን እጅግ ከመጨመሩ የተነሳ ሬሳውን መመገብ አላጠግብ ብሏቸው በረሀብ ይተራመሳሉ፡፡
ገደብ ያለፈው ስግብግብነታቸው እና የተመሳሳይ ዘራቸውን ስጋ በልነታቸውን አቅላቸውን አስቶ ያዋልላቸዋል፡፡
በየቀኑ የሚበሏቸውን የሙታኑን አጥንትም ከቤት መስሪያነት በተጨማሪ ለመቆፈሪያነትም በመገልገል የምድሪቱን ቁፋሮ ጠበቅ አድርገው ይዘዉታል፡፡

ይሁን እንጂ ምድርን በቆፈሩ ቁጥር ከሆዱ የሚወጣው ቀላጭ መኖሪያዎቻቸውን ያጥለቀልቅ ይዞታል፡፡
ዙል ቀርነይን አላህ ባገራለት እውቀት ተጠቅሞ ዘመናዊያን ያልሞከሩትን ኦክስጅን በሌለበት እሳትን በማንቀልቀል ለረጅም ዘመናት የቆየ ብልህ ንጉስ ነው፡፡
አዎ!!!አላህ የፈቀደ እለት እንጂ ለነዚህ ያእጁጃውያን መውጫ የላቸውም፡፡ የጅልነት ተስፋቸው ይህን የቀላጭ ክምር ጥሰው ሳይወጡ በፊት የንዴት ዛቻዎችን እንዲደረደሩ አድርጓቸዋል፡፡ አንዳንድ ያእጁጃውያንም ከረሀብ ብዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ያብራክ ክፋይ ልጆቻቸውን አጣጥመው መብላት ይጀምራሉ፡፡ የልጆቻቸውን መብላት ያላጠገባቸው ያእጁጃውያን በዙሪያቸው ያለውን ቋጥኝ እና ተራራዎችንም መብላት ይጀምራሉ፡፡

ዙለል ቀርነይን እና ህዝቦቹ ለዘመናት ያሰቃይዋቸው ህዝቦች ላይ የተሳካ ግድብን በመገደባቸው በደስታ ፈንድንቀዋል፡፡አላህ እስከወሰነው ቀን እስከሚወጡ ድረስ ከያእጁጃውያኑ ተንኮል የተገላገሉ ህዝቦችም ለአላህ ምስጋነሠ ሰላት በመስገድ ደስታቸውን ሙሉ አድርገዋል፡፡
ነገር ግን በመሀላቸው ያለው ዘረ ቅይጥ አይጁር በደስታ እና በሀዘን መካከል ነበር የነበረው
ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት አመታትን ታጅበው ጊዜው ይነጉድ ጀመር፡፡ ምድር ሰላማዊ ሆና ህዝቦችዋን ትውልድን በትውልድ መተካቱን ተያይዟቸዋል፡፡
ትውልድ ትውልድን እየተካ ረዥም አመታት ከተቆጠረ በኀላ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ኑህን ዐለይሂ ሰላም ወደ ምድር ነዋሪያን ላከው፡፡

Part ➊➌
ይቀጥላል......
አላህ የሠጣችሁን የተረጋጉ እና በጤና የተሞላ ቀኖቻችሁን ዉደዱ። የግድ እኮ በሰርፕራይዝ፣ ብር በማግኘት እና በፌሽታ መሞላት የለባቸዉም።
ይህንንስ ማን አይቶብኝ አትሉም እንዴ።
ዛሬ የገባው ወር ዙልቂዕዳ ይሠኛል። ከተከበሩ አራት የዓመቱ ወራቶች ዉስጥ አንዱ ነው። ቀጥሎ ያለው የተከበረው የሐጅ ወር ነው። ሐጅ ያሰባችሁ አላህ ለታላቁ ምኞታችሁ ያብቃችሁ። አርደልሐረምን ዘይሩልን። ለመዲናው ሙስጦፋ ሰልሙልን። እኛም በአላህ ፈቃድ አንድ ቀን እንደምንመጣ ንገሩልን።
ሶልሏሁ ዐለይሂ ወሰለም።
➲ለሰዎች ሁልጊዜ የደስታ ሰበብ እንጂ ለአንድም ሰው የሀዘን ምንጭ አትሁን ማስደሰት እንኳን ባትችል ማንንም ለመጉዳት አታስብ !!!
በሰው ቀልብ እየተጫወቱ አላህ ጌታ ሆይ ቀልቤን አረጋጋልኝ ብለው ይለምናሉ።
አይታሰብም።
አላህ ሥራችሁን አይመዘግብም መሰላችሁ እንዴ!
እንባ ከዐይናችን እንደሚወድቀው ሁሉ፣ የሆነ ጊዜ ላይ አንዳንድ ሰዎችም ከዐይናችን ዱብ ዱብ ይላሉ። ወሏሁል ሙስተዓን።
አንዱ እኮ ነው ጫት እየቃመ ተርዚናውን የሌለ ቆልሎት ሲጋራ ለኩሶ ሊያጨስ ሲል የሆነች የገጠር ሴትዮ ምን ብትለው ጥሩ ነው ። 😉
.
አይ ልጀ አትድከም እሱን ሁሉ ጎመን እቺን እሳት ታበስለዋለች ብለህ ነው።
ሕይወትን ወደ ዕድሜያችሁ ጨምሩ እንጂ ዕድሜን ወደ ሕይወታችሁ አትጨምሩ። ዕድሜ ከዉብ ሕይወታችሁ ከመስረቁ በፊት ሕይወትን ከዕድሜያችሁ ስረቁ።
ገብቷችኋል አይደል ...።

ጁምዓ ሙባረክ!
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭


አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84 አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል።
ሁላችንም ይመለከታል ።
ኡበይዱላህ ኢብን ኡመር አንድ ጊዜ
እንዲህ ብለው ነበር “ጀምዐ ሰላት
በተለይ ኢሻና ሱብሂ አምልጦኝ
አያውቅም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ቤቴ
እንግዳ መጣና ከርሱ ቆይቼ ኢሻ ሶላት
አመለጠኝ፡፡ ከቤት ወጣሁ፤ ጀምዐ
ሶላት ለማግኘት ብዬ በስራ ከተማ ላይ
የሚገኙ መስጂዶች በሙሉ ዞርኩ፤
ሁሉም መስጂዶች ተሰግዶ አልቋል፡፡
ሰዎቹ ባጠቃላይ ሰግደው
ወደቤታቸው ሄደዋል፡፡ እኔም ወደ
ቤቴ ተመለስኩና ማሰብ ጀመርኩ፤
ለራሴ እንዲህ አልኩኝ ‘በሀዲስ
በግለሰብ ከሚሰገደው ሰላት በጀምዐ
ሚሰገደው በ 27 ደረጃ ይበልጣል
ተብሎዋል፤ ስለዚህ 27 ጊዜ ኢሻን
ሰላት ብሰግደው በጀምዐ ከሰገዱት ጋር
እኩል ይሆናል’ ብዬ በማሰብ
ኢሻን ሰላት በቤቴ 27 ጊዜ ሰገድኩና
ተኛሁ፡፡ በዛው ቀን ለሊት በህልሜ
ከፈረሰኞች ጋር ፈረስ ውድድር
ስንወዳደር አየሁ፤ ፈረሴ ጠንካራ
ብትሆንም
እንኳ ሌሎቹ ላይ ልደርስባቸው
አልቻልኩም፤ ወደ ዃላ ቀረሁ፡፡ ፈረሴ
ትደርስባቸው ዘንድ እደበድባት
ጀመርኩ፤ ነገር ግን ምንም ለውጥ
ልታመጣልኝ አልቻለችም፡፡ አንደኛው
ፈረሰኛ ወደኔ በመዞር “ፈረስህን
አታሰቃያት እኛ ላይ ልትደርስብን
አትችልም” አለኝ፡፡ እኔም “ለምን?”
ብዬ
ስጠይቀው “ምክንያቱም እኛ ኢሻን
ሶላት በጀምዐ ነው የሰገድነው፤ አንተ
ግን ብቻህን ሰገድከው” በማለት
መለሰልኝ፡፡ ከዚህ ትልቅ ትምህርት
ወሰድኩ፤ በጣምም አዘንኩ፡፡” ይለናል
ኡበይዱላህ፡፡
ሱብሃነላህ!!
እኛ ስንት ሶላት ይሆን ጀምዐ
ያመለጠን?? ስንቶቻችን ይሆን በዚህ
ምክንያት ተፀፅተን የምናውቅ??
“አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84
አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል”
መባሉን ምናስታውስ ስንቶቻችን
ነን??
ዛሬውኑ እንነይት “ኢንሻ አላህ ካሁን
በሗላ አንድም ሶላት ጀምዐ
አያመልጠኝም” ብለን…ለኔም
ለናንተም ሰደቀቱል ጃሪያ ይሆናልና
መልክቱን
ሼር እናድርገው —
ያረብ በሰላት ላይ ጥንካሬና ብርታት ስጠን ከሰይጣን ተንኮል ጠብቀን።
ዋ!! ፈራሁልሽ ነፍሴ 😭😭😭
ውበት የሚደምቀው በአለባበስ ብቻ
ሳይሆን በአስተሳሰብ ጭምር ነው
ውስጣዊ ስሜቶች አይፃፍም፣
ቢፃፍ እንኳ ፍፃሜ የላቸውም ።
የአንዳንድ ነገሮች መሰባበር
ሲሰማህ ትንሽ ራቅ በል።
ንግግር ስሜትህን የመግለጽ አቅም ሲያጥረው ትንሽ ዝም በል።
#ሁሌም_ቢሆን ስለ መልክህ ሳይሆን ስለ መልካምነትህ ተጨነቅ...ከሰው ጋር ሊያዘልቅህ የሚችለው መልክህ ሳይሆን መልካምነትህ ነው
ለምሰራው ጥፋት አታላክ በሰው ላይ፣
ለራስህ ፡ እራስህ አትሁን አታላይ!

ከህሊና ችሎት ማምለጫ ሳይኖረህ
ጣትህን አቀስር በመጥፎ አመልህ!!

@MotivateEthiopia
👉ሁሌም ሐሳቦችህ ልክ ነህ እስከሚያስብሉህ አትጠብቅ፤ እንደዛ ከሆነ ተቀባይነት እስክታገኝ ድረስ ጊዜ ልትፈጅ ነው ማለት ነው! ግን ላንተ ልክ ሆኖ ከተሰማህ ከመሞከር አትቦዝን!!!
👉እኔ ማን እንደሆንክ ታውቃለህ! ይቺ ቃል ክብርን ከምታስጠብቀው በላይ ክብርን የምታስንድ ናት!…መከበር በስራ እና እንደነበርክበት ቦታ እንዳሳለፍከው ጊዜ ፤ እንዲሁም በመልካም ተግባራትህ እንጂ በስም ለመከበር አትሞክር! ማንም ማንንም አያቅምና!!!
👉ከአበቦች ሁሉ በላይ በቁመቷ ለየት ያለች አበባ ፈተናዋ ብዙ ነው፤ እንዴት? በንቦች ለመከበብ ፤ በሌሎች ነፍሳት ለመኖሪያነት በመመረጥ ፤ እንዲሁም በሰዎች በመቆረጥና የራሷ ቁምት እጅግ ከፍ ሲል መቀንጠስ ሚባሉት ነገሮች ይከሰቱባታል!!! ሰውም ከሚኖርበት ማህበረሰብ ጋር መስማማት ካልቻለ እና ካፈነገጠ መኖር ለርሱ ከባድ ይሆንበታል፤ ምንም እንኳ ሰው በሔደበት መንገድ ሳያምኑበት ተከትሎ መሔድ ባይገባም፤ ቢቻል ሐሳብን መግለፅና ጠቀሜታውን አጉልቶ ማሳየት ይገባል፤ ግን የነርሱን እያየን በመልካሙ መንገድ አካሔዳችን ሊመስላቸው ይገባል! ሚኖረው ከሰው ጋር ነውና!!!

@MotivateEthiopia
👉መቸኮል እና ነገርን አለማጣራት መደምደሚያቸው ጥፋት ነው፤ ሁለቱም በስሜት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ያስከትላሉ ያ ደግሞ ኋላ ሚያስቆጩ ሁኔታ ውስጥ ይከተናል! ውሳኔአችን ከምን የመነጨ እንደሆነ ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል!!!
👉ገደብ፡ ይሕ ምን ያህል መሔድ እንዳለብን የሚወስነን ነው፤ ገደብ አስፈላጊ ነገር ነው፤ የምንጠይቀው ፤ የምናወራው ፤ የምናስበው ፤ የምንመኘው ፤ የምንፈጽመው ነገር ሁሉ ገደብ ሊኖረው ይገባል፤ ካልሆነ ኑሮአችን ቅጥ ያጣ ፤ ስብዕናችን የተናቀ ፤ ድርጊታችን የጭካኔ መሆኑ የማይቀር ነው!!!

@MotivateEthiopia
🤔 እንዲ ባደርግ...እንዲ ቢሆን...እያልክ ስታሰላስል ጊዜው ይነጉዳል። የሚሻለው እስኪ ልሞክረው ብሎ ቶሎ መሳሳትና እያስተካከሉ መሄድ ነው። ከወደክ አይቀር ቶሎ ውደቅ፤ ግን ስትወድቅ ወደፊት ውደቅ። የ 42 ኪሎ ሜትር ማራቶን በአንድ እርምጃ ነው የሚጀመረው...ፍጥነትህንና ስትራቴጂህን ለመቆጣጠርም እዛው እየሮጥክ ሁኔታዎችን እያየህ አይሻልም? አልጋ ውስጥ ሆነህ እንዲ ባደርግ ከዛ ይሄን ባደርግ ከምትል፤ መጀመሪያ ስራውን ጀምረው ከዛ እያየህ ትጨምርበታለህ። ዳይ ወደ ስራ!

@MotivateEthiopia
መካ
=
ሀሳብ ሰንቄያለሁ ከዚያ ከበረሃ
አንጀት ከሚበላው ከሚያሰኘው ውሃ
የነሱመያ ጣር የነቢላል “አሐድ”
ያብከነክነኛል በትዝታ ንዳድ
በነብይ ዱዐ የሞላሽ በረካ
ሰላማዊት ሀገር ቅድስቲቷ መካ!
-
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 2/2006)
< < ምንድን ነው ብሄሩ? > >

(

አባቱ ወሎ ነው መካነ ሠላም
እናቱ ከጎጃም መርጦ ለማርያም
ጃንተከል ያደገች ጎንደሬ ናት ሚስቱ
የወለዱት ፍሬ ደቡብ ሆነ እድገቱ
ከለምለሟ ምድር አግብቶ ሲዳማ
ልጃቸው ለስራ ሄደ ወደ አዳማ
ካ'ሠላዋ ቆንጆ ተጋብተው ወለዱ
የነሱ ልጆችም በየአቅጣጫው ሄዱ
ትግራይ ሱማሌ አፋር ሄዱና ጋምቤላ
ተጋብተው ወለዱ አብሮ የሚበላ
አዲስ አበቤዎች ድሬ ላይ ፏ! ሲሉ
አፖስቶ ነው አቦ! ሀረሪ ባህሉ
ወሎ ከቤኒሻንጉል ልጅ ወልደው ካፈሩ
እስኪ የነሱ ልጅ ምንድን ነው ብሄሩ??
የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን»