La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
የኔ ጁመአ😍

በጠዋቱ ቤቱ ፏ ብሏል፤ ቁርኣኑ ከመስጂዱ ያስተጋባል።
ለካ ቀኑ ጁምአ ነው። አለማስተዋል ነው እንጂ ቀኑ ልዩ መሆኑን ጠዋት መልእክት ገብቶልኝ ነበር። የቁርኣኑ ድምጽ ከቀኑ ልዩነት ጋር ተጣምሮ ቀኔን አፈካው።

ሀጃችን የሚወጣበት 🙏
ሀሳባችን የሚሳካበት 😋
ምርጥ ቀን ያድርግልን😊

ጁመአዬ ሁሌም አዲስ ነው😍
የጁምዐ ሱናዎች
👉መታጠብ
👉ሽቶ መቀባት
👉ጥርስን መፋቅ
👉ጥሩ ልብስ መልበስ
👉ሱረቱል ከህፍን መቅራት
👉 በጊዜ ወደ መስጅድ መሄድ
👉ዱዐ እና ሰለዋት ማብዛነት
ያማረ የደመቀ በኢባዳ የተዋበ ጁምዓ ይሁንልን ውዶቼ😍
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዚክርዚክር_ዚክር🌹🌹🌹
#ስንቱን እያወን አነዚህን ከባድ ዚክሮች በየቀኑ በየሌሊቱ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ልብ በሉ ለሰዓታት አላልኩም ሰዓታትም አይፈጇ ማለት ከከበደን ልባችን እውነትም በጠና ታሟል!!
የኛ ስንፍና እንጂ ጀነት ለመግባትኮ ቀላል ነበር......!
ጁሙዓ ቀን ሰላዋት ማብዛትን በተመለከተ

ከአውስ ኢብኑ አውስ እንደተላለፈው ነብዩ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:– " ከቀናት ሁሉ በላጩ የጁሙዓ እለት ነው፤ በዚህ እለት በእኔ ላይ ሰላት ማውረድን አብዙ " ብለዋል። ( ሀዲሱን አቡ–ዳውድ፣ ነሳኢ እና ኢብኑ–ማጃህ ዘግበውታል አልባኒ ሰሂህ ነው ብለዋል )
" ባንች እናት እና በኔ በእናቴ መካከል ያለዉን ልዮነት ታውቂያለሽ ግን?" አላት ለሚስቱ።

"እህ ምንድነው እሱ?" አለችው አዲስ ሀሳብ መስሏት።
ፈገግ እያለ
"እናቴ ለዚህች ዓለም ሕይወት አበቃችኝ፣ ያንች እናት ደግሞ ሕይወትን ራሷን ሰጠችኝ።" አላት።

"ጌጦቻችን" ሆይ! አላህ የረመዷን ድካማችሁን አነባብሮ ይክፈል።
🔸ኢብኑል ጀውዚይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ:-

"በአሏህ ይሁንብኝ ለመቃብር ሰዎች ተመኙ ቢባሉ ኑሮ ከረመዳን አንዲትን ቀን በተመኙ ነበር" አት-ተብሲራህ [2/78]

ያ አላህ ከሚጠቀሙበት አድርገን !
ፆመኛን በማስፈጠር ላይ እንሽቀዳደም ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል :-

«ፆመኛን ያስፈጠረ የጿሚውን ምንዳ ያገኛል፣ ይህም የጿሚው ምንዳ ሳይቀነስ ነው!»
አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነዉና አትፍሩ ሰፋ አድርጋችሁ ለምኑት።
"ሮጠ ድረሱበት"

ረመዳኑ ሄደ ሳይርቅ ድረሱበት፣
ምንም ሳናስበው አለፈ አስራ5፣

እንጠቀምበት ሇላ ከመፀፀት፣
የወራቶች በላጭ የምርጦቹ አይነት፣

በኢባዳ መበርታት በፆምም በሰላት፣
ገባ ሳንል ገና አለፉ ሳምንንታት፣

ወሩ የተውበት ነው ፈጥኖ ነው መቶበት፣
ወሩ የራህመት ነው ለድሀ እንራራበት፣

ማግኘት ከፈለግን የከሪሙን እዝነት፣
ረሒሙ አድርገን ከሚጠቀሙበት።


https://t.me/httpsLatahzen
◾️የንያ ቦታው ምላስ ሳይሆን ቀልብ ነው
☑️☑️☑️☑️☑️☑️

🌐ኢብኑ ኡሰይሚን "አላህ ይዘንለት" እንዲህ ብሏል።

➡️ ንያ ቦታዋ ቀልብ ነው። በሁሉ መልካም ስራዎች ላይ ንያ በምላስ ቦታ የላትም። ለዚህም ነው ሶላት ሊሰግድ፣ ሊፃም፣ ሀጅ ሊፈፅም፣ ውዱእ ሊያደርግና ሌላም ማንኛውም ስራ ሊሰራ ፈልጎ ንያውን በምላሱ የሚናገር የሆነ ሰው የዲን አካል ያልሆነ ነገር የተናገረ ሙብተዲእ ይሆናል።

📚شرح رياض الصالحين "13/1"

♦️በነገራችን ላይ ኢማሙ ሻፍእይ የንያ ቦታ ምላስ ነው ብለዋል የሚባለው ነገር ውሸት ነው። እንዲህ ብለው አያውቁም። እንደውም አራቱም የመዝሀብ ባለቤቶች የንያ ቦታ ቀልብ ነው የሚሉ ናቸው።

♦️ሰፊነቱ ነጃ በተሰኘው ትንሹ የፊቅህ ኪታብ ላይም "ومحلها قلب" ንያ ቦታው ቀልብ ነው የሚለውም ስህተት ነው።

♦️የሚገርመው አንድ ሰው በምላሱ ነወይቱ እያለ ተናግሮ ነገር ግን በቀልቡ ካልነየተ በምላስ መናገሩ እንደንያ ስለማይቆጠር ስራው ውድቅ ይሆናል።

♦️ስለዚህ ሶላትም ይሁን ረፀዷን ፃም ላይ ስራውን በቀልባችን ማሰብ እንጂ ድምፅ ከፍ ተደርጎ የሚነየት ወይም የተለየ የሚባል ዚክር ከመልእክተኛው ስላልተገኘ ከዚህ አዲስ ፈጠራ እራሳችንን ልናቅብ ይገባል።

♦️ብዙ ሰዎች ንያ አስተምሩኝ እስቲ አስነይቱኝ ምን ልበል ንገሩኝ እያለ ይቸገራል። ሶላት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት እጃቸው አንስተው ነወይቱ ፈርድ ሶላት አርበአ ረከአ…… ይላሉ። የረመዷን ሌሊት ላይ ነወይት ፈርድ ረመዷን ኣዳአን… በማለት ሲቸገሩ ይታያል። ይህ ሁሉ ከንቱ ልፋት ነው። አላህ ምን እንደምትሰራ ጮክ ብለህ ልትነገረው የማይሻ በቀልብህ የምታስበው ሁሉ አዋቂ ነው።

https://t.me/httpsLatahzen
ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንድህ አሉ:
" የሰው ልጅ (አማኝ) የኸይር በር በተከፈተለት ቁጥር በኸይር/መልካም ነገር ሊቻኮልና ሊፈጥን ይገባዋል"
ለበደለን፣ ላስከፋን፣ ለሰደበን፣ ላስቸገረን፣ ለናቀን፣ ላማን፣ ላነወረን፣ ድንበር ላለፈብን፣ ሳንናገረው ለተናገረን፣ ሥማችንን ላጠፋ፣ በመጥፎ ለጠረጠረን፣ ዋጋችንን ላራከሰ፣ ...
'ሐስቢየሏሁ ወኒዕመልወኪል' ከማለት በላይ ምን እንላለን !።

ሰባሐል ኸይር ቆንጆዎቼ
ሶደቃ ልክ እደውጊየ ነው ፈሪ ሲርገፈገፍበት ጀግና ይፀናበታል።

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተየሚያህ رحمه الله
እየዉልሽ ኡኽታ ዉዷ ሆይ يَاغَاَلِيِةَ
ስለተገላለጥሽ አይደለም ቆንጆ ምትሆኚዉ
ጀሊሉ ሲፈጥርሽ ቆንጆ ነሽ
!!

ሴት መሆን በራሱ ዉበት ነዉ
የሸይጣን ቻሌንጅ ይቅርብሽ
ወደ ጀሀነም እሳት ነዉ ሚያመራሽ
!!

በሂጃብሽ በኒቃብሽ ዉብ ንግስት ነሽ
ድብቅ ስትር በይ የዛንኔ ነዉ ምታጓጊዉ !

➤የኔ እንቁ💎
ስንቅ አዘጋጅተሀል
~~

በቅርብ ጠሩሀል ስንቅ አዘጋጅተሀል?
ለቀጣዩ አለም ምንስ ሸምተሀል?፣

ቀኑ አይታወቅም ድንገት ይጠሩሀል፣
ለድንገት ቀጠሮ ነቅተሀል ፈዘሀል?
ፈዘህ ካሳለፍከው ሗላ ይቆጭሀል፣

በዘፈን ሙዚቃ ጆሮ አደንቁረሀል⁉️
በፊልም ድራማ ልብን አድርቀሀል⁉️ ከአጅነቢ ጋራ ኢኽቲላጥ ፈጥረሀል⁉️
ነፍስህን ተሳሰብ እሱ ያዋጣሀል፣
=====================

አንቺስ ውዷ እህቴ ስንቅሽን ይዘሻል?
ወይስ ተክዘሻል በዱንያ ፈዘሻል?

በሰላት በመስነፍ ሰው ሁሉ አውቆሻል⁉️
ሜካፕ እና ሽቶ ራስሽ ላይ ደፍተሻል⁉️
በሀራሙ መንገድ ዝሙት ላይ ወድቀሻል⁉️
በአለባበስሽስ ስስ ጠባብ ለብሰሻል⁉️
ከቂርዓት ርቀሽ ቻት ላይ ተጥደሻል⁉️
ከነዚህ ችግሮች ከፊል ታይቶብሻል⁉️
እንግዲያውስ ቶብች ቀኑ ቀርቦብሻል፣
ወንድሜም ተመለስ ዲኑ ይበጅሀል፣

ሞትንም አስታውሰው ኢማንህ ይሞላል፣
አልቅሰህ ለምነው ገፋር ይምርሀል፣

ሁኔታው ይከብዳል ከልብ ያስጨንቃል፣
ዝም ብሎ ሲታሰብ የሞትስ ይለያል፣

አንተን ሳያማክር መለይካው ይመጣል፣
ባለህበት ሳለህ ሩህንም ያወጣል፣
የዛኔ ነው ስራህ አንተን ያባሽራል።

እጅግ ተጠንቅቆ ነፍስህን ያወጣል፣
ወደጌታዋ ዘንድ ፈጥኖ ይወስዳታል፣

መልካም ብስራትን ለሷ ይነግሯታል፣
የዚህ ተቃራኒ ራሷን የምትበድል፣

በዱንያ ሳለች ዘካን ምትከለክል፣
በሙሉ ጊዜዋን ለአላህ ማታውል፣

ሀራምን ለመስራት የማታወላውል፣
የዝች አይነቷን ነፍስን መለይካው ያወጣል፣

በጭንቀት ፍርሀት ያወናብዳታል፣
ልክ እንደ መንጠቆ ይፈለቅቃታል፣

ያመጥፎ ስራዋ መጥቶ ያጅባታል፣
ጥቁር ተመስሎ ያስደነግጣታል፣

ቀብር ይጠብባታል ስቃይ ይበረታል፣
በዱንያ ለአፍታ መመለስ ይመኛል፣

"ያለይተኒ" ብሎ ራሱንም ይወቅሳል፣
ታዳ ምን ያደርግል ጊዜ ረፍዶባታል።

ይሄ ሳይመጣብህ ወይኔ ጉዴ ሳትል፣
በዲንህ ቀጥበል ለተውሂድም ታገል፣

ስሜትና ሸይጣን ወዲያ አርቀህ ጣል፣
በጌታህም ታገዝ በማያፈርሰው ቃል፣
ያረብ አታድርገን ጀሀነም ከሚጣል።


https://t.me/httpsLatahzen
وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ
#ወደ_ አላህ ከ_ጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው።
ስንፆም መግሪብ ይደርሳል እናፈጥራለን ብለን እንታገሳለን።
ችግር ሲገጥመንም ለፆም ጊዜ እንደምንታገሰው እንታገስ።
ያልፋል፣ ያሰብነው ይደርሳል ቢኢዝኒላህ።
ጌታዬ ሆይ ለባሮችህ ሁሉ ከመልካም ሲሳይህ ለግስ።
لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ ۖ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا ۚ أَنتَ مَوْلَانَا فَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ

[ አል-በቀራህ - 286 ]
አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡ ከእኛም ይቅርታ አድርግ ለእኛም ምሕረት አድርግ፡፡ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፡፡ በከሓዲዎች ሕዝቦች ላይም እርዳን፡፡
➪ኢማሙ አህመድ ተጠየቁ፡

ጥያቄ፦ መልካም ስነምግባር ማለት ምን ማለት ነው ?
መልስ፦ መልካም ስነምግባር ማለት ከሰወች የሚደርስብህን አዛ መቻል ማለት ነው።
☞︎︎︎ ሹዕቡል ኢማን (7726)
☞ከጓደኛ ምርጡ ማነው? ተብለው ሲጠየቁ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት መለሱ "አላህን እንድትፈራ የሚያስታውስህ መልካም ሲሰራ ስታየው ተግባሩን የምትከተል ለችግርህ
ስትጠራው የሚደርስልህ ነው አሉ
አላህ ጥሩ ጥሩ ጓደኞችን ያብዛልን።