La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
«ያ አላህ! ባልሰራበት እንኳ ወደ በጎ ነገር ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ።»
የልብ መድሀኒቶች

➤ ቁርአን እያስተነተኑ ማንበብ
➤ ሆድን አለመሙላት
➤የሌሊት ሶላት መቆም
➤ፈጅር ከመድረሱ በፊት ወደ አላህ መተናነስ፣ ምህረትን መጠየቅና ዱአ ማድረግ
➤ አላህን የሚፈሩ ሰዎችን መወዳጀት

[الأذكار النووية1/ 107]
La tehzen
حجابك أيتها المسلمة #ሙስሊሟ_ሴት_ሆይ_ሒጃብሽን_አደራ! '' ክፍል''2⬇️ الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا `` ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ ፤ ለእናንተም…
حجابك أيتها المسلمة
#ሙስሊሟ_ሴት_ሆይ_ሒጃብሽን_አደራ!

'' ክፍል''3⬇️

#አሏህ_በተከበረው_ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡-
(قال تعالى) إِن تَجْتَنِبُوا كَبَائِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًا كَرِيمًا
ከእርሱ ከተከለከላችሁት ታላላቆቹን (ሃጢያቶች) ብትርቁ (ትናንሾቹን)
ሃጢያቶቻችሁን ከእናንተ እናብሳለን፡፡ የተከበረንም ስፍራ (ገነትን)
እናገባችኋለን፡፡” (አን ኒሳእ/ ዓያ 31)

( قال تعالى) قَدْ أَفْلَحَ مَن زَكَّاهَا
(ከኀጢኣት) ያጠራት ሰው ፍላጎቱን በእርግጥ አገኘ፡፡ (አሽ ሸምስ/ ዓያ 9)

(قال تعالى) وَقَدْ خَابَ مَن دَسَّاهَا
(በኀጢኣት) የሸፈናትም ሰው በእውነት አፈረ፡፡ (አሽ ሸምስ/ ዓያ 10)

3'' የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ይህንን አሏህ የሰጠሽን ክብር ለመንጠቅና አንቺ
ውርደት ላይ የምትወድቂበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚንቀሳቀሱ የኢስላም ጠላቶች
መኖራቸውን እዎቂ፡፡ ከእነዚህ ግንባር ቀደም ጠላቶች መካከል የአሏህና የዲኑ
ጠላት የሆነው ሸይጣን ነው፡፡
አሏህ በተከበረው
#ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡-

(قال تعالى) إِنَّ الشَّيْطَانَ لَكُمْ عَدُوٌّ فَاتَّخِذُوهُ عَدُوًّا ۚ إِنَّمَا يَدْعُو حِزْبَهُ لِيَكُونُوا مِنْ أَصْحَابِ السَّعِيرِ
“ሸይጣን ለናንተ ጠላት ነው፡፡ ስለዚህ ጠላት አድርጋችሁ ያዙት፡፡ ተከታዮቹን
የሚጠራው ከእሳት ጓዶች እንዲሆኑ ብቻ ነው፡፡”( ፋጢር/ ዓያ 6)

የአሏህ ጠላቶች ዋና ግብ ሙስሊሟ ሴት በዱንያና በአኼራ ነጃ የምትወጣበትን ስርዓት
ለቃ የእነርሱን የተበላሸ ስርዓት እንድትከተል በመሆኑ ማንኛውንም ጥንቃቄ ማድረግ
ይኖርባታል፡፡
4'' የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ወደመልካም አቅጣጫ መመራት በአሏህ መሆኑን ፤
አሏህ ያላቀው እርሱ ብቻ የተላቀ ፤ አሏህ ያዋረደው ደግሞ እርሱ ብቻ የተዋረደ
መሆኑን ልታረጋግጭ ይገባል፡፡
አሏህ በተከበረው
#ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡-

(قال تعالى) وَمَن يُهِنِ اللَّهُ فَمَا لَهُ مِن مُّكْرِمٍ ۚ إِنَّ اللَّهَ يَفْعَلُ مَا يَشَاءُ
አሏህ የሚያዋርደውም ሰው ለእርሱ ምንም አክባሪ የለውም፡፡ አላህ የሻውን
ይሰራልና፡፡”(ሓጅ 18)

ስለዚህ ከአላህ ጋር ያለሽን ግንኙነት ማጥበቅና ማጠናከር ፤ ወደአሏህ መጠጋት ፤
በዲኑና እና በዱዓ ላይ ጽናት ልታደርጊ ይገባሻል፡፡
#ከዱዓዎች_ሁሉ_ትልቁ፡-
اللهم أصلح لي ديني الذي هو عصمة أمري وأصلح لي دنياي التي فيها معاشي وأصلح لي آخرتي التي فيها معادي واجعل الحياة زيادة لي في كل خير واجعل الموت راحة لي من كل شر (رواه مسلم)
አላህ ሆይ! የነገሬ ሁሉ መጠበቂያ የሆነውን ሐይማኖቴን አብጅልኝ ፤ መኖሪያየ
የሆነችውን ምድረ ዓለም አብጅልኝ ፤ መመለሻየ የሆነችውን የመጨረሻ ዓለም አብጅልኝ
፤ ህይዎቴን ለበጎ ስራ መጨመሪያ አድርግልኝ ፤ ሞቴንም ለእኔ እረፍት አድርግልኝ፡፡”
(ሙስሊም፡ 2720)

5'' የተከበርሽ እህቴ ሆይ! በአሏህ ውዴታ ክብርና ልቅና የምትጎናጸፊበትን መንገድ
ትኩረት ልትሰጭ ይገባል፡፡

#አሏህ_በተከበረው_ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል

(قال تعالى) إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ اللَّهِ أَتْقَاكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው።(አል ሑጁራት/ዓያ 13)

وفي صحيح البخار ي عن أبي هريرة رضي الله عنه قال قيل للنبي صلى الله عليه وسلم من أكرم الناس؟ قال أكرمهم أتقاهم''

ቡኻሪ በዘገቡት አቡ ሁረይራ ረዲየሏሁ ዓንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-
ረሡል صلى الله عليه وسلم” እጅግ በጣም የተከበረው ሰው ማን ነው?” የሚል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡
“(ከአሏህ ዘንድ) በጣም የተከበረው እጅግ በጣም አላህን ፈሪያቸው ነው፡፡” በማለት
ምላሽ ሰጡ፡፡ (ቡኻሪ 3374)

ከዚህ ውጭ በሆነ መንገድ ልቅናን የፈለገ ሊዳሰስና ሊጨበጥ በማይችል ምናብ
ውስጥ ነው ያለው፡፡

6'' የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ሴቶችን አስመልክቶም የመጣው የሸሪዓ ህግ ልክ
እንደሌላው የዲኑ ህግ ክፍተትና ጉድለት የሌለው የማይበድል መሆኑን በደንብ
ጠንቅቀሽ እዎቂ፡፡ ይህ የሸሪዓ ህግ ባሮችን ሁሉ ተመልካች ፤ ጥበበኛ እና ከዳኞች
ሁሉ በላጭ ከሆነው አሏህ የተዘጋጀ ህግ ነው፡፡
ቁርኣን በሴቶች ላይ በደል ፈጽሟል በማለት ወሰን መተላለፍ ትልቁ ሐጢያት
መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡ እንዲህ አይነት አነጋገር የሚናገሩ ሰዎች ጌታቸውን ተገቢ የሆነ
ክብር አላከበሩቱም፡፡ አሏህን ይፍሩ ፤ የአላህን ህግጋት ክብር ይስጡ፡፡

ኢንሻ አሏህ






إعداد:
الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر
#የኪታቡ_አዘጋጅ_ሸይኽ_ዓብድረዛቅ_ቢን_ዓብድል_ሙሕሲን_አል_በድር
ኢብኑ ዓብዱል'በር ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ:-
"አስተዋይ የሆነ ሙዕሚን ከመልካም ስራ ምንንም አሳንሶ ሊመለከት አይገባውም።
ምናልባትም በትንሿ ስራ አላህ ሊምረው ይችላልና።"
ምንጭ:📚التمهيد (١٢/٢٢ )
🌿🌿እውነትን ለመደበቅ ብለክ የትም አለም 🌍ወሥደህ ብትቀበረዉ እራሡን አባዝቶ ይበቅላል እመነኝ
በወንድ ልጅ በደል ምክኒያት
የሴት ልጅ አይን ካነባች/ካለቀሰች
"በሚራመደው እርምጃ ልክ
መላኢኮች ይረግሙታል!
🗣 [ዐሊይ ኢብኑ አቡ ጣሊብ]
የለይለተል ቀድር ዱዓ!
~~~
በነዚህ በረመዷን የመጨረሻዎቹ 10 ለሊቶች ላይ ለይለተል ቀድር ስለሚከጀል ይህን ነብዩ ﷺ ለአዒሻ ረዲየሏሁዓንሃ ያስተማሯትን ዱዓ ማድረግን እናብዛ ፦

{ اللَّهُمَّ إِنَّكَ عَفُوٌّ تُحِبُّ الْعَفْوَ فَاعْفُ عَنِّى }
ትርጉሙም ፡ አላህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህና ይቅር በለኝ።
የታል ጓደኛህ ትናንት አብሮህ የነበረና አሁን የተጓዘ ያ ብዙ ገንዘብና ሰፊ ህልም የነበረው የታል ሁሉም ከስራው ጋር ከቀብር ውስጥ አልገባምንእ
የታል ያ ባማረ ህንፃ የኖረ ወደ ቀብር አልወረደምንእ ከስካርህ ንቃ!
ወደ ጉድጓድ መግባትህንም አስታውስ ከቤተሰብህም መለየትን አስታውስ ወላሂ ዛሬ የሬሳ ሳጥን የተሸከመ ቀን ይመጣል ሰወች እሱንም በትከሻቸው ተሸክመውት የሚሄዱበት!
ለዚያራ መቃብር የገባ አንድ ቀን እሱም ላይወጣ ይገባል
ዛሬ ወደ ቤቱ የተመለሰ ቀን ይመጣል የማይመለስበት
አስታውሱ ወንድሞቼ እርግጠኛም ሁኑ ሞት የማትቀር እውነታ ነች!።

የዱንያ ሂወት አታታላችሁ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው አላህን መገናኜት የፈለገ የአላህ ቀጠሮ እውነት ነው ይዘጋጅ።

እንመለስ ወደ አላህ አላህ ይባርካችሁ



Share share share
ብዙዎቹ የቁርአንን ትርጉም እንኳን አያውቁም፣ ቀኑን በፆም ይውላሉ፣ ምሽት ሳይደክማቸው ረጅም ሰዓት ይቆማሉ፣ ለኃያሉ አምላካቸ ያጎነብሳሉ፣ ለፈጣሪያቸው በግንባራቸው መሬት ላይ ይደፋሉ። ለረጅሙ የኢማሙ ዱዓእ ከልብ ሆነው ኣሚን ይላሉ።
ሁኔታቸው ሁሉ ያሳዝናል፣ ልብ ይነካል። ካንተ ፈላጊ ድሆች መሆናቸዉን አምነው፣ እዝነትህን ከጅለው፣ ምህረትህን አስበው ቤትህ መጥተዋልና እዘንላቸው፣ ማራቸው።

ረመዷን 20
➲ኢእቲካፍ
➱➱➱➱➱

➧የኢቲካፍ ትርጉሙና ሸሪዓዊ ድንጋጌው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➧ኢእቲካፍ_ማለት አምልኮን አስቦ መስጂድ ውስጥ መቆየት ሲሆን ሸሪዓዊ ብይኑ ሱና ነው፡፡ አላህ እንዲህ ብሏል፦

▪️وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَ‌ٰهِۦمَ وَإِسْمَـٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَـٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ  البقرة: (١٢٥)

“ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን ለዘዋሪዎቹና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን” አል-በቀራህ 125

▪️وَلَا تُبَـٰشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَـٰكِفُونَ فِى ٱلْمَسَـٰجِدِ البقرة: ١٨٧

“እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ አትገናኙዋቸው”፡፡ አል-በቀራህ 187

➲አዒሻ ረዲየሏህ ዐንሀ እንዳለችው “ነብዩ(ﷺ) የረመዳንን የመጨረሻዎች አስር ቀናት እስኪሞቱ ድረስ ኢእቲካፍ ያደርጉ ነበር፡፡”

➲የኢእቲካፍ መስፈርቶች
➛➛➛➛➛➛➛➛➛➛

➧ኢእቲካፍ ፈፃሚው ሙስሊም መሆን፣ የመለየት እድሜ የደረሰና አእምሮው ጤናማ መሆን አለበት፡፡ በአንፃሩ ከሃዲ የአእምሮ ህመምተኛ ወይም የመለየት እድሜ ያልደረሰ ህፃን ኢእቲካፋቸው ትርጉም አይኖረውም፡፡ ለኢእቲካፍ አቅመ አዳም (ሄዋን) መድረስና ወንድ መሆን መስፈርቶቹ አይደሉም፡፡ የመለያ እድሜ (ሰባት አመት) የደረሰ እንዲሁም ሴት ልጅ ኢእቲካፍ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

➻ኒያ፦ ነቢዩ (ﷺ) “ስራዎች የሚለኩት በኒያ ነው” ብለዋል::

➲መስጂድ ውስጥ መሆን አለበት፦“እናንተም በመስጊዶች ተቀማጮች ስትኾኑ” አል-በቀራህ 187

➠ነቢዩም (ﷺ) ኢእቲካፍ የሚያደርጉት መስጂድ ውስጥ ብቻ እንጂ ቤት ውስጥ ወይም ሌላ ቦታ ኢእቲካፍ አድርገው አያውቁም፡፡

➤የኢእቲካፍ ወቅት ተወዳጅ ተግባሮቹና ኢእቲካፍ ላይ ላለ ሰው የሚፈቀዱ ነገሮች

➲የኢእቲካፍ ወቅት፦ኢእቲካፍ ሊባል የሚችለው አንድ ግለሰብ መስጂድ ውስጥ ለተወሰነ ወቅት ሲቆይ እንጂ ምንም ካልቆየ ኢእቲካፍ አይሰኝም፡፡ ትንሹ የኢእቲካፍ መጠንን በተመለከተ በዑለማዎች መካከል የተለያዩ ሃሳቦች ቢኖሩም ነገር ግን የተሻለው አቋም ገደብ የለውም የሚለው ነው፡፡

ይሁንና ከአንድ ቀን ባያንስ የተሻለ ነው ምክንያቱም ነቢዩም (ﷺ) ሆኑ ከሰሃቦች አንድም ግለሰብ ከአንድ ቀን ያነሰ ወቅት ኢእቲካፍ እንዳደረጉ አልተዘገበም፡፡

ኢእቲካፍ ከሚደረግባቸው ጊዜያት በላጩ የመጨረሻዎቹ የረመዳን አስር ቀናት ናቸው፡፡ ይህን በተመለከተ አዒሻ ረድየሏህ አንሀ እንዳለችው“ነብዩ(ﷺ) እስኪሞቱ ድረስ የረመዳን የመጨረሻ አስር ቀኖችን ኢእቲካፍ አድርገዋል፡፡”

➧የረመዳን አስር ቀኖችን ኢእቲካፍ ማድረግ የፈለገ የሃያ አንደኛውን ቀን ንጋት ሱብሂ ሰላት ኢእቲካፍ ያሰበበት መስጂድ ውስጥ በመስገድ ይጀምርና የመጨረሻው የረመዳን ቀን መግሪብ ከሰገደ በኋላ ያጠናቅቃል፡፡
ለይለቱል ቀድር
Sadat
➡️ ለይለቱል_ቀድርን እንደት እናሰልፈው በሚል ርዕስ አጭር ትምህርት

《اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني》
አሏህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል [አቡ መርየም] ሀፊዘሁሏህ

https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
La tehzen
🔰 #የእጁጅ_ወመእጁጅ 🔷 ክፍል #ሁለት 2⃣ ይህን ጊዜ ትላልቅ የያእጁጆች የጎሳ መሪዎች ሰብሰብ በማለት ከምድር ታች ብርሀን በማይኖርበት ሰዎች በማይደርሱበት የራሳቸውን ከተማ ለመመስረት ተስማሙ፡፡ በመጨረሻም ምድርን እየሰነጠቁ በመግባት እና ከተማዎቻቸውን በመቆርቆር የተደራጀ የጦር ሰራዊትንም አቋቁመው አፄዎችንም ሾሙ። እነዚህ የያእጁጅ ነገዶችም ከመሬት ውስጥ ያለውን የፅልመት…
🔰🔰 #የእጁጅ_ወመእጁጅ

ክፍል #ሶስት 3⃣

አስራአንዱ ዘረ ቅይጦችም አይጁርን በማስቀደም ለረጅም አመታት በከርሰ ምድር ታጉረው የነበሩት ፍጥረታት ለመጀመሪያ ጊዜ ከከርሰ ምድር ወደ ገፀ ምድር ብቅ አሉ ።
ልክ ከምድር ወጥተው የመጀመሪያ እይታቸውን ወደ ፍጥረተ አለሙ ሲያደርጉ ሁሉም በግርምት ተዋጡ። አዲስአለም...፤ንፁህ አየር የምትሞቅ ፀሀይ ወ.ዘ.ተ ይህ ሁሉ በግርምት ማዕበል ውስጥ አቁሞ አዋለላቸው።መልኩ ምክንያቱም ምድር ውስጥ ተወልደው ምድር ውስጥ ያደጉ ፍጥረታት ናቸው እና ይህ አለም ለነሱ ድንቅ እና አዲስ ነው።
በማያውቁት አለም ላይ ድንገት መከሰታቸው በአግራሞት መስጧቸው እርስ በርስ ማውራታቸውን ትተው ዙሪያቸውን ግራ በመጋባት ይቃኛሉ። ከዚያም ወደ ሰዎች መንደር ጉዞ ጀመሩ። በጉዞዋቸው ላይም ሰዎችን ሲመለከቱ በንቀት እና እጅግ በጥላቻ በተሞላ መልኩ ይመለከቷቸዋል።
ምክንያቱም እነዚህ ዘረ ቅይጥ ወጣቶቹ ከቅድመ አያቶቻቸው አንስቶ እየሰሙ ያደጉት የሰው ዘር ባጠቃላይ ለነሱ ጠላቶች እንደሆኑ ነውእንጂ በእናቶቻቸው ሰው መሆናቸውን አያውቁም ነበር።
ይህን ሁኔታቸውን የተመለከተው ብልሁ አይጁርም አብረውት ላሉት ዘረ ቅይጥ ወጣቶች፦"ወገኖቼ ሆይ እነዚህ በላይኛው ምድር የሚኖሩት የሰው ዘሮች ለኛ እጅግ ጠላቶቻችን መሆናቸውን ታውቃላችሁ።
ማንነታችንን ካወቁ ተራ በተራ ነው የሚቆራርጡን ፤ስለዚህም ማንነታችሁ ላይ እጅግ ተጠንቀቁ። በውስጣችሁ ያለውን ጥላቻ ግልፅ አታሳይዋቸው ። እኛ ላይ ሀላፊነት የጣሉ እና የኛን መልስ በጉጉት የሚጠብቁ ህዝቦች አሉና በብልሀት እንንቀሳቀስ"በማለት ምክር ሰጣቸው።
አይጁር በትኩረት ወደ ሰው ልጆች አለባበስ እና ቋንቋ ሲመለከት ካደገበት ቋንቋ እና የአለባበስ ወግ እጅግ ይለያያል'ና፤ እራሱ እና አብረውት ያሉ ወጣቶችን እንደ ዱዳ ሁነዉ ወደ ህዝቡ ለመቀላቀል ወሰነ።
ይህን ሀሳብ ለጓደኞቹ አቅርቦ በማስማማት በምን መልኩ ወደ ከተማ ገብተው ከሰው ዘሮች መቀላቀል እንዳለባቸው ሲወያዩ ድንገት በአቅራቢያ ከሚገኘው ተራራ በኩል አዋራ እያስነሳ ወደነሱ የሚቀርብ እንግዳ ነገረ ተመለከቱ።
ይሁን እንጂ የሰው ልጆች ነበሩና ወደ ዘረ-ቅይጦች መጠጋት ጀመሩ።ይህን ግዜ አይጁር እና ግብራበሮች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ወደቁ። የሰው ዘሮች ሚስጥራቸውን አውቀውባቸው ሊያጠፏቸው እንደሚመጡም በመገመት ክስተቱትን በትዕግስት መከታተል ጀመሩ።ፈረሰኞቹ(የሰው ዘሮችም) በፍጥነት ወደ ዘረ ቅይጦቹ ወጣቶች በመድረስ እነማን ናችሁ ፡፡፡፡ከየትነው ወደየት ነው ወ.ዘ..ተ አሏቸው
ይሁን እንጂ የፈረሰኞቹ ንግግር ለዘረ ቅይጦቹ ምንም ማይገባቸው ቋንቋ ነውና ዝምታን መልስ አደረጉላቸው። ፈረሰኞቹ በተደጋጋሚ ጥያቄውን ቢያቀርቡላቸውም ያእጁጃውያን ሊመልሱላቸው ባለመቻላቸው ከፈረሰኞቹ ዋናቸው የሆነው ያእጁጃውያኑ እንዲገደሉ አዘዘ። (ያእጁጃውያን መሆናቸውን ማንም አያውቅም) ይህን ጊዜ ከፈረሰኞቹ አንደኛው ለአዛዡ አለቃቸው "ከምንገላቸው ወደ ባሪያ ገበያ አውጥተን እንሽጣቸው" በማለት ሹክ አለው።
አዛዡም በጓደኛው ሀሳብ ተስማምቶ ወደ ባሪያ ገበያ ያእጁጃዉያኑን ይዘው ጉዞ ጀመሩ። ወደ ገበያው እንደ ደረሱም የፈረሰኞቹ አዛዥም የባሪያ ነጋዴዎችን በማስጠራት ለሽያጭ ያዘጋጃቸውን (ዘረ ቅይጥ) ወጣቶች አቀረበላቸው።
የባሪያ ነጋዴውም በግርምት ወጣቶቹን እየተመለከተ እና በተክለ ሰውነታቸው እየተገረመ፦ ከየት ነው ያመጣሀቸው? የየት
ሀገር ነዋሪ ናቸው በማለት አዛዡን ፈረሰኛ ጠየቀው፡፡
የፈረሰኞቹ አዛዥም በቁጣ" ከየትም ይምጡ ከየት አንተ አይመለከትህም፡፡ ትገዛለህ ወይስ ለሌላ ልሽጣቸው አለው።
የባሪያ ነጋዴውም በፈረሰኛው ሀሳብ ተስማምቶ የዘረ ቅይጥ ወጣቶቹን ሂሳብ ከፍሎ ወደ ባሪያዎቹ አቀላቀላቸው ፡፡በመቀጠልም ይህ የባሪያ ነጋዴ ዘረ ቅይጦቹን ለገበያ አውጥቶ ገዢ እየተጣራ ሳለ ከነዚህ ዘረ ቅይጦች አንደኛውን ነጥሎ የሚገዛ ሸማችመጣና ሂሳቡን ከፍሎ ነጥሎ ሊወስድ ሲል............

Part ➍
ይቀጥላል......

💎----------------------🌹-----------------💎
La tehzen
حجابك أيتها المسلمة #ሙስሊሟ_ሴት_ሆይ_ሒጃብሽን_አደራ! '' ክፍል''3⬇️ #አሏህ_በተከበረው_ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡- (قال تعالى) إِن تَجْتَنِبُوا كَبَائِرَ مَا تُنْهَوْنَ عَنْهُ نُكَفِّرْ عَنكُمْ سَيِّئَاتِكُمْ وَنُدْخِلْكُم مُّدْخَلًا كَرِيمًا ከእርሱ…
حجابك أيتها المسلمة
#ሙስሊሟ_ሴት_ሆይ_ሒጃብሽን_አደራ!

'' ክፍል''4⬇️


#አላህ_በተከበረው_ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡-

ذَٰلِكَ وَمَن يُعَظِّمْ شَعَائِرَ اللَّهِ فَإِنَّهَا مِن تَقْوَى الْقُلُوبِ
“(ነገሩ) ይህ ነው፡፡ የአላህንም የሃይማኖት ምልክቶች የሚያከብር ሰው እርሷ
ከልቦች የሆነች ጥንቃቄ ናት፡፡”( ሐጅ፡32)

እነዚህ ከዚህ በላይ የጠቀስናቸው ህግጋቶች በተግባር ሊተገበሩና ሁልጊዜም
ልናስታውሳቸው ፤ ቀልባችን እንዲለዝብና የአላህን ህግጋት እንድንቀበል የሚያደርጉ
በአጠቃላይ ደረታችንን የሚያሰፉ፣ የሚያረጋጉ፣ ወደአላህ ህግጋት ፊታችንን
እንድናዞርና በዱንያም ይሁን በአኼራ እድለኛ እንድንሆን የሚያግዙ መሰረታዊ ታላቅና
ጠንካራ ህግጋቶች እና ደንቦች ናቸው፡፡
የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ዲነል ኢስላም ሴቶች ከወንድ ጋር አይቀላቀሉ ፣ ሂጃብ ይልበሱ
በማለት ትዕዛዝ ያስተላለፈው የሴቶችን ክብር ከባለጌዎች ለመከላከል ነው፡፡ ሴት
በኢስላም ከማንኛውም ቆሻሻ የጠራች እንቁ ነች፡፡ በዲኑ ህግና ስርዓት ለመስራት ዕድሉ
የገጠመው ምን ትልቅ እድል አጋጠመው! ሁኔታውን ምን አላቀው! በረካውን ምን
ከፍ አደረገው!
የአላህን ህግ መከተል ከተለያዩ ጥቅሞች ያግዳል ፤ መጥፎ ነገር ያስከትላል ብሎ
መናገር በአላህ ላይ ያለእውቀት መናገር ነው የሚሆነው፡፡ ከሓጢያቶች ሁሉ ታላቁ
ደግሞ በአላህ ላይ ያለእውቀት መናገር ነው ፡፡

#አሏህ_በተከበረው_ቁርዓን_የሚከተለውን_ተናግሯል

وَأَن تَقُولُوا عَلَى اللَّهِ مَا لَا تَعْلَمُون
“በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ብቻ ነው በላቸው፡፡” (አል አዕራፍ፡ 33)

የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ሴቶችን በተመለከተ ከአላህ ኪታብ ባነበብሽ ጊዜ ደረትሽን
አስፍተሸ በእርጋታና በጥሞና በማስተንተን አንብቢው፡፡ ምክንያቱም የምታነቢው ንግግር
አንችን የፈጠረሽ ያስገኘሽ መስሚያ እና መመልከቻ ማለትም አምስቱን የስሜት
ህዋሳት የሰጠሽ ጥንክርናን እና ብርታትን ያደረገልሽ ጌታ ንግግር ነው፡፡ የአላህ ንግግር
እና የፍጡር ንግግር ልዩነቱ ልክ በእርሱ እና በፍጡሮች መካከል ያለውን ልዩነት ማለት
ነው፡፡
ከአላህ በመጣው መመሪያ ላይ አደራ በልቦናሽ ውስጥ ያለመቀበል ስሜት
እንዳታሳድሪ!

#አላህ_በተከበረው_ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡-
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا فِي أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
“በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ
ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና
ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም ፤ (ምእመን አይሆኑም)፡፡
(አን ኒሳእ፡65)

በነብዩ صلى الله عليه وسلمሐዲሶች መስራት ማለት በቁርኣን መስራት ማለት ነው፡፡
#አላህ_በተከበረው_ቁርኣን_የሚከተለውን_ተናግሯል፡-
وَمَا آتَاكُمُ الرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَاكُمْ عَنْهُ فَانتَهُوا
“መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከእርሱም
የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡”(አል ሐሽር፡7)

ቡኻሪ በዘገቡት (ዓብደሏህ ብን መስዑድ አሏህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

#ወቃሪ_ተወቃሪ_የቅንድብን_ጸጉር_የሚያቀጥኑ_ጥርስ_የሚፈነጩ_ለውበት_የአላህን_ፍጥረት_ቀያሪ_የሆኑትን_አላህ_ረግሟል_ከበኒ_አሰድ_የሆነች_ስሟ_ኡሙ_የእቁብ_የምትባ_ሴት_ዓብደላህ_ብን_መስዑድ_አሏህ_ስራቸው_ይውደድላቸውና_የተናገረው_ንግግር_ደርሷት_ወደርሱ_እየገሰገሰች_መጣች፡፡_ይህን ይህን ተግባር የሚፈጽምን ሰው የተራገምክ መሆኑ
ደርሶኝ ነው ወደአንተ የመጣሁት” አለችው፡፡ “ረሡል صلى الله عليه وسلم የረገሙትን በአላህ
ኪታብ የሚገኝ የሆነውን የማልረግመው ምን አለኝ?!” በማለት ምላሽ ሰጣት፡፡
#በሁለቱ_ሰሌዳ_መካከል_ያለውን_ቁርኣን_ቀርቻለሁ_አንተ_የምትለውን_በፍጹም _አላገኘሁትም_አለች፡፡ “
,,ብትቀሪው ኖሮ በእርግጥ ታገኝው ነበር አላትና፡፡
#መልክተኛውም_የሰጣችሁን_ማንኛውንም_ነገር_ያዙት_ከእርሱም_የከለከላችሁን_ነገር_ተከልከሉ፡፡” (አል ሐሽር፡7) አላት፡፡ “ቀርቸዋለሁ” አለች ፤ “ታዲያ
ከእንዲህ አይነት ተግባር እኮ ከልክሏል!” አላት፡፡( ቡኻሪ፡ 4886)

#ስለዚህ_በትክክለኛ_ሐዲሶች_መስራት_በቁርኣን_መስራት_ማለት_ነው፡፡ ምክንያቱም
ከነብዩ صلى الله عليه وسلم የመጣውን መያዝ እንዳለብን አላህ በቁርኣን አዟል፡፡
አላህ ለሙእሚን እናቶች የሚከተለውን ተናግሯል፡

ኢንሻ አሏህ






إعداد:
الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر
#የኪታቡ_አዘጋጅ_ሸይኽ_ዓብድረዛቅ_ቢን_ዓብድል_ሙሕሲን_አል_በድር


ኢንሻ አሏህ




وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ

[ ሱረቱ አል-አዕራፍ - 179 ]
ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤
عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️ صلى الله عليه وسلم❤️❤️❤️
ውዶቼ ጁመአኮ ነው
ሰለዋት እናብዛ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

በቁርአን መንፈሳችንን እናድስ نجدد روحنا بالقرآن
ቁርኣን የመንፈሳችን የአካላችን እና የሕይወታችን መመሪያ እና ዘመን የማይሽረው መድሐኒት ነው
『የዛ ውብ ነብይ ኡመት መባሉ በራሱ ትልቅ ልቅናን ያጎናፅፋል』

ሶሉ ዓለል ሀቢብ ያ አህባቢ

صلى الله عليه وسلم
መድረክ አግኝታችሁ ስለ ዒልም የምትናገሩ ሰዎች ... ከሚያዳምጧችሁ መካከል በዒልም የሚበልጧችሁ ትሁቶችና ተቂዮች ሊኖሩ ይችላሉና በጥንቃቄና በጥራት ተናገሩ።
የማሰገድ ዕድሉን ያገኛችሁ ወጣቶች ... ከሚከተሏችሁ መካከል ያልታወቁ ሓፊዞችና ቃሪኦች ሊኖሩ ይችላሉና ቁርአንን ዝም ብላችሁ አትሸክሽኩ።
በሁሉም ነገር ዉስጥ አላህን የመፍራቱ ነገር እንዳለ ሆኖ።
ያለ ቁርአን
ሕይወት ባዶ ናት።
ወላሂ ባዶ።
ተማሩት
አጣጥሙት።
የጀመርኩት የእጁጅ ወመዕጁጅና
ሙስሊማ ሴት ሆይ ሂጃብሽን አደራ
የሚለውን ፅሁፍ ከረመዳን በኃላ የምንጨርስ ይሆናል አፍወን ያ ጀማ
➲በነዚህ ተወዳጅ በሆኑት አስርት ቀናቶች ይህቺን ዱአ እናብዛ!

《اللهم إنك عفو تحب العفو فاعف عني》
{አሏህ ሆይ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅርታንም ትወዳለህ ይቅር በለኝ!!}